Muler IT Solutions Ethio GSM, Ethio Dish, ሞባይል ጥገና፣ ዲሽ ሶፍትዌር፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ ዌብሳይት ስራ
Kanalga Telegram’da o‘tish
👉👉 አዳዲስና ትኩስ የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎችንና፣ ሞያ አዘል ፅሁፎችን፣ ጥያቄና መልሶችን፣የኮምፒውተርና የዲሽ ሪሲቨር ሶፍትዌሮችን፣ ጠቃሚ የሞባይል አፖችን ከተለያዩ የ Hacking እና Technical Trick ና ቲፖች የሚገኙበት ምርጥ ቻናል:: ለማንኛውም ጥያቄ @mulerjolly ን ወይም @africustomercare ን ይጠቀሙ!! ወይም በ 0938020816 ይደውሉ።
Ko'proq ko'rsatish2 846
Obunachilar
+424 soatlar
+77 kun
+2330 kun
Postlar arxiv
በ"Facebook" ፕሮፋይል ላይ Meta Verified ምልክት እንዴት ማስቀመጥ ይቻላል?
በ" Facebook" ፕሮፋይል ላይ Meta Verified የማረጋገጫ ምልክት ለማግኘት በቀጥታ መግዛት ወይም መመዝገብ ይቻላል።
#በFacebook App ላይ የሚደረጉ ደረጃዎች፦
1. Facebook App ይክፈቱ።
2. ወደ Profile ይግቡ።
3. ☰ Menu - Settings & privacy - Settings ይጫኑ።
4. Meta Verified የሚለውን አማራጭ ይፈልጉ።
5. ከታየ Subscribe / Get Meta Verified ይጫኑ።
6. የክፍያ ሂደቱን ይፈጽሙ። ክፍያውን ከፈጸሙ በኋላ Meta ማረጋገጫውን ያከናውናል።
7. Facebook የሚጠይቀውን የመታወቂያ ማረጋገጫ (ID verification) ያጠናቅቁ።
8. ማረጋገጫው ከተፈቀደ እና ከተረጋገጠ በኋላ verified ምልክቱ በፕሮፋይልዎ ላይ ይታያል።
1. Elicit.com — ለምርምር ሥራዎች የሚያገለግል የኤአይ መተግበሪያ ሲሆን የምርምር ጽሑፎችን በፍጥነት ይፈልጋል። የሚፈለጉ መረጃዎችን ለይቶ ያወጣል፤ ማጠቃለያዎችን ለመሥራት ያስችላል፡፡
2. Otter.ai — በድምፅ የተቀረጹ መረጃዎችን፣ ንግግሮችን በቀጥታ ወደ ጽሑፍ የሚቀይር የድምፅ-ወደ-ጽሑፍ ሶፍትዌር ነው፡፡
3. Decktopus.com — አርዕስት እና መረጃ ብቻ በመስጠት በአጭር ጊዜ ውስጥ ውብ እና ሙያዊ የሆኑ የፓወር ፖይንት ማቅረቢያዎችን (Slides) በኤአይ የሚሰራ መተግበሪያ ነው፡፡
4. Gitmind.com — ሀሳቦችን፣ ዕቅዶችን እና ፕሮጀክቶችን በምስላዊ የሀሳብ ካርታ (Mind Map) እና በሥራ ፍሰት ንድፎች መልክ ለማደራጀት ያገለግላል፡፡
5. Lightpdf.com — የፒዲኤፍ (PDF) ፋይሎችን አርትኦት ለመስራት፣ ለመለወጥ፣ ለማዋሃድ እና በፋይሎቹ ላይ ፊርማ ለማስቀመጥ የሚያስችል የኤአአይ መተግበሪያ ነው፡፡
6. Picwish.com — የፎቶዎችን ጀርባ (Background) ለማስወገድ፣ የምስል ጥራትን ለማሻሻል እና አላስፈላጊ ነገሮችን ከምስል ላይ ለማንሳት የሚያስችል የፎቶ ማስተካከያ ኤአይ ነው፡፡
7. Reccloud.com — ስክሪን ለመቅረፅ፣ ቪዲዮዎችን ለማጫወት እና በኤአይ ታግዞ አጫጭር የቪዲዮ ይዘቶችን ለመፍጠር የሚያገለግል ፕላትፎርም ነው፡፡
8. Kapwing.com — ቪዲዮዎችን ለመቁረጥ፣ የግርጌ ጽሑፍ (Subtitle) ለመጨመር እና ይዘቶችን በማህበራዊ ሚዲያ መልክ ለማዘጋጀት የሚያስችል የኦንላየን ቪዲዮ ማስተካከያ ነው፡፡
9. Podcastle.ai — የፖድካስት ድምፆችን ለመቅረፅ፣ የጀርባ ጫጫታዎችን ለማስወገድ እና ጥራታቸውን ጠብቆ ለማዘጋጀት የሚረዳ የድምፅ ማስተካከያ ኤአይ ነው፡፡
10. Consensus.app — ሳይንሳዊ ጥያቄዎችን ሲጠይቁ ከታመኑ የምርምር ጽሁፎች በማስረጃዎች የተደገፉ መልሶችን ፈልጎ የሚያቀርብ የኤአይ መተግበሪያ ነው፡፡
11. Researchrabbit.ai — በተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ተመሳሳይ የምርምር ጽሁፎችን ለመፈለግ እና ጽሁፍን በግራፍ መልክ ለማሳየት የሚያገለግል ነው፡፡
12. Zotero.org — ለምርምር ሥራዎች የሚያስፈልጉ መጻሕፍት እና የጽሑፍ ምንጮችን (References) ለማደራጀት፣ ለማስቀመጥ እና ለመጥቀስ የሚያገለግል ነፃ የኤአይ መተግበሪያ ነው፡፡
13. Scite.ai — የምርምር ጽሁፎች በሌሎች ተመራማሪዎች እንዴት እንደተጠቀሱ (በድጋፍ፣ በተቃውሞ ወይም በጥቀስ መልክ) ለመተንተን የሚያስችል መተግበሪያ ነው፡፡
14. Scholarcy.com — ረጅም የምርምር ጽሁፎችን፣ መጻሕፍት እና ሪፖርቶችን በማንበብ ዋና ዋና ነጥቦቻቸውን በአጭሩ አጠቃልሎ የሚያቀርብ መተግበሪያ ነው፡፡
15. Connectedpapers.com — የአንድን የምርምር ርዕስ መነሻ በማድረግ ተዛማጅነት ያላቸውን ሌሎች ጥናቶች በምስላዊ ካርታ መልክ የሚያሳይ መተግበሪያ ነው፡፡
16. Writefull.com — ለአካዳሚክ እና ለሳይንሳዊ ጽሑፎች የተዘጋጀ የሰዋስው፣ የስፔሊንግ እና የቃላት አጠቃቀም ማስተካከያ የኤአይ መተግበሪያ ነው፡፡
AI-tools-image-2025-10-c7463f1a9aa7ec350de4e7b45b03c156.webp0.12 KB
በጉጉት የተጠበቀው ቀን በስተመጨረሻም ደረሰ ! 🥊🔥
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ETFC (የአድዋ ፋይት ናይት) ታላቁ የፍልሚያ ምሽት አንድ ቀን ቀረው !
MMA | Boxing | Muay Thai
በዚያ ምሽት ከዓባይ ቲቪ ውጭ ሌላ ቀጠሮ አይታሰብም!
ሙሉ ግጥሚያውን በቤትዎ ሆነው፣ ጥራት ባለው የካሜራ ሽፋን የኢትዮጵያ ምርጥ በሆነው ዓባይ ቲቪ በ”ቀጥታ ስርጭት” (Live) ይመልከቱ።
📅 ነገ ሃሙስ ነሃሴ 21 ምሽት
🕕 12፡00 ሰዓት ጀምሮ
📺 በዓባይ ቲቪ (ቀጥታ ስርጭት)
የታሪክ ሰሪዎቹን የመጨረሻ ፍልሚያ በዓይንዎ ይመልከቱ!
ዓባይ ቲቪ - የኢትዮጵያ ምርጥ!
#AbbayTV #ETFC #adwafightnight #mma #boxing #muaythai #fight #live @etfc @shegaevent @sweatbox
🔷 ውድ የቻናላችን ተከታዮች ተከታዮች ከስር እና ከላይ ያሉት ስለ ፎሬክስ ትሬዲንግ የተፃፉ ምርጥ ምርጥ መፃህፍቶች ናቸው። አብዛኞቹ በውድ ዋጋ የፎሬክስ ኮርስ ሲገዙ የሚሰጡ ሲሆኑ ሌሎቹ ደሞ በዶላር የሚሸጡ ናቸው። ከብዙ ጥረት በኋላ እነዚህ መፃህፍት እጃችን ውስጥ ገብተዋል። እኛም ለውድ የቻናላችን ተከታዮች በነፃ አውርዳችሁ እንድትጠቀሙበት ለቀንላችኋል። ይመቻችሁ!
💎 መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ ሼርና ፎርዋርድ ማድረግ አይርሱ
🔺 @muleritsolutions2
🤖🎙️ማንኛውንም ረጅም PDF ወይም ማስታወሻ ወደ ማራኪ ፖድካስት (Audio) የሚቀይረው የ-AI ድንቅ!
🔷 መጽሐፍ፣ የትምህርት ሞጁል ወይም ረጅም ሪፖርት ለማንበብ ጊዜ የላችሁም? ጽሑፎችን በራሱ አጥንቶ ሁለት ሰዎች እርስ በእርስ እየተወያዩ የሚያስረዱበትን የድምፅ ፋይል (Podcast) በነፃ የሚያዘጋጀውን መሣሪያ ያውቃሉ?
🎧 Google NotebookLM (notebooklm.google.com)ይህ በነፃ የሚሠራ የጉግል AI መሣሪያ ማንኛውንም ፋይል ወደ ድምፅና ወደ ጥናት ማጠቃለያ ይለውጣል፦
🎙️ Audio Overview (አውቶማቲክ ፖድካስት)፦ PDF፣ የWord ሰነድ ወይም የጽሑፍ ሊንክ ስታስገቡለት፤ ሁለት የ-AI አቅራቢዎች በድምፅ እርስ በእርስ እየተወያዩ መጽሐፉን የሚያስረዱበትን ማራኪ የድምፅ ፋይል ይፈጥርላችኋል።
📚 Instant Study Guide (የጥናት ረዳት)፦ የትምህርት ማስታወሻዎችን በማስገባት አውቶማቲክ ማጠቃለያዎችን፣ የፈተና ጥያቄዎችን እና ዋና ዋና ነጥቦችን በሰከንዶች ውስጥ ያዘጋጃል።
🎯 ትክክለኛ መልስ (ከእርስዎ ሰነድ ብቻ)፦ ከውጭ የኢንተርኔት መረጃ ሳይቀላቅል፤ እርስዎ ከሰጡት ሰነድ ብቻ ተመስርቶ ፍጹም ትክክለኛ መልስ ይሰጣል።
💡 ማን ይጠቀምበታል?
ተማሪዎች፣ ተመራማሪዎች፣ የመጽሐፍ ወዳጆች እና በጉዞ ላይ እያሉ መረጃ ማዳመጥ የሚፈልጉ በሙሉ!
💎 መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ ሼርና ፎርዋርድ ማድረግ አይርሱ
🔺 @muleritsolutions2
✅የኤሌክትሪክ አጥር (Electric Fence) አሰራር እና የደህንነት መመሪያዎች❗️
======
👉ዘመናዊ የደህንነት ጥበቃ ላይ የኤሌክትሪክ አጥር (Electric Fence) በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል። ነገር ግን ብዙ ሰዎች "ይህ አጥር ሰው ይገድላል❓" የሚል ስጋት አላቸው።
👉አንድ የኤሌክትሪክ አጥር በስርዓቱ ሲገጠም ህይወት ሳያጠፋ ነገር ግን ከፍተኛ የሆነ ድንጋጤና ህመም በመፍጠር ሌባን የሚያባርር እጅግ አስተማማኝ የደህንነት ዘብ ነው!❗️
👉ዛሬ የዚህን ሲስተም ልብ የሆነውን 'Energizer' (ኢነርጃይዘር) አሰራርን እና ሳይንሳዊ የደህንነት ሚስጥሮችን እንደ ባለሙያ እንመረምራለን❗️ 👇
1⃣. Energizer ምንድን ነው❓ እንዴትስ ይሰራል❓
👉Energizer' ማለት መደበኛውን የቤታችንን መብራት (220V AC) ወስዶ እጅግ ከፍተኛ ወደሆነ ቮልቴጅ (በአማካይ ከ 7,000V እስከ 10,000V DC) የሚቀይር፣ ነገር ግን ሃይሉን በቅፅበት (Pulse) ወደ አጥሩ ሽቦዎች የሚለቅ ማሽን ነው።👉 የፐልስ (Pulse) ሚስጥር፦
👉አጥሩ ላይ ያለው ኤሌክትሪክ እንደ ቤታችን መብራት ቀጣይነት ያለው (Continuous) አይደለም። ከ 1 ሰከንድ ባነሰ የጊዜ ልዩነት (ለ 3 ሚሊ-ሰከንዶች ብቻ) ብልጭ እያለ የሚጠፋ ምት (Pulse) ነው። ይህ አሰራር ሰውየው አጥሩን ሲነካ ኤሌክትሪኩ ከተጣበቀበት ላይ በሃይል እንዲፈናጠር (Let-go effect) ያደርገዋል እንጂ አያጣብቀውም❗️
2⃣. 10,000 ቮልት (Voltage) ለምን ሰው አይገድልም❓ (The Physics)
👉ይህ የብዙዎች ጥያቄ ነው!❗️
👉የቤታችን 220 ቮልት አደገኛ ሆኖ ሳለ፣ የኤሌክትሪክ አጥር 10,000 ቮልት ለምን ህይወት አያጠፋም❓
👉 ሚስጥሩ ያለው በ Joules (የጉልበት መጠን) እና Amps (የከረንት መጠን) ላይ ነው❗️
👉ቮልቴጁ (Voltage) ከፍተኛ የሆነው የሰውን የቆዳ መከላከያ (Resistance) በስቶ፣ አልፎም ልብስን ሰንጥቆ ሾክ ማድረግ እንዲችል ነው። ነገር ግን ገዳይ የሆነው የከረንት (Current) መጠኑ እጅግ በጣም አነስተኛ (በሚሊ-አምፒየር የሚቆጠር) እና የሚለቀቀው ጉልበት (Energy) እንደ ስታንዳርዱ ከ 5 እስከ 8 ጁል (Joules) ብቻ ነው። ይህ ከፍተኛ ህመም እና የጡንቻ መኮማተር ይፈጥራል እንጂ ህይወትን ፈፅሞ አያጠፋም።
3⃣. የአለም-አቀፍ የደህንነት እና የገጠማ ስታንዳርዶች (Installation Standards)እውነተኛ ባለሙያ ሲያገጥም እነዚህን ስታንዳርዶች ማሟላት ህጋዊና ሙያዊ ግዴታው ነው፦
🔹. ራሱን የቻለ ኧርዝ (Independent Earthing)፦
👉የኤሌክትሪክ አጥር በትክክል ሾክ እንዲያደርግ ከፈለጋችሁ ከቤቱ ኧርዝ የተነጠለ፣ እጅግ ጥራት ያለው የኧርዝ (Earth) ሮድ መሬት ውስጥ መቅበር ያስፈልጋል። ሌባው አጥሩን ነክቶ መሬት ሲረግጥ የኤሌክትሪክ ዑደቱ (Circuit) የሚሞላው በመሬት በኩል ነው❗️ኧርዝ ከሌለ ሲስተሙ ዜሮ ነው❗️
🔹 የማስጠንቀቂያ ምልክቶች (Warning Signs)፦
👉በየ 10 ሜትሩ ርቀት ላይ ቢጫ ቀለም ያላቸው የማስጠንቀቂያ ታፔላዎች (Warning: Electric Fence) በግልፅ በሚታይ ቦታ መታሰር አለባቸው። አደጋ ቢፈጠር ህጋዊ ተጠያቂነትን ያድናል❗️
🔹 ከዕፅዋት ነፃ ማድረግ (Vegetation Clearance)፦
👉የዛፍ ቅጠል ወይም ቅርንጫፍ አጥሩን ከነካ፣ ቮልቴጁ በዛፉ በኩል ወደ መሬት ስለሚሾልክ (Leakage) ሲስተሙ ቮልቴጁን ያጣል፤ ይህ ደግሞ ሌሊት አላስፈላጊ ጩኸት (False Alarm) ይፈጥራል።
👉ጥሩ የኤሌክትሪክ አጥር ገጠማ ስራ ሁልጊዜ ከ Siren (የማስጠንቀቂያ ጩኸት) እና ከ Backup Battery ጋር መያያዝ አለበት። ሌባው ሲስተሙን ለማቋረጥ ሽቦውን ቢቆርጠው፣ ወይም አንደኛውን ሽቦ ከሌላኛው ጋር ቢያጋጨው (Short Circuit ቢያደርገው) ቮልቴጁ መቋረጡን ሲስተሙ ስለሚረዳ (Voltage drop detection)፣ ኢነርጃይዘሩ ወዲያውኑ ከፍተኛ ጩኸት በማሰማት አካባቢውን ይቀሰቅሳል❗️
👉 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ስልጠናዎች በተግባር (Practically) እየሰሩ በመማር የዘመኑ ከፍተኛ ተከፋይ እና ተፈላጊ ባለሙያ ይሁኑ❗️
1️⃣ አድቫንስድ የቤት ዕቃዎች ጥገና(ፍሪጅ፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽን፣ ስማርት ቲቪ፣ እና የኤሌክትሪክ ምድጃ/ኦቨን ጥገና)
2️⃣ አድቫንስድ የደህንነት ሲስተም ዝርጋታ (CCTV ካሜራ፣ ፋየር አላርም፣ አክሰስ ኮንትሮል፣ የኤሌክትሪክ አጥር፣ ታይም አቴንዳንስ፣ ቪዲዮ ኢንተርኮም ወዘተ...)
3️⃣ አድቫንስድ የኢንዱስትሪ ማሽነሪዎች ጥገና (የጀነሬተር ጥገና፣ ሞተር ኮንትሮል ሲስተምና ኤሌክትሪካል ሞተር ሪዋይንዲንግ)
4️⃣ አድቫንስድ አውቶካድ ኤሌክትሪካል ዲዛይን
5️⃣ አድቫንስድ የሕንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታና ጥገና
👉 ምንጭ:- አሜን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት
💎 መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ ሼርና ፎርዋርድ ማድረግ አይርሱ
🔺 @muleritsolutions2
🟢 የደበዘዙ ፎቶዎችን ጥራት መጨመር፣ ከፎቶ ላይ አላስፈላጊ ሰዎችን/ነገሮችን ማጥፋት ወይም የቪዲዮ ባክግራውንድ (Background) ማስወገድ ፈልገው ከባድ ሶፍትዌሮች ተቸግረዋል ❓
🟡 ዛሬ ያለ ምንም ሙያዊ የኤዲቲንግ ዕውቀት፣ በሰከንዶች ውስጥ ፎቶዎችንና ቪዲዮዎችን በከፍተኛ ጥራት ኤዲት የሚያደርጉልን 3 አዳዲስና ነፃ የ-AI መሣሪያዎች ይዘንላችሁ ቀርበናል ።
🎨 ፎቶና ቪዲዮ ኤዲት የሚያደርጉ 3 አዳዲስ የ-AI መሣሪያዎች፦
1. Clipdrop (clipdrop.co)
🎯 ምን ይሠራል? ከፎቶ ላይ ያልፈለጉትን ሰው፣ ጽሑፍ ወይም አላስፈላጊ ነገር በጥራት የሚያጠፋ (Cleanup)፣ የፎቶዎችን ብርሃንና ጥራት የሚያስተካክል እጅግ ድንቅ መሣሪያ ነው።
2. Upscayl (upscayl.org)
🎯 ምን ይሠራል? የቆዩ፣ የደበዘዙ ወይም ጥራታቸው ዝቅተኛ የሆኑ ፎቶዎችን (Low Resolution) ወደ ከፍተኛ የጥራት ደረጃ (4K/8K Resolution) የሚያድስና የሚያጥር የ-AI ሶፍትዌር ነው።
3. Unscreen (unscreen.com)
🎯 ምን ይሠራል? አረንጓዴ ጨርቅ (Green Screen) ሳያስፈልግ፣ የትኛውንም የተቀረጸ ቪዲዮ ባክግራውንድ (Background) በሰከንዶች ውስጥ ሙሉ በሙሉ የሚያስወግድና የሚቀይር መሣሪያ ነው።
💎 መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ ሼርና ፎርዋርድ ማድረግ አይርሱ
🔺 @muleritsolutions2
ለሪሴቨራችሁ ማድረግ የሚኖርባችሁ ጥንቃቄ!!
===========================================
የሳተላይት ሪሴቨር (Receiver) ከዲሽ ሰሃን የሚመጣውን የሞገድ ምልክት ወደ ምስልና ድምፅ በመቀየር በቴሌቪዥናችን እንድንመለከት የሚያስችል መሣሪያ ነው።
አሰራሩን፣ ለብልሽት የሚዳርጉትን ምክንያቶች እና መደረግ ያለባቸውን ጥንቃቄዎች ከዚህ በታች በዝርዝር ቀርበዋል።
📡 የሳተላይት ሪሴቨር እንዴት ይሰራል?
ምልክት መቀበል (Signal Reception)፦ የዲሽ ሰሃኑ ከሳተላይት የሚመጣውን የራዲዮ ሞገድ ሰብስቦ ኤል ኤን ቢ (LNB) ወደተባለው መገናኛ ያስተላልፋል።
ምልክት ማስተላለፍ (Signal Transmission)፦ ኤል ኤን ቢው የሞገዱን መጠን አስተካክሎ በኮአክሲያል ኬብል (በዲሽ ገመድ) አማካኝነት ወደ ሪሴቨሩ ይልካል።
መበተንና መተርጎም (Decoding)፦ ሪሴቨሩ የደረሰውን ዲጂታል ምልክት ፈልቅቆ (Decode አድርጎ) ወደ ምስልና ድምፅ ይቀይረዋል።
ማሳየት (Output)፦ የተቀየረውን ምስልና ድምፅ በኤች ዲ ኤም አይ (HDMI) ወይም በኤቪ (AV) ገመድ አማካኝነት ወደ ቴሌቪዥኑ ይልካል።
⚠️ ሪሴቨሮች በምን ምክንያት ይበላሻሉ?
የመብራት መዋዠቅ፦ የኃይል መጠን በድንገት መጨመር ወይም መቀነስ (Power Surge) የውስጥ ዕቃዎችን (Power Supply) ያቃጥላል።
ከፍተኛ ሙቀት፦ ሪሴቨሩ አየር በማያገኝበት ጠባብ ቦታ ከተቀመጠ ከመጠን በላይ ግሎ ሊቃጠል ይችላል።
የውሃ ወይም የእርጥበት መግባት፦ በዲሽ ገመድ በኩል ውሃ ሾልኮ ከገባ ወይም ፈሳሽ ነገር ካረፈበት (Short Circuit) ይፈጥራል።
የሶፍትዌር መበላሸት፦ ትክክለኛ ያልሆነ የቻናል ሶፍትዌር (Flash) ሲጫን ወይም ሶፍትዌር እየጫነ መብራት ሲጠፋ ሪሴቨሩ ሙሉ በሙሉ ሊዘጋ ይችላል።
የእድሜ መግፋት፦ በረጅም ጊዜ አገልግሎት ምክንያት የውስጥ ዕቃዎች (በተለይ ካፓሲተሮች) ጥቅማቸውን ያጣሉ።
🛡️ መደረግ ያለበት ጥንቃቄ
ስታብላይዘር (Stabilizer) መጠቀም፦ የመብራት መዋዠቅ ሪሴቨሩን እንዳያቃጥለው የኤሌክትሪክ መቆጣጠሪያ ወይም የተጠበቀ ማራዘሚያ (Surge Protector) ይጠቀሙ።
አየር እንዲያገኝ ማድረግ፦ ሪሴቨሩን በሌሎች ዕቃዎች ላይ አይደረድሩ፤ በቂ አየር በሚያገኝበት ክፍት ቦታ ላይ ያስቀምጡት።
በመብረቅ ጊዜ መንቀል፦ ኃይለኛ ዝናብ እና መብረቅ በሚኖርበት ጊዜ የዲሽ ገመዱን እና የኤሌክትሪክ ሰካኪውን ይንቀሉ።
ከፈሳሽ ማራቅ፦ ሪሴቨሩ አጠገብ ውሃ፣ ሻይ ወይም ማናቸውንም ፈሳሽ ነገሮች አያስቀምጡ።
በትክክል ማጥፋት፦ ሪሴቨሩን ለረጅም ሰዓት የማይጠቀሙበት ከሆነ በሪሞት ብቻ ሳይሆን ከዋናው የኤሌክትሪክ ሶኬት ነቅሎ ማጥፋት ዕድሜውን ያራዝመዋል።
+1
❇️ ታሪካዊ የምስራች ለስፖርት ቤተሰቡ!
******
⚽️ የዓለማችን ቁጥር አንድ ሊግ የሆነው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ — አሁን በነፃ ወደ ቤትዎ ሊመጣ ነው!
🇪🇹 በኢትዮጵያ የግል ሚዲያ ታሪክ ግዙፍ የስፖርት ሁነቶችን ለህዝብ በማቅረብ ፈር ቀዳጅ የሆነው ሀገሬ ቴሌቪዥን፣ የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የነፃ አየር ስርጭት (FTA) ብቸኛ ባለመብት በመሆን አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል!
📺 ሀገሬ ቴቪ በቀጣዮቹ ሁለት ተከታታይ የውድድር ዘመናት ያለምንም ክፍያ የሚከተሉትን ድንቅ ዝግጅቶች በነፃ ወደ ቤትዎ ያደርሳል፦
👉 በሳምንት አንድ ጨዋታ፦ ዘወትር ቅዳሜ ከቀኑ 11፡00 ላይ የሚደረጉ የተመረጡ አጓጊ
የፕሪሚየር ሊግ ፍልሚያዎች።
👉 የሰኞ ምሽት ማጠቃለያ (Highlights)፦ የሳምንቱን ሙሉ ጨዋታዎች ግቦችና ምርጥ
እንቅስቃሴዎች።
👉የረቡዕ ምሽት ዘጋቢ ፊልም (Documentary)፦ በፕሪሚየር ሊጉ ዙሪያ የሚያጠነጥኑ
ሳቢና ማረኪ ታሪኮች።
👉የአርብ ምሽት ቅድመ-ጨዋታ (Preview)፦ ሳምንታዊ የጨዋታዎች ትንተና እና ዝግጅት።
📺 ሀገሬ ቴቪ ይሄን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስርጭቱን በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ተመልካቾች ያለምንም ክፍያ በቤታቸዉ በነፃ ያደርሳል።
🪧 ምንጭ:- Hagere TV Official Facebook Page
❇️ አዲስ ነገር ከሀገሬ ቴሌቪዥን!
🔷 ከዩቲዩብ ገቢ ለማግኘት የሚጠየቀው መስፈርት በሁለት እጥፍ አደገ
🔶 ዩቲዩብ አዲስ ይዘት የሚፈጥሩ አካላት ከማስታወቂያ እና ከዩቲዩብ ፕሪሚየም ገቢ ማግኘት የሚጀምሩበትን የዩቲዩብ ፓርትነር ፕሮግራም መስፈርት በሁለት እጥፍ ማሳደጉን አስታወቀ።
🔶 እ.ኤ.አ Feb 1, 2027 ጀምሮ ተግባራዊ በሚሆነው በዚህ አዲስ መመሪያ መሠረት፣ አዳዲስ ፈጣሪዎች በዩቲዩብ ፓርትነር ፕሮግራም ተቀብለው ገቢ ማግኘት ለመጀመር ፦
⚫ በመደበኛ/ ረጃጅም ቪዲዮዎች ላለፉት 12 ወራት 8,000 የታዩ ሰዓታት /Watch Hours/ ማሟላት አለባቸው። ይህም ቀደም ሲል ከነበረው 4,000 ሰዓታት በሁለት እጥፍ ያደገ ነው።
⚫ በአጭር ቪዲዮዎች /Shorts / በኩል ማመልከት የሚፈልጉ ደግሞ ባለፉት 90 ቀናት ውስጥ 20 ሚሊየን የታዩ ዕይታዎች ማሳካት ይኖርባቸዋል። ይህም ከዚህ ቀደም ከነበረው 10 ሚሊየን እይታ በሁለት እጥፍ ጨምሯል።
⚫ የ1,000 ተከታዮች መስፈርት አልተለወጠም።
🔶 ይህ ለውጥ ከፈረንጆች 2018 ወዲህ በዩቲዩብ የገቢ አስተዳደር ደንብ ላይ የተደረገ ትልቁ ማሻሻያ ነው ተብሏል።
🔶 በተጨማሪም ቀደም ሲል በፕሮግራሙ ውስጥ ያሉ የአጭር ይዘት ፈጣሪዎች የገቢ ክፍያቸውን ለማስቀጠል በየ90 ቀናት ውስጥ 10 ሚሊየን እይታዎችን ጠብቀው መቀጠል እንዳለባቸው ተገልጿል።
💎 መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ ሼርና ፎርዋርድ ማድረግ አይርሱ
🔺 @muleritsolutions2
🔴 መሰረታዊ የፕሪንተር ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸው
👉 ወረቀት ነክሶ ማስቀረት፦ ወረቀቱ ቀጥ ብሎ ባግባቡ መግባቱን ማርጋገጥ፣ ያስገባነው ወረቀት ትክክለና መጠን(size) መሆኑን ማረጋገጥ፣ ፕሪንተሩ ውስጥ የገባ ቆሻሻ አለመኖሩን ማረጋገጥ ይኖርብናል። የነከሰ ወረቀተ ካለ ደግሞ ቀስ ብለን ጎትተን ማውጣት እና መንም ወረቀቱን ሊይዘው የሚችል ነገር አለመኖሩን ማረጋገጥ ይኖርብናል።
👉 ሙሉ ለሙሉ ፕሪንት አያደርግም ወይም ይደበዝዛል፦ ቀለም ወይም ቶነር ካርትሪጅ አለማልቁን ማረጋገጥ ካለቀ መቀየር ይኖርብናል
👉 የፕሪንት ጥራት መጓደል(ወረቀቱን ማቆሸሽ)፦ የፕሪንት ማድረጊያውን ጫፍ(printing nozzle and head) ማጽዳት ይኖርብናል፣ የፕሪንት ሴቲንግ ማስተካከል ይኖርብናል
👉 ከኔትዎርክ ወይም ከኮምፒዩተር ጋር እይገናኝም፦ ኔትዎርክ መሰራቱን ማርጋግጥ፣ ከፕሪንተሩ ጋር የምናገናኝበት ኬብል በእግባቡ መስራቱን ማረጋገጥ ይኖርብናል፣ የፕሪንተሩ ድራይቨር መዘመኑን(up to date) መደረጉን ማረጋገጥ ይኖርብናል
👉 ፕሪንተሩ ይግላል፦ በፕሪንተሩ ዙሪያ በቂ አየር እንደሚዘዋወር ማረጋገጥ ይኖርብናል፣ ብዙ የስራ ጫና ብዝቶበት ሊሆን ስለሚችል ማሳረፍ ይኖርብናል
👉 ፕሪንተሩ የብልሽት ኮድ ያሳያል፦ የአጠቃቀም መመሪያውን ማንበብ እና በመመሪያው መሰረት ማስተካከል ይኖርብናል
👉 ፕሪንተሩ ሲሰራ ያልተገባ ድምጽ ያሰማል፦ የፕሪንትሩ የውስጥ የሰበረ ነገር አለመኖሩን ማርጋግጥ፣ የላላ ነገር አለመኖሩን ማረጋገጥ ይኖርብናል
⚠️ ማስታወሻ፦ እነዚህን መፍትሄዎች ተጠቅመው ካልተስተካከለልዎ የጥገና ባለሙያ ማናገር ይኖርብዎታል።
💎 መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ ሼርና ፎርዋርድ ማድረግ አይርሱ
🔺 @muleritsolutions2
+4
🔴 GTMEDIA V8 Finder 2 | 2026 Model / GT media V8 Finder 2026 Model
✅ 4000 mAh Battery ስላለው እስከ 7 ቀን ድረስ ቻርጅ ይዞ ይቆያል።
✅ TYPE C ቻርጀር የሚወስድ ስለሆነ ቻርጅ ሲያረግ በጣም ፈጣን ነው።
✅ 3.5 ኢንች HD ጥርት ያለ Screen አለው።
✅ Quality ሲያመጣ ፈጣን ነው።
✅ ለSoftware መጫኛ ሙዚቃና ምስል ማጫወቻ የሚሆን የ USB port ያለው ( Flash ይቀበላል።)
✅ በጣም Original እና አስተማማኝ ዕቃ።
✅ BISSKEY ይቀበላል (Biss key option አለው)
✅ HDMI INPUT , AV IN/OUT ስላለው ከTV ጋር በ HDMI ኬብልና በጃክ ማገናኘት እንችላለን።
✅ ከሪሲቨር ጋር አገናኝነትንም ምስል Finder ላይ ማየት እንችላለን!
✅ የራሱ ቦርሳ ስላለው ለአያያዝ እና ላጠቃቀም በጣም ምቹ ነው።
✅ ለረጅም ዓመት የቆዬ ምርጥና የታዋቂው Shenzhen GTMEDIA Technology ካምፖኒ ምርት የሆነ ብራንድ ኦሪጅናል እቃ።
⚠️ አዲስ ወደ ዲሽ ስራው አለም ውስጥ መግባት ለሚፈልጉ፣ ለጀማሪ እና አድቫንስድ የሳተላይት ዲሽ ቴክኒሻኖች በነፃ የማማከር አገልግሎት እንሰጣለን። ከእርስዎ የሚጠበቀው ከስር የሚገኙትን የቴሌግራም፣ እና Tiktok ቻናላችን ፎሎው (Join) ማድረግና ቤተሰብ መሆን ብቻ ነው።
🔷 https://www.tiktok.com/@africaelectronics
💵 💵 ዋጋ እና ሙሉ Product Description ለማግኘት ይሄንን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ 👉 https://t.me/africaelectronicsshop
➡️ ለመግዛት በቴሌግራም @africustomercare ያዋሩን ወይም በስልክ ቁጥር 📲 0938020816 ሃሎ ይበሉ
➡️ @africaelectronicsshop
+2
❇️ ተወዳጁ እና ለብዙ ጊዜ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው Findsat 8620 | የጊዜው በጣም ተፈላጊ Finder ወደሱቃችን አስገብተናል
✅ እስክሪኑ Black and White ስለሆነ ፀሃይ ላይ በደንብ ይታያል በተጨማሪም ባትሪ በደንብ ይቆጥባል።
✅ Switch ከባለ 4 እስከ ባለ 16 ድረስ ያነባል።
✅ S2 ያሳያል በዚህም አስቸጋሪ የሆኑ Satellite ለመስራትም ይመቻል።
✅ KUBAND እና Cband LNB ያስመርጣል።
