uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

የደጉ ሳምራዊ መልካምነት®

የደጉ ሳምራዊ መልካምነት®

Kanalga Telegram’da o‘tish

ይህ ትክክለኛ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት የቴሌግራም ቻናል ነው:: /በመምህር ሲራክ ሰሎሞን/ በዚህ የቴሌግራም ቻናል:- ➮አስተማሪ እና መንፈሳዊ ፅሁፎችን ➮የቅዱሳን ገድላት ➮ መዝሙሮችን ➮መንፈሳዊ ትምህሮቶችን ያገኛሉ። የመወያያ ግሩፕ: https://t.me/+QKiTJYGJvYpmNWM0 የዚህ ግሩፕ ዓላማ ለበጎ ምግባር ቃለ እግዚአብሔርን መማማር ነዉ::

Ko'proq ko'rsatish
1 234
Obunachilar
+124 soatlar
+17 kun
+2130 kun
Postlar arxiv
🛑#"ታላቅ ስህተት ስለ ሥላሴ"‼️👉መጋቤ ሐዲስ መምህር አድነው ወንድሙ‼️EOTC 👉ቤዛ ኩሉ ሚዲያ_Beza kulu ... https://youtube.com/watch?v=sGgFUQ8lK9Q&si=6qRpzg7VXwfdpCux

#ተስፋ_ከቆረጣችሁ_የክረምቱን_ውበት_ታጣላችሁ! አራት ልጆች የነበሩት አንድ ሰው ነበረ፡፡ ልጆቹ ነገሮችን በችኮላ አለመወሰንን እንዲማሩ ስለፈለገ ከመንደራቸው 'ራቅ ብለው የሚገኝ የሸክኒት ዛፍን ፈልገው እንዲመለከቱ ይሰዳቸዋል፡የመጀመሪያው ልጅ በበጋ፤ ሁለተኛው ልጅ በፀዳይ፤ ሦስተኛው ልጅ በክረምት እና የመጨረሻው ልጅ ደግሞ በመኸር ወቅቶች ጉዟቸውን አደረጉ፡፡ አባትም አራቱም ልጆቹን ከጉዟቸው መልስ በኋላ ሁሉንም ሰብስቦ ያዩትን እንዲናገሩ አደረገ። የመጀመሪያው ልጅ ዛፉ አስቀያሚ፣ ጎባጣ እና ጠማማ እንደሆነ ተናገረ፡፡ ሁለተኛው ልጅ በጭራሽ ዛፉ አረንጓዴ እንቡጦችን ያዘለ እና ተስፋን የቋጠረ ነበር አለ። ሦስተኛው ልጅ ደግሞ በተቃውሞ ዛፉ በአበቦች ፍካት የተንቆጠቆጠ እና መዓዛው ከሩቅ የሚጣራ እንደሆነ ገልጾ በሕይወቱ እንደዛ ዓይነት መልካም ነገር ገጥሞት እንደማያውቅ ተናገረ። የመጨረሻው ልጅ በተቃራኒው ሁሉንም በመቃወም ዛፉ በበሰሉ ፍሬዎች የዘመመ እና ስኬት እና እርካታ እንደሚነበብበት ገለጸ፡፡ ከዚያ በኋላ አባትም ሁሉም ልጆቹ ትክክል እንደሆኑ ማብራራት ጀመረ፡፡ ምክንያቱም ሁሉም የተመለከቱት የዛፉን ሕይወት አንድ ወቅት ብቻ ስለነበረ ነው፡፡ በመጨረሻም ሰውም ሆነ ዛፍ የአንድ ወቅት ይዞታውን በመመልከት ብቻ መፍረድ እንደማይገባቸው አስረዳቸው። የሰው ልጅ ፍስሐ፣ ሐሴት እና ፍቅር እንዲሁም መሠረታዊ ማንነቱ የሚመዘነው ሁሉም ወቅቶች ካለፉ በኋላ በመጨረሻ እንደሆነ አሳሰባቸው፡፡ በበጋ ወራት ተስፋ ከቆረጣችሁ የፀደዩን ተስፋ፣ የክረምቱን ውበት እና የመኸሩን ሙላት ታጣላችሁ፡፡ ሕይወትን በአንድ አስቸጋሪ ወቅት ብቻ አትገምግሙ። የአንድ ወቅት መከራ የሌሎቹን ወቅቶች ሐሴት እንዳያጠፋቸው ተጠንቀቁ!። የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ! ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ:👇🏽 Telegram: ☞https://t.me/joinchat/S3QVyScP7Saom-Lv

⛪️ #ወደ_ምስራቅ_ተመልከቱ ⛪️ ✍️በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖታችን ቤተክርስቲያን የምትታነፀው ምስራቁን አቅጣጫ ጠብቃ ነው እዲሁም ከቤተክርስቲያኑ ጋር አብሮ የሚሰራው ቤተልሄም በስተምስራቅ በኩል ይደረጋል በፀሎት ሰዓትም ወደምስራቅ ዞረን ነው የምንፀልየው በስረአተ ቀብር ላይም የሞተ ሰው ሲቀበር ራሱ ወደ ምዕራብ እግሩ ወደ ምስራቅ ሆኖ ይቀበራል ሌላው ዲይቆኑ በስረአተ ቅዳሴው ላይ ወደምስራቅ ተመልከቱ ይላል ለምን ይሆን ? 💠1 ፦የአዳም አባታችን ጥንተ ርስት ገነት በምስራቅ ናት (ዘፍ 2፥8) ይች እርስታችን በአዳም በደል ምክኒያት በኪሩቤል ሰይፍ ተዘግታ ስትኖር ሞትን ድል አድርጎ በበደልን ክሶ ጌታችን መዳህኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሞቱ ከፈተልን (ሉቃ 23፥43) ወደምስራቅ በዞርን ቁጥር ወደገነት ለመግባት የተሰጠን ተስፍ ትዝ ይለናል የተከፈተችውም ቤታችን ገነት በእምነት ወለል ብላ ትታየናለች በክርስቶስ ያገኘነውን ፀጋ እናስባለን ምድራውያን አለመሆናችንም ይታወሰነል 💠2 ፦ጌታ የተወለደው በምስራቅ ነው ሰብዓሰገል ኮከቡን ያዩት በምስራቅ ሲሆን ያኮከብ የምህረተ እግዚአብሄር ምሳሌ ነው እነርሱን ወደ እግዚአብሄር እዳደረሳቸው ሁሉ እኛንም ወደ ለመለመው መስክ ይመራናል (ማቴ 2፥2) (መዝ 22፥14) ወደ ምስራቅ በዞርን ቁጥር የጌታ መወለድ እና ያደረገልን ውለታ ይታወሰናል የምህረቱ ኮከብ እየመራን መሆኑ ትዝ ይለናል ። 💠3 ፦ ምስራቅ የእመቤታችን ምሳሌ ነው ከምስራቅ ጨለማውን የሚገፈው ፀሀይ እደሚወጣ ሁሉ ከእመቤታችን ከድንግል ማርያምም የአለምን የሀጥያት ጨለማ የሚገፍ ፀሀዬ ፅድቅ ኢየሱስ ክርስቶስ ወጥቶል (ተገኝቱል) ለእናንተ ስሜን ለምትፈሩ የፅድቅ ፀሀይ ትወጣላችሁለች (ሚል 4፥1) (ህዝ 44፥1፦4) ነብዩ ህዝቅየልም እመቤታችንን ያያት በምስራቅ ነው ስለዚህ ወደ ምስራቅ በዞርን ቁጥር እመቤታችን ትዝዝዝ ትለናለች የፅድቅ ፀሀይ ክርስቶስ ስለተወለደልን በጨለማ አለመሆናችን ትዝ እያለን ከሀጥያት እንርቃለን 💠4፦የአለም ድህነት የተገኘው በምስራቅ ነው ጌታ የተሰቀለው እና አለምን ያዳነው በምስራቅ ነው እየሩስ አሌም ምስራቃዊት ከተማናት እና በመሆኑን ወደ ምስራቅ በዞርን ቁጥር የተሰቀለውን ክርስቶስን እና የተከፈለልንን ዋጋ እናስባለን 💠5፦ክርስትናና ቤተክርስቲያን የተመሰረቱት በምስራቅ ነው። የመጅመሪያው ቤተክርስቲያን የተመሰረተው በእየሩስ አሌም ሲሆን ወንጌል የተሰበከውም ከዚሁ በመነሳት ነው ።ስለዚህ ወደምስራቅ ስንዞር የቤተክርስቲያን ጉዞ የወንጌል መስፍፍት ና የህዝበ አለም መዳን ትዝ ይለናል 💠6፦ ምስራቅ የእግዚአብሄር ክብር መገለጫ ነው ። (ኢሳ 28:13) እግዚአብሄርን በምስራቅ የእስራኤልንም አምላክ የእግዚአብሄርን ስም በባህር ደሴቶች አክብሩ ህዝ 43፦2 የእስራኤል አምላክ ክብር ከምስራቅ መንገድ መጣ 💠7፦የጌታ ዳግም ምፅአትም ከምስራቅ ነው (ዘካ 14፥14) በዚያን ቀን እግሮቹ በእየሩስ አሌም ትይዩ በምስራቅ በኩል ይቆማሉ (ሐዋ 1፦11) ይህ ከእናንተ ወደሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደሰማይ ሲርግ እዳያችሁት እንዲሁ ይመጣል ። 💠8፦ቅዱሳን አበው ሲፀልዩ ወደ ምድራቅ ይዞሩ ነበር (ዳን 6፥9) ወደ እየሩስ አሌም ያለውን መስኮት ከፍቶ ይፀልይ ነበረ ነብዩ ዳንኤል እግዚአብሄር ምሉዕ በኩልሄ (የሌለበት ቦታ የሌለ) መሆኑን ያውቃል። ነገርግን ወደ እየሩስ አሌም መዞሩ ነፍሱ የምታስባት እዲኖራት ነው 💠9፦ ታቦቱ በምስራቅ በኩል ባለው ቤተ መቅደስ አስቀምጠን ስጋወ ደሙ የሚፈተተው ጌታ በምስራቅ ሀገር ጎለጎታ ለኛ ስጋውን መቁረሱ ደሙን ማፍሰሱበማሰብ ነው ። 💠10፦በስረአተ ቅዳሴ ላይ ዲያቆኑ ወደ ምስራቅ ተመልከቱ በምስራቅ የተደረገልንን ውለታ የተከፈለልንን ዋጋ ምስራቀ ምስራቃት ከሆነችው እመቤታችን የተገኘውን ፀሀዬ ፅድቅ ኢየሱስ ክርስቶስን አስቡ ማለቱ ነው ። 💠11፦ በቀብር ስነስረአት የአስከሬኑን ፊት ወደ ምስራቅ የሚዞርበት ምክኒያት በዳግም ምፅአት በሚነሳበት ጊዜ ፊቱን ወደጌታ እዲያዞር እና እዲመለከት በማስብ ነው ። እንግዲህ ወደምስራቅ መዞር የክርስቶስን የማዳን ስራ የቅዱሳንን ህይወት የሰማዕታትን ገድል የክርስቲያንን ተስፈ የሚያሳስበን ነው እና ወደ ምስራቅ እንዞራለን ይህንን ስረአት ያስተማሩን አበው በረከታቸው ይደርብን አሜን:: የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የቴሌግራም ቻናላችን ቤተሰብ ይሁኑ! ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ:👇🏽 Telegram: ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

