💎🎀«المرأة الصالحة كنز من كنوز الدنيا»💎🎀
Kanalga Telegram’da o‘tish
💎ሀያዕ ሲወሳ ለሴት ልጅ ጌጧ ነውና ሁሌም አብራ ትወሳለች፣ #ሴት ልጅና #ሀያዕ አብረው የሚኖሩ መቼም የማይነጣጠሉ ጥምሮች ናቸው። 👉 ሴት ልጅ ስትፈጠርም በሀያዕ ዘውድ አሸብርቃ ነው። 💎ይህንን ዘውድ ከራሷ የገፈፈች ሴት ግን ህያው ከሆኑ ሰዎች መሀል እንደምትንቀሳቀስ በድን ትሆናለች።
Ko'proq ko'rsatish8 843
Obunachilar
+824 soatlar
+237 kun
-3530 kun
Postlar arxiv
~ራስን ከብዙዎች የከፋ አድርጎ ማሰብ ወደ ተሻለ አቋም ለመሻገር ይጠቅማል ።
በርካታ አማኞች በተቅዋና በመልካም ስራዎች ቀድመውናል እያሉ ማሠብ ለቀልብ ተሃድሶ ያግዛል ። ወደ መልካም ስራዎች ለመነሳት ይረዳል ።
ራስን ከብዙዎች የተሻለ አድርጎ ማሰብ የተከለከለ ነገር ከመሆኑ ጋር ጎታች እና ጎጂ ሃሣብ ነው ።
የተሻለውን አዋቂው አላህ ነው ::
ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ
👉ልብህ ሲደክማት ...
๏ ፍላጎት ነፍስህን ሲያሸንፋት
๏ መጥፎ ሀሳቦች መጥተውልህ
ወንጀሉን ስራው ብለው ሲጎተጉቱህ
እንዲህ በላቸው.
﴿قُلْ إِنِّي أَخَافُ إِنْ عَصَيْتُ رَبِّي عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ﴾
« እኔ በጌታዬ ባምጽ የታላቁን ቀን ቅጣት
እፈራለሁ » በላቸው ፡፡
[አንዓም 15]
~ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ደስታ ብለህ
ላልተወሰኑ ጊዜያት እሳት እንዳትገባ ።
ነገ ሰኞ ነው!❕
☑️ በተከበረ ወር ላይ ነን
❝የቻለ ይፁም፤ ያልቻለ ደግሞ ሌሎች ይፆሙ ዘንድ ያስታውስ።❞
ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፡-
❝ማንኛውም የአላህ ባሪያ ለአንድ ቀን በአላህ መንገድ የፆመ አላህ በዚህ ቀን ምክንያት ፊቱን ከእሳት (ከጀሀነም) እስከ ሰባ አመት ድረስ ያርቃል።❞
● [ صحيح مسلم ١١٥٣]
➡️ጾም ከብዙ መጥፎ ነገር ይገድባል።
➡️ ስሜትን ያስራል ።
➡️ እይታን ከሀራም ያርቃል ።
➡️ ከጀነት አንዱን በር ይዟል ።
كَيْفَ تَصْلُحُ لَكَ الذُّرِّيَّةُ؟
قال الشيخ عبدالرزاق البدر حفظه الله:
"لَا يُمْكِنُ أَنْ يَصْلُحَ لَكَ فَرْدٌ مِنْ أَفْرَادِ ذُرِّيَّتِكَ إِلَّا إِذَا أَصْلَحَهُ اللَّهُ لَكَ، مَهْمَا اجْتَهَدْتَ فِي تَأْدِيبِهِ وَتَرْبِيَتِهِ وَأَطْرِهِ عَلَى الْحَقِّ.. وَإِلْزَامِهِ بِالِاسْتِقَامَةِ لَا يُمْكِنُ أَنْ يَسْتَقِيمَ وَيَصْلُحَ إِلَّا إِذَا أَصْلَحَهُ اللَّهُ لَكَ... فَالْهَادِي هُوَ اللَّهُ.... وَالْمُوَفِّقُ هُوَ اللَّهُ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى.
وَلِهَذَا يَنْبَغِي عَلَى الْمُسْلِمِ أَنْ يَعْظُمَ رَجَاؤُهُ بِاللَّهِ.. وَسُؤَالُهُ لِلَّهِ وَإِلْحَاحُهُ عَلَى اللَّهِ ـ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى ـ أَنْ يُصْلِحَ ذُرِّيَّتَهُ...
فَهَا هُوَ خَلِيلُ الرَّحْمَنِ فِي دُعَائِهِ يَقُولُ: {رَبَّنَا وَاجْعَلْنَا مُسْلِمَيْنِ لَكَ وَمِن ذُرِّيَّتِنَا أُمَّةً مُّسْلِمَةً لَّكَ}."
📚 تفسير آيات من القرآن لشيخ الإسلام (16:40).
قال الشّيخ السّعدي رحمه اللّٰه:
"من تركَ معاصي لله ونفسُه تشتهِيها ؛ عوَّضه اللّٰهُ إيمانًا في قلبِه ، وسعةً وانشراحًا وبركةً في رزقِه ، وصحّةً في بدنِه ".
"الفواكه الشّهية" (١٣٨/١) .
አኺራን እናስታውስ
ሙሐመድሲራጅ ሙ. ኑር
https://t.me/MerkezulimamiAhmed
ኢማም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ይላሉ:-❝ በዱንያ ላይ ያለ እውነተኛ ጀነት (ደስታ) አላህን ማወቅ፣ እሱን መውደድና እሱን በማውሳት መረጋጋት ነው። ❞
Repost from 📱[ انتبه أنت مراقب ] 📲
🔑 ልቤን ጠየቁት
ከየት ነበር ህመም ሁሉ የጀመረኝ ?
መለሰልኝ ፦
አላህን ከራቅበት ቀን ጀምሮ ።
@sleslkachin
☑️
ዚክር ማለት ባንተና በአላህ መካከል ያለ ቀጥታ ወደሱ የሚያደርስህ ክፍት በር ነው። ይህን በር ከዚክር በመዘናጋት እንዳትዘጋው።
#قال_الإمام_ابن_القيم_رحمه الله تعالى
الذكر هو باب الله الأعظم المفتوح بينه وبين عبده مالم يغلقه العبد بغفلته.
📚 (مدارج السالكين 2 / 46)
t.me/https_AsselfyaRepost from قناة ابن محمد الولوي (abu abdirehman)
ኢማም ኢብኑል ቀዪም (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦
«ከሸይጣን ታላላቅ ተንኮሎች መካከል አንዱ፡ ለአሽራኮች (ለአጋሪዎች) ሰዎች የሚያከብሩትን የተከበረ ቀብር ያቆምላቸዋል። ከዚያም ከአላህ ውጭ የሚመለክ ጣዖት ያደርገዋል። በመቀጠልም ወደ ወዳጆቹ (እንዲህ ሲል) መመሪያን ያስተላልፋል (ያጠናውታል)፦ “ይህን ቀብር ከመመለክ፣ (በዓል ተደርጎ) መፋሰሻ ከመደረግና ጣዖት ሆኖ ከመያዝ የከለከለ ሰው፤ እርሱማ የሟቹን ደረጃ አሳንሷል፣ ሐቁንም በድሏል (አጉድሏል)” ይላቸዋል።
በዚህም ምክንያት እነዚያ መሃይም የሆኑት አሽራኮች ያንን ሰው ለመግደልና ለመቅጣት ይጣጣራሉ፣ ያከፍሩታልም። እሱ በአጋሪዎች ዘንድ ያለበት ወንጀል፡ አላህና መልክተኛው ያዘዙበትን ማዘዙ፣ እንዲሁም አላህና መልክተኛው የከለከሉትን መከልከሉ ብቻ ነው፤ ይኸውም ቀብሩን ጣዖትና (የአምልኮ) በዓል ከማድረግ፣ በላዩ ላይ መብራት (ሻማ) ከመለኮስ፣ በላዩ ላይ መስጊዶችንና ጉልላቶችን (ቁባዎችን) ከመገንባት፣ በኖራ ከመለሰን፣ ከፍ አድርጎ ከመገንባት፣ ከመሳም፣ (በረካ ለመፈለግ) ከመሻሸት፣ እርሱን (ቀብሩን) ከመለመን፣ ወይም በርሱ (በሟቹ ጃህ) ከመለመን፣ ወይም ወደ እርሱ (ለዚያ ተብሎ) ጉዞ ከመጓዝ፣ ወይም ከአላህ ውጭ ከእርሱ እገዛን ከመጠየቅ (ኢስቲጋሣ ከማድረግ) መከልከሉ ነው። እነዚህ ሁሉ ነገሮች አላህ መልክተኛውን የላከበትን አላማ — ይኸውም ተውሒድን ለአላህ ብቻ ማጥረትንና ከአላህ ውጭ ሌላ እንዳይመለክ የተላኩበትን መሰረት — የሚፃረሩ መሆናቸው ከእስልምና ዲን በግልጽና በግድ (በአስገዳጅ እውቀት) የሚታወቁ ጉዳዮች ናቸው።
ተውሒድን አጥባቂው (ሙዋሒዱ) ሰው ይህንን በከለከለ ጊዜ አሽራኮች ይቆጣሉ፣ ልቦቻቸውም ይሸበራሉ (ይጸየፋሉ)። እንዲህም ይላሉ፦ “እርሱማ የከፍተኛ ማዕረግ ባለቤቶችን (ደረጃ) አሳንሷል፤ ለእነርሱ ምንም ክብርና ደረጃ እንደሌላቸውም ሞግቷል!” ይላሉ። ይህም (የሸይጣን ማታለያ) በመሃይማን፣ በዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎችና ወደ እውቀትና ዲን በሚያስጠጉ በብዙ ሰዎች ነፍስ ውስጥ ይሰርጻል። በዚህም ሳቢያ የተውሒድ ሰዎችን ጠላት ያደርጋሉ፣ ታላላቅ (የሃሰት) ወንጀሎችንም ይለጥፉባቸዋል፣ ሰዎችንም ከእነርሱ ያሸሻሉ። በአንጻሩ የአሽራኮችን (የአጋሪዎችን) ወገን ይወዳሉ፣ ያከብሯቸዋልም፤ እነርሱ ራሳቸው የአላህ ወዳጆች (አውሊያኦች)፣ የዲኑና የመልክተኛው ረዳቶች እንደሆኑም ይሞግታሉ (ያምናሉ)!
አላህ ግን ይህንን እምቢ ይላል! እነርሱ ፈጽሞ የእርሱ ወዳጆች አይደሉም፤ የእርሱ ወዳጆች እኮ እነዚያ አላህን የሚፈሩት (ሙተቁን)፣ እርሱን የተከተሉት፣ ከእርሱ (ትዕዛዝ) ጋር የተስማሙት፣ እርሱ ይዞት የመጣውን ያወቁትና ወደ እርሱ የሚጣሩት ብቻ ናቸው። እነዚያ ባልተሰጣቸው ነገር ተለባብሰው (የሌላቸውን ትልቅነት አውርተው) የሐሰት ልብስን እንደለበሱት፣ ሰዎችን ከነቢያቸው ሱና እንደሚያግዱትና (መንገዷን) ጠማማ ለማድረግ እንደሚፈልጉት፣ እነርሱም መልካም እየሠሩ ይመስላቸዋል (እንደነዚህ ያሉትማ የአላህ ወዳጆች ሊሆኑ አይችሉም)!»
📚 ኢጋሠቱል ለህፋን [1/384]
