uz
Feedback

Firibgarlarga uchmang! Telemetrio bunday kanallarni topadi va belgilaydi 👉 Belgini ko‘rmoqchi bo‘lsangiz, obuna bo‘ling

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Kanalga Telegram’da o‘tish

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
915
Obunachilar
Ma'lumot yo'q24 soatlar
-67 kun
+5630 kun
Postlar arxiv
Repost from Dr. Seid Musa
🕌 የደሴ መስጂደ አስ-ሱና የእርዳታ ጥሪ! ዛሬ የምናበረክተው የነገውን የዕውቀት ብርሃን ለማስፋት  ነው! በአላህ ፈቃድ የሚተላለፍ የዒልም ብርሃን፤ ከዱንያ ሕይወታችን በኋላም የሚቀጥል ሰደቀተል ጃሪያ ነው! 📢 ለዓለም ዙሪያ ለምትገኙ ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሙሉ የተላለፈ የኸይር ጥሪ! በደሴ ከተማ የሰለፊዮች ዐይን ፣ የሱና ብርሃን መፍለቂያ እና የቁርአንና የሸሪዓ ዕውቀት መማሪያ የሆነችው መስጂደ አስ-ሱና ዛሬ በእናንተ እገዛ የሚታሰብ ታሪክ ለመሥራት በር ከፍታለች! በቅርብ ጊዜ ይህ መስጂድ በትንሽ ቦታ፣ ቆርቆሮ በቆርቆሮ በትንሽ ቦታ ላይ ፣ በትንሽ አቅምና በታላቅ ተስፋ ተጀመረች። በሸይኽ መሐመድ መኪን መሪነት የተለያዩ ቂርኣቶች፣ የዳዕዋ ፕሮግራሞች፣ የዒልም ደርሶችና የኮርስ ትምህርቶች ሲሰጡባት ቆይተዋል። በዚያ ትንሽ ቦታ ውስጥ የአላህ ቃል ተነብቧል፤ የነቢዩ ﷺ ሱና ተምሯል፤ የዒልም ተማሪዎች ተቀምጠዋል፤ የብዙ ሕፃናትም ልብ በቁርአን ብርሃን እንዲበራ ጥረት ተደርጓል። ነገር ግን፣ አልሐምዱ ሊላህ! ዛሬ በዚህች መስጂድ የሚቀሩ ሕፃናት ቁጥር እጅግ ጨምሯል። ይህ የሚያስደስት የኸይር ዜና ቢሆንም፣ የሚማሩበት ቦታ መድረሳ ጠባብ በመሆኑ ትልቅ ፈተና ሆኗብናል። ዛሬ በዚያ ጠባብ መድረሳ ውስጥ የሚቀመጡት ሕፃናት የነገው የኡማችን ተስፋዎች ናቸው። ከእነርሱ መካከል የቁርአን ሐፊዞች፣ የሐዲስ ዕውቀት ተሸካሚዎች፣ የሱና ጥሪ አስተላላፊዎችና ለእስልምና የሚጠቅሙ የዒልም ሰዎች ሊወጡ ይችላሉ። እነዚህ ሕፃናት የአላህን መጽሐፍ በሰፊ ቦታ፣ በተመቻቸ አካባቢና በተሻለ የመማሪያ ሁኔታ እንዲማሩ ማድረግ የእኛ የዛሬ ኃላፊነት ነው። ⚠️ ወዳጆቻችን ሆይ! የዚህ ታላቅ ኸይር ተባባሪዎች እንሁን! የመስጂደ አስ-ሱናን የመማሪያ ቦታ ለማስፋፋት፣ ሕፃናቱ የሚቀሩበትን መድረሳ ለማሻሻልና የቁርአንና የሱና ትምህርት የበለጠ እንዲስፋፋ ለማድረግ የእናንተን ድጋፍ እንሻለን። አንዳንዶቻችን ብዙ ልናዋጣ እንችላለን፤ ሌሎቻችን ደግሞ ትንሽ ልናዋጣ እንችላለን። ነገር ግን በአላህ ዘንድ የሚቀበለው በቁጥር ብቻ የሚለካ ሳይሆን በኢኽላስና በመልካም ዓላማ የሚመዘን ነው። በትንሽ አቅማችሁ ትልቅ ለውጥ ማምጣት ትችላላችሁ! አንድ ሕፃን በእናንተ ድጋፍ ቁርአንን በትክክል ቢያነብ፣ አንድ ተማሪ ትክክለኛ የዲኑን ዕውቀት ቢያገኝ፣ አንድ ልጅ የተማረውን ዕውቀት ለሌሎች ቢያስተላልፍ፣ የእናንተ እገዛ በዚህ መልካም ሥራ ውስጥ ድርሻ እንዲኖረው አላህ ሊያደርግ ይችላል። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «إِذَا مَاتَ الْإِنْسَانُ انْقَطَعَ عَنْهُ عَمَلُهُ إِلَّا مِنْ ثَلَاثَةٍ: إِلَّا مِنْ صَدَقَةٍ جَارِيَةٍ، أَوْ عِلْمٍ يُنْتَفَعُ بِهِ، أَوْ وَلَدٍ صَالِحٍ يَدْعُو لَهُ». “የሰው ልጅ በሞተ ጊዜ ሥራው ይቋረጣል፤ ከሦስት ነገሮች በስተቀር፦ የሚቀጥል ሰደቃ፣ ከእርሱ የሚጠቀምበት ዕውቀት፣ ለእርሱ ዱዓ የሚያደርግ መልካም ልጅ።” 📚 ሰሒሕ ሙስሊም፣ 1631 ወንድሞችና እህቶች ሆይ! ዛሬ በመስጂድ ማስፋፊያ ላይ የምናዋጣው ገንዘብ የዛሬ ድጋፍ ብቻ አይደለም። በዚያ ቦታ ቁርአን ሲነበብ፣ የአላህ ዲን ሲማር፣ ልጆች ሲያድጉና የሚጠቅም ዕውቀት ሲተላለፍ፣ አላህ ከምሕረቱ ድርሻ እንዲያደርግልን የምንሻበት ታላቅ እድል ነው። እኛ እዚህ ምድር ላይ ለዘላለም አንኖርም። ነገር ግን በኢኽላስ የተሠራ መልካም ሥራ አላህ ከተቀበለው፣ ከሞታችን በኋላም የምንጠብቀው የኸይር ምክንያት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ዛሬ የምንችለውን እናድርግ፤ የምንችለውን እናዋጣ፤ ሌሎችም እንዲሳተፉ እንጋብዝ። ምናልባት በእኛ የተነሳ የአላህ ዲን የሚማሩ ልጆች ቁጥር ይጨምር ይሆናል። ⚠️ዛሬ የእናንተ ድጋፍ የእነዚህ ሕፃናት ተስፋ ነው! 🌍 በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በዓለም ዙሪያ ለምትኖሩ ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን፦ በዚህ የኸይር ሥራ ላይ የቻላችሁትን ያህል ድጋፍ እንድታደርጉልን በአላህ ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን። የምትሰጡት ትንሽ ቢመስልም አትናቁት። የምታደርጉት ድጋፍ በአላህ ፈቃድ ለብዙ ሕፃናት የዒልም መንገድ ሊያመቻች ይችላል። ካልቻላችሁ ደግሞ ይህን ጥሪ ለሌሎች በማድረስ ተባበሩን። የኸይርን መንገድ የሚያመለክትም ከሠሪው ምንዳ ያገኛል። ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 🏦 የመስጂደ አስ-ሱና የባንክ ሂሳቦች 💳 1. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) 1000469830277 💳 2. ዘምዘም ባንክ 0005649620101 💳 3. ሂጅራ ባንክ 1000030300001 📌 ከላይ የተጠቀሱት የባንክ ሂሳቦች በመስጂደ አስ-ሱና ስም የተመዘገቡ ናቸው። ስለ መስጅዱ ሙሉ መረጃ ለማገኘትና ለመጠየቅ ስልክ፦+251914718693 ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📣 ይህን መልእክት ሼር በማድረግ ለመስጂደ አስ-ሱና ማስፋፊያ የሚያግዙ ወንድሞችና እህቶች እንዲደርሱ እንርዳ! 🕌 በመስጂደ አስ-ሱና — ላይ የማናደርገው የዛሬው ድጋፋችን፣ የነገው የዒልም ብርሃን ያሰፋል!

