uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Kanalga Telegram’da o‘tish

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
902
Obunachilar
-424 soatlar
-167 kun
+4030 kun
Postlar arxiv
በነገራችን ላይ ዐረብኛ ቋንቋ የዐረቦች ብቻ አይደለም፣ የመላው ዓለም ሙስሊሞችም ጭምር እንጂ። 0ረብኛ የቁርኣን፣ የሐዲሥ፣ የፊቅህ የኢስላም ቋንቋ ነው። ዐረብኛ የሶላት፣ የዚክር ቋንቋ ነው። ስለዚህ
በነገራችን ላይ ዐረብኛ ቋንቋ የዐረቦች ብቻ አይደለም፣ የመላው ዓለም ሙስሊሞችም ጭምር እንጂ። 0ረብኛ የቁርኣን፣ የሐዲሥ፣ የፊቅህ የኢስላም ቋንቋ ነው። ዐረብኛ የሶላት፣ የዚክር ቋንቋ ነው። ስለዚህ ኢስላም ማንነታችን እስከሆነ ድረስ ዐረብኛ ቋንቋ የማንነታችን አካል ነው። ስለሆነም የማንችለው ለመቻል፣ የምንችለው ለማሻሻል ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል። በአራቱም የቋንቋ ክህሎቶች (መናገር፤ ማዳመጥ፣ መፃፍ እና ማንበብ) ላይ አቅማችንን ለማዳበር ብንጥር እንጠቀማለን። አላህ አግርቶለት ቋንቋውን የቻለ ደግሞ በሂደት እንዳይረሳው የሚችሉ ሰዎች ጋር ሲገናኝ ቢጠቀምበት መልካም ነው። ዛሬ ደግሞ ዐረብኛ ለሚሊዮኖች የእንጀራ ሰበብም ሆኗል። ስለዚህ ከራሳችን አልፎ ልጆቻችንም እንዲማሩት ትኩረት ብንሰጥ መልካም ነው። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ሙስሊም ወንድሞቼ ፣ ጊዜው ሳያልፍ እንንቃ! ያ አላህ! ጉዳዩ እየከበደና እያሳሰበ መጥቷል። ሀገራችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ለተለያዩ ፊርቆችና አስተሳሰቦች እየተጋለጠች ነው። አንዳንድ ቡድኖችና እንቅስቃሴዎችም በሕዝቡ መካከል እየተስፋፉ ሲሆን፣ በተለይም ወጣቶችንና ሕፃናትን ማነጣጠራቸው እየጨመረ ነው። በቅርብ ጊዜም ከአህሉስ-ሱና ወልጀማዓ አስተምህሮ ፍፁም የሚለያዩ ቡድኖች፣ ከእነሱም መካከል ሺዓ፣ አሕመዲያ እና ሌሎችም በአንዳንድ አካባቢዎች እየተስፋፉ እንደሚገኙ እናስተውላለን። በተለይም በባቲና በአካባቢዋ የተለያዩ የትምህርትና የዳዕዋ እንቅስቃሴዎች እየተካሄዱ መሆናቸው ትኩረታችንን ይሻል። በተለይ ልንጠነቀቅ የሚገባን ሕፃናትና ወጣቶች ላይ የሚደረገው ትኩረት ነው። አንዳንድ ወገኖች ትምህርት ቤቶችን፣ ማዕከላትንና የትምህርት ተቋማትን በመክፈት ሕፃናትን ገና ከልጅነታቸው ከ kg ጀምሮ ለማስተማር እየሰሩ ነው። እንግዲህ ራሳችንን መጠየቅ ይገባናል፦ ልጆቻችን እና ወጣቶች ምን እየተማሩ ነው? ምን ዓይነት እምነትና አስተሳሰብ እየተቀበሉ ነው? ትምህርታቸውን የሚከታተልና አቅጣጫ የሚሰጣቸው ማን ነው? ወንድሞቼና የተከበራችሁ ወገኖቼ ሆይ! ከሀገራችን ጫፍ እስከ ሌላኛው ጫፍ ድረስ፣ የአህሉስ-ሱና ወልጀማዓ ተከታዮች ሆይ፣ የአካባቢያችን ሰዎች ሆይ፣ በተለይም የባቲ ነዋሪዎች ሆይ! የልጆቻችን የወጣቶችን የራሳችንንእምነት መጠበቅና የአላህን መጽሐፍ እና የነቢዩን ﷺ ሱና ማስተማር ታላቅ ኃላፊነት ነው። ይህንንም በዘፈቀደ ግጭት፣ በስድብ ወይም ሌሎችን በማዋረድ ሳይሆን፣ በዕውቀት፣ በጥበብ፣ በትክክለኛ ትምህርት፣ በግንዛቤ ማስጨበጥ እና ማህበረሰባችንን በቁርአን፣ በሱናና በትክክለኛ የእስልምና እምነት ማጠናከር ነው። ማህበረሰባችንን በቅርብ ልንከታተል፣ ምን እንደሚማሩም ልናውቅ ይገባል። በራሳችን ትምህርት ቤቶችና የእስልምና ማዕከላት ውስጥም ጠንካራና ጠቃሚ ትምህርት እንዲያገኙ ልንጥር ይገባል። ይህም ቁርአንን፣ ትክክለኛ የአቂዳ ትምህርትን፣ ፊቅህን፣ መልካም ሥነ-ምግባርንና የዓረብኛ ቋንቋን ያካተተ መሆን አለበት። ሌሎች ሰዎች ቦታውን እንዲይዙ ከፈቀድን በኋላ፣ ሐሳቦቻቸው ስለተስፋፉ ብቻ ማማረር መፍትሔ አይሆንም። ስለዚህ ኃላፊነታችንን እንወጣ። ማህበረሰባችን ከሌሎች ዘንድ ከመማራቸው በፊት እኛ እናስተምራቸው። የተሳሳቱ አስተሳሰቦችንም በዕውቀት፣ በማስረጃና በጥበብ እንመልስ። ኢንሻአላህ፣ እነዚህ ቡድኖች ምን እንደሆኑ፣ መሠረታዊ ሐሳቦቻቸውና እምነቶቻቸው ምን እንደሆኑም በማስረጃና በታማኝ ምንጮች ላይ በመመስረት አብራራለሁ፤ ዓላማዬም ሙስሊሙ ስለ ዲኑ በቂ ዕውቀት እንዲኖረውና በጉዳዮች ላይ በግልጽ እውቀት እንዲቆም ነው። አላህ ሆይ! ሀገራችንንና ማህበረሰባችንን ጠብቅ። እኛንና እነርሱን በቁርአንና በሱና ላይ አጽና። ዑለማዎቻችንን፣ ዳዒዎቻችንንና መምህራኖቻችንን ኃላፊነታቸውን በትክክል እንዲወጡ እርዳቸው። ከቀናው መንገድ የራቁትንም ወደ እውነት ምራቸው። አላህ ሆይ! የሙስሊሞችን ልጆች ጠብቅ፣ እምነታቸውን ጠብቅ፣ ወደ እውነትና መልካም ሥራ የሚጠሩ ዳዒዎች አድርጋቸው። አሚን! = አቡ አዩብ ሙሐመድ ሰዒድ ሙሐመድ https://telegram.me/abutoiba https://telegram.me/abutoiba

በሲህር ምክንያት ሰዎች ቀብር ገብተዋል፤ ጤናቸውን ተነፍገዋል፤ ሰላማቸውን አጥተዋል፤ ፍቅር እና ደስታ እርቋቸዋል፤ የገንዘብ ህይወታቸው ተዘበራርቋል፤ ትዳራቸው ተበትኗል... ​ ይህ ሁሉ እየሆነ ሳለ፣ አንድ ተጎጂ በሰው ዐይን ወይም በሲህር ምክንያት ችግር ገጠመኝ ሲል፣ "ቆንጆ ነኝ፣ ሀብታም ነኝ፣ ታዋቂ ነኝ" እያለ እንደሆነ አድርገን የምንተረጉመው ለምንድነው ?፤ ​አንዳንዶች ደግሞ የሰውየውን የእምነት እና የአስተሳሰብ ጥንካሬ ጥያቄ ውስጥ የሚከቱም አሉ። ነገር ግን ነብያችን ﷺ "የሰው ዐይን ሀቅ ነው" በማለት አስተምረውናል፤ የህይወት ተሞክሯችንም የሚያረጋግጠው ይህንኑ ነው። ካላወቅን መጠየቅ ደግ ነው፤ ችግሩን በሚያውቅ እና ገፈቱን እየቀመሰ ባለ አካል ላይ ለመሳለቅ መሞከር ግን አላዋቂነት ነው። ​በቁም በፈላ ዘይት ውስጥ እንዲነከሩ ከምመኛቸው ሰዎች መካከል ሳሂሮች እና አስደጋሚዎች ግንባር ቀደሞቹ ናቸው። አላህ ያዋርዳቸው !! t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman

ጥያቄ:- ጀመዓዎች በዙ  ሁሉም የሚሞግተው በሱና ላይ ነኝ ብሎ ነው። የሐቅ ጀማዓዎች የሚታወቁት እንደት ነው ? መልስ: 🎙ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ሒዛም (حفظه الله) 🔷👉https://t.me/abujemila25 🔷👉https://t.me/abujemila25

👉ለፊትና አይቸኩልም ይፈራል አደጋ፤ 👉ሱናን ይጠብቃል ነቅቶ ሳይዘነጋ፤ 👉ውዳሴም አይሻ የማንንም ታርጋ፤ 👉አፉን የለጎመው #የለተሞን መንጋ፤ 👉ያላግባብ ሲወራጭ ተሳክሮ ሲንጋጋ፤ 👉ድምፅ ባለ
👉ለፊትና አይቸኩልም ይፈራል አደጋ፤ 👉ሱናን ይጠብቃል ነቅቶ ሳይዘነጋ፤ 👉ውዳሴም አይሻ የማንንም ታርጋ፤ 👉አፉን የለጎመው #የለተሞን መንጋ፤ 👉ያላግባብ ሲወራጭ ተሳክሮ ሲንጋጋ፤ 👉ድምፅ ባለው ፅሁፍ ቅጥፈት የተዋጋ 👉#የሙነወር ልጅ ነው የባጢል አለንጋ፤

