Muler IT Solutions Ethio GSM, Ethio Dish, ሞባይል ጥገና፣ ዲሽ ሶፍትዌር፣ ኮምፒውተር ጥገና፣ ዌብሳይት ስራ
前往频道在 Telegram
👉👉 አዳዲስና ትኩስ የቴክኖሎጂ ነክ መረጃዎችንና፣ ሞያ አዘል ፅሁፎችን፣ ጥያቄና መልሶችን፣የኮምፒውተርና የዲሽ ሪሲቨር ሶፍትዌሮችን፣ ጠቃሚ የሞባይል አፖችን ከተለያዩ የ Hacking እና Technical Trick ና ቲፖች የሚገኙበት ምርጥ ቻናል:: ለማንኛውም ጥያቄ @mulerjolly ን ወይም @mulerjolly3 ን ይጠቀሙ!! ወይም በ 0938020816 ወይም 0918711801 ይደውሉ። Share
显示更多2 659
订阅者
+224 小时
+297 天
+13630 天
帖子存档
🔺 አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ! 🚨
⚠️ ሰሞኑን በቴሌግራም ላይ እጅግ አደገኛ የሆነ የአካውንት ጠለፋ እና የማጭበርበር ድርጊት እየተፈጸመ ይገኛል።
⚠️ በጣም ፀያፍ የሆኑ ምስሎችን እና ቪዲዮዎችን እንደ ሽፋን በመጠቀም፣ ከስራቸው ሊንክ (Link) ያያይዛሉ።ሊንኩ የሚላክላችሁ ከማታውቁት ሰው ብቻ ሳይሆን፣ አካውንታቸው በተጠለፈ የቅርብ ጓደኞቻችሁ ወይም ዘመዶቻችሁ ስም ሊሆን ይችላል።
⚠️ ከዚያ ሊንኩን ልክ እንደነካችሁት የእናንተም የቴሌግራም አካውንት ወዲያውኑ በሰከንዶች ውስጥ ይጠቃል፣ ከቁጥጥራችሁ ውጪ ይሆናል። ከዚያም በእናንተ ስም ለሌሎች ሰዎች ተመሳሳይ ቫይረስ ይልካል።
⚠️ስለዚህ ከማንኛውም ሰው (የምታውቁትም ይሁን የማታውቁት) የሚላክላችሁን ማናቸውንም አይነት ሊንክ በፍጹም አትንኩ! አትክፈቱ!
እባካችሁ ይህንን መረጃ ለምትወዷቸው ሰዎች ሁሉ በማጋራት ከጠላፊዎች ይታደጓቸው።
☑️ መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ ሼርና ፎርዋርድ ማድረግ አይርሱ
🔶 @muleritsolutions2
+1
❇️ Mobiledit Ultra 9.8 Tool Cracked
🔷 ከላይ የለቀቅናቸው ሶስት የተለያዩ Mobiledit Ultra 9.8 Tool Cracked ፋይሎች ሲሆኑ ጥቅሙም የሞባይል ሶፍትዌር ጥገና ባለሞያዎች ሆነው ከዚህ በፊት በ ISP Pinout ይሰሩ የነበሩ አብዛኞቹን Exynos Chipset ያላቸውን Samsung ስልኮች በ Download Mode ራሱ ADB Enable ካደረገልን በኋላ በነፃ እና Paid Tools FRP እንድንከፍት ከፍተኛ ሚናውን ይጫወታል።
🔐 በተጨማሪም የቅርብ ሞዴል የሆኑ የተላያየ ብራንድና ሞዴል ያላቸውን ስልኮችን ፋይላቸው ሳይጠፋ PIN እና Pattern read በማድረግ Unlock ማድረግ ያስችለናል።
✅ ይሄ ቱል ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል:-
🔷 Exynos 850 Chipset ለሚጠቀሙ ስልኮች FRP Remove all binary
☑️ A047f
☑️ A135f
☑️ M135f
☑️ E135f
☑️ እና ሌሎች ሞዴሎችን መጥቀስ ይቻላል
✅ ከዚህ በተጨማሪ ብዙ MTK፣ SPD፣UniSoc እና HiSilicon Kirin Chipset ያላቸውን ሞዴሎች Support ያደርጋል::
🔺 ይሔን ቱል በዋናነት ህግ አስከባሪ አካላት፣ የውትድርና ተቋማት፣ ወንጀል ምርመራ ላይ የተሰማሩና በስለላ ተቋማት ውስጥ data extract ለማድረግና analysis ለመስራት ይጠቀሙበታል።
☑️ ለሞባይል ቴክኒሻኖች ደሞ በ ISP ይሰሩ የነበሩ ስልኮችን በደቂቃዎች ውስጥ ስልኩን መፍታት ሳያስፈልገን FRP Remove በማድረግ ድካምንና ገንዘብን በእጅጉ የሚቆጥብ የቴክኒሻኖች የምንጊዜም ባለውለታ የሆነ ገራሚ ቱል ነው።
