en
Feedback

Don't get caught by a cheater! Telemetrio finds and tags such channels 👉 If you want to see the tag, subscribe

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Open in Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Show more
The country is not specifiedThe category is not specified
914
Subscribers
-324 hours
-177 days
+5330 days
Posts Archive
Repost from N/a
🥀አድስ ወሳኝ ግጥም 🎙 ርዕስ✈ሶባ ድመቂልን✈ ሽርኮችሽ ይውደሙ ባጢል አይቅረብሽ ፧አርባጫማም፧ ይቁም ፧አድሩስ ፧አይምጣብሽ ፧ላይ ሶባም፧ይነሳ አይነግድ በስምሽ ፧ማይበርም፧ ይቋረጥ ይተውት ህዝቦችሽ ፧ንጉስም፧ ይረሳ ይብዙልን ጀግኖችሽ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ 🎤በወንድም አቡ ሹራ አህመድ ኢብኑ ካሳየ አሶብይ(ሀፊዘሁላህ) ------------------------------------------------------------------------------------------------------------------ ✨የግጥሙን ሙሉ ፅሁፍ ለማገኘት https://t.me/Sobabilalmesjid https://t.me/Sobabilalmesjid ✈️የሶባ አህሉሱነቲ ወልጀመአህ የቴሌግራም ቻናል ነው ተቀላቀሉ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://t.me/Sobabilalmesjid https://t.me/Sobabilalmesjid

📌كثيرٌ من الشباب يسأل نفسه: ما هو المشروع الذي سأكرس له سنوات عمري؟ والجواب عن هذا السؤال أخطر من السؤال عن الوظيفة، أو الراتب، أو التخصص. لأن الإنسان قد ينجح في مشروعه... ثم يكتشف بعد عشرين عامًا أنه كان يصعد السلم الخطأ. لقد أصبحنا نعيش في زمنٍ يُعظِّم كل مشروع يحقق الشهرة، أو المال، أو كثرة المتابعين، حتى أصبح بعض الشباب يظن أن قيمة المشروع تُقاس بحجم الضجيج الذي يحدثه. لكن القرآن يعلِّمنا معيارًا آخر. قال الله تعالى: إِنَّا لَا نُضِيعُ أَجْرَ الْمُصْلِحِينَ تأمل... لم يقل: الناجحين. ولم يقل: الأغنياء. ولا قال: المشهورين. بل قال: ﴿الْمُصْلِحِينَ﴾. وكأن القيمة الحقيقية لأي مشروع ليست فيما يعود على صاحبه وحده، بل فيما يتركه من خيرٍ في حياة الناس. ولهذا، فإن المشروع الشبابي الحق لا يبدأ بسؤال: كيف أصبح معروفًا؟ بل يبدأ بسؤال: أيُّ ثغرٍ يحتاجني؟ فقد يكون ثغرك تعليم طفل. أو إصلاح أسرة. أو بناء مؤسسة نافعة. أو نشر علم. أو علاج مريض. أو إنشاء مشروع يوفر فرص عمل للشباب. أو الدفاع عن قيمةٍ أخلاقية بدأت تضعف في المجتمع. فالرسالة لا تُقاس بحجمها في أعين الناس، وإنما بصدقها، وبقدر ما تدفع شرًّا أو تجلب خيرًا. وليس كل مشروعٍ كبيرٍ عظيمًا... كما أن كثيرًا من المشروعات الصغيرة غيّرت وجه التاريخ. لقد بدأ تعليم النبي ﷺ في دار الأرقم بعددٍ قليل من الرجال... لكن الله غيّر بهم العالم. ولم يبدأ الإصلاح الإسلامي بحشودٍ غفيرة... بل بقلوبٍ امتلأت بالوحي، ثم حملت همَّ الناس قبل همِّ نفسها. ولهذا، فإن أخطر ما يواجه الشباب اليوم ليس قلة الفرص... بل كثرة المشاريع التي تستهلك أعمارهم، ولا تترك بعدهم أثرًا. إن العمر أقصر من أن يُنفق في مطاردة كل جديد. وأثمن من أن يُستهلك في صناعة صورةٍ براقة لا تخدم حقًا، ولا ترفع باطلًا. فإذا أراد الشاب أن يعرف قيمة مشروعه، فليسأل نفسه سؤالًا واحدًا: لو متُّ غدًا... ماذا سيبقى من هذا المشروع؟ فإن كان سيبقى علمٌ يُنتفع به، أو إنسانٌ أصلحته، أو قيمةٌ أحييتها، أو بابُ خيرٍ فتحته... فذلك مشروعٌ يستحق أن يُعاش له. أما ما ينتهي بانتهاء صاحبه... فهو تجارةٌ مع الزمن، لا رسالةٌ للحياة. د. عبد الكريم بكار