✅ 1500 mAh battery አለው በዚህም እንደ ስራው ብዛት ከ3 ቀን እስከ 7 ቀን ያሰራል።
✅ በስራ አጋጣሚ ቢበላሽ ሁሉንም መለዋወጫ ከእኛ ዘንድ ማግኘት ይችላሉ።
✅ የLNB short መቆጣጠሪያ እና ማሳወቂያ የተገጠመለት ስለሆነ በቀላሉ በLNB short አይበላሽም።
✅ ለአያያዝ እና ለአጠቃቀም በጣም አመቺ ነው።
📍 ጎግል ማፕ (Google Maps) ላይ ሎኬሽን እንዴት ማጋራት (Share) እንችላለን? 📱
1️⃣ Google Maps ይክፈቱ 🗺️
2️⃣ ከላይ ቀኝ ያለውን የፕሮፋይል ፎቶዎን 👤 ይንኩ።
3️⃣ "Location sharing" (ሎኬሽን ማጋራት) 📍 ይምረጡ።
4️⃣ "Share location" ➕ ይንኩ።
5️⃣ ሎኬሽኑን ለምን ያህል ጊዜ እንዲጋራ ይምረጡ ⏰ (1 ሰዓት ወይም እርስዎ እስኪያቆሙት ድረስ)።
6️⃣ የሚላክለትን ሰው ወይም መተግበሪያ (WhatsApp, Telegram, Messenger...) 👥 ይምረጡ።
7️⃣ "Share" ✅ የሚለውን ይንኩ።
📌 አንድ ቦታ ብቻ ማጋራት ከፈለጉ፦
🔍 ቦታውን ይፈልጉ።
📍 ፒኑን (Pin) ይንኩ።
📤 Share የሚለውን ይጫኑ።
📲 በሚፈልጉት መተግበሪያ ይላኩ።
💡 ጠቃሚ ምክር:
📡 Location (GPS) እና 🌐 Wi-Fi ወይም Mobile Data መብራታቸውን ያረጋግጡ፤ ይህ ትክክለኛ ሎኬሽን ለመጋራት ይረዳል። 📍
❇️ የኮምፒውተራችን እድሜ ስንት እንደሆነ ለማወቅ👇
1. System information በመጠቀም
👉Search bar ላይ System information ብላችሁ ጻፉ
👉 ክሊክ ስትሉት ከሚመጡት ዝርዝር አማራጮች BIOS Version/date ላይ ኮምፒተሩ የተገጣጠመበትን ቀን ታገኛላችሁ
2. CMD በመጠቀም
👉አሁንም Search bar ላይ CMD ብላችሁ ጻፉ
👉 open CMD
👉CMD ሲከፍት systeminfo.exe ብላችሁ ጻፉና ENTER በሉት ከሚመጡት ዝርዝር አማራጮች BIOS Version ላይ ኮምፒተሩ የተገጣጠመበትን ቀን ታገኛላችሁ።
በቅርቡ የመልቲቾይስ/ዲኤስቲቪ ባለቤት የሆነው ካናልፕሉስ (CANAL+) ተወዳጁን ሻምፒዮንስ ሊግ ጨምሮ የአውሮፓ እግር ኳስ የክለቦች ውድድሮችን ከሰሃራ በታች አፍሪካ ሀገራት የማስተላለፍ ሙሉ መብት ማሸነፉን ገለፀ።
የፈረንሳዩካናል ፕሉስ ግሩፕ (አዲሱ የመልቲቾይሰ/ዲኤስቲቪ/ ባለቤት) እስከ 2031 ድረስ ለአራት የውድድር ዘመናት የሚቆይ የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር (UEFA) በስሩ የሚያከናውናቸውን የወንዶች ክለቦች ውድድሮችን ከሰሃራ አፍሪካ አገራት በብቸኝነት የማስተላለፍ መብት ማግኘቱ ነው ያስታወቀው።
በዚህም መሰረት ይህ የፈረንሳዩ ግዙፍ የቴሌቪዥን ኩባንያ የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ፣ ዩሮፓ ሊግ እና ኮንፈረንስ ሊግ ጨዋታዎችን በሙሉ ያስተላልፋል።
ይህ ስምምነት ከ2027 አጋማሽ እስከ 2031 የሚዘልቅ ሲሆን ኢትዮጵያን ጨምሮ በ40 የአፍሪካ ሀገራት የሚያሰራጭ ይሆናል።
ፈረንሳይኛ ተናጋሪ በሆኑ የአፍሪካ ሀገራት ሙሉ ጨዋታዎች በካናል ፕሉስ ስፖርት (CANAL+ Sport)በፈረንሳይኛ ቋንቋ እንደሚተላለፉ የተገለፀ ሲሆን እንግሊዝኛና ፖርቹጋልኛ ተናጋሪዎች ደግሞ እንደተለመደው በሱፐርስፖርት(SuperSport/DStv) ስርጭቶችን የሚከታተሉ ይሆናል፡፡
ደንበኞች ተወዳጆቹን የአውሮፓ ከዋክብት ክሊያን ምባፔ፣ አርሊንግ ሀላንድ፣ ላሚን ያማልን ጨምሮ የበርካታ አፍሪካውያን ድንቅ ብቃት በቀጥታና በላቀ ጥራት መከታተል ይችላሉ ሲል ካናልፕሉስ በጋዜጣዊ መግለጫው አሳውቋል።
ምንጭ :- DSTV Official Page