እንኳን ለጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ። ✍🏽=>ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ:: አባታችን ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ: የቅዱሳን የበላይ: ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው::
የጻድቁን ክብር መናገር የሚችል ምን አንደበት ይኖራል? እንደ ምንስ ባለ ብራና ይጻፋል? ዜናቸውንስ ለመስማት የታደለ እንደ ምን ዓይነት ሰው ይሆን?
አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ እህል ያልቀመሱ (ምግባቸው ምስጋና ነውና): ልብስ ያልለበሱ (ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና): ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮዽያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ አባት: ሃገራችንን አስምረው: አስራት እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ አርፈዋል:: ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም: ገብረ ሕይወትም ይባላሉ:: በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብጸ እስከ ኢትዮዽያ ወንጌልን ሰብከዋል:: በዚህም በሚሊየን (አእላፍ) ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል:: ጻድቁ እንደ ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን ተቀብለዋል:: እንደ ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው ሳያዩ ቆይተዋል:: ለየት የሚለው ግን የጽድቅ ሕይወታቸው ነው:: ከእልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር ተዋግተው ድል ማድረግ ችለዋልና:: የንሒሳው ኮከብ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለኢትዮዽያ ልዩ ፍቀር አላቸው:: ስለ ሃገሪቱና ሕዝቧ ፍቅር ሲሉ ለ100 ዓመታት በደብረ ዝቁዋላ መከራን ተቀብለዋል:: ምሕረትን ሲለምኑ ሥጋቸው አልቆ በአጥንታቸው ቁመው ነበርና ሃገራችን አሥራት ሆና ተሰጠቻቸው:: ስለዚህም ነው በሃገሪቱ ውስጥ ከ2,000 በላይ የጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳማትና አድባራት ዛሬም ድረስ ያሉት:: በ8ኛው ክ/ዘመን አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው:: ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል:: ሥላሴን የተሸከመ አካላቸው በጐልጐታ ተቀብሯል የሚሉም አሉ:: "ሰላም ለመቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ: ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ: ዜና መቃብሪከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ: ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም አጸድ: ወቦ ዘይቤ ኀለወ በከብድ::" እንዲል:: የጻድቁ በዓል ጥቅምት 5 ቀን የሚከበረው ብዙ ጊዜ #መጋቢት_5 ዐቢይ ጾም ውስጥ ስለሚውል ተውላጥ (ቅያሪ) ሆኖ ነው:: አምላከ ቅዱሳን በእነርሱ ላይ የበዛች ፍቅሩን ለእኛም ያድለን:: ፍሬ ትሩፋት: ፍሬ ክብር እንድናፈራም ይርዳን:: ክብራቸውንም አያጉድልብን:: ከጻድቁ ዋጋና በረከት ይክፈለን:: Telegram: ☞☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

#ኧረ_እንዴት_ነው_አቡዬ ኧረ እንዴት ነው አቡዬ ኧረ እንዴት ነው ጻድቁ/2/ የሌጌዎን ጭፍሮች በስምህ አለቁ ኧረ እንዴት ነው አቡዬ አረ እንዴት ነው ጻድቁ በፆም በጸሎትህ በመብረቅ ወደቁ ኧረ እንዴት ነው አቡዬ አረ እንዴት ነው ጻድቁ ገድሉ አንፀባራቂ ተአምሩ የገነነ ኧረ እንዴት ነው አቡዬ አረ እንዴት ነው ጻድቁ በረከት ያገኛል ኪዳኑን ያመነ ኧረ እንዴት ነው አቡዬ አረ እንዴት ነው ጻድቁ ስእለትን ይሰማል ፀበሉ ፈዋሽ ነው ኧረ እንዴት ነው አቡዬ ኧረ እንዴት ነው ጻድቁ ገብረመንፈስ ቅዱስ ለጠሩት አባት ነው ኧረ እንዴት ነው አቡዬ ኧረ እንዴት ነው ጻድቁ እናቱ አቅሌሲያ አባቱ ስምዖን ኧረ እንዴት ነው አቡዬ ኧረ እንዴት ነው ጻድቁ ምግቡ ምስጋና ነው ተሰጥቶታል ኪዳን Telegram: ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

እንኳን ለጻድቁ "#አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት: እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በ
እንኳን ለጻድቁ "#አቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን።
ነገር ግን ዓለም ለእኔ የተሰቀለበት: እኔም ለዓለም የተሰቀልሁበት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ:: በክርስቶስ ኢየሱስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይጠቅማል እንጂ መገረዝ ቢሆን ወይም አለመገረዝ አይጠቅምምና:: ገላ. 6:14
=>አምላከ ቅዱሳን በእነርሱ ላይ የበዛች ፍቅሩን ለእኛም ያድለን:: ፍሬ ትሩፋት: ፍሬ ክብር እንድናፈራም ይርዳን:: ክብራቸውንም አያጉድልብን:: የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ! ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ:👇🏽 Telegram: ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv #ቃለ_እግዚአብሔር_ለሁሉም_ይዳረስ_ዘንድ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።