ቢደርስብህ ሀዘን ቢደርስብህ በደል «ተሸሽገህ አልቅስ ወንድ ልጁ ነህ አይደል?» ሚሉህን አትስማ ተረቱን አፍርሰው አልቅስ አልቅስ ካለህ... መሀል አደባባይ ዕንባህን አፍስሰው፤ ግድ የለም ተንሰቅሰቅ
ቢደርስብህ ሀዘን ቢደርስብህ በደል «ተሸሽገህ አልቅስ ወንድ ልጁ ነህ አይደል?» ሚሉህን አትስማ ተረቱን አፍርሰው አልቅስ አልቅስ ካለህ... መሀል አደባባይ ዕንባህን አፍስሰው፤ ግድ የለም ተንሰቅሰቅ... በልብህ እያነባህ ስቃይ አታስታምም ይህንን አስተውል፤ ውስጥ ሲፈስ ነው የሚገድለው ደም' ም።

በመጨረሻም ሙስጠፋ -አላህ ይምራውና- አሁን ሀገር አቋርጦ ተጉዞ እየተማርኩባቸው ነው የሚላቸው ሸይኽ ዓብዱል ዓዚዝ አርራጂሒይ ስለ ሸይኽ ረቢዕ ምን እንዳሉ አውስቸ ፅሁፌን አጠናቃለሁ። ▫️ሸይኽ ዓብዱል ዓዚዝ አርራጂሒይ:- ↩️ فقد سئل فضيلة الشيخ عبدالعزيز الراجحي –حفظه الله-: ما نصّه: بعض الناس يتهم من تمسك بالمنهج السلفي بأنّه جامي، ويحذر من الشيخ ربيع والشيخ النجمي والشيخ زيد بن محمد هادي المدخلي وغيرهم من أهل العلم؟ "ከፊል ሰዎች የሰለፊያን መንሃጅ አጥብቆ የያዘን አካል ጃሚይ ነው ይላሉ። ከሸይኽ ረቢዕ፣ ከሸይኽ አሕመድ አንነጅሚይ፣ ከሸይኽ ዘይድ አልመድኸሊይና ከሌሎችም የዒልም ባለቤቶች  ያስጠነቅቃሉ። ተብለው ተጠየቁ። فأجاب بقوله: ((الألقاب لا تغيّر، النبز بالألقاب لا يصلح، المهم ثقل الشخص، المشايخ نعرف أن معتقدهم سليم، ومن أهل السنة والجماعة، الشيخ ربيع والشيخ أحمد والشيخ زيد لا غبار عليهم)). ሸይኹም -ሓፊዘሁላህ- እንዲህ ሲሉ መለሱ:- "ስያሜ ለውጥ አያመጣም። በቅፅል ስም መሰየምም አይገባም። ዋናው የሰወየው ማንነት ነው። የተወሰቱ መሻኢኾች ዓቂዳቸው እንከን የሌለበት መሆኑን እናውቃለን። ከአህሉሱናዎችም ናቸው። ሸይኽ ረቢዕ ሸይኽ አሕመድ ሸይኽ ዘይድ ምንም አይነት አቧራ (እንከን)  የለባቸውም።" ↩️ وسئل –أيضاً-: ما رأيكم في كتب وأشرطة الشيخ ربيع بن هادي المدخلي –حفظه الله، هل تنصحون بقراءة كتبه واستماع أشرطته؟ በሌላም ጊዜ "ስለ ሸይኽ ረቢዕ ኪታቦች እና ካሴቶች ምን ይላሉ? ኪታቦችን በማንበብና ካሴቶችን በማዳመጥ ይመክሩናልን?" ተብለው ተጠየቁ። فقال: ((نعم، لا بأس بها، كتبه وأشرطته ما رأينا فيها ما ينتقد، ما انتقدت فيها شيئاً، أشرطته جيّدة، وكتبه جيدة ومفيدة)) [من شريط لدى تسجيلات منهاج السنّة بالرياض].   እርሳቸውም እንዲህ ሲሉ መለሱ "አዎ! ችግር የለባቸውም። ኪታቦቹም ካሴቶቹም ውስጥ የሚተቹ ነገሮችን አላየንም። ካሴቶቹ ምርጥ ናቸው። ኪታቦቹም ምርጥና ጠቃሚዎች ናቸው።" የሸይኹ ንግግር ይህን ይመስላል። የሌሎችም የሱንና ዑለማኦች በተመሳሳይ "ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ አልመድኸሊይ የሱንና ዓሊም ናቸው።" ይሉናል። መነሻና መድረሻ የሌላቸው የኸዋሪጅ ስራ አስፈፃሚ እና የተክፊር አቀንቃኝ የሆኑት እነ ሙስጠፋ ደግሞ "የሱንና ሰው አይደሉም። ሙርጂእ ናቸው።" ይላሉ። ማንን መስማትና መቀበል እንዳለብህ እራስህ ታቃለህ። ይህን ስል ሊሰመርበት የሚገባ ነጥብ እኛ ሸይኽ ረቢዕም ይሁኑ ማንም ዓሊም አያጠፋም አይሳሳትም ማለታችን አይደለም። ነገር ግን የሱንና ዓሊም የሱንና ዓሊም ነው። ስህተቱ እንደ ስህተት እውቀታዊ ምላሽ ሊሰጠው ይገባል እንጅ ማንም የመንደር ጎረምሳ እገሌ ሙርጅእ ነው እያለ ሊላገግ አንፈቅድለትም። እናም ማንሳት የፈለኩት ሸይኽ ረቢዕን ከሱንና ውጭ ናቸው የሚለው የነ ሙስጠፋ አቋም የሓዳዲያና የተክፊሮች ቅዠት እንጅ ሁሉም የሰለፊያ ዑለማኦች ሸይኽ ረቢዕ የሱንና ሰው መሆናቸውን ያረጋገጡት እወነታ መሆኑን ነው። የነ ሙስጠፋ ቁማር ግን እንዲህ ነው ከገባህና ከሰማሃኝ። የሆነን አቋም ሲዪዙ በሆኑ ዓሊሞች ለመጠለል ይሞክራሉ የፈለጉትን ይሰቅላሉ የፈለጉትን ያወርዳሉ። ትላንት የሕየል ሓጁሪን በጭፍን ተከትለው ሃገር ሲያምሱ እያለ ሲሉ የነበረው ይታወቃል። ዛሬ ደግሞ የሕያን ጠብ እርግፍ አድርገው ትተው ላመጡት የተክፊር ጉዞ በመዲና ዑለማኦች እራሳቸውን ይወሽቃሉ። የመዲና ዑለማኦች ያሉበትና የነእርሱ ጉዞ ግን ሰማይና ምድር ነው። እስኪ መልሱልን ሸይኽ ረቢዕን ኢብኑ ባዝ ናቸው ሙርጂእ ያሉት? ወይስ ሸይኽ ፈውዛን? ወይስ ራጂሒይ እስኪ ንገሩን። አላህ ሁላችንንም ለሚወደው መንገድ ይምራን። رحم الله الشيخ المجاهد ربيع السنة وأسكنه فسيح جناته، ሐምሌ 6/2017 በድጋሜ የተለጠፈ የቴሌግራም ቻናል = t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy

▫️. ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሷሊሕ ኢብኑ ዑሠይሚን -ረሒመሁላህ- ↩️ قد سئل الشيخ العلامة محمد بن صالح بن عثيمين –رحمه الله- عن الشيخ ربيع كما في (شريط الأسئلة السويدية) فقال :” أما بالنسبة للشيخ ربيع فأنا لا أعلم عنه إلا خيراً والرجل صاحب سنة وصاحب حديث”. ኢብኑ ዑሰይሚን ስለ ሸይኽ ረቢዕ ተጠይቀው እንዲህ ሲሉ መለሱ:- "ሸይኽ ረቢዕን በተመለከተ ከእርሳቸው ኸይርን እንጅ አላቅም። ሰውየው የሱንና እና የሓዲሦ ባለቤት ናቸው።" ↩️ وجاء في الشريط الأول الذي هو بعنوان (كشف اللثام عن مخالفات أحمد سلام ) -عبر الهاتف من هولندا-: سؤال: ما هي نصيحتكم لمن يمنع أشرطة الشيخ ربيع بن هادي بدعوى أنها تثير الفتنة وفيها مدح لولاة الأمور في المملكة وأن مدحه ـ أي مدح الشيخ ربيع للحكام ـ نفاق؟ الجواب : "رأيُنا أن هذا غلطٌ وخطأٌ عظيم، والشيخ ربيع من علماء السنة، ومن أهل الخير، وعقيدته سليمة، ومنهجه قويم. لكن لما كان يتكلم على بعض الرموز عند بعض الناس من المتأخرين وصموه بهذه العيوب." በሌላም ቦታ የሸይኽ ረቢዕን ካሴቶች ከማዳመጥ ስለሚከለክሉ ሰዎች ተጠይቀው እንዲህ ይላሉ:- "ይህ ታላቅ ስህተት ነው። ሸይኽ ረቢዕ ከሱና ዑለማኦች ውስጥ ናቸው። ከኸይር ባለቤቶችም። ዓቂዳቸውም እንከን የለሽ መንሃጃቸውም የተስተካከለ ነው። ..." ↩️ وسئل ما نصّه: يقال أن منهج الشيخ ربيع يخالف منهج أهل السنة والجماعة؟ فأجاب بقوله: "ما أعلم أنه مخالف، والشيخ ربيع أثنى عليه أهل العلم المعاصرين، أنا ما أعرف عنه إلا خيراً" [شريط ثناء أئمة الدعوة على الشيخ ربيع]. "የሸይኽ ረቢዕ መንሃጅ የአህለሱንና ወልጀማዓዎችን ይቃረናል ይባላል?" ተብለው ተጠየቁ። እርሳቸውም "እኔ መቃረናቸውን አላቅም። ሸይኽ ረቢዕ ማለት የዘመናችን ዑለማኦች አወድሰዋቸዋል። እኔ ከርሳቸው ኸይርን እንጅ አላቅም።" ▫️.ሸይኽ ፈውዛን -ሐፊዘሁላሁ ተዓላ- ↩️ قد أثني عليه الشيخ العلامة صالح بن فوزان الفوزان –حفظه الله- في تقديمه لكتاب “منهج الأنبياء في الدعوة إلى الله فيه الحكمة والعقل” و في تقديمه لكتاب “جماعة واحدة لا جماعات” في الرد على عبدالرحمن عبدالخالق، ሸይኽ ፈውዛን ለሸይኽ ረቢዕ ብዙ መፅሃፎች መግቢያ ሲፅፉ በርካታ ውዳሴዎችን ተችረዋቸዋል። አንዴ ደግሞ ተጠይቀው በዚህ መልኩ መልስ ሰጥተዋል። ↩️ وسئل فضيلته في شريط ” الأسئلة السويدية ” (5 ربيع الآخر 1417 هـ) فقال بعد ما ذكر الشيخ ربيعاً مع مجموعة من أهل العلم: "كذلك من العلماء البارزين الذين لهم قدم في الدعوة، فضيلة الشيخ عبدالمحسن العباد، فضيلة الشيخ ربيع هادي ...،" ▫️. ሸይኽ ሙቅቢል አል'ዋዲዒይ -ረሒመሁላህ-: ↩️ فقد سئل فضيلة الشيخ العلامة مقبل بن هادي الوادعي –رحمه الله-: في شريط ” الأسئلة الحضرمية”: ما رأيك فيمن يقول عن الشيخ ربيع أنه متهّور؟ فأجاب –رحمه الله- : "الشيخ ربيع له خبرة بمعرفة الواقع لأنه عاش مع الإخوان المفلسين زمناً طويلاً -والحمد لله- هو أحسن من يعالجون الأمور وينكر على المبتدعة ابتداعهم فأسال الله أن يحفظه. ሸይኽ ሙቅቢልም በዚህ መልኩ አወድሰዋቸዋል። የሸይኽ ረቢዕን ኪታቦችና ካሴቶች እንድንጠቀምባቸውም በዚህ መልኩ ይመክራሉ። ↩️ وقال الشيخ –رحمه الله- في جواب له على سؤال: "وأنا أنصح الأخوة بالاستفادة من كتب أخينا الشيخ ربيع بن هادي –حفظه الله تعالى- فهو إن شاء الله [بصير] بالحزبيين، ويخرج الحزبية بالمناقيش .... ،" ↩️ وقال في كتاب “تحفة القريب والمجيب” السؤال (75): "وأنصح بقراءة كتاب أخينا في الله ربيع بن هادي “جماعة واحدة لا جماعات وصراط واحد لا عشرات” فهو كاف واف". በሌላም ቦታ ሰዎች ከታላላቅ ዑለማኦች ጋር ግንኙት እንዲኖራቸውና ከቻሉም ወደእነርሱ በአካል እንዲጓዙ ሲመክሩ ሸይኽ ረቢዕን ለምሳሌ ያወሳሉ። ↩️ وقال في السؤال (123): "الذي ننصح به، أن يراسلوا أهل العلم، وان استطاعوا أن يرحلوا إليهم فعلوا، مثل الشيخ الألباني، والشيخ ابن باز، والشيخ عبدالمحسن العباد، والشيخ ربيع بن هادي، والشيخ ابن عثيمين، فإن استطاعوا أن يرحلوا إليهم فعلوا، وإن لم يستطيعوا أن يرحلوا إليهم فبواسطة الهاتف والمراسلات". በሌላም ጊዜ ወደ እነርሱ ሊመለሱባቸው ስለሚገቡ ዑለማኦች ተጠይቀው ሲመልሱ "ሸይኽ ረቢዕ የጥመት አንጃዎችን በማወቅ ረገድ ከአላህ ተዓምራቶች አንዱ ነው" ሲሉ ያወዱሷቸዋል። ↩️ وفي السؤال (135) لما سئل عن العلماء الذين يرجع إليهم قال: "والشيخ ربيع بن هادي المدخلي، فهو آية من آيات الله في معرفة الحزبيين، لكن لا كآيات إيران الدجالين" ↩️ وفي السؤال (140) سئل: مَن مِن علماء السعودية تنصحون بالأخذ عنهم وحبذا لو ذكرت لنا بعض الأسماء؟ فقال: "أمّا الذين أنصح بالأخذ عنهم والذين أعرفهم فهم الشيخ: عبدالعزيز بن باز حفظه الله، والشيخ محمد بن صالح بن عثيمين حفظه الله، والشيخ ربيع بن هادي حفظه الله،..." ሸይኽ ረቢዕ ታላቅ የሱንና ዓሊም ለመሆናቸው የተወሱት ታላላቅ አኢማዎች ውዳሴ ከበቂም በላይ ነው። እነዚህን ለምሳሌ አወሳሁ እንጅ ከነዚህም ውጭ እነ ሸይኸ አሕመድ አንነጅሚይ፣ ሸይኽ ዘይድ ኢብኑ ሙሐመድ አል'መድኸሊይ፣ ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ዓብዲላህ አስሰቢል፣ ሸይኽ ሷሊሕ አስሱሓይሚይ፣ ሸይኽ ዑበይድ አልጃቢሪይ፣ ሸይኽ ዓብዱል ዓዚዝ አርራጂሒ እና ሌሎችም በዓለም የሚገኙ ታላላቅ ዑለማኦች በጣም በተዋቡ ገለፃዎች ሸይኽ ረቢዕን አወድሰዋቸውል።

~ ሙስጠፋ ዓብደላህ እና ዑለማኦች    የሙስጠፋ ዓብደላህ ማንነት ዛሬም ያልገባቹህ ካላቹህ እዚህ ጋ ሸይኽ ረቢዕ ላይ ሐያእ በጎደለው አንደበቱ እንዴት እንደሚላገግ ተመልከቱ። የእርሱን የተክፊር አካሄድ አጥብቀው ስለኮነኑና የሓዳዲያዎችን ፀያፍ ገፅታ በሚገባ ስላብራሩ ብቻ አስፀያፊ በሆነው የኢርጃእ ቢድዓ ይወርፋቸዋል። ሙርጂኣዎች አህለሱናዎች አለመሆናቸው የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። ሙስጠፋ እከተላቸዋለሁ እያለ የሚሞግታቸው የመዲና ዑለማኦችም ይሁኑ በዓለም ያሉ የሱና ዑለማኦች ግን ሸይኽ ረቢዕ -ረሒመሁሏህ- ታላቅ የሱንና ዓሊም፣ የሰለፊያ ረዳት እና የቢድዓ ሰዎችን አንገት ያስደፉ ታላቅ ሙጃሂድ መሆናቸውን ባንድ ድምፅ ይመሰክራሉ። ሸይኽ ረቢዕን ያወደሱ ዑለማኦች እጅግ በጣም በርካታ ናቸው። ከእነርሱ ውስጥ የተወሰኑትን እናውሳ። ◾️ ለምሳሌ :- ▫️. ሸይኽ ኢብኑ ባዝ -ረሒመሁሏህ-: ↩️ قال الإمام العلامة سماحة الشيخ عبدالعزيز بن باز -رحمه الله تعالى- "الشيخ ربيع من خيرة أهل السنّة والجماعة، ومعروف أنّه من أهل السنّة، ومعروف كتاباته ومقالاته" [شريط بعنوان ثناء العلماء على الشيخ ربيع-تسجيلات منهاج السنة]. "ሸይኽ ረቢዕ ከምርጥ አህለሱንና ወልጀማዓዎች ናቸው። ከአህለሱንና መሆናቸው የታወቀ ነው። እንደዚሁም ኪታቦቹና ንግግሮቹም ታዋቂ ናቸው።" ↩️ وقد سئل ـ رحمه الله تعالى ـ عن الشيخ ربيع بن هادي والشيخ محمد أمان فقال: "بخصوص صاحبي الفضيلة الشيخ محمد أمان الجامي والشيخ ربيع بن هادي المدخلي، كلاهما من أهل السنة، ومعروفان لدي بالعلم والفضل والعقيدة الصالحة،" [شريط الأسئلة السويدية]. ስለ ሸይኽ ሙሐመድ አማን እና ስለ ሸይኽ ረቢዕ ተጠይቀው ሲመልሱ እንዲህ ይላሉ:- "ሁለቱም የተከበሩ የሱንና ሰዎች ናቸው። ሁለቱም እኔ ዘንድ በዒልም፣ የተከበሩ በመሆናቸውና በትክክለኛ ዓቂዳቸው የታወቁ ናቸው።" ↩️ وقال-رحمه الله-: "وإخواننا المشايخ المعروفون في المدينة ليس عندنا فيهم شك، هم أهل العقيدة الطيبة ومن أهل السنة والجماعة مثل الشيخ محمد أمان بن علي، ومثل الشيخ ربيع بن هادي ... ،" [شريط توضيح البيان]. "መዲና ውስጥ ያሉ የታወቁ መሻኢኾችና ወንድሞቻችን እነርሱን በተመለከተ እኛ ዘንድ ምንም አይነት ጥርጥር የለም። እነርሱ የምርጥ ዓቂዳ ባለቤቶች ናቸው። ከሱንና ሰዎችም ናቸው። ምሳሌ ሸይኽ ሙሐመድ አማን አልጃሚ፣ ሸይኽ ረቢዕ ኢብኑ ሃዲ፣..." ↩️ وقال الشيخ العلامة ربيع بن هادي المدخلي في كتابه “إزهاق أباطيل عبداللطيف باشميل” (ص:104): "لقد زرت سماحة الشيخ ابن باز –حفظه الله- فنصحني بالرد على كل مخالف للحق والسنة. ونِعْمَة النصيحة، فما أعظمها، وأوجبها على من يستطيع القيام بها." ሸይኽ ረቢዕ እንዲህ ይላሉ:- "ሸይኽ ኢብኑ ባዝን አንዴ ዘየርኳቸውና በማንኛውም ሐቅን የተፃረረ አካል ላይ መልስ እንድሰጥ መከሩኝ። ያማረች ምክር!! ምን የገዘፈች አደረጋት!! በእርሷ ለሚቆምባት አካል ምን የወጀበች አደረጋት!" ↩️ قال الشيخ خالد بن ضحوي الظفيري: "وقد سمعت بأذني الشيخ ابن باز –رحمه الله- يقول مخاطباً الشيخ ربيعاً: "يا شيخ ربيع رد على كل من يخطئ، لو أخطأ ابن باز رد عليه، لو أخطأ ابن إبراهيم رد عليه…" وأثنى عليه ثناءً عاطراً، والله على ما أقول شهيد. [الثناء البديع من العلماء على الشيخ ربيع] ሸይኽ ኻሊድ እንዲህ ይላሉ:- "ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ሸይኽ ረቢዕን እንዲህ ብለው ሲያናግሩ በጆሮየ ሰምቻለሁ:- "ሸይኽ ረቢዕ ሆይ! በማንኛውም የተሳሳተ አካል ላይ ረድ አድርግ (መልስ ስጥ)። ኢብኑ ባዝም ቢሳሳት መልስበት። ኢብኑ ኢብራሂምም ከተሳሳቱ መልስባቸው።" ↩️ ويقول الشيخ خالد أيضا : "بل قد أذن له سماحة الشيخ عبدالعزيز بن باز بالتدريس في مسجده وذلك قبل وفاته بأشهر، مما يدل على أنه توفي وهو عنه راض." [المصدر السابق] እንዲህም ይላሉ:- "ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ከመሞታቸው ከወራት በፊት ሸይኽ ረቢዕ በመስጅዳቸው እንዲያስተምሩ ፈቅደውላቸዋል። ይህም ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ሸይኽ ረቢዕን እንደወደዷቸው መሞታቸውን ነው የሚያመላክተን።" ¤ ከዚህም ውጭ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ሸይኽ ረቢዕን ያወደሱባቸው ንግግሮች በጣም በርካታ ናቸው። የሸይኽ ኢብኑ ባዝን ንግግር ደጋግሜ ያወሳሁት እነ ሙስጠፋ እንከተላቸውዋለን እያሉ በሚሞግቱት ቀጣፊዎች መሆናቸውን ለማሳየት ያክል ነው። ▫️. ሸይኹል አልባኒይ -ረሒመሁላህ-:- ↩️ قال الشيخ العلامة المحدث محمد ناصر الدين الألباني –رحمه الله- في شريط (الموازنات بدعة العصر للألباني) بعد كلامٍ له في هذه البدعة العصرية: "وباختصار أقول: إن حامل راية الجرح والتعديل اليوم في العصر الحاضر وبحق هو أخونا الدكتور ربيع، والذين يردون عليه لا يردون عليه بعلم أبداً، والعلم معه،"   "ባጭሩ በዘመናች የጀርሕ እና ተዕዲል ባንዴራ ተሸካሚ በእርግጥም ወንድማችን ዶ/ር ረቢዕ ናቸው። በእርሱ ላይ መልስ የሚሰጡ ሰዎች መቸም በእውቀት ላይ አይመልሱም። እውቀት ከእርሱ ጋር ነው።" ↩️ ويقول أيضا عن الشيخ ربيع والشيخ مقبل رحمهم الله تعالى: "... فهؤلاء الذين ينتقدون الشيخين ـ كما ذكرنا ـإما جاهل فيُعلّم، وإما  صاحب هوى فيُستعاذ بالله من شره، ونطلب من الله -عز وجل- إما أن يهديه وإما أن يقصم ظهره." شريط ( لقاء أبي الحسن المأربي مع الألباني )  ሸይኹ በሌላ ጊዜ ስለ ሸይኽ ሙቅቢል እና ስለ ሸይኽ ረቢዕ እንዲህ ሲሊ ተናግረዋል:- "ሁለቱን ሸይኾች የሚተች አካል ወይ መሃይም ነው ሊማር ይገባዋል። ወይ ስሜቱን ተከታይ ነው።...."

እንደምን ነው #ወሎ አፈሩ መሬቱ፤ በሰው ሀገር ሁኘ ገደለኝ ናፍቆቱ፤ እንደምን ነው ወሎ ደሴና ኮምቦልቻ፤ የሚወለድበት ቆንጆ ቆንጆ ብቻ፤ እንደምን ነው ወሎ ኸሚሴ እና ሀርቡ፤ ብሉልኝ ጠጡልኝ የሚሉት
እንደምን ነው #ወሎ አፈሩ መሬቱ፤ በሰው ሀገር ሁኘ ገደለኝ ናፍቆቱ፤ እንደምን ነው ወሎ ደሴና ኮምቦልቻ፤ የሚወለድበት ቆንጆ ቆንጆ ብቻ፤ እንደምን ነው ወሎ ኸሚሴ እና ሀርቡ፤ ብሉልኝ ጠጡልኝ የሚሉት አህሪቡ፤ እንደምን ነው ወሎ ሀይቅ የጁና ጊራና፤ የሚወለድበት ደፋር እና ጀግና፤ እንደምን ነው ወሎ ባቲና ወረኢሉ፤ በፍቅር በናፍቆት ሰዉን የሚገሉ፤ እንደምን ነው ወሎ ቦረና እና መርሳ፤ #ነዉር አይሆንም ወይ እናንተን ብረሳ፤ እንደምን ነው ወሎ ወረባቦ አርዲቦ፤ እንግዳ የሚሸኘዉ አብልቶና አጥግቦ፤ እደዉ በጠቅላላው እደት ነዉ መሬቱ፤ በሰው ሀገር ሁኘ ገደለኝ ናፍቆቱ፤

ነገ ሰኞ ነው የቻለ ይፁም ያልቻለ ደግሞ ያስታውስ "ወደ ኸይር ያመላከተ የሰራውን ሰው አጅር ያገኛል"

الحق لا يُعرف بالرجال..! الشيخ صالح بن فوزان الفوزان حفظه الله.

✍ [ الولاء والبراء ] لمعالي الشيخ الدكتور / صالح بن فوزان الفوزان 🔷👉https://t.me/abujemila25

ሕይወት የምትሰጥህ የቆምክበትን ሳይሆን የሄድክበትን ያህል ነው። ወይ ያሰብነው ይሳካል። ወይም እየሞከርን እንሞታለን። ከዚህ ውጪ ያለው መንገድ ሁሉ የፍርሃት፣ የቁጭትና የግማሽ ሕይወት ህልውና ነው።
ሕይወት የምትሰጥህ የቆምክበትን ሳይሆን የሄድክበትን ያህል ነው። ወይ ያሰብነው ይሳካል። ወይም እየሞከርን እንሞታለን። ከዚህ ውጪ ያለው መንገድ ሁሉ የፍርሃት፣ የቁጭትና የግማሽ ሕይወት ህልውና ነው። ​በዚህች ምድር ላይ በርካታ ሰዎች ሳይሞክሩ ይሞታሉ። ከፍርሃታቸው ጋር እየኖሩ፣ ከህልማቸው ይልቅ ሰበባቸውን እያደመጡና በሌሎች ታሪክ ላይ አጨብጭበው ዕድሜያቸውን ይጨርሳሉ። አንተ ግን የሌሎችን ታሪክ የምታይ ተመልካች ልትሆን አልተፈጠርክም። ሕይወት የተጋድሎ ሜዳ ናት፤ በዚህ ሜዳ ላይ ትልቁ ሽንፈት ወድቆ መቅረት ሳይሆን፣ ወድቆ ለመነሳት አለመሞከር ነው። ​ተስፋ አትቁረጥ፣ ወደ ኋላም አትበል! ወይ የታገለህለትን ታላቅ ህልም በእጅህ ጨብጠህ በድል አድራጊነት ትቆማለህ፤ ወይም ደግሞ እስከ መጨረሻው የትንፋሽ ጠብታ ድረስ ሳታወላውል በመታገልህ በክብርና በጀግንነት ታወሳለህ። በሁለቱም መንገድ አንተ አሸናፊ ነህ! ትልቁ ውድቀት ትንፋሽ ማጣት ሳይሆን፣ በውስጥህ ህልም እያለህ አንተ ቀድመህ መሞትህ ነው። ​ስለዚህ፡ ●​መንገድህን እመነው፡ ልብህ ያሰበውን ዓላማ አጥብቀህ ያዝ፤ ማንም እንዲያጠፋው አትፍቀድ። ● ​ሰበብን አወግድ፡ ውጣ ውረዱ፣ መውደቅና መነሳቱ የትግሉ አካል እንደሆኑ ሙሉ በሙሉ ተቀበል። ● ​ሞክረህ እለፍ፡ በቃ ሕይወት እንዲህ ናት! ዕድልን እየጠበቁ የሚኖሩ ሳይሆኑ፣ ዕድልን በላባቸው የሚፈጥሩ ሰዎች ብቻ ናቸው ታሪክ የሚጽፉት። ዛሬውኑ ተነሳ! ህልምህን መሬት ላይ ጥለህ ከመኖር፣ ህልምህን እያደደድክ መውደቅ ይበልጣል። እስከ መጨረሻው ታገል—ወይም ግብህን ትመታለህ፣ ወይም ደግሞ ወደፊት እያመራህ በክብር ትወድቃለህ። ሁለቱም የጀግና መንገድ ናቸው! 𝓪𝓫𝓾 𝓶𝓪𝓱𝓲

🚨 አላህ ሰዎችን እና ጅኖችን የፈጠረው እሱን ብቻ እንዲያመልኩ ነው❔ Free promoter :- @Suna_waver

አላህ (የወንድን) ልብ ሊጠግን ሲፈልግ፤ በፊቷ ደካማ ሆኖ ለመታየት የማይፈራትን ሴት ይሰጠዋል። በአንድ ቃል ድካሙን የምታቀልለትን፣ በአንድ እይታም ጭንቀቱን የምታስወግድለትን ሴት። አላህ የሴትን ልብ ሊጠብቅ ሲፈልግ ደግሞ፤ ቀናት ዝናባማ በሚሆኑበት ጊዜ መጠለያ (ጣራ) የሚሆናትን ወንድ ያዘጋጅላታል! ያሰላም ሾውቅ ፍቅሩን እንደ ጉዞ የማያይ፣ በግማሽ መንገድም ጥሏት የማይሄድን ወንድ። አላህ የሁለት ልቦችን ሰላምና እረፍት ሲሻ ደግሞ፤ በመካከላቸው ምቹ የሆነ ዝምታን ይተክላል ያለ አንድ ቃል እርስ በርሳቸው የሚተዋወቁበት...አካላቸው ከመገናኘቱ በፊት... ነፍሳቸው አስቀድሞ የተዋወቀች ያህል እንዲሰማቸው ያደርጋል.. ... ....ያሰላም 🌹 t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy