cookie

Sizning foydalanuvchi tajribangizni yaxshilash uchun cookie-lardan foydalanamiz. Barchasini qabul qiling», bosing, cookie-lardan foydalanilishiga rozilik bildirishingiz talab qilinadi.

avatar

አቡ አብዱራህማን

አላህ መልካም የሻለት ሰው ዲኑን ያስገነዝበዋል

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganTil belgilanmaganToif belgilanmagan
Reklama postlari
183
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
Ma'lumot yo'q7 kunlar
Ma'lumot yo'q30 kunlar

Ma'lumot yuklanmoqda...

Obunachilar o'sish tezligi

Ma'lumot yuklanmoqda...

ይህች በምስሉ ላይ የምትመለከቷት እህታችን ትላንት ማታ (21/08/2014) በኮልፌ ቁባ መስጂድ ለተራዊሕ ገብታ ከዛም ተሃጁድ ሰግዳ ሱብሒ እየተሰገደ እያለ ከመስጂድ ወጥታ መንገድ ላይ ስትጮህ ሰጋጆች ይዘዋት ወደ መስጂድ አስገቧት። ከሱብሒ በኋላ እስካሁኑ ሰዓት ድረስ እየተቀራባት ነው። አስቸጋሪው ነገር ልጅቷ ራሷን አታውቅም፣ ስልክም አልያዘችም፣ መታወቂያም የላትም፣ የሚያውቃትም ሰው የለም። ስለዚህ የምታውቋት ካላችሁ ቤተሰቦቿን ወይም የሚያውቋት ጓደኞቿን በማሳወቅ ተባበሩን። ከታች ባለው ስልክ ደውላችሁ ማግኘት ትችላላችሁ። መቅሱድ 0913721341 ሙሳ 0946940163 ዓቲቅ 0973649365 ሼር ሼር ሼር
Hammasini ko'rsatish...
በበአል ቀን ባንክ ለምን ይከፈታል? ~ አዋሽ ባንክ በመስቀል በዓል ቀን የባንክ አገልግሎት እሰጣለሁ በማለቱ ጫጫታ ሲበዛበት ውሳኔውን አጥፎ ይቅርታ ጠይቋል። ይህንን ለስራ እንቅፋት የሆነ ባህል የሚነቅፉ ሰዎች እያየሁ ነበር። ነቃፊዎቹ ሙስሊሞች ሲሆኑ ታዲያ "በዒዳችሁ ቀን ቢከፈት ይህን አትሉም ነበር" የሚሉ ተቃዋሚዎችን አይቻለሁ። በዒድ ቀንኮ ብዙ ሙስሊም ሱቅ ይከፍታል፡፡ ከጥቂት አመታት በፊት በሃገራችን አንድ ከተማ ውስጥ "በበዓላችን ቀን ለምን ሱቅ ከፈታችሁ?" በሚል መነሻ ሙስሊሞችን ያጠቃሉ፡፡ በዚያ የተነሳ ግርግር ተነሳ። ጉዳዩ ጠንከር ሲል የክልሉ መስተዳድር በቦታው ተገኝቶ ህዝቡን ሲያነጋግር "በበአላችን ቀን እንዴት የንግድ ተቋማትን ይከፍታሉ?" አሉ። መስተዳድሩ ታዲያ "እነሱኮ በራሳቸውም በዓል ጊዜ ሱቅ ይከፍታሉ" አላቸው። ለማንኛውም ባለ ሃይማኖቶች ሆይ! የመዝጋት መብት ያላችሁ በራሳችሁ ተቋም ላይ ብቻ ነው። ሌሎች ለምን ሰሩ ብሎ አቧራ ማስነሳት ተገቢ አይደለም። አገሪቱን ወደ ኋላ ያስቀራትም እንዲህ ዓይነቱ አሳሪ ባህል ነው። እዚህ ላይ አንድ የማይረሳኝ ገጠመኝ ላንሳ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አንድ መምህር ስለ አሕመድ ብኑ ኢብራሂም (አሕመድ “ግራኝ”) ዘመን የሙስሊሞችና የክርስቲያኖች ጦርነት ያነሳል፡፡ በመሀሉ አንድ ከታች ክፍል ጀምሮ የሚነሳ የተለመደ ጥያቄ ጠየቀን፡፡ “በዚያን ጊዜ በሙስሊሞችና ክርስቲያኖች መካከል የተካሄደው ጦርነት ምን መሰረታዊ ለውጥ አስከትሏል?” የሚል፡፡ ተማሪ የተለመደ መልሱን መደርደር ተያያዘው፡፡ - “ቅርስ ወደመ” ሲሉት “ሌላ?” ይላል፡፡ - “ብዙ ህዝብ አለቀ” ሲሉት “ሌላ፣ ሌላ?” ይላል፡፡ - “ቤተ-ክርስቲያን