<<#የዘመነ_ስደት_መታሰቢያ_ለምን_በዚህ_ጊዜ_ሆነ?>> *ከመስከረም 26 እስከ ህዳር 5* ✥ እመቤታችን ከልጅዋ ጋር ስደትን የጀመረችው ጥር 3 ነው፥ አገረ ግብጽ የገባችው ግንቦት 24 ነው፥ በግብፅ እና በኢትዮጵያ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ከቆዩ በኋላ ስደቱ አብቅቶ ተመለሱ ብሎ መልአኩ ሲነግራቸው ካሉበት ተነስተው ቁስቋም ከተባለች ቦታ ኅዳር 6 ደርሰዋል ። *የስደት_መታሰቢያ_ለምን_በመነሻው_ጥር_3_አልሆነም? ይህ ወቅት ዘመነ አስተርእዮ የደስታ ጊዜ ነው ታህሳስ 29 ልደቱን ጥር 11 ጥምቀቱን የምናከብርበትና በልደቱ እና በጥምቀቱ የተደረገልንን እያሰብን ደስ የምንሰኝበት ጊዜ በመሆኑ ለስደት መታሰቢያ ለማድረግ አይመችም። *ግንቦት_24_አገረ_ግብፅ_የገባችበትን_ይዘን_ለምን_ስደትን_አናስብም? ግንቦት 24 በዓለ ሃምሳን የምናከብርበት እንደመሆኑ በዚህ ወቅት ጌታችን በትንሳኤው የሰጠንን ነጻነት የምናስብብት ደስ የምንሰኝበት ጊዜ ስለሆነ መስገድ መጾም ስለማይፈቀድ የስደት መታሰቢያ ለማድረግ አይመችም። ✥  ከመስከረም 26 እስከ ኅዳር 5 ዕፅዋት አበባን ፍሬን የሚያሳዩበት ወቅት ነው። *  ወቅቱ ለምሳሌ የተመቸ ነውና። « ትወጽእ በትረ እምሥርወ እሤይ ወየዓርግ ጽጌ እምኔሃ » (ት ኢሳ11፥1) እንዲል የእሤይ የዘር ግንድ ከተባለች ከእመቤታች ጽጌ ጸኣዳ ወቀይህ የተባለ የፍጥረት ሁሉ ጌጥ ጌታችን የተገኘ ነውና በዚህ መስሎ ለማስተማር የሚያመች ወቅት ነውና። በተጨማሪም ጽጌ በእመቤታች ፍሬ በጌታችን ይመሰላል #አንድም፦ ተመለሰ ከማለት በፊት ተሰደደ ማለት ይቀድማል። — በዓመት ውስጥ ያሉት የወራት ቅድመ ተከተል ኅዳር 6 ከጥር 3 እና ከግንቦት 24 ይቀድማል። ኅዳር ላይ ከስደት ተመለሰ ብለን ካከበርን በኋላ ጥር ተሰደደ ግንቦት ግብፅ ገባ ብንል አመቺ አይደለም። ስለዚህ ከጥር 3 ወይም ከግንቦት 24 ይልቅ ኅዳር 6 መታሰቢያ ለማድረግ አመቺ በመሆኑ ቤተክርስቲያን በዚህ ወቅት የስደቱን መታሰቢያ ታደርጋለች። ✥ በቅዱስ ያሬድ አባባል ስደት ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 20 ሲነገር፤ ከጥቅምት 21 እስከ ኅዳር 6 ድረስ ሚጠት (መመለሳቸው) ይነገራል። ይኼውም ተመየጢ ተመየጢ ሰላመ ሰጣዊት የሚለው ሰላም እንዲቀርብ በማህሌት ስለተወሰነ ነው። የበረከት ጾም ይሁንልን። ከእመቤታችን በረከት ያሳትፈን:: አሜን!!! Telegram: ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።

‹‹ወርሃ ጽጌ›› "ጽጌ" ማለት አበባ ማለት ሲሆን በዚህ ወር የጽጌሬዳ አበባ የሚፈካበት ወር ነው። ይቺ 40 ቀን "ወርሃ ጽጌ" በመባልም ይጠራል። ጽጌሬዳም በመዓዛዋ ደስ ታሰኛለች፣ በውበቷም ዓይንን ትማርካለች። በዚህም እመቤታችንን እንመስላታለን፤ ጉድፍ የሌለባት፣ የሥጋና የነፍስ ድንግል ናትና። በነገረ ማርያም እንደተጻፈው፣ ጌታችን ኢየሱስ ከተወለደ በኋላ ኄሮድስ ሊገድለው ሲፈልግ፣ መልአኩ ለዮሴፍ፦ «ተነስተህ እናቱንና ብላቴናውን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ» አለው። በዚህም እመቤታችን ልጇን ይዛ ከዮሴፍ ጋር ወደ ግብፅ ተሰደደች። እመቤታችንም ልጇን ይዛ ከዮሴፍ ጋር ወደ ግብፅ ከመስከረም-26-ህዳር-6 ተሰደደች። ፆመ ጽጌ የአዋጅ ፆም አይደለም፤ የእመቤታችንን ፍቅር ያለው ሰው ስደቷንና መከራዋን ለማስታወስ በውዴታ የሚፆመው ጾም ነው። ፆመ ጽጌ የድንግልን ስደት ለምለም አካላቷ ያልጠና ሰውነቷ ጥፍሯ እስኪነቀል ድረስ በሀሩሩ በውርጭኝ ያለ ሀጢያቷ እንግልት በማየቷ በረከትን ለማግኘት እንፆማለን ማለት ነው። የበረከት ጾም ይሁንልን። ከእመቤታችን በረከት ያሳትፈን:: አሜን!!! Telegram: ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።

እንኳን ከዘመነ ክረምት ወደ ዘመነ መጸው አሸጋግሮ በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። ✍️ ስንዱ #እመቤት #ቤተ_ክርስቲያን (ሃገራችን) ሁሉ ነገሯ በሥርዓት ነውና ዓመቱን በዘመናት ከፍላ ትጠቀማለች:: እሊሕም ዘመናት #መጸው (ጽጌ): #ሐጋይ (በጋ): #ጸደይ (በልግ) ና ክረምት ናቸው:: ዘመናቱ ወቅቶችን ከመለየትና ማሳወቅ ባሻገር የእኛ ሕይወትም ምሳሌዎች ናቸውና ልብ ልንላቸው ይገባል:: #ዘመነ_መጸው / #ወርኀ_ጽጌ/ #ጥቢ እየተባለም ይጠራል:: በዚህ ወቅት ምድር በአበባ የምታጌጥበት: ክረምት የተለፋበት አዝመራ የሚደርስበት በመሆኑ ደስ ያሰኛል:: በጊዜውም:- 1. የእመቤታችን የቅድስት #ድንግል_ማርያም ስደቷ ይታሠባል:: እርሷ ስለ እኛ:- *💠የሕይወት እንጀራን ተሸክማ መራቧን:: *💠የሕይወት መጠጥን ይዛ መጠማቷን:: *💠የሕይወት ልብስን አዝላ መራቆቷን:: *💠ሙቀተ መንፈስ ቅዱስን የሚያድለውን ተሸክማ ብርድ መመታቷን እናስባለን:: *💠ዘመኑ የበረከት ነው:: 2. በሌላ በኩል ጊዜው ወርኀ ትፍሥሕት (የደስታ ወቅት) ነው:: በክረምት የደከመ ዋጋውን አግኝቶ: በልቶ: ጠጥቶ ደስ ይለዋልና:: ያልሠራው ግን ከማዘን በቀር ሌላ እድል የለውም:: ይኼውም ምሳሌ ነው:: ዘመነ ክረምት የዚህ ዓለም ምሳሌ: ዘመነ መጸው ደግሞ የመንግስተ ሰማያት:: በዚህ ዓለም ምግባር ትሩፋትን የሠራ በወዲያኛው ዓለም ተድላን ሲያደርግ ሰነፎች ኃጥአን ግን እድል ፈንታቸው: ጽዋ ተርታቸው ከግብዞች ጋር የመሆኑ ምሳሌ ነው:: በወርኀ ትፍስሕት እንደ ሊቃውንቱ እንዲህ ብለን ልንጸልይ ይገባል:: "ድኅረ ኀለፈ ክረምት ወገብአ ዝናም: ዘአስተርአይከ እግዚኦ ጽጌያተ ገዳም: አፈወ ሃይማኖት ነአልድ ወፍሬ ምግባር ጥዑም: አትግሃነ ለስብሐቲከ ከመ ትጋሆሙ አዳም: ለጽብስት ንሕብ ወነአስ ቃሕም::" 🙏 የዘመናት ባለቤት ዘመነ መጸውን #ወርኀ_ትፍስሕት ያድርግልን::🙏 የቴሌግራም #ቻናሉን_ይቀላቀሉ ቤተሰብ ይሁኑን! #Join 👉 https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

#የእመቤታችንን_ስደት_በጾም_በጸሎት የምታስቡ ወይም የምታሳልፉ የእመቤታችን የድንግል ማርያም የቃልኪዳን ልጆች እንኳን #ለጽጌ_ጾም_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ፤_አደረሰን። የበረከት ጾም ይሁንልን። ከ
#የእመቤታችንን_ስደት_በጾም_በጸሎት የምታስቡ ወይም የምታሳልፉ የእመቤታችን የድንግል ማርያም የቃልኪዳን ልጆች እንኳን #ለጽጌ_ጾም_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ፤_አደረሰን። የበረከት ጾም ይሁንልን። ከእመቤታችን በረከት ያሳትፈን:: አሜን!!! Telegram: ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።

✍️ቅዳሴ ላይ ሶስት ዲያቆን ለምን ይሆናሉ??? ​ሦስቱ ዲያቆናት የአንድ አምላክ የሦስትነታቸው (የአብ፣ የወልድ፣ የ መንፈስ ቅዱስ) ምሳሌ ናቸው። ​በቅዳሴ ጊዜ አብረው በአንድነት በመቆም በመጸለይና በማገልገል የአንድነታቸውንና የሦስትነታቸውን ምስጢር ያሳያሉ። ​✍️. የቅዱሳን መላእክት ምሳሌ ​ቅዳሴ የምድርና የሰማይ አንድ የሚሆኑበት፣ የሰው ልጅ ከመላእክት ጋር አብሮ አምላክን የሚያመሰግንበት ሥርዓት ነው። ​ሦስቱ ዲያቆናት በዙፋኑ ፊት ቆመው "ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ" ብለው የሚያመሰግኑትን የመላእክት (የሱራፌልና ኪሩቤል) ምሳሌ በመሆን ያገለግላሉ። ​3. የተግባር እና የሥርዓት ክፍፍል (ሥራን በአግባቡ ለማከናወን) በቅዳሴ ጊዜ እያንዳንዱ ዲያቆን የተመደበለት የራሱ የሆነ የነቃ አገልግሎት አለው፦ ✍️​ዋናው ዲያቆን (የቀኝ ዲያቆን)፦ ቅዳሴውን የሚመራ፣ ህዝቡን በትእዛዛት (እንደ "ጸልዩ"፣ "ተነሱ" ያሉ) የሚያሳስብ፣ እንዲሁም ጽዋውን (ደሙን) ለመቁረብ የሚይዝ ነው። ✍️​ረዳት ዲያቆን (የግራ ዲያቆን)፦ ከዋናው ዲያቆን ጎን በመሆን መልእክታትን (የሐዋርያት መልእክት) የሚያነብ፣ ማዕጠንቱን የሚያዘጋጅና ካህኑን የሚረዳ ነው። ✍️​ንፈቅ ዲያቆን (ሦስተኛው ዲያቆን)፦ በቤተ መቅደስ ውስጥ የሚያስፈልጉ ቅዱሳት ንዋያትን የሚያቀርብ፣ የሚያስተናግድ እና ለሥርዓቱ ቅደም ተከተል ድጋፍ የሚሰጥ ነው። የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ!!! Telegram: ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።

✝️ #ጉባኤ_ኒቅያ ✝️ ✍️በዚህች ዕለት በሃገረ ኒቅያ በእመቤታችን እና በአምላክ ልጇ የሚያምኑ 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት ተሰብስበዋል:: የሊብያው ሰው አርዮስ ጌትነት ገንዘቡ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክዶ ሊያስክድ ሲሯሯጥ በፈቃደ እግዚአብሔር: በጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጥሪ: 2348 ምሑራን ከመላው ዓለም ተሰበሰቡ:: ጥሪው የተላለፈው በወርኀ ሚያዝያ ሲሆን በመንገድ ችግር ሁሉም ተጠቃለው ኒቅያ የገቡት #መስከረም_21_ቀን ነበር:: ከተሰበሰበው ብዙ ሰው መካከል የአበውን ደቀ መዛሙርት ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና: ምግባራቸው የጸና 318ቱ አበው ሊቃውንት ተገኙ:: እነዚህ አባቶች "ሊቃውንት" ሲባሉ እንዲሁ በእውቀት ብቻ የበሰሉ እንዳይመስሉን:: 318ቱ አበው እኩሎቹ በዘመነ ሰማዕታት እጅና እግራቸውን የተቆረጡና ለሃይማኖታቸው ብዙ ዋጋ የከፈሉ ናቸው:: እኩሎቹ ደግሞ በገዳማዊ ሕይወት ያጌጡ: ፍቅረ ክርስቶስ በውስጣቸው የሚነድ: የመንፈስ ቅዱስ ቤት ናቸው:: እስኪ እናውቃቸው ዘንድ የጥቂቶችን ማንነት በስምና በመገለጫ እንመልከት:- 👉1. ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ (በዘመነ ሰማዕታት ለ22 ዓመት ሲቆራርጡት ኖረው በጉባኤው ላይ የተገኘው ያለ እጅ: እግር: ጀሮ: ከንፈር: ቅንድብ ነው) 👉2. ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ (ስለ ቀናች እምነት ለ50 ዓመታት የተጋደለና ለ15 ዓመታት በስደት የኖረ ነው) 👉3. ቅዱስ እለእስክንድሮስ ሊቅ (ከሰማይ ብርሃን ይወርድለት የነበረ አባት ነው) 👉4. ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ (በጸሎቱ አጋንንትን ያንቀጠቀጠ: ነፍሳትን ከሲዖል የቀማና ከከዊነ እሳት የደረሰ አባት ነው) 👉5. ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ (ስለ ቀናች እምነት መጸዳጃ ጉድጓድ ውስጥ ለ15 ዓመታት ተጥሎ የኖረ ሰማዕት ነው) 👉6. ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሜራ (ከሕጻንነቱ የተቀደሰ: በበርሃ የተጋደለ: በዘመነ ሰማዕታት ብዙ መከራን የተቀበለ አባት ነው) 👉7. ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን (በደግነቱ ሙታንን ያስነሳ: ወንዝን በጸሎቱ ያቆመ: በንጽሕና የተጋደለ አባት ነው) 👉8. ቅዱስ ሶል ጴጥሮስ (ቅዱሱን ንጉሥ ያጠመቀ: ቁስጥንጥንያን በወንጌል ያበራ ሊቅ ነው) 👉9. ቅዱስ ኤዎስጣቴዎስ (ስለ ቀናች እምነቱ ብዙ ግፍ የደረሰበትና በስደት ያረፈ አባት ነው) ለአብነት እንዲሆኑን እነዚህን አነሳን እንጂ 318ቱም ሊቃውንት ስለ ቤተ ክርስቲያን ተግተው የተጋደሉ: ብዙ ዋጋም የከፈሉ አባቶች ናቸው:: በወቅቱ ታዲያ ቤተ ክርስቲያንን የበጠበጡ ብዙ መናፍቃን ቢኖሩም የአርዮስ ግን ከመጠኑ አለፈ:: የእርሱ ኑፋቄ (ፈጣሪያችንን ፍጡር ነው ማለቱ) መነሻው ከእርሱ በፊት ነው:: መናፍቃን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ ቤተ ክርስቲያንን ሲያውኩ መኖራቸው ግልጽ ነው:: በተለይ ደግሞ ቢጽ ሐሳውያንና ግኖስቲኮች የወለዷቸው እሾሆች አባቶቻችንን እንቅልፍ ነስተው ነበር:: የሚገርመኝ በዘመኑ እንደ ነበሩ መናፍቃን ኃይለኝነት የእኞቹ ከዋክብት ሊቃውንት ባይኖሩ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ያሳስብ ነበር:: ግን እግዚአብሔር ለሁሉ እንደሚገባ ያዘጋጃልና አበው ብርቱ መናፍቃንን በብርቱ መንፈሳዊ ክንድ እያደቀቁ ከጐዳና አስወገዷቸው:: የዛሬውን ደካማ ትውልድ ደግሞ የአርዮስ ልጆች 2 (3) ጥቅስ ይዘው ሲያደናብሩት ይውላሉ:: ሐረገ መናፍቃን በርጉም ሳምሳጢ ጳውሎስ: በመርቅያንና በማኒ ይጀምራል:: በእርግጥ አርጌንስ እና የግብጹ ቀሌምንጦስም ተቀላቅለዋቸዋል:: ርጉም ሳምሳጢ ድያድርስን በኑፋቄ ወልዶታል:: ድያድርስ ሉቅያኖስን: ሉቅያኖስ ደግሞ አርዮስን ወልደዋል:: ይህ አርዮስ እጅግ ተንኮለኛ በመሆኑ ልክ እንደ ዘመኑ መሰሎቹ ግጥምና ዜማ እየጻፈ በየመንገዱ እያደለ: በየቤቱ እየሰበከ ብዙዎችን በኑፋቄው በከለ:: በመጀመሪያ ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ (አስተማሪው) መከረው:: ባይሰማው ከአንዴም ሁለት ጊዜ አወገዘው:: ቆይቶ ሰነፉ ጳጳስ አኪላስ ቢፈታውም ሊቁ ቅዱስ እለእስክንድሮስ እንደ ገና አወገዘው:: እንደ አርዮስ ሐሳብ መድኃኒታችን ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ አይደለም (ሎቱ ስብሐት!) ማለት ክርስትናን ከሥሩ ፈንቅሎ መጣል ነው:: ስለ ክርስቶስ እግዚአብሔርነት ብሉይም ሐዲስም እየመሰከሩ (ኢሳ. 9:6, መዝ. 46:5, 77:65, ዘካ. 14:4, ዮሐ. 1:1, 10:30, ራዕይ. 1:8, ሮሜ. 9:5) አርዮስና የዛሬ መሰሎቹ አንዲት ጥቅስ ይዘው ክርስትናን ከመሠረቱ ለመናድ መሞከራቸው በእርግጥም ከሰይጣን መላካቸውን ያሳያል:: በወቅቱም በመወገዙ "ተበደልኩ" ብሎ የጮኸው አርዮስ ከ2ቱ አውሳብዮሶች ባልንጀሮቹ (ዘቂሣርያና ዘኒቆምድያ) ጋር ሆኖ ወደ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ ሔዶ ከሰሰ:: ቅዱሱ ንጉሥም የጉዳዩን ክብደት ተመልክቶ የዓለም ሊቃውነት ይሰበሰቡ ዘንድ አዘዘ:: ከሚያዝያ 21 እስከ መስከረም 21 ተጠቃለው ገቡ:: በ325 ዓ/ም (በእኛው በ318 ዓ/ም) ለ40 ቀናት የሚቆይ ሱባኤን ያዙ:: ሱባኤውን ሲጨርሱም በ4ቱ ፓትርያርኮች (እለእስክንድሮስ: ሶል ጴጥሮስ: ዮናክንዲኖስና ኤዎስጣቴዎስ) መሪነት: በእለእስክንድሮስ ሊቀ መንበርነት: በአትናቴዎስ ጸሐፊነት ጉባኤው ተጀመረ:: በጉባኤው ሙሉ ስልጣን በሰማይ ከፈጣሪ: በምድር ከንጉሡ የተሰጣቸው አበው አርዮስን ተከራክረው ከነ ጀሌዎቹ ምላሽ አሳጡት:: ክርስቶስ አምላክ ወልደ አምላክ: ሥግው ቃል: ራሱም እግዚአብሔር መሆኑን አስረዱት:: በጉባኤው መጨረሻም:- ✅1. አልመለስም በማለቱ አርዮስን አወገዙ:: ✅2. ጸሎተ ሃይማኖትን "ለመንግስቱም ፍጻሜ የለውም" እስከሚለው ድረስ ተናገሩ:: ✅3. ፍትሐ ነገሥትን ሥጋዊና መንፈሳዊ ብለው አዘጋጁ:: ✅4. ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን እንደሚገባ አደራጁ:: ✅5. በስማቸው የሚጠራ አንድ ቅዳሴን ደረሱ:: ይህ ሁሉ ሲሆን መድኃኒታችን ክርስቶስ 319ኛ ሆኖና ገሊላዊ ጳጳስን መስሎ ሁሉን አከናውኖላቸዋል:: አባቶችም ሥራቸውን ከጨረሱ በኋላ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስን ባርከው ወደየ ሃገረ ስብከታቸው ተመልሰዋል:: 💠በየዘመኑም ዐርፈው ለክብረ መንግስተ ሰማያት በቅተዋል:: እኛም እነሆ "አባቶቻችን: መምሕሮቻችን: መሠረቶቻችን: ብርሃኖቻችን: ምሰሶዎቻችን" እያልን እናከብራቸዋለን:: "እውነት እላቹሃለሁ ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁ::" (ማቴ. ፲፰፥፲፰) #ቻናሉን_ይቀላቀሉ ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

እንኳን ለመስከረም 21፤ ለብዙኃን ማርያም ዓመታዊ የንግሥ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን። #ብዙኃን_ሊቃውንት_ለተሰበሰቡበት_ብዙኃን_ማርያም_፤ #ክቡር_መስቀሉና_ሌሎችም_ንዋያተ_ቅድሳት-በግሸን_ደብረ_ከርቤ_አምባ_ላይ_በክብር_ላረፉበት_ዕለት፤ #ለቅዱስ_ቆጵርያኖስ_(ኃይለኛ ሥራየኛ ጠንቋይ የነበረውና በኋላም አምኖ ለክርስቶስ ምስክር ሆኖ አንገቱን የተሰየፈው )ና ፡ ቆጵርያኖስን ያሳመነችውና ስሟ በተጠራበት ቦታ ሰይጣናት እንደ ትቢያ ሆነው የጠፉት ታላቋ ቅድስት ድንግሊቱ ዮስቴና በሰማዕትነት ላረፉበት ዕለት፤ #ሃይማኖታቸው_ለቀና_ለ318ቱ_አበው_ሊቃውንት (#በ325 ዓ.ም #አርዮስን_አስተምረው_ለመመለስ_#በኒቅያ_የተሰበሰቡባት_ዕለት )፣ /የጉባኤውም ፍጻሜ ኅዳር ዘጠኝ ነው/ እንዲሁም #ከ72ቱ_አርድእት_አንዱ_ለሆነው_ለሐዋርያው_ቅዱስ_ጢባርዮስ_ዕረፍት በሰላምና በጤና አምላከ አበው መድኀኔዓለም አደረሳችሁ አደረሰን፡፡ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓሏ መስከረም ፳፩ ቀን መከበሩ ስለ ሁለት ነገር ነው፡፡ ፠1ኛ) መስከረም ፳፩ የምናከብርበት አንደኛው ምክንያት መስቀልን አስመልክቶ ነው፡፡ መስቀሉ በመስቀልኛ ቦታ በግሸን ደብረ ከርቤ በክብር ያረፈበት ዕለት ነው፡፡ #ግሸን_ደብረ_ከርቤ ደብረ #ንገሥት ፣ ደብረ #ነጐድጓድ ፣ ደብረ #እግዚአብሔር በሚባሉ ስም ትጠራ ነበር ፡፡ በመጀመርያም የተመሠረትቸው በአፄ ካሌብ ዘመን ነበር ፡፡ሁለት ጽላቶች ከናግርን (አጼ ካሌብ ድል አድርጎ ከተመለሰ በኃላ ) በአባ ፈቃደ ክርስቶስ አማካኝንት (መነኰስ) አምጥተዋል ፤ ከዛም ሲመጡ ወደ ጊሸን ተራራ ሊወጡ ሲሉ በዚያ ንብ ሰፎ ማር ሲንጠባጠብ በማየታቸወው በግእዝና አረብኛ ቋንቋ #አምባ አሰል ብለው ጠሩት ትሩጉሙም የማር አማባ ማት ነው እስካሁንም አካባቢው አምባሰል እየተባለ ይጠራል፡፡ የመጡትንም ጽላቶች በማስገባት የመጀመሪያውን ቤ.ክ ሠረተው ደብሩን መስርተዋል፡፡ በሺህ አንድ መቶ ሃያ ሰባት ዓመት ሰማዕታት ሃይማኖታቸው የቀና የዳግማዊ ዳዊት ልጅ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ከአፄ ይኩኖ አምላክ ከተረፈው የመንግሥት ቅብዓት ተቀብተው ነገሡ፡ ስመ መንግሥታቸውም #ቆስጠንቲኖስ ተባለ፡ በተወለዱም በሃምሣ ዓመት ‹‹ መስቀሌን በመስቀል ላይ አስቀምጥ የሚል ራዕይ አይተው ›› ጠይቀው ሲረዱ አባታቸው የተረከበው መስቀል በመካ መዲናው አሕዛብ ሹም እንዳለ ተረዱ ክተት ሰራዊት ብለው አደሊዋ ድረስ ዘመቱ በዚህ ጊዜ የምስሩ ንጉሥ የአባትህ ገንዘብ እኔጋ ስላለ እባክህ ከእኔ ጋር አተዋጋ መስቀሉን ፣ ሥዕላቱን እና ንዋያተ ቅዱሳቱን እስጥካለሁ አላቸው ( ማብራርያ መስከረም 17 የለጠፋነውን ጽሑፍ ተመልከቱ ) ይህንን ተቀብለው ተመልሰው ለ3 ዓመታት መስቀለኛ ቦታ ፈለጋ በኢትዮጵያ ተራሮች ዞሩ ቅዱስ ዑራኤልም ይራዳቸው ነበር ፡፡ ከሥስት ዓመት ቦኃላም አምባሰል ደርሰው ቦታዋ በመስቀል አምሳል የተቀረጸች መሆኗን አዩ፡፡ መግቢያው ቦታ እጅግ አስቸጋሪ ስለነበር አረፈው በነበሩበት ጊዜ ቅዱስ ዑራኤል ተገልፆ ይህች ደብረ ከዛሬ ጀምሮ ደብረ ከርቤ ትባላለች ፡፡ደብረ ነጐድጓድ ትባለ የነበረውም የካህናትና የነገሥታት መኖርያ ስለሆነች ነው ፡፡ሥላሴን የሚክዱ ሊኖሩባት አይችሉም ፡፡ ወደ ውስጥ ስትገባ ሁለት አብያተ ቤ.ክ ታገኛለህ አንዲቱ #በእግዚአብሔር አብ ስም የተሠራች ናት፡፡ አንዲቱ ደግሞ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም የታነጸች ናት፡፡ እመቤታቸንም ተገልጻለት #በኢትዮጵያ በተሰደድኩበት ጊዜ ለልጅ ልጅ መታሰቢያ ርስት ትሁንሽ ብሎ ስምሽ እስከ ዕለተ ምጽአት ሲመሰገን ይኑርባት ብሎ ሰጥቶኛል እና ሄድ ብላ ቦታዋን #ጠቆመችው፡፡ በ1446 ዓ.ም መስከረም 21 ወደ ተራረው ገብተው አይተው ተደሰቱ በታዘዙትም መሠረት ቅዱስ መስቀሉን በእግዚአብሔር ስም በተሰራው መቅድስ #አስቀመጠው፡፡ መስከረም 21 ቀንም መስቀሉ የተቀመጠበት የእግዚአብሔር አብ ቤ.ክ ቅዳሴ ቤቱ ሆነ ፡፡ ጌታችን በዘባነ ኪሩቤል ላይ ሆኖ አእላፍ መላእክትን አስከትሎ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር መጣ ፡፡ እጅግም ብዙ ቃል ኪዳን ገባለት፡፡ ለቦታዋም ታላቅ ክብርን ሰጣት ደብረ ታቦርም ትሁንልህ አለው፡፡ ፠ #ብዙኃን_ማርያም፤ ፠2ኛ) ደግሞ #ጉባኤ_ኒቅያን ይመለከታል፤ ለ፲፰ኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ለተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ካሉት ደቀ መዛሙርት መካከል አርዮስ፣ አኪላስና እለእስክንድሮስ የሚባሉት ዋነኞቹ ነበሩ፡፡ አርዮስ እውቀቱ በመምህሩ የተመሠከረለት ሊቅ ነበር፡፡ ነገር ግን “እጅግ ጥበብ ያደርሳል ከሞት” እንዳለ ሰሎሞን የተጻፈውን ትቶ ባልተጻፈው ላይ ፍልስፍና ጀመረ፡፡ በምሳ. ፰÷፳፪ ላይ ያለውን ቃል በተሳሳተ መንገድ ፈታው፤ ነገር ግን ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ጠርቶ ቢመክረው ቢገስጸው እንቢ በማለት የክህደት ትምህርቱን ቢቀጥልበት ከሹመቱ አውርዶ አወገዘው፡፡ ተፈጻሜተ ሰማዕት ከደቀመዛሙርቱ መካከል አኪላስን ተክቶ ኅዳር ፲፱ ቀን በሰማዕትነት አረፈ፡፡ አኪላስም የጓደኝነት ፍቅር አድልቶበት አርዮስን ከውግዘት ቢፈታው በመቅሠፍት ሞት ሞተ፡፡ በመንበሩም እለእስክንድሮስ ተተካ፡፡ በዚህ ጊዜ የአርዮስ የክህደት ትምህርት በሀገሪቱ ሞላ፡፡ ይህ ነገርም እየተባባሰ በመሔዱ በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ዘንድ ተሰማ፡፡ ንጉስ ቈስጠንጢኖስም ይህን ሲሰማ ለአርዮስ ጥያቄ መልስ ይሠጥበት ዘንድ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጕባኤ እንዲደረግ ሰኔ ፳፩ ቀን አዋጅ አስነገረ፡፡ ይህንን አዋጅ የሰሙት ሊቃውንት ሁሉ መስከረም ፳፩ ቀን የእመቤታችን እለት ተሰባሰቡ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ “ለምን ቈስጠንጢኖስ መልዕክት ከላከበት ጊዜ በኋላ ወዲያውኑ ለምን አልመጡም? ለምን ዘገዩ?” የሚለው ጥያቄ ይነሳል፡፡ ምክንያቱም፤ #አንደኛ መጓጓዣ ችግር ስለነበር፤ #ሁለተኛ ሁሉም ሊቃውንት አስተማሪዎች በመሆናቸው ለምዕመናኑ (ለተማሪዎቻው) ሌላ መምህር ማዘጋጀት ስለነበረባቸው፤ #ሦስተኛ ደግሞ በእድሜ የገፉ ስለነበሩ አንድም ሊቃውንቱ ሲያስተምሩ በአላውያን ነገሥታት ባላመኑ ሰዎች ግፍ ይድርስባቸው ስለነበር ነው፡፡ ለምሳሌ ቶማስ ዘመርዓስ በእነዚህ ሰዎች በግፍ እግሩና እጁ ተቆርጦ ስለነበር ለማስተማር በቅርጫት ይዘውት ነበር የሚጓዘው፡፡ ወደ ጕባኤውም ሲመጣ ደቀ መዛውርቱ ያመጡት #በቅርጫት ይዘውት ነበር፡፡ ከዚህ በኋላ 2,340 ሊቃውንት መስከረም ፳፩ ቀን ተሠባሰቡ፡፡ ከእነዚህ መካከል ግን 318ቱ ሊቃውንት ‹‹ዘእሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ ›› በማለት በሃይማኖታቸው የጸኑ ነበሩ፡፡ ጉባኤውን ከመጀመራቸው በፊት አርባ (፵) ቀን ሱባኤ እስከ ኅዳር ዘጠኝ (፱) ቀን ይዘውና ጕባኤውን አድርገው በአንዲት ቀን ያንን ታላቅ መናፍቅ አርዮስን ድል ነሥተውታል፡፡ ከዚህ ጋር አያይዘውም የኃይማኖታችን መሠረት የሆነውን ጸሎተ ሃይማኖትን አዘጋጅተዋል፡፡ የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ!!! ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