አቡ ሙዓዝ❌➛ወደ ሀዋሳ ከሸሼ ቡኃላ የሱና መሻይኾችን መዘለፍ መጀመሩ አስገርሞኛል‼️ ሙመይዓ ስትል ባለህበት መንደር ታመኝ ለመምሰል ያሰብክ ትመስላለህ ሀቂቃ‼️ እንደመናቅ እሚያም ነገር ባይኖርም ባ
አቡ ሙዓዝ❌➛ወደ ሀዋሳ ከሸሼ ቡኃላ የሱና መሻይኾችን መዘለፍ መጀመሩ አስገርሞኛል‼️ ሙመይዓ ስትል ባለህበት መንደር ታመኝ ለመምሰል ያሰብክ ትመስላለህ ሀቂቃ‼️ እንደመናቅ እሚያም ነገር ባይኖርም ባተላይ ህመሙ መዳኒት መጥፋቱ እንደተ ናክ ሲገባህ ክፉኛ አቃጠለህ ለስደትም ዳረገህ‼️ በመጨረሻ ላስታውስህ የማይነካ ባትነካ በጣም ይሻልሀል አጸፋውን መቋቋም አትችል‼️ ምናልባት ካለህ ግርጭ ርጭ ፀባይህ ግንፍለተኝነትህ ይነሳብህና በጥገኝነት ከምትኖርበት ቡድን ጋር ትጣላ ለህ‼️ 🍃👉https://t.me/abujemila25 🍃👉https://t.me/abujemila25 🍃👉https://t.me/abujemila25

ያ አባ ሙዓዝ በል በነካ እጅህ የሸይኽ ሙሐመድ ሐሚዲንን ደረሳ (ሸይኽ አቡ ዘርን)ም ኢኽዋን/ሙመይዕ በልልኝማ ጎሽ የኔ ጎበዝ። ወይንስ በደንብ እንድታምነኝ ቪድዎውን ልላክልህ? ለነገሩ ባለፈው ሸይኽ
ያ አባ ሙዓዝ በል በነካ እጅህ የሸይኽ ሙሐመድ ሐሚዲንን ደረሳ  (ሸይኽ አቡ ዘርን)ም ኢኽዋን/ሙመይዕ በልልኝማ ጎሽ የኔ ጎበዝ። ወይንስ በደንብ እንድታምነኝ ቪድዎውን ልላክልህ? ለነገሩ ባለፈው ሸይኽ ሰዒድ አሐመድ ሙስጦፋ ላይ የቀራበትን ልኬልህ የለ? ፈተዋህ ግን አልደረሰኝም እሳ‽ ይልቁንስ አንተ ምንም ነገር አያምርብህም ዝም ብለህ ብትቀመጥ ይሻልሃል የቋጠርኩትን ሁሉ እንዳታስፈታኝ። አቡ ዑበይዳ t.me/AbuOubeida

🪶የሁኔታዎች መቀየያየር በዱኒያ ህይወት የሚጠበቅ ነው! ስለ አኼራ ጉዳዮች ሲወራ ኢማንህ እንደሚጠነክረው ሁሉ ከዚህ በተቃራኒ ሲሆን ደግሞ ስሜቱ ሌላ ነው! ሁሌም ቢሆን ግን ኢማንህን በሚያጠነክሩ ነ
🪶የሁኔታዎች መቀየያየር በዱኒያ ህይወት የሚጠበቅ ነው! ስለ አኼራ ጉዳዮች ሲወራ ኢማንህ እንደሚጠነክረው ሁሉ ከዚህ በተቃራኒ ሲሆን ደግሞ ስሜቱ ሌላ ነው! ሁሌም ቢሆን ግን ኢማንህን በሚያጠነክሩ ነገሮች ላይ ታገል!! ከሐንዘላ አል-ኡሰይዲ (🤎) ተይዞ: እንዲህ ይላሉ፦ ﴿نَافَقَ حَنْظَلَةُ يَا رَسُولَ اللَّهِ. فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: "وَمَا ذَاكَ ؟" قُلْتُ: يَا رَسُولَ اللَّهِ، نَكُونُ عِنْدَكَ تُذَكِّرُنَا بِالنَّارِ وَالْجَنَّةِ، حَتَّى كَأَنَّا رَأْيُ عَيْنٍ، فَإِذَا خَرَجْنَا مِنْ عِنْدِكَ عَافَسْنَا الْأَزْوَاجَ وَالْأَوْلَادَ وَالضَّيْعَاتِ، نَسِينَا كَثِيرًا. فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: "وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، إِنْ لَوْ تَدُومُونَ عَلَى مَا تَكُونُونَ عِنْدِي، وَفِي الذِّكْرِ ؛ لَصَافَحَتْكُمُ الْمَلَائِكَةُ عَلَى فُرُشِكُمْ، وَفِي طُرُقِكُمْ، وَلَكِنْ يَا حَنْظَلَةُ، سَاعَةً وَسَاعَةً" ثَلَاثَ مَرَّاتٍ﴾ “ሐንዘላ መናፍቅ ሆነ እኮ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አልኩኝ። የአላህ መልእክተኛም (🤎)፦ ‘ምንድን ነው ነገሩ? (ምን አጋጠመህ?)’ አሉ። እኔም፦ ‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ከአንተ ዘንድ ስንሆን እሳትና ገነትን ታስታውሰናለህ፤ ልክ በአይናችን የምናያቸው ያህል እንሆናለን። ከእርስዎ ዘንድ ወጥተን ወደ ሚስቶቻችን፣ ልጆቻችን እና ንብረቶቻችን ስንቀላቀል ግን ብዙ እንረሳለን (የቀድሞው ልባዊ ስሜት ይቀንሳል)’ አልኩኝ። የአላህ መልእክተኛም (🤎) እንዲህ አሉ፦ ‘ነፍሴ በእጁ በሆነችው አምላክ እምላለሁ! ከእኔ ዘንድ ባለችሁበት ሁኔታ እና በዝክር (በአላህ ማስታወስ) ላይ ሁልጊዜ ቢቀጥል ኖሮ መላእክቶች በአልጋችሁ ላይ እና በመንገዳችሁ ላይ በጎበኟችሁ (በጨበጧችሁ) ነበር። ነገር ግን ሐንዘላ ሆይ! ሁኔታችን አንዴ ለዚህ (ለተለያዩ የዱኒያ ህይወት ግዴታዎች)፣ አንዴ ለዚያ (ለዒባዳ) ሊሆን ይገባል ይህንንም ሶስት ጊዜ ደገሙት።’” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 2750 ➖➖➖➖➖➖➖ ✅️ በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦ 📱 Telegeram 📱 Whatsup 📱 Facebook  📱 Instagram 📱 X 📱 Youtube 📱 Tik tok

አዲስ የተጀመረ ደርስ ክፍል 01 ሙንከራቱን ሻኢዐህ #አዘጋጁ_የተከበሩት_ሸይኽ_ሙሐመድ_ብኑ_ሒዛም_ሐፊዞሁሏህ ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ ደሴ 🕌 ጅብሪል ጎራ መስጅድ የደርሱ አቅራቢ 🎙Abu Useymin Ibnu Shfi ሶፍት ኮፒውን ለማግኘት፦ t.me/Ezedin_Ibnu_Shafi/11108 የቴሌግራም ቻናል፦ ¤t.me/Ezedin_Ibnu_Shafi

አስር ምክሮች ለሙስሊም መምህራን ~~ ① ሃላፊነት ይሰማህ። የምትገነባው ትውልድ ነው። የምታስተላልፈው ነገር እጅግ ውድ ነው። "ሃላፊነት የሚሰማው ሰው እራሱን እንደ ህዝብ ንብረት አድርጎ ይቆጥራል።" ② የሚያዩህ፣ ምሳሌ የሚያደርጉህ አሉና ተጠንቀቅ። ክፉ ምሳሌ እንዳትሆን። ከባህሪህ፣ ከገፅታህ፣ ከአቀራረብህ ሰዎች ይማሩ ዘንድ መልካም ሁን። ③ ፍትሃዊ ሁን። አንዱ ባጠፋው በጅምላ አትቅጣ። በጥቂቶች ጥፋት ተማሪዎችን በትምህርት፣ በፈተና አትቅጣ። በበደለኛ አስተማሪዎች ሳቢያ ስንቶች ትምህርት አቋርጠዋል?! ስንቶች የተወሰኑ የትምህርት አይነቶችን ጠልተዋል። የስንቶች ውጤት ተበላሽቶ  ሞራላቸው ተነክቷል። "የትምህርት ተቋማት በሰፊው ስለ መብት የሚቀነቀንባቸው፣ ብዙ ጭቆና የሚፈፀምባቸው የግፍ አፀዶች ናቸው።" ④ ልዝብ ሁን አታስበርግግ። ቁጥብ ሁን አትባልግ። ትሁት ሁን አትጨፍግግ። የቸገረው ሊያዋይህ የማይፈራህ፣ የከበደው ሊጠይቅህ የማይሰጋህ፣ ያበጠበት የማይደፍርህ ሁን። ሚዛንህን ጠብቅ። ለሁሉም የሚገባው ቋንቋ ይኑርህ። ⑤ ክፋትን፣ ዘረኝነትን አትመግብ። ትውልድ አትመርዝ። በአሁኑ ሰዓት ዘረኝነት ከገበሬው ይልቅ ምሁሩ ጋር ጎልቶ የሚታይበት ምክንያቱ አርቀው ማየት የማይችሉ የተማሩ መሀይማን በመብዛታቸው ነው። ⑥ ብቁ ሁን። እራስህን በእውቀት ገንባ። ተዘጋጅተህ ወደ ክፍል ግባ። ካልሆነ ትናቃለህ። ካልሆነ ሃላፊነትህን በአግባቡ አትወጣም። ካልሆነ ልበ ሙሉነት /confidence/ ታጣለህ። የምትስሰለች ሳይሆን ልብ የምታንጠለጥል፣ የምትናቅ ሳይሆን የምትወደድ፣ የምትፍፈራ ሳይሆን የምትከበር ሁን። ⑦ ለችግር ደራሽ ሁን። የተማሪ ችግር ይግባህ። የጤና፣ የኢኮኖሚ ችግር ያለበት፣ ቤተሰባዊ ቀውስ ያጋጠመው፣ ስነ ልቦናው የተጎዳ፣ ልቡ በሀዘን፣ በጉዳት የተሰበረ ይገጥማልና በምትችለው አግዝ። "አይዞን"፣ "አብሺር" ማለት ለተጎዳ ሰው ዋጋው ትልቅ ነው። ⑧ ቂመኛ አትሁን። ያለፍክበትን ያላለፉ፣ ነገን አሻግረው የማያዩ ጨቅላዎች ጋር ቂም አትጋባ። ከተማሪ ጋር እልህ ውስጥ አትግባ። ተማሪህ የሚናገረውን፣ የሚጠይቀውን ሁሉ በክፉ አትተርጉም። ⑨ ጥንቃቄ ይኑርህ። በአነጋገርህ፣ በአቀራረብህ፣ በሁለ ነገርህ ጥንቃቄ አይለይህ። በምታስተምራቸው ተማሪዎች ቁጥር ልክ በየቤቱ አጀንዳ እንደሆንክ ልብ በል። በክፉ ወይም በበጎ በየቤቱ ትነሳለህ። ከረጅም አመታት በኋላ ዛሬም ድረስ በክፉ ወይም በበጎ የማንረሳቸው አስተማሪዎች አሉ። ለሰዎች ከልብ የማይጠፋ ክፉ ትዝታ አትሁን። (10) ለዲንህ ዋጋ ስጥ። ዲንህን ስታውቅ ለተማሪዎችህ መልካም ምሳሌ ትሆናለህ። ዲንህን ስታውቅ የተሳሳተ አስተምህሮ ለተማሪዎችህ አትመግብም። መጠናቸው ቢለያይም ሁሉም የትምህርት አይነቶች ውስጥ ከዲን ጋር የማይሄዱ ነገሮች ይገጥሙሀል። ንቁና ብቁ ከሆንክ እርምት እየሰጠህ ማለፍ ትችላለህ። = የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/IbnuMunewor

ኢብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁማ እንዲህ ይላሉ፦ التقوى أن لا ترى نفسك خيراً مـن أحد "ተቅዋ ማለት ራስህን ከማንም በላይ አድርገህ ላታይ ነው።" 📚 [ተፍሲሩል በገዊ ፡ 1/60] = የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor

​بسم الله الرحمن الرحيم ((ለእዉቀት ፈላጊወች በሙሉ አድስ ብስራት ከመርከዝ ኢብኑ ዐብ'ባስ (ONLINE) መደረሳ)) የዐረብኛ ቋንቋ ሰዋሰው (ነህዉ) የትምህርት መረሃ ግብር ፡የዐረብኛ
​بسم الله الرحمن الرحيم ((ለእዉቀት ፈላጊወች በሙሉ አድስ ብስራት ከመርከዝ ኢብኑ ዐብ'ባስ (ONLINE) መደረሳ)) የዐረብኛ ቋንቋ ሰዋሰው (ነህዉ) የትምህርት መረሃ ግብር ፡የዐረብኛን ቋንቋ ቁልፍ በሰለጠነና ጥልቅ መንገድ ይማሩ " ​📖 የሚቀራው ኪታብ፦ «الممتع في شرح الآجرومية» አል-ሙምቲዕ ፊ ሸርሒል አጅሩሚያህ) ​✍️ የኪታቡ ደራሲ፦ አቡ አነስ ማሊክ ቢን ሳሊም አል-መህዘሪ ​🎙 አስተማሪ፦ ኡስታዝ ኸድር አህመድ አል ኸሚሴ ሀፊዘሁሏሁ ተአላ ​💡 በኮርሱ ምን ያገኛሉ? 🔹 የዐረብኛ ቋንቋ ሰዋሰው (ነህው) መሠረቶችን በቀላልና ግልጽ አቀራረብ። 🔹 ኪታቡን በብቃት ከመረዳት አንጻር ሰፊና ጥልቅ ማብራሪያ። 🔹 ለጀማሪዎችም ሆነ እውቀታቸውን ለማዳበር ለማጠናከር ለሚፈልጉ ሁሉ የሚመጥን አሰላለፍ። ​📝 አሁኑኑ ይመዝገቡ! ለዚህ ውብ የዕውቀት ዕድል ቀድመው በመመዝገብ ቦታዎን ያስይዙ! ​📲 ለመመዝገብ እና በቂ መረጃዎችን ለማግኘት 👉 @Hussein_cod018 👉 +966538936875 ​📌 ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት የኸይር ሥራ ተካፋይ ይሁኑ! https://t.me/UstazKedirAhmed https://t.me/UstazKedirAhmed

✨ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ (DDUMSJ) ✨ السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🌟 እንኳን ደስ አላችሁ ውድ አዲስ ገቢ ተማሪዎች! 🌟 ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ
✨ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ (DDUMSJ) ✨ السلام عليكم ورحمة الله وبركاته 🌟 እንኳን ደስ አላችሁ ውድ አዲስ ገቢ ተማሪዎች! 🌟 ወደ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እንኳን በሰላም መጣችሁ እያልን፤ እቃ ከመቀበል ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍና መመሪያ ለመስጠት የአቀባበል ቡድናችን ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቆ እየጠበቃችሁ ይገኛል። አስቀድመን መረጃችሁን አውቀን የተሟላ አቀባበልና ድጋፍ እንድናደርግላችሁ፣ ከታች ያለውን የምዝገባ ቅጽ (form) እንድትሞሉ በአክብሮት እንጠይቃለን። 👉 የምዝገባ ፎርም ሊንክ፦ https://forms.gle/StTFLPABmgbLRkB3A 🗓 የቅበላ ጊዜ፦ ጥቅምት 7 እና 8 ቀን (ከዚህ ቀን ቀደም ብላችሁም ሆነ በተለያዩ ምክንያቶች ዘግይታችሁ የምትመጡ ተማሪዎችንም ጀመዓችን በተሟላ ሁኔታ የሚያስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን።) 📞 ለግንኙነትና ድጋፍ የስልክ ቁጥሮች፦ ወደ ግቢ ስትመጡ መረጃ ለመጠየቅም ሆነ እንድንቀበላችሁ የሚከተሉትን ወንድሞች ማግኘት ትችላላችሁ፡ • Furkan Jemil - 0968278025 • Selehadin Muzemil - 0983048814 • Hamza Safi - 0963799603 • Amir Mahdi - +251975984541 • Ibrahim Jemal - 0976710967 🔴ለእህቶች፦ የእህቶችን ስልክ ለማግኘት ወንድሞች ጋር በዚህ 0968278025 ስልክ በመደወል ማግኘት ትችላላችሁ 📢 ይህ መረጃ ላልደረሳቸው አዲስ ገቢ ወንድሞችና እህቶች ሼር (Share) በማድረግ ተባበሩን። ስለ ጀመዓው ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡ 👉 [https://t.me/DDUMSJofficialpage] 🤲 አላህ በሰላም ያገናኘን፤ መልካም የትምህርት ዘመን ይሁንላችሁ! ©️ DDUMSJ

በህይወት ምክንያትና ውጤት ብዙ አትገረም።  ከተስፋ ቢስ ማህፀን ድል ሊወለድ ይችላል። ከነብስ ጠላትህ  አስገራሚ ስጦታ ሊመጣልህም ይችላል። ምናልባት ፀጋና ሰላምን ልታገኝ  ዘንድ በመከራ ድልድይ ላይ ማለፍህ የግድ ይሆናል። ባለመኖር ምክንያቶች ውስጥ መኖርን ልትረዳው ትችላለህ። እና በቃ በህይወትህ ውስጥ ለክስተቶች አትገረም። t.me/abdu_rheman_aman t.me/abdu_rheman_aman

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ውድ የአል-ሂሒዳያ ቤተሰቦች 👉 ዛሬ እሁድ 🌆ምሽት 🌃 3:00:3:30
👉አድስ ደርስ
🔷የኪታቡ ስም       
🔘شرح لمعة الإعتقاد للعلامة العثيمين
🔷የደርሱ አቅራቢ      
🔘 حسين علي
🔷የኪታቡ pdf 👇👇 https://t.me/HawassaUniversityAlumniSunaJamaa/26478 🔷ደርሱ የሚተላለፍበት ግሩፕ 👇👇👇🔘https://t.me/HawassaUniversityAlumniSunaJamaa

ስለ ለተሞ { አ/ልሀሚድ አልለተሚይ ቡድን } የተደረጉ በውድ እና በሱና ኡስታዞች  ሙሓደራወች ስብሰብ በቀላሉ ለማገኘት👇👇👇👇👇👇
የተለያዩ መሳጭ ዳእዋወች ርዕሶቹ ከዚህ በታች ናቸው ርዕሱን አንዲ ብቻ በመካት  ማዳመጥ ይችላሉ
❶የለተሞ ቡድን እና ኢብኑ መስኡዶች ጉዳይ ❷የለተሞ ውሸት ➌ኡ/ዝ ሳዳትና ኢብኑ ሙነወር ሱናን የኻለፍባቸው የቱ ➍ረድ በሻኪር ሱልጣን ➎የመሻይኮችጀለሳ ይሂን ያዳመጥብዥታአይገባውም ➏የሱና መፅሀፎችን ማቃጠል ➐በኡ/ዝ ኸድር እና አቡ ዘር መካከል የተደረገ ውይይት ➑እየው ሲላተምበት ➒ለተሞ አባጋራ ➓ ቡድንተኝነት ቅጥ ከማሳጣቱም በላይ ሐቅ ያሳጣል ❶❶ለተሞ ኡ/ዝ ሳደት እና ኢብኑ ሙነወር ሲሳደብ ❶❷በእውር ድብር የሚጓዘው የለተሞ ቡድን በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ክፍል 🥇ለቅጥፈት አራጋቢዎች ክፍል 🥈ስለ ኢልዛም ረድ በወሰን ተላላፊዎች ላይ
በኡስታዝ ኸድር አህመድ  አል ኬሚሴ ሀፊዘሁሏህ
ክፍል ❶ የአ/ልሀሚድ አልለተሚይ ስህተቶች ክፍል ❷ የአቡዘር ስህተቶች እና ግጭጭቶች ክፍል ➌ለከት የሌለው የተገጫጨ ንግግራቸውን ክፍል ➍ እውነት የአቋም ለውጥ የተከሰተው ከማን? ክፍል ➎ አ/ልሀሚድ መረጃዎች ያለቦታቸው እየደረደረ ክፍል ➏ አ/ልሀሚድ የዑሰይሚን የአልባኒይ ተማሪ❓ ክፍል ➐ አ/ልሀሚድ ከወደቀባቸው ስህተቶች ውስጥ ክፍል ➑አ/ልሀሚድሙጅተሂድ እናኢጅቲሀድከበደው ክፍል ➒ የአ/ልሀሚድ ነጫጭ ውሸቶችን ማጋለጥ ክፍል ➓ አ/ልሀሚድ የሱፍያን ተግባር የፈፀመ ነው ረድ በ ሁሰይን ሙሀመድ አስልጢይ ላይ
ሚያመጣቸው ማምታቻዎች እና ማደናገሪያዎችን ግልፅ ማድረግ   !!!
በኡስታዝ ኸድር አህመድ  አል ኬሚሴ ሀፊዘሁሏህ
ክፍል ❶ ክፍል ❷ ክፍል ➌ ክፍል ➍ ክፍል ➎ ክፍል ➏ ክፍል ➐ ክፍል ➑ ክፍል ➒ ክፍል ➓ ረድ በሸይኽ  በአቡዘር ላይ
ሸይኽ ሙሓመድ አሚን ላይ ላደረገው ንግግር የተሰጠመልስ
በኡስታዝኸድር አህመድ  አል ኬሚሴ ሀፊዘሁሏህ
ክፍል 🥇 ሸይኽ አቡዘር ከ ኢኽዋኖች የወረሰው አቋሙ ክፍል 🥈 የሱና ሰው ማስወጣት እና ኢብኑ መስዑዶችን ክፍል 🥉ከሙብተዲዕ ጋር መቀማመጥ አስመልክቶ

"ሰለፊይ ወንድሜ በአቋምህ ፅና"     ✒️   ሐቅን መንገድህ ስታደርግ ከተለያየ አቅጣጫ የተለያየ ትችት ፣ ተቃውሞና  ትንኮሳ መምጣቱ አይቀሬ ጉዳይ ነው።  አንተ ግን ወደ ቀኝ ወደ ግራ ሳትዟዟር በአቋምህ ላይ መፅናት ይኖርብሃል ምክኒያቱም የያዝከው መንገድ የነብያቶች መንገድ ነው።      ረሡል ዓለይሂ ሶላቱ ወሰላም ዉሸታም ፣ ደጋሚ ፣ እብድ  መባላቸውን  ካወቅክ አንተን አሕባሹ ዉሃቢይ ፣ ሙጀሲም ፣ ሙሸቢህ የሚል ስም ቢያወጣልህ ፤ የዲን ሸፍጠኛው የኢኽዋንና የሙመዪዕ መንጋ ሙተሸዲድ እና ጥራዝ ነጠቅ ቢልህ ፤ ጅህልናን ቀሚስና ጥምጣም ያደረገው የተክፊር ወንበዴ ሙርጂኣዎዎች ብሎ ቢወርፍህ ፤ የእውር ድምብር ጉዞን የመረጠው የሐጁሪ መንጋ ጀምዕዮዮዮች እያለ ቢጮህ ፤ አጉል ወገንተኚነት ያውወረው የለተሞ መንጋ በሌለህበት አዲሶቹ ሙመዪዖዖዖች እያለ ቢያቅራራና ቢቀጥፍብህ ቅንጣት እንዳይደንቅህ !!!     ምክኒያቱም አንተ በሐቅ ላይ ነህ። ሐቅን እስካልለቀክ ድረስ ይህ ሁሉ ትችትና የስም ልጠፋ እንደማይቀርልህ አስረግጨ እነግርሃለሁ። ከዚህም ባለፈ አካል እና ህይወትህ ላይ አደጋ ሊደርስብህ ሁሉ ይችላል። አንተ ግን በአቋምህ ፅና ኢማሙ አሕመድ ረሒመሁሏህ ተዓላ  "ቁርኣን የአሏህ ቃል ነው"  በማለታቸው ብቻ ነበር ለሶስት ዘመነ መንግስታት በእስርና በግርፋት የተሰቃዩት።     ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁሏህ ትክክለኛውን የነብዩን ሶለሏህ ዓለይሂ ወሰለም እና ሶሐቦች መንገድ በማስረጃ የበላይ በማድረጋቸው ብቻና ብቻ ነበር ለበርካታ ጊዜ ለእስር የተዳረጉት በመጨረሻም እዛው እስር ቤት የሞቱት።     ስለዚህ አንተም የነእርሡን መንገድ መንገድ እስካደረክ ድረስ በነእርሱ ላይ የደረሰው በአንተም ላይ መድረሡ አጠራጣሪ አይደለምና በአቋምህ ፅና አዎ ሁሌም በአቋምህ ፅና። የሡና ወንድምህ አቡ ዒምራን መጋቢት 4 / 2016 t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy