uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Kanalga Telegram’da o‘tish

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
908
Obunachilar
-324 soatlar
-157 kun
+4830 kun
Postlar arxiv
♦️♦️♦️ሰውን በተስፋ አታንከራትቱ 📍አንድ ሰው ወደ እናንተ ሲመጣ ገንዘብ ብቻ አይፈልግም፤ ተስፋ ይፈልጋል፣ መፍትሔ ይፈልጋል፣ ከልብ የሚያዳምጠውን ሰው ይፈልጋል። 📍የልቡን ብሶት፣ የቤተሰቡን ጭንቀት፣ የሥራ ማጣቱን እና የኑሮ መከራውን ከፍቶ ሲነግራችሁ በእናንተ ላይ እምነት አድርጎ ነው። ከዚያ በኋላ ግን፦
“እንረዳሃለን፣ እናግዝሃለን፣ ሥራ እናስገባሃለን፣ ጉዳይህ የእኛ ጉዳይ ነው…”
ብላችሁ ተስፋ ትሰጡታላችሁ። ነገር ግን ዛሬ ና፣ ነገ ና፣ ሳምንት ጠብቅ፣ ይሄን አድርግ፣ ያንን ሰው አግኝ እያላችሁ ለምን ታንከራትቱታላችሁ? የሰውን ጊዜ ማጥፋት ብቻ አይደለም፤ የልቡን ተስፋ ማድከም ነው። የማይሆን ከሆነ… “አይሆንም” በሉ። አዎ፣ እውነት አንዳንድ ጊዜ ትከብዳለች፤ ግን ከሐሰተኛ ተስፋ ትሻላለች። ሰው ግልጽ መልስን ይቀበላል፤ ነገር ግን የማያልቅ ጥበቃ ይሰብረዋል። 📍እስቲ ራሳችሁን ጠይቁ ዛሬ የደረሳችሁበት ከመድረሳችሁ በፊት ምን ላይ ነበራችሁ? ማን እጁን ዘርግቶ አነሳችሁ? ማን አንድ በር ከፍቶ ዕድል ሆነላችሁ? እናንተም አንድ ቀን የሰው ደጅ የቆማችሁ ሰዎች ነበራችሁ። ስለዚህ ዛሬ ያንን ታሪክ አትርሱ። ለሰው ሰበብ ሁኑ ማድረግ ከቻላችሁ በተቻላችሁ መጠን አድርጉ። ማድረግ ካልቻላችሁ ግን በክብር ንገሩት። “አልችልም” የሚል እውነተኛ ቃል፣ “እንረዳሃለን” ከሚል ባዶ ተስፋ ይሻላል። ሰውን በተስፋ አታሰቃዩ። ችግሩን አታብዙበት። ተስፋውን አትጫወቱበት።
ዛሬ ለሌላው የምትሆኑት ሰበብ፣ ነገ ለእናንተ የሚመጣው ሰበብ ሊሆን ይችላል።
ተፃፈ :በአቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba

አብሽሩ የኛም ቀን ይመጣል.... ኢንሻአላህ

ያ ኢላሂ እኔ ካንተ ዉጭ ማንም ረዳት የለኝም አንተዉ እርዳኝ ኸይሩን ነገር ሁሉ ወፍቀኝ ሸርን ነገር ሁሉ አርቅልኝ በእዝነትህ ያረብብ🤲 http://t.me/UmuAbais

