Apex Sexual Health Clinic 🇪🇹
📈 Telegram kanali Apex Sexual Health Clinic 🇪🇹 analitikasi
Apex Sexual Health Clinic 🇪🇹 (@drshemse) Amxar til segmentidagi kanali faol ishtirokchi. Hozirda hamjamiyat 14 107 obunachidan iborat bo'lib, Tibbiyot toifasida 1 787-o'rinni va Efiopiya mintaqasida 2 395-o'rinni egallagan.
📊 Auditoriya ko‘rsatkichlari va dinamika
невідомо sanasidan buyon loyiha tez o‘sib, 14 107 obunachiga ega bo‘ldi.
07 Iyul, 2026 dagi oxirgi ma’lumotlarga ko‘ra kanal barqaror faollikka ega. Oxirgi 30 kunda obunachilar soni -359 ga, so‘nggi 24 soatda esa -16 ga o‘zgardi va umumiy qamrov yuqori darajada qolmoqda.
- Tasdiqlash holati: Tasdiqlanmagan
- Jalb etish (ER): Auditoriya o‘rtacha 33.48% darajada jalb etiladi. Nashrdan keyingi dastlabki 24 soatda kontent odatda umumiy obunachilar sonining 13.26% ini tashkil etuvchi reaksiyalarni to‘playdi.
- Post qamrovi: Har bir post o‘rtacha 4 723 marta ko‘riladi; birinchi sutkada odatda 1 871 ta ko‘rish yig‘iladi.
- Reaksiyalar va o‘zaro ta’sir: Auditoriya faol: har bir postga o‘rtacha 7 ta reaksiya keladi.
📝 Tavsif va kontent siyosati
Muallif resursni shaxsiy fikrni ifoda etish maydoni sifatida ta’riflaydi:
“Apex Sexual Health Clinic
ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ከጠዋቱ 4-8:30”
Yuqori yangilanish chastotasi (oxirgi ma’lumot 08 Iyul, 2026 da olingan) sababli kanal doimo dolzarb va katta qamrovli bo‘lib qoladi. Analitika auditoriya kontent bilan faol hamkorlik qilishini, uni Tibbiyot toifasidagi muhim ta’sir nuqtasiga aylantirishini ko‘rsatadi.
Ma'lumot yuklanmoqda...
| Sana | Obunachilarni jalb qilish | Esdaliklar | Kanallar | |
| 08 Iyul | +2 | |||
| 07 Iyul | 0 | |||
| 06 Iyul | 0 | |||
| 05 Iyul | 0 | |||
| 04 Iyul | 0 | |||
| 03 Iyul | 0 | |||
| 02 Iyul | 0 | |||
| 01 Iyul | 0 |
| 2 | https://youtu.be/GOB0wJJakC0?si=gZs6E_cNPX_L9FKb | 3 167 |
| 3 | https://youtu.be/GOB0wJJakC0?si=nbFSaGS7siKcB_lu | 1 168 |
| 4 | ✍️ድንገተኛ የወሊድ መከላከያ ወይም ፖስት ፒል ደጋግሞ የመወሰድ ጉዳቶች
👉ድንገተኛ #የወሊድ #መከላከያ ወይም #ፖስት #ፒል በመባል የሚታወቀው ታስቦ የተሰራው ባልታቀደና ባልታሰበ ግንኙነት አማካይነት እርግዝና እንዳይፈጠር ለመከላከል ቢሆንም ብዙ ወጣት ሴቶች ግን እንደ መደበኛ የወሊድ መከላከያነት ሲጠቀሙበት በስፋት ይስተዋላል ።
👉በወር እስከ ሁለት ጊዜ ቢወሰድ ብዙም ችግር የማይፈጥር ቢሆንም በተደጋጋሚ እና ለብዙ ጊዜ ሲወሰድ በርካታ ችግሮችን ሊያመጣ ይችላል ።ከነዚህም መካከል :- #የወር #አበባ #መዛባት :-ጊዜውን ያልጠበቀ፣ከፍተኛ ደም ያለው ወይ ዝቅተኛ ደም ያለው የወር አበባ ሊያስከትል ይችላል ።በአብዛኛው ፔሬድ እስከ ሳምንት ሊያዘገይ ቢችልም ከዛ በላይ ከቆየ ግን እርግዝና ሊሆን ስለሚችል መመርመር ያስፈልጋል ።
✅#ከማህፀን #ውጪ #እርግዝና :-እንደ አጠቃላይ ሲታይ ፖስት ፒል እርግዝናን እና ስለዚህም ከማህፀን ውጪ እርግዝናን የሚቀንስ መሆኑ ይታወቃል ።ነገር ግን አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከፖስት ፒል በኋላ የሚፈጠር እርግዝና ከማህፀን ውጪ የመፈጠር እድሉ ከፍ ይላል ።ከማህፀን ውጪ የተፈጠረ እርግዝና በጊዜ ታውቆ ካልታከመ ለህይወት አስጊ ችግር ነው።
✅ክብደት መጨመር :-ለረጅም ጊዜ ፖስት ፒል በተደጋጋሚ መውሰድ የሰውነት ክብደት እንዲጨምር ሊያደርግ ይችላል
✅#የደም #መርጋት :-በተለይ እድሜ ከ35 በላይ ከሆነ፣ሚያጨሱ፣ወፍራም እና በቤተሰብ የደም መርጋት ችግር ባለባቸው ሴቶች የመከሰት እድሉ ይጨምራል።
በመሆኑም ማንኛውም የወሊድ መቆጣጠሪያ ከመጠቀም በፊት ሐኪም ማማከር ተገቢ ነው። | 3 420 |
| 5 | https://youtu.be/i6P9ODlvK_I?si=zviPuS0buUWJsp19 | 1 365 |
| 6 | የጨብጥ በሽታ (Gonorrhea) ምንድን ነው?