✅ ይሄን ቱል ከላይ በሶስት አይነት አማራጭ ለቀንላችኋል አውርዳችሁ ተጠቀሙበት።
☑️ መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ ሼርና ፎርዋርድ ማድረግ አይርሱ
🔶 @muleritsolutions2
Repost from 𝔾𝕠𝕠𝕘𝕝𝕖 ℂ𝕙𝕒𝕔𝕙𝕒
MOBILedit_Forensic_ULTRA_9_8_0_34378_WITH_KEYGEN_UNLIMITED_2.rar3944.43 MB
Setup:
https://www.mediafire.com/file/t8zmq177egezvm2/Setup+MOBILedit+Forensic+ULTRA+9.8.0.34378.rar/file
Loder:
https://www.mediafire.com/file/k7vn5ulxxk06klm/MOBILedit+Loader.7z/file
Keygen:
https://www.mediafire.com/file/rdcvfiujl9anfdi/Keygen_MOBILedit_Forensic_ULTRA_9.8.0.34378_.rar/file
Driver:
https://www.mediafire.com/file/y1ds9jlxbqypzah/Drivers.zip/file
Zip password:
arieffservicecenter.com
ሀገሬ ቴሌቭዥን የአለም ዋንጫን በብቸኝነት በ HD (High Definition) የስርጭት ጥራት ማስተላለፍ በመቻላችሁ፣ የተሰማንን ደስታ ለመግለፅ እንወዳለን።
ኢትዮ ሳትም ከ ሀገሬ ቴሌቭዥን ጋር ወደፊት በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን በደስታ ይገልፃል።
Ethiosat
#Telegram
#ቴሌግራም
ቴሌግራም (Telegram) ኦፊሴላዊ ያልሆኑ የቴሌግራም መተግበሪያዎችን (Unofficial Apps) በሚጠቀሙ አካውንቶች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እና ማስጠንቀቂያ መስጠት እንደጀመረ አስታወቀ።
ቴሌግራም " ኦፊሴላዊ ያልሆኑ የተለያዩ መተግበሪያዎች የሚጠቀሙ ከሆነ የመልዕክት ልውውጡ ደህንነት ሊጠበቅ አይችልም፤ ለአደጋ ሊጋልጥም " ይችላል ብሏል።
በተለይ በሩሲያ ውስጥ "Telega" የተሰኘ የቴሌግራም መሰል መተግበሪያ ተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው።
የደህንነት ባለሙያዎች እንደሚሉት፥ ይህ መተግበሪያ የተጠቃሚዎችን አጠቃላይ መልዕክቶች እና መረጃዎች የመጥለፍ አቅም አለው።
ቴሌግራም እነዚህን ኦፊሴላዊ ያልሆኑ መተግበሪያዎች የሚጠቀሙ አካውንቶችን ለይቶ "Flag" እያደረገ (ምልክት እየሰጠ) ይገኛል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኦፊሻል ያልሆነው "Telega" አፕል ከአፕስቶር ላይ አውርዶታል።
ኦፊሴላዊ ያልሆኑ የቴሌግራም መተግበሪያዎች ምንድናቸው ?
እነዚህ መተግበሪያዎች የቴሌግራምን Open Source ኮድ በመጠቀም የተሰሩ ቢሆንም አበልፃጊዎቹ የራሳቸውን ኮዶች ይጨምሩበታል።
ለምሳሌ፦ Nicegram, Telega, Nekogram , Mobogram , Vidogram፣ Nijagram ... ሌሎችም እጅግ ብዙ ብዙ አሉ።
እነዚህ ከኦፊሴላዊ ቴሌግራም ውጭ በተለያዩ ሀገራት በሚገኙ የመተግበሪያ አበልጻጊዎች የሚሰሩ ናቸው።
🚨 አንዳንድ " ቴሌግራም መሰል " መተግበሪያዎች ምን ያስከትላሉ ? ኦፊሴላዊ ያልሆነውን ቴሌግራም መጠቀም ምን መዘዝ አለው ?
