uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Kanalga Telegram’da o‘tish

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
913
Obunachilar
-324 soatlar
-177 kun
+5330 kun
Postlar arxiv
ኢላሂ...! በዱንያ ጩኸትና ውክቢያ ውስጥ የጠፉትን ቀልቦቻችንን ወደ አንተ መልሳቸው። የውስጣችንን ስብራት በሰፊው እዝነትህ ጠግንልን፤ በትከሻችን ላይ የከበዱንን የህይወት ሸክሞች በሙሉ አንተ አቅልልን። አላህ ሆይ! ያንተን ውዴታ የምናገኝበትን በርን ክፈትልን፤ ሁሌም ላንተ ታዛዥና ምስጋና አቅራቢዎች አድርገን። ጌታችን ሆይ... ከአንተ መራቅንና ከልብ መድረቅ ጠብቀን። በህይወታችን ውስጥ የምንወስናቸውን ውሳኔዎች ሁሉ ኸይራቱን ምረጥልን፤ እግሮቻችንን በዲንህ ላይ አፅናቸው።መጨረሻችንን አሳምረህ በጀነትህ ጥላ ስር ሰብስበን።አሚን።

ኢላሂ...! በዱንያ ጩኸትና ውክቢያ ውስጥ የጠፉትን ቀልቦቻችንን ወደ አንተ መልሳቸው። የውስጣችንን ስብራት በሰፊው እዝነትህ ጠግንልን፤ በትከሻችን ላይ የከበዱንን የህይወት ሸክሞች በሙሉ አንተ አቅልልን። አላህ ሆይ! ያንተን ውዴታ የምናገኝበትን በርን ክፈትልን፤ ሁሌም ላንተ ታዛዥና ምስጋና አቅራቢዎች አድርገን። ጌታችን ሆይ... ከአንተ መራቅንና ከልብ መድረቅ ጠብቀን። በህይወታችን ውስጥ የምንወስናቸውን ውሳኔዎች ሁሉ ኸይራቱን ምረጥልን፤ እግሮቻችንን በዲንህ ላይ አፅናቸው። መጨረሻችንን አሳምረህ በጀነትህ ጥላ ስር ሰብስበን።አሚን።

"እኛን ቢያጡ ምንም ለማይመስላቸው ሰዎች እኮ ነው እኛ የምንጨነቀው።"

ጥያቄ ?   📮📮   ትክክለኛውን  መልስ ያገኝ ሰው  add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ እውነት/ ሀሰት በማለት መልሱ ። ለመጀመሪያ ግዜ ሳሙና ያዘጋጀው ነብይ ነብዩሏህ ሱለይማን ናቸው።

ጁሙዓ፣ ጁምዓ፣ ጁመዓ በሶስቱም መልኩ መጥራት ይቻላል። ጁሙዓ የሚለው ግን በስፋት የሚታወቀው መጠሪያ ነው። የመሰባሰቢያ ዕለት ማለት ነው ትርጉሙም። በዘመነ ጃሂሊያ ዑሩባህ ነበር የሚባለው።

በሰለፊያ ስም ጭፍን ተከታይነት እየተስፋፋ ነው። ይህን እኩይ ዓመል ሁሌም ልንቃወምና ከእርሱም እራሳችንንም ልናርቅ ይገባል። አንዳንድ ወንድሞች -አላህ ያስተካክላቸውና- ለሸይኻቸው ያላቸው ምልከታና መረን ያለፈ ወገንተኝነት ልክ ሺዓዎች ለዓሊይ እንደሚያሳዩት አጉል ወግንና እየመሰለ ሂዷል። በአንፃሩ ሸይኻቸውን ለሚቃረን አካል ያላቸው ጥላቻና ወሰን መተላለፍ ልክ ሺዓዎች በአቡ በክርና በዑመር -ረዲየላሁ ዓንሁማ- ላይ እንደሚያሳዩት ደረቅ ጥላቻና ድንበር ማለፍ እየሆነ እያየን ነው። እና ውድ ሰለፊዮች ለሰዎች ያለንን ምልከታ እናስተካክል። ሰዎችን የሐቅ መመዘኛ አናድርግ። ሰዎች በሐቅ ይታወቃሉ እንጅ ሐቅ በሰዎች አይታወቅም። = የቴሌግራም ቻናል t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy

Repost from Abu Hayder Aliy
سَرَقَ لِصٌّ بَابَ هَذَا الضَّرِيحِ، فَطَارَدَهُ أَهْلُ الْقَرْيَةِ، فَأَمْسَكُوا بِهِ وَقَالُوا لَهُ: لِمَاذَا سَرَقْتَ بَابَ قَبْرِ الشَّيْخِ؟ فَقَالَ: هُوَ أَعْطَانِي الْبَابَ. قَالُوا: كَيْفَ يُعْطِيكَ بَابَهُ وَهُوَ مَيِّتٌ؟! فَقَالَ: فَكَيْفَ تَأْتُونَهُ لِيُعْطِيَكُمْ الرِّزْقَ وَالْوَلَدَ وَهُوَ مَيِّتٌ، فَهَبُّوا جَمِيعًا. አንድ ሌባ የዚህን የመቃብር ዶሪህ በር ሰረቀ። የመንደሩም ሰዎች እያሳደዱትና ያዙት፦ “የሸይኹን መቃብር በር ለምን ሰረቅክ?” ብለው ጠየቁት። እሱም፦ ኧረ እኔ አልሰረኩም“እርሱ ነው በሩን የሰጠኝ” አለ። እነርሱም፦ እንዴ“እርሱ የሞተ ሰው ሆኖ እንዴት በሩን ይሰጥሃል?” አሉት። እሱም፦ “እንግዲያ እናንተ የሞተ ሰው ሆኖ ሳለ ሲሳይና ልጅ እንዲሰጣችሁ ለምን ትመጡበታላችሁ?” አለ። ከዚያም ሁሉም ተገረሙ/ደነገጡ። ከዚህ የምንማረው — ተውሒድ ነው ይህ ታሪክ የሚያስታውሰን ትልቁን ጉዳይ አምልኮን ለአላህ ብቻ ማድረግ ነው። ሲሳይን፣ ልጅን፣ ፈውስን፣ እርዳታንና ሌሎችንም ነገሮች ከሞተ ሰው ወይም ከመቃብር መጠየቅ ከተውሒድ ጋር የሚጋጭ መሆኑን ነው። ጌታችን አላህም እንድህ ሲል ያዘናል ﴿وَلَا تَدْعُ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَنفَعُكَ وَلَا يَضُرُّكَ﴾ “ከአላህ ሌላ የማይጠቅምህንና የማይጎዳህን አትጣራ።” [ዩኑስ 10፥106] ነቢዩ ﷺ ኢብኑ ዐባስን رضي الله عنهما እንዲህ አሉት፦ «إِذَا سَأَلْتَ فَاسْأَلِ اللَّهَ، وَإِذَا اسْتَعَنْتَ فَاسْتَعِنْ بِاللَّهِ» “ስትጠይቅ አላህን ጠይቅ፤ እርዳታ ስትሻ ከአላህ ብቻ እርዳታን ፈልግ ።” (ቲርሚዚይ 2516) ስለዚህ ተውሒድ ማለት አላህን ብቻ ጌታ እንደሆነ መቀበል ብቻ ሳይሆን፣ የአምልኮ ዓይነቶችንም ሁሉ ለአላህ ብቻ ማድረግ ነው። ዱዓ፣ መለመን፣ ተስፋ፣ ፍርሃት፣ መተማመንና ሌሎችንም የአምልኮ ተግባራት ለአላህ ብቻ መሆን አለባቸው። ሕያው የሆነን ሰው በሚችለው ነገር እርዳታ መጠየቅ ከዚህ የተለየ ነው፤ ለምሳሌ “ውሃ ስጠኝ” ማለትህ ችግር የለውም። ነገር ግን ከሞተ ሰው የማይችለውን ነገር መጠየቅ የተውሒድ ጉዳይ ነው። አላህ ሆይ! በተውሒድ ላይ አጽናን፣ ከሽርክ በግልጽም ሆነ በስውር ጠብቀን፣ በተውሒድ ላይ ሕይወታችንን እንድንጨርስ አድርገን። 🤲🤲አሚን። https://t.me/abu_hayder_aliy https://t.me/abu_hayder_aliy

أخي السلفي… إذا أردت الزواج من أختٍ سلفية، فافهم هذه الحقيقة جيدًا لا تدخل الزواج وأنت تتخيل أنك ستتزوج امرأةً معصومة من الخطأ، لا تغضب، ولا تحزن، ولا تتأثر، ولا تختلف، ولا يكون لها شيء من طباع النساء. ❗️السلفية ليست عصمة من الخطأ، وليست ملائكية في الطباع. فالمرأة السلفية امرأة قبل كل شيء؛ لها مشاعر، وعواطف، وغيرة، وقد تغضب، وقد تحزن، وقد تخطئ، وقد تصيب، وقد تحتاج إلى من يصبر عليها ويفهمها ويعلمها بالحكمة. لكن الفرق أن المرأة الصالحة التي تربت على الكتاب والسنة، وتحب اتباع الحق، إذا أخطأت تُذكَّر بالحق فتقبله، ويُبيَّن لها الخطأ فتراجعه، وتُوجَّه بالحكمة بدل العناد والمكابرة. 🌸 فلا تنتظر منها أن تكون بلا أخطاء، بل انتظر منها أن تكون محبة للحق، حريصة على الطاعة، خائفة من الله، مستعدة للرجوع إلى الصواب. وكذلك أقول للأخت السلفية: لا تتزوجي الرجل السلفي وأنت تظنين أنه لن يخطئ أبدًا، أو أنه سيكون كامل الأخلاق في كل لحظة. هو كذلك بشر يخطئ ويصيب، ولكن المطلوب أن يكون منهجه صحيحًا، وأن يخاف الله، وأن يحفظ الحقوق، وأن يقبل النصيحة، وأن يرجع إلى الحق إذا تبين له. ⚠️ المشكلة ليست في وجود النقص، وإنما المشكلة في الإصرار على الباطل وسوء الخلق ورفض النصيحة. والزواج ليس بين شخصين كاملين، وإنما بين شخصين يسعيان معًا إلى الكمال بطاعة الله. فيا أخي السلفي: لا تبحث عن امرأة لا تغضب أبدًا، ولا تغار أبدًا، ولا تخطئ أبدًا؛ فهذا من خيال الناس، وليس من طبيعة البشر. بل ابحث عن امرأة صالحة، عفيفة، صاحبة عقيدة صحيحة، تحب السنة، تحرص على الصلاة والطاعة، تحفظ لزوجها حقه، وتحترم أهلها وأهله، وإذا أخطأت قبلت النصيحة ورجعت إلى الحق. 🌿 والمنهج السلفي الحقيقي لا يجعل الإنسان معصومًا، وإنما يعلمه كيف يتعامل مع الخطأ، وكيف يرجع إلى الكتاب والسنة، وكيف يتقي الله في نفسه وفيمن حوله. وتذكر: لا تتزوج لتبحث عن إنسان بلا عيوب، بل تزوج من إنسان إذا ظهرت عيوبه كان عنده من الدين والعقل والأخلاق ما يعينه على إصلاحها. فالمرأة تبقى امرأة، والرجل يبقى رجلًا، وكلاهما بشر. ولكن أجمل ما في الزواج أن يجتمع اثنان، كل واحد منهما يعلم نقص نفسه، ويعرف فضل الآخر، ويتعاونان على طاعة الله، ويصبران على بعضهما، ويغفران الزلات، وينصح أحدهما الآخر بالمعروف.