የጨብጥ በሽታ (Gonorrhea) በባክቴሪያ (Neisseria gonorrhoeae) የሚከሰት እና በአብዛኛው በወሲባዊ ግንኙነት የሚተላለፍ በሽታ ነው።
ምልክቶቹ
💠 ሽንት በሚሸኑበት ጊዜ ማቃጠል ወይም ህመም
💠 ከብልት ቢጫ,አረንጓዴ ወይም ነጭ ፈሳሽ መውጣት
💠 በሴቶች የታችኛው ሆድ ህመም
💠 በግብረ ስጋ ግንኙነት ጊዜ ህመም
መንስኤዎች
💠 ከታመመ ሰው ጋር ያልተጠበቀ የወሲብ ግንኙነት (በብልት፣ በአፍ ወይም በፊንጢጣ)
💠 ከእናት ወደ ህፃን በወሊድ ጊዜ መተላለፍ
💠 ከተበከለ ፈሳሽ ጋር ቀጥተኛ ንክኪ
⚠️ ካልታከመ ሊያመጣ የሚችለው
💠 በሴቶች የማህፀን እና የወሊድ መስመር ኢንፌክሽን (PID)
💠 መካንነት በወንዶችም ሆነ በሴቶች
💠 ከማህፀን ውጭ እርግዝና (Ectopic Pregnancy)
💠 ኢንፌክሽኑ ወደ ደም እና ሌሎች አካላት መዛመት
መከላከያ
💠 ኮንዶምን በትክክልና በቋሚነት መጠቀም
💠 አንድ ታማኝ የወሲብ አጋር መኖር
💠 መደበኛ የSTI ምርመራ ማድረግ
💠 ኢንፌክሽን ከተገኘ የወሲብ አጋርንም በአንድነት ማከም
በሽንት ጊዜ ማቃጠል, ከብልት ያልተለመደ ፈሳሽ ወይም ሌሎች የጨብጥ ምልክቶች ካሉብዎ ቶሎ ወደ ጤና ተቋም መሄድ ይኖሩቦታል። | 1 977 |
| 7 | ለማርገዝ የሚረዱ 6 አጋዥ ንጥረ ነገሮች
አዲሱን የ Youtube ቻናል subscribers ያድርጉ https://youtube.com/@4_doctors?si=8XUD1paB7Lmj6Z7_ | 4 776 |
| 8 | https://youtu.be/olW2QSxNuLc?si=HLxRV8njtXw3xREE | 6 384 |
| 9 | ✍️#የስፐርም #ቁጥር #ማነስ #Oligospermia #ምክንያቶች?
👉ወንዶችን ዋነኛው ልጅ እንዳይወልዱ ከሚያረጋቸው ምክንያቶች ውስጥ የስፐርም ቁጥር ማነስ (Oligospermia) አንደኛው ነው። ታዲያ የስፐርም ቁጥር ማነስ (Oligospermia) እንዴት ይመጣል?
