ድብቁ ህሊና ለስኬት ፕሮግራም ማድረግ!!!
Kanalga Telegram’da o‘tish
የዚህ ቻናል አላማ ሰዎች በመልካም አስተሳሰባቸው የሚፈልጉትን ህልም እንዴት ማሳካት እንደሚችሉ ፣ የአሸናፊነት ልማድ እንዴት እንደሚገነባ እንዲሁም የአእምሯችንን ሚስጥራዊ አሰራር የምናውቅበት እና የስኬታማ ሰዎች ተሞክሮም እናቀርባለን። ዘለቄታዊ የሆነ ለውጥ ለማምጣት ደግሞ በነፃ የማማከር አገልግሎትም እንሰጣለን (0912098256 )። ስልጠናዎችን በኦዲዮ ፣ በቪድዮ እንዲሁም በፁሁፍም ይቀርባሉ።
Ko'proq ko'rsatish8 230
Obunachilar
+324 soatlar
+177 kunlar
+13930 kunlar
Postlar arxiv
የህይወት ጋሪ የኑሮ ፈረስ...፦
አይታወቅም የት እንደሚያደርስ...፤
ከቀኝ ከግራ ከኋላም ከፊት...፤
ሲያተራምሰው የጊዜ ወንፊት...፤
ሲያጥወለውለው ራሱ ሲዞር...፤
ከሱነቱ ላይ ትንሽ ላይጨምር...፤
መንገዱ በዝቶ መሄጃ እያጣ...፦
ላይማርበት እየተቀጣ...!
በድንግዝግዙ እያነከሰ...፤
ካሰበው ቦታ ወይ አልደረሰ...፤
ደግሞ ሲያማትር...
ደግሞ አዲስ ሲመኝ....፤
የሌላ አድናቂ የራሱን ኮናኝ...፤
መርካት ያቃተው ሀሴት ተራቢ
ዛሬን የረሳ ነገን አሳቢ...
ሁልጊዜም ተጓዥ..."
ሁልጊዜ ማይደርስ...፤
አንዱን ሲበድል አንዱን ለመካስ...፤
ከራሱ ጋራ ዘውትር ሲካሰስ...፤
አለ የሰውልጅ የልብ ሳይደርስ...።
🌅 መልካም አዲስ ሳምንት!
ትልቁ እንቅፋትህ ከውጪ ያለ አስቸጋሪ ሁኔታ ሳይሆን፣ በውስጥህ የምታዳምጠው የሰበብ ድምፅ ነው። "አልችልም፣ ጊዜ የለኝም" የሚሉትን ድምፆች ዛሬ አጥፋቸውና "እችላለሁ!" በሚል አዲስ ጉልበት ጀምር።
💡 የአስተሳሰብህን ድንበር ሰብር ሕይወትህ ይስፋፋል!
የእናንተው ቤተሰብ 👉 ✅ @BNega
🌅 ሰላማዊ እሁድ!
ዛሬ ያለፈውን ሳምንት ስኬቶችህን የምታመሰግንበት እና የቀጣዩን ሳምንት ድሎችህን በምናብህ የምትስልበት ቀን ነው። ሕይወትህን በንቃተ-ህሊናህ መምራት ጀምር።
📝 የነገውን ሰኞ እቅድ ዛሬ ማታ ማስታወሻህ ላይ ማስፈርህን አስታውስ።
የእናንተው ቤተሰብ 👉 https://t.me/BilinersNega ✅ @BNega
🌅 የቅዳሜ ጠዋት ንቃት!!!
እውነተኛ የገንዘብ ነጻነት የሚመጣው ለገንዘብ ብቻ መሮጥ ስታቆም እና ገንዘብ ላንተ የሚሰራበትን የቢዝነስ ሲስተም መገንባት ስትችል ነው። ዛሬ የምትተክለው ዘር የነገ ነጻነትህን ይወስናል።
🔑 ጊዜህን ወደ ሲስተም ቀይረው ሲስተሙ ወደ ነጻነት ይቀይረሃል።
የእናንተው ቤተሰብ 👉 @BNega ✅ https://t.me/BilinersNega
🌅 መልካም የአርብ ጠዋት!
ስኬት ማለት በአንድ ቀን የሚመጣ ተዓምር ሳይሆን፣ በየቀኑ የምታደርጋቸው ትናንሽ ነገሮች ድምር ውጤት ነው። ዛሬ ስሜት ባይኖርህ እንኳን የተለመደውን ሥራህን ዞር ሳትል በዲስፕሊን ፈጽም።
🌱 ጽናት ካለህ የማታሸንፈው ምንም አይነት ፈተና የለም!
የእናንተው ቤተሰብ 👉 ✅
📌 ሰላም ወዳጆቼ!