​አምላኬ ሆይ፤ ለትእዛዝህና ለመብትህ ተገቢውን ቦታ አልሰጠሁም፤ ከ አንተ ውጪ ሌላ አካል አለመንኩም።  ​አምላኬ ሆይ፤ ወደ በጎ ስራዎች ለመሮጥ አልቸኮልኩም፤ የታማኝነትን  በር ለማንኳኳት አልተጋሁም።  ​አምላኬ ሆይ፤  ከሐሜት የራቅኩኝ ባልሆንም፤ ነብያቶችህንና የመረጥኳቸውን  ባሮችህን ግን አልተሳደብኩም።  ​አምላኬ ሆይ፤ ከበርህ ከቶ አርቅም፤ ምክንያቱም ከአንተ ውጪ ሌላ ማውራት አልፈልግም።  ​አምላኬ ሆይ፤ ከበርህ ፈቀቅ አልልም፤ ምክንያቱም ከአንተ ውጪ በሌላ አካል አልደሰትም።  ​አምላኬ ሆይ፤ ስራዬ ልክ እንደ ውኃ ቅዠት  ባዶ ነው፤ ልቤም አንተን ከማምለክ ባዶ ነው።  ​አምላኬ ሆይ፤ ሃጢያቴም ከአፈር ብዛት በላይ ብዙ ነው፤ አንተ ግን ይቅርታ ለማድረግና ላለመውቀስ ከሁሉ በላይ ባለቤት  ነህ።  ​ስለዚህም በችሮታህና በልግስናህ ማረን፤ ይቅርም በለን፤ አንተ የልቅናና የማላቅ ባለቤት የሆንከው ሆይ!

حرم الله على النار وذريته كل من نصر هذا الدين واو بكلمة أو دعوة بظهر الغبب

📢 አስቸኳይ የማስተላለፊያ ጥሪ! ይህ የእውቀት ጥሪ ለሁላችንም ነው! 📚🌿 👉 መልዕክቱን በTelegram ሼር አድርጉ፤ 👉 ያላዩትን ተማሪዎች እና የእውቀት ፈላጊዎችን በስልክ ደውላችሁ አሳውቁ። 📞 🤲 ምናልባት በእርስዎ ማስታወቂያ አንድ ሰው የእውቀት መንገድ ይጀምር ይሆናል። ⏰ ዛሬ ከመግሪብ በኋላ 🕌 መስጅደል አዝሀር — ጅብሪል ጎራ ሼር ያድርጉ፣ ደውለው ያሳውቁ፣ አንድም ሰው እንዳይቀር! 🌿📚 بارك الله فيكم ونفع بكم 🤲 https://t.me/abuabdelah123

🌹 ፍቅር ሪዝቅ ነው… ያፈቀሩትን ማግኘት ደግሞ መድኃኒት ነው። 🥀 አንዳንድ ሰዎች ወደ ልባችን የሚመጡት በዕድል አይደለም፤ በአላህ የተጻፈ ሪዝቅ ሆነው ነው። ልብህ ያለምክንያት ለአንድ ሰው ሲያዘነብል፣ በእርሱ መገኘት ሰላም ሲሰማህ፣ ድምፁ የድካምህን ጫና ሲያሳርፍልህ… እነዚህ ሁሉ ልብ የሚገልጣቸው ስሜቶች ናቸው። ፍቅር ማለት ሰውን ማየት ብቻ አይደለም፤ በልብ ውስጥ ለእርሱ ልዩ ቦታ መኖሩ ነው። አንዳንዴ አንድ ሰው ከሺዎች መካከል ልዩ ይሆናል፤ ምክንያቱም ልብህ እርሱን ብቻ በሚያውቅ ቋንቋ ይገናኘዋል። እና እንዴት ያለ በረከት ነው… የምትወደው ሰው አንተንም ሲወድ፣ የምትፈልገው ሰው አንተንም ሲፈልግ፣ የምትናፍቀው ሰው አንተንም ሲናፍቅ! ከሁሉም የሚያምረው ግን ፍቅሩ በሕላል መንገድ ሲጠናቀቅ ነው። ያኔ የብቸኝነት ምሽቶች ይረሳሉ፣ የመናፈቅ እንባዎች ይደርቃሉ፣ ረጅም ጊዜ የጠበቀው ልብም በሰላም ይሞላል። ምክንያቱም ያፈቀሩትን ማግኘት መድኃኒት ነው፤ ከእርሱ ጋር በሕላል ሕይወት መጋራት ደግሞ የዚያ መድኃኒት ሙሉ ፈውስ ነው። 🌿ስለዚህ አንድን ሰው ከልብህ ከወደድከው፣ ሁሉንም ነገር በእጅህ ለማድረግ አትሞክር። ፍቅርህን አክብር፣ ልብህን ጠብቅ፣ አላህንም አመን። ከተጻፈልህ ሰው አትሸሽም፤ ከአንተ ጋር እንዲኖር ካልተጻፈም በምንም ኃይል ወደ ህይወትህ አታስገባውምና። አንዳንድ ፍቅሮች ወደ ሕይወታችን የሚመጡት ለመቆየት ነው፤ ሌሎች ደግሞ ለመማር። ነገር ግን አላህ የጻፈው ሰው ከሆነ… ርቀት፣ ጊዜ፣ መሰናክልና መጠበቅ ሁሉ በመጨረሻ መንገዱን ያገኛል። ፍቅር ሪዝቅ ነው… መናፈቅ ፈተና ነው… መጠበቅ ሰብር ነው… መገናኘት ግን ስጦታ ነው። እና ከሁሉም በላይ፦ በሕላል መንገድ ያፈቀሩትን ሰው አግኝተው፣ “አላህ ሆይ፣ ይህን ሰው በሕይወቴ ውስጥ ስላስገባልኝ አመሰግንሃለሁ” ማለት… ከፍቅር በላይ የሆነ ኒዕማ ነው። t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