✅#የአባላዘር ኢንፌክሽን (Virus)
✅የዘር ፈሳሽ ወደ ሽንት ቧንቧ መመለስ (retrograde ejaculation)
✅የተለያዩ መድሃኒቶች ስንወስድ (beta blocker)
✅#የሆርሞን ችግር
✅መድሃኒቶች እና ኬሚካሎች (ጸረ-አረም፣ የማጽጃ ኬሚካሎች፣ የቀለም ኬሚካሎች)
✅ከመጠን በላይ ሙቀት የዘር ፍሬዎች አካባቢ ማድረግ (ሳውና፣ ሲቲም)
✅ለጎጂ ሱሶች ተጋላጭ መሆን (#ሲጃራ፣ #አልኮል)
✅ከመጠን ያለፈ #ውፍረት
✅የወንድ #የዘር #ፍሬ ላይ ያሉ ደም መላሾች ሲያብጡ (varicocele)
አዲሱን የ Youtube ቻናል subscribers ያድርጉ https://youtube.com/@4_doctors?si=8XUD1paB7Lmj6Z7_ | 6 114 |
| 10 | https://youtu.be/5qiiE80sjs0?si=bQEXr5eP25QETXZ- | 5 065 |
| 11 | የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽንን (UTI) የመከላከያ መንገዶች
የሽንት ቧንቧ ኢንፌክሽን ባክቴሪያዎች ወደ ሽንት ማስተላለፊያ ቱቦ ውስጥ ገብተው ሲባዙ የሚፈጠር ችግር ነው። ይህንን ለመከላከል የሚከተሉትን ማድረግ ያስፈልጋል፦
ብዙ ውሃ መጠጣት፦ በቂ ውሃ በየቀኑ መጠጣት ሽንት በቶሎ ቶሎ እንዲመጣና ባክቴሪያዎችን በሽንት አማካኝነት ጠርጎ እንዲያስወጣ ይረዳል።
ሽንትን አለመያዝ፦ ሽንት ሲመጣ ሳይቆጥቡ ወዲያውኑ መሽናት ያስፈልጋል። ሽንትን ለረጅም ጊዜ አቁሮ ማቆየት ባክቴሪያዎች እንዲራቡ ዕድል ይሰጣል።
ከፊት ወደ ኋላ መታጠብ፦ መጸዳጃ ቤት ከተጠቀሙ በኋላ ሁልጊዜ ከፊት ወደ ኋላ ማበስ ወይም መታጠብ። ይህ ከፊንጢጣ አካባቢ ያሉ ባክቴሪያዎች ወደ ሽንት ቧንቧ እንዳይሻገሩ ይከላከላል።
ከግንኙነት በኋላ መሽናት፦ ከባለቤት ጋር የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ካደረጉ በኋላ ወዲያውኑ መሽናት በግንኙነት ወቅት ወደ ቧንቧው የገቡ ባክቴሪያዎችን ያጥባል።
የውስጥ ሱሪ ምርጫ፦ አየር የሚያስገቡ ከጥጥ (Cotton) የተሰሩ የውስጥ ሱሪዎችን መልበስ እና በጣም ጥብቅ ያሉ ልብሶችን አለማዘውተር።
TenaSeb -ለሴቶች! በስነተዋልዶ እንዲሁም በቆዳ እንክብካቤ ዙርያ በብቁ ባለሞያዋች የተሟላ ህክምና ለሴቶች ይሰጣል።
አዲሱን የ Youtube ቻናል subscribers ያድርጉ https://youtube.com/@4_doctors?si=8XUD1paB7Lmj6Z7_ | 2 782 |
| 12 | የወንድ ድንግልና በምን ይታወቃል | 3 004 |
| 13 | የወንድ የዘር ፍሬ (Sperm) ጥራትን የሚቀንሱ 5 ልማዶች 💠
የወንድ የዘር ፍሬ (Sperm) ጥራት ለወሊድ አቅም ትልቅ ሚና አለው። አንዳንድ የዕለት ተዕለት ልማዶች ግን የዘር ብዛትን,እንቅስቃሴውን እና ቅርጹን ሊጎዱ ይችላሉ።
1️⃣ ማጨስ 🚬
ሲጋራ ማጨስ የዘር ፍሬ ብዛትንና እንቅስቃሴውን ይቀንሳል, በተጨማሪም በDNA ላይ ጉዳት ሊያደርስ ይችላል።
2️⃣ ከመጠን በላይ አልኮል መጠጣት 🍺
ብዙ አልኮል መውሰድ የቴስቶስትሮን መጠንን ያሳንሳል,ይህም የዘር ፍሬ ማምረትን ሊቀንስ ይችላል።
3️⃣ ከፍተኛ ሙቀት መጋለጥ ♨️
ለረጅም ጊዜ ሙቅ ውሃ ውስጥ መቆየት,ሳውና መጠቀም ወይም ላፕቶፕን በጭን ላይ ረጅም ጊዜ ማስቀመጥ የዘር ፍሬ ማምረትን ሊያዳክም ይችላል።
4️⃣ የተመጣጠነ ምግብ አለመመገብ
በቪታሚኖች,ማዕድናት እና አንቲኦክሲዳንቶች የበለፀገ ምግብ አለመመገብ የዘር ፍሬ ጥራትን ሊያሳንስ ይችላል።
5️⃣ ከፍተኛ ውጥረት 😔
ረጅም ጊዜ የሚቆይ ውጥረት የሆርሞን ሚዛንን በማዛባት የዘር ፍሬ ምርትንና ጥራትን ሊጎዳ ይችላል።
✅ መከላከያ
✔️ ማጨስን ማቆም
✔️ አልኮልን በመጠኑ መጠቀም
✔️ ጤናማ ምግብ መመገብ
✔️ መደበኛ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ
✔️ ውጥረትን መቀነስ እና በቂ እንቅልፍ መተኛት
📌 ጥራት ያለው የዘር ፍሬ ለተፈጥሯዊ እርግዝና መፈጠር አስፈላጊ ስለሆነ ጤናማ የኑሮ ዘይቤን መከተል በጣም ጠቃሚ ነው።
📞 ስልክ- 0948339660
📍 አድራሻ- ቦሌ ሚካኤል (የርዋንዳ ታክሲ መያዣ)
አፔክስ የውስጥ ደዌ ክሊኒክ See less | 2 972 |
| 14 | https://youtu.be/6_o2DniE_vo?si=o0Mz-MBdNagYzGWt | 5 570 |
| 15 | Matn yo'q... | 6 107 |
| 16 | ✍️የፖርኖግራፊ ሱስ ምልክቶች
👉የፖርኖግራፊ ሱስ በተለያየ አይነት ምልክቶች ሊታይ ይችላል።
✅ጊዜና ገንዘብን ለፖርኖግራፊ በከፍተኛ ሁኔታ ማዋል። ፖርኖግራፊ ለማየት አላስፈላጊ የሞባይል ካርድ መሙላት፣ ዋይፋይ ያለበት ቦታ መሄድ፣ ከቤተሰብ እና ከጓደኛ ጋር መሆን አለመፈለግ፣ ስራ ለመሰራት ፍላጎት ማጣት።
✅ፖርኖግራፊን ለጭንቀት እና ስሜት ማስተካከያ መጠቀም ይህም ፖርኖግራፊን የተለያዩ ድብርት እና ጭንቀት በሚሰማን ሰዐት ስሜታችንን ማስተካከያነት መጠቀም።
✅ለትክክለኛ ጾታዊ ግንኙነት ፍላጎት ማጣት ይህም ለመደበኛው ወይም ለተቃራኒ ጾታ የወሲብ ፍላጎት ማጣት አንዱ ፖርኖግራፊ ሱስ ምልከት ነው።
✅ፖርኖግራፊ ማየት ያለመፈለግ ነገርግን እራስን መቆጣጠር ያለመቻል ይህም እራስን ለከፍተኛ ፖርኖግራፊ ሱስ ተጋላጭ ስለመሆናቸው ምልከት ይሰጠናል።
✅ከፍቅረኛ ወይም ከትዳር አጋርህ ጋር ወሲባዊ ፍላጎት ማጣት ይህም የተለያዩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት የፖርኖግራፊ ሱስ ተጠቂ የሆነ ባለትዳሮች ፖርኖግራፊ ሱስ ከሌለባቸው ባለትዳሮች 50 ከመቶ የፍቺ ተጋላጭነታቸው ይጨምራል እንዲሁም በትዳር ላይ የመወስለት እድላቸ እስከ 300 ፐርሰንት ይደርሳል።
✅ከፖርኖግራፊ ውጭ ለሌሎች ነገሮች ተነሳሽነት ማጣት ይህም ስራ ለመስራት፣ ከቤተሰብ እና ጓደኛ ጋር ጊዜ ለማሳለፍ አለመፈለግ ወይም ተነሳሽነት ማጣት
✅ፖርኖግራፊ ማየት ለማቆም ይፈልጋሉ ግን አይችሉም ይህም ፖርኖግራፊ ካላዩ ድብርት፣ መነጫነጭ እና ነገሮች ሁሉ ያስጠላዎታል ከዚያም ፖርኖግራፊውን ካዩ በኃላ ደሞ ጸጸት እና ካሁን በኃላ አላይም ብለው ቃል ይገባሉ።
👉እነዚህ ሁሉ ምልክቶች በአጠቃላይ የፖርኖግራፊ ሱስ እንደተያዝን ማሳያ ናቸው። ስለዝህ የፖርኖግራፊ ሱስ እንደማንኛውም ሱስ መታከም ይችላል ከዝህ ጋር በተያያዘም የህክምና ባለሙያ ጋር ሄደው በቂ ምክር እና ክትትል ካደርጉ ከዚህ ሱስ መላቀቅ ይቻላል።
አዲሱን የ Youtube ቻናል subscribers ያድርጉ https://youtube.com/@4_doctors?si=8XUD1paB7Lmj6Z7_
📌ዶ/ር ሸምሴ በአካል ቀጠሮ ለማስያዝ 0948339660 | 6 049 |
| 17 | https://youtu.be/g1FGuzXfQaU?si=vAE-MyCY4GsBOI1m | 2 706 |
| 18 | ጠቃሚ መረጃ
አዲሱን የ Youtube ቻናል subscribers ያድርጉ https://youtube.com/@4_doctors?si=8XUD1paB7Lmj6Z7_ | 2 468 |
| 19 | Matn yo'q... | 4 586 |
| 20 | ✍️የቴስቴስትሮን ወይም የወንድ ሆርሞን ምንድን ነው? እንዴት ሊቀንስ ይችላል?
👉የቴስቴስትሮን ሆርሞን ማለት ወንዶችን ጺም እንዲያበቅሉ ፣ ድምጻችው እንዲጎረንን እና በአጠቃላይ ወንዶችን ወንድ የሚያስመሰል ሆርሞን ነው። ይህ ሆርሞን በሚቀንስበት ወቅት ወንዶች በከፍተኛ ደረጃ ለሰንፈተ ወሲብ ይጋለጣሉ። ከዚህም ጋር በተያያዘ የተለያዩ መንሴዎች ይጠቀሳሉ።
📌ቴስቴስትሮን ሆርሞን እንዴት ይቀንሳል?
✅የመጀመሪያው ከፍተኛ የሰውነት ክብደት መጨመር ሲሆን ይህም ለቴስቴስትሮን መቀነስ ጉልህ ሚና አለው ከዚህም ጋር በተያያዘ የተስትካከለ የሰውነት አቋም ለቴስቴስትሮን ሆርሞን እጅግ ጠቃሚ ነው።
✅ሁለተኛው ሀይለኛ ማንኮራፋት (Obstructive sleep apnea) ያለባችው ሰዎች ሲሆኑ በዝህም የተነሳ የቴስቴስትሮን ሆርሞናቸው ሊቀንስ ይችላል።
✅በሶስተኛ ደረጃ ደግሞ የኤችአይቪ ኤድስ (HIV/AIDS) ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ለረጅም ጊዜ የቆየባቸው ሰዎች ለዝህ ተጋላጭ ናቸው። በተለይም ለረጅም ጊዜ ሳይቆጣጠሩት ሲቀሩ የቴስቴስትሮን መጠናቸው ይቀንሳል።
✅በአራተኛ ደረጃ የስኳር ህመም (Type 2 Diabetes) ታማሚ ከሆኑ እንዲሁ የቴስቴስትሮን ሆርሞን መቀነስ ሊጋለጡ ይችላሉ ። ይህም የሚሆነው የስኳር መጠን ለረጅም ጊዜ ከፍ ብሎ በሚቆይበት ጊዜ ነው። ከዚህም ጋር በተያያዘ የተለያዩ የምንወስዳቸው መድሃኒቶች ለቴስቴስትሮን መጠን መቀነስ ሊያጋልጡን ይችላሉ። 📌በተለይም ለስኳር ህመም ተብሎ የሚወሰደው metformin በከፍተኛ ደረጃ የቴስቴስትሮን መጠን እንዲቀንስ ያደርጋል። ይህንንም ተያይዞ metformin መወሰድ ማቆም ደግሞ የስኳር መጠን እንዲጨምር እና ለሌላ ከባድ አደጋ ያጋልጣል። ከዚህም ጋር በተያያዘ ቁልፍ መፍትሄው ከዶክተር ጋር በመመካከር የስኳር እና የቴስቴስትሮን መጠን መከታተል እናም ደግሞ መድሃኒት በመቀየር መቆጣጠር ይቻላል።
✅በመጨረሻም የልብ ድካም፣ የኩላሊት እና የጉበት ድክመት ያለባቸው ስዎች የቴስቴስትሮን መጠናቸው ሊቀንስ ይችላሉ።
📌ዶ/ር ሸምሴ በአካል ቀጠሮ ለማስያዝ 0948339660
አዲሱን የ Youtube ቻናል subscribers ያድርጉ https://youtube.com/@4_doctors?si=8XUD1paB7Lmj6Z7_ | 5 399 |