በእርግጥ የሁላችንም ፍላጎት በስራችን፣ በህይወታችን እና በቢዝነሳችን የተሻለ ቦታ መድረስ ነው። ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ ትልልቅ ነገሮች ላይ ብቻ ትኩረት ስንሰጥ፣ በየቀኑ በህይወታችን ውስጥ የምናስቀራቸው ጥቃቅን የሚመስሉ ግን ወሳኝ የሆኑ ልምዶች እንዘነጋቸዋለን (ይረሱብናል)።
አንዳንዴ ህይወታችንን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ትልቅ ተአምር ሳይሆን የሚጠበቅብን፣ እነዚህን ጥቃቅን ልምዶች በጥቂቱ ማሻሻል ብቻ ነው።
💼 በስራ እና በቢዝነስ (Work & Business)
1, የወጪ እና ገቢን በትክክል መመዝገብ (Tracking Income & Expenses)
2, አስፈላጊ ስልኮችን መደወል/ውይይቶችን ማድረግ (Making Tough Calls & Conversations)
3, አዳዲስ አሰራር እና ክህሎቶችን መማር (Learning New Skills)
4, የቀኑን አስፈላጊ ስራዎች አስቀድሞ ማቀድ (Daily Planning & Prioritization)
5, የረጅም ጊዜ ግብ ከተግባር እቅድ ጋር ማስቀመጥ (Writing Down Long-term Goals)
🧠 በስብእና እና በአስተሳሰብ (Personal Growth)
1, ለግብህ ቀጣይነት ያለው የንባብ ባህል ማዳበር (Consistent Reading Habits)
2, አስፈላጊ በሆነበት ቦታ ላይ "አይሆንም" ማለት (Setting Boundaries & Saying No)
3, ከሰዎች ጋር ያሉ አለመግባባቶችን ወዲያው መፍታት (Resolving Conflicts Quickly)
4, በየሳምንቱ የራስን እድገት መገምገም (Weekly Self-Reflection)
5, የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ (Consistent Physical Exercise)
🤝 በጤና እና በግንኙነት (Health & Relationships)
1, በቂ ውሃ መጠጣት እና ጥንቃቄ ያለው ምግብ (Hydration & Healthy Eating)
2, ለቤተሰብ እና ለወዳጅ በቂ ጊዜ መስጠት (Nurturing Relationships)
3, የጤና ምርመራዎችን ማድረግ (Routine Health Check-ups)
4, የእንቅልፍ ሰዓትን ማስተካከል (Maintaining a Healthy Sleep Schedule)
5, አላስፈላጊ ጥቃቅን ወጪዎችን መቀነስ (Cutting Unnecessary Small Expenses)
እስኪ ከታች ከተዘረዘሩት 15 ነገሮች ውስጥ የትኞቹን ይበልጥ ማሻሻል ይፈልጋሉ?
👉 @BNega
🌅 እንኳን ለሐሙስ ጠዋት አደረሰህ!
ሁልጊዜ ተመሳሳይ ነገር እየሰሩ የተለየ ውጤት መጠበቅ ሞኝነት ነው። ህይወትህ እንዲቀየር ከፈለግክ የ90 ቀናት ትኩረትና ትክክለኛ መመሪያ ያስፈልግሃል። ዛሬ አዲስ ውሳኔ የምትወስንበት ቀን ነው።
🎯 የእለቱ ልዩ ጥሪ፦
የ90 ቀናት የጌም ፕላን አባል በመሆን የገቢ ምንጭህን ለማሳደግ እና በውስጥ መስመር ስልጠና ለመጀመር አሁኑኑ "ስልጠና እፈልጋለሁ" ብለህ መልዕክት ላክ 👉 @Ela216
የእናንተው ቤተሰብ 👉 ✅
🌅 ብሩህ የረቡዕ ጠዋት!
ሰዎችን Attract ማድረግ የምትችለው የውስጥህን ማንነት ስታሳድግ ነው። አንተ በራስህ ስትተማመን፣ ግልጽ ራዕይ ሲኖርህና ለሰዎች እሴት ስትጨምር ምርጥ መሪዎች ወዳንተ መሳብ ይጀምራሉ።
የእናንተው ቤተሰብ 👉 ✅
በህይወት ደክመን ከተኛንበት የሚያነሳ ብቻ ሳይሆን የተኛንበንም አልጋ አንስተን እንድንሄድ ስለሚያበረታን ተመስገን !!!
ተመስገን !!!
🌅 የማክሰኞ ጠዋት ሰላምታ!
አእምሮህን በየቀኑ በምስጋና መሙላት ሲለምድ ሕይወትህ በበረከት መሞላት ትጀምራለች። ዛሬ ጠዋት ስላገኘኸው አስደናቂ ሕይወት፣ ስላለህ ውስጣዊ አቅም እና ስለምትሰራቸው ሥራዎች ፈጣሪን አመስግን።
✨ ምስጋና የተትረፈረፈ ሕይወት መክፈቻ ቁልፍ ነው!
የእናንተው ቤተሰብ👉
🌅 አዲስ ሳምንት! አዲስ ጉልበት!
