💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
Kanalga Telegram’da o‘tish
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Ko'proq ko'rsatish8 856
Obunachilar
+224 soatlar
+357 kun
-330 kun
Postlar arxiv
ይችን አያ እናስተንትናት!
👈(أيهم أحسن عملا)
" የትኞቹ ስራን አሳማሪ እንደሆኑ ለመፈተን ነው ።
የትኞቹ ብዙ ስራ እንደሚሰሩ አላለም።ምክንያቱም ሚፈለገው ስራን ማብዛት ሳይሆን ማሳመር(ለአላህ ብሎ መስራት) ነውና !🔖ከደጋግ ቀደምቶች መንደር ለእህቶች አርኣያ የምትሆን ድንቅ ሴት!!
———
ኢብኑል ጀውዚ (ረሒመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
«ሰያር (ረሒመሁላህ) ከሪያህ ረሒመሁላህ እንዲህ ማለቱን ዘገበልኝ:-
ሪያህ:- “አንዲትን እንስት ተጠቆምኩኝ እና አገባሁዋት። ሁሌም የዒሻ ሶላት ሰግዳ እንደጨረሰች ሽቶ ላይዋ ላይ ትነሰንስና፤ ራሷን በእጣን አጥና (ተቆነጃጅታ) ምርጥ ልብሷን ትለብስና ወደኔ በመቅረብ ...
“አንዳች ፍላጎት አለህን?” ብላ ትጠይቀኛለች። መልሴ “አዎን” ከሆነ አብራኝ ትቆያለች “አይ” ከሆነም ምርጡን ልብሷን ትቀይርና እስከ ንጋት ድረስ በሶላት ታሳልፋለች።»
ሪያህ እንዲህ ሲል ይጨምራል:-
"በአላህ ይሁንብኝ! በጣም ነውያስደሰተችኝ!"
[ሲፈቱ ሰፍወህ ገፅ:116]
~
አንቺስ እህቴ በዒባዳሽ ምን ያህል ብርቱ ነሽ?፣ ወይስ ካገባሽ በኋላ ደርስ ትተሽ፣ ከዒባዳሽ ተዘናግተሽ፣ ለዱኒያ መንገብገብሽና ጭንቀትሽ ጨምሯል??፣ ባለ ቤትሽን ከሀራም ለመጠበቅና በአንቺ ድክመት ሰበብ ሌላ እንዳይመኝ ለባለቤትሽ ምን ያህል ትቆነጃጂያለሽ? ሀቁን ጠብቀሽ ምን ያህል ታዝናኚዋለሽ? ወይስ ካገባሽው በኋላ እራስሽን ጥለሽ የቤት እቃሽን ውበት ነው ምትጠብቂው?
አስቢበት!!። ከደጋግ ቀደምቶች መንድር ይህቺን ድንቅ ሴት ከትዳር ጋር ዒባዳን በማጣጣም በዒባዳ ላይ በመበርታትና ድንቅ በሆነው የባል አያያዟ አርኣያ አድርጊያት!!። መልካም ሴት ማለት:- መልእክተኛው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሷሊህ ብለው የጠሯትና ሷሊህ የሆኑ ወንዶች የሚደሰቱባት፣በጥሩ የሚዘክሯት ሴት ናት!!
منقول✔ ባጣሽው ነገር አትዘኚ የፈለግሽውን አግኝተሽ ቢሆን ኖሮ የበለጠ ልታዝኚ ትችይ ይሆናል! የአሏህ ውሳኔዎችን ውደጂ ጥበብ የተሞሉ ረቂቅ ሚስጥሮች ናቸው።
#እህቴ_ሆይ
ሂጃብ ሁለት አይነት ነው
☀️አንደኛው ትኩረትን ከመሳብ የሚሸፍን ሂጃብ ሲሆን....
☀️ሌላው ደግሞ ትኩረትን የሚስብ ሂጃብ ነው።
ከነዚህ ሂጃብ ውስጥ የትኛው ነው ሂጃብሽ???
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
👉ባለቻናሎች ለምን ጨከናችሁ⁉️
«ሁሌም የሱና ቻናሎች ለሙስሊሞች ድምፅ አይሆኑም ለምን ...እንዴ የሙስሊሙ ግፍ አይታያችሁም ነው⁉️
👉ለምንድነው ሰው በክፉ እንድመለከታችሁ የምታደርጉት⁉️
👉ሙስሊሙ ከዚህ በላይ ምን አይነት በደል ይድረስበት ⁉️
«ቢያንስ ሌላው ቢቀር «ኢና ሊላሒ ወኢና ኢለይሒ ራጂዑን»አይባልም ወይ‼️«የሙስሊሞችን ግፍ የሚያስተጋባው ኢብኑ_ሙነወር ብቻ ነው ብሎ ያቀራችሁ ማነው⁉️ ቆይ እንደት ነው የሚያስችላችሁ⁉️ በምን አቅም ነው ወገናችሁ እያለሸ ፀጥ ለማለት የጨከናችሁት⁉️ 🛑እስኪ ከልምዳችሁ ለኔም ንገሩኝ እኔም ዝም ልበል...አላስችል እያለኝ እንጂኮ እኔም እንደናንተ ዝም ብል ...እህህህ ግን አያስችለኝም በቃ‼️ ⭕️ስለ ሙስሊሙ ብትጮሁ ቻናላችሁ ይቀንሳል⁉️ ⭕️ስለሚሞተው ወገናችሁ ድምፅ ብቶኑ #ከሱና ትወጣላችሁ⁉️ 🛑ስለ ሙስሊሞች በደል ብትናገሩ #ከሰለፍያ የሚያባርራችሁ ሰው አለ⁉️ ....በአሏህ ምን ሆናችሁ ነው⁉️ ....ለምንድነው ሳንፈልግ እንድንናገራችሁ የምታደርጉን⁉️ እንወዳችኋለን እናከብራችኋለን ግን ስንሞት ስንገደል ቢያንስ ሀዘናችሁን አሳውቁን በአሏህ⁉️ 👉የሱና ሰዎች አዛኝ እንጂ ጨካኝ አይደሉም 👉የሐቅ ሰውች የተግባር እንጂ የወሬ ሰዎች አይደሉም። 👉ሰለፍዮች ከማንም ላይ ሩህሩህ እንጂ የወገናቸው በደል የማይሰማቸው አይደሉም። 🛑«የሙስሊሙ በደል አይመለከታችሁም ነው⁉️ 🛑«የሙስሊሙ መገ*ደል አያሳዜናችሁም ንገሩን⁉️ ....ፀጥ ማለታችሁ መስለሀው ምንድነው⁉️ የአፄ ዩሀንስ የቦሩ ሜዳ ጭፍጨፋ የአፄ ሚኒሊክ የጨለንቆ ግፍ የሀረር ሙስሊሞች የጂምላ እልቂት በአንዴ የተከሰተ አይደለምኮ .....ለምን ታሪክ አታነቡም⁉️ ልክ እንደ አሁኑ በየትም ቦታ ሙስሊሙን እየመረጡ በዘግናኝ ሁኔታ በመ*ግደል ካስፈራሩ በኋላ በመጨረሻ ሀይላቸውን አሰልፈው ተነጋግረውና ተናበው ቦታና ቀን መርጠው...ግፋቸውን ይፈፅማሉ ....አሁንም ዝግጂት ላይ ናቸው። ⭕️ወላሒ ሀታ በዚህ በስደት እንኳን የተቃወማቸውን #ገዳይ_እስኳድ አላቸው በዚህ ልክ ነው #የተደራጁት ልንገራችሁ። ሙስሊም ባለ ቻናሎች ለምንድነው የሚስሊሙን በደል የማታሰራጩት ምንድነው ያስጨከናችሁ ነገር⁉️ ምን እየጠበቃችሁ ነው⁉️ ምንስ ነው አላማችሁ⁉️ 🛑#ሰለፍይ አያዝንም እንዴ 🛑ሰለፍይ ወጣት የሙስሊም በደል አያመውም እንዴ⁉️ በስም እጠራለሁ ወላሒ ምን ያክል እንደምወዳችሁ ታውቃላችሁ ወላሒ ለሱና ወንድሞቼ ነፍስን እንኳን አልሰስትላችሁም ግን በሙስሊሙ መበደል ላይ እጂግ ችልተኛ ናችሁ ለምን⁉️ 👉ሰለፍያ ሁሌ ስለትዳር መፃፍ ብቻ ነው እንዴ‼️ 👉የሰለፍዮች አላማ ስለ ሴቶች እየፃፉ ቻናላቸውን ማሳደግ ብቻ ነው እንዴ⁉️ ⭕️በዚህ ወቅት ለወገናችሁ ድምፅ ካልሆናችሁ ለመቼ ነው የምትደርሱልን⁉️ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi
•የኔ ልባም ሴት🌸👈
» ልባም መሆን ማለት ዝምተኛ መሆን ማለት አይደለም፤ ልባምነት ማለት መቼ መናገርና መቼ ዝም ማለት እንዳለብሽ ማወቅ ነው። የኔ ልባም ሴት፣ አንቺ በዙሪያሽ ላሉት ሰዎች ብርሃን፣ ለቤተሰብሽ መከታ፣ ለራስሽ ደግሞ ኩራት ነሽ።
» ብዙ ፈተናዎች ሊገጥሙሽ ይችላሉ፣ አለም ተስፋ እንድትቆርጪ ሊገፋፋሽ ይችላል። ነገር ግን አንቺ ውስጥ ያለው ያ የማይበገር የልባምነት መንፈስ "ገና ነኝ!" ይልሻል። እራስሽን ውደጂ፣ እውቀትሽን አሳድጊ፣ እናም በምትሄጂበት መንገድ ሁሉ በልበ ሙሉነት ተራመጂ።
» አንቺ የጥበብ ምንጭ፣ የጽናት ተምሳሌት ነሽ።ዛሬ የምታደርጊው ጥቃቅን በጎ ነገር ነገ ትልቅ ታሪክ ሆኖ ይነበባል። በርቺ፣ የኔ ልባም ሴት!
=
t.me/https_Asselefya1
ይህ መልእክት
አሁንም ትኩረት ስጡት በብልግና ቪዲዮ ተታለው ብዙዎች አካውንታቸው እየተጠለፈ ነው። ከዛ በናንተ አካውንት የብልግና ምስል በመላክም ሰዎችን አዛ እያደረጉ ነው።አላህ ይጠብቀን🔖قال ابن عباس رضي الله عنهما:
~የቁርአን ሰዎች ቁርአን ላይ የሚገባውን ሀቅ ቢወጡለትና በአግባቡ ቢይዙት አላህ በወደዳቸው ነበር
~ነገር ግን በቁርአናቸው ዱንያን ፈለጉበትና አላህም ጠላቸው ሰዎች ዘንድም ያነሱ ሆኑ
📙 تفسير القرطبي [٢٠/١]
t.me/https_Asselfya
ሸይኹል-ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ይላሉ፦
"ብልህ ሰው ማለት መልካሙን ከመጥፎው የሚያውቅ ሳይሆን ከሁለት መልካም ነገሮች የሚሻለውን መልካም የሚያውቅ እና ከሁለት መጥፎዎች የሚከፋውን መጥፎ (የሚለይ) ነው።"
(መጅሙዑል-ፈታዋ 20/54)
=
የቴሌግራም ቻናል
t.me/AbulbukhariSeid
ኡመር ኢብኑል'ኸጥ'ጧብ -رضـــي الله عنه- እንዲህ ይላሉ፦
➻አንድ ሰው በአላህ ከማመን ብኋላ መልካም ስነ-ምግባር ካላት፣ ተወዳጅ እና ብዙ ምትወልድ ከሆነች ሴት የበለጠ መልካም ነገር አልተጠቀመም።
📚[ሰሂህ ኢብን አቢይ ሸይባህ (27/174)]
የሚልኩትን ሊንክ አትንኩ እህቶች
ትላንት የአንዷ ተጠልፎ ሸር ሲደረግ ነበረ ዛሬ ደግሞ የሌላዋ ተጠንቀቁ!
ላልሰሙትም እያደረስን
ያገኛችሁትን ሊንክ ሳታስተውሉ አትንኩ።
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
📣 ታላቅ ብስራት የደውራ ፕሮግራም ጥሪ!
✅ በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘው የአንሷር መስጂድ ለ 4 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ እጅግ ደማቅ እና ታላቅ የኮርስ ፕሮግራም አዘጋጅቶ ለመላው ሙስሊም ወንድሞች እና እህቶች ጥሪውን ያቀርባል።
📚 የፕሮግራሙ ልዩ እንግዳ፦
ታላቁ የ-የመን ሙሓዲስ ፈደይለቱ ሸይኽ ዐሊ አል-ራዚሒ (ሀፊዘሁላህ) —(በየመን የሚገኘውና በርካታ ተማሪዎችን ያፈራው የታዋቂው የመዕበር መርከዝ አስተማሪ)
◈እንድሁም ትልቁ አባታችን ፈደይለቱ ሸይኽ ሙሳ አል-ቀጧን (ሀፊዘሁላህ) ይገኛሉ።
🎙️ በፕሮግራሙ ላይ የሚታደሙ መሻይኾች እና ኡስታዞች፦
▪️ ሸይኽ ሙሐመድ መኪን ከደሴ
▪️ ሸይኽ ጀማል ዘሀቢ ከደሴ
▪️ ሸይኽ ሙሐመድ ሰዒድ ከደሴ
▪️ ሸይኽ ይማም ሰዒድ ከደሴ
▪️ ሸይኽ አሕመድ አወቀ ከደሴ
▪️ ሸይኽ በድሩ ዩሱፍ ከደሴ
▪️ ሸይኽ ሙሐመድ ሁሴን ከቢስቲማ
▪️ ሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ ከደሴ
▪️ ሸይኽ ሙሐመድ አሚን ከደሴ
▪️ ሸይኽ ሐሰን አሊ ቃዲ ከደሴ
▪️ ሸይኽ ሁሰይን አቡ ሶላሑዲን ከደሴ
▪️ ሸይኽ አወል አሕመድ መነዮ ከመረሳ
▪️ ሸይኽ አወል አህመድ ከከሚሴ
▪️ሸይኽ ዒሳ አደም ከደሴ
🔸 ዶክተር /ኡ ሁሴን አሊ ከከላላ
🔸 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ከአ.አበባ
🔸 ዶክተር/ኡ ሰዒድ ሙሳ ከአ.አበባ
🔸 ኡስታዝ ኸድር አሕመድ ከከሚሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሒዛም ከአዳማ
🔸 ኡስታዝ ዐብደሽኩር ከአሶሳ
🔸ኡስታዝ ዐብዱሰላም ሐሰን ከአዳማ
🔸 ኡስታዝ አቡ ዒምራን ከሀርቡ
🔸 ኡስታዝ አቡ አዩብ ከኮቦልቻ
🔸 ኡስታዝ ሙርሰል ከደሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሻኪር ከኮንቦልቻ
🔸 ኡስታዝ አቡ ረያን ከመርሳ
🔸ኡስታዝ መሀመድ አያሌው ከወልዲያ
🔸ኡስታዝ አቡ ዓብዱ ረዛቅ ጅረሳ ከመርሳ
🔸 ኡስታዝ አቡ ዑበይዳ ከኬሚሴ
🔸 ኡስታዝ ዐብዱልመሊክ ከኬሚሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሐሳን ከኮቦልቻ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሃኒፋ ከኬሚሴ
🔸 ኡስታዝ መ/ሲራጁ ከኬሚሴ
🔸 ኡስታዝ ዐሊይ ሰይድ ከደሴ
🔸 ኡስታዝ አንሷር መሀመድ ከደሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሐፍሷ ከደሴ
🔸ኡስታዝ ጀውሀር ክፍሌ ከደሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ዐብዲረሕማን ከመርሳ
🔸 ኡስታዝ አቡል መዓሊ ከመርሳ
🔸 ኡስታዝ አቡ ሹራ ከደሴ
🔸 ኡስታዝ አቡ ማሂ ከኮንቦልቻ
🔸 ወንድም አቡ ሂበቲላህ ከደሴ
👥 የአንሷር መስጅድ ኢማምና ጀመዓዎቹ ባጠቃላይ...
👤እንዲሁም ሌሎች ከተለያየ ሀገር በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው መሻይኾችና ኡስታዞችም በቦታው ይገኛሉ!
📆 የፕሮግራሙ ቀናት፦
የመጀመሪያ ቀን፦ ሰኔ 6/2018 (ከፊታችን ቅዳሜ ጧት 3:00) ጀምሮ ለ 4 ተከታታይ ቀናት ይቆያል።
🏘 ማሳሰቢያ፦
ለታዳሚዎች በቂ የምግብ እና የመኝታ ቦታ ተዘጋጅቷል።—የሌሊት ብርድ ልብስ ይዛችሁ ብትመጡ መልካም ነው።—
🤩በእነዚህ የቴሌ ግራም አድራሻ ሙሉ ስም እና ስልክ ቁጥር በመላክ ይመዝገቡ፦
📝ኡስታዝ አቡ ሻኪራ አህመድኑር
@Abuhureirehonline
0923467646
📝 ኡስታዝ አቡ ዐዩብ
092 588 7118
@Attewhid11
📝 ወንድም አቡ ሂበቲላህ ሁሰይን
@Abu_Hibetillah_Al_aseriy
0942819970
💙የቦታው አቅጣጫ ካስቸገራችሁ በነዚህ የእንግዳ ተቀባይ ወንድሞች ስልክ ቁጥሮች ላይ ይደውሉ፡
📞 ወንድም አንዋር
0916582567
📞 ወንድም አቡ አማር
0913803997
📞 ወንድም ሰኢድ
0935568513
🔖 የተዉሒድ ጥቅም !
⓵ )በቀጣይ አለም ከቅጣት ሰላም መሆን ደህንነት ማግኘት ነዉ።
⓶)በዱኒያ በቀጥተኛዉ መንገድ የተመሩ መሆን ነዉ።
⓷)ወንጀሎችን መሰረዙ ነዉ ።
الَّذِينَ آمَنُوا وَلَمْ يَلْبِسُوا إِيمَانَهُمْ بِظُلْمٍ أُولَئِكَ لَهُمُ الْأَمْنُ وَهُمْ مُهْتَدُونَ} [الأنعام
~
t.me/https_Asselfya
በእስልምና (በሸሪዓ) እይታ፣ በስራ ቦታም ሆነ በማንኛውም የህይወት ዘርፍ ሰውን መመቀኘት (ሀሰድ) በጥብቅ የተከለከለ (ሀራም) እና በጣም አደገኛ የስነ-ልቦና በሽታ ነው።
ሸሪዓው በስራ ቦታ ለሚፈጠር ምቀኝነት ልዩ ትኩረት ይሰጣል፤ ምክንያቱም ስራ የሰው ልጅ ሲሳይ (ርዝቅ) የሚፈልግበት እና ከሰዎች ጋር በቅርበት የሚገነባበት መድረክ በመሆኑ፣ እዚህ ቦታ ላይ የሚፈጠር ምቀኝነት የስራ አካባቢን መርዛማ ከማድረጉም በላይ የአንድን ሙስሊም እምነት (ኢማን) ያበላሻል።
በስራ ጉዳይ ላይ የሚንጸባረቅን ምቀኝነት የሸሪዓ መነጽር በሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ያስረዳናል፦
### 1. የ"ሀሰድ" (የምቀኝነት) ትርጉም በሸሪዓ
በእስልምና ምቀኝነት ማለት፡ "አላህ ለአንድ ሰው የሰጠው ጸጋ (ደሞዝ፣ ማዕረግ፣ እውቀት፣ የስራ ስኬት) ከእሱ ላይ ተነስቶ ለእኔ ቢሰጠኝ ወይም ዝም ብሎ ቢጠፋለት" ብሎ መመኘት ነው።
* አንድ ባልደረባዎ በስራው ጎበዝ ሆኖ ሲመሰገን ወይም ሲያድግ በውስጥዎ መጨነቅ እና ውድቀቱን መመኘት የሀሰድ መገለጫ ነው።
### 2. ምቀኝነት በሸሪዓ የተከለከለበት ዋና ዋና ምክንያቶች
* ከአላህ ውሳኔ (ቀድር) ጋር መጣላት፦ አላህ በቁርኣኑ ላይ እንዲህ ይላል፡-
> *"በቁርጠኝነት እኛ በመካከላቸው የዚህችን ዓለም ኑሮአቸውን አካፈልን፤ ከፊላቸውም ከፊሉን ታዛዥ አድርጎ እንዲይዝ ከፊላቸውን ከከፊሉ በላይ በደረጃዎች ከፍ አደረግን።"* (አል-ዙኽሩፍ: 32)
> ስለዚህ የአንድን ሰው የስራ ስኬት መጥላት፣ አላህ ለዛ ሰው የወሰነውን ሲሳይ እና እውቀት እንደመቃወም ይቆጠራል።
>
* መልካም ስራን ማጥፋቱ፦ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦
> *"ምቀኝነትን ተጠንቀቁ፤ እሳት እንጨትን እንደምትበላ ሁሉ ምቀኝነትም መልካም ስራዎችን ትበላለችና።"* (አቡ ዳውድ)
> አንድ ሰው ስራውን በአግባቡ ቢሰራም፣ ቢሰግድም፣ ቢጾምም በውስጡ ምቀኝነት ካለ መልካም ምንዳው (አጅሩ) ይበላሻል።
>
* ሙስሊሞችን መጉዳት መከልከሉ፦ በሀዲስ ላይ *"አትመቃቀኑ፣ አትጣሉ፣ የላህ ባሮች ወንድማማቾች ሁኑ"* ተብሏል። በስራ ቦታ ሰውን ለመጣል ወሬ ማማት፣ ስሙን ማጥፋት ወይም ስራው እንዳይሳካ ማሰናከል ትልቅ ወንጀል ነው።
### 3. በሸሪዓ የተፈቀደው "ምቀኝነት" (ግبطة - ฆิบጠህ)
እስልምና በበጎ ነገር መቅናትን እና መወዳደርን ይፈቅዳል። "ጚብጠህ" ማለት፦ "ያ ሰው ባለው የስራ ብቃት፣ ታማኝነት ወይም ማዕረግ ደስተኛ መሆን፣ ነገር ግን 'እሱ እንዳለ ሆኖ አላህ ለእኔም እንደሱ አይነት ስኬት ቢሰጠኝ' ብሎ መመኘት እና ለዛ መጣር" ነው።
ይህ ጤናማ የስራ ውድድር (ሙናፈሰህ) ስለሚፈጥር በሸሪዓ የተወደደ ነው።
### 4. በስራ ቦታ ከምቀኝነት ለመንጻት ምን መደረግ አለበት?
1. ርዝቅ ከአላህ መሆኑን ማመን፦ ያ ሰው ስላገኘ የእርስዎ ሲሳይ አይቀንስም። አላህ ለእርስዎ የጻፈው ነገር በማንም ተጽእኖ እንደማይቀር ማወቅ።
2. ዱዓ ማድረግ፦ ለዚያ ለተቀናቃኝዎ ወይም ለበላይዎ ስኬት በውስጥዎ ዱዓ ማድረግ። ይህ በውስጥ ያለን የበታችነት ስሜት እና ምቀኝነትን ያጠፋል።
3. በራስ ስራ ላይ ማተኮር፦ የሰውን ስህተት ከመፈለግ ይልቅ የራስን ብቃት ማሳደግ እና በሃላል መንገድ ለመግፋት መጣር።
ባጭሩ በስራ ቦታ ሰውን መመቀኘት በዱንያም የስራ ሰላምን ያውካል፣ በአኺራም ከአላህ ዘንድ ቅጣትን ያስከትላል። የስራ ባልደረባ ሲያድግ "ማሻአላህ" ብሎ መመረቅ እና ለራስም ስኬትን ከአላህ መለመን የሙስሊም ባህሪ ነው።
🖊 በአቡ አኢሻ 1447/ذوالحجة/22።
t.me/Abuebrahim22322
t.me/Abuebrahim22322
