አህሉል ዊርዲ
Kanalga Telegram’da o‘tish
{ادْعُ إِلَىٰ سبِيلِ رَبِّكَ بِالْحِكْمَةِ وَالْمَوْعِظَةِ الْحَسَنَةِ ۖ } ۚ [ወደ ጌታህም መንገድ በጥበብና በጥሩ ምክር ተጣራ።] 🔰የተውሒድ ደርስ 🔰የተዝኪያ ደርስ 🔰የሲራ ደርስ 🔰የሉጋ ፋኢዳ T.me/Ustaz_ebin_Selman Comment👉 https://t.me/Tafach_Tarikoch
Ko'proq ko'rsatish7 919
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-47 kun
-2130 kun
Postlar arxiv
7 917
«ጭር ባለው የዐረቢያ በረሃ ውስጥ በነበርኩበት ወቅት..»ይላሉ መውላ ነስሩዲን ለተሰበሰበው ታዳሚ
«በበረሃው ውስጥ የነበሩትን አስፈሪና ደም የተጠሙ ወንበዴዎች በአንድላይ አሯሯጥኳቸው»
ይህንን የሰማው ታዳሚ በመገረም🙆🏻♀️« እንዴት እንዲህ አደረጉ ሙላ» ብለው በአንድ ድምፅ ጠየቁ
ነስሩዲን መለሱላቸው «ልክ ሲያፈጡብኝ እሮጥኩ..ያኔ እነሱም ከኋላዬ ተሯሯጡ»🤌😂
7 917
🦋✨ይድረስ ለልብህ✨🦋
✍️በረካ ማለት ብዙ ነገር መኖር ማለት አይደለም ይልቅስ ያለው ነገር ጥሩ ተፅዕኖ ማሳደሩ ነው።
ሰው ሰፊ ጊዜ ሊኖረው ይችላል ግና ለራሱ የሚሆን ጊዜ ሊያጣ ይችላል። በቂ ገንዘብ ሊኖረው ይችላል ግና የባለጸግነት ስሜት ላይሰማው ይችላል። ብዙ ነገሮች ሊከቡት ይችላሉ ሆኖም ልቡ የሚጎድለውን ነገር በማሰብ ብቻ ተጠምዶ ይቆያል።
ምክንያቱም በረካ በነገሮች ብዛት ብቻ አይደለም ይልቅስ አላህ በነገሩ ውስጥ በረካን በማኖሩ ባለቤቱ የሚጠቀምበት እና ሌሎችም የሚጠቀሙበት መሆኑ ላይ ነው።
አምላክ እንዲህ ይላል:
🦋✨﴿وَلَوْ أَنَّ أَهْلَ الْقُرَىٰ آمَنُوا وَاتَّقَوْا لَفَتَحْنَا عَلَيْهِم بَرَكَاتٍ مِّنَ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ﴾
«የከተሞቹም ሕዝቦች ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ ከሰማይና ከምድር በረከቶችን በከፈትንላቸው ነበር»
ሀቂቃው በረካ በነገር ላይ ከመጨመር የሰፋ ነው። አላህ በውስጡ የሚያስቀምጠው መልካም ነገር ነው።ተፅዕኖው ይሰፋል..ጥቅሙ ያምራል..ባለቤቱንም ከብዛት ጋር ምንም ግንኙነት በሌለው መንገድ ይበቃዋል።
ለዚህም ነው በረካ በአንዲት ሰዓት ውስጥ ልትኖር የምትችለው በዚያች በቀናት ውስጥ ያልሰራሀውን ነገር ትሰራለህ። አነስ ባለ ገንዘብ ውስጥም ሊኖር ይችላል..በዚ ከሱ የሚበልጠውን ገንዘብ የሚተካ በቂነትና ጥቅም ይኖረዋል።
እጅግ ረጅም ባልሆነ ዕድሜም ውስጥ ሊኖር ይችላል..ግና ከሱ መለየት በኋላ ለባለቤቱ በሚጠቅሙ ነገሮች የተሞላ ይሆናል።
ስለዚህ ሁልጊዜ በህይወትህ ውስጥ ስላደገው ነገር ብቻ አትመልከት..ይልቅስ አላህ ውስጡ ያስቀመጠውን መልካም ነገር ላይ ተመልከት።
እያንዳንዱ ጭማሪ በረካ አይደለም እንዲሁም እያንዳንዱ ማነስ እጦት አይደለም።
ሩህህ በበረካ ሀያት ትለመልምና የዚያ አነስተኛው የብዙ ጥቅም ባለቤት ይሆናል
ብዙውም የብዙ መልካም ነገር ባለቤት ይሆናል🩵