አሸናፊዎች ችግር ባለበት ቦታ ላይ መፍትሄ እና ወርቅማ ዕድልን ያያሉ። ተሸናፊዎች ግን ዕድል ባለበት ቦታ ላይ ሰበብ እና መሰናክልን ያያሉ። ዛሬ አእምሮህን መፍትሄ አነፍናፊ አድርገህ አስነሳው።
💡 ዛሬ ምንም ሰበብ የለም። የምንፈልገው ውጤት ብቻ ነው!
የእናንተው ቤተሰብ 👉
Happy Monday!
Setting yourself up for success doesn’t require a 20-step morning routine, it just requires focus. Real productivity isn’t about how many tasks you check off, but about dedicating your energy to the right ones. Instead of overwhelming your to-do list, pick three non-negotiables for the day and tackle the hardest one first. Clear away the noise, protect your time, and let consistent execution do the heavy lifting this week.
🌅 ሰላማዊ እሁድ ጠዋት!
ዛሬ የወደፊት ሕይወትህን በምናብህ የምታይበት ቀን ነው። አይንህን ጨፍነህ የምትፈልገውን ትልቁን ግብህን ስታሳካ እራስህን ተመልከት።
📝 የቀጣዩን ሳምንት 3 ዋና ዋና ግቦችህን አሁኑኑ በማስታወሻህ ላይ ጻፍ።
🌅 የቅዳሜ ጠዋት ሰላምታ!
"ትልቁ ስኬት ውድቀትን አለማወቅ ሳይሆን፣ በወደቅክ ቁጥር ተነስተህ መቀጠል መቻልህ ነው!" ዛሬ የእረፍት ቀንህን ራስህን ለመገንባት፣ መጽሐፍ ለማንበብና እውቀትህን ለማሳደግ ተጠቀምበት።
🔑 ትናንት ካለፈበት ቦታ ላይ ዛሬን በአዲስ ተስፋ ጀምር።
የእናንተው ቤተሰብ 👉
🌅 እንኳን ለሐሙስ ጠዋት አደረሰን!
🌼ታላቅ ራዕይ ኖሮህ በተግባር ካልደገፍከው ምንም ዋጋ የለውም። በሕይወታቸው ስኬታማ የሆኑ ሰዎች ልዩነታቸው ሳይደናቀፉ ዛሬ የመጀመሪያውን እርምጃ መውሰዳቸው ነው። ሰበብ መደርደር እናቁምና ዛሬን የተግባር ቀን እናድርገው።
🎯 የእለቱ የለውጥ ጥሪ፦
የቆየውን አስተሳሰባችን ሰብረን፣ ዛሬን፣አሁንን እንሁን። ሒይወታችን ለመለወጥ ከወሰንን የስከፀታማ ሰዎችን ማንነትን እንላበስ!!!🎯🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
🌅 መልካም አዲስ ሳምንት!
ባለፈው ወር ያላሳካኸው ግብ ካለ ዛሬ አዲስ ወርቅማ እድል ተሰጥቶሃል። ትናንትን እርሳው። ዛሬ በአዲስ ጉልበትና በማያወለውል እምነት ወደ ፊት ተራመድ። አንተ አሸናፊ ነህ!
💡 ዛሬ አዲስ ቀን ነው። አዲስ ታሪክ ጻፍ
Happy Monday!
New week, same commitment to doing the right thing.
Ethics isn't a checklist we look at once a year. It’s the daily practice of integrity, accountability, and respect. Before the week gets hectic, let's set an intention to keep our values at the center of everything we do.
"ስኬት በአንድ ቀን አይመጣም። በትህትና፣ በትዕግስት፣ በጽናት፣ በምስጋና እና በራስ መተማመን የሚገነባ ጉዞ ነው። አንዳንዶች ወደ ታች ሊጎትቱህ ይሞክራሉ፤ ነገር ግን አንተ ዓይንህን በግብህ ላይ አድርገህ ቀጥል። ዛሬ የምትወጣው አንድ እርምጃ፣ ነገ የስኬትህ ጫፍ ያደርስሃል።" 🌿🏆
#ባዶ_ነው_የሚሉህን_ነግሰህ_የምታሳፍርባቸው_5_ስልቶች፦
1. ድምጽህን አጥፋ
👉 ትልቅ አሳ በትልቅ ጫጫታ አይያዝም፤ በዝምታ ስራ
2. የእውቀት ረሃብ ይኑርህ
👉 መነሻ የለኝም አትበል፤ መረጃ ካለህ ብር አለህ
3. በነፃ መስራትን አትፍራ
👉 መጀመሪያ ልምዱን ግዛ፤ በኋላ ብሩ ራሱ ይከተልሃል
4. ገጽህን አጠንክር
👉 መናቅና መገፋትን እንደ ነዳጅ ተጠቀምባቸው
5. ጨለማን እለፍ
👉 ተደብቀህ የምትጓዝባቸው ቀናት ለብርሃኑ ያበቁሃል
በብልኃት_ሥራ መጽሐፍ
