ᴛʜᴏᴜɢʜs.ᴘʟᴄ🔥
رفتن به کانال در Telegram
...Quotes from different societies. Also👉https://t.me/LilOriIII
نمایش بیشتر686
مشترکین
-124 ساعت
-47 روز
-830 روز
آرشیو پست ها
686
Repost from የ እዝራ ሀሳቦች ✍🏻
ዋጋ የሚከፍሉልን ሰው በጠፋ ግዜ ከጎናችን የሚሆኑ እውነት ለራሳቸው ሁሉም ነገር ሙሉ ሁኖ አይደለም ሰው በሚያስፈልግ ግዜ አብሽርር ብለው ከጎናችንን የሚሆኑት ሁሉ የራሳቸው የሆነ ቁስል የሌለባቸውም አይደሉም" የሚሰጥምም ነገር ሁሉ ከእኛ የበለጠ ያላቸው ሰውም አይደሉም መስጠት ገንዘብ ወይም ንብረት ብቻ መካፈል አይደለም አንዳንድ ሰዎች የቀራቸውን ትዕግሥት ያካፍሉናል በልባቸው የቀረውን ተስፋ ይሰጡናል ከራሳቸው ረጅም ጭንቀት ሀሳብ ሀዘን በፊት የመጨረሻዋን ፈገግታ እንኳ ከእኛ ጋር ይካፈላሉ " ስለዚህ ለሚያሳዩን ፍቅርና ደግነት አክብሮት እንስጥ ' እነዚህ ሰዎች የእውነትም ውድ ናቸው ። እግዚአብሔር ይጠብቃቸው በእውነት በጣም ውድ ናቸው
686
Repost from ᴛʜᴏᴜɢʜs.ᴘʟᴄ🔥
when i hear your voice,and the whole world fades, i’ll always remember us this way.
686
Repost from የ እዝራ ሀሳቦች ✍🏻
ስትከሳ ስትንገላታ ስታጣ ስትነጣ ባትሰርቅም ሌባ ይሉሀል ባልዋልክበት ያውሉሀል ... ማጣትንማ በደንብ ተጠየፈው ብሮ ... ያጣን ሰው አትጥላ እንጅ ማጣትህ ከሁሉም በላይ ልትጠላው የሚገባ መሆን አለበት።
686
Repost from የ እዝራ ሀሳቦች ✍🏻
ጦር ሜዳውን ለራሱ ለባለስልጣናቱ እና ስልጣኑን ለሚፈልጉ እንድሁም ለራሳቸው ዘመድ አዝማዶች አስረክቦ ሌላው በሰላም መኖር የሚችልበት ሁኔታ ቢፈጠር እንዴት ደስ ባለኝ ነበር ።
ለማንኛውም ደህና እደሩ የነገ ሰው ይበለን✌️🏾
686
Repost from የ እዝራ ሀሳቦች ✍🏻
በሰዎች ለመወደድ ትግል ውስጥ አልገባም፤ ለሰዎች ጥሩ እና ቀና የሚያስብ ማንነት እንዲኖረኝ ግን ዋጋ እከፍላለሁ!!