لا تترك الحق من أجل الناس، بل اترك الناس من أجل الحق. «ለሰዎች ብለህ ሐቅን ነገር አትተው! ለሐቅ ብለህ ግን ሰዎችን ተዋቸው።»

[هل تعرف من هم الغرباء الذي ورد فيهم حديث طوبى للغرباء ؟ ] قال الإمام الآجري عليه رحمة الله : أغرب الغرباء في وقتنا هذا من : ١ - أخذ بالسنن وصبر عليها ٢ - وحذر البدع وصبر عنها ٣ - واتبع آثار من سلف من أئمة المسلمين ٤ - وعرف زمانه وشدة فساده وفساد أهله فاشتغل بإصلاح شأن نفسه من حفظ جوارحه ٥ - وترك الخوض فيما لا يعنيه ٦ - وعمل في إصلاح كسرته ٧ - وكان طلبه من الدنيا ما فيه كفايته ٨ - وترك الفضل الذي يطغيه ٩ - ودارى أهل زمانه ولم يداهنهم !! ١٠ - وصبر على ذلك فهذا غريب من يأنس إليه من العشيرة والإخوان قليل ولا يضره ذلك [ الغرباء للآجري ص ٧٩]

በእርግጥም ተኩላ ስለ ታማኝነት ብዙ ያስተምረናል።» ጠቢባን ህይወትህን እንደ ተኩላ መምራት/መኖር አለብህ ለምን እንደሚሉ ታውቃለህን? ምክንያቱም ተኩላ በሌሎች ፍጥረታት ዘንድ እምብዛም በማይገኙ ልዩ ፀባያት ተለይቶ ይታወቃል፦ አንደኛ፡ እንደ አንዳንድ እንስሳት ሰርከስ ውስጥ ትርኢት ሲያሳይ ተኩላን በጭራሽ አታየውም። ምክንያቱም ተኩላ ክብሩን ይጠብቃል፤ መዋረድና መዋረድን ፈጽሞ አይቀበልም። ሁለተኛ፡ ተኩላ ከእናቱ ወይም ከእህቱ ጋር አይጋባም። ይልቁንም የህይወት አጋሩን በጥንቃቄ ይመርጣል፤ በህይወት ዘመኑም ሙሉ ለእሷ ታማኝ ሆኖ ይኖራል። ሴቷም ተኩላ እንዲሁ ታደርጋለች። ከሁለቱ አንደኛው ቢሞት፣ በሌላኛው ላይ ቢያንስ ከሶስት ወር የማያንስና እስከ ሙሉ አመት ሊቆይ የሚችል የሃዘን ጊዜ ውስጥ ይገባል። ሶስተኛ፡ ተኩላ ‘ታዛዥ/ደጋግ ልጅ’ ተብሎ ይጠራል፤ ምክንያቱም ወላጆቹን የሚያከብር ብቸኛ እንስሳ ነው። ወላጆቹ አርጅተው ማደን ሲያቅታቸው፣ ወጣቶቹ ተኩላዎች ኃላፊነት ይወስዱላቸዋል። ወጥተው አድነው ምግቡን ይዘውላቸዋል ይመለሳሉ። https://t.me/kuruhara040 https://t.me/kuruhara040