1. የመረጃ ደህንነት ጥሰት ፦ ወደ መተግበሪያዎቹ ሲገባ ዋናው የቴሌግራም አካውንት አክሰስ ይደረጋል ፤ በዚህም የግል የቴሌግራም መረጃዎች አደጋ ላይ ይወድቃሉ።
የተጠቃሚውን እና ቴሌግራም ላይ የተመዘገቡ ስልክ ቁጥሮችን የማግኘት፣ የግል መልዕክቶችን የማንበብ እንዲሁም የኦንላይን ሁኔታቸውን እንዲያውቁት እድል ይሰጣቸዋል።
2. ማልዌር እና ስፓይዌር ፦ 2023 ላይ ባለሙያዎች ጥናት ሲያደርጉ፣ 60000 ስልኮችን በቫይረስ የበከሉ የቴሌግራም አምሳያ መተግበሪያዎች ተገኝተዋል።
ልክ እንደ እውነተኛው ቴሌግራም የሚመስሉ ነገር ግን "ሌቦች የሰሯቸው" መተግበሪያዎች ስልክ ላይ አንዴ ከገቡ በኋላ ፦
👥 በስልክ ላይ የተቀመጡ የሰዎች ስም እና ስልክ ቁጥር በሙሉ ሊወሰዱ ይችላሉ።
💬 ሰዎች የሚጽፏቸውን እና የመጡላቸውን የግል መልዕክቶች በሙሉ እየገለበጡ ይወስዳሉ።
ሚስጥር በሌሎች እጅ ላይ ይወድቃል። ከጀርባ ብዙ ግላዊ መረጃዎች ተጋላጭ ይሆናሉ።
3. አካውንትን ሙሉ በሙሉ መነጠቅ (Account Hijacking) ፦ አንዳንድ መተግበሪያዎች "Trojanized" ናቸው ማለትም ከውጭ ሲታዩ ጠቃሚ ይመስላሉ፣ ውስጣቸው ግን አጥፊ ሶፍትዌር የያዙ ናቸው።
እነዚህ የሶስተኛ ወገን የቴሌግራም መተግበሪያዎች የሰዎችን Session / የመግቢያ ፍቃድ ይሰርቃሉ። በዚህም ምክንያት ፦
- እንደ ሩስያ ፣ ዩክሬን ፣ ኢራን ፣ ሊባኖስ ... የመሳሰሉ የጦርነት ቀጠና እንዲሁም የፖለቲካ ውጥረት ባለባቸው ሀገራት ሰዎች ሳያውቁት በግድ የተለያዩ ቻናሎች እና ግሩፖች ውስጥ አባል ይደርጋሉ። በዚህም ሰዎች ያለፍላጎታቸው እንዲገቡ ተደርገው ፕሮፖጋንዳ እና የተለያዩ መልዕክቶች ወደ ስልካቸው እንዲደርሳቸው ይደረጋል። (በግድ ሰዎችን ግሩፕ እና ቻናል ላይ የሚያስገቡት ሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎች ናቸው)
- ዋናውን የአካውንቱን ባለቤት አስወጥተው / Log out አድርገው አካውንቱን ሙሉ በሙሉ ሊቆጣጠሩት ይችላሉ ፤ ቀጥሎም ለወንጀል እና ማጭበርበር ስራዎች ይውላል።
ሲጠቃለል በተለያዩ ሀገራት የታየው ነገር ፥ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች የቴሌግራም ሚስጥራዊ ኮድ በዋናው መተግበሪያ ፣ በኢሜል፣ ወይም በስልክ እና በSMS ተቀብለው ወደ ኦፊሴላዊ ያልሆኑ መተግበሪያዎች ውስጥ ከገቡ በኋላ ወዲያው ፍቃዳቸውን እንዲያጡት ይሆናል ፤ እንዲሁም ያለ ሰዎቹ ፍቃድ አካውንታቸው እንቅስቃሴ ይደረግበታል።
ቴሌግራም ምን ይላል በዚህ ጉዳይ ?
የቴሌግራም መስራቹ ፓቬል ዱሮቭ ከዚህ ቀደም ግልጽ አድርገው እንደተናገሩት፥ ቴሌግራም ኦፊሴላዊ ያልሆኑ መተግበሪያዎችን ደህንነት ሊያረጋግጥ አይችልም።
በእነዚህ መተግበሪያዎች አማካኝነት መረጃ ቢሰረቅ ወይም አካውንት ቢጠለፍ ቴሌግራም ምንም ዓይነት ኃላፊነት አይወስድም።
ቴሌግራም ለደህንነት ሲባል ሁሌም ቢሆን የሶስተኛ ወገን መተግበሪያዎችን ከመጠቀም ይልቅ ዋናውን ቴሌግራም መጠቀም ይመክራል።
⚫ ኦፊሴላዊ ያልሆኑ ቴሌግራሞች በተለይ ጦርነት እና ፖለቲካው በጦዘባቸው አካባቢዎች የሰዎችን መረጃ ለመመንተፍ በስፋት ይውላሉ።
ዋናውና ኦፊሴላዊው ' ቴሌግራም ' የሚባለው የቱ ነው ? በዚህ ምልክት 📱 የምናገኘው ትክክለኛው፣ እውነተኛውና ህጋዊው የድርጅቱ የቴሌግራም መተግበሪያ ነው።
⚠️ የቴሌግራም አካውንታችሁን Log Out ከማድረጋችሁ በፊት ተጠንቀቁ!
🛑 ብዙ ተጠቃሚዎች አካውንታቸውን Log Out አድርገው በድጋሚ ለመግባት ሲሞክሩ "Code አንልክም፤ በኢሜይል እንዲላክ Premium ግዙ" የሚል መልዕክት እየመጣባቸው ተቸግረዋል 📉🤯
🔺 ችግሩ ምንድነው? ቴሌግራም የደህንነት መጠበቂያ ኢሜይል (Recovery Email) ያላስገቡ ተጠቃሚዎች አካውንታቸውን በሌላ ስልክ ወይም ከወጡ በኋላ ለመግባት ሲሞክሩ የኤስኤምኤስ (SMS) ኮድ ከመላክ ይልቅ በኢሜይል እንዲላክ ያስገድዳል 📧🔒 ኢሜይል ከሌለህ ደግሞ በክፍያ (Premium) እንድትገባ ሊጠይቅህ ይችላል 💸.
💡 መፍትሄው፦
1️⃣ አካውንታችሁ ሳይዘጋ፦ አሁኑኑ Settings ➡️ Privacy and Security ➡️ Two-Step Verification ውስጥ በመግባት ትክክለኛ የኢሜይል አድራሻችሁን አስገቡ
2️⃣ አካውንቱ ለተዘጋበት ሰው፦ በሌላ ስልክ ወይም ኮምፒውተር ላይ አካውንቱ ክፍት ካልሆነ፣ የቴሌግራም Support መጠየቅ ወይም ጥቂት ቀናትን ጠብቆ በድጋሚ መሞከር ሊያስፈልግ ይችላል ⏳🆘
⚠️ ማሳሰቢያ፦ አካውንታችሁ በሌላ ስልክ ላይ ክፍት ካልሆነ በስተቀር Log Out አታድርጉ! 🚫📱
❇️ ድንገት ቴሌግራም ላይ "Log out" ብታደርጉ ያለምንም code እንደገና ለመግባት passkey feature ን ይጠቀሙ !
🔶 ይህን setting on ለማድረግ Telegram setting ላይ በመግባት -> privacy and security -> passkeys -> create passkeys የሚለውን በመጫን passkey ይፈጠሩ !
📌 ይህ ለምን ይጠቅማል ? ድንገት ከ telegram log out ብትሉ በቀላሉ በ አሻራ / pattern/screen lock ወይ face በቀላሉ እንድንገባ ያደርጋል !
🔶 @muleritsolutions2
❇️ For FDRE Immigration and Citizenship
ለአዲስ ፖስፖርት አመልካቾች እና ፖስፖርት ላላችሁ በሙሉ አዲስ ጥሩ ዜና
✅ ከዚህ በኋላ አዲስ ፖስፖርት ለማውጣትም ሆነ ለማሳደስ የግድ ኢሚግሬሽን ቢሮ መሄዳ ሳይጠበቅባችሁ ቤታችሁ ሁናችሁ በ15 ደቂቃ ሙሉ መረጃዎቻችሁን ምታጠናቅቁበት ሂደት Immigration and Citizenship Services አጠናቅቆ ይፋ በማድረግ ላይ ይገኛል
🔷 እንደሚታወቀው ከዚህ በፊት አዲስ ፖስፖርት ለማውጣት የአሻራ ቀናችሁ አሻራ ለመስጠት ቢያንስ ከ5 ሰአት በላይ መሰለፍ እንዲሁም ሌሎች ሌሎች እንግልቶች ይጠበቅባችሁ ነበር ያ ነገር አሁን እየተቀረፈ ነው
📖 ከናሽናል ID ጋር በመተባበር እናንተ የናሽናል ID በመጠቀም ሙሉ መረጃችሁን ከዛላይ በመውሰድ አገልግሎቱን ቀላል እና ፈጣን ለማድረግ ተችሏል
✅ እንዲሁም ፖስፖርታችሁ ድርሶ የመውሸጃ ቀናችሁ ለማታውቁ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ባሉ ቀናቶች በስም ዝርዝራችሁ ቀን ብቻ በመሄድ ማውጣት ትችላላችሁ የቀን ፊደል ዝርዝሩ ከላይ ፎቶው ላይ ማግኝት ትችላላችሁ
ለተጨማሪ መረጃ ቻናላቸውን ይቀላቀሉ https://t.me/ICS_Ethiopia
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነገ ግንቦት 30 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን የኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው አካባቢዎች፦
✅ከጠዋቱ 1፡00 – 8፡00
👉በአዲስ አበባ ብሔረ ፅጌ፣ በአዲስ ታየር ፋብሪካ፣ በቀይ አፈር፣ በሳሪስ አቦ፣ በቦል ቡልቡላ፣ በአዋሽ ሌዘር ፋብሪካ፣ በሳሪስ አደይ አበባ፣ በአዲስ ሰፈር፣ ኦስካ ሜታል ፋብሪካ እና አካባቢው፣
✅ከጠዋቱ 3፡00 – 9፡00
👉በካዎ ጄጄ ፋብሪካ፣ 40/60 ኮንዴሚኒየም፣ በአወልያ፣ በአስኮ ገብርኤል፣ በአዲስ ሰፈር፣ በሚኪሊላንድ፣ በሳንሱሲ፣ በከታ መምህራን ሰፈር እና አካባቢው
✅ከጠዋቱ 12፡00 –11፡00
👉የአዳሚ ቱሉ ገንዳ አርባ 132 ኪ.ቮ አግሮ ኢንዱትሪ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ለመዘርጋት በታወር ቁጥር 3 እና በቁጥር 4 መካከል የሚገኘው ጀላን 33 ኪ.ቮ የኤሌክትሪክ መስመር የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል፡፡
✅ከጠዋቱ 2፡00 – 11፡00
👉መቀሌ ማጂክ ትምህርት ቤት፣ መከላኪያ ኮንዶሚኒየም፣ ደብረ ዳሞ፣ ሓወልቲ፣ ሰማዕታት፣ ዲ.ደብልዩ (DW) ቢሮ፣ ፕላኔት ሆቴል፣ አብርሃ ካስል፣ ማዕበል ሬስቶራንት፣ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን፣ ጅብሩክ፣ ቀደማይ ወያኔ፣ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ፣ መስኪድ፣ ቀበሌ 04 እና አካባቢው፣
✅ከጠዋቱ 2፡30 – ምሽቱ 4፡00
👉ወንጂ እርሻ፣ ፖሊስ ኮሌጅ ፣ AISO4፣ AIS፣ አዋሽ መልካሳ፣ ሲሬ፣ ሁሩታ፣ ዴራ፣ ዲና ፉድ ኮምፕሌክስ፣ አሉሚኒየም ሰልፌት (Aluminium Sulphate) ፋብሪካ/ኮምፕሌክስ (በፌዝ ተጠቃሚነቱ ይለያያል)።
✅ከጠዋቱ 2፡30 – 6፡00
👉ጁኒፐር ግላስ ፋብሪካ ፣ደብረ ብርሃን ከተማ (ሀቢታት፣ ጮሌ እና ተባሴ) ፣ የባትሪ ፋብሪካ፣ ሞሪጋ ፋብሪካ፣ ደጋ ውሃ ፋብሪካ፣ ሐገረ ማርያም፣ ጊናገር፣ ጫጫ፣ ሸኖ አና አካባቢዎች
✅ከቀኑ 7፡00 – 11፡00
👉ደብረ ብርሃን ከተማ፣ አጎንሌላ፣ መንዲዳ፣ ደነባ አካባቢው የኃይል አቅርቦት ተቋርጦ ይቆያል፡፡
ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ የተከበራችሁ ደንበኞቻችን የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን እንጠይቃለን፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ከ ሰኔ 4 እስከ ሐምሌ 12 የሚካሄደውን የ2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ (FIFA World Cup 2026) በነፃ የለምንም ክፍያ በነዚህ ቻናሎች መከታተል ይቻላል ።
📺 Hagerie TV 🆓
📡 NSS12 57°E 11105H45000
📺 World Cup HD 🆓
📡 Yahsat 52°E 12034V27500
📺 GEM SPORT HD 🆓
📡 Yahsat 52°E 12034V27500
📺 IRIB Varzesh HD 🆓
📡 Express 40°E 11640H30000
📺 IRIB TV3HD🆓
📡 Express 40°E 11640H30000
📺 ATN HD 🆓
📡 Yahsat 52°E 11938H27500
📺 Arezo TV HD🆓
📡 Yahsat 52°E 12015H27500
📺 Esteqlal TV 🆓
📡 Yahsat 52°E 12015H27500
📺 1TV HD 🆓
📺 2TV HD 🆓
📡 Eutelsat 36°E 11221H30000
📺 MAKAN HD 🆓❓
📡 ናይል ሳት 7°W 11631V27500
📺 ETV ENT HD 🆓❓
📡 NSS12 57°E 11105H45000
🔷 በተጨማሪም በክፍያ በ DSTV, bein Sport እና የተለያዩ VIP ሰርቨሮች መከታተል ይቻላል።
🔺 ወደፊት አዳዲስ መረጃዎችን እየተከታተልን የምናቀርብላችሁ ይሆናል።
❇️ Safety Tip For Kids
☑️ ስልክ ገዝታችሁ ለልጆች በምትሰጡበት ወቅት አልባሌ ነገሮችን መቆጣጠር አስፈላጊ ነገር ነው። ታዲያ በርካቶቻችን ስልክ የሚገኘው google chrome browser በብዛት አልባሌ ነገር ሲታይበት ይስተዋላል። ይህንንም ችግር መቀነስ የሚያስችል አንድ የ chrome setting እናሳያችሁ።
☑️ በመጀመሪያ google chrome browser ከከፈታችሁ በኋላ ሶስት ነጥብጣቡን ነክታችሁ ወደ setting ውስጥ ግቡ።
☑️ Privacy and security የሚለውን ምረጡ።
☑️ በመቀጠል ትንሽ scroll እንዳደረጋችሁ የምታገኙትን "use secure DNS" የሚለውን ምረጡ።
☑️ "use your current service provider" የሚል በdefault ተመርጦ የምታገኙ ሲሆን እኛም ከታች ያለውን "choose another provider" የሚለውን እንመርጣለን።በመጨረሻም ከስር የሚመጣልንን "custom" የሚለውን ነክተን "clean browsing (family filter)" የሚለውን መምረጥ።
☑️ ከዚህ በኋላ chrome ላይ ማንኛውንም አልባሌ ነገር አታገኙም።
☑️ መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ ሼርና ፎርዋርድ ማድረግ አይርሱ
🔶 @muleritsolutions2
+2
📖 Content Writing & Website Development Service from Muler IT Solutions
📖 Content Writing & Website Development Service from Muler IT Solutions
🔷 ሽያጭዎን በእጅጉ ከፍ የሚያደርጉ ለተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች የሚሆኑ የቴክኖሎጂ ኮንቴንቶችን በጥራት እናዘጋጃለን
✅ ለተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የሚሆኑ ስክሪፕቶችን ማዘጋጀት
✅ የቴክ ፕሮዳክት (Tech Product) ዝርዝር ፅሁፍ (Product Description) ማዘጋጀት
✅ ለተለያዩ ሶሻል ሚዲያ የሚሆኑ አጫጭር Storyboard ማዘጋጀት
✅ የቤት ውስጥ መገልገያ ሻጭ ካምፓኒዎች፣ ለኤሌክትሮኒክስ ካምፓኒዎች፣ ለቴክ ካምፓኒዎች፣ ለነጋዴዎች፣ Resellers፣ E-commerce ላይ ለሚሰሩ ወዘተ...
✅ አዳዲስ ፕሮዳክቶችን ለማህበረሰቡ በማራኪና ደረጃውን የጠበቀ አቀራረብ
ማስተዋወቅና ገበያውን ሰብሮ መግባት የሚያስችሉ ፅሁፎችን ማዘጋጀት
✅ ጊዜ ለሌላቸው፣ Tech Field ላይ ላልተሰማሩ፣ ለአከፋፋዮች፣ Social Media ማኔጅመንት ለሚሰሩ፣ Digital Marketing ላይ ለተሰማሩ ወዘተ.. ጊዜና ገንዘብ የሚቆጥቡ በብቁ ባለሞያዎች ማራኪ ይዘቶችን ማዘጋጀት
✅ Remotely ለሚሰሩ Graphics Designers, Video Editors, 3D Animators, Promoters, Producers ወዘተ.. አጋዥ ኮንቴንቶችን በጥራት ማዘጋጀት
✅ ቀልብ የሚይዙ፣ ወቅታዊ Trend የሆኑ ርዕሶችን ያማከሉ ፅሁፎችን፣ Hooks ፣ Brand የማስተዋወቂያ ፅሁፎችን በጥራት እናዘጋጃለን።
✅ በተጨማሪም ለ Start up ቢዝነሶች፣ ለተለያዩ ትላልቅ ካምፓኒዎች፣ ለግለሰቦች ወዘተ.. ጥራት ያለውና ፅድት ያለ ድህረ-ገፅ እጅግ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ በአጭር ጊዜ ውስጥ ገንብተን እናስረክባለን።
✅ እንዲሁም ዌብሳይት ጥገናና የማስተካከል ስራ ብሎም SEO optimization (የተለያዩ Search Engines ላይ ዌብሳይትዎ የመጀመሪያው ገፅ ላይ እንዲመጣ እናደርጋለን።)
📱 አሁኑኑ ይደውሉልን! Muler IT Solutions!
📞 +251938020816
🔶 @muleritsolutions2
የጥገና ሥራ ለማከናወን የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት
ነገ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም የጥገና ሥራ ለማከናወን ኃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸው ቦታዎች ፦
⏰✅ ከጠዋቱ 2:30-7:00
👉 በአዲስ አበባ አስኮ ገብርኤል፣ ሳንሱሲ፣ እያሱ ምንጭ፣ ብርጭቆ ኮንዶሚኒየም፣ ከታ አፍያ ዴቄት፣
⏰✅ ከጠዋቱ 3:00 እስከ ምሽቱ 4:00 ድረስ
👉 ቂሊንጦ ኮንዶሚኒየም፣ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት፣ አስቱ ዩኒቨርስቲ እና ኢንዱስትሪ መንደር፣ ኬኬ ብርድ ልብስ ፋብሪካ፣ ዋልያ ቢራ
⏰ ✅ከጠዋቱ 6:00-9:00
👉 በምዕረብ አደስ አበባ ሪጅን ስልጤ ሰፈር፣ አጃምባ ኮንዶሚኒየም
⏰ ✅ከቀኑ 7፡00- 11፡00
👉 ሸጎሌ አንበሳ ጋራዥ፣ ሸጎሌ መንደር-7፣ ፊናንስ፣ አበበ ቢቂላ፣ ኳስ ሜዳ፣ መሳለሚያ
⏰✅ ከጠዋቱ 2:00-12:00
👉 በአዳማ ሪጅን አዳማ ቆርቆሮ፣
⏰✅ ከጠዋቱ 2:00-11:00
👉አዳማ ፈትል ፋብሪካ፣ ሬድሬስ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ፣ አህዋን ፋብሪካ
⏰✅ ከጠዋቱ 2:30-9:00
👉 በአዳማ ሪጅን ከአዋሽ መልካሳ ወደ አዱላላና አሮሪቲ፣
⏰✅ ከቀኑ 7:30-10:30
👉 በሽረ ረጅን እደጋ አርቢ፣ ማይ ቐንታል
ስለሆነም በአካባቢው የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻች የጥገና ሥራው ተጠናቆ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ በትእግስት እንድትጠብቁን በአክብሮት እናሳስባለን፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
❇️ በየካፌው እና ሆቴሉ የሚያገኟቸውን "ነፃ ዋይፋዮች" (Public Wi-Fi) ያለምንም ጥንቃቄ የመጠቀም ልምድ አለዎት? ይህ ልምድዎ ስልካችሁ ሳይታወቅ እንዲጠለፍ ትልቅ በር ሊከፍት ይችላል!
⚠️ ጠላፊዎች "Man-in-the-Middle" በሚባል ዘዴ እናንተና በዋይፋዩ መካከል በመግባት የምትልኳቸውን ሚስጥራዊ መረጃዎች፣ ፓስወርዶችን እና የባንክ አካውንቶችን ሊሰርቁ ይችላሉ።
✅ ራሳችሁን ለመጠበቅ እነዚህን 3 ወሳኝ ህጎች ተግብሩ፦
1️⃣ የባንክ አፖችን በፍጹም አትክፈቱ፦ በህዝብ ዋይፋይ አገናኝታችሁ በምትጠቀሙበት ሰዓት የባንክ አካውንታችሁን፣ ቴሌብርን ወይም የትኛውንም የገንዘብ ማንቀሳቀሻ አፕሊኬሽን በፍጹም እንዳትከፍቱ።
2️⃣ አስተማማኝ VPN ይጠቀሙ፦ የግድ የህዝብ ዋይፋይ መጠቀም ካለባችሁ፣ መረጃዎቻችሁ ተመስጥረው (Encrypted ሆነው) እንዲሄዱና ጠላፊዎች እንዳያነቡት ለማድረግ ጥራት ያለው VPN አብሩ።
3️⃣ "Auto-Connect" አጥፉ፦ ስልካችሁ ያገኛቸውን ክፍት ዋይፋዮች በራሱ ጊዜ እንዳያገናኝ (Auto-Connect) የሚለውን ሴቲንግ አጥፉት።
🔺 ባለማወቅ ለጠላፊዎች መረጃ ከመስጠት፣ ጥቂት የባንክ ዳታ ተጠቅሞ ራስን መጠበቅ ያተርፋል! 🛡️✨
☑️ መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ ሼርና ፎርዋርድ ማድረግ አይርሱ
🔶 @muleritsolutions2
+2
ውድ ደንበኛችን!
የተሻሻለውን የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ አዘምነው አገልግሎቱን ለመጠቀም ሲሞክሩ 'Passphrase' ጠይቆዎት የነበረው ጊዜያዊ ችግር የተፈታ መሆኑን እየገለፅን፤ አሁን ላይ አገልግሎቱን በነባሩ የይለፍ ቃልዎ በቀላሉ መጠቀም የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን።
በዚህ አጋጣሚ ከሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ጋር በተያያዘ በስልክ ተደውሎ የሚሰጥ ምንም አይነት የአሰራር ሂደት የሌለ መሆኑን በመረዳት እራስዎን ከአጭበርባሪዎች ይጠብቁ።
ለማንኛውም አይነት መረጃ 951 በነፃ ይደውሉ!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ!
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!!
❇️ ስልካችሁ በውሃ ውስጥ ቢገባ ወይም ቢረጭ በፍጹም ሊታደርጓቸው የማይገቡ ስህተቶች!
✅ ብዙዎቻችን ስልካችን ውሃ ሲነካው በድንጋጤ የምንሰራቸው ስህተቶች ስልኩን ሙሉ በሙሉ እንዲበላሽ ሊያደርጉት ይችላሉ።
🔺 እነዚህን 3 ነገሮች በፍጹም አታድርጉ፦
✅ ፀጉር ማድረቂያ (Hair Dryer) መጠቀም፦
የፀጉር ማድረቂያው የሚረጨው ከፍተኛ ሙቀት የስልኩን ስስ የውስጥ ክፍሎች (Sensors) ሊያቀልጥ ይችላል። በተጨማሪም ውሃው ይበልጥ ወደ ውስጥ እንዲገባ ይገፋዋል።
✅ ስልኩን ለማድረቅ ማወዛወዝ፦
ስልኩን በሀይል መነቅነቅ ውሃው ባልደረሰባቸው የውስጥ ክፍሎች ላይ እንዲሰራጭ ያደርገዋል። በለስላሳ ጨርቅ መጥረግ ብቻ በቂ ነው።
✅ ቻርጅ ማድረግ፦
ስልኩ ውስጥ እርጥበት እንዳለ ቻርጅ ማድረግ "Short Circuit" ፈጥሮ ስልኩን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲቃጠል ያደርገዋል።
🔺 ምን ማድረግ አለብኝ? ስልኩን ማጥፋት፣ ሲም ካርዱና ሚሞሪውን ማውጣት፣ ከዚያም አየር በሚገባበት ቦታ ላይ ቢያንስ ለ24 ሰዓታት ማስቀመጥ የተሻለ መፍትሄ ነው።
☑️ መረጃው ለወዳጅ ዘመድ እንዲዳረስ ሼርና ፎርዋርድ ማድረግ አይርሱ
🔶 @muleritsolutions2
የስልካችሁ ስፒከር (ድምፅ ማውጫ) እንደ ከዚህ ቀደሙ በደንብ አይጮህም? ወይስ ድምፁ ተሰነጣጥቆ ወይም ታፍኖባችኋል?
ብዙ ጊዜ ስልካችንን ኪሳችን ውስጥ ስንከት ወይም በተለያየ ቦታ ስናስቀምጠው ጥቃቅን አቧራዎች ስፒከሩ ውስጥ ይገባሉ። እንዲሁም ድንገት ውሃ ወይም ላብ ሲነካው ድምፁ ይታፈናል። ይህንን ችግር ለመፍታት ስልኩን መፍታት ወይም መርፌ መክተት አያስፈልግም (መርፌ መክተት ስፒከሩን ይቀደዋል!)። በከፍተኛ የድምፅ ሞገድ (Sound Frequency) ብቻ አቧራውንና ውሃውን ማስወጣት ይቻላል።
🛠 ይህንን ለማድረግ 2 ቀላል መንገዶች እነሆ፦
1️⃣ የሺያኦሚ (Xiaomi/Redmi) ስልክ ተጠቃሚ ከሆናችሁ፦ የእናንተ ስልክ ይህንን ችግር የሚፈታ ድብቅ የራሱ ሴቲንግ አለው።
👉 መፍትሄ፦ ወደ ስልካችሁ Settings ➡️ Additional Settings ➡️ Clear Speaker ውስጥ በመግባት ማብሪያውን ያብሩት። ስልካችሁ ለ 30 ሰኮንዶች ያህል ከፍተኛ ሳይረን (ድምፅ) ያሰማል፤ በዚህ ሰዓት ስፒከሩ ውስጥ ያለውን አቧራ በንዝረት ፉት አድርጎ ያወጣዋል። (ይህንን 2 ወይም 3 ጊዜ ደጋግሙት)።
2️⃣ ለሳምሰንግ፣ ለአይፎን እና ለሌሎች ስልኮች በሙሉ፦ የስልካችሁን የድምፅ መጠን መጨረሻ ላይ (Max) አድርጉትና በማንኛውም ብሮውዘር (ለምሳሌ Chrome) በመግባት ይህንን ድረ-ገጽ ክፈቱ፦
👉 🌐 www.fixmyspeakers.com 👈 👉 መፍትሄ፦ ድረ-ገጹ ሲከፈት የውሃ እና የንፋስ ምስል ያለበትን ትልቅ ቁልፍ ይጫኑ። ስልካችሁ አቧራውንና የገባውን ውሃ ገፍቶ የሚያወጣ ልዩ የንዝረት ድምፅ ማውጣት ይጀምራል። ድምፁ ለ 1 ደቂቃ ያህል እንዲሰራ ካደረጋችሁ በኋላ ስፒከራችሁ ሙሉ በሙሉ ጸድቶ ወደ ቀድሞ ጥራቱ ይመለሳል!
⚠️ ወሳኝ ምክር፦ ይህንን ድምፅ ስታጫውቱ ስልካችሁን ስፒከሩ ወደ ታች እንዲመለከት አድርጋችሁ ያዙት (አቧራውና ውሃው በቀላሉ እንዲረግፍ)።
✅ አሁኑኑ ሞክሩትና የስልካችሁን ድምፅ ጥራት ይመልሱ! ⚡️
现已上线!2025 年 Telegram 研究 — 年度关键洞察 