ምክንያቱም ለራሴ ሰላም እና እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝበት ልብ እንዲኖረኝ ስል!!! 🙌
686
Repost from የ እዝራ ሀሳቦች ✍🏻
ለምወድሽ❤️እኔ አንቺን ስወድሽ አንድ ቀን ሺ ሆነ፣ ሀዘኔ ጠፋና ደስታዬ ሰፈነ፣ እኔ አንቺን ሰወድሽ ቀናች ጨረቃይቱ፣ ተዘባረቀባት ቀንና ሌሊቱ፣ እኔ አንቺን ሰወድሽ ፀሀይት ደበነች፣ ቅናት አንገብግቧት በንዴት በገነች፣ እኔ አንቺን ሰወድሽ በጋና ክረምቱ ለፀብ ተጋበዙ፣ አመዳም ተራሮች አብረቅርቀው ወዙ፣ ብቻ እታለሜ እኔ አንቺን ስወድሽ፣ ተፈጥሮ ይናጣል ምን ብዬ ልንገርሽ፡፡ @ezreal_1
686
Repost from የ እዝራ ሀሳቦች ✍🏻
በአንድ ቅዳሜ ምሽት በካርኒቫል ውስጥ የሚጨፍሩትን በግማሽ እርቃናቸውን ያሉ ልጃገረዶችን በሴሰኝነት የሚመለከቱ ሰዎችን አያለሁ፣ በእሁድ ጠዋት ደግሞ በካርኒቫሉ ሌላኛው ጫፍ ለድንኳን ወንጌላውያን ኦርጋን ስጫወት፣ እነዚህኑ ሰዎች ከሚስቶቻቸው እና ከልጆቻቸው ጋር በቤተክርስቲያን ወንበሮች ላይ ተቀምጠው እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን ይቅር እንዲላቸው እና ከስጋዊ ፍላጎት እንዲያነጻቸው ሲጠይቁ አያለሁ። እና በሚቀጥለው ቅዳሜ ምሽት ወደ ካርኒቫሉ ወይም ወደ ሌላ የሥጋዊ ደስታ ቦታ ይመለሳሉ።
በዚያን ጊዜ የክርስቲያን ቤተክርስቲያን በግብዝነት ላይ እንደምታድግ፣ እና የሰው ልጅ ሥጋዊ ተፈጥሮም ማሸነፉ እንደማይቀር አወቅሁ!@ezreal_1
686
Repost from የህይወት ቅኔ🥀
ለምን መኖር ደከመህ? ለምን ህይወት ድግግሞሽ ሆነብህ? ለምን ራስህን ለማጥፋት ወሰንክ? በስደት ስላለህ? በህመም ስለሆንክ? ያሰብከው ስላልተሳካ? ያመንከው ስለከዳህ? አሞታለሁ ብለህ ለምን ታስባለህ? አበቦች ሲፈኩ እንደሚደርቁ ያውቃሉ፡፡ ግን እደርቃለሁ ብለው ሳይፈኩ አይቀሩም፡፡ ሰውም ሟች ነው ግን ሟች ነኝ ብሎ መተው የለበትም፡፡ ሁሉም ሰው በየመስኩ ያብብ፡፡ ወዳጄ እፅፍልሀለው አንተ አላስፈልግም ትላለህ እንጂ ያላንተ የማይሆኑ ብዙ ነገር አለ
ያላንተ የማይሞቅ ቤት አለ፡፡
ያላንተ የማይሳካ ህልም አለ፡፡
ያላንተ የማያምር ጨዋታ አለ፡፡
ያላንተ የማይደምቅ ቤት አለ፡፡
ይህቺ አለም ትልቅ ዳመራ ናት አንተ በዳመራው ስር ያለህ አንድ ችቦ ነህ አንተ ስትጠፋ የዳመራው ብርሀን ይቀንሳል፡፡ የቻልከውን ያህል ብራ አንተ ከነገሮች በላይ ነህ፡፡ በነገሮች አትረበሽ፡፡ እደግመዋለሁ ህይወት ልክ እንደ ክራር ጨዋታ ነው፡፡ አጨዋወቱን ያወቀ ጥሩ ሙዚቃ ይሰማል ያላወቀ ደግሞ ዝብርቅርቅ ጩኸቷን ለመስማት ይገደዳል፡፡ አሁንም እልሀለው ህይወት በደመነፍስ አትሄድም ስልቷን እወቀው፡
፡ በህይወትህ ትላንት ያለፈውን መጥፎ ህይወትህን መቀየር ማስተካከል መሰረዝ አትችልም፡፡ የምትችለው አምኖ መቀበልና ለተሻለ ነገ መስራት ነው፡፡ "መቀየር የማንችለውን ነገር መቀበል ማለት ተስፋ መቁረጥ ወይም መሸነፍ ማለት ሳይሆን አቅማችንን የምንችለው ነገር ላይ ማዋል ማለት ነው::"
በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን አቅምህን የምትችለው ነገር ላይ አውለው፡፡ ሳትኖር ለመሞት አትቸኩል ....😊
686
Repost from ጲንኤል
#ተስፋ የሚያስቆርጡ ነገሮች ወደ ሂወትህ ሲመጡ እነዚህን ሶስት ነገሮች አስብ
1. እግዚአብሔር ካንተ ጋር እንደነበር
2. እግዚአብሔር ከአንተ ጋር እንዳለ
3. ነገም ሁሌም እግዚአብሔር ካንተ ጋር እንደሚኖር❤️
686
Repost from የህይወት ቅኔ🥀
.....በህይወት ጉዞአችን ውስጥ ስንብት የሚባል ነገር ትልቁ የነፍስ ፈተና ነው። አብዛኞቻችን ቻው ማለት ወይም መሰናበት እንደ ቀላል ጉዳይ ይታያል። ለአንዳንዶቻችን ግን ስንብት ቀላል የቃላት መለዋወጫ ሳይሆን በልብ ውስጥ የነበረን አንድ ውብ ገጽ በግድ የምንዘጋበት ያንኑ ቅርርብ በአንድ ቃል የምናቋርጥበት እጅግ ከባድ ስሜት ነው። ቻው ብለን....
ለሰዎች... መሰናበት ሲያቅተን እንደ መጥፎ ባህሪ ወይም እንደ ቸልተኝነት ሊቆጠር ይችላል። ነገር ግን ይህ ስሜት የሚመጣው ከመውደድ ነው። አንድን ሰው መሰናበት ማለት ያ ሰው በህይወታችን የነበረውን ድርሻ በአንድ ጊዜ የምንገታበት የጋራ ጊዜያችንን ወደ ትዝታነት የምንቀይርበት ሂደት ነው። መለያየትን ለመቀበል የሚከብደን ያንን የፍቅር ወይም የጓደኝነት ትስስር ማቋረጥ ስለማንፈልግ ነው።
ስንብትን መሸሽ ማለት የልብን ባዶነት ለመቋቋም መሞከር ነው። ብዙ ጊዜ ዝም ብሎ መሄድ ወይም ሳይሰናበቱ መለየት ያንን የስንበት ሰላምታ ለመናገር የሚጠይቀውን የልብ መፍረስ ላለመጋፈጥ ነው። ያንን ቃል ከተናገሩና ከተቃቀፉ በኋላ የሚመጣው ርቀት ስንብትን ለሚጠሉት ሰዎች እጅግ ይከብዳል።
አንዳንዴ ስንብት ሳይደረግ የሚደረግ ጉዞ ለራስ የምናደርገው ጥበቃ ነው። መለያየትን ለመቀበል መቅረት የሚችሉትን የልብ ትስስር ይዞ ለመቀጠል ነው። ቻው ማለት ከባድ ነው ምክንያቱም ልብ ሁሌም አብሮ መኖርን እንጂ መለያየትን ስላልተማረ።
ራስ ወዳድነት ሊመስል ይችላል ግን ደግሞ ጠለቅ ብሎ ላየው ከልብ ላለመውጣት የሚደረግ ትግል ነው።
ሁሌም አብሮ ያለ አይሰነባበትም😍
እስራኤል ሰይፉ (ቦዔዝ)
686
Repost from የህይወት ቅኔ🥀
ሙሉ ደቂቃ ቁጭ ብዬ ኳስ ያየሁበትን ቀን እምብዛም አላስታውስም። ነገር ግን በተለይ ሃይስኩል እያለሁ በአጋጣሚ ሳልፍ አልያም ደግሞ መሄጃ ከሌለኝ ሻይ እየጠጣሁ ሀይላይት አይ እንደነበር ግን በደምብ ትዝ ይለኛል። ልጅ እያለሁ በራሱ ታላላቆቼ ብስራት ኤፍ ኤም ከፍተው ሲሰሙ ግን እማልክደው የልጅነት ሀቅ ነው። መሰለ መንግስቱ ያወጣው ዘፈን ዛሬም ጆሮዬ ላይ አለ።
''እግርኳስን በሬድዮ ተመልከቱ።
መሰ...............ለ መንግስቱ!..'' የሚል ድምጽ....
በዚህ መሃል ግን አርሰናል ከሌሎች ክለቦች በተሻለ ለእኔ ጎልቶ እንዲታይ የሆነበትን ምክንያት ግን እነሆ....
ልጅ እያለሁ ከማልረሳቸው ኵነቶች አንዱ በታላላቅ ወንድሞቼ የሚደረገው የአርሰናል እና ማንችስተር ጨዋታ ነው። ምን DSTV ገብቼ የእውነተኛውን አርሰናል እና ማንችስተር ጨዋታ ባላይም፣ እውነተኞቹን ተጫዋቾች በመልክ ባላውቃቸውም (በስም ሲጠሩ ስለምሰማ) አርሰናል ልቤ እንዲገባ ግን የግድ DSTV መግባት አልተጠበቀብኝም ነበር።
...ሁሌም ቅዳሜ ቅዳሜ አዳሪ ትምህርት ቤቱ ውስጥ ጨዋታ አይጠፋም ነበር። ብዙውን ሳምንት ጨዋታው የሚደረገው በአርሰናል እና በማንችስተር ሲሆን (አንዳንዴ ቆላ እና ደጋ፣ ድፍን ምስር ክፍት ምስር....እየተባለ ቢከፈልም አብዛኛው እና ምቹው ግን የአርሰናልና ማንችስተር ክፍፍል ነበር)
... አሸናፊው ቡድን ታድያ ሳምንቱ የሱ ነው። ቀጣይ ሳምንት መጥቶ ተሸናፊው ቡድን መልሶ አሸንፎ ድሉን እስካላስመለሰ ድረስ ሳምንቷን ተሸማቆ ነው የሚጨርሰው።
ሁሌም የምበሳጭበት ግን አንድ ነገር ነበር። ትንሹ ስለነበርኩ ለትዕዛዝ ተመችቼ ይሁን አልያም ፊትለፊት ተገኝቼ ባላውቅም ተጫዋቾቹ በሙሉ በተራ ተራ ውሀ እንዳመጣላቸው የሚልኩኝ ነገር...
...እንዳያመልጠኝ እልና እየፈጠንኩ ሄጄ በያዝኳት ማንቆርቆርያ የምትመስል የፕላስቲክ ጆግ (ትልቱ እኔን ይበልጣል😀) ውሀዬን ይዤ ልክ ሜዳ ስደርስ የላከኝ ልጅ ኳሷን ይዟል እየተጫወተ...
ሌሎች ተጫዋቾች ይቀሙኝና ይጠጡታል... አልከለክል መቼስ ኩርኩሙስ🤛
የላከኝ ልጅ ሲመጣ ውሀው አልቋል። ''
ለምን አባክ ሰጠሀቸው?...'' ይለኝና መልሶ ይልከኛል...
...እንዲህ ውሀ እያመላለስኩ የጓጓሁለትን ኳስ ሳላየው ያልቃል.. ሳምንቱን ደግሞ እቅድ አወጣለሁ።
"...ሜዳው አጠገብ ያለው ትልቁ ዛፍ ጫፍ ላይ እወጣለሁ መቼስ ከዛ አያስወርዱኝም እንደውም በደምብ ይታየኛል ወደታች..'' ብዬ አቅድና ልክ ሳምንቱ ሲመጣ እወጣለሁ ዛፍ ላይ።
ልክ ኳሱ ተጀምሮ ትንሽ እንዳየሁ አንዱ ተጫዋች ይጣራል
"...እስራኤል አይቼሀለሁ ና ውረድ...'' እየተነጫነጭኩ እወርዳለሁ።
''..ኤጭ ምንድነው? ሌሎቹ ልጆች አያመጡም እንዴ? ወይስ እኔ ማመጣው ውሀ ይጣፍጣቸዋል?...'' ንጭንጭ እያልኩ ወደ ስራ..
ሙሉ ኳስ የማየው ከስንት አንዴ ነው እንደ እድል። ሰአት ያዝ ከተባልኩ... ጥቁሯን እጅ ላይ የምትታሰረዋን ሰአይ ይሰጡኝና ኳስ ሲወጣ ሰአት እያቆምኩ...(ከሜዳው ጀርባ ያሽቆለቆለ ስለሆነ ኳሷ ሩቅ ሄዳ እስክትመጣ ይቆያል) ኳሷ ስትመለስ ደግሞ እንዳስቀጥል።
እሱም ደግሞ ኳሱን ሙሉ ደቂቃ እንዳይ ጥሩ እድል ቢሆንም ግንሌላ ጣጣ አለው። እየመራ ያለ ቡድን ሁሌም ማሸነፍ ይፈልጋል ስለዚህ ደቂቃው አላልቅ ሲለው እኔ ላይ ሲጮህ... እየተመራ ያለ ቡድን ደግሞ ኳሷ የእጅ እንኳን ስትሆን እንዳቆምለት ይጨቃጨቃል።
ሌላው ጣጣ ደግሞ ድንገት እመሰጥና ኳሱ ሲወጣ ያቆምኩት ደቂቃ ኳሷ ስትመለስ አላስጀምረውም። ልክ ሁለተኛ ፎሪ ሲወጣ ሰአቱን ለማቆም ሳየው ለካ ቅድም እንዳቆምኩት ነው....
...ያዩብኝ ይመስል ድንግጥ እልና ኳሱ ውጪ እንዳለ ማስቆጠር እጀምራለሁ... አንዳንዴ ደግሞ አጫውት የተባልኩት ደቂቃ ሳላውቀው አልቆ ሌላ አጫውት የተባልኩትን ግማሽ የሚያህል ደቂቃ... ሰአት መያዜን ሳላውቀው ረስቼ እያጫወትኩ በመሀል አንዱ የደከመው
'' ኧረ ዳኛ ምንድነው ሰአት..'' ሲል ድንግጥ እልና
''የባከነ አምስት ደቂቃ ጨምሬአለሁ..'' ብዬ እጮሀለሁ።
ሰአት መያዙ ግን ለኔ አሪፍ መበቀያ መንገድ ሆኖልኝ ነበር። ሁሌ ውሀ አምጣ ብሎ የሚልከኝ የአርሰናል ተጫዋች ይሆንና ውሀውን ሳመጣው በግድ የሚወስድብኝ ካልሰጠሁትም የሚኮረኩሙኝ የማንችስተር ተጫዋች ነበር። (አጋጣሚ ይሁን ታስቦበት ግን አላውቅም) ...ውሀ እንዳመጣ የላከኝ ቢያናድደኝም ያመጣሁትን ውሀ ሳይልከኝ ኮርኩሞ ከወሰደ በኋላ መልሶ እንዳመጣ የሚያደርገኝ የማንችስተር ተጫዋችን መበቀያዬ ታድያ ሰአት ነው።
ሌላው የማንችስተር ተጫዋቾች የሚያናድዱኝ ጉልበት ይጠቀማሉ። ኳስ ካለፈ እግር አይለፍ አይነት ነገር። ... ሁለቱም ቡድን ላይ የተሻለ ብቃት ያላቸው ልጆች ቢኖሩም አርሰናል ላይ ያሉት በብቃት በልጠው ጉልበት እንደሌላቸው (ከማንችስተር የበለጠ) ሳይ ለአርሰናል እንዳደላ የሚያደርገኝ ምክንያት ነበር።
... አርሰናል ሲመራ ኳሷ ብትወጣ እንኳን ሰአቱ አይቆምም። ማንችስተር ሲመራ ግን የግድ አርሰናል እስኪያገባ እጠብቃለሁ። ማግባት ካቃታቸውና ተስፋ ካልቆረጡ በቀር ያልታወቀ ጭማሪ ግድ ነው።
...በዚህ መልኩ የእንግሊዙን አርሰናል ሳላይ የኛው አርሰናል ግን በትንሹ ልቤ ገብቶ ነበር። አድጌ ታድያ "ማናቸው እንዲህ በልጅነት ያስጨነቁኝ ክለቦች?" ብዬ ሳያቸው ምንም ለውጥ አላየሁባቸውም። ልክ በስልካችን ላይ ከምናስጭናቸው አኒሜሽን ጌሞች ሊለዩልኝ አልቻሉም። ውሃ አልቀዳላቸው፣ሰአት አልይዝላቸው...ወይ ኳስ አላቀብላቸው ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ ዝም ብሎ ማየት... ኳስ ገብተው ባይጫወቱም የጫወታው አንዱ አካል መሆን ግን ደስ የሚል ጣዕም ያለው ይመስለኛል። እንግሊዝ ተኪዶ አንድ አካል አይኮን ነገር...
ብቻ እንደኔዎቹ ማንችስተርና አርሰናሎች አልጥም አለኝ ጨዋታቸው። ከዛን ጊዜ በኋላ አርሰናል እና ማንችስተር ሲባል የልጅነቴ ይናፍቀኛል። አላገኘው መቼስ።
አርሰናል ከ22 አመት በኋላ ዋንጫ በላ ሲሉኝ ታድያ ደስ አለኝ። ልክ በልጅነቴ ውሀ ያመጣሁላቸው እና ሰአት የጨመርኩላቸው አርሰናሎች እኔ በሌለሁበት ዋንጫ የበሉ አይነት ነገር ነው ደስታው።
አሸናፊነት የትናንት የጽናት ውጤት ነው። በውጣ ውረድ፣ በሽንፈትና በድል ውስጥ አብሮ የቆየ ሰው ውጤት። አርሰናል ሻምፒዮን ሲሆን፣ እኔም ሻምፒዮን ነኝ። ይህ ዋንጫ የክለቡ ብቻ ሳይሆን፣ እኔን ጨምሮ በክለቡ ላይ እምነት ላሳዩ ደጋፊዎች ሁሉ የተበረከተ በልጅነት ያመላለስኩት ውሀ ውጤት ነው።
ዛሬ የምደሰተው በዋንጫው ብቻ አይደለም፤ የልጅነቴ አርሰናል ደጋፊዎች እንደዛ ሲጫወቱ እና ሲለፉ አርሰናል ያልሰጣቸውን ዋንጫ ዛሬ እንደሰጣቸው ሳስብ ነው የምደሰት። ይህ ደስታ የዘመናት ጥያቄያቸው መልስ ነው።
አርቴታ አርሰናል ሲጫወት ያላገኘውን ዋንጫ እልህ ይዞት አሰልጣኝ ሆኖ ተመልሶም ዋንጫውን ለማሳካት 7 አመት ፈጅቶበታል። ልቤን የነካው ደግሞ እንዲያ እየለፋ የሊቨርፑል ይሁን የሲቲ ደጋፊዎች ሚዜ አድርገው የሰሩበት ምስልን ሲያሳዩኝ ነበር ዘንድሮ ሙሽራ ሆኖ ስላሳያቸው ደስ ብሎኛል። ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ቃል አትናገር ማለት ይሄኔ ነው።
ለማንኛውም የልጅነቴ አርሰናሎች እነ ራያችን እንኳን ደስ አላችሁ! ዛሬም የእናንተ ደጋፊ ነኝ!🏆🏆🏆🏆 አብረን ሆነን ባነብላችሁ ደስ ይለኝ ነበር ግን አብረን ስላልሆንን እናንተው አንብቡት።
የእናንተው አርሰናለር
እስራኤል ሰይፉ (ቦዔዝ)
686
Repost from የህይወት ቅኔ🥀
ህእ!
+++++++
ረጅም ዘመን ያስቆጠረ ትዳር ነው።
ባል ስቅታ ይዞታል። ከነጋ ለሶስተኛ ጊዜ እንደ አዲስ ሲጀምረው ክፉኛ ተበሳጨ።
“አረ ማናባቱ ነው ስሜን ሲያነሳና ሲጥል የዋለው? ህእ! ” አለ ለሚስቱ።
“ስኳር ቃምክበት?” አለችው።
“አዎ።”
“ደረቅ እንጀራ በላህበት?”
“ህእ! አዎ”
“ቀዝቃዛ ውሃ ጠጣህበት?”
“አዎ”
"በረዶ ያለው?"
"ህእ! አዎ አልኩሽ እኮ"
“እሺ ትንፋሽህን ይዘህ ሞከርከው? ”
“አዎ ”
“እና አሁንም አልቆመልህም?”
“ህእ! አልቆመልህም? እያየሽኝ አይደል? አሁንም እያነቀኝ? ህእ! "
ትኩር ብላ አየችው።
ከቅድሙ አሁን ንጭንጭ አብዝቷል።
“እንጃ እንግዲህ” አለች። “እስቲ የፈረደበትን ቻት-ጂፒቲን ሌላ መፍትሄ ጠይቀው?”
“አይ! እሱማ ‘ልትሞት ነው’ ብሎ ነው የሚያስበረግገኝ። ህእ! ካንሰር ነው ምናምን ብሎ ቆሌዬን እንዳይገፈው። ጉግል ይሻለኛል።”
“እሺ ጉግል አርገዋ”
ስልኩን አነሳ።
በፍጥነት ተየበ።
የስልኩ ሰማያዊ ብርሃን ፊቱ ላይ አርፎ ይታያል።
ህእ! ህእ! ህእ!
“ኦ!” አለ ከደቂቃዎች በኌላ።
“ምነው? ምን አለህ?” ጠየቀችው
“ለካስ ያልሞከርኩት ነገር አለ”
“ምንድነው?”
“ብነግርሽም አታምኚኝም”
“ተናገር እንጂ። ለምንድነው ማላምንህ?"
“መፍትሄው ላይ ትረጂኛለሽ?”
“እንዴ! የምችለው ከሆነ ለምን አልረዳህም? ቀኑን ሙሉ አሸህ እኮ! ድምፅህ ራሱ ያሳዝናል፤ በዛ ላይ ነገ ስራ ነው። በጊዜ መተኛት አለብን።”
ዝም ብሎ ቆየ።
ከዚያ ደግሞ
ህእ! አለ።
"ንገረኝ እንጂ"
“ያ ነገር ስቅታን ቶሎ ያስቆማል ይላል” አላት።
ጮክ ብላ ሳቀችና...
“አትለኝም?!” አለችው በለበጣ።
“በእውነት!"
" አታሹፍ"
" እውነቴን ነው ስልሽ?"
" ውይ አንተ! ቀልድና ቁምነገርህ አይለይ!"
" እውነቴን ነው እያልኩሽ?"
“አንተ ከምር አንበበኸው ቢሆን እንኴን አንድ ሰው ለቀልድ የጻፈው ይሆናል ።”
“አይደለም፤ ‘ስዊዲሽ ጆርናል’ ነው ይላል፤ ሳይንሳዊ ጥናት ነው። ህእ!"
“በእውነት?”
“እውነት"
አስተዋለችው። መኝታ ክፍላቸው ያው እንደተለመደው ነው። ሰላላ ብርሃን፣ አልጋ፣ ልብስ የተከመረበት ወንበር...
“የሚገርም ነው” አለች ሰረቅ አድርጋ እያየችው።
“እሱስ አዎ። ህእ! እና ታዲያ...?” አላት።
ተጠጋችው።
የሚደረገውን ካደረጉ በኋላ...
ትሄዳለች ብሎ የሰጋ ይመስል እርቃን ገላዋን ከእርቃን ገላው አጣብቆና አጥብቆ አቀፋት።
ፈገግ ብላ አየት አደረገችውና፣
“እሺ በል፤ ደህና እደር የኔ ጌታ” አለችው።
“ደህና እደሪ የእኔ እመቤት” መለሰላት።
“ሳመኛ”
ሳማት።
ጀርባዋን ሰጥታው ተኛች። ከኋላዋ አቀፋት።
“ባሌ..” አለች ፀጉሯ ውስጥ ተደብቆ ሙቅ ትንፋሹ በአንገቷ በኩል ሽው ሲላት ደስ እያላት።
" ሚስቴ"
“ኢንተርኔቱ ምንም ይበል ምን” አለች ፊቷም ባዞረችበት ፈገግ ብላ። “በበኩሌ ስቅታ ስላስቸገረህ ደስ ብሎኛል።”
ከት ብሎ ሳቀ።
ተቃቅፈው ባሉበት ብዙ ደቂቃዎች በዝምታ አለፉ።
ከዚያ ግን ባል እንዲህ ብሎ ዝምታውን ረበሸ....
"ህእ!"
