قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
Kanalga Telegram’da o‘tish
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
907
Obunachilar
-224 soatlar
-127 kun
+4630 kun
Postlar arxiv
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
➛ኢንተርኔት ፈጣሪው‼️
ሁሉም ያሰማናል የውሻሸት ሰበር፡
አሊ-ባባ ያሁ ጎግልና ቫይበር፡
የዘር የክፉ አሳብ የተንኮል ማዲያ፡
ለኔ ዘመን ወጣት ካንሰር ነው ሚዲያ፡
እንደ ሞኝ አፍጥጬ ስልኬ ላይ እንዳረጅ፡
ኢንተርኔት የሚባል የፈጠርከው ፈረንጅ፡
እኔ እሮኬት የለኝ የማስወነጭፈው፡
የአለማት አምላክ ጥርስህን ያርግፈው፡
🎙በኑረዲን አል-ዓረብ
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
በነገራቹህ ላይ የለተሞ መንጋ ማለት ሰለፊዮች "ከኢኽዋን የሚያስጠነቅቁት" እነርሱን ለማስደሰት የሚመስላቸው ድርብ ግብዞች ናቸው። በመሰረቱኮ ሰለፊዮች ከኢኽዋን በሚያስጠነቅቁበት ሰዓት እነርሱ እራሳቸው ከመሪያቸው ሸይኽ ዓብዱል ሐሚድ ጀምሮ አብዘሃኞቹ የኢኽዋን አጋፋሪና ተከራካሪ የነበሩ ናቸው። ታዲያ እንዴት ነው ዛሬም እንደትላንቱ የኢኽዋንን ጥመት ማጋለጣችን እናንተን ለማስወደድ የሚመስላቹህ!?
قَلِیلࣰا مَّا تَذَكَّرُونَ
=
የቴሌግራም ቻናል
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
Repost from درر العلامة المحدث-ربيع بن هادي المدخلي
خطر أهل البدع ودعاة الفتن علىٰ حياة المسلمين🎙 لفضيلة الشيخ العلامة ربيع بن هادي المدخلي • رحمه اللّٰه •
⛔️ስለ ኢኽዋኑል ሙስሊሚን" ንቅናቄ አመሰራረት፣ ታሪካዊ ዳራና ስለተበላሸው አደገኛ አላማቸው በአላህ ፈቃድ በአጭሩ እንመለከታለን።
⚠️ የኢኽዋኑል ሙስሊሚን ጥቁር ታሪክና ጠምዛዛው አጀንዳቸው - ክፍል 1 ⚠️
● የኢኽዋኑል ሙስሊሚን (የሙስሊም ወንድማማቾች) ንቅናቄ በ20ኛው ክፍለ ዘመን በሙስሊሙ ዓለም ውስጥ ከተከሰቱ እጅግ አደገኛና "ፖለቲካዊ" የጥመት ቡድኖች መካከል ዋነኛው ነው። ይህ ቡድን እንዴት ተመሰረተ? እውነተኛ አላማውስ ምንድነው የሚለውን ስንመለከት?
🏗️ ንቅናቄው በ1928 እ.ኤ.አ (1347 ሂጅሪ) በግብፅ ኢስማዒሊያ ከተማ በሐሰን አል-በና አማካኝነት ተመሰረተ። ሐሰን አል-በና ንቅናቄውን ከመጀመሩ በፊት በ"ሐሳፊያ" በተሰኘው የሱፊያ ጠሪቃ (መንገድ) ውስጥ የሰረጸና በሱፊያ አስተሳሰብ የታነፀ ሰው ነበር።
⛔️ የኢኽዋን መሠረት ከትክክለኛው የነቢዩ (ﷺ) ሱና ይልቅ በሱፊያ ስርአት (መሪን ፍጹም መታዘዝ ወይም 'ተቅሊድ') ላይ የተገነባ ነው። ይህ ደግሞ በቡድኑ ውስጥ ለሚታየው "መሪን ማምለክ" ደረጃ ትልቅ በር ከፍቷል።
ይህ ቡድን የነቢያት ሁሉ ጥሪ "ተውሒድን" (አላህን በብቸኝነት ማምለክና ከሽርክ ማጽዳት) ነበር። ኢኽዋኖች ግን ይህንን ታላቅ መሠረት ወደ ጎን በመተው ዳዕዋቸውን በፖለቲካዊ ስልጣን ላይ ነው የመሰረቱት።
⛔️ የእነሱ ትልቁ ስኬት የሚለካው ስንት ሰው ወደ ተውሒድ ገባ በሚለው ሳይሆን፣ ስንት ሰው የድርጅቱ አባል ሆነና ወደ ቤተ መንግስት ስልጣን ምን ያህል ተቃረብን በሚለው ነው።
⚠️ ሸይኽ አል-አልባኒ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ *"ኢኽዋኖች ተውሒድን አያውቁም፤ ተውሒድን የሚማር ሰው ደግሞ አይወዱም፤ ምክንያቱም ተውሒድ ሰውን ይለያል (ሀቅና ባጢልን ይለይባቸዋል)፤ እነሱ ግን የሚፈልጉት የሰውን ብዛት ብቻ ነው።"*
⚠️ የኢኽዋን ንቅናቄና ዓላማው "ስልጣን" ስለሆነ፣ ያንን ስልጣን ለማግኘት ማንኛውንም አይነት የተበላሸ መንገድ ከመጠቀም አይመለሱም።
⛔️ ዋና መገለጫቸው ተልቢስና ማታለል ነው ፦ ለፖለቲካ ጥቅም ሲሉ ከሺዓዎች፣ ከሊበራሎችና ከአላህ ጠላቶች ጋር እንኳ ሳይቀር ግንኙነት አንድነት ይፈጥራሉ። ሐሰን አል-በና በሚታወቀው ንግግሩ፦ *"ከአይሁዶችና ከክርስቲያኖች ጋር ያለን ጠላትነት የሃይማኖት ሳይሆን የፖለቲካና የድንበር ነው"* በማለት የዲኑን መሠረት (አል-ወላእ ወል-በራእ) የሚንድ ሰው ነው ይሄንን ሰው ነው እንዴ መሪ አድርገው የሀገራችን ኢኽዋኖች የሚንቀሳቀሱት።
🗡️ ኢኽዋኖች ከመጀመሪያው ጀምሮ "" (ድብቅ ወታደራዊ መዋቅር) ነበራቸው። ዓላማቸውም በሙስሊም መሪዎች ላይ በማመፅ ተቃውሞ በመውጣት ስልጣን መቆጣጠር ነው።
⚠️ ይህ የተበላሸው አላማቸው፦ ሰላማዊውን ሙስሊም ማህበረሰብ በገዢዎቻቸው ላይ በማነሳሳት ሀገርን ማተራመስ። ዛሬ በሙስሊሙ ዓለም የምናያቸው አብዛኞቹ አብዮቶች እና ብጥብጦች ምንጫቸው የኢኽዋን አጥፊ አስተሳሰብ ነው።
☣️ እንዲሁም አሁን ላይ እነ ሸይኽ መሀመድ ሀሚዲን ታሪኩን አለባብሰው የሚያቀርቡለት ሰይድ ቁጥብ የ"ተክፊር"የኸዋሪጆችን መርዝ የሚረጭ ዋናው መሪያቸው ነው ከሐሰን አል-በና በኋላ የመጣው ሰይድ ቁጥብ፣ የኢኽዋንን አላማ ይበልጥ ወደ አክራሪነትና ወደ ተክፊር (ሰውን ማክፈር) ቀየረው።
● አጠቃላይ ሙስሊሙን ማህበረሰብ "ጃሂሊያ" (ካፊር) በማለት መፈረጁ።
● ይህ አመለካከት ደግሞ ዛሬ ዓለምን እያስጨነቁ ላሉት እንደ አልቃኢዳና iss ላሉ ጋጠወጥ ቡድኖች "መንፈሳዊ አባት" እንዲሆን አድርጎታል።
በመጨረሻም የኢኽዋን ቆሻሻ አላማ በአራት ነጥብ እንመለክት
1. እነሱ ዘንድ ስልጣን ከዲን ይቀድማል ፦ ዲን ለእነሱ ለፖለቲካ ስኬት መጠቀሚያ "መሳሪያ" ብቻ ነው።
2. ትልቁ ግባቸው አቂዳን መግደል ነው፦ ሽርክና ቢድዓን ዝም በማለት "ህዝብን እናስተባብር አንድ እናድርግ" በሚል ስሜት ተውሒድን ማዳከምና ትክክለኛውን ዐቂዳ ማጥፋት ነው የሚፈልጉት።
3. ድርጅታዊ አምልኮ ውስጥ የገቡ ናቸው፦ ለድርጅቱ (ለተንዚሙ) የታመነ አማኝን ማፍራት እንጂ ለአላህና ለሱና የታመነ ሙስሊም መገንባት በጭራሽ አይፈልጉም።
4. ሁከትና ብጥብጥ መፍጠርን ይወዳሉ ሙስሊም መሪዎችን በማክፈርና ህዝብን በማነሳሳት ደም መፋሰስን እንደ "ጅሃድ" በመቁጠር በሙስሊሙ መካከል አጥፍቶ መጥፋትና ተቃውሞ ሰልፍ ውጡ በማለት ከባድ ብጥብጥ ይፈጥራሉ።
ሸይኽ ሙቅቢል አል-ዋዲዒ (ረሒመሁላህ) እንዳሉት፦ *"ኢኽዋኑል ሙስሊሚን ኡመቱን ወደ ኋላ የጎተቱ፣ ለጠላቶች በር የከፈቱና በዲን ስም የሚነግዱ አጭበርባሪዎች ናቸው።"*
ክፍል ሁለት ይቀጥላል ...የዑለሞችን ጠንካራ ትችትና ማስረጃዎችን እንዳስሳለን።
ይሄ ስለ ኢኽዋኖች ሀይላይት ብቻ ነው ሸር በማድረግ በነሱ ለተሸወዱ ሙስሊሞች እንድረስላቸው።
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/Abu_hibetillah_AsselfiyRepost from «🔵Abu_Aisha (Awel_kasaw)»
احذر الحاسد القريب
البعيد لا يعلم تفاصيل حياتك، ولا يستشعر قيمة النعم التي بين يديك لأنها لا تقع تحت عينيه يومياً.
https://t.me/Abuebrahim22322
Repost from የሰለፊዮች መገናኛ በሐይቅ ملتقى السلفيين في حيق
ሰውም ከዘመዱ አህያም ካመዱ
ሰዎች በባህሪያቸው የራሳቸውን እምነት፣ ርዕዮተ ዓለም እና ስነ-ልቦናዊ ዝንባሌ ከሚያንፀባርቁ ሰዎች ጋር መወዳጀት እና መሞዳሞድ ይቀናቸዋል። አንድ ሰው በቃሉ "እኔ እንዲህ ነኝ፤ አቋሜም ይህ ነው" ብሎ ሺህ ጊዜ ቢከራከርም፣ የሚውልባቸው ቦታዎች እና የሚያሞግሳቸው ሰዎች ሌላ ከሆኑ፣ እውነተኛ ማንነቱ ያለው ከሚውልበት እንጂ ከሚናገረው ጋር አይደለም። የሃሳብ ዝምድና ከደም ዝምድና በላይ ሰዎችን ያስተሳስራልና።
ሰይድ ቁጥብን የሚያሞግስን ሰው እንደት ነው ሰለፊይ ነው ብለህ የምትለኝ ... ?
ሰውም ከዘመዱ አህያም ካመዱ ነው ....እዛው ራስህን ቻልልን
https://t.me/MULTEQA_SELEFIYIN
https://t.me/MULTEQA_SELEFIYIN
🎊 አስደሳች ዜና 🎊
🎉 እንኳን ደስ አላቹ የ 1ወር ክፍያ ብቻ በመፈፀም ለሁለት ወር የሚቆይ የአረብኛን ቋንቋ ስልጠና ልንሰጣቹ ዝግጁ ነን
🗓 ሊሳን የቋንቋ መማሪያ ማዕከል የሁለተኛ ዙር የአረብኛ ቋንቋ ትምህርት ምዝገባ መጀመሩን ሲነግርዎ በታላቅ ደስታ ነው
📍ስልጠናውን ለመውሰድ የትም መሄድ አይጠበቅቦትም በእጅዎ ላይ ያለውን ስልክ በመጠቀም በ ቴሌግራም መውሰድ ይችላሉ
✅ ስልጠናውን ወስደው፦
◍ መሰረታዊ የዐረቢኛን ቃላት ይረዱ
◍ ቀላል ውይይት ማድረግ ይልመዱ
◍ ከሰው ጋር መግባባት በሚችሉበት መልኩ መናገርን ይጀምሩ
📞 በ 09-13-35-36-13 በመደወል አልያም ባስቀመጥነው የቴሌግራም መለያችን ያናግሩን @lisan_35
Repost from N/a
.
ጥያቄ
▬▭▬▭
ቁርዓን ውስጥ ስንት ምህራፎች አሉ ?
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
#SaudiArabia🇸🇦
በሳዑዲ አረቢያ፣ የሰው ህይወት ያጠፋው ግለሰብ በሞት ተቀጣ።
የሳዑዲ ዓረቢያ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በመካ ክልል በግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ተብሎ የሞት ፍርድ የተፈረደበት የየመን ዜጋ የሞት ቅጣቱ እንደተፈጸመበት አስታወቀ።
ዚያድ ዋሊድ መሐመድ አብዱላህ ሀይደራህ የተባለው ግለሰብ ከሌላ የየመን ዜጋ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በሹል ነገር ጭንቅላቱን በመምታት ለሞት እንደዳረገው ሚኒስቴሩ ገልጿል።
ጉዳዩ በፍርድ ቤት ታይቶ ጥፋተኛ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ፣ ተከሳሽ ይግባኝ ቢጠይቅም የሞት ፍርዱ ጸንቷል። ይህንንም ተከትሎ በንጉሳዊ ትዕዛዝ የሞት ፍርዱ ትላንት ተፈጻሚ ሆኗል።
ሚኒስቴር እንዳለው፥ እርምጃው የሀገሪቱን ደህንነት ለማስጠበቅ፣ ፍትሕን ለማስከበር እና በሕይወት የመኖር መብት ላይ ሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመከላከል የሚወሰድ ሕጋዊ እርምጃ ነው።
ተመሳሳይ ወንጀል ለመፈጸም የሚያስቡ ሰዎችም በሕግ የተደነገገውን ከባድ ቅጣት እንደሚጋፈጡ ሚኒስቴሩ አስጠንቅቋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ/ም
@tikvahethiopia
=
በዚህና መሰል ዜናዎች ስር ኢትዮጵያውያን የሚያሳዩትን ከፍተኛ ድጋፍ የተመለከተ ህዝቡ ምን ያህል በሀገራችን የወንጀል መንሰራፋትና በቅጣት ህጉ መላላት ቆሽቱ እንዳረረ መረዳት ይቻላል።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ሸይኽ ረቢዕ ብኑ ሃዲ አልመድኸሊይ رحمه الله እንዲህ ብለዋል፡-
👉 “በምድር ላይ እንደ ሰይድ ቁጥብ ተከታዮች ውሸታም አላየንም። ከነሱ የከፋ ውሸታም፤ ከነሱ የከፋ የንፁሃንን ክብር ለማጠልሸት የሚዳፈር አላየንም። ወላሂ! ከራፊዷዎች (ከሺዓዎች) በበዛ አስመሳዮችና ቀጣፊዎች ናቸው!! ይህ ነው የሰይድ ቁጥብ አስተምሮ ውጤት!!! ቀጣፊና አመፀኛ ትውልድ አፈራልን፡፡ ፖለቲካቸው አመፅ፣ ቅጥፈት፣ ውሸት፣ ከጥፋት ሰዎች በሀሰት መከላከል እና የሐቅ ሰዎችን በቅጥፈት መወንጀል ላይ የተገነባው ነው።”
[መርሐበን ያ ጧሊበል ዒልም፡ 394]
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
ውድና የተከበራቹ እህት ወንድሞች ከራጁ ላይ የምትመለከቱት ስብር በካንሰር በሽታ ምክኒያት ነው እንድህ የሆነው ውዷ እናታችንን ካንሰሩ ከሰውነቷም አልፎ አጥንቷን ሰብሮታን እስከዛሬ ቤተሰብ ሲያሳክሟት ኑረዋን አሁን ግን የተጠየቀው ገንዘብ በጣም ከአቅም በላይ ሰለሆነ ህክምናው ወዴ ውጭ ሀገር ድረስ ሰለሚያስከድ ወደናተ መጥተናን የቻለ በገንዘብ ያልቻለ በዱአ እንድታግዙን እንጠይቃለን
https://chat.whatsapp.com/KJh1Wr53oGt5bItMgyLVYf?s=cl&p=a&mlu=4
የአካውንት ቁጥር
1000245518106
ሙሀመድ አረቡ ሙሄ
Repost from jelalu husseyn (abu zikra)
ያረብ
ያለ ጥላቻ
ያለ ጭንቀት
ያለ ትካዜ
ያለ ጥበት
ያለ ማነስ
ያለ ድካም
በእነዚያ ውድ የጀነት ክፍሎች ሰብስበን
ــــــــــــــــــ 👑 ــــــــــــــــــ
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የ “ዘመን መለወጫ” ኮተቶች
~
ኢትዮጵያ በምትከተለው ክርስቲያናዊው የዘመን አቆጣጠር መሰረት አዲስ አመት ሊገባ የያዝነው አመት እየተጠናቀቀ ነው። በያመቱ በዚህ ሰሞን የሚፈፀሙ ከሃይማኖታችን ጋር የማይሄዱ በርካታ ነገሮ አሉ። ከነዚህም ውስጥ:-
1. ድግምትና ጥንቆላ፦
በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ነሐሴ ሊጠናቀቅ ሲል በየጠንቋዩ ቤት የሚልከሰከሱት ብዙ ናቸው። ከዚያም አምስቱ ወይም ስድስቱ የጳጉሜ ቀናት መንገዶች በድግምት ስራዎች ይሞላሉ። በነዚህ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲረግጣቸው/ እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ የሞቱ ፍየሎች፣ ዶሮዎች፣ ድመቶች፣ ጥንቸሎች ወዘተ ታርደው ይጣላሉ። በደም የተነከሩ ሳንቲሞች፣ ብሮች፣ ጌጣ ጌጦች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ።
* ጥንቆላና ድግምት ከኢስላም የሚያስወጡ ከባባድ ወንጀሎች ናቸው፡፡
وَاتَّبَعُوا مَا تَتْلُو الشَّيَاطِينُ عَلَى مُلْكِ سُلَيْمَانَ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَانُ وَلَكِنَّ الشَّيَاطِينَ كَفَرُوا يُعَلِّمُونَ النَّاسَ السِّحْرَ
“በሱለይማን ዘመነ-መንግስት ሸይ ^ጧኖች የሚያነቡትንም (ድግምት) ተከተሉ። ሱለይማን ግን አልካደም (ድግምተኛ አልነበረምና።) ግና ሸይ^ጧኖች ሰዎችን ድግምት የሚያስተምሩ ሲሆኑ ካዱ።” [አል-በቀራህ፡ 102]
ነብዩም ﷺ {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ በሚናገረው ያመነ፣ በሙሐመድ ላይ በወረደው ክዷል} ብለዋል። [አስ-ሶሒሐህ፡ 3387]
* ደጋሚዎችና ከነሱ ዘንድ የሚመላለሱ ሰዎች መቼም ቢሆን ስኬት የላቸውም። ጌታችን “ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም” ብሏል። [ጦሃ፡ 69]
* ጠንቋይና ደጋሚ ዘንድ የሚሄድ ሰው የተነገረውን ባያምን እንኳን ከባድ ቅጣት ይከተለዋል። ነብዩ ﷺ {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ስለሆነ ነገር የጠየቀው የአርባ ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም} ብለዋል። [ሙስሊም፡ 5957]
2. ሎሚ መምጠጥ እና ፌጦ መብላት:-
በአንዳንድ አካባቢዎች ከድግምትና ጥንቆላ ለመጠበቅ በማሰብ ወላጆች ልጆቻቸውን ጳጉሜ ላይ ሎሚና ፌጦ ይመግባሉ። ድግምትና ጥንቆላ ሸይ^ ጧናዊ ተግባራት ናቸው። መጥጠበቂያ መንገዶቹ አዝካር፣ አየቱል ኩርሲይ፣ ሱረቱል ኢኽላስን (ቁል ሁወላሁ አሐድ)፣ ሙዐዊዘተይን (ቁል አዑዙ ቢረቢል ፈለቅ፣ ቁል አዑዙ ቢረቢናስ) ከሶላት በኋላ እና ጧትና ማታ መቅራት፣ እንዲሁም ከሱረቱል በቀራ የመጨረሻዎቹን ሁለት አንቀፆች መቅራት፣ ሩቅያ ማድረግ ናቸው። አጉል እምነት ላይ የተመሰረቱ ሰበቦችን መጠቀም ከሺርክ ነው።
በተረፈ የተጣለ የድግምት ስራ ቢያጋጥመን ምንም መደናገጥ አያስፈልግም። በአላህ ላይ ጠንካራ እምነት ማሳደር (ተወኩል) ቀዳሚው መከላከያ መንገድ ነው። አጉል መጨናነቅ ለችግር ይዳርጋል። ከዚያም የድግምት ስራውን ሙዐዊዘተይን በመቅራት ማስወገድ ነው (ማቃጠል፣ መቆራረጥ ወይም ቆፍሮ መቅበር)።
3. የጳጉሜ ዱዓእ የሚል ቢድዐ:-
በአንዳንድ አካባቢዎች የጳጉሜ ዱዓእ “መቅቡል ነው” (ተቀባይነት ያለው ነው) የሚል እምነት አለ። ይሄ አጉል እምነት ነው። በጣም የሚገርመው ለዱዓእ የሚጣዱት እስልምናን ያውቃሉ ሰዎችን ያስተምራሉ የሚባሉት ሰዎች መሆናቸው ነው። ነብዩ ﷺ “አላህ እውቀትን ከባሪያዎቹ መንጠቅን አይነጥቅም። ይልቁንም ዑለማዎችን በመውሰድ (በመግደል) እውቀትን ይወስዳል። ከዚያም ዓሊም እስከማይቀር ድረስ። በዚያኔ ሰዎች መሀይማንን መሪዎች አድርገው ይይዛሉ። ሲጠየቁም ያለ እውቀት ፈትዋ ይሰጣሉ። በዚህም ይጠማሉ፣ ያጠማሉም” ብለዋል። [ሶሒሕ አልቡኻሪይ፡ 100] [ሶሒሕ ሙስሊም፡ 2673]
4. የጳጉሜ ጸበል (ጥምቀት)፦
ጳጉሜ 3 ቀን በኦርቶዶክስ ክርስትና የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ በዓል ነው ይላሉ። በዚህ ዕለት "የሰማይ ደጆች ይከፈታሉ፣ ዝናቡም የበረከትና የፈውስ ውሃ ሆኖ ይወርዳል" ተብሎ ይታመናል። በዚህም የተነሳ ሕዝቡ ሕፃናትን ጨምሮ ከሰማይ የሚወርደውን ዝናብ (የጳጉሜን ዝናብ) እንደ ጸበል በመቁጠር ሰውነታቸውን ይጠመቁበታል። ሙስሊሞች ከንደዚህ ዓይነት እምነቶችና ተግባራት ሊርቁ ይገባል።
5. እንቁጣጣሽ ማክበር:-
ሌላኛው የ “ዘመን መለወጫን” ተከትሎ የሚፈፀመው ጥፋት መስከረም አንድን ወይም እንቁጣጣሽን ማክበር ነው። ዕለቱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን እምነት መሠረት "ቅዱስ ዮሐንስ" በመባል የሚጠራ ሲሆን፣ የመጥምቁ ዮሐንስ መታሰቢያ እና የቅዱሳን አበው መታሰቢያ ይደረግበታል። በቤተክርስቲያን ደረጃ የማህሌት፣ የቅዳሴ እና የምስጋና ሥርዓት ይፈጸምበታል።
በተጨማሪም የበዓሉ ስም (እንቁጣጣሽ የሚለው) ከንግሥተ ሳባ እና ከንጉሥ ሰሎሞን አፈ ታሪክ ጋር ይያያዛል። ንግሥተ ሳባ ከኢየሩሳሌም ስትመለስ መኳንንቶቿ "እንቁ ለጣጣሽ" (ለጌጥሽ ይሁን) በማለት በዕንቁ ስለተቀበሏት ይህ ስም እንደወጣ ይነገራል።
አቆጣጠሩ ሀገራዊ እንጂ እምነታዊ መሰረት እንደሌለው ሊያሳምኑ የሚሞክሩ ሰዎች አሉ። ነገሩ ግልፅ ቢሆንም ድንገት የሚሰወራቸው ካሉ ለማስታወስ ያህል:-
* አቆጣጠሩ ከግብፅ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን የተቀዳ ነው።
* አመቱ ሲፃፍ መጨረሻ ላይ “ዓመተ ምህረት” የሚባለውም ክርስቲያናዊ ስለሆነ ነው።
* የነብዩ ዒሳን (ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) መወለድ መሰረት ያደረገ እንደሆነ የሚታመን ነው።
* በእለቱም የሚፈፀሙት የተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶችም በዓሉ ክርስቲያናዊ እንደሆነ በሚገባ አጉልተው ያሳያሉ፦
- የዋዜማ ጸሎትና ማኅሌት፦ በበዓሉ ዋዜማ (ጳጉሜን 5 ወይም 6) ሌሊቱን ሙሉ በቤተክርስቲያን ልዩ የቅዱስ ዮሐንስ ማኅሌትና ጸሎት ይቆማል።
- የቅዳሴ ሥነ-ሥርዓት፦ በዕለቱ ጠዋት ምዕመናን አዲስ ልብስ ለብሰው ወደ ቤተክርስቲያን በመሄድ በቅዳሴና በዕለቱ ትምህርተ ወንጌል ላይ ይሳተፋሉ።
- ዘመነ ዮሐንስን መቀበል፦ በቤተክርስቲያን ዘመን መለወጫን አስመልክቶ ልዩ ጸሎት ይደረጋል፤ የወንጌላዊው ዘመንም (ዘመነ ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ ወይም ዮሐንስ) ይታወጃል። “እንኳን ከዘመነ ማቲዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ፣ ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ፣ ... አደረሳችሁ” ማለታቸው አቆጣጠሩና በዓሉ ሃይማኖታዊ መሆናቸውን አጉልተው የሚያሳዩ ነጥቦች ናቸው፡፡
ይህንን ስንል የሚጎረብጣቸው አሉ። እኛ'ኮ የኛን ዒድ አብራችሁን ካላከበራችሁ አላልንም። ይልቁንም የኛን እምነታዊ መገለጫ ካላንፀባረቃችሁ ብሎ ሌሎችን መወረፍ አክራሪነት ነው። እምነታችን የሌሎች ህዝቦች #መለያ በሆኑ እምነቶችና ልማዶች መመሳሰልን አይፈቅድም። ነብያችን ﷺ “በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው” ብለዋል።
(ኢብኑ ሙነወር፣ 18/11/1436)
=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሱብሀነሏህ እንዴት የሚደንቅ የፅናት ታሪክ ነው
------
በ1977 በኢትዮጵያ በነበረው ድርቅ ምክኒያት የተፈጠረውን ርሃብ ተከትሎ የተከሰተውን ይህን አሳዛኝ ታሪክ ሌላ ሰው ቢያወራው ኖሮ ለማመን ይከብድ ነበር ነገር ግን ይህን ታሪክ የሚናገሩት ኩዌይታዊ ሼኸ ዶ/ር አብዱራህማን አስ-ሰሚጥ ናቸውና ለማመን እንገደዳለን አላህ ይማራቸውና በአፍሪካ አህጉር ከ11ሚሊዮን በላይ ሠዎችን ያሰለሙ ሸይኽ ናቸው
ታሪኩ እንዲህ ነው በ1977 አንድ የክርሰትያን በጎ አድራጊ ማህበር ከሰሜን አሜሪካ እርዳታ ለመሰጠት ወደ ኢትዮጵያ ይመጣና በቀጥታ ድርቅና ርሃብ ወደ ተከሰተበት ገጠር ሂደው እርዳታ መሰጠት ይጀምራሉ ከዚያም የመስጂድ ኢማም የሆኑ አንድ ትልቅ ሠው እርዳታ ለመቀበል ይመጣሉ አሜሪካዊው እርዳታ ሰጪ ሲያያቸው የሀይማኖት አባት መሆናቸውን አውቆ ክርሰትያን እንዲሆኑ ጠየቃቸው እሳቸውም «ክርሰትያን አልሆንም የምትሰጠኝ ከሆነ ሰጠኝ» አሉት አሜሪካዊውም «እሺ አሁን በህዝብ ፊት በውሸት ክርሰትያን ሁኜያለሁ በል እና የፈለግከውን እሰጥሃለሁ» አላቸው እሳቸውም «በውሸትም በእውነትም አልልም ሀይማኖቴን አልቀይርም አሉት» ሰውየው ተናደደ እና «በቃ የሚሰጥ የለንም» ብሎ መለሳቸው ኢማሙ ባዶ እጃቸውን ወደ ቤታቸው ተመለሱ የሳቸው ቤተሰብም ጨርሶ እርዳታ ሳያገኝ ቀረ ፥
ከ3 ወራት በኋላ ይህን ታሪክ የሰሙት ኩዌታዊ ሸይኽ አብዱራህማን እንዲህ ይላሉ «ይህን ወሬ ከሰማሁኝ በኋላ በቀጥታ ከኩዌት ወደ ኢትዮጵያ ሄድኩኝ እና እኚህ ኢማም ወደ ሚኖሩባት አካባቢ ተጓዝን እንደ ደርሰን በአካባቢው ሰው የሚባል የለም ሁሉም ድርቁን ሽሽት አካባቢውን ለቀውት ሄደዋል ይዘውኝ የሄዱት ሰዎች የኢማሙን ቤት አሳዩኝና በራቸውን አንኳኳን የሚከፍትልን ስናጣ በሩን ገፋ አድርጌ ገባሁ ያየሁት ነገር እጅግ ዘግናኝ እና አስደንጋጭ ነበር አይኔን ማመን ከበደኝ ኢማሙ ሚሰታቸው እና ልጆቻቸው ሁሉም እንደተኙ በርሃብ ሙተዋል የአጥንታቸው ሃይከል ብቻ ተኝቶ አገኘሁት ፥ «በርሃብ እንሞታለን እንጂ ሀይማኖታችንን አንቀይርም» ብለው የሞቱ የሀበሻ ቤተሰብ አይቼ ተመለሰኩኝ ፥ በተጨማሪ እነዚያ በክርሰትና ስም ይዘውት የመጡት እርዳታ የኛ የአረብ አገሮች እና የሌሎች የመላው የአለም ህዝብ አዋጥተን ለተባበሩት መንግሰታት ድርጅት በሰብአዊነት የሰጠነው እርዳታ ነበር እነርሱ ግን በእንደዚህ አይነት አሳዛኝ ሁኔታ አከፋፍለውታል» ሲሉ ታሪኩን ያጠቃልላሉ
Abdulfetah Mahmud
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
ወደ ፊት ብቻ!
~
ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሁሉም አይነት ሰው አለ። ሞቅ ያለ ተሳትፎ ካለን በተለያዩ አካላት እንገመታለን። እንገመገማለን። እንተመናለን። በአቋም የሚመስለን እንዳለ ሁሉ የሚቃረነንም ብዙ ነውና ዋጋችንና ቦታችን ከሰው ሰው ይለያያል።
* ከፊሉ የምትፅፈው/ የምትናገረው ነገር አይጥመውም። ከፊሎቹ ጋር ደግሞ እውነታው ይለያል።
* ከፊሉ ቀድሞ በጥላቻ ስለተሞላ የኔ የሚለው ሰው ቢናገረው የሚደግፈውን ብትናገር እንኳ ሰበብ ፈልጎ ያብጠለጥልሃል።
* ከፊሉ ዘንድ ሚዛናዊ ነህ። ሌላው ዘንድ ደግሞ ፅንፈኛ፣ ፍርደ ገምድል ነህ።
* ከፊሉ ዘንድ አስተዋይና በሳል ነህ። ሌላው ዘንድ የሃገርና የወቅት ተጨባጭ ያልገባህ ጥሬ ነህ።
* ከፊሉ ዘንድ አዛኝ ነህ። ከፊሉ ዘንድ ጨካኝ ነህ።
* ከፊሉ ዘንድ እየበሰልክ ነው። ሌላው ዘንድ እየባሰብህ ነው።
* ከፊሉ ዘንድ ቡድንተኛ ነህ። ሌላው ዘንድ ውግንናህ ለሐቅ ብቻ ነው።
የሚርቅህ ብቻ ሳይሆን የተሻለ የሚቀርብህ ራሱ የበለጠ ሊጠላህ እና ንግግርህንም ዝምታህንም ያላሰብከውን ትርጉም እየሰጠ ሊያጣጥልህ ይችላል። ቢሆንም ታገስ። ሞራልህ ሳይጎዳ ወደፊት ገስግስ።
የተራራቁ አመልካከቶች በበዙበት፣ ከዒልምና ተርቢያ የራቀ ትውልድ እንደ አሸን በፈላበት፣ በሺርክና መልከ ብዙ ቢድዐዎች ላይ የተዘፈቀው ወገን በበዛበት፣ ይሄ ሁሉ ወፈ ሰማይ በነፃነት የሚናገርበት መድረክ አግኝቶ ከየትኛውም አካል ጉንተላ ሳያገኘኝ ሰላም እጓዛለሁ ማለት ዘበት ነው፣ አጉል ምኞት።
ስለዚህ ደዕዋ ላይ ያለኸው ወገኔ ሆይ! በደዕዋህ ላይ ትችትና ዘለፋ አያስደንብርህ። ቲፎዞና ጭብጨባም አያቅልጥህ። ሰዎች የሚሰጡህ ደረጃም አይድነቅህ። ሁሉም አላፊ ነው። ይልቅ አላህን ብቻ አስብ። በኢኽላስ ተጓዝ። በኢኽላስ ለካ! በኢኽላስ ቁረጥ። ጫጫታ ሳይበግርህ ወደፊት ብቻ። እልህ እንዳይሾፍርህም ሚዛንህን ጠብቅ። ዝቅ ብለህ ጀምር። ወርደህ ስራ። ተግተህ ጣር። መስመር ይዘህ፣ አላህን እያሰብክ እስከተጓዝክ ድረስ መንናቅ አያሳምምህ። ዝናም አያንጠባርህ። በየትኛውም ሁኔታ ከደዕዋ እንዳትርቅ። እንዳትርረታ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from N/a
➲ኢስላማዊ ታሪኮች📜
➲ዲናዊ ምክሮች📝
➲የተለያዩ ዳዓዋዎችን📣
➲ቁርዓን እና ሀዲስ የምታገኙበት📖
🧩 ምርጥና ተወዳጅ ቻናል ✨
# ተቀላቀሉ ✅👇
https://t.me/+KXmTq2tJLzxjYzQ0
Repost from نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے
ፉዩሽ ለሚማሩ ኢቲዩጵያውያን የተሰጠች አጭር ምክር። በዚሁ አጋጣሚ ወንድም ኢዲሪስ ጀዛከላህ
الشيخ الفقيه المربي أبي عمار محمد بن عبدالله باموسى حفظه الله
t.me/abdu_rheman_aman
t.me/abdu_rheman_aman