እንኳን ለመስከረም 21፤ ለብዙኃን ማርያም ዓመታዊ የንግሥ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን። የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ!!! Te
+1
እንኳን ለመስከረም 21፤ ለብዙኃን ማርያም ዓመታዊ የንግሥ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን። የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ!!! Telegram: ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።

#ቅዱስ_መስቀል በመስቀል ከጠላትነት ድነናል፤ በመስቀል ወደ እግዚአብሔር አንድነት ተመልሰናል፡፡ በመስቀል ዲያብሎስ አርነት ወጥተናል፤ በመስቀል ከሞትና ከጥፋት ድነናል፡፡ ብሥራተ መስቀል ባልተነገረበት ዘመን በሞት ጥላ ሥር ተይዘን ነበር፤ አሁን ብሥራተ መስቀል በተገለጠበት ጊዜ ግን ህልውና እንኳን እንደሌለው አድርገን ቈጥረን የዘለዓለም ሕይወትን እየናፈቅን ሞትን ንቀነዋል፡፡ ብሥራተ መስቀል ባልተነገረበት ዘመን ለገነት እንግዶች ነበርን፤ መስቀል በተገለጠ ጊዜ ግን ወንበዴስ እንኳን ለገነት የተገባ ሆኖ ተገኘ፡፡ የሰው ልጅ እንደዚህ ካለ ጨለማ መጠን ወደ ሌለው ብርሃን፣ ከሞት ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት፣ ከመዋቲነት ወደ ኢመዋቲነት ታድሶ ተሸጋገረ፡፡ ዓይነ ልቡና ባለማወቅ ጽልመት ከመታወር ድኖ በመስቀል የዕውቀት ብርሃን ተጥለቀለቀ፡፡ እዝነ ልቡና ካለማመን ድንቁርና ወጥቶ የእግዚአብሔርን ቃል ወደ መስማት ተመለሰ፤ ዕውራንም ብርሃናቸው ተመልሶላቸው የእግዚአብሔርን ክብር ማየት ተችሎአቸዋል፡፡ በቅዱስ መስቀሉ የተሰጡን ሀብታት እነዚህ ናቸው፡፡ በቅዱስ መስቀሉ ያልተሰጡን በረከቶችስ ምን አሉ? እነሆ ቅዱስ መስቀሉ ተገልጧል ፤ በእግዚአብሔር ማመንም ተመልሷል፤ የእውነት ወንጌልም ወደ ዓለም ሁሉ ደርሷል፡፡ ቅዱስ መስቀሉ ተገልጧል ፤ ሰማዕታትም ከመስቀል በኋላ ሞት ሞት መኾኑ እንደ ቀረና የሹመት የሽልማት ማሳ መኾኑን ዐውቀው አብረው ተገልጠዋል፤ በክርስቶስ ማመንም በሁሉም ዘንድ ተሰራጭቷል፡፡ ቅዱስ መስቀሉ ተገልጧል ፤ በእርሱም ሞት ራሱ ሞቷልና ትንሣኤ ሙታንም ተገልጧል፤ ሕይወትም ታይታለች፤ መንግሥተ እግዚአብሔርም እንደዚሁ እርግጥ ኾናለች፡፡ ቅዱስ መስቀሉ ለእነዚህ ኹሉ ነገሮች ምክንያት ኾኗል፡፡ በመስቀሉ እግዚአብሔርን ማመስገን ተማርን፡፡ እንግዲህ ከቅዱስ መስቀሉ ይልቅ ሌላ የተወደደ ምን አለ? እኮ ከቅዱስ መስቀሉ በላይ ለነፍሳችን የሚረባት ወይም የረባትና የጠቀማት ሌላ ምን አለ? ስለዚህ በሙሉ ልባችን ይህን እንመስክር እንጂ ስለ ቅዱስ መስቀሉ ለመናገር ቅንጣት ታህልስ እንኳን አንፈር፡፡ #መልካም_የደመራ_በዓል። Telegram: ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

#እንኳን_ለብርሃነ_መስቀሉ_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ_አደረሰን። #የመስቀል_ደመራ በዓል #ታሪክና_አከባበር ✍🏽👉ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ከወደቀበት መርገም ያድነው ዘንድ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ በ33 ዓመቱ በራሱ ፈቃድ በመስቀል ላይ ተሰቀለ፡፡ በመገረፉ ቁስል እኛ ተፈወስን (1ጴጥ 2፥24):: በስቅለቱም ዲያብሎስን ድል ነሥቶ በወህኒ /በሲዖል/ ለነበሩ ነፍሳት ነጻነትን ሰበከላቸው (1ጴጥ 3፥18-19):: የሰው ልጅ በሙሉ ከዲያብሎስ ባርነት ፍጹም ነጻ ወጣ:: ሰላምንም ያደርግ ዘንድ ጥልንም በመስቀሉ ገድሎ ሕዝብና አሕዛብን በአንድ አካል ከራሱ ከእግዚአብሔር ጋር አስታረቀ (ኤፌ 2፥16)፡፡ ከፍተኛ ወንጀል የሠሩ ሰዎች ብቻ ይሰቀሉበት የነበረው መስቀል ከጌታ ስቅለት በኋላ የመዳን ምልክት ሆነ:: ዳሩ ግን ጌታ የተሰቀለበት መስቀል ተአምራትን በማድረጉ የታወኩ አይሁድ መስቀሉን ከሰዎች እይታ ለመሠወር ወሰኑ:: ጉድጓድ ቆፍረው ቀበሩት:: መስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ ለ300 ዓመታት ያህል የቆሻሻ መጣያና ማከማቻም አደረጉት:: ምንም እንኳን አይሁድ ለጊዜው መስቀሉን ከዐይን ለመሰወር ቢችሉም ከክርስቲያኖች ልቡና ግን ሊያወጡት አልቻሉም:: የመስቀሉ ብርሃን በልቡናቸው የሚያበራ ክርስቲያኖች እየበዙ መጡ:: መስቀሉንም መፈለግ ጀመሩ:: #የንግሥት_እሌኒ_ድካምና_ፍሬ 👉ንግሥት እሌኒ ልጇን ቆስጠንጢኖስን ከልጅነቱ ጀምሮ ስለ ክርስትና ሃይማኖትና ስለ ክርስቲያኖች መከራ ታስተምረው ስለነበር በክርስቲያኖች ላይ የነበረው አመለካከት በሮም ከነገሡት ቄሣሮች ሁሉ የተሻለ ነበር፡፡ ቆስጠንጢኖስ የሮም ንጉሠ ነገሥት ከሆነ በኋላ በ300 ዓመታት ውስጥ ለመጀመርያ ጊዜ ለክርስቲያኖች የነጻነት ዐዋጅ ዐወጀ፡፡ ክርስትናም ብሔራዊ ሃይማኖት ሆነች፡፡ ንግሥት እሌኒም የተፈጠረውን አመች ሁኔታ በመጠቀም የጌታችንን መስቀል ከተቀበረበት ለማውጣት በ327 ዓ/ም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች፡፡ ንግሥት እሌኒ ልጇ ቆስጠንጢኖስ ክርስቲያን ከሆነላት ወደ ኢየሩሳሌም ሔዳ መስቀሉን ለመፈለግ እንዲሁም በኢየሩሳሌም ያሉ ቅዱሳት መካናትንና አብያተ ክርስቲያናትን ለማሳነፅ ለእግዚአብሔር ተሳለች፡፡ ከዚህ በኋላ ቆስጠንጢኖስ አምኖ በ337 ዓ/ም ተጠመቀ፡፡ ቅድስት እሌኒም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች እንደደረሰችም ስለ ክብረ መስቀል መረመረች ጠየቀች፡፡ ቦታውን የሚያስረዳት ግን አላገኘችም፡፡ አይሁድ የተቀበረበትን ቦታ ለማሳየት ባይፈልጉም በኋላ ባደረገችው ጥረት አረጋዊው ኪራኮስ የጎልጎታን ኮረብታ አመላከታት ዳሩ ግን ኪራኮስ ዘመኑ ከመርዘሙ ጋር ተያይዞ በአካባቢው ከነበሩት ከሦስቱ ተራሮች ውስጥ መስቀሉ የሚገኝበት የትኛው እንደሆነ ለይቶ ማወቅ አልቻለም፡፡ ንግሥት እሌኒ ከሦስቱ ተራሮች የቱ እንደሆነ ለመለየት በእግዚአብሔር መልአክ እርዳታ ደመራ አስደምራ ብዙ እጣንም በመጨመርና በማቃጠል ጸሎት ተያዘ፡፡ የእጣኑ ጢስ ወደ ሰማይ በመውጣት በቀጥታ ተመልሶ መስቀሉ ባለበት ተራራ ላይ በማረፍና በመስገድ መስቀሉ ያለበትን ትክክለኛ ስፍራ አመለከታት፡፡ ቅዱስ ያሬድም ጢሱ ሰገደ ብሎታል፡፡ ከዚያም መስከረም 16 ቀን ቁፋሮው እንዲጀመር አዘዘች፡፡ ሰባት ወር ያህል ከተቆፈረ በኋላ መጋቢት 10 ቀን ሦስት መስቀሎች በአንድነት ተገኙ፡፡የክብር ባለቤት ጌታችን የተሰቀለበት የትኛው እንደሆነ ለማወቅ ተቸገሩ፡: መስቀሎቹን ወስደው በሞተ ሰው በተራ ቢያስቀምጡ ጌታችን የተሰቀለበትና በዕለተ ዐርብ ተሰቅሎ የዋለበትና በደሙ መፍሰስ የተቀደሰው መሰቀል የሞተውን ሰው በማስነሣት በሠራው ተአምር ሌሎቹ ሁለቱ ታምራት ባለማድረጋቸው የጌታን መስቀል ለይቶ ማወቅ ተችሏል። እሌኒና ክርስቲያኖች ሁሉ ለመስቀሉ ሰገዱለት፡፡ በየሀገሩ ያሉ ክርስትያኖች ሁሉ የመስቀሉን መገኘት በሰሙ ጊዜ መብራት አብርተው ደስታቸውን በመግለጥ ለዓለም እንዲታወቅ አደረጉ፡፡ ንግሥት እሌኒ ለመስቀሉ ቤተ መቅደስ ከሠራችለት ጊዜ ጀምሮ #በመስከረም_17 ቀን አሁን በኢትዮጵያ እንደሚከበረው በክርስቲያኖች ዘንድ መስቀል ይከበራል። #መልካም_የደመራ_በዓል። Telegram: ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

#እንኳን_ለብርሃነ_መስቀሉ_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ፤_አደረሰን። መስቀል ዕፀ ሕይወት ነው። መስቀል ዕፀ መድኃኒት ነው። መስቀል ዕፀ ትንቢት ነው። መስቀል ዕፀ ዕረፍት ነው። መስቀል ለሚጋደሉ የድል
+7
#እንኳን_ለብርሃነ_መስቀሉ_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ፤_አደረሰን። መስቀል ዕፀ ሕይወት ነው። መስቀል ዕፀ መድኃኒት ነው። መስቀል ዕፀ ትንቢት ነው። መስቀል ዕፀ ዕረፍት ነው። መስቀል ለሚጋደሉ የድል አክሊል፤ ወደ በጉ ሰርግ ለተጠሩትም የሰርግ ልብሳቸው ነው። መስቀል የማይነጥፍ ምንጭ፣ በቁዔትም ጥቅምም የሞላበት የክብር ጉድጓድ ነው። 1ኛ ቆሮ. 1፥18 የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ! ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ:👇🏽👇🏽👇🏽 #መልካም_የደመራ_በዓል። Telegram: ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv ቃለ እግዚአብሔር ለሁሉም ይዳረስ ዘንድ ለወዳጆችዎ ያካፍሉት።

#ነገ_ለአንተ_የተሸለ_ነው ያለህበት ዛሬ ለአንተ እጅግ አሰልቺ ከሆነ ለነገህ ኑር። በዚህ ነገህ ዉስጥ አንተን ለማረጋጋት የእግዚአብሔር እጅ ወደ አንተ መዘርጋቱን ተመልከት፡፡ ይህንን ካደረግህ በዚህ ነገህ ዉስጥ ለችግሮችህ ብዙ መፍትሔዎችን መመልከት ትችላለህ። የአንተ ዛሬ ጨለማ ከሆነ ነገህ በፊትህ የብርሃን መስኮቶችን ይከፈትልሀል ፡፡ ቅዱሳን ነገ ለሚያገኙት የዘለዓለም ህይወት ስለ ኖሩ ተስፋቸዉን ሁሉ በዚህ ነገ ላይ ጥለዉት ነበር። ሳዖል ባሳደደዉ ጊዜ ነብዩ ዳዊት የኖረዉ ለነገዉ ነዉ። ነብዩ ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ዉስጥ ሳለ የኖረዉም ለነገዉ ነዉ። ቅዱስ ዮሴፍ በወኅኒ ሳለ አባቱ ቅዱስ ያዕቆብ ደግሞ በወንድሙ በዔሳዉ በተሳደደ ጊዜ የኖሩት ለነጋቸዉ ነበር፤ ያዕቆብም ከመሰደድ ዮሴፍም ከግዞት ህይወት እንደሚወጡ በእግዚአብሔር ታምነዋልና። ነገሮች ለአንተ አስቸጋሪ ከሆኑ ለራስህ ነገ መፍትሔ ይገኝላቸዋል ብለህ ንገረዉ። ከዚህም በኋላ ለዚህ ነገህ በፈገግታና በደስታ ኑር!! #ብጹዕ_ወቅዱስ_አቡነ_ሽኖዳ የደጉ ሳምራዊ ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ!ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ: 👇🏽👇🏽👇🏽 ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv

#የተሠጠህን_ቁጠር ሔዋን ከዕባብ ጋር እየተነጋገረች ነው። የመጀመሪያ ጥፋትዋ ካለደረጃዋ ወርዳ ከዕባብ ጋር ወዳጅነት መጀመርዋ ሳይሆን አይቀርም። ዕባብ ደግሞ የስይጣን አንደበት ነበረ። ሰይጣን እንዲ
#የተሠጠህን_ቁጠር ሔዋን ከዕባብ ጋር እየተነጋገረች ነው። የመጀመሪያ ጥፋትዋ ካለደረጃዋ ወርዳ ከዕባብ ጋር ወዳጅነት መጀመርዋ ሳይሆን አይቀርም። ዕባብ ደግሞ የስይጣን አንደበት ነበረ። ሰይጣን እንዲህ አላት:- በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአልን? አላት። ልብ አድርጉ እግዚአብሔር "ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ" አላለም። የከለከለው አንዲት ዛፍ ነው:: ሰይጣን ግን ሁሉን ተከልክላችሁዋል? ብሎ እንዳላዋቂ ጠየቀ። ሰይጣን በመጽሐፍ ቅዱስ ንግግሩን የከፈተው በውሸት ነበረ። ዓላማው ከሔዋን መረጃ ለማግኘት አልነበረም። ሔዋን እስከዛሬ ያላሰበችውን ማሳሰብ ነበር። ብሉ ተብሎ ከተሠጣቸው ብዙ ሺህ ዛፍ ይልቅ የተከለከሉትን አንዲት ዛፍ አሳይቷት ሔደ። ከዚያች ደቂቃ ጀምሮ ስላልተሠጣት ማሰብ ጀምራ ደስታዋን አጣች። የተከለከለችውን በልታ የተሠጣትን ብዙ ሥጦታ ከነሠጪው አጣች። :-ወዳጄ የቀደመው እባብ ዛሬም መርዙን ይረጫል-:- በሕይወታችን ከተሠጠን ብዙ ነገር ይልቅ ያልተሠጠንን ጥቂት ነገር እናስባለን። ገንዘብ እንደሌለህ እያሰብክ ጤና እንዳለህ ትረሳለህ። ጫማ እንደሌለህ እያሰብክ እግር እንዳለህ ትረሳለህ። አልጋ እንደሌለህ እያሰብክ እንቅልፍ እንዳለህ ትረሳለህ። ስለዚህ ውስጥህ ያለውን የዕባቡን ድምፅ አትስማ ከሌለህ ይልቅ ያለህ ይበልጣልና የተሠጠህን ቁጠር። የበለጠ መረጃ እንዲደርሶ የደጉ ሳምራዊ መልካምነት ቴሌግራም ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ!ለወዳጅ ዘመድዎ እንዲሁም ለጓደኛዎ ያጋሩ: 👇🏽👇🏽👇🏽 ☞ https://t.me/+S3QVyScP7Saom-Lv