‏"إنَّ اللياليَ والأيامَ حامِلَةٌ ولَيسَ يَعلَمُ غَير الله ما تَلِدُ" ለሊት እና ቀናት ነፍሰ-ጡሮች ናቸው ፣ ምን እንደሚወልዱ አላህ እንጂ ማንም አያውቅም !! t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman

​✨ ታላቅ የምስራች ለወራቤ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ በሙሉ! ✨ ​السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 👉​እነሆ የ2019 ዓ.ል የቂርዓት ፕሮግራማችንን ማስጀመርያን እና ለእናንተ ለውድ
​✨ ታላቅ የምስራች ለወራቤ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ በሙሉ! ✨ ​السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 👉​እነሆ የ2019 ዓ.ል የቂርዓት ፕሮግራማችንን ማስጀመርያን እና ለእናንተ ለውድ ወንድምና እህቶቻችን የተዘጋጀውን ልዩ Welcome Program ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው 👉​በፕሮግራማችን ላይ በተወዳጁ ኡስታዛችን ኡስታዝ ኻሊድ ሙሀመድ (አቡ ሱለይማን) የተዘጋጀ ልዩና መንፈስን የሚያድስ የዳዕዋ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል. ​ከጥዑም አንደበታቸው የሚወጡ ጠቃሚ ተግሳፆችንና ምክሮችን በመቅሰም የመንፈስ ምግብ እንድንሸምት ሁላችሁም ተጋብዛችኋል. 🕌​ቦታ፦ ሰልማኑል ፋሪስ የተማሪዎች መስጂድ 🕧​ቀን እና ሰዓት፦ ዛሬ ጁመአ ከ መግሪብ ሰላት ቡሃላ ⭐​እጅግ የተወደዳችሁ ወንድሞችና እህቶች እንዳያመልጥዎ. ​ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የኸይር ስራው ተካፋይ ይሁኑ. ⭐الدآل عل الخير كفاعله.⭐

🕋 ረሱል ﷺ በኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ አላህ በርሱ ላይ __ሰለዋትን ያወርድበታል። ғᴏʀ ᴡᴀᴠᴇ ➙ @Suna_waver

እስቲ ወደ ኋላ መለስ በል! የሆነ ቀን ላይ በጣም ተጎድተህ ነበረ። አለሁ ባይን ያጣህ የብቸኝነት ጊዜን ከችግርህ ጋር ያሳለፍክበት ቀን ነበር። አሁን ደግሞ ወደዛሬው ኑሮህ ተመልከት። ያኔ ጨለማ መሳይ ቀናቶች አልፈው ሂወት መልኳን ቀይራ ከነበርክበት ከፍ ብለሀል ፣ብዙ ሰዎችም በዙርያህ አሉ። ስለዚህ ትላንትም ዛሬም ነገም አብሮህ ያለው #አላህ ብቻ ነው።እሱን አጥብቀህ ያዝ መጥፎ ቦታ አትወድቅም።ነገር ግን የሰው ልጅ ሁሌም አብሮህ አይሆንም። እና በደንብ ተጠንቀቀው። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/Abulabas1444 https://t.me/Abulabas1444.

ለፈገግታ ግን ምን ያስቃችኋል አንዱ ጫማዋ ጠፍቶባች እኮ ነው የምታለቅሰው አደናጋሪ ጊዜ https://t.me/abu_hassan_aliy_yusuf

♦️በልብ ውስጥ የሚቀመጥ መርዝ‼️ ደስት ስሜት ሳይሆን ውስጣዊ ሰላም ነው። ደስታ ማለት  የውስጥ ሰላም ሲሆን ጠላቶቹ ደግሞ ቂም እና ጥላቻ ናቸው። ቂመኛ አትሁኑ፣ በማንም ላይ ጥላቻ አይኑርባችሁ። ቂም በሰው ልብ ውስጥ ተቀምጦ የሰውን ህይወት የሚያበላሽ እና የሚበላ #ትል ነው። የሰውን ህይወት የሚጎዳው ደስታ አልባ የሚያደርገን አንዱና ዋናው #ቂም ነው። ..#ቂመኛ ሰው ሰላም የለውም፣ ..#ቂመኛ ሰው የህሊና እረፍት የለውም፣ ..#ቂመኛ ሰው እውነተኛ ደስታም የለውም፣ #ቂመኛ ሰው ትክክለኛ ስኬትም የለውም፣ #ቂመኛ ሰው የአሏህ ፍቅር የራቀው ነው። ትል የቆሰለ እና የተጎዳ አካል እንደሚበላ ሁሉ ቂምም የሰውን ህሊና የሚበላ እና የሚጎዳ በሰው ልጅ አእምሮ ውስጥ የተቀበረ #አውሬ ነው። .......ቂም ውስጥን እየቦረቦረ፣ ......እንቅልፍ የሚያሳጣ፣ .....ደስታን የሚቀማ፣ በስራችን ስኬት እና ውጤት አልባ የሚያደርግ፣ከመሰሎቻችን ጋር በሰላም እንዳንንኖር በማድረግ ከሰውነት ተራ የሚያወጣ በሽታ ነው። #ቂመኛ ሰው ቂም የያዘበትን ሰው ባየው እና ባስታወሰው ቁጥር አዕምሮው እንዲደማ የሚያደርግ #አሲድ በውስጡ ማስቀመጥ ማለት ነው። የሰላም ህይወት መኖር ከፈለክ በሰው ላይ ቂም አትያዝ፣ጥላቻ አይኑርብህ። ድንገት ካለብህም ያልተጣለ ቆሻሻ እየሸተተ እንደሚመጣ ሁሉ ያልተሻረ ቂምም እየመረዘህ ይመጣልና ቶሎ በይቅርታ አስወግደህ የውስጥ ሰላምህን አግኝ። ......ሰላማዊ ሰው ማለት ሰውን ያልበደለ እና በሰው ላይ ቂም የለለበት ሰው ነው። ቂም በልብ ውስጥ የሚቀመጥ መርዝ ነው። ♦️#ወገኖቸ_ሆይ‼️ ወላሒ በልባችሁ ቂም አይኑርባችሁ። ጠልታችሁ  እና ቂም ይዛችሁ  እንዳትሞቱ ተጠንቀቁ ለማለት እወዳለሁ።   t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

