uz
Feedback
የጥበብ ማዕድ

የጥበብ ማዕድ

Kanalga Telegram’da o‘tish

ዝም ብለህ ተቀላቀል!

Ko'proq ko'rsatish

📈 Telegram kanali የጥበብ ማዕድ analitikasi

የጥበብ ማዕድ (@yetbebmead_ab) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 16 214 obunachidan iborat bo'lib, Din & Maʼnaviyat toifasida 5 264-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 092-o'rinni egallagan.

📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika

невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 16 214 obunachiga ega bo‘ldi.

11 Iyul, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni 587 ga, so‘nggi 24 soatda esa -8 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.

  • Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
  • Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 2.53% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 2.04% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
  • Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 410 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 331 ta ko‘rish yig‘iladi.
  • Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 13 ta reaksiya keladi.

📝 Tavsif va kontent siyosati

Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
ዝም ብለህ ተቀላቀል!

Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 12 Iyul, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Din & Maʼnaviyat toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.

16 214
Obunachilar
-824 soatlar
+397 kunlar
+58730 kunlar
Postlar arxiv
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በስላም አደረሳቹ ቤተሰብ በዓሉ የሰላም እና የደስታ እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ!

ወቀሳን ወደ ሰው፡ ምስጋና ወደ ራስ፡ አንድነት አጣፍተን፡ ራስ መውደድ የባስ። ለዚህ ነው! አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ)

እብድ የሚበልጠውን ይፈራል!

፡ እንግልተ መስቀል ደስታ እንዴት ይሆናል? ብሎ ለሚጠይቅ፡ ጌታ በፍቃዱ ያ'ለም መድን ሆኗል!!! ፡ ከዘላለም ዲን ገንዳ እጆችን ጎተተ፣ ራቁት ሊያለብስ ፡ ገላው ተሸለተ፤ ከደሙ ጠብታ 'መሳዪት ሸተተ! ፡ ያዳም ቀዳማዊ ፡ የጌትነት ሚስጥር፡ አምላክ ነገሰለት፡ በሾህ ተክኖ ከናቁት ፍጥረት ስር!!! ፡ መሪር ተጎነጨ ፡ ልብሱ ተገፈፈ፣ ሰማይ 'አገለደም ፡ 'ላዳም እያለፈ፣ ያቺ መሐል ምድር ፡ ያቺ የራስ ቅል፣ ጌታን ብትበርዘው ፡ በሐሞተ ብቅል፡ ተዓምር አይታለች ፡ ማይሸምተው ሰቅል!!! መልካም የስቅለት በዓል ቤተሰቦች! ✍አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ) 📩 @Abuuuuu_bot

"አንዱ ሰለ ሁሉ ሞተ" (2ኛ ቆሮ ም 5:14) ለመለው የክርስትና ዕምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለቱ መታሰቢ ዕለት በሰላም አደረሳቹ ከወዲሁ መልካም በዓል

ይቆይ እንጂ የኔ ያልከው ፤ ግልጽ የሆንክለት ሰው ወረኛ ብሎ ይሰይምኸል!!!

ህመም ከየሰዉ ስናበላልጥ መዳን እየቻልን ስንቶች ይሆን የሞትን?!

እናቶቻችን ምን ያህል ትዕግስተኛ እንደሆኑ ምታውቀው ዳንቴል ሚባለውን የቁሳት አልባሳትን ሰርተው ካስቀመጡበት አጋጥሞህ ስታይ ነው።

አሉልኝ ፡ ያልኩትን፡ የቆሙ ከበሩ፣ እውነትም ፡ ለማለት፡ መታመም ነው ጥሩ! አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ)

አንዳንዴ ዛሬ ለራስህ ሚገባህን ነፋጊ አትሁን ነገ ላይ ወይ ታልፋለህ ወይ እርሱ ያልፋል፤ቁጭት እንዳይተርፍህ ምንድነው ምትፈልገው? ለምንስ እምቢኝ አልክ? ለራስህ እውነቱን መልስ?!

ጀማሪ ሌባ በየኮሽታው ራሱን ሲያስፈጅ ጀማሪ ሹፌር ደግሞ ተሳፋሪን በአደጋ ባይፈጅ እንኳን የሰቀቀንን ላብ ያስጠምቃል!!!

እሱ ሳይኖር ምትኖር ለማይመስለው ሰው ዳዴን ያስተማረህ እርሱ እንዳልሆነ ንገረው እርሱ ባይኖርም አንተ ትኖራለህ!!!

ብቻነት እንድትበረታም ፣ እንድትነሳ አልያም እንድታንስምና እንድትረከስ ባጠቃለህ ከሕሊናህ እንድትጎድል ያደርግሃል።ጥንቃቄ በጣም ሚያሻው ቦታ ብቻነት ነው!!!

ቀን ማታ እየተመላለሳችሁበት የ 15 ብሩን መንገድ 20 ብር ሰታቹ የ አንድ ሰው ምትሉ ሰዎች ግን ምን ሆናቹ ነው? ወይ ከጎናቹ ሰው የለ?!

ኩራታቸው ከ አንተነትህ ከበለጠ ያንተ መኖር ትርጉም የለሽ ነው! ተጓዝ አንተ ምትፈለግበትን ቦታ ታገኛለህ!!!

የቱንም ነገር መደባበቅ ካበዛህ ለዛ ነገር ያለህን ቦታ ግልጽ እያደረክ ነው። ነገ ደግሞ ሌላኛውን ለመደበቅ ትሔዳለህምና!!!

አለው ማለት ከንቱ፡ አለኝ ማለት መና፣ አርግዞ አይቀርም፡ ይጥላል ደመና፣ ጌጥ አይሆን የያዙት፡ አይጸናም ከመዳፍ፣ ይለቅ ብቻ ማለት፡ አብርቶ እንደ ጧፍ! አቡ(አላዛር ቴዎድሮስ)

መሰበር የጥንካሬ ዋነኛው መለኪያ ነው ስብራቱ ከፍ ሲል ስስነታችን እና መልካሙ ነገራችን ይታያል።

እንደየጉዳዮቹ ስሜትሕን ቶሎ ምትቀያይር ከሆነ ጠንካራ ማንነት ላይኖርህ ይችላል! ጠንካራ ማንነት በመጽናት ውስጥ እንዲሁም በመጋፈጥ ውስጥ ይገኛል! ምናልባት እስስት ጥንካሬዋ መለዋወጧ ስለሆነ እራስህን በሷ ውስጥ እየፈለከው እንደሆነ እንጂ!!!

እንዳትሳሳት ፣ እንዳትገመት ብዙ አታውራ ፤ እንድትፈራ ዝምታ አብዛ!