ነቢዩ ﷺ አብዛህኛው ጊዜ ዝምታ የሚያበዙ፣ ያለ አስፈላጊነት የማያወሩና፣ በማይመለከታቸውም ነገር የማይናገሩ፣ ምንዳውን ከአሏህ በሚፈልጉበት ነገር ካልሆነ በስተቀር የማይናገሩ ነበሩ፤ አንድን ነገር ሲጠሉ ደግሞ በፊታቸው ላይ ይታወቅ ነበር።
📚ابن القيِّم
t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie

||
የተስሒሑ ቲላዋ በሙሐመድ ሲራጅ
አል-ኬሚሴ
|| √√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√√
ከ1_30 ያሉትን በዚህ ሊንክ እየገባችሁ ተከታተሉ
┈──── ••⇣⇣┈──── ⇣⇣───⇣⇣─── ክፍል ❶ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/836 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ➋ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/844 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል❸ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/861 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ➍ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/889 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ❺ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/900 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል❻ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/914 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ❼ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/943 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ❽ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/943 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ➒ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/970 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል❿ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/992 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ⓫ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1015 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ⓬ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1038 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ⓭ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1052 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል⓮ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1068 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ⓯ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1080 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል⓰ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1090 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል⓱ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1110 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል⓲ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1118 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል⓳ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1136 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል⓴ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1155 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል➋❶ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1171 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል➋➋ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1193 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል➋❸ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1748 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል➋➍ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1777 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል➋❺ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1791 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል➋❻ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/1817 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል➋❼ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/2026 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል➋❽ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/2046 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል➋➒ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/2065 ⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦⤥⤦ ክፍል ❸⁰ https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie/2830 የቴሌግራም ቻናል ↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️↪️ 💙📎https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie 💙📎https://t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie

ደስታን_በዲናችን_ውስጥ_እንፈልግ_!!.m4a21.96 MB

የከሀዲያንን በዓል "እንኳን አደረሳችሁ" ማለት ይቻላል ወይስ አይቻልም ⁉️ 𝚏𝚘𝚛 𝚠𝚊𝚟𝚎 ➙ @suna_waver

✍ልዩነት..... 🤎በጀግና ወንድ ጭንቅላት ውስጥ ብዙ የሱናህ ኪታቦች እና የአሏህ ቃል ቁርኣን ሲኖር.... 🤎 በማይረባ ወንድ ጭንቅላት ውስጥ ደግሞ ብዙ አይነት ቅርፅ ያላቸው እና ብዙ አይነት ከለር ያላቸው ሴቶች አሉ.... 🤝ምርጫው ያንተ ነው ማን...?! https://t.me/abu_hassan_aliy_yusuf https://t.me/abu_hassan_aliy_yusuf

✔️ጥቂትም ቢሆን መልካም ስራን አሳንስህ አትመልከት! ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ما مِنكُم مِن أحَدٍ إلّا وسَيُكَلِّمُهُ اللَّهُ يَومَ القِيامَةِ، ليسَ
✔️ጥቂትም ቢሆን መልካም ስራን አሳንስህ አትመልከት! ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ما مِنكُم مِن أحَدٍ إلّا وسَيُكَلِّمُهُ اللَّهُ يَومَ القِيامَةِ، ليسَ بيْنَ اللَّهِ وبيْنَهُ تُرْجُمانٌ، ثُمَّ يَنْظُرُ فلا يَرى شيئًا قُدّامَهُ، ثُمَّ يَنْظُرُ بيْنَ يَدَيْهِ فَتَسْتَقْبِلُهُ النّارُ، فَمَنِ اسْتَطاعَ مِنكُم أنْ يَتَّقِيَ النّارَ ولو بشِقِّ تَمْرَةٍ﴾ “ከእናንተ ውስጥ በቂያማ እለት በአላህና በሱ መካካል አስተርጓሚ ሳይኖር አላህ የማያናግረው አንድም ሰው አይኖርም። ከዚያም ወደ ፊት ለፊቱ ይመለከታል ምንም ነገር አያይም። ከዚያም በስተቀኙ በስተግራውም ይመለከታል እሳትም ትቀበለዋለች (ትጋፈጠዋለች)። ከእናንተ ውስጥ እሳትን በግማሽ ቴምርም ቢሆን (ምፅዋት ሰጥቶ) መከላከል የቻለ ያድርገው።” 📚 ቡኻሪ (6539) ሙስሊም (1512) ዘግበውታል ➖➖➖➖➖➖➖ ✅ በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦ 📱 Telegeram 📱 Whatsup 📱 Facebook  📱 Instagram 📱 X 📱 Youtube 📱 Tik tok

ህይወትና መሰናክሏ እኛም እንደዚሁ ነን። ወደ ድል በቀረብን ቁጥር ከማናውቀው አቅጣጫ የተረገመ አንድ ውሻ ይመጣል። t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

ፊዳከ አቢ ወዑሚ ያረሱለላህ!ያነብየላህ!ያአሽረፈልኸልቅ!

የማይበርደው ሃዘን ~ ውዱ ነቢያችን - ﷺ - በ23 አመት መሪር ትግል መናገሻውን በመዲና ከተማ ያደረገ ተምሳሌት የሆነ ኢስላማዊ ሃገር መስርተው፣ በታሪክ አምሳያ የሌለው ድንቅ ትውልድ ኮትኩተው፣ የተውሒድን መሰረት አፅንተው በ63 አመታቸው በ11ኛ አመተ ሂጅሪያ በወርሃ ረቢዑል አወል 12ኛ ቀን እለተ ሰኞ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡ ይህ የሳቸው ህልፈት በታሪክ የሰው ዘርን የገጠመው ትልቁ አደጋ ነው፡፡ ህመሙን፣ ስሜቱን፣ ክብደቱን የሚያውቁት ያውቁታል፡፡ አነስ ኢብኑ ማሊክ - ረዲየላሁ ዐንሁ - እንዲህ ይላሉ፡- “የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - የገቡ እለት መዲና ሁለ ነገሯ ነበር ያበራው፡፡ የሞቱ እለት ደግሞ ሁለ ነገሯ ነበር የጨለመው፡፡” በዳሪሚ ዘገባ ደግሞ እንዲህ ብለዋል፡- “የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - ወደኛ እንደመጡበት ቀን ያለ ያማረና የፈካ ቀን አላየሁም፡፡ የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - እንደሞቱበት ቀን ያለ አስቀያሚና የጨለመ ቀን አላየሁም፡፡” [ሚሽካቱል መሷቢሕ፣ አልባኒ፡ 5962] ሲመጡ ደስታ! ሐሴት! ብርሃን!! ሲሞቱ ሃዘን! ስብራት፣ ፅልመት! “አስቀያሚና የጨለመ ቀን” ሲሉ ቀኑን ማውገዛቸው አይደለም፡፡ የደረሰባቸውን የሃዘን ክምር፣ በክስተቱ የተነሳ የነበረውን የእለቱን ድባብ ነው እየገለፁ ያሉት፡፡ አዎ አማኝ ለሆነ ሰው የሳቸው ህልፈት የሙሲባ ሁሉ ጥግ ነው፡፡ ለዚያም ነው “አንዳችሁን መከራ ከደረሰበት በኔ (ህልፈት የደረሰበትን) መከራ ያስታውስ፡፡ ምክንያቱም ከመከራዎች ሁሉ ከባዱ ይህ ነውና” ማለታቸው፡፡ አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል፡፡ [አሶሒሐህ፡ 1106] እናልህ ወዳጄ! የደረሰብንም የሚደርስብንም ሁሉ ከሳቸው ሞት በላይ አይደለም፡፡ ዱንያ ላይ ስንት ውዶቻችንን፣ ስንት ወዳጆቻችንን አጥተን በሃዘን ተሰብረናል፡፡ ግና ሞት ለታላቁ ነቢይም - ﷺ - አልቀረም፡፡ ሙሲባቸው ሙሲባችን ነው፤ ህልፈታቸውም ህመማችን፡፡ ለኛ ሲሉ ከደናቁራን ጋር ተጋፍጠው አበሳቸውን አይተዋል፡፡ የታፈሩት የተከበሩት፣ ለሰማይ ለምድር የከበዱት ነቢይ! ክብራቸው ተደፍሯል፡፡ አካላቸው ዝሏል፡፡ በተደጋጋሚ ቅስማቸው ተሰብሯል፡፡ የገማ እንግዴ ልጅ ተጥሎባቸዋል፡፡ ለኛ ሲሉ ተደብድበዋል፣ ተንገላተዋል፣ እትብታቸው የተቀበረባትን ሃገር - ያውም መካን - ጥለው ተሰደዋል፡፡ ለኛ ሲሉ በረሃብ አለንጋ ተገርፈዋል፣ ሆዳቸው ላይ ድንጋይ አስረዋል፡፡ የኛ ነቢይ ለኛ ሲሉ ያልደረሰባቸው የለም፡፡ አኺራዊ መፃኢያችን ቢያስጨንቋቸው አልቅሰዋል፣ አንብተዋል፡፡ በአንድ ወቅት እንዲህ የሚለውን የነቢዩ ዒሳን ንግግር አነበቡ፡- ﴿ إِنْ تُعَذِّبْهُمْ فَإِنَّهُمْ عِبَادُكَ وَإِنْ تَغْفِرْ لَهُمْ فَإِنَّكَ أَنْتَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ( “ብትቀጣቸው እነርሱ ባሮችህ ናቸው፡፡ ለነርሱ ብትምርም አንተ አሸናፊው ጥበበኛው ነህ፡፡” [አልማኢዳህ፡ 118] ርህሩሁ ነቢያችን - ﷺ - እጆቻቸውን አንስተው “አላህ ሆይ! ህዝቦቼ ህዝቦቼ!” ብለው አለቀሱ፡፡ [ሙስሊም፡ 346] ውዱ ነቢያችን ከጎናቸው ከተሰለፉ ሶሐቢዮች አልፈው ከዘመናት በኋላ የሚመጡ ተከታዮቻቸውን ይናፍቃሉ፡፡ በአንድ ወቅት “ምነው ወንድሞቼን ባገኘው ብየ ተመኘው” አሉ፡፡ “እኛ ወንድሞችህ አይደለን?” ብለው ሶሐቦች ሲጠይቁ፡ “እናንተ ባልደረቦቼ ናችሁ፡፡ ወንድሞቼ ሳያዩኝ በኔ ያመኑት ናቸው” አሉ፡፡ [አሶሒሐህ፣ አልባኒ፡ 2888] እኛስ እሳቸውን እንናፍቃለን? እኛስ እሳቸውን ለማየት እንጓጓለን? እኚህን አዛኛችንን፣ ተቆርቋሪያችንን፣ ናፋቂያችንን ነው ያጣነው፡፡ በሳቸው ህልፈት የነፍስ ህይወት የሆነው ወሕይ ተቋርጧል፡፡ ይሄ ለአማኞች ቀላል ሙሲባ አልነበረም፡፡ በአንድ ወቅት ከነቢዩ - ﷺ - ህልፈት በኋላ “እስኪ ተነስ! የአላህ መልእክተኛ - ﷺ - ኡሙ አይመንን ሲዘይሯት እንደነበረው እኛም ሄደን እንዘይራት” በማለት አቡበክር አሲዲቅ ዑመርን ጠየቋቸው - ሁሉንም አላህ ይውደድላቸውና፡፡ ተነስተው ሄዱ፡፡ ሲደርሱ ኡሙ አይመን አለቀሰች፡፡ “ምንድነው የሚያስለቅስሽ? ለአላህ መልእክተኛ - ﷺ - አላህ ዘንድ ያለው የሚበልጥ አይደለም ወይ?” አሏት፡፡ “ለአላህ መልእክተኛ - ﷺ - አላህ ዘንድ ያለው በላጭ እንደሆነ ስላላወቅኩ አይደለም የማለቅሰው፡፡ የማለቅሰው ወሕይ ከሰማይ በመቋረጡ ነው” ብላ ለቅሶዋን ቀጠለች፡፡ ለቅሶዋ አስለቀሳቸው፡፡ ተያይዘው ተላቀሱ፡፡ [ሙስሊም፡ ሐዲሥ ቁጥር 2454] ዓለም እኚህን ታላቅ ሰው ካጣች በሂጅሪያው አቆጣጠር ሲሰላ 1431 ዓመት ሆናት፡፡ የአላህ ሶላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈን፡፡ (ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 17/2013) የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ያፈቀራችሁትን ለመርሳት ለተጎዳችሁ....ይህችን ዱዓ ብላችሁ ብትተኙስ? ❝ያ አላህ! ልቦችን እንደሻህ የምትገለባብጥ ጌታዬ ሆይ… እኔ ደካማ ባሪያህ ነኝ፤ አቅሜ ተሟጧል፣ ልቤም ሰላሙን ባጣ ፍቅር ደክሟል። ጌታዬ ሆይ! ልቤ ያለው በእጅህ ነውና፤ ከአንተ ያራቀኝን፣ ለዲኔም ሆነ ለዱንያዬ የማይበጀኝን ሰው ከልቤ ውስጥ ፈጽመህ አውጣልኝ። የተሳሰረውን የልቤን ቋጠሮ ፈትተህ፣ መርሳትንና መረጋጋትን በራሕመትህ ለግሰኝ። በልቤ ውስጥ የነበረውን ህመም በፍቅርህና በሰላምህ ተካልኝ፤ ባዘዝክልኝም ነገር ረክቼ እንድኖር አድርገኝ።❞ —ልባችሁን ለጌታችሁ ሰጥታችሁ ተኙ፤ እርሱ ፈጽሞ አያሳፍራችሁም።— ➔ t.me/Sle_qelbachn1