Repost from Abu Hayder Aliy
🌿حقوق المسلم على المسلم🌿 قال النبي ﷺ: «حَقُّ الْمُسْلِمِ عَلَى الْمُسْلِمِ سِتٌّ» قِيلَ: مَا هُنَّ يَا رَسُولَ اللَّهِ؟ قَالَ: «إِذَا لَقِيتَهُ فَسَلِّمْ عَلَيْهِ، وَإِذَا دَعَاكَ فَأَجِبْهُ، وَإِذَا اسْتَنْصَحَكَ فَانْصَحْ لَهُ، وَإِذَا عَطَسَ فَحَمِدَ اللَّهَ فَسَمِّتْهُ، وَإِذَا مَرِضَ فَعُدْهُ، وَإِذَا مَاتَ فَاتْبَعْهُ» رواه مسلم 1⃣. ردُّ السلام وإفشاؤه قال الله تعالى: ﴿وَإِذَا حُيِّيتُمْ بِتَحِيَّةٍ فَحَيُّوا بِأَحْسَنَ مِنْهَا أَوْ رُدُّوهَا﴾ [النساء: 86]. አንድ ሙስሊም ወንድሙን ሲያገኘው ሰላምታ መስጠት እና ሰላምታውን በተሻለ ወይም በተመሳሳይ መመለስ ከሙስሊም መብቶች ነው። 2⃣. دعوتُه إذا دعاك ሙስሊም ወንድምህ ወደ ሚፈቀድ ጉዳይ ከጋበዘህ በተቻለህ መጠን ግብዣውን መቀበል ይገባል። 3⃣. النصيحة قال النبي ﷺ: «وَإِذَا اسْتَنْصَحَكَ فَانْصَحْ لَهُ» የሙስሊም ወንድምህ ምክር ከጠየቀህ፣ በቅንነት መምከር አለብህ። ለእርሱ መልካም የሆነውን እንጂ የሚጎዳውን አትመክረው። 4⃣. تشميتُ العاطس إذا عطس المسلم وقال: الحمد لله، تقول له: يرحمك الله فإذا قال: يهديكم الله ويصلح بالكم فقد ورد ذلك في الحديث. አንድ ሙስሊም ካስነጠሰ በኋላ «الحمد لله» ካለ፣ «يرحمك الله» ማለት ከመብቶቹ ነው። 5⃣. عيادة المريض قال النبي ﷺ: «وَإِذَا مَرِضَ فَعُدْهُ» ሙስሊም ወንድምህ ሲታመም ሊጠይቀው መሄድ ከመብቶቹ ነው። ይህም ለታመመው ሰው መጽናናትና መደገፍ ነው። 6⃣. اتباعُ جنازته قال النبي ﷺ: «وَإِذَا مَاتَ فَاتْبَعْهُ» ሙስሊም ወንድምህ ከሞተ የጀናዛውን ሥርዓት መከተልና ቀብሩ ላይ መገኘት ከመብቶቹ ነው። ومن أعظم حقوق المسلم أيضًا قال الله تعالى: ﴿إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ فَأَصْلِحُوا بَيْنَ أَخَوَيْكُمْ﴾ [الحجرات: 10]. «ምእመናን በእርግጥ ወንድማማቾች ናቸው፤ ስለዚህ በሁለቱ ወንድሞቻችሁ መካከል እርቅ አድርጉ።» እንዲሁም ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «الْمُسْلِمُ أَخُو الْمُسْلِمِ، لَا يَظْلِمُهُ، وَلَا يَخْذُلُهُ، وَلَا يَحْقِرُهُ» رواه مسلم. «ሙስሊም የሙስሊም ወንድም ነው፤ አይበድለውም፣ አይጥለውም፣ አያዋርደውም።» ስለዚህ ከሙስሊም ወንድማችን መብቶች መካከል ሰላምታ፣ ምክር፣ በችግር መርዳት፣ በሕመም መጠየቅ፣ ክብሩን መጠበቅ፣ አለመበደል፣ አለመናቅ እና በመልካም ነገር መተባበር ይገኙበታል። https://t.me/abu_hayder_aliy https://t.me/abu_hayder_aliy

أصبحنا على فطرة الإسلام، وعلى كلمة الإخلاص، وعلى دين نبينا محمد ﷺ، وعلى ملة أبينا إبراهيم حنيفًا مسلمًا وما كان من المشركين..! صـلـوا على الحـبـيـب المصـطـفى ﷺ...!!

🤩የሆነ ጊዜ ሚዳቆን ለምን ሁሌ እንደሚበልጠዉ ዉሻ ጠየቀ ይባላል.. ሚዳቆዉም :-እኔ የምሮጠዉ ሁሌ ለነፍሴ ነዉ ሩሄን ለማትረፍ ነዉ ..አንተ ደሞ ለአለቃህ ነዉ የምትሮጠዉ... ለእዉነት ሚዳቆ መሆን ባትችል ለስህተት ዉሻ አትሁን!                      ተቀላቀሉ💗 💗💗💗💗💗💗 https://t.me/abu_hassan_aliy_yusuf