en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

Muler IT Solutions Ethio GSM, Ethio Dish, ሞባይል ጥገና፣ ዲሽ ሶፍትዌር፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ ዌብሳይት ስራ

Muler IT Solutions Ethio GSM, Ethio Dish, ሞባይል ጥገና፣ ዲሽ ሶፍትዌር፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ ዌብሳይት ስራ

Open in Telegram

👉👉 አዳዲስና ትኩስ የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎችንና፣ ሞያ አዘል ፅሁፎችን፣ ጥያቄና መልሶችን፣የኮምፒውተርና የዲሽ ሪሲቨር ሶፍትዌሮችን፣ ጠቃሚ የሞባይል አፖችን ከተለያዩ የ Hacking እና Technical Trick ና ቲፖች የሚገኙበት ምርጥ ቻናል:: ለማንኛውም ጥያቄ @mulerjolly ን ወይም @africustomercare ን ይጠቀሙ!! ወይም በ 0938020816 ይደውሉ።

Show more
2 866
Subscribers
-124 hours
-87 days
-130 days
Posts Archive
❇️ የAI ቴክኖሎጂ እየጎለበተ በሄደ ቁጥር በማህበራዊ ሚዲያና በኢንተርኔት የምናያቸው ምስሎች፣ ቪዲዮዎችና ድምፆች በAI የተሰሩ መሆናቸውን መለየት ትልቅ ፈተና እየሆነ መጥቷል። 🔺 Google ይህ
❇️ የAI ቴክኖሎጂ እየጎለበተ በሄደ ቁጥር በማህበራዊ ሚዲያና በኢንተርኔት የምናያቸው ምስሎች፣ ቪዲዮዎችና ድምፆች በAI የተሰሩ መሆናቸውን መለየት ትልቅ ፈተና እየሆነ መጥቷል። 🔺 Google ይህንን ችግር ለመፍታት የሚያስችል SynthID የተሰኘ  Platform አስተዋውቋል። 🔺 በዚህ Platform አማካኝነት በGoogle AI የተሰሩትን ብቻ ሳይሆን በOpenAI, NVIDIA, Kakaoና በቅርቡ ደግሞ በApple AI  አማካኝነት የተፈጠሩ ይዘቶችን በቀላሉ ማረጋገጥ ይቻላል። 🔺 ለመጠቀም synthid.com ላይ ከገባችሁ በኋላ በGoogle አካውንታችሁ login ታደርጋላችሁ። ከዛ ማረጋገጥ የፈለጋችሁትን ፎቶ፣ ቪዲዮ ወይም ድምፅ በማስገባት check ማድረግ ትችላላችሁ። 💎 መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ ሼርና ፎርዋርድ ማድረግ አይርሱ 🔺  @muleritsolutions2

🔴 የሃኪንግ አይነቶች ስንት ናቸው? በቴክኖሎጂው ዓለም ውስጥ ሃኪንግ በዋናነት በ3 ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል። ልዩነታቸው የሚመጣው ከሚያደርጉት ድርጊት ዓላማ እና ከህጋዊነታቸው ነው። 1️⃣ ኋይት
🔴 የሃኪንግ አይነቶች ስንት ናቸው? በቴክኖሎጂው ዓለም ውስጥ ሃኪንግ በዋናነት በ3 ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል። ልዩነታቸው የሚመጣው ከሚያደርጉት ድርጊት ዓላማ እና ከህጋዊነታቸው ነው። 1️⃣ ኋይት ሐት ሐከር (White Hat Hackers)ህጋዊ ሃከሮች በመባል ይታወቃሉ።ድርጅቶችን ለመርዳትና ሲስተም ላይ ያሉ ክፍተቶችን ቀድሞ ለመጠገን ይሰራሉ። 2️⃣ ብላክ ሐት ሐከር (Black Hat Hackers)ወንጀለኛ ሃከሮች ናቸው።የግል ጥቅምን ለማግኘት፣ መረጃ ለመስረቅ ወይም ሲስተምን ለማበላሸት በህገ-ወጥ መንገድ ጥቃት ያደርሳሉ። 3️⃣ ግሬይ ሐት ሐከር (Grey Hat Hackers)በሁለቱ መካከል ያሉ ናቸው።ያለፈቃድ ሲስተም ውስጥ ይገባሉ፤ ነገር ግን ዓላማቸው ለመስረቅ ሳይሆን ክፍተቱን ለባለቤቱ ለማሳወቅ ወይም ለመዝናናት ሊሆን ይችላል። 🛡 እራስዎን ከሳይበር ጥቃት ይጠብቁ!

❇️ ከዓለም ታዋቂ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ነፃ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence — AI) ስልጠናዎችን ይማሩ። 🚀 1. አንትሮፒክ (Anthropic) 🔗 https://a
❇️ ከዓለም ታዋቂ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ነፃ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence — AI) ስልጠናዎችን ይማሩ። 🚀 1. አንትሮፒክ (Anthropic) 🔗 https://anthropic.skilljar.com 2. ጉግል (Google) 🔗 https://grow.google/ai 3. ሜታ (Meta) 🔗 https://ai.meta.com/resources 4. ኤንቪዲያ (NVIDIA) 🔗 https://developer.nvidia.com/cuda 5. ማይክሮሶፍት (Microsoft) 🔗 https://learn.microsoft.com/en-us/training 💡 እያንዳንዱ ኮርስ ነፃ መሆኑን፣ ቅድመ እውቀት የሚፈልግ መሆኑን እና የሰርተፊኬት አሰጣጡን በድረ-ገጹ ላይ ያረጋግጡ። 💎 መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ ሼርና ፎርዋርድ ማድረግ አይርሱ 🔺  @muleritsolutions2

የስልካቹን ብራይትነስ እስከመጨረሻ ቀንሳቹም ያዉ ከሆነ ! ✔️የስልካቹን ብራይትነስ እስከመጨረሻዉ ቀንሳቹም ያዉ ከሆነና ላይቱ ያዉ ሁኖ ካስቸገራቹ ይህን አስተካክሉ። ወደ ስልካቹ Setting ግቡ➡️
የስልካቹን ብራይትነስ እስከመጨረሻ ቀንሳቹም ያዉ ከሆነ ! ✔️የስልካቹን ብራይትነስ እስከመጨረሻዉ ቀንሳቹም ያዉ ከሆነና ላይቱ ያዉ ሁኖ ካስቸገራቹ ይህን አስተካክሉ። ወደ ስልካቹ Setting ግቡ➡️ የሰርች ምልክቷን ንኩና 'Extra Dim' ብላቹ ሰርች አርጉ➡️ ሲመጣ ነክታቹ ግቡና መጨረሻ ላይ Extra dim ሚለዉን ነክታቹ በመግባት ON አርጉት ➡️ ከዛ ቀጥሎ Extra dim shortcut ሚለዉን ነክታቹ ግቡና እሱንም  On አድርጋቹ " Tab button in quick Setting panel " ሚለዉ ላይ አድርጉና Ok ብላቹ ዉጡ። ✔️ከዛ የስልካቹን Quick Pannel ወደታች ስታደርጉ Extra dim የሚል አዲስ Menu ተጨምሯል እሱን ጫን አድርጋቹ ግቡና Intensity የሚለውን በእጃቹ ወደ ፊለፊት ጨመር ጨመር ስታደርጉ Brightness ይቀንሳል። እንደዛ Intensity ውን ጨመር ቀነስ እያደረጋቹ Adjust በማድረግ ማስተካከል ትችላላቹ። 💎 መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ ሼርና ፎርዋርድ ማድረግ አይርሱ 🔺  @muleritsolutions2

✅የኤሌክትሪክ_ክፍያ_ከመጠን_በላይ_እየጨመረብዎ_ተቸግረዋል❓ ወጪዎን በ50% እና ከዚያ በላይ ለመቀነስ የሚያስችሉ 12 ምርጥ እና የተሞከሩ የቤት ውስጥ ብልሃቶች❗️ ==== 👉ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብዙ ተጠቃሚዎች የኤሌክትሪክ ክፍያ ጨመረብን እያሉ ሲያማርሩ ይሰማል ለዚህ ደግሞ 2 ዋና ዋና ምክንያቶች አሉ❗️ 1⃣ኛ. በየ 3 ወሩ የሚጨምረው የኤትዮጵያ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ክፍያ ስርዓት ሲሆን 2⃣ኛው ደግሞ የኤሌክትሪክ አጠቃቀማችን ነው❗️ 👉ስለዚህ በቤትዎ ውስጥ እነዚህን ቀላል የአጠቃቀም ለውጦች በማድረግ ብቻ የቀጣዩን ወር የኤሌክትሪክ ክፍያ ቢልዎ በሚገርም ሁኔታ እስከ 50% ቀንሶ ያገኙታል። 👉እነሆ ለቤትዎ እና ለኪስዎ እፎይታ የሚሰጡ 12 ወሳኝ ዘዴዎች፦ 1⃣ የእንጀራ ምጣድ እና ስቶቭ አጠቃቀም፦ 👉 የጋለ ምጣድ ላይ በአንድ ጊዜ በቂ እንጀራ ይጋግሩ፤ በወር 8 ጊዜ የሚጋግሩ ከሆነ ወደ 6 ጊዜ ዝቅ ለማድረግ ይሞክሩ። 👉 ምጣዱን አየር እና ንፋስ በሚገባበት ቦታ አያስቀምጡ (ንፋስ ምጣዱን ካቀዘቀዘው ለመጋል ተጨማሪ ሀይል ይስባል)። 👉 ጥራጥሬዎችን(ባቄላ፣ በቆሎ እና ሌሎችም) ከማብሰልዎ በፊት በውሃ መዘፍዘፍ ጊዜንና ኤሌክትሪክ ከረንትን በከፍተኛ ሁኔታ ይቆጥባል። 2⃣ የልብስ አጠባ፣ ማድረቅ እና መተኮስ፦ 👉 የልብስ ማጠቢያ ማሽን ከፍተኛ ሀይል የሚጠቀመው ውሃ ሲያሞቅ ስለሆነ ልብሶችን በቀዝቃዛ ወይም ለብ ባለ ውሃ ያጠቡ። 👉 ልብስ ማድረቂያ ማሽን (Dryer) ከመጠቀም ይልቅ በተፈጥሮ የፀሐይ ብርሃን ማድረቅን ይምረጡ። 👉 የሳምንቱን ልብሶች በአንድ ላይ በማጠራቀም መተኮስ የካውያ ኮረንቲ ብክነትን ያስቀራል። 3⃣ የፍሪጅ እና ማቀዝቀዣዎች ጥንቃቄ፦ 👉 ፍሪጅን በሆነ ባልሆነው ደጋግመው አይክፈቱ፤ ይህ ቀዝቃዛ አየር አስወጥቶ ሞተሩ ድጋሚ ሀይል አውጥቶ እንዲሰራ ያደርጋል። 👉 ትኩስ ምግቦችን በቀጥታ ወደ ፍሪጅ አያስገቡ፤ ውጭ ሙሉ ለሙሉ አብርደው ያስገቡ። 👉 የበሩ ላስቲክ (Gasket) አየር የሚያስገባ ከሆነ ተጨማሪ ሀይል ስለሚባክን በአፋጣኝ ያስተካክሉ/ይቀይሩ። 4⃣ የድብቅ ኤሌክትሪክ ከረንት ሌቦችን (Standby Mode) ማስወገድ፦ 👉 ኮምፒውተር፣ ቴሌቪዥን እና ዲኮደርና ሌሎችንም ተጠቅመው ሲጨርሱ በሪሞት ብቻ አጥፍተው አይተውዋቸው። 👉 ሙሉ ለሙሉ አጥፍተው ፕለጉን ከሶኬት ይንቀሉ፤ ምክንያቱም ሶኬት ላይ እስካሉ ድረስ ኤሌክትሪክ ከረንት መብላታቸውን አያቆሙም። 5⃣ የውሃ ማሞቂያ (ቦይለር) ሚስጥር፦ 👉 ቦይለርን ለ24 ሰዓት በርቶ መተው ከፍተኛ ኪሳራ ስለሆነ መጠቀም ሲፈልጉ ብቻ (ከ30 ደቂቃ በፊት) ያብሩ። 👉 እንደተጠቀሙበት ወዲያውኑ ፕለጉን መንቀል ወይም ማጥፋትን አይርሱ። 👉 በኤሌክትሪክ ውሃ ሲያሞቁም የሚፈልጉትን ያህል መጠን ብቻ ያሙቁ። 6⃣ የተፈጥሮ ብርሃንን መጠቀም እና አምፖል መቀነስ፦ 👉 ቀን ላይ የመስኮት መጋረጃዎችን በመክፈት የተፈጥሮ ብርሃን ይጠቀሙ እንጂ መብራት አያብሩ። 👉 ማታ ያልተጠቀምንባቸውን ክፍሎች መብራት ማጥፋት (በከፊል ማብራት) ልመድ ያድርጉ። 👉 አምፖሎችን ሙሉ በሙሉ ወደ ሀይል ቆጣቢ LED ይቀይሩ። 7⃣ ምግብ ለማሞቅ ማይክሮዌቭ (Microwave) መምረጥ፦ 👉 የተጋገረ እንጀራ ወይም ቀዝቃዛ ምግብ ለማሞቅ ምጣድ ወይም ትልቅ ኦቨን ደጋግመው አይለኩሱ። 👉 ማይክሮዌቭ መጠቀም ጊዜንም ከፍተኛ ሀይልንም ይቆጥባል። 8⃣ የቤት ሙቀት እና ቅዝቃዜ መቆጣጠር፦ 👉 ለሙቀት እና ለቅዝቃዜ ጊዜ ተስማሚ የሆኑ በሮችን እና መስኮቶችን (Isolating windows & doors) ይጠቀሙ። 👉 ይህ በክረምት የቤቱ ሙቀት ወደ ውጭ፣ በበጋ ደግሞ ቅዝቃዜው እንዳይወጣ በማድረግ ተጨማሪ ሀይልን ያስቀራል። 9⃣ የእቃዎች ጽዳት እና ወቅታዊ ጥገና፦ 👉 አቧራ የጠጣ እና የቆሸሸ የኤሌክትሪክ ሲስተም የእቃውን አቅም (Efficiency) ይቀንሰዋል። 👉 እቃው የተፈለገውን ስራ ለመስራት ሲል ተጨማሪ ኮረንቲ ስለሚስብ በአግባቡ ያፅዱትና ወቅታዊ ጥገና ያድርጉለት። 🔟 በስማርት ቆጣሪ (CIU) ታሪፍን መቆጣጠር፦ 👉 የኤሌክትሪክ ታሪፍ ፍጆታዎ በጨመረ ቁጥር የአንዱ ኪሎ-ዋት ክፍያ እየጨመረ ይሄዳል (Block tariff)። 👉 በቤትዎ STS ስማርት ቆጣሪ ተጠቃሚ ከሆኑ በስማርት ቆጣሪ ኪቦርድ እና ስክሪን ላይ ፍጆታዎን በየጊዜው ይከታተሉ። 👉 ወደ ከፍተኛ ታሪፍ ከመግባትዎ በፊት አላስፈላጊ እቃዎችን በማጥፋት ወጪዎን ይቆጣጠሩ። 1⃣1⃣ ምግብ ሲያበስሉ የድስት ክዳን መጠቀም፦ 👉 ምግብ በሚሰሩበት ጊዜ ድስቱን ከድነው ማብሰል ሙቀቱ እንዳይወጣ ስለሚከለክል ምግቡ ቶሎ ይበስላል። 👉 ይህ የስቶቭን የማብሰያ ሰዓት በማሳጠር ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሀይል ይቆጥብልዎታል። 👉እንዲሁም የኤሌክትሪክ ምድጃ ሲጠቀሙ በጣም ትንሽ ድስት ጥዶ ሃይል ከማባከን በኤሌክትሪክ ምድጃው ልክ የሆነ ድስት መጠቀም ፍጆታን ይቀንሳል። 1⃣2⃣ የግፊት ማብሰያ (Pressure Cooker) መጠቀም፦ 👉 ስጋ ወይም ጠንካራ ጥራጥሬዎችን በተለመደው ክፍት ድስት ከማብሰል ይልቅ ፕሬዠር ኩከር መጠቀም የማብሰያ ጊዜውን እስከ 70% ያፈጥረዋል። 👉 ማብሰያው ቶሎ ደረሰ ማለት ደግሞ፣ ከፍተኛ ኮረንቲ የሚስበው ስቶቭዎ የሚሰራበትን ጊዜ በማሳጠር የኤሌክትሪክ ወጪዎን በከፍተኛ ሁኔታ ይቀንሰዋል ማለት ነው። 👉ይሞክሩትና ለውጡን ይመልከቱ❗️ ከእነዚህ 12 ዘዴዎች ውስጥ እርስዎ ዛሬውኑ ቤትዎ ውስጥ መተግበር የሚጀምሩት የቱ ነው❓ ሃሳባችሁን በኮመንት አጋሩን❗️ 🙏 ምንጭ :- ©አሜን ኤሌክትሪካል ቴክኖሎጂ

❇️ Smart TV Box-ክዎ በጣም slow ሆኖብዎታል? 😫 Don’t replace it yet! እነዚህን 5 ነገሮች ይሞክሩ!” 1️⃣ Uninstall unnecessary apps “መጀመሪያ የማይጠቀሙ
❇️ Smart TV Box-ክዎ በጣም slow ሆኖብዎታል? 😫 Don’t replace it yet! እነዚህን 5 ነገሮች ይሞክሩ!” 1️⃣ Uninstall unnecessary apps “መጀመሪያ የማይጠቀሙባቸውን apps uninstall ያድርጉ። Too many apps የTV Box-ዎን storage እና performance ሊጫኑት ይችላሉ።” 2️⃣ Free up storage “Storage በጣም full ከሆነ TV Box-ዎ slow ሊሆን ይችላል። የማይፈልጉትን videos እና files delete ያድርጉ።” 3️⃣ Clear app cache “ለምሳሌ YouTube slow ከሆነ፣ Settings → Apps → YouTube → Clear Cache ይሞክሩ። ⚠️ Clear Data ግን ሲያስፈልግ ብቻ ይጠቀሙ፤ login information እና settings ሊጠፉ ይችላሉ።” 4️⃣ Restart your TV Box “TV Box-ዎን restart ማድረግ አይርሱ። Sometimes a simple restart can fix temporary freezing and slow performance.” 5️⃣ Check your Internet “TV Box-ዎ slow የሚመስለው ከInternet ችግርም ሊሆን ይችላል። YouTube buffering ካለ፣ Wi-Fi ወይም internet connection ይመርምሩ።” 🔥 Ending: 🔺 እነዚህን ሁሉ ካደረጉ በኋላም TV Box-ዎ slow ከሆነ፣ hardware, overheating ወይም software problem ሊኖረው ይችላል። 💎 መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ ሼርና ፎርዋርድ ማድረግ አይርሱ 🔺  @muleritsolutions2

❇️ ጉግል አዲስ “ጄሚናይ 4 አርጎን” የተሰኘ የኤአይ ሞዴል ይፋ አደረገ 🔷 ጉግል እንደ ኮዲንግ፣ ምርምር እና ጽሁፍ ያሉ ውስብስብ ስራዎችን ማከናወን የሚችል “ጄሚናይ 4 አርጎን” (Gemini 4
❇️ ጉግል አዲስ “ጄሚናይ 4 አርጎን” የተሰኘ የኤአይ ሞዴል ይፋ አደረገ 🔷 ጉግል እንደ ኮዲንግ፣ ምርምር እና ጽሁፍ ያሉ ውስብስብ ስራዎችን ማከናወን የሚችል “ጄሚናይ 4 አርጎን” (Gemini 4 Argon) የተባለ አዲስ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴል አስተዋውቋል። ይህ አዲስ ሞዴል በተለይም ለሳይበር ደህንነት ስራዎች የጎላ አቅም አለው። 🔷 ሞዴሉ ለተከላካይ የሳይበር ደህንነት (Defensive Cybersecurity) ስራዎች የሰለጠነ ሲሆን፤ በሶፍትዌሮች ላይ የሚታዩ ወሳኝ የደህንነት ክፍተቶችን በራሱ መለየት፣ ማረጋገጥ እና ማስተካከል እንደሚያስችል ተገልጿል። 🔷 አርጎን በተጨማሪም ለኮዲንግ እና ለሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ስራዎች የላቀ ብቃት አካብቷል፡፡ ረጅም ቪዲዮዎችን እና ቻርቶችን ጨምሮ ምስሎችን በጥልቀት የመተንተን ከፍተኛ አቅም አለው። 💎 መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ ሼርና ፎርዋርድ ማድረግ አይርሱ 🔺  @muleritsolutions2

❇️ Types of phone front cameras 🔷 አሁን ላይ በርካቶቻችን ስልክ ስንገዛ ትኩረት ከምንሰጣቸው ነገሮችን አንዱ camera መሆን አይዘነጋም። ታዲያ የስልካችንን የፊተኛው ካሜራ አቀ
❇️ Types of phone front cameras 🔷 አሁን ላይ በርካቶቻችን ስልክ ስንገዛ ትኩረት ከምንሰጣቸው ነገሮችን አንዱ camera መሆን አይዘነጋም። ታዲያ የስልካችንን የፊተኛው ካሜራ አቀማመጥ ላይ በመመኮዝ በአራት ከፍለን ልናስቃኛችሁ ወደደን 1. Waterdrop Notch የፊተኛው ካሜራ ከስክሪኑ ፍሬም ጋር የተገናኘ ነው። በብዛት እንደዚህ አይነት የፊት ካሜራ ያላቸው ስልኮች ትንሽ ቆየት ያሉ ናቸው። የውሃ ጠብታ ዓይነት መልክም አለው። ለምሳሌ Samsung A05... 2. Punch-Hole የስልኩ ጠርዝና የካሜራው ቦታ ክፍተት ያለበት ካሜራ አይነት ነው። በብዛት የነዚህ ስልኮች የካሜራ መጠን  ከ Waterdrop notch አነስ ያለ ነው። በተመሳሳይ በርካቶቹ ጥራታቸውም የተሻለ ነው። ለምሳሌ samsung galaxy S10... 3. Pop-Up Camera ይህኛው የካሜራ አይነት ትንሽ ለየት ይላል። ይህም የሆነበት ምክንያት ምንም ዓይነት selfie camera አናይም። ይሁን እንጂ ፎቶ መነሳት በምንፈልግበት ጊዜ selfie ካሜራው ከስልኩ body በመውጣት ፎቶ እና ቪዲዮ የሚቀርጽ የካሜራ አይነት ነው። ለምሳሌ one plus 7 pro... 4. Under-Display Camera እነዚህ ካሜራዎች የሚገኙት ከscreen ጀርባ ሲሆን እኛ ምንም አይነት selfie camera አናይም። ከscreen ጀርባ ሆኖ ፎቶ ማንሳትም ሆነ ቪዲዮ መቅረፅ ይችላል። ለምሳሌ ZTE Axon 205g 💎 መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ ሼርና ፎርዋርድ ማድረግ አይርሱ 🔺  @muleritsolutions2

🛒ለ PLAYSTORE ተጠቃሚዎች ፦ 🟢Playstore ስትጠቀሙ እናንተ ሳታውቁት በራሱ የአፕልኬሽኖችን UPDATE OR DOWNLOAD እያረገ ካርዳችሁን እየጨረሰ ከተቸገራችሁ ይህን ወሳኝ ነገር አስ
🛒ለ PLAYSTORE ተጠቃሚዎች ፦ 🟢Playstore ስትጠቀሙ እናንተ ሳታውቁት በራሱ የአፕልኬሽኖችን UPDATE OR DOWNLOAD እያረገ ካርዳችሁን እየጨረሰ ከተቸገራችሁ ይህን ወሳኝ ነገር አስተካክሉ። በመጀመሪያ ወደ Playstore ትገቡና➡️ የ Profile ምልክቷን ነክታችሁ➡️ Settings ሚለው ውስጥ ትገቡና  ➡️ Network Preference የሚል እሱ ውስጥ➡️ Auto Update የሚለውን Off በማድረግ ካለናንተ ፈቃድ አፕ Update or Download እንዳያረግና ካርዳችሁን እንዳይጨርስባችሁ ማድረግ ትችላላችሁ። 💎 መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ ሼርና ፎርዋርድ ማድረግ አይርሱ 🔺  @muleritsolutions2

📱ስልካቹ ላይ ሰዎች Hack አንዳያደርጓችሁ ይህን አስተካክሉ:- ➡️ ወደ Setting ግቡና Security & Privacy ሚለዉን ንኩ ➡️ ከዛ ወረድ በሉና More security setting ሚለ
📱ስልካቹ ላይ ሰዎች Hack አንዳያደርጓችሁ ይህን አስተካክሉ:- ➡️ ወደ Setting ግቡና Security & Privacy ሚለዉን ንኩ ➡️ ከዛ ወረድ በሉና More security setting ሚለዉን ንኩ ➡️ በመቀጠል ከታች "Device admin app" የሚለዉን ነክታቹ ሰትገቡ እዛ ውስጥ የምትፃፃፉትን የምታወሩትን የሚከታተሉ አፖች አሉ እየነካቹ በመግባት "Deactivate " ሚለዉን በመንካት ደንነታቹን መጠበቅ ትችላላቹ:: 💎 መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ ሼርና ፎርዋርድ ማድረግ አይርሱ 🔺  @muleritsolutions2

📱ስልካቹ ላይ ሰዉ Hacked አንዳያደርጋችሁ ይህን አስተካክሉ:- ➡️ወደ Setting ግቡና Security & Privacy ሚለዉን ንኩ ➡️ከዛ ወረድ በሉና More security setting ሚለዉ
📱ስልካቹ ላይ ሰዉ Hacked አንዳያደርጋችሁ ይህን አስተካክሉ:- ➡️ወደ Setting ግቡና Security & Privacy ሚለዉን ንኩ ➡️ከዛ ወረድ በሉና More security setting ሚለዉን ንኩ ➡️በመቀጠል ከታች "Device admin app" ሚለዉን ነክታቹ ሰትገቡ እዛ ዉስጥ የምትፃፃፉትን የምታወሩትን የሚከታተሉ አፖች አሉ እየነካቹ በመግባት "Deactivate " ሚለዉን በመንካት ደንነታቹን መጠበቅ ትችላላቹ::

❌ #ፍሪጅ_ቶሎ_ቶሎ_እንዲበላሽ_የሚያደርጉ10_ዋና_ዋና #ምክንያቶች_እና_መወሰድ_ያለባቸው_ወሳኝ_ጥንቃቄዎች❗️ ==== 👉ማቀዝቀዣ (Refrigerator) በቤታችን ውስጥ ያለ ውድ እና የማያቋርጥ አገልግሎት የሚሰጥ እቃ ነው። ነገር ግን ከጥቅም ውጭ የሚሆኑባቸው አብዛኛዎቹ ምክንያቶች ከቴክኒክ ችግር ይልቅ ሳናውቃቸው ከምንፈጽሟቸው አሰራሮች እና #የአጠቃቀም_ስህተቶች የሚመነጩ ናቸው። 👉ከዚህ በፊት የፍሪጅ ዋና ዋና ብልሽቶችና መፍትሄዎችን ይዘን መጥተን ነበር ዛሬ ደግሞ ፍሪጅ ቶሎ ቶሎ የሚበላሽባቸው 10ሩ ዋና ዋና ምክንያቶች እንደሚከተለው ይዘን  ቀርበናል አንብበው ሲጨርሱ ከወደዱት ብቻ ለሌሎች #ሼር ያድርጉት❗️ 1⃣ የኮንደንሰር ቧንቧዎች(ቱዩቦች) በአቧራ መሸፈን (Condenser Coils Dust Buildup) ❌ ምክንያቱ፦ 👉የኮንደንሰር ቧንቧዎች (አብዛኛውን ጊዜ ከፍሪጁ ጀርባ ወይም ከታች በኩል የሚገኙት) ሙቀት የማስወገድ ሃላፊነት አላቸው። በአቧራ ሲሸፈኑ ሙቀት ማስወጣት ስለማይችሉ ኮምፕረሰሩ ያለ እረፍት እንዲሰራ እና እንዲቃጠል ያደርጋሉ። ✅ ጥንቃቄው፦ 👉ቢያንስ በዓመት ከሁለት እስከ ሶስት ጊዜ የፍሪጁን ጀርባ ክፍት በማድረግ በብሩሽ ወይም በቫኪዩም ክሊነር አቧራውን ማጽዳት። 2⃣ የቮልቴጅ መዋዠቅ እና የኤሌክትሪክ መቆራረጥ (Voltage Fluctuations) ❌ምክንያቱ፦ 👉የኮምፕረሰሩ ሞተር ለመነሳት ከፍተኛ ኤሌክትሪክ ይፈልጋል። የኤሌክትሪክ ከረንት መዋዠቅ ሲኖር ሞተሩ ለመነሳት ይቸገራል፤ ይህም ሪሌይ (Relay) እና የሞተር ዋይንዲንግን ያቃጥላል። ✅ ጥንቃቄው፦ 👉ፍሪጁን በቀጥታ ከሶኬት ጋር ከመሰካት ይልቅ ትክክለኛ አቅም ያለው የፍሪጅ ስታብላይዘር (Voltage Guard/Protector) መጠቀም። 3⃣ በሩን ለረጅም ሰዓት ክፍት ማድረግ ወይም የበር ላስቲክ መላላት (Gasket Failure) ❌ ምክንያቱ፦ 👉የበሩ ላስቲክ (Gasket) ሲበላሽ ውጭ ያለ ሞቃታማ አየር ወደ ውስጥ ይገባል። ፍሪጁም ያንን ቅዝቃዜ ለመጠበቅ ሲል ያለ እረፍት ይሰራል፤ ይህም የኮምፕረሰሩን እድሜ ይቀንሰዋል ። ✅ጥንቃቄው፦ 👉የበሩን ላስቲክ ንጽህና ሁልጊዜ መጠበቅ፤ ሲበላሽ ሳይቆዩ አዲስ መቀየር፤ እንዲሁም ምግብ ካወጡ በኋላ በሩን አጥብቆ መዝጋት። 4⃣ ትኩስ ምግብ በቀጥታ ማስገባት (Putting Hot Food Inside) ❌ምክንያቱ፦ 👉ከእሳት የወጣ ትኩስ ምግብ ወይም ሻይ በቀጥታ ፍሪጅ ውስጥ ሲገባ የፍሪጁን የውስጥ ሙቀት በድንገት ይጨምረዋል። ይህንን ለማቀዝቀዝ ኮምፕረሰሩ ከመጠን በላይ መስራት ይጀምራል። ✅ጥንቃቄው፦ 👉ምግቦች ሙሉ በሙሉ የክፍል ሙቀት (Room Temperature) እስኪያገኙ ድረስ ከፍሪጅ ውጭ አቀዝቅዞ ከዚያ ወደ ውስጥ ማስገባት። 5⃣ ፍሪጁን ከግድግዳ ጋር አቅርቦ ማስቀመጥ (Poor Ventilation) ❌ ምክንያቱ፦ 👉ፍሪጅ በሚሰራበት ጊዜ ከጎኖቹ እና ከጀርባው ሙቀት ይለቃል። በቂ የአየር ዝውውር ቦታ ከሌለ ሙቀቱ ተከማችቶ ሞተሩን ይጎዳዋል። ✅ ጥንቃቄው፦ 👉ፍሪጁ ከግድግዳ እና ከሌሎች እቃዎች ቢያንስ ከ 10 እስከ 15 ሴንቲሜትር ርቀት እንዲኖረው አድርጎ ማስቀመጥ። 6⃣ ፍሪጁን ከመጠን በላይ ማጨናነቅ (Overloading the Fridge) ❌ምክንያቱ፦ 👉ምግቦችን እና እቃዎችን በጣም አጭቆ ማስገባት የውስጥ የአየር ዝውውርን (Air Circulation) ይዘጋል። አየሩ በነፃነት ካልተዘዋወረ፣ ሞተሩ ሁሉንም ለማቀዝቀዝ ሲል ጫና ይበዛበታል። ✅ ጥንቃቄው፦ 👉በአየር ዝውውር መንገዶች (Vents) አካባቢ ክፍተት መተው እና በፍሪጁ ውስጥ እቃዎች እንዳይተፋፈኑ ማድረግ። 7⃣ የሙቀት መቆጣጠሪያውን (Thermostat) አላግባብ መጠቀም (Incorrect Temperature Settings) ❌ ምክንያቱ፦ 👉ቴርሞስታቱን ሁልጊዜ በከፍተኛ ቅዝቃዜ (Maximum/Coldest) ላይ ማድረግ ኮምፕሬሰሩ ያለ እረፍት እንዲሰራ እና ቶሎ እንዲያረጅ ያደርገዋል። ✅ ጥንቃቄው፦ 👉ቴርሞስታቱን በመካከለኛ (Medium) ወይም በአምራቹ በተመከረው ደረጃ (ብዙውን ጊዜ 3 ወይም 4 ቁጥር) ላይ ማድረግ። 8⃣ ፍሪጅን አጋድሞ ማንቀሳቀስ እና ወዲያውኑ ማብራት (Incorrect Moving & Immediate Plugin) ❌ ምክንያቱ፦ 👉ፍሪጅን አጋድሞ ካጓጓዙ በኋላ ወዲያውኑ ሶኬት ላይ መሰካት የኮምፕሬሰሩ ዘይት (Compressor Oil) ወደ ቧንቧዎች (Cooling lines) ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ሲስተሙን ይዘጋዋል/ያበላሻል። ✅ ጥንቃቄው፦ 👉ፍሪጅ ከተንቀሳቀሰ በኋላ ከመሰካቱ በፊት ዘይቱ ወደ ቦታው እስኪመለስ ቢያንስ ከ4 እስከ 24 ሰዓታት (እንደተጓጓዘበት ሁኔታ) አቆይቶ ማብራት። 9⃣ ከሙቀት ምንጭ አጠገብ ማስቀመጥ (Near Heat Sources) ❌ ምክንያቱ፦ 👉ፍሪጅን ከምድጃ (Stove/Oven) አጠገብ ወይም ቀጥታ የፀሐይ ብርሃን በሚያገኝበት መስኮት ስር ማስቀመጥ ውጫዊ ሙቀትን ስለሚጨምር ሞተሩን ያደክማል። ✅ጥንቃቄው፦ 👉ፍሪጅን ሁልጊዜም ቀዝቃዛ እና ፀሐይ ወይም ሌላ ሙቀት በቀጥታ ከማይመታበት የቤቱ ክፍል ማስቀመጥ። 🔟 የበረዶ መከማቸት እና በስለት ለማንሳት መሞከር (Ice Buildup & Puncturing) ❌ ምክንያቱ፦ 👉በረዶ በነፃነት አየር እንዳይዘዋወር ስለሚከለክል ፍሪጁ የማቀዝቀዝ አቅሙ ይቀንሳል። ከዚህም የባሰው ደግሞ፣ የተከማቸውን በረዶ በስለት (በቢላዋ) ለመስበር ሲሞከር የጋዝ ቧንቧው ተቀዶ ጋዝ ይፈሳል። ✅ ጥንቃቄው፦ 👉ፍሪጁ 'ኖ-ፍሮስት' (No-Frost) ካልሆነ፣ በረዶ ሲደራረብ ማጥፊያውን በመጫን (Defrost) ወይም ሶኬቱን በመንቀል ወይም በሙቅ ውሃ  ማቅለጥ እንጂ ፈፅሞ በስለት በረዶውን ለመስበር አለመሞከር። 💎 መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ ሼርና ፎርዋርድ ማድረግ አይርሱ 🔺  @muleritsolutions2

❇️ ያለ ምንም ኢንተርኔት ኮኔክሽን (100% Offline) በስልካችሁና በኮምፒውተራችሁ ላይ በነፃ የሚሠሩ አዳዲስ የ-Local AI Models አብዮት! 🔷 እስከዛሬ የነበሩት እንደ ChatGPT፣ Claude እና Gemini ያሉ የ-AI መሣሪያዎችን ለመጠቀም የግድ ፈጣን ኢንተርኔትና የዳታ ፓኬጅ ያስፈልግ ነበር። አሁን ግን የቴክኖሎጂው ዓለም ትልቅ ማሻሻያ በማድረግ፤ ምንም ዓይነት ኢንተርኔት ሳይኖር በራሳችሁ ስልክ ወይም ኮምፒውተር ላይ ሙሉ በሙሉ በነፃ የሚሠሩ On-Device Local AI Agents ይፋ አድርጓል! 📱 ያለ ኢንተርኔት የሚሠሩ 3 አዳዲስ የ-AI መሣሪያዎች፦1. Jan AI (jan.ai) — ሙሉ በሙሉ በኮምፒውተር ላይ የሚሠራ ChatGPT 🎯 ምን ይሠራል? በኮምፒውተራችሁ ላይ አንዴ በመጫን፤ ያለ ምንም ኢንተርኔት ኮኔክሽን ጽሑፎችን ለመጻፍ፣ ኮድ ለማስተካከል እና መረጃዎችን ለመተንተን የሚያስችል 100% ነፃ እና ሚስጥራዊነቱ የተጠበቀ AI ነው። 2. Ollama (ollama.com) — ኃይለኛ የ-AI ሞዴሎችን በቤት ውስጥ ማስኬጃ 🎯 ምን ይሠራል? እንደ Llama-3፣ Mistral እና DeepSeek ያሉ ዓለማቀፍ ኃይለኛ የ-AI ሞዴሎችን በኮምፒውተራችሁ ውስጥ በመጫን፤ ያለ ምንም ወርሃዊ ክፍያ ወይም ኢንተርኔት እንደ የራሳችሁ የግል AI እንድትጠቀሙበት ያደርጋል። 3. PocketPal AI — ለስልክ የሚሆን Offline AI 🎯 ምን ይሠራል? በስልካችሁ (Android / iOS) ላይ በመጫን ዋይፋይ (Wi-Fi) ወይም የሞባይል ዳታ በሌለበት ቦታ ሁሉ ማንኛውንም ጥያቄ መመለስና የጽሑፍ ሥራዎችን መሥራት የሚችል አዲስ የሞባይል AI ነው። 💡 ዋና ጥቅሙ፦ ምንም ዓይነት የኢንተርኔትና የዳታ ወጪ የለውም፤ በተጨማሪም ማንኛውም የምትጽፉት መረጃ ወይም ሰነድ ከስልካችሁና ከኮምፒውተራችሁ ውጭ ወደ የትም ስለማይሄድ ከፍተኛ የሳይበር ደህንነትና ሚስጥራዊነት (Privacy) ይሰጣችኋል! 💎 መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ ሼርና ፎርዋርድ ማድረግ አይርሱ 🔺  @muleritsolutions2

✝️ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ ! ✝️ ⛪️ መልካም በዓል ! Muler IT Solutions!
+1
✝️ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ ! ✝️ ⛪️ መልካም በዓል ! Muler IT Solutions!

📺 አዲስ የህፃናት ቻናል በኢትዮሳት ገብቷል 🖥 Channel Name = AMECO kids ✅ Frequency = 11165 ✅ Polarization = Horizontal ✅ Symbol Rate = 450
+1
📺 አዲስ የህፃናት ቻናል በኢትዮሳት ገብቷል 🖥 Channel Name = AMECO kids ✅ Frequency = 11165 ✅ Polarization = Horizontal ✅ Symbol Rate = 45000 ☑️ አሁኑኑ በሪሞትዎ ሞልተው በቤትዎ ይመልከቱ። 🏵 መልካም ቀን/ ምሽት 🏵 🔴 አዳዲስ ፍሪኩዌንሲዎችና ቻናሎች ትኩስ ቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎች እንዲደርስዎ የ Telegram ቻናላችንን አሁኑኑ ይቀላቀሉ በርግጠኝነት ብዙ ነገር ይማሩበታል። @muleritsolutions2

🟢 ምን አይነት ሪሞት ኮንትሮል ይፈልጋሉ? 🟢 What type of remote control do you need? 🔷 የቲቪዎ፣ ጂፖስዎ፣ ሬሲቨርዎ፣ ሳውንድ ሲስተምዎ ፣ ቲቪ ስማርት ማድረጊያዎ፣ ፕሮጀክተርዎ ወዘተ ሪሞት ኮንትሮል በተለያየ ምክኒያት ጠፍቶብዎታል? 🔷 በትክክል ከእቃዎ ጋር ተጣጥሞ የሚሰራ ኦሪጅናል ቅያር ሪሞት አጥተው ተቸግረዋል? 🔶 እንግዲያውስ አያስቡ እኛ Remote ወርልዶች በተለያየ አጋጣሚ፣ የተሰበሩ፣ የጠፉ፣ ዋና ዋና በተኖቹ የማይሰሩ፣ ላያቸው ላይ ያለው ፅሁፍ የጠፋ፣ ጉዳት የደረሰባቸውና ማዘዝ የማይችሉ የተለያዩ ሪሞቶችን የሚተኩ ተለዋጭ ኦሪጅናል ሪሞቶችን እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ይዘንልዎት ቀርበናል። 🔺 ከርስዎ የሚጠበቀው የጠፋብዎትን ሪሞት የእቃውን ሞዴል በፎቶ፣ ከተበላሸ ደግሞ ራሱን የተበላሸውን ፎቶ አንስተው በዚህ ቴሌግራም ዩዘርኔም https://t.me/Sol5172 ወይም በ +251934595709 ፎቶና ሞዴሉን መላክ ነው። እኛም ለእርስዎ እቃ የሚገጥመውን ኦሪጅናል ተለዋጭ ሪሞት በተመጣጣኝ ዋጋ ያሉበት ድረስ አምጥተን ሞክረን እናስረክባለን። 🏨 በየቀኑ ብዙ እንግዳ ለሚያስተናግዱ ኢንተርናሽናል ሆቴሎች፣ budget- friendly ሆቴሎች፣ገስት ሃውሶች፣ ፔንሲዮኖች፣ ሎጆች፣ ሪዞርቶችና ሌሎችም ያሉበት ድረስ መጥተን ለቲቪዎ የሚገጥሙ ኦሪጅናል ተለዋጭ ሪሞቶች በየክፍሎቹ እየገባን ሞክረን መስራታቸውን ካረጋገጥን በኋላ ከነሪሞት መያዣ ሴፍቲ ከቨር ጋር እናስረክባለን። ⚠️ ገበያው ላይ በቀላሉ ተለዋጭ ሪሞት ለማይገኝላቸው እቃዎች ደግሞ Universal Remote (ለአብዛኞቹ እቃዎች የሚሆን ሪሞት) በማፈላለግ ያሉበት ድረስ መጥተን እንሞላለን። ድጋሚ እንዳይጉላሉ ደግሞ አሞላሉን እናሳይዎታለን። 📱በ +251934595709 ሃሎ ይበሉን ወይም በቴሌግራም ያዋሩን በተቻለ ፍጥነት መልስ ለመስጠት እንሞክራለን🙏 📍 Sol Dish Installation / Remote World

🔷 4G Simcard V380 smart camera / V380 4G battery camera ❇️ በ 4G ሲም ካርድ የሚሰራ እንዲሁም መብራት ኖረ አልኖረ ካሜራዎትን መከታተል እንዲችሉ ባትሪ በውስጡ ስ
+2
🔷 4G Simcard V380 smart camera / V380 4G battery camera ❇️ በ 4G ሲም ካርድ የሚሰራ እንዲሁም መብራት ኖረ አልኖረ ካሜራዎትን መከታተል እንዲችሉ ባትሪ በውስጡ ስላለው በቻርጅ የሚሰራ የደህንነት ካሜራ። 🔷 ይሔ በብዙ ደንበኞችና የካሜራ ገጠማ ባለሞያዎች ዘንድ እጅግ ተወዳጅና ተመራጭ የሆነ ካሜራ ዋጋው በግማሽ ቀንሶ ወደ ገበያ መጥቷል። ⚠️ ካሜራ ለማስገጠም አስባችሁ ዋጋው የተወደደባችሁና ያለ WiFi በሲም ካርድ ብቻ የሚሰራ በወር እጅግ ዝቅተኛ ወጪ ብቻ የሚያስወጣ ካሜራ የምትፈልጉ ይሄንን ድንቅ እድል እንድትጠቀሙበት ቤተሰባዊ ምክራችንን እንለግሳለን።

🚨 አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ 🚨 በቅርብ ጊዜ በቴሌግራም ላይ እጅግ አደገኛ የሆነ የአካውንት ጠለፋ እና የማጭበርበር ዘዴ በስፋት እየተሰራጨ ነው። ⚠️ ጠላፊዎች አሳሳች ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን በመጠ
🚨 አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ 🚨 በቅርብ ጊዜ በቴሌግራም ላይ እጅግ አደገኛ የሆነ የአካውንት ጠለፋ እና የማጭበርበር ዘዴ በስፋት እየተሰራጨ ነው። ⚠️ ጠላፊዎች አሳሳች ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን በመጠቀም ከእነሱ ጋር የተያያዙ ሊንኮችን (Links) ይልካሉ። ❗ እነዚህ መልዕክቶች ከማታውቋቸው ሰዎች ብቻ ሳይሆን፣ አካውንታቸው ከተጠለፈ ጓደኞቻችሁ፣ ዘመዶቻችሁ ወይም የምታምኗቸው ሰዎች ሊመጡ ይችላሉ። ⛔ ሊንኩን ጠቅ እንዳደረጋችሁ ወይም እንደከፈታችሁት፣ የቴሌግራም አካውንታችሁ በሰከንዶች ውስጥ በጠላፊዎች ቁጥጥር ስር ሊገባ ይችላል። 📤 ከዚያም አካውንታችሁን በመጠቀም ተመሳሳይ አደገኛ ሊንኮችን ለምታውቋቸው ሰዎች ይልካሉ። ለምሳሌ - እዚህ ዌብሳይት ላይ ፎቶህን እየውት የሚል ሊንክ ተልኮላችሁ ይሆናል ለመጠንቀቅ እነዚህ ነገሮች ፈፅሙ ቴሌግራም ውስጥ 1. ወደ Profile or setting ይግቡ 2. Devices የሚለውን ንኩት 3. Active session ላይ የማታውቁት ስልክ ካያችሁ Terminate አድርጉት ሁለተኛ 1. ወደ Setting and privacy ያቅኑ 2. Two step verification የምትል ከላይ ትመጣለች 3. የማትረሱትን  Password አስገብታችሁ Save ⚠️ አደራ Hint የሚለው ላይ ያስገባችሁትን ፖስዎርድ መልሳችሁ እንዳታስገቡ.. ብዙ ሰው ይህንን ሲሳሳት ስላየው