እኮ የእኔንም ጥያቄ እየመለስክልኝ? አትለፈኝ እንጂ‽ ወንዝ ተሻግረህ ከምትወረውር እዛው እስርህ ካሉት ጀምር እንጂ ያ አባ ሙዝ! ነው ፊርማህን እንዳይቀዱት ፈራሃቸው? አረም የሚነቀለው ከግር ስር ጀ
እኮ የእኔንም ጥያቄ እየመለስክልኝ? አትለፈኝ እንጂ‽ ወንዝ ተሻግረህ ከምትወረውር እዛው እስርህ ካሉት ጀምር እንጂ ያ አባ ሙዝ! ነው ፊርማህን እንዳይቀዱት ፈራሃቸው? አረም የሚነቀለው ከግር ስር ጀምሮ ነው አለቃ! እየነቃህ! እኔ ግን ተው ይቅርባችሁ ብያለሁ፡ ከዚህ በኋላ እንኳን አፍራችሁና አርፋችሁ አትቀመጡም ወይ፡ ሰማሃኛ ከዚህ በኋላ ያለው ጉዞ ለራሳችሁ ነው የሚጨንቃችሁ እናንተ ስራ ጨርሳችኋል የቀረው የእኛ ነው። እርሱም ለሌሎች በቆፈራችሁት ጉርጓድ ውስጥ እየሳቡ ማስገባት!! አቡ ዑበይዳ t.me/AbuOubeida

​በእስልምና ፍቅር በራሱ ወንጀል አይደለም! በእስልምና ፍቅር በራሱ #ወንጀል አይደለም። ምክንያቱም የሰው ልጅ ልብ ውስጥ የሚፈጠር ተፈጥሯዊ ስሜት ነው። አላህ ልባችንን ሲፈጥረው የመውደድ እና የመፈለግ ባህሪ አድርጎበታል። ​ከእነርሱ ዘንድ እንድትረጉ (እንድታርፉ) ከራሳችሁ ሚስቶችን ለእናንተ መፈጠሩ፣ በመካከላችሁም ውዴታንና እዝነትን ማድረጉ ከምልክቶቹ ነው።ሱረቱ አር-ሩም    ​ይህ የሚያሳየው እውነተኛ ፍቅር«መተሳሰብ እና መረጋጋት» እንጂ ልብን የሚያስጨንቅ እና አላህን የሚያስረሳ መሆን እንደሌለበት ነው። ነቢዩ ﷺ ስለ ባለቤታቸው ኸዲጃ ሲናገሩ እንድህ ይላሉ፦​እኔ የእርሷ ፍቅር (ከአላህ ዘንድ) ተሰጥቶኛል። ሙስሊም ዘግበውታል። ይህ የሚያሳየው ንፁህ
እና
ሸሪዐዊ የሆነ ፍቅር ከአላህ የሚሰጥ ውድ ስጦታ መሆኑን ነው። ​ፍቅር ሀራም የሚሆነው ስሜቱ በራሱ ሳይሆን ስሜቱን የምናስተናግድበት መንገድ እና ወሰን ማለፋችን ነው።​ከጋብቻ ውጭ ያለ ያልተገደበ ግንኙነት፡ ሁለት የሚቀራረቡ ወንድ እና ሴት ያለ ኒካህ የሚያደርጉት የፍቅር ግንኙነት፣ ምስጢራዊ ንግግር እና ቀጠሮ አላስፈላጊ ንክኪ እና የልብ ቁርኝት ወደ ወንጀል ስለሚመራ ሀራም ነው። ​አላህእንዲህ ይላል፦ ወደ ዝሙትም አትቀርቡ እርሱ መጥፎ ስራ ነውና መንገድነቱም ከፋ።ሱረቱ አል-ኢስራዕ አላህ «ዝሙት አትስሩ» ብቻ አላለም «ወደ እሱ አትቀርቡ» ነው ያለው። ፍቅረኝነት ደግሞ ወደ ዝሙት የሚያደርስ ዋነኛ መንገድ ነው። ​አላህን የሚያስረሳ ፍቅር፡ አንድ ሰው የሚያፍቀረውን/ የምታፍቅረውን ሰው ከአላህ አስበልጦ ሲወድ ለዚያ ሰው ሲል ሶላቱን ሲተው ወይም አላህ የከለከለውን ነገር ለማስደሰት ሲል ሲፈጽም ያ ፍቅር ሀራም ይሆናል። ​ከሰዎችም አላህን ትተው ጣዖታትን እንደ አላህ የሚወዷቸው አድርገው የሚይዙ አሉ እነዚያ ያመኑት ግን አላህን በመውደድ በኩል በጣም የበረቱ ናቸው።ሱረቱ አል-በቀራህ። ​ሸሪዐው ለአንድ ሰው ልብ ቢንጠለጠል እና ቢወድ ሶስት ዋና ዋና መፍትሂዎች ይኖሩታል፦ ​1.ኒካህ ​ነቢዩ ﷺለተዋደዱ ሁለት ሰዎች ከጋብቻ ውጭ የሚበጃቸው ነገር እንደሌለ ነግረውናል፦ ለተዋደዱ ሁለት ሰዎች እንደ ጋብቻ ያለ መፍትሔ አልታየም። ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል አንድን ሰው ከወደድ በሩን መጥናት ወላጆቹን ማናገር እና በሃላል መንገድ መያዝ እንጂ ከጀርባ በሚደረግ ስሜታዊ ግንኙነት ጊዜን እና ልብን ማሳደፍ የለብንም። 2.የልብን ንጽህና መጠበቅ ​አንድ ሰው ለአንዲት ልጅ ልቡ ቢያደላ ነገር ግን ጋብቻውን ለመፈጸም አቅም ባይኖረው ስሜቱን ውጪ ማውጣት ሳይሆን አላህን በመፍራት እና በመታገስ ልቡን መጠበቅ አለበት። ​ነቢዩ ﷺ ወጣቶችን ሲመክሩ፦ ​እናንተ ወጣቶች ሆይ! ከእናንተ መካከል ማግባት የሚችለው ያግባ፤ ማግባት የማይችለው ግን ይጹም፤ ጾም ለእርሱ መከላከያ ነውና። ቡኻሪ እና ሙስሊም ይህ ለሁለቱም ትልቅ ሰላምን የሚሰጥ እና በሁለቱም መካከል ቀልብን የሚጠብቅ ከአላህ ያማያጣላ ነው። 3.በላጩ ፍቅር ​በዓለም ላይ ካሉ ፍቅሮች ሁሉ ልብን የሚያረካው እና ዘላቂው ለአላህ ብሎ መዋደድ ነው። ​ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ​አላህ በትልቁ የቂያማ ቀን እንዲህ ይላል፡- በእኔ ታላቅነት ምክንያት የተዋደዱት ሰዎች የት አሉ? ዛሬ ከእኔ ጥላ ውጭ ምንም ጥላ በሌለበት ቀን በ ጥላዬ ስር አጥላቸዋለሁ። ሙስሊም ዘግበውታል ስለዚህ አንዲትን ልጅ ብንወድ እሷን ወደ ሀራም አስፈላጊ ነገር ከመጥራት የተሻለው በሀላሉ መንገድ ተጉዞ ነገ በቂያም ቀን በአላህ ጥላ ውስጥ እንድትሆን እና ሸሪዐዊ ውዴታን መለገስ ነው። ​ንፁህ ፍቅር፡ በአላህ ወሰን ውስጥ ያለ ወደ ጋብቻ የሚያመራ ልብን የሚያረጋጋ እና አላህን የበለጠ እንድትወድ የሚያደርግ ነው። ​ሀራም ፍቅር፡ በአላህ ትዕዛዝ ላይ ያመጸ በምስጢር እና በኃጢአት የተሞላ ልብን በጭንቀት እና በቅናት የሚያቃጥል እንዲሁም መጨረሻው ጸጸት የሆነ ነው። ​ቀልብን ለአላህ ፍቅር አስቀድሞ መስጠት  አላህ ደግሞ ህይወትን የሚያበራ እና ልብህ የሚያረጥብ ሃላል አጋር በጊዜው ይሰጣል። كتبه الفقير إلى عفو ربه ابو عبدالله