ተቃጠለ” ሲሉት * “ዝም በሉ! ከዚያ በፊትም ከዚያ በኋላም መስጊዶች ሲቃጠሉ ነበር፡፡ ይልቅ ሌላ መሰረታዊ ለውጥ ንገሩኝ” አለ፡፡ ሌላ ከየት ይምጣ? ተማሪ ከታች ጀምሮ ሲጠጣ የኖረው ወደ አንድ አቅጣጫ ያጋደለ ታሪክ ነው፡፡ ከታች ክፍል የመጡት መልሶች ደግሞ አለቁ፡፡ * አስተማሪው ካጠቃላይ ታዳሚው ምላሽ ሲያጣ ሙስሊሞችን እየለየ ጠየቀን። ግና እነሱው ከነገሩን ውጭ ሌላ ከየት እናምጣ? የሚፈልገውን ምላሽ ያላገኘው መምህር ድንገት ወዳላሰብነው አቅጣጫ ወሰደን፡፡ * “ዛሬ ቀኑ ማነው?” አለ፡፡ ምን እንደመለሱለት ረሳሁት፡፡ * “ቆይማ ከአንድ እንጀምር፣ በአንድ ምንድነው?” አለ። - “ልደታ” አሉት፡፡ * “በሁለትስ?” - “የሆነ ነገር” አሉት፡፡ እሱ ሲቆጥር እነሱ ሲነግሩት እሱ ሲቆጥር እነሱ ሲነግሩት 18 ደረሰ፡፡ * “በ18 ምንድነው?” ሲላቸው - “የለም” አሉት፡፡ * “አንድ የስራ ቀን አገኘን” አለ፡፡ (አለች ነገር) አሁንም ቆጠራው ቀጠለ፡፡ 22 ሲደርስ - “የለም” አሉት፡፡ * “ሁለት የስራ ቀን አገኘን” አለ፡፡ (በቅንፍ ውስጥ 18 እና 22 እራሱ እነሱ እንዳሉት ክፍት እንዳልሆኑ ኋላ አውቄያለሁ፡፡) ቆጠራውን አቆመና * “እርግጠኛ ነኝ ደብተራ ቢመጣ ሰላሳውንም ይገጥመዋል!” አለ፡፡ ከዚያም ድንገት ወደሙስሊሞቹ ዞረ፡፡ * “እ አንተ ጎበዝ! በኢስላምስ ስራ የማይሰራው መቼ ነው?” አለ፡፡ - “የማይሰራበት የለም!” የሚል ምላሽ አገኘ። * “የስ! ኢቭን ጁሙዐ! ሰግደህ ተበተን ነው የሚለው! ኢስላም ለስራ 'ፍሌክሲብል' የሆነ ሃይማኖት ነው!!” አለ። ተንጫጩ። - “እንዴ ቲቸር! የኛም እኮ እነዚህ ሁሉ በአላት መፅሀፍ ቅዱሳዊ አይደሉም” አሉት፡፡ * "ዝም በል! ለኔ ነው የምትነግረኝ! ከትግራይ ነው የመጣሁት! እንኳን ክርስቲያኑ ሙስሊሙ ሲሰራ እራሱ መቅሰፍት ልታወርዱብን ነው” እያሉ የሚቃወሙ አውቃለሁ፡፡ ይልቅ አዳምጡ፡፡ በዚያን ጊዜ የተካሄደው ጦርነት ይሄ የደገኛው ባህል እንዲሸረሸር አድርጓል፡፡ ቆለኛው ሙስሊም ወደ ደጋ ሲመጣ እነዚህን በአላት ስለማያውቃቸው ቀንን ከቀን ሳይለይ አመቱን መስራት ያዘ፡፡ ህዝቡም በነዚህ በአላት ምክኒያት ከቤቱ ይውል የነበረውን በሂደትም እያላላው ሄደ፡፡ የዚያ ጦርነት መሰረተዊ ውጤት ይሄ ነው አለ።" (በነገራችን ላይ ሰውየው ሙስሊም አይደለም!!) እና ምን ለማለት ነው? እኛ በበዓል ቀን ስራ ስለተሰራ፣ ተቋማት ስለተከፈቱ አይከፋንም። (ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 25/2007) የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor
Hammasini ko'rsatish...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

دروس وفوائد ابن منور

Photo unavailableShow in Telegram
ዘካችሁን ለንግድ ባንክ እንዳትሰጡ! ~~~~~ ~~~~~~ ~~~~~~ ባያያዝኩት ማስታወቂያ ላይ እንደምታዩት ንግድ ባንክ ዘካ እሰበስባለሁ እያለ ነው። ንግድ ባንክ ፈፅሞ ለዚህ ኃላፊነት የሚሆን አይደለም። ማንንም የሸሪዐ ቦርድ አድርጎ ስላቀፈ እንዳትሸወዱ። ዘካ ቀልድ አይደለም። ቀላል ሃላፊነትም አይደለም። ወይ በራሳችሁ ወይም ደግሞ ታማኝነቱን በምታውቁት አካል በኩል ብቻ አውጡ። ~ የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor
Hammasini ko'rsatish...
የሙስሊም ወንድሙ ጭንቀት ለሚያሳስበው ሁሉ የእርዳታ ጥሪ አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ ውድ ሙስሊም ወንድምና እህቶች እነሆ " በዚህች ምድር የወንድሙን ጭንቀት ያስወገደ አላህ በመጪው አለም/በአኺራ/ የሱን ጭንቀት ያስወግድለታል" ሲሉ አዛኙ ነብይ ﷺ ነግረውናል ። ኡስታዝ ኻሊድ ከሌሎች ሁለት ወንድሞቹ ጋር ሆኖ በአንድ እቁብ አደረጃጀት ላይ ለስምንት አመታት እና ከዚያ በላይ ሃላፊ ሆነው እያገለገሉ ባለበት ሰዓት ከዛሬ ስድስት አመታት በፊት ጀምሮ ግን በየአመቱ በርከት ያሉ የእቁቡ አባላቶች ከፊሎቹ ኪሳራ እያጋጠማቸው መክፈል ባለመቻላቸው ፣ከፊሎቹ ደግሞ እቁቡ ከደረሳቸው በኋላ ከነ ተያዣቸው/ወኪላቸው/ ሀገር እየለቀቁ አድራሻቸው በመጥፋቱ ምክንያት ባጠቃላይ የስድስት አመት ኪሳራዎች ሲደመሩ ወንድሞቻችንን ላይ ወደ አራት ሚሊዮን ገደማ እዳ ውስጥ እንድገቡ አድርጓቸዋል። በዚህም ምክንያት ይህ ወንድማችን በበኩሉ የልጆቹን መኖሪያ ቤቱን ሽጦ ወደ 1.6 ሚሊዮኑ ቢከፍልም የቀረውን ደግሞ ሰርቶ እንዳይከፍል እንኳ ሲያንቀሳቅሰው የነበረው ሱቅም ብዙ ኪሳራ ስላጋጠመው አይደለም ሰርቶ እዳውን ሊከፍል ይቅርና የመኖሪያ ቤት ኪራይ የሚከፍለው እንኳ የለውም። ወላሂ ያለበት ሁኔታ እጅግ በጣም አሳዛኝ ነው በዛ ላይ አሁን ላይ ገንዘቡ የጠፋባቸው ባለንብረቶች ገንዘባችንን ሊከፍለን ይገባል ብለው ስለከሰሱት በዚህ ረመዳን እንኳ ፍርድ ቤት እየተመላለሰ ነው ያለው ።ብቻ ለመናገር ስለከበደን እንጅ ወንድማችን እጅግ በጣም ከባድ ጭንቀት ውስጥ ነው ያለው ። እንደ ሸሪዓችን ደሞ ስምንቱ ዘካ ከሚሰጣቸው ሰዎች ውስጥ አንዱ መክፈል የማይችለው እዳ ውስጥ የገባ ሰው ነው እና ዘካ የምትሰጡ ወንድሞች እና እህቶች እንድሁም በዚህ በተከበረው ረመዳን የታላቅ አጅር ፈላጊ የሆናቹህ ኸይር ፈላጊ ወንድምና እህቶች ለዚህ ለተጨነቀ ወንድማችን ገቢ በማድረግ ቢቻል እዳውን ለመክፈል ካልሆነ ደግሞ ቢያንስ እንኳ ያቅማችንን የሆነ ነገር አድርገን እንድቋቋሞ በማድረግ ካለበት ጭንቀት ወጥቶ ለቤተሰቡም ለድኑም የሚያገለግል ወንድማችን እንዲሆን የአቅማቹህን እንድታበረክቱ ስንል ለሁሉም ኸይር ፈላጊ ወንድምና እህቶች የእርዳታ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ሌላ ባትችሉ share በማድረግ ተባበረት ወንድማችንን ለመርዳት የተቋቋመ የባንክ አካውንት ቁጥር :- 1000 471 864 785 ንግድ ባንክ #የአካውንቱ ስም :- አህመድ ሚፍታህ እና ከድር ናስር እና ሀሰን ኸሊፋ ለበለጠ መረጃ ስልክ +251964932006 አህመድ +251912498064 ሀሰን +251919470897 ከድር https://t.me/+Ku15s29Husw2MmU0
Hammasini ko'rsatish...
🔉 አንብባችሁ አትለፉት የተከበራችሁ የሱና ቤተሰቦች ዛሬ በዚህ ቻናል ያልተለመደ ነገር ይዤ መጥቻለሁ ። እሱም የአንድ ቀን የጨለመባት ምድር ከመስፋቱ ጋር የጠበበባት እህታችን የሰቆቃ ጥሪ ነው ። እህታችን መዲና ደምሴ ትባላለች እዚሁ ፉሪ 20ሜትር አካባቢ ነዋሪ ነች ። እህታችን መዲና ከመጀመሪያ ጀምሮ በአስም በሽታ የምትሰቃይ የነበረ ቢሆንም የሰመረ ትዳር ሳይኖራት ሶስት ልጆችን ወልዳ እነሱን ለማሳደግ ልብስ ሰፊ ቤት ተቀጥራ እየሰራች እያለ ሶስተኛው ልጅ ወልዳ አራስ ላይ ሆና ጡቷ ትታመማለች ። በዚህ ሁኔታ ላይ እያለች ያ በስሙ ባል ሆኗት የነበረው የልጆቹ አባት ጥሎ ይጠፋል ። እሷም ለጡቷ ብዙም ትኩረት ሳትሰጠው ህመሙ አየጨመረ ሲሄድ ሀኪም ቤት የምትሄድበት ስላልነበራት ይህን ያወቁ ሰዎች ሳንቲም አዋጥተውላት ጥቁር አንበሳ ስትመላለስ መጨረሻ ላይ ወደ ካንሰር እንደ ተቀየረ ተነገራት ። የህመሙ ስቃይ በአንድ በኩል የልጆቿ እጣ ፈንታ እሷ ጥላቸው ከሞተች ምን ይሆናሉ የሚለው በሌላ በኩል የህመምና የህይወት ውጋት ቀስፎ ይዟት እንቅልፍ አጥታ ጎምዛዛ ህይወት መግፋት ግድ ሆኖባታል ። ለህመሙ ኬሞ የተባለ መድሃኒት ታዞላት መውሰድ ስትጀምር የመድሃኒቱ ክብደት በሰውነት ላይ ያለ ፀጉር ቅንድብና ሽፋሽፍት ሳይቀር ስለሚያራግፍ እሷም የዚህ ሰለባ ሆና የመጀመሪያ ልጇ ሲያይ የ11ኛ ክፍል ትምህርቱን አቁሞ ተሸክሞም ይሁን ጫማ ጠርጎ የእናቱን ህይወት ለመታደግ ይወስናል ። ይህ በእናት ላይ ሌላ ጭንቀት ይሆናል ። የሱም ውሳኔ ከምኞት ያለፈ አልሆነም ። ለእናቱ ወይስ ለወንድሞቹ ወይስ ለቤት ኪራይ ለየትኛው ይድረስ ? መልስ ያጣ ጥያቄ እናቱ ደግሞ በጣም ጥሩጥሩ ምግብ ያስፈልጋታል ለመድሃኒቱ !!!!! መድሃኒቱ ከ1ኛ ደረጃ እስከ 7ኛ ያለውን ወስዳ ስምንተኛውና የመጨረሻው ይቀራታል ። ሐኪሞች የመጨረሻው መድሃኒት ወስደሽ ወዲያው ካልተቆረጠ ወደ አጠቃላይ ሰውነትሽ ተሰራጭቶ ህይወትሽ አደጋ ላይ ይወድቃል አሉዋት ። ጥቁር አንበሳ ወረፋ ስለሆነ በግል መቆረጥ አለበት ነው ያሉት ። በመሆኑም ልጆቼን እያለች የጣር ጩኸት እያሰማች ትገኛለች ። አላህ ብሎ እኛን ሰበብ አድርጎን ብትድን ከህመሟ እስክታገግም የልጆቿና የሷ ቀለብ የቤት ኪራይ ጡቷ ከተቆረጠ በኋላ የጨረር ህክምናና የመሳሰሉት ዙሪያ ገደል እንዲሆኑባት ያደረጉባት ነገሮች በአላህ ፍቃድ እኛ ከተረባረብን አላህ ህይወቷን አትርፎ ልጆቿን አሳድጋ መልካም ቦታ ደርሰው ማየት ትችል ይሆናል ። ሴቶች ፣ ሴት ልጅ ያለን ፣ እናት ያለን ፣ ሚስት ያለን ፣ እህት ያለን ይህን ፁፍ አንብበን ማለፍ የለብንም ። ለእህታችን መትረፍ ሰበብ እንሁን ። የእህታችን መዲና አካውንት ንግድ ባንክ 1000282991695 መዲና ደምሴ በአካል ማግኘትና ያለችበትን ሁኔታ ማየት ለሚፈልግ ስልክ ቁጥር 0940787737
Hammasini ko'rsatish...
የወረቀት ብር ኖት ዘካ ~~~ በጥንት መን ሰዎች ግብይት የሚፈፅሙት እቃን በእቃ በመለዋወጥ ነበር። የልውውጥ ገበያ ለአጠቃቀም አስቸጋሪ በመሆኑ የተነሳ ቀስ በቀስ እየቀዘቀዘ ሄዶ አንዳንድ እቃዎችን (ለምሳሌ በሃገራችን አሞሌ ጨው) እንደመገበያያ ገንዘብ በመጠቃቀም ተተካ። ይሁን እንጂ እነዚህ እቃዎች ለአያያዝ አስቸጋሪ በመሆናቸው የተነሳ ሰዎች ወደ ሌሎች አማራጮች ማማተር ይጀምራሉ። በዚህም የተነሳ ነበር ወርቅና ብር ለመገበያያነት መዋል የጀመሩት። ወርቅና ብር ታዲያ በጊዜ ሂደት በአንጣሪዎች አማካኝነት ተመሳሳይ መጠንና ክብደት እንዲይዙ ተደርገው ለአስተማማኝነታቸው ማህተም ዲዛይን ተደርጎባቸው መዘጋጀት ያዙ። እነዚህን ገንዘቦች ለደህንነታቸው በመስጋት ገንዘብ መንዛሪዎችና አንጥረኞች ዘንድ በማስቀመጥ መተማመኛ ደረሰኞችን በምትካቸው ይቀበሉ ነበር። ሰዎች በነዚህ ድርጅቶች ላይ ያላቸው እምነት በጨመረ ቁጥር ደርሰኞቹ በግብይት ላይ ለክፍያ መዋል ያዙ። የወረቀት ብር ኖት ታሪካዊ አነሳሱ በዚህ መልኩ ነበር። በጊዜው እነዚህ ከገንዘብ መንዛሪ ድርጅቶች የሚመጡ ወረቀቶች ሰውየው በነዚህ የግል ድርጅቶች ዘንድ ወርቅ/ ብር እንዳስቀመጠ በመግለፅ ወረቀቱን የተቀበለ ሰው ሄዶ ወርቁን/ ብሩን መውሰድ እንደሚችል ከመጠቆም ባለፈ ኦፊሴላዊ ይዘትም ሆነ የህግ ከለላ አልነበራቸውም። አገልግሎታቸው በሰፋ ቁጥር ግን በጊዜ ሂደት መንግስታት የህግ ሽፋን ሊሰጡ ግድ ብሏቸዋል። በዚህን ጊዜ የታወቀ ተመን በመስጠት ላምጪው እንዲከፈል አስገዳጅ ህግ ወጣ። የማተሙ/ የማሳተሙ ኃላፊነትም የመንግስታት ሆነ። ይህ ነገር የተጀመረው በ1833 እንደሆነ ድርሳናት ይጠቁማሉ። (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር ነው።) መንግስታት ካላቸው ተቀማጭ የወርቅ መጠን በላይ እነዚህን የወረቀት መገበያያዎች ገበያ ላይ ሲያቀርቡ ጊዜ ግን በነባሩ የወርቅ መገበያያ ላይ ፈተና ተደቀነ። በዚህን ጊዜ የወረቀት መገበያያዎችን ወደ ወርቅ ከመቀየር የሚከለክል ህግ መውጣት ያዘ። በዚህ ረገድ ቀዳሚዋ ብሪታኒያ ስትሆን ይህ የሆነውም በ1931 ነበር። አሜሪካ በ1934 ተከተለቻት። የክልከላው ተግባራዊነት ግን ድንበር ተሻጋሪ ሳይሆን በሃገራቱ ውስጥ የተገደበ ነበር። ሃገራት ከሃገራት ጋር ሲገበያዩ ግን የወረቀት ብሩን ወደ ወርቅ የመቀየር ውላቸውን ይጠብቁ ነበር። ከ1971 ጀምሮ ግን የወርቅ መጠን እያነሰ ስለመጣ አሜሪካ ይህንኛውን አሰራር ጭምር አቆመች። የመጨረሻው ወርቅን ለግብይት ተመን የመጠቀም አሰራር በዚህ መልኩ ተዘጋ። የወረቀት ብር ኖት እነዚህን ታሪካዊ ለውጦች በማሳለፉ የተነሳ ምንነቱን በመግለፅ ላይ የኢስላም ምሁራን እይታቸው ሊለያይ ችሏል። የብዙሃን ዑለማዎችን አቋም ብቻ ሳሰፍር የወረቀት ብር ማለት እራሱን የቻለ የተለየ መገበያያ ገንዘብ ሲሆን ወርቅና ብርን (ሲልቨር) የሚመለከቱ ህጎች ይመለከቱታል። የየሃገራቱ የወረቀት ኖት እራሱን የቻለ አንዱ ከሌላው የሚለይ ገንዘብ ነው። ለማሳጠር ስል ለዚህ ትርጓሜ የሚውሉ አጋዥ መረጃዎችን አልጠቅስም። እነዚህ የወረቀት ብር ኖት ሲጀመሩ አካባቢ ዘካ ይወጅብባቸዋል ወይስ አይወጅብባቸውም በሚለው ላይ በኢስላም ምሁራን መካከል ውዝግብ ተከስቶ ነበር። የልዩነቱ መነሻ ለዚህ ገንዘብ ምንነት የተሰጡ ትርጓሜዎች መለያየት ነበር። ነገር ግን ይሄ መገበያያ በከፍተኛ መጠን በመስፋፋቱና የወርቅና የብርን ቦታ በመተካቱ የተነሳ ውዝግቡ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ከስሟል። ስለዚህ ትኩረታችን ይህ የወረቀት ብር ኖት ለዘካ መጠን በሚደርስበት መነሻ ተመን (ኒሷብ) ላይ ይገደባል ማለት ነው። የወረቀት ብር ኖት ዘካ የሚወጅብበት መነሻው ተመን (ኒሷብ) ስንት ነው? በዚህ ላይ ሶስት የተለያዩ ሃሳቦች ተሰንዝረዋል። አንደኛ:– የወረቀት መገበያያ ኖት መነሻ የዘካ ተመን የብር (ሲልቨር፣ ፊዷ) ኒሷብ ነው ያሉ አሉ። ይህም 200 ዲርሃም ማለትም 595 ግራም ነው። ሁለተኛ:– ኒሷቡ የወርቅ ኒሷብ ማለትም 20 ዲናር ውይም 85 ግራም ነው ያሉም አሉ። ሶስተኛ:– መነሻው መጠን ከወርቅና ከብር መነሻ ተመኖች ዝቅ ያለው ነው ያሉም አሉ። ከሶስቱ ሃሳቦች ውስጥ ሶስተኛው ሚዛን የሚደፋ እንደሆነ በርካታ ዑለማዎች ደምድመዋል። መነሻቸውም:– 1ኛ፦ ድሃዎቹን የተሻለ ተጠቃሚ ያደርጋል። 2ኛ፦ ለዘካ አውጪውም ከውዝግብ ቀጠና ለመውጣት፣ ከተጠያቂነት ስጋት ለመትረፍ ይበልጥ ሰላማዊ ነው። 3ኛ፦ የመጀምሪያዎቹን ሁለት አቋሞች ያንፀባረቁ ምሁራን የሚያቀርቧቸውን መርጃዎችና ትንታኔዎች አንፃራዊ በሆነ መልኩ የተሻለ የሚያቀራርብ ነው። 4ኛ፦ ለዚህ የወረቀት መገበያያ ኖት የዘካ ተመን ከወርቅና ከብር (ሲልቨር) አንዱን መጠቀም ግድ ከሆነ ከሁለት አንዱ ቀድሞ የደረሰውን ኒሷብ በምን አሳማኝ መነሻ ልንዘለው እንችላለን? እንደሚታወቀው የብር (ሲልቨር) ኒሷብ ዛሬም በነብዩ ﷺ ዘመን ከነበረው አይቀየርም። ዛሬም እንደ ጥንቱ 200 ዲርሃም ማለትም 595 ግራም ብር ያለው ሰው ዘካ ማውጣት ግድ ይለዋል። ይህ አቋም የሰዑዲያ የታላላቅ ዑለማእ ምክር ቤት፣ የእውቀታዊ ምርምር ቋሚ ኮሚቴ (ለጅነተ ዳኢማህ)፣ በራቢጦተል ዓለሚል ኢስላሚ ስር ያለው ቀራረል መጅመዒል ፊቅሂይ እና የሌሎችም ምርጫ ነው። የዘንድሮ የወረቀት ብር ዘካ መነሻ (ሂሳብ) ስንት ነው? ````````
`````````
የሚችል ሰው
ወቅታዊን የወርቅና የብር ዋጋ አጣርቶ በራሱ ማስላት ይችላል። በኔ በኩል በተወሰኑ ወንድሞች አማካኝነት ለማጣራት እንደሞከርኩት ወቅታዊ (የ 2014) ወርቅ የሚሸጥበት ዋጋ በግራም ከ 3800 እስከ 4,500 ብር ነው። የብር መሸጫ ዋጋ ደግሞ ከ 120 እስከ 150 ብር ነው። ስለዚህ፡ [ሀ] የወርቅ ዘካ ኒሷብ የሆነውን 20 ዲናር (85 ግራም) በወቅቱ ዋጋ 3,800 ብር ስናባዛው 323,000 ብር ሲሆን [ለ] የብር ዘካ ኒሷብ ደግሞ 200 ዲርሃም (595 ግራም) በወቅቱ ዋጋ 120 ብር ሲባዛ 71,400 ብር ይሆናል። ስለዚህ ከሁለቱ ኒሷቦች የብሩ ስለሚያንስ ከላይ በቀረበው 3ኛው አቋም መሰረት ለዚህ አመት (1443 ሂጅሪያ) ይህንን መጠን 71,400 መነሻ እናደርጋለን ማለት ነው። እናም 71,400 ብር እና የበለጠ አመት የቆየ ብር ያለው ሰው ዘካ ማውጣት ግድ ይለዋል ማለት ነው። ስለሆነም ለዘካ መጠን የደረሰ ገንዘብ ኖሮት አመት ከቆየ የገንዘቡን የ1/10ኛውን እሩብ ማለትም 2.5% ዘካ ያወጣል ማለት ነው። ስሌቱን ግልፅ ለማድረግ ጥቂት ምሳሌዎችን ልስጥ፦ 1– አመት የዞረ 300,000 ብር ያለው ሰው የ 300,000ን 2.5% ያወጣል፡፡ 300,000 x 0.025=7,500 ብር 2– አመት የዞረ 450,000 ብር ያለው ሰው የ 450,000ን 2.5% ያወጣል፡፡ 450,000 x 0.025=11,250 ብር 3– አመት የዞረ 5 ሚሊዮን ብር ያለው ሰው የ 5,000,000ን 2.5% ያወጣል፡፡ 5,000,000 x 0.025=125,000 ብር ይሆናል ማለት ነው። ወይም ደግሞ አጠቃላይ ገንዘቡን ለ40 ቢያካፍለው ማውጣት ያለበትን የዘካ መጠን ይሰጠዋል። የቀረቡትን ምሳሌዎች ለ40 ቢያካፈል ተመሳሳይ መጠን ያገኛል። ማሳሰቢያ፦ ~ በብሄራዊ ባንክ በኩል የሚወጣውን የወርቅና የብር ዋጋ ያልተጠቀምኩት ህዝብ የሚገባያይበት ትክክለኛ ዋጋ ነው ብየ ስላላመንኩበት ነው። ወሏሁ አዕለም። (ረመዳን 15/1442፣ ሚያዚያ 20/ 2013) https://t.me/IbnuMunewor
Hammasini ko'rsatish...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

دروس وفوائد ابن منور

የተለያዩ ወቅታዊ ወሳኝ መልእክቶች ➡️ በሱና ላይ ለመፅናት የሚረዱ ሰበቦች ➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷ https://t.me/AbumuslimAlarsi/8716 https://t.me/AbumuslimAlarsi/8716 ➡️ "ይህ ነው አቋማችን" ወቅታዊ ጉዳዮች ➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷ https://t.me/Muhammedsirage/2315 https://t.me/Muhammedsirage/2315 ➡️ "እራስን መመልከት" ወሳኝ ፅሁፍ ➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷ https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/6519 https://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru/6519 ➡️ "ለሱና እህቶች ትውስታ" ወሳኝ ግጥም ➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷ https://t.me/nuredinal_arebi/12299 https://t.me/nuredinal_arebi/12299 ➡️ "ረድ በሻኪር ሱልጣን ላይ" ክፍል አንድ ➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷ https://t.me/UstazKedirAhmed/6794 https://t.me/UstazKedirAhmed/6794 ➡️ "ፊዮሽ መርከዝ" ላይ የተቀጠፈ ቅጥፈት ➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷ https://t.me/IbnuMuhammedzeyn/966 https://t.me/IbnuMuhammedzeyn/966 ➡️ ጥቂት ነጥቦች ለኢልም ፈላጊዎች ➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷ https://t.me/IbnuMunewor/2894 https://t.me/IbnuMunewor/2894 ➡️ "ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር" ➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷ https://t.me/Abulbuhari/178 https://t.me/Abulbuhari/178 ♦️ሼር በማድረግ የኸይር ሰበብ ሁኑ
Hammasini ko'rsatish...
አሰላምአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ውድ የሱና ወንድሞችና እህቶች በሀገር ውስጥም በውጭም ያላችሁ በሙሉ ይህ ከታች ተለቆ የምታዩት ቪዲዬ በኮምቦልቻ ከተማ አንሷር መስጅድ ያለው የደረሶች ማደሪያ ፤ መፀዳጃ ቤት የህፃናት መድረሳ እና የእህቶች የቂርአት ቦታ ተብሎ ተጀምሮ በፋይናስ እጥረት ምክንያት ባለበት ቦታ እንዲቆም ተገደናል ። ቢያንስ ይህ መስጅድ አሁን ላይ ከ80 በላይ አዳሪ ደረሶችን (በቦታ ጥበት ምክንያት ተጨማሪ እየመለስን) በተመላላሽ ከ100 በላይ የአካባቢ ህፃናትን እና በረካታ የሴት እህቶቻችን ጀመዓ እና የሱናው ማህረሰብ በውስጡ አቅፎ ድናዊ የሆኑ ትምህርቶችን እየሰጠ ቢሆንም በአንዳንድ መሰረታዊ ነገሮች ጉድለት ምክንያት እና ያለ ምንም ገቢ የሚንቀሳቀስ በመሆኑ መስጅዱ የተፈለገበትን ጉዞ ሊጓዝ አልቻለም ። አሁን ላይ ካለው ከፍተኛ ቦታ እጥረት የተነሳ የደረሶችን ማደሪያ ቀንቀን ለህፃናት የመቅሪያ ቦታ እየተጠቀምን አንገኛለን። ደረሶች የማደሪያ ቦታቸው በቂ ስላልሆነ በግቢው ውስጥ የላስቲክ ቤቶችን በመስራትእንድሁም መስጅድ ውስጠ በማደር ያሳልፋሉ። ከስር የተለቀቀውን ቪዲዮ ስታዩ የበለጠ ትረዳለችሁ ብዬ አምናለሁ ።ራሱ ይናገራል። ለአላህ ብላችሁ ይህ ቪዲዬ ተመልክቱት 👇👇👇👇👇 ▶ ቪዲዬ ቁጥር አንድ https://t.me/Ye_kombolcha_Ansuar_Mesjid_Jemea/2480ቪዲዬ ቁጥር ሁለት https://t.me/Ye_kombolcha_Ansuar_Mesjid_Jemea/2482ቪዲዬ ቁጥር ሶስት https://t.me/Ye_kombolcha_Ansuar_Mesjid_Jemea/2481ቪዲዬ ቁጥር አራት የመጨረሻው https://t.me/Ye_kombolcha_Ansuar_Mesjid_Jemea/2479 የሚገረመው የሚደቀው በዚህ ብቸኛ የሱና መስጅድ ከየቦታው ከየክፍለ ሃገሩ ለመጡ ለዚህ ሁላ ደረሳ በዚህ ብቸኛ የሱና መስጅድ ውስጥ በአንድ ሸይኽ እና በአጋዥ ኡስታዞች ብቻ ነውአገልግሎት እየተሰጠ የሚገኝ ነው ። እሱም አጥጋቢ ባለመሆኑም ሰፋ አድርገን ልንስራ በማሰብና በማቀድ ሃሳብና ትበብራችሁን ልትለግሱን ዘንድ ወደ እናንተው ይዘነው መተናል። ስለሆነም ይህንን ጀመዓ ካሉበት ጊዜያዊ ችግሮች እና በዘላቂነት የራሱ የሆነ የገቢ ምንጭ በመፍጠር ምናልባትም በዚህ ሰአት ሰፊ ርብርብ በማድረግ የተሻለ ገቢ በመሰብሰብ ቋሚ የገቢ ምንጭ በመፍጠር ሁለተኛ ወደ ልመና መግባት ሳያስፈልግው የጀመረውን ከፍተኛ አላማ ይህም ትክክለኛውነ የእስልምና አሰተምህሮ አና መንገድ ለህብረተሰቡ ማድረስ፤የዳዕዋ እና የኢልም ማእከል እንድሆን ፤የሂፍዝ ማእከላት መክፈት፤ተጨማሪ የመስጅድ እና መድረሳወችን የማስፋፋት እና መሰል አላማወችን ከግብ ለማድረስ የሁላችንም ሀላፊነት ነውና የሁላችንንም ረብርብ ይጠይቃል።ስለሆነም ሁላችንም በቻልነው ዛሬ የነገ ቤታችንን እንገንባ፣በሚያልቅ እና አላቂ በሆነው ገንዘባችን ዛሬ ላይ ጠፊ በሆነችው ዱንያ ላይ ሆነን ከሞት በሗላ ላለው ዘላለማዊ ህይወት እናስቀድም።አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ በሰጠን እድል እንጠቀምበት።በዚህ አይነት መልካም ስራ ላይ መመካከር እና መተጋገዝ በራሱ እድለኝነት ስለሆነ ። አላህ ያግዘን!!!!!! የዚህ ጀመአ አባል ሁናችሁ ቪዲዬን አለመመለከት አይቻልም ። ሸር በማድረግም የበኩላችሁን ድርሻ ተወጡ ። ወደ ግሩፑ ለመቀላቀል 👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Ye_kombolcha_Ansuar_Mesjid_Jemea ወደ ቻናሉ ለመቀላቀል 👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/kombolcha_Ansuarmesjid_channel
Hammasini ko'rsatish...
የኮምቦልቻ አህለ ሱና አንሷር መስጅድ ጀመዓ ግሩፕ መርዳት ለፈለጉ የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ 1000 35 19 72 94 8 ሰይድ ሙሐመድ ሸይኽ አህመድ እና ሰይድ እንድሪስ

ቁጥር አንድ ▼ ይህ የምትመለከቱት የደረሶች አንደኛው ማደሪያችው ይህ ነው ▼ በዚች ክላስ ውስጥ ቢያንስ ከ 40 እስከ 50 በላይ ደረሶች ያርፋባታል ። ▶ በተጨማሪም ቀን ቀን ላይ ደግሞ ህፃናቶች በምታዩት ክላስ ውስጥ ይቀራሉ ። ውስጡ ብታዬት በጣም በሚያሳዝን መልኩ ምን ያህል ተቸግረው እውቀትን ለመፈለግ እንደሚጥሩ ያሳያል ። የበለጠ ደግሞ ቪዲዬዎን ብታዪት ትረዳላችሁ ብየ አስባለሁ ። ቪዲዬውን በአላህ ተመልከቱት

https://t.me/Ye_kombolcha_Ansuar_Mesjid_Jemea

#መልእክት_ለባለ_ቴሌ_ግራም_ቻናሎች <>=====<>====<> ለ ወንድማችን ሳዳት ከማል ለኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ለኡስታዝ ሙሀመድ ሲራጅ ለኡስታዝ ኸድር አቡ ሓቲም ለዶክተር ሰዒድ ሙሳ ለወንድም አቡል ዐባስ ናሲር ለኡስታዝ አቡ ሙስሊም ለወንድም ኑረድን አረብ ለወንድም አቡ ረይስ ለወንድም ፉአድ ሙሀመድ ለወንድ አቡ ኡሰይሚን ለወንድም ኢብኑ ኸይሩ ለወንድም አቡ አዩብ ለወንድም አቡ ሂበቲላህ ለየመን ወንድሞች #ለሌሎችም_ስማቹህ_ላልተጠቀሳቹህ ወንድምና እህቶች ይህንን ከስር የማያይዘውን ሊንክ ሼር በማድረግ መስጊዱን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማድረስ የቡኩላችን ድርሻ እንወጣ ስል በአሏህ ስም እጠይቃለሁ #መልእክቱን_እንዳስተላልፍ_ያዘዙኝ የኮምልቻ በርበሬ ወንዝ አንሷር መስጊድ አስተባባሪዎችና ተገልጋዮች ናቸው ባረከሏሁ ፊኩም። t.me/Ye_kombolcha_Ansuar_Mesjid_Jemea
Hammasini ko'rsatish...
የኮምቦልቻ አህለ ሱና አንሷር መስጅድ ጀመዓ ግሩፕ መርዳት ለፈለጉ የኢትዩጵያ ንግድ ባንክ 1000 35 19 72 94 8 ሰይድ ሙሐመድ ሸይኽ አህመድ እና ሰይድ እንድሪስ

የግሩፑ አለማ :- በኮምቦልቻ ከተማ አንሷር መስጅድ ያለውን ሁለተናዊ ችግር በማየት በተለይም በመስጅዱ ውስጥ ካሉት ደረሳዎች ብዛት አንፃር ያለውን የማደሪያ ቦታ እጥረት ችግር ፣ የመድረሳ የማስፋፋት ስራዎችንና የመስጅዱ የቀሩ ውሳጣዊና ውጫዊ ችግሮችን በመቅርፍ ላይ ለመተባበር የተከፈተ የገቢ ማሰባሰቢያ ግሩፕ ነው ።

Boshqa reja tanlang

Joriy rejangiz faqat 5 ta kanal uchun analitika imkoniyatini beradi. Ko'proq olish uchun, iltimos, boshqa reja tanlang.