uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling 👈

ጲንኤል

ጲንኤል

Kanalga Telegram’da o‘tish

ጲንኤል ...አንዳንድ ጦርነቶች በውስጣችን ይካሄዳሉ። ይህ ቻናል እነዚያ ጦርነቶች በቃላት የሚገለጹበት፣ ሰው ከራሱ ጋር የሚገናኝበት፣ ሀሳብ፣ ትዝታ እና ውስጣዊ ግጭቶች የሚጻፉበት ገጽ። ✍️ እስራኤል ሰይፉ

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
194
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-17 kun
-430 kun

Ma'lumot yuklanmoqda...

O'xshash kanallar
Ma'lumot yo'q
Muammo bormi? Iltimos, sahifani yangilang yoki bizning qo'llab-quvvatlash boshqaruvchimizga murojaat qiling>.
Taglar buluti
Ma'lumot yo'q
Muammo bormi? Iltimos, sahifani yangilang yoki bizning qo'llab-quvvatlash boshqaruvchimizga murojaat qiling>.
Kirish va chiqish esdaliklari
---
---
---
---
---
---
Obunachilarni jalb qilish
Okt '26
Oktabr '26
+2
0 kanalda
Sentabr '26
+4
1 kanalda
Get PRO
Avgust '26
+1
0 kanalda
Get PRO
Iyul '26
+6
2 kanalda
Get PRO
Iyun '26
+56
3 kanalda
Get PRO
May '260
0 kanalda
Get PRO
Aprel '26
+6
0 kanalda
Get PRO
Mart '26
+145
1 kanalda
Sana
Obunachilarni jalb qilish
Esdaliklar
Kanallar
13 Oktabr+1
12 Oktabr0
11 Oktabr0
10 Oktabr+1
09 Oktabr0
08 Oktabr0
07 Oktabr0
06 Oktabr0
05 Oktabr0
04 Oktabr0
03 Oktabr0
02 Oktabr0
01 Oktabr0
Kanal postlari
ሚስት ባሏን በስሱ ትጠረጥረዋለች... ብዙ አይደለም አለ አይደል አንዳንዴ ስልኩን ትፈታትሻለች፤ የስልኩን ፓስወርድ አልደበቃት ፣ ሁልጊዜ ክፍት ነው፣  ወይ የሆነ የሚያስጠረጥር ነገር አላደረገ ግን በቃ ለወንድ ልጅ መዘናጋት አያስፈልግም "ቅድመ ውስለታን መከላከል" የሚል መርህ አላት። ግን ስልኩ ሰላም ነው።  ሁልጊዜ ከቴሌና እርሷ ራሷ  ከስድስት ዓመት በፊት "ምጣድ ለሚሰራው ሰውየ ደወልክለት?" ብላ ከላከችለት ቴክስት  በስተቀር ማንም ቴክስት ልኮለት አያውቅም። አንዳንዴ "ማንም የማይፈልገው ሰው ነው እንዴ ያገባሁት?"  የሚል ሀሳብ ውል ይልባታል። ሲታመኑ መከራ ሲክዱ መከራ! ከሰባት ዓመት የትዳር ቆይታ በኋላ አንድ ምሽት ውሃ ልትደፋ ስትወጣ አጋጠማታ!! ባሏ ጨለም ያለ ቦታ ቁሞ በሹክሹክታ ስልክ ሲያናግር ተገጣጠሙ፤ ድንብርብሩ ወጥቶ ስልኩን ዘጋው። ወደቤት ገብቶ ሳትጠይቀው "ከመስሪያ ቤት አለቃየ ደውሎ  ..." ምናምን ከማለቱ  ወደስልኩ ተደጋጋሚ ቴክስት ሲገባ ተሰማ ..ጢን. ጢን! "ዘንድሮ አለ ነገር አለች። " ብልህ " ስለሆነች እስኪተኛ ምንም እንዳልተፈጠረ ተረጋግታ ቆየች። ካለወትሮው ሲገላበጥ አምሽቶ ሲተኛ በቀስታ ስልኩን አንስታ ወደሳሎን ሄደችና ከፍታ አየችው...ምንም የለም... ዋትስ አፕ ላይ ሄደች አገኘችው! የድምፅ መልዕክት ተልኳል.... ድምፁን ቀንሳ ከፈተችው .... "ሰላም ግርምሽ የፅግየ እናት አርፈዋል በጧት መጥተን ስለምናረዳት በሆነ ሰበብ አዘጋጃት" ፅግየ ራሷ ናት።

2
‹‹ያየን ሁሉ ተሰናክለን የማናውቅ ይመስለው ዘንድ የተረጋጋና ዝም ብሎ የሚሄድ ሰው መሆን ምን ማለት እንደሆነ አያውቁትም። ማንም ምን ያህል እንደደከመን አይገነዘብም። በዝምታ ፈገግ ማለታችንና የተስተካከለ ቁመናችንን ስላዩ ብቻ ምን ያህል የድካም ዝርዝሮችን እንደተሸከምን አያውቁም፤ ቢያውቁም ማንም ስለዛ ጉዳዩ አይደለም። በቃ አይረዱኋችሁም.. ሺህ ማይል እያሰብን የተራመድንበትን ነገር አፍ አውጥተን ብናወራው እነሱ አንድ እርምጃ እራሱ ስላልተራመዱ አይሰማቸውም። በልባችን ውስጥ ቤት ስለሰሩት የለሊት ሃሳቦች ሚሊዮን ጊዜ ብናስረዳ የልባቸውን በር አንዷን ሌሊት እንኳን አያንኳኳም። በዚህ ምክንያት አንድ ሰው ተቀብሎ ባለመኖር እና ሳይቀበሉት በመኖር መካከል ይሞታል››                         ―አህመድ ካሊድ ታውፊቅ              
120
3
በአምላክ እጅ በተጠበበችውና መንፈሳዊ ምሥጢርን በያዘችው የበገና ጅማት ላይ ጣቶች ሲያርፉ፣ የድምፁ ንዝረት ወደ ደረት ሰርጎ በመግባት የነፍስን ህዋሳት ያነቃቃል። የበገና ጥበብ፣ የታሪክ፣ የጸሎት፣
በአምላክ እጅ በተጠበበችውና መንፈሳዊ ምሥጢርን በያዘችው የበገና ጅማት ላይ ጣቶች ሲያርፉ፣ የድምፁ ንዝረት ወደ ደረት ሰርጎ በመግባት የነፍስን ህዋሳት ያነቃቃል። የበገና ጥበብ፣ የታሪክ፣ የጸሎት፣ የፍልስፍናና የእግዚአብሔር ምስጋና ታላቅ መንፈሳዊ ሀብት ነው። ታላቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ምስጋናና ስለ መንፈሳዊ ዜማ ሲናገር፣ የምስጋና ድምፅ የሰውን ልብ ከምድር ከንቱነት ወደ ሰማያዊው ምስጢር እንደሚያሸጋግርና ነፍስን ከአምላኳ ጋር እንደሚያገናኝ ያስተምራል። ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ «በገናን አንሱ፤ በበገናም ለእግዚአብሔር ዘምሩ» እያለ እንደተናገረው፣ በገና የንጉሡ የዳዊት እጆች ያረፉበት፣ የነቢያት መንፈስ የፈሰሰበት፣ የቅዱሳን ማኅሌትና የእግዚአብሔር ምሕረት መጠየቂያ ታላቅ የዜማ ዕቃ ነው። እኛም የዚህን ታላቅ መንፈሳዊ ሀብትና ጥበብ መሠረት በመጣስ ሳይሆን በመጠበቅ፣ ትውልድ ከመንፈሳዊ ሥሩ እንዳይደናቀፍና የቅዱስ ዳዊትን በገና ድርደራ በጥበብና በፍልስፍናው መንገድ እንማር ዘንድ ይህን ታላቅ የትምህርት መንገድ ያሻናል። የበገና ድርደራ ድምፅን ማውጣት ብቻ ሳይሆን፣ ነፍስን የማንጻት፣ ምስጢርን የማስተዋልና ከአምላክ ጋር የጠበቀ ቅርበት የመፍጠር ጥበብ ነው። በኆኅተ ብርሃን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ሰንበት ትምህርት ቤት የ1ኛ ዙር የበገና ሥልጠና ዝግጅታችንን አጠናቀናል። ይህ ታላቅ ጥበብ ከተራ የዓለም ድምፅ ተለይቶ ወደ እግዚአብሔር ቅድስና የሚመራበትን ምስጢር ለመቅሰም፣ በዚሁ መንፈሳዊ ጉዞ ላይ እንድትሳተፉና የዚህ ታላቅ ጥበብ አካል እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። https://t.me/Oct13wed
698
4
በአምላክ እጅ በተጠበበችውና መንፈሳዊ ምሥጢርን በያዘችው የበገና ጅማት ላይ ጣቶች ሲያርፉ፣ የድምፁ ንዝረት ወደ ደረት ሰርጎ በመግባት የነፍስን ህዋሳት ያነቃቃል። የበገና ጥበብ፣ የታሪክ፣ የጸሎት፣
በአምላክ እጅ በተጠበበችውና መንፈሳዊ ምሥጢርን በያዘችው የበገና ጅማት ላይ ጣቶች ሲያርፉ፣ የድምፁ ንዝረት ወደ ደረት ሰርጎ በመግባት የነፍስን ህዋሳት ያነቃቃል። የበገና ጥበብ፣ የታሪክ፣ የጸሎት፣ የፍልስፍናና የእግዚአብሔር ምስጋና ታላቅ መንፈሳዊ ሀብት ነው። ታላቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ስለ ምስጋናና ስለ መንፈሳዊ ዜማ ሲናገር፣ የምስጋና ድምፅ የሰውን ልብ ከምድር ከንቱነት ወደ ሰማያዊው ምስጢር እንደሚያሸጋግርና ነፍስን ከአምላኳ ጋር እንደሚያገናኝ ያስተምራል። ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ «በገናን አንሱ፤ በበገናም ለእግዚአብሔር ዘምሩ» እያለ እንደተናገረው፣ በገና የንጉሡ የዳዊት እጆች ያረፉበት፣ የነቢያት መንፈስ የፈሰሰበት፣ የቅዱሳን ማኅሌትና የእግዚአብሔር ምሕረት መጠየቂያ ታላቅ የዜማ ዕቃ ነው። እኛም የዚህን ታላቅ መንፈሳዊ ሀብትና ጥበብ መሠረት በመጣስ ሳይሆን በመጠበቅ፣ ትውልድ ከመንፈሳዊ ሥሩ እንዳይደናቀፍና የቅዱስ ዳዊትን በገና ድርደራ በጥበብና በፍልስፍናው መንገድ እንማር ዘንድ ይህን ታላቅ የትምህርት መንገድ ያሻናል። የበገና ድርደራ ድምፅን ማውጣት ብቻ ሳይሆን፣ ነፍስን የማንጻት፣ ምስጢርን የማስተዋልና ከአምላክ ጋር የጠበቀ ቅርበት የመፍጠር ጥበብ ነው። በኆኅተ ብርሃን ቅድስት ኪዳነ ምህረት ሰንበት ትምህርት ቤት የ1ኛ ዙር የበገና ሥልጠና ዝግጅታችንን አጠናቀናል። ይህ ታላቅ ጥበብ ከተራ የዓለም ድምፅ ተለይቶ ወደ እግዚአብሔር ቅድስና የሚመራበትን ምስጢር ለመቅሰም፣ በዚሁ መንፈሳዊ ጉዞ ላይ እንድትሳተፉና የዚህ ታላቅ ጥበብ አካል እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
1
5
Matn yo'q...
1
6
አዲሱ ዓመት 2019፦ ሀዘን ፣ የዜጎችን ሞት ፣ ሰቆቃ ፣ ረሃብ ፣ የእርስ በእርስ መገዳደልና መጠፋፋት የማንሰማበት፤ ለተበደሉት ፣ ለተገፉት ዜጎች ሁሉ ፍትሕ የሚገኝበት፤ ምስኪን እናቶች፣ ህፃናት ፣ አረጋውያን ምንም በማያውቁት ፖለቲካ የማይሰቃዩበት ፤ ወጣቶችም ነፍሳቸውን የማይነጠቁበት፤ ዘውትር ጭንቀት ለሆነብን የኑሮ ውድነት መፍትሄ የሚያገኝበት፤ ዜጎች ወጥተው ለመግባት የማይሳቀቁበት፤ ወጥተን የማንቀርበት፤ በአጠቃላይ ሀገራችን ከጫፍ እስከጫፍ ሰላም እና ተስፋ የሚነግስበት ዓመት እንዲሆን እንመኛለን። የአዲስ ዓመት በዓልን ስናከበር ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖቻችን በማሰብ ፣ የሚወዱትን ከአጠገባቸው የተነጠቁ ወገኖችን በማፅናናት ፣ የታመሙትን በመጠየቅ ፣ ፈጣሪ ለሀገራችን አስተማማኝ የሆነ ሰላምን እንዲሰጠን በመማፀን ይሆን ዘንድ አደራ እንላለን። መልካም አዲስ ዓመት !
104
7
"አንተሰ አንተ ክመ ወዓመቲከኒ ዘኢየኀልቅ!" መዝ ፻፪ የዓመታትና የዘመናት ባለቤት            🇪🇹✞እንኳን✞🇪🇹 ከዘመነ ማርቆስ  ወደ  ዘመነ ሉቃስ     በሰላም በጤና አሸጋገራችሁ! 🇪🇹 መልካም አዲስ ዓመት 🇪🇹    🇪🇹 ሰናይ 🌻 በዓል 🇪🇹
190
8
የዓመቱ የመጨረሻ ቀናት ሁልጊዜም የተለየ የሕሊና ድምፅ አላቸው። እነዚህ ጥቂት ቀናት አልፈው አዲሱ ዓመት ከመግባቱ በፊት በአሮጌው ዓመት ውስጥ ለመጨረሻ ጊዜ የምናደርጋቸው እና የምንሰማቸው ነገሮች በሙሉ የራሳቸው የሆነ ከባድ ሚዛንና የራሳቸው የሆነ ጥልቅ ትርጉም አላቸው። ይህን ትርጉም ከልቤ መጋራት እንድጀምር አስቤ ይሆን አልያም የአመቱ መጨረሻ ካደረከው የምታስታውሰውን ተናገር ብባል ከአፌ (ይጥበቅ) ጋር አውርቻለሁ ለማለት ባላውቅም ወደሳቸው ቤት አቀናሁ። (አፌ(ይጥበቅ) ማለት እድሜአቸው ወደ ሰማንያዎቹ የሚሆኑ ጎረቤታችን ናቸው) አፌ ቤት እንደደረስኩ ሁለት ሰዎች ቁጭ ብለው አፌን እያስወሯቸው ነበር። ስገምት የንስሀ ልጆቻቸው ናቸው። ቤት ገባሁና መስቀል ተሳልሜ ''...ይቅርታ ረበሽኩ መሰል..'' ብዬ ልወጣ ስል... ''...እንደውም ስፈልግህ ነበር ቁጭ በል!..'' አሉኝ አፌ። ቁጭ እንዳልኩ ለሰዎቹ የጀመሩላቸውን ማውራት ቀጠሉ... ''... እና እንዳልኳችሁ ሰው በሕይወቱ ጎዳና ሲመላለስ እንደ ዓመቱ መቃረቢያ ያለ የጸጥታ ጊዜ አያገኝም። ቀኖቹ እያለቁ ሲሄዱ አየሩ ሳይቀር የለውጥና የምስጢር ጠጠሮችን የተሞላ ይመስላል። በነዚህ ጥቂት ቀናት ውስጥ ለመጨረሻ ጊዜ የምንተንፍሰው የአሮጌው ዓመት አየር፣ ለመጨረሻ ጊዜ የምናያቸው የጨለማና የብርሃን ቅያሬዎች፣ እንዲሁም ለመጨረሻ ጊዜ የምናስባቸው የኃዘንና የደስታ ትዝታዎች በሙሉ የነፍስን ደጅ ያንኳኳሉ። ለመጨረሻ ጊዜ ሰውን ይቅር ማለት፣ ለመጨረሻ ጊዜ የቆየን ቂም ከልብ አውጥቶ መጣል፣ ለመጨረሻ ጊዜ በነበረን ነገር ሁሉ ላይ ረክቶ ማመስገን እነዚህ ሁሉ የዓመቱን በር የመዝጊያ ቁልፎች ናቸው። ​ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በስበከቱ እንደሚያስተምረን የጊዜ መለወጥ የሰማያዊውን መንገድ የሚያስታውስ፣ የሰው ልጅም በዚህ ምድር ላይ እግረኛና አላፊ መንገደኛ እንጂ ነዋሪ አለመሆኑን የሚያስረዳ ትልቅ ትምህርት ቤት ነው። ፍትሐ ነገሥትም ቢሆን የሰውን ልጅ የሕይወት ዘመንና የጊዜን ፍሰት ሲያመላክት፣ ሰው እያንዳንዱን ቀንና እያንዳንዱን የተሰጠውን አጋጣሚ በንጹሕ ልብና በበጎ ምግባር ሊፈጽመው እንደሚገባ ያስረዳል። በዓመቱ ማጠቃለያ ላይ ለመጨረሻ ጊዜ የሚደረግ መልካም ነገር፣ ባለፉት አስራ ሁለት ወራት ውስጥ የነበሩትን ጉድለቶች በሙሉ አልፎ የሚሸፍን፣ የነፍስን ቁስል የሚያድን ታላቅ ቅባት ይሆናል። ​አሮጌው ዓመት ሲሸኝ ለመጨረሻ ጊዜ የምናፈስሰው የንስሐ እንባና ለመጨረሻ ጊዜ የምንዘረጋው የምጽዋት እጅ፣ ወደ አዲሱ ምዕራፍ የምንዞርበትን ብርሃን ያበራል። የሰዓቱ እጆች ወደፊት እየተራመዱ አሮጌውን ዓመት ወደ ታሪክ መዝገብ ሲሸኙት፣ ሰውም በውስጡ ያለውን አሮጌ ማንነት ለመጨረሻ ጊዜ ትቶ፣ በይቅርታና በምስጋና ታጥቦ፣ በአዲስ ተስፋና በንጹሕ ሕሊና ወደ አዲሱ ዘመን ይሻገራል። እናንተም ታድያ እንዲሁ ልትሆኑ ይገባል። አሁን ጊዜውም እየመሸ ነው መሰል። ለማንኛውም በሰላም ያሳድረንና ነገ ከቅዳሴ በፊት በሰፊው እንነጋገራለን። መልካም አዳር ይሁንላችሁ! በሉ ተነሱ! እንደው ሻይ ቡናም ሳልል ዝም ብዬ በደረቁ አስቀመጥኳችሁ ልጆቼ ይቅር በሉኝ!.'' አሉ በተማጽኖ... ..ልጆቹም ብድግ ብለው ''...ኧረ አባቴ ምንም አያስፈልግም ከዚህ በላይ ምን አለና። ደህና እደሩ!'' ብለው መስቀል ተሳልመው ወጡ። እንደወጡም ወደ እኔ ዞረው ''...እንዴት ያሉ መልካም ሰዎች መሰሉህ። ስለ እውነት።  የተባረኩ ልጆች።.... እኔማ የፈለኩህ...'' አሉና መጥፋቴ ትዝ ብሏቸው እንደመገረም አሉና  "..ኧረ እንደው እስራኤል ልክ አልሰራህም። ስለእውነት ልክ አልሰራህም። መች ነው የመጣህ? ዛሬ ይኸው አምስተኛ ቀንህ። ወይንስ ጻጉሜ አይቆጠርም?..'' አሉና በእጃቸው የያዙትን የአጽዋማትና የበአላት ማውጫ እየሰጡኝ '' በል እስቴ ይህንን አንብብልኝ። ልጆቹንም ብጠይቅ አላወቁትም መሰል መልሰው ሰጡኝ። ያው የዘንድሮ ሰው አላውቅም አያውቅም። እኔም እንደምታየው አይኔ ከቀን ወደ ቀን እየደከመ ነው።'' ተቀብዬ ቀኑን እየጠየቁኝ እመልሳለሁ። አበቅቴ? ...፳፫ መጥቅዕ? ...፯ ''...ኧረ ባክህ?...'' እዎ እንደዛ ነው የሚል። ምነው? ''አበቅቴ ሲጨምር ጾመ ሀዋርያት ይቀንሳል ብዬ ነው ቀጥል እሺ... ቀጠልኩ... ጨረስኩላቸው። የገረመኝን ጥያቄ አስከተልኩ ''...እኔ የምሎት አፌ ይህንን ቀመር አባቶቻችን እንዴት ቀምረው እንደሚያውሉት ሳስብ ግርም ይለኛል። እንዴት ነው ግን?" አልኳቸው። የአያቶቻችንን እውቀት ጥልቅ መሆኑን ባውቅም ጥያቄዬ ግን የጅል አይነት መሰለኝ። ''...ኧይ እስራኤል እንደው ይንህን ትተህ እኮ የየእለት እና ወር ጸባዩ ይታወቃል። አየህ... እንጨት ሲቆረጥ እንዳይበሰብስ መችና በምን ሰአት መቆረጥ እንዳለበት ይታወቃል። ለሰውም እንደዚያው ነው።" ብለው አቆሙ። የሰው ምን እንደሆነ ለማወቅ እና እንዲያብራሩልኝ ብፈልግም አልቀጠሉም። የሰጡኝን የአጽዋማት እና የበአላት ማውጫ መልሰው ተቀብለው ዳዊታቸው ውስጥ ከተቱ። እኔም "...የሰዉም እንደዚሁ ነው...'' የሚል እንቆቅልሽ ይዤ ወደ ቀጣዩ አመት እዘዋወር ዘንድ ግድ እያለኝ ተሰናብቻቸው ወጣሁ። የአመቱ የመጨረሻው እና እንቆቅልሹ የህሊና ድምጽ! ✍️እስራኤል ሰይፉ https://t.me/Oct13wed
128
9
እኔና ውሳኔ... ...ለመሄድ ቆርጬ ብድግ ከማለቴ መልሼ ተቀመጥኩ ከዚህ ጋር ሁለቴ ያውም ያሁን ብቻ የሌላው ቀን ቀርቶ የተመለስኩበት እንኳንስ ሊቆጠር አይታሰብ ከቶ ምን ይሆን የያዘኝ እንዳልሄድ ሚስበኝ ቆርጬ እንዳልቆርጥ አቋርጦ 'ሚያስቀረኝ? ልሄድ ያሰብሁ ድሮ ለምን እዚህ ልቅር ለራሴም አልገባኝ እንኳንስ ልናገር። እንዲህ ግራ ገብቶኝ...                         ሳልወስን ቀርቼ እንዲሁ ሳልሻሻል አመቱም አለቀ    መጣ ሌላ ፍቼ። ኤ.....ጭ! ሲያበሳጭ ቆርጦ እንደመነሳት ለምን ከንቱ ልልፋ? ካሁን ወዲህ ይብቃኝ ላቁም ሰውም አላስከፋ! ..በቃ ልነሳ ልተው መወላወል ይቆይ መነሳቴ እንደው አይቀርም ቢዘገይ  ብድግ...ቁጭ ኤ....ጭ ሲያበሳጭ! https://t.me/Oct13wed ✍️እስራኤል ሰይፉ (ለአንዱ...)
106
10
እኔና ውሳኔ... ...ለመሄድ ቆርጬ ብድግ ከማለቴ መልሼ ተቀመጥኩ ከዚህ ጋር ሁለቴ ያውም ያሁን ብቻ የሌላው ቀን ቀርቶ የተመለስኩበት እንኳንስ ሊቆጠር አይታሰብ ከቶ ምን ይሆን የያዘኝ እንዳልሄድ ሚስበኝ ቆርጬ እንዳልቆርጥ አቋርጦ 'ሚያስቀረኝ? ልሄድ ያሰብሁ ድሮ ለምን እዚህ ልቅር ለራሴም አልገባኝ እንኳንስ ልናገር። እንዲህ ግራ ገብቶኝ... ሳልወስን ቀርቼ እንዲሁ ሳልሻሻል አመቱም አለቀ መጣ ሌላ ፍቼ። ኤ.....ጭ! ሲያበሳጭ ቆርጦ እንደመነሳት ለምን ከንቱ ልልፋ? ካሁን ወዲህ ይብቃኝ ላቁም ሰውም አላስከፋ! ..በቃ ልነሳ ልተው መወላወል ይቆይ መነሳቴ እንደው አይቀር ምን ቢዘገይ  ብድግ...ቁጭ ኤ....ጭ ሲያበሳጭ! ✍️እስራኤል ሰይፉ (ለአንዱ...)
1
11
ትንሽ መሆን ግድ ነው... ...የሰርክ ጸሎት የሚደወለው 11:00 ላይ ነው። ምሁር ኢየሱስ ገዳም። ያኔ ህጻን ሳለሁ ታድያ ውስጤ ትልቅ ሰው ነበር መሰለኝ ንግግሬ ሁሉ እንደኔ ካለ ህጻን የሚጠበቅ አ
ትንሽ መሆን ግድ ነው... ...የሰርክ ጸሎት የሚደወለው 11:00 ላይ ነው። ምሁር ኢየሱስ ገዳም። ያኔ ህጻን ሳለሁ ታድያ ውስጤ ትልቅ ሰው ነበር መሰለኝ ንግግሬ ሁሉ እንደኔ ካለ ህጻን የሚጠበቅ አይነት አልነበረም። (ኧረ እንደውም ዳኛው እስከመባልም ደርሼ ነበር😁) ...አንድ ቀን ታድያ የሰርክ ጸሎት ረፍዶብኝ እየተቻኮልኩ እግሬን እታጠባለሁ። (ምን አልባት ምስባክ ሳያጠኑ ከደረስኩ ስለማልቀጣ) ልክ ግራ እግሬን ጨርሼ ቀኙን ልጀምር ስል ኤርሚ ጨ (''ጨ'' ቅጽል ስሙ ነው) እየተጣደፈ መጣና "..ዞር በል ኩታራ!'' ብሎ ገፋ አደረገኝና እጁን ታጥቦ አለፍ እንዳለ ''...ኧዪ ጊዜ ጥሎኝ እንጂ እኔም እኮ ይሄኔ ካንተ እኩል ነበርኩ.!'' አልኩት። ኦሆ! ብሎ ነጠላውን ትከሻው ላይ እየጫነ ሄደ። እኔም ' ምን አጋፋው ቆይ? እኔም እኮ ረፍዶብኛል። ተራ እንኳ ባይጠብቅ በስርአት ታጥቦ አይሄድም? አልከለከልኩት! ወይንስ ትንሽ ስለሆንኩ ነው?..' እያልኩ ብቻዬን እያጉረመረምኩ ታጥቤ ተከተልኩት። ወደ ቤተ ጸሎት። አድጌ ትልቅ ከሆንኩ በኋላ ታድያ ልክ ይህን ፎቶ የተነሳን እለት አስታወሰኝ ''...አንተ ግን ያኔ ልጅ እያለን ያልከኝን ግን መቼም አልረሳውም።'' ''...የቱን ነው?'' አልኩት እየሳኩኝ። በልጅነቴ የማልለው ነገር ስላልነበር ምን እንዳልኩት ለማስታወስ "...ያኔ እግርህን እየታጠብክ ያልከኝን። ''..ጊዜ ጥሎኝ እንጂ...' ነው ምናምን ያልከኝን'' ''..ታድያ ምን ያጋፋሃል አርፈህ በስርዓት አትታጠብም ነበር?" አልኩት ''..ኧረ ልክ ነው እኮ ያው የልጅ መልስ ስላልሆነ ገርሞኝ እንጂ'' ''..ልጅ መሆን ግድ ነው'' ተሳሳቅን ዛሬ ታድያ ልደቱ ነው። ...ታላቅየው እንኳን ተወለድክልን (አሁንማ እኩል ነን የምን ታላቅ😁) መልካም ልደት ይሁንልህ ውዱ ወንድሜ!🎂🎂🎂
92
12
+6
ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ ዘሰኑይ.mp3
133
13
የሐረር ልጅ ተወልዶ ባደገበት ወግ አያልቅም ። መንገድ ላይ ያገኘውን አላፊ አግዳሚ ሰላም ሳይል፣ ወሬ ሳይጀምርና የቡና ጥሪ ሳይቀበል ማለፍ ሞቱ ነው፤ እናም የሄደበት ቦታ ያልታሰበውን ያህል ዘግይቶ ቢደርስ ወይም መንገዱ ላይ አድሮ ቢቀር አይገርምም። እኔም ይሄው የዘሬን ብተው ይዘርዝረኝ ሆኖብኝ፣ ከዶርሜ ወጥቼ ወደ ክፍልም ሆነ ወደ ቤተክርስቲያን ለመሄድ በምነሳበት እያንዳንዱ ቅጽበት መንገዱ እስታክ አደርግ ነበር። ወዳጄ እስራኤልና ሌሎች ጓደኞቼ በዚህ የሐረር ልምዴ ስልችት ብሏቸዋል። አንድ ቀን ግን ይሄን አባዜዬን ገታ አድርጌ፣ ነገሮችን በሙሉ መስመር ለማስያዝ ቁርጥ ውሳኔ ላይ ደረስኩ። የሰመራ ካምፓስ ሁለት ዋና ዋና በሮች አሉት። የመጀመሪያው በበግ ተራ ጀርባ የሚገኘው ጭር ያለው የኬንያ በር ነው። እኔ በግሌ ይሄን መንገድ በፍጹም አልወደውም። አንድ የጊቢ ጉባኤ መምህሬ «ክርስቲያን ወደ በግ ተራ አይሄድም!» ብለው ያስተማሩኝ ትምህርት ሁልጊዜ በሕሊናዬ ይመላለሳል። ለመሆኑ ለምን «በግ ተራ» ተባለ? እኔ ግን ሳስበው ሰው ሰው ሆኖ ተፈጥሮ የእንስሳትን ያህል አስተዋጽኦ የሚያጡበት፣ ማንነት የሚረክስበት ቦታ ስለሆነ ይመስለኛል። ሁለተኛው መንገድ ደግሞ ስለይሽ በእንባን አቋርጦ በዋናው የአስተዳደር ህንፃ በኩል የሚያወጣውና በሰው ማዕበል የተሞላው ዋና መግቢያ በር ነው። ያን ዕለት ግን መንገድ ላይ ከሚቆሙ ሰዎች ለመሸሽ ስል፣ የማልደሰትበትን የኬንያ በር መርጬ የምሽት የቤተክርስቲያን ጉዞዬን ተያያዝኩት። ምሽቱ ገፍቷል፤ ጸሎቴን አጣድፌ ፈጸምኩ። ስመለስ ግን «ወንድ ልጅ በመጣበት መንገድ አይመለስም» የሚለው ፉከራ ትዝ አለኝና በዋናው በር ለመግባት ወሰንኩ። አይዲዬን አሳይቼ ጥቂት እንደወረድኩ ግን ያችው የሐረሯ ልጅ ሔርሜላ ከቀለም ጋር ከፊቴ ተደቀኑ። «ኧረ ዛሬ አንዱ አምሮብሃል!» አለችኝ ሔርሜላ። «አመሰግናለሁ... ግን ወዴት እየሄዳችሁ ነው?» አልኩኝ፣ ወሬውን አሳጥሬ ለማለፍ እየሞከርኩ። «ድንኳን ሰበራ! አብረኸን ና እንጂ!» አሉኝ። ማታ ላይ የተደገሰ ሰርግ ማየቴ ገርሞኝ «የዘንድሮ ሰርግ አቤት መፈላሰፍ!» አልኩ በውስጤ። ድንኳኑ ስር ስንደርስ ግን እንግድነታችን እንዳይታወቅና እንደ ቤተሰብ እንድንቆጠር ከህፃናት ጋር መጫወት፣ ድንኳኑን ማስተካከል ጀመርን። ብዙ ሳይቆይ እውነትም የቤቱ አካል መስለን ታየን። ይህንን ስመለከት በድፍረት ስልኬን አውጥቼ ወዳጄ እስራኤልን ደወልኩለት፤ ቶሎ ና! አልኩት። እሱም ፍፁምን፣ አለማየሁንና ሌሎችንም አሰባስቦ «ደርሰናል!» ብሎ መልሶ ደወለልኝ። በሩ ላይ በአክብሮት ዱላ ይዞ ይቆጣጠር የነበረውን ሰው «እየጠሩህ ነው» ብዬ በተንኮል ከመንገድ አስወግጄ፣ ጓደኞቼን በደስታ አስገባኋቸው። ነገር ግን ገና ገብተው ሳያርፉ፣ የሙሽሪት አባት ነገሩን ነቁበት! በታላቅ እፍረትና ቅሌት ከሰርጉ ድንኳን አባረሩን። አቤት ማፈር! እስራኤል በሁኔታው ክፉኛ ተበሳጨ፤ ቆይ ታያለህ፣ እበቀልሃለሁ !» እያለ ዛተብኝ። ቀናት ተቆጠሩ። አንድ ቀን እስራኤል የዛተብኝን በቀል ሊበቀል «ታላቅ ግብዣ አለብህ» ብሎ አራት ኪሎ በሚገኘው የሥላሴ ሁለገብ አዳራሽ ወሰደኝ። ነሐሴ 3 ቀን የመምህር ሲሳይ የበገና ማሰልጠኛ ማዕከል ታላቅ መርሃ ግብር ነበረው። እዚያ ቦታ በእውነት የነፍስ ምግብ የሆነ ልዩ ዝማሬና ትምህርት ተመገብኩ፤ የበቀሉ ዓይነት ባረከኝ! በዚህ መንፈሳዊ ድግስ መካከል፣ እኔና እስራኤል በዲላ ዋለሜ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን የኆተ ሰንበት ትምህርት ቤት ያሰብነውን የበገና ማሰልጠኛ ፕሮጀክት እውን ለማድረግ ሰዎችን ማናገር ጀመርን። እኔም ከልጅነቴ ጀምሮ የማውቀውን ዘማሪ ሐዋዝን አየሁትና ተጠጋሁት። ሐዋዝ በሞቅ ያለ ፍቅር እጁን ዘርግቶ «ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ?» አለኝ። እኔም በሙሉ እምነት አንድ በገና ግዛልን! አልኩት። እሱም ፈገግ ብሎ «ኧረ የምን አንድ ብቻ! ከማውቃቸው ሰዎች ጋር በመሆን የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን!» ሲል ተስፋችንን አለመለመው።
73
14
የአውቶብስ ውስጥ ሌባ ..              ቁጥር  25  አውቶቡስ  ከአቃቂ ለገሀር         አውተቢሷ በተሰፋሪ ብዛት ተጨናንቃለች ። በመሃል የጆሮ ታንቡር የሚቀድ ስለታም የሴት ድምፅ ከፍ ብሎ ተሰማ ።       "  ብሬን  ብሬን   ኡኡኡኡኡ   !  " ተሳፋሪው ግራ ተጋብቶ ወደ ሚሰማው ድምፅ ዞር ዞር እያለ አፈጠጠ  ። ሴትዬዋ የአውቶብሱን የውስጥ ቋሚ ዘንግ ይዛ መጮዃን ቀጠለች ።        "  ብሬን ብሬን ! ሹፌር  አቁምልኝ  "    አውቶቡሷ ስትቆም ተሳፋሪው አጉተመተመ ።  እርስ በራሱ በጥርጣሬ እየተያየ አንሾካሾከ ። ሴትዬዋ አጠገቧ የቆመውን ሰው አፍጥጣ እያየች   " ፈትሹልኝ   ፈትሹልኝ  "   አለች በጩኸት ።          ሰውየው በአይኑ ጮኸባት ።                       " አልፈተሽም  "  በአፉ ደገመላት     ተፈተሽ አልፈተሽም በሚሉት ቃላት የሞቀ ጭቅጭቅ ተነሳ  ። ጭቅጭቁ ሲከር  ማንም መንገደኛ ሳይወርድ አውቶቡሷ ፖሊስ ጣብያ በር ላይ እንድትቆም ተመሰነ ።  በመጀመርያ አልፈተሽም ያለው ሰው ተገዶ እንዲፈተሽ ተደረገ እጆቹን እንደ ክርስቶስ ግራና ቀኝ ዘረጋላቸው  ።  ግን ምንም አልተገኘበትም ።  ቀጥሎ ሁሉም ተሳፋሪ ተራ በተራ እንደ ገብስ እየተፈተገ ተፈተሸ ። ምንም !  በመጨረሻ ሴትዬዋን  እስኪ እንፈትሽሽ አሏት ። ቀሚሷንና ቦርሷዋን እያራገቡ ፈተሿት ።      ጠፋ የተባለው ብር እሷ ውስጥ ተገኘ               አይኖቿ  ፈጠጡ     የፈጠጡ አይኖቿን በእንባ ሸፍና ተሳፋሪውን ሁሉ ይቅርታ ጠየቀች ። ይበልጥ ደግሞ ሌባ የተባለውን ሰው አያነባች ይቅር በለኝ አለችው ። እያለቀሰ ይቅር አላት። እያለቀሰ የስልክ ቁጥሯን ጠየቃት ።         ይሄው ዛሬ  የ ሀያ አምስተኛ የጋብቻ በአላቸውን  25  ቁጥር  አውቶብስ ውስጥ እያከበሩ ይገኛሉ ።                 በፈጣሪ  ተጋበዙልን  !!!                  (  እውነተኛ ታሪክ  )
100
15
ተለያይተው ይኖሩ ነበር አሉ እሱ ፀሀፊ ነበር ። እድሜውን በቃል የሚቆጥር ። በስተርጅና ታሞ ከአልጋ የወደቀ ግዜ ይሄን ተናዘዘ "በምድር ላይ ያለኝ ሁሉ የእርሷ ነው ከንብረቴ አንዲት ቁራሽ እንዳይነካባት አፍልቄ የፃፍኩት ሁሉ የሷ ነው ። በልቤ ያሰብኩትም"*` ደረሳት መልዕክቱ። ብጫቂ ወረቀት ላከችለት። "የሞትኩ እንደው ፤ ብል ከአፈር ጋር ያላወሰኝ ከግጥምህ አንድ ስንኝ ከፈኔ ይሁን አልብሰኝ" -------- የባሴ ሀብቴ ኑዛዜ
121
16
"ጊዜው የሾርት ነው" የረዘመ ነገር አይፈለግም(😳🤣) ፥ ሰዉ ከአጭር ነገር ጋር ያበደ አፍቅሮት ላይ ወድቋል❤❤ short video....short movies...short stories... short scripts ...easy way of success...short memory....short answer... scroll and scroll our hand used device videos again and again🤣 በቃ የሆነ ያጣጠረ ነገር ይመቸናል😭 ላብ ያልታከለበት business, ድካም ያልታከለበት ስኬት፥ ትጋትን ያላማከለ ሃብት friendship ራሱ ዘለግ አይልም ቋሚ ጓደኛሞች ያን ያህል የሉም....በቃ መሞካከር ፋሽን ነው.....ፍቅር፥ ትዳር፥ ጓደኝነት፥ ስራ፥ ትምህርት፥ ሃይማኖት፥ everything has its own sample time አጭር ቀሚስ፥ አጭር ግንኙነት፥ አጭር ቆይታ፥ አጫጭር ኮርስ፥ አጭር ቀጠሮ  ነገረ ስራችን ቢኪኒ በቢኪኒ ሆኗል😂 ዝንጉነታችን ራሱ short memory ለተባለ pandemic factors አሳልፎ ሰጥቶናል ድሮ ለመጋባት ሲጠናኑ ቢያንስ ሶስት አራት ዓመት ይከርሙ ነበር አሁን ላይ በ6 ወር መጠናናት የተጋቡ ጥንዶችን በብዛት አውቃለሁ ...6 ወር እንኳን የማያልቅ የሰዉን ባህሪ ቀርቶ ስም ከነ አያት ለመጠናናት አይበቃም🤣 "እጥር፥ ምጥን፥ ቅጥን" የሚሰኙ ቃላቶች ተለምደዋል ባያጥር ብርቱ ጉዳይ ያለበት የሃገር መሪን ይመስል ሁሉም ይጠዳደፋል😂 ሌላው ይቅር የዓለም ዋንጫ በአራት ዓመት አንዴ እየመጣ እንዲህ ማጠር ነበረበት??🙄 ስኬት ሳይቀር በአቋራጭ ካልሆነ አይፈለግም....የሁለት ሰዓት ርዝማኔ ያለው ስብሰባ ላይ ሰብሳቢውና ተሰብሳቢው  እኩል ሲያንቀላፉ ትታዘባለህ😁 ረጅም መንገድ አይ.ነዳም.....ረጅም walk አይፈለግም......ረጅም ዕድሜ መኖር ቢፈቀድ እንኳን በlife boringness ምክንያት ሰዉ ቢያጥር አይደብረውም🙄 ሰዉ እምነቱ ላይም አይረዝምም...ሃይማኖቱ ላይም አይከርምም....አቋማችን ሁላ ሳይቀር በፍጥነት ይቀያየራል....በህይወታችን የማንደራደርበት pillars የሉንም፤ የመርህ ሰው አይደለንም .....flexibility የራሱ ውበት ቢኖረውም አቋመ-ቢስነት ሲታከልበት አድርባይነትን ይወልዳል። አንረጋም....አንረካም...ቶሎ ተወልደን ሳንጎረምስ እናረጃለን፤ ቶሎ ተመርቀን ሳንሰራ እንጃጃለን። ዝና ሁላ ሳይቀር ቁመት የለውም...ዕውቅናም ከአንድ ሃሙስ አይዘልም...ሃሳብ አይበረክትም... እልል የተባለላቸው አይነ-ግቡ ጥንዶች ወዲያው ይፋታሉ....የት ይደርሳሉ ተብለው የሚጠበቁ ዝግጅቶች ጳጉሜያቸው ይፈጥናል........ በጋራ ሰርተው ሽቅብ ይወነጨፋሉ የምንላቸው business partners ድርጅታቸውን ይዘጋሉ....ሰማይ ራሱ ከኛ ያደመ፥ ምድር ራሷ ከኛ ያበ'ረች ይመስል ቶሎ መሽተው ቶሎ ይነጋሉ።  ቀን አይበረክትም....ሰኞ ብለህ ሐሙስ ይመጣል ያኔ በመሐል የት ነበርኩ ብለህ ከራስህ ጋር ትወዘጋገባለህ🤣 አሁን ሁላ ይሄን ስፅፍ እንዳይሰለቸኝ short video እያየሁ ነው የጨረስኩት🤣 እናንተም በአንቀፅ ከፋፍላችሁት በሳምንት ውስጥ short episode አድርጋችሁ እንደምትጨርሱት እተማመንባችኋለሁ🤙🤙
108
17
የተወደድኩ ሰሞን ሰርግ ቤት ከሰወች መሀል አይኔን የሳበች አንዲት ልጅ ተዋወቅኩ። ምግብ ተጎራረስን ጠላም ጠጅም ጠጣን ሞቅም ሲለን ተነስተን ጨፈርን፣ ስልክ ተለዋውጠን በሰፊው ለመዝናናት ቀጠሮ ይዘን ተለያየን። በየቀኑ መደዋወል ጀመርን። ጭፈራ ከሚለው መንፈስ ወጥተን በንጹህ ፍቅር ተፈላለግን። ቤት ገብቼ አልጋዬ ላይ እየተንፈራፈርኩ ለረጅም ሰዐት አወራታለሁ። በተደጋጋሚ ዌይቲንግ ላይ የሚገባ ስልክ ነበር። እኔ እና እሷ በምናወራበት ሰዐት ነበር ደግሞ የሚደወልልኝ። ብዙ ጊዜ አይቼ አልፈዋለሁ። አንድ ቀን ከፍቅረኛዬ ጋ አውርተን እንደጨረስን በተደጋጋሚ ወደ ሚደወልልኝ ስልኩ ደወልኩ። በጣም ለስላሳ እጅግ በጣም የሚያምር ነፍስን የሚያሳርፍ ልብ የሚያረጋ ድምጽ ሰማሁ። ጆሮዬን ኮርኩሬ... "አቤት?" አልኩ። "አባ ነህ?" አለቺኝ ተለሳልሳ። አረ ድምጿጿጿ ልታሳብደኝ ነው፣ ልቤ ከደረቴ ጋ እየተጋጨች ስትመለስ ይሰማኛል። "አዎ ነኝ... ግን ይቅርታ አላወኩሽም"! ከስልኩ በስተጀርባ ለጊዜው የማላስታውሰው የአስቴር ዘፈን ተከፍቷል ትንሽ ዝምታ... "ሄሎ"! አልኩ በጉጉት "ወዬ አባ ... ዝምምም የአስቴር ዘፈን በርቀት ይሰማኛል ስልኬን ጆሮዬ ላይ ለጥፌ ወደ ውስጥ አየር ሳብኩ "አታውቀኝም ካልደበረህ ዝም ብለህ አውራኝ በናትህ?" አረ አንጀቴ ተንሰፈሰፈ። ምን እንደሆንኩ ምን እንዳስነካቺኝ አላውቅም። በአንዲት ቅጽበት በሽርፍራፊ ቃላት ሀዘን ይሁን ደስታ መፈለግ ይሁን ቀልድ ብቻ የማላውቀው ስሜት ተቆጣጠረኝ። ስልኩን መዝጋት አልፈለኩም፣ ምን ብዬ ምን እንደማወራት የማሰቢያ ጊዜም አላገኘሁም። "ሄሎው አባ?" ከሀሳቤ ነቃሁ "ወዬ ... እ እ እ አቤት ምናልሺኝ?" "ካልተመቸህ ሌላ ጊዜ እናወራለን በቃ ደህና እደር"! "ቆይ እንዳትዘጊው"! "ካወራኸኝ ደስ ይለኛል"! አልጋዋ ላይ እየተገላበጠች ነው መሰል። "ስልኬን ማን ሰጠሽ?" የፍቅረኛዬ ስልክ ዌይቲንግ ገባ "እሱን ሌላ ጊዜ ነግርሀለው...ግን በቃ ...ሳይህ ደስስስ ትለኛለህ እውነት"! ... ዝምምም ፍቅረኛዬ ደጋግማ እየደወለች ነው "አውራኝ እንጂ አባ ምነው ዝም አልክ?" "ይቅርታ አንዴ መልሼ ልደውል ትንሽ ጠብቂኝ"! ጆሮዋ ላይ ዘጋሁት። በጀርባዬ ጋደም ብዬ ከልጅቷ ድምጽ ተነስቼ ፊቷን ሰውነቷን መሳል ጀመርኩ ፍቅረኛዬ ያለ ማቋረጥ እየደወለች ነው። ምክንያቱን ባላውቀውም ማንሳት ደበረኝ ሶስት አራት ጊዜ ደጋግማ ደወለች። ስልኬ አስጠላኝ አሁንም ስልኬ እየጠራ ነው ብስጭት ብዬ ሳየው አዲሷ ልጅ ናት። ከተኛሁበት ተስፈንጥሬ ተነስቼ "ወዬ ጠፋሁብሽ አይደል?" "ችግር የለውም አባ ስላወራሁክ ደስ ብሎኛ...ል" ፍቅረኛዬ እየደወለች ነው አሁንም። "ምናልሺኝ ውዴ?" ቀልቤን ሰብሰብ ለማድረግ እየሞከርኩ። "ደህና እደር ሲመችህ ደውልልኝ"! ድምጿ ተቀየረ "ምን ሆንሽ ውዴ እንዳትዘጊው አውሪኝ? ከድምጿ መለየት ሞት መስሎ ታየኝ "ከጓደኛዬ ጋ እያወራህ እንደሆነ አውቃለሁ...ፈትኚው ብዬ ሰለላኳት ከፈተናው እንድትወጣ ደጋግሜ ደወልኩልህ ደህና ሁን። የሚል ቴክስት ከፍቅረኛዬ ደረሰኝ። ስልኬን በድንጋጤ ወረወርኩት፣ እንዲው አይኔ ፈጦ ሳልተኛ ስገላበጥ አደርኩ። "ደህና አደርክ ተወዳጁ ልጅ" የሚል ቴክስት ከአዲሷ ልጅ በጠዋት ደረሰኝ "ሳስብሽ አደርኩ ምንም"! እየፈራሁ መለስኩላት። "ፈጠንሽ አትበለኝ እና ጊዜ ካለህ ሰሞኑን ብንገናኝ?" አንዴ ጨቅይቻለሁ "ዛሬም ነገም በተመቸሽ ቀን መገናኘት እንችላለን"! ፍቅረኛዬን ካጣኋት አይቀር የዚህችን ድምጸ መረዋ ልጅ ፊት ባየው። ✍....
91
18
ስንት ሰዎች የነበሩ ይመስልሃል? "የድኃ እንባ ሲፈስ የወንዝ ውኃ የሚፈስ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ድኃ ሲጮህ ውሻ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ድኃ ታስሮ ወይም በሌላ ጭንቅ ነገር ተይዞ ሲሞት የወፍ ግልገል የሚሞት የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ጉልበት ካለን ብለው በደካሞች ላይ ያሰቡትን ሁሉ የሚሠሩ ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ሰውን ለማጥፋት እጅግ የሚጥሩ ሰውን ካላጠፉ እንቅልፍ የማይወስዳቸው ስንት ሰዎች ነበሩ፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀድሞ የነበሩት ሁሉም መሬት ሆነዋል፡፡ ከመሬት የተገኘ ሁሉ መሬት ስለ ሆነ ወደ መሬትም የማይመለስ ስለሌለ እኛም ነገ እንደዚያው እንሆናለን፡፡ ስለዚህ በማናቸውም ምክንያት ቢሆን፤ የሰው ደስታውና አዘኑ እጅግ አጭር መሆኑን በጣም እወቅው፡፡..." /ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ፤ ለልጃቸው ለፈቃደ ሥላሴ የፃፉት ምክር፤/- ወዳጄ ልቤና ሌሎች ላይ የተቀነጨበ።
80
19
መልካም ነገር ሰርተህ ወንዝ ውስጥ ጣለው : አንድ ቀን በርሀ ላይ ታገኘዋለህ
96
20
ትናንትን እንጂ ነገን አላውቅምና ፈጣርዬ ነገን አደራ 🙌ይህ የሁላችንም ፀሎት ነው 🙏 በሉ ደህና እደሩ የነገ ሰው ይበለን❤️🫶
129