​በእስልምና ፍቅር በራሱ ወንጀል አይደለም! በእስልምና ፍቅር በራሱ #ወንጀል አይደለም። ምክንያቱም የሰው ልጅ ልብ ውስጥ የሚፈጠር ተፈጥሯዊ ስሜት ነው። አላህ ልባችንን ሲፈጥረው የመውደድ እና የመፈለግ ባህሪ አድርጎበታል። ​ከእነርሱ ዘንድ እንድትረጉ (እንድታርፉ) ከራሳችሁ ሚስቶችን ለእናንተ መፈጠሩ፣ በመካከላችሁም ውዴታንና እዝነትን ማድረጉ ከምልክቶቹ ነው።ሱረቱ አር-ሩም ​ይህ የሚያሳየው እውነተኛ ፍቅር«መተሳሰብ እና መረጋጋት» እንጂ ልብን የሚያስጨንቅ እና አላህን የሚያስረሳ መሆን እንደሌለበት ነው። ነቢዩ ﷺ ስለ ባለቤታቸው ኸዲጃ ሲናገሩ እንድህ ይላሉ፦​እኔ የእርሷ ፍቅር (ከአላህ ዘንድ) ተሰጥቶኛል። ሙስሊም ዘግበውታል። ይህ የሚያሳየው ንፁህ እና ሸሪዐዊ የሆነ ፍቅር ከአላህ የሚሰጥ ውድ ስጦታ መሆኑን ነው። ​ፍቅር ሀራም የሚሆነው ስሜቱ በራሱ ሳይሆን ስሜቱን የምናስተናግድበት መንገድ እና ወሰን ማለፋችን ነው።​ከጋብቻ ውጭ ያለ ያልተገደበ ግንኙነት፡ ሁለት የሚቀራረቡ ወንድ እና ሴት ያለ ኒካህ የሚያደርጉት የፍቅር ግንኙነት፣ ምስጢራዊ ንግግር እና ቀጠሮ አላስፈላጊ ንክኪ እና የልብ ቁርኝት ወደ ወንጀል ስለሚመራ ሀራም ነው። ​አላህ እንዲህ ይላል፦ ወደ ዝሙትም አትቀርቡ እርሱ መጥፎ ስራ ነውና መንገድነቱም ከፋ።ሱረቱ አል-ኢስራዕ አላህ «ዝሙት አትስሩ» ብቻ አላለም «ወደ እሱ አትቀርቡ» ነው ያለው። ፍቅረኝነት ደግሞ ወደ ዝሙት የሚያደርስ ዋነኛ መንገድ ነው። ​አላህን የሚያስረሳ ፍቅር፡ አንድ ሰው የሚያፍቀረውን/ የምታፍቅረውን ሰው ከአላህ አስበልጦ ሲወድ ለዚያ ሰው ሲል ሶላቱን ሲተው ወይም አላህ የከለከለውን ነገር ለማስደሰት ሲል ሲፈጽም ያ ፍቅር ሀራም ይሆናል። ​ከሰዎችም አላህን ትተው ጣዖታትን እንደ አላህ የሚወዷቸው አድርገው የሚይዙ አሉ እነዚያ ያመኑት ግን አላህን በመውደድ በኩል በጣም የበረቱ ናቸው።ሱረቱ አል-በቀራህ። ​ሸሪዐው ለአንድ ሰው ልብ ቢንጠለጠል እና ቢወድ ሶስት ዋና ዋና መፍትሂዎች ይኖሩታል፦ ​1.ኒካህ ​ነቢዩ ﷺለተዋደዱ ሁለት ሰዎች ከጋብቻ ውጭ የሚበጃቸው ነገር እንደሌለ ነግረውናል፦ ለተዋደዱ ሁለት ሰዎች እንደ ጋብቻ ያለ መፍትሔ አልታየም። ኢብኑ ማጃህ ዘግበውታል አንድን ሰው ከወደድ በሩን መጥናት ወላጆቹን ማናገር እና በሃላል መንገድ መያዝ እንጂ ከጀርባ በሚደረግ ስሜታዊ ግንኙነት ጊዜን እና ልብን ማሳደፍ የለብንም። 2.የልብን ንጽህና መጠበቅ ​አንድ ሰው ለአንዲት ልጅ ልቡ ቢያደላ ነገር ግን ጋብቻውን ለመፈጸም አቅም ባይኖረው ስሜቱን ውጪ ማውጣት ሳይሆን አላህን በመፍራት እና በመታገስ ልቡን መጠበቅ አለበት። ​ነቢዩ ﷺ ወጣቶችን ሲመክሩ፦ ​እናንተ ወጣቶች ሆይ! ከእናንተ መካከል ማግባት የሚችለው ያግባ፤ ማግባት የማይችለው ግን ይጹም፤ ጾም ለእርሱ መከላከያ ነውና። ቡኻሪ እና ሙስሊም ይህ ለሁለቱም ትልቅ ሰላምን የሚሰጥ እና በሁለቱም መካከል ቀልብን የሚጠብቅ ከአላህ ያማያጣላ ነው። 3.በላጩ ፍቅር ​በዓለም ላይ ካሉ ፍቅሮች ሁሉ ልብን የሚያረካው እና ዘላቂው ለአላህ ብሎ መዋደድ ነው። ​