uz
Feedback
Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት

Kanalga Telegram’da o‘tish

የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት analitikasi

Finote Hiwot የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት (@finotehiwott) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 15 366 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 5 631-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 191-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 15 366 obunachiga ega bo‘ldi.

20 Iyun, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni -39 ga, so‘nggi 24 soatda esa -5 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 22.39% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 7.98% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 3 441 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 226 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 22 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
የቀጨኔ መድኃኔዓለም ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት ነሐሴ 26/ 1958 ዓ.ም ተመሠረተ።

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 21 Iyun, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

15 366
Obunachilar
-524 soatlar
+297 kunlar
-3930 kunlar
Postlar arxiv
++++#ታላቍ_መቃርዮስ_እንዲህ_አሉ#+++++ ጥላቻ የሚመጣው ቂምን ወይም ክፉን ከመሰወር ነው፣ ክፉን መሰወር ደግሞ ከኩራት፣ ኩራት ከግብዝነት፣ ግብዝነት ከእምነት ጉድለት፣ የእምነት ጉድለት ከልብ ድንዛዜ፣ የልብ ድንዛዜ ከቸልተኝነት፣ ቸልተኝኀት ከስንፍና፣ ስንፍና ከተስፋ መቁረጥ፣ ተስፋ መቁረጥ ከትዕግሥት ማጣት፣ ትዕግሥት ማጣት ከትዕቢት ይመጣል። ጸሎት በፍቅር ላይ ይመሠረታል፣ ፍቅር ደግሞ በደስታ፣ ደስታ ደግሞ በቅንነት፣ ቅንነት በትሕትና፣ ትሕትና በአገልግሎት፣ አገልግሎት በተስፋ፣ ተስፋ በእምነት፣ እምነት በመታዘዝ፣ መታዘዝ በግልጸኝነት ወይም ራስን ቀለል በማድረግ ላይ ይመሠረታል። Ven. Macarius the Great https://t.me/phronema

#ምስባክ #መጻጕዕ ዘመጋቢት ፳፪ የምስባኩንና የመዝሙሩን ዜማ በተራኪ አፕ ጣቢያችን ያድምጡ https://terakiapp.page.link/h6JfpJoTT5HgXr9d9
#ምስባክ #መጻጕዕ ዘመጋቢት ፳፪ የምስባኩንና የመዝሙሩን ዜማ በተራኪ አፕ ጣቢያችን ያድምጡ https://terakiapp.page.link/h6JfpJoTT5HgXr9d9

ድንግል ሆይ ! ሰማይ በስፋቱ ብራና ቢሆን ባሕርም ቀለም ቢሆን ምስጋና የተመላውን ክብርሽን ገናንንትሽን ለመጻፍ በዚህም ምስጋናሽን ለመፈጸም አልችልም ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ #Orthodox_Quo
ድንግል ሆይ ! ሰማይ በስፋቱ ብራና ቢሆን ባሕርም ቀለም ቢሆን ምስጋና የተመላውን ክብርሽን ገናንንትሽን ለመጻፍ በዚህም ምስጋናሽን ለመፈጸም አልችልም ፡፡ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ #Orthodox_Quotes

የሰንበት ትምህርት ቤታችን የዘውትር አገልጋይን ዲ/ን ዮሴፍ ሰውነት #ታስሯል ። ++++++ ወንድማችን ዲያቆን ዮሴፍ ፍሥሓ ሰውነት [Yosef Fiseha Sewunet]፥ በነገረ መለኮት ምሩቅነቱ ፣ በታሪክ መምህርነቱ እና በሚድያ ባለ ሙያነቱ ከሚሰገው አገልግሎት ባሻገር ለቤተ ክርስቲያን አንድነት፣ ለሀገር ዕድገት፣ ለሰዎች ስኬት የሚጨነቅ ቀና ወንድም ነው። ይኼን እውነትም በፌስ ቡክ ገጹ ከሚጽፋቸው መልእክታቱ መረዳት ይቻላል። በተለይም ትውልዱ ቁም ነገር አዘል መጻሕፍትን እንዲያነብ ለማትጋት በሚያደርገው ወደር የለሽ ጥረት ይታወቃል። ለዚኽም ዐዳዲስ መጻሕፍት በታተሙ ቍጥር ይዘታቸውን እያስተዋወቀ፣ አንባብያንን አወዳድሮ እያሸለመ፣ ከፍ ሲልም በሚድያ እያቀረበ የሚሠራው በጎ ሥራ ማስረጃ ነው። ከማንም ምንም ጥቅም ሳያገኝ በነጻ ይኼን ኹሉ ማድረጉ፥ ቅንነቱን ያሳያል። ወንድማችን ዮሴፍ፥ ከዚኽ በጎ አስተዋፅኦው ባለፈ በቤተ ክርስቲያንም በሀገርም ጉዳይ የሚያየውን ክፍተት በምክንያት ይተቻል። ጥሩ ሥራ ተሠርቶ ሲያይ ደግሞ ያደንቃል። በድብቅ ማሤርን እና ነገር መሥራትን ግን ይጸየፋል። ከቅንነቱ በተጨማሪ ይኼ ሰብእናው ይማርከኛል። እንዲኽ ዐይነት ሰው ጠላት እንደሚበዛበት በራሴ ስለ ተማርኹም ሕይወቱ ያሳዝነኛል። ይኼ ቅን ወንድማችን፥ በቅርቡ በፌስ ቡክ በጻፈው ፖለቲካዊ ሒስ ምክንያት ለእስር መዳረጉን ከራሱ አንደበት አረጋግጫለኹ። መታሰሩን ቶሎ ባለ መስማቴ ለመጠየቅ ብዘገይም፥ በዛሬው ዕለት፥ ከኹለት ወንድሞች ጋራ ፖሊስ ጣቢያ ሔጄ ጠይቄዋለኹ። ለብዙ ሰው የሚጠቅም ሐሳብ ያለው ወንድማችን ማንም ሳይጠይቀው በመሰንበቱም አዝኛለኹ። በእርግጥ የእውነት አምላክ እንደማይለየው አምናለኹ። ዛሬ ልንጠይቀው በሔድን ጊዜ ከራሱ አንደበት እንደ ሰማኹት፥ ዲያቆን ዮሴፍ፥ በፌስ ቡክ በጻፈው ፖለቲካ ነክ አስተያየት ምክንያት፥ ከመጋቢት ፱ ቀን ፳፻፲፮ ዐ.ም ጀምሮ፥ ከዐዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አጠገብ [ግቢ ውስጥ] በሚገኘው ሦስተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ሰንብቷል። የሚፈታበትን ቀንም በተስፋ ይጠባበቃል። ፖሊስ ክስ ባይመሠረትበትም ያሰረው በጽሑፉ ምክንያት መኾኑን ግን ነግሮታል። ይኸውም ወቅታዊ ጉዳይ ነው። የታሰረበት ምክንያት ወቅታዊ ጉዳይ እንደ መኾኑ፥ በግልጽ ሳይከሰስ፣ ጉዳዩም ለፍርድ ቤት ሳይቀርብ ያለ ጠያቂ በፖሊስ ጣቢያ ሊቆይ ይችላል። ይኼ ኹኔታ ደግሞ በወንድማችን ላይ ሥነ ልቡናዊ ጕዳት ያመጣል። ከሥራውም ከኑሮውም በከንቱ ይስተጓጐላል። ከዚኽም በላይ የብቸኝነት እና የባይተዋርነት ስሜት ሊሰማው ይችላል። ይኼ ኹሉ ጣጣ በወንድማችን ላይ ከመድረሱ በፊት ኹላችንም ድምፅ ኾነን ልናስፈታው ይገባል። በመጨረሻም በመንግሥትም በግልም ተቋማት የምትሠሩ ኦርቶዶክሳውያን፥ ይልቁንም የሕግ ባለ ሙያዎች፥ ከሚመለከተው አካል ጋራ በመነጋገር ዮሴፍን እንድታስፈቱት፤ የእስር ጊዜው ያጥር ዘንድም እንድትፋጠኑለት፤ በአጠቃላይ መላው ኦርቶዶክሳውያን፥ የዮሴፍ አምላክ በሰላም ያስፈታው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንድንጮኽለት በወንድምነት ስሜት እጠይቃለኹ!! መውጫ ቅኑ ወንድሜ ዮሴፍ ሆዬ፥ መታሰርኽን ከሰማኹባት ሰዓት ጀምሬ ስለ አንተ ተጨንቄአለኹ። እውነትን ይዘኽ የምትሞግት፣ በሰው ስኬት የምትደሰት፣ በሰው ላይ ክፉ ነገር የማትዶልት ቅን ወንድም መኾንክን ዐውቃለኹና። ስለዚኽም እስራትኽ እስራቴ፣ ጭንቀትኽ ጭንቀቴ ነው። ከልቤ የጻፍኹት ይኽ መልእክቴ ፍሬ አፍርቶ በቅርቡ እንደምትፈታ ተስፋ አደርጋለኹ። በተረፈ ስሙ ስምኽ ነውና የዮሴፍ አምላክ እንዳይለይኽ ወንድምኽ እመኝልኻለኹ!! © ኤፍሬም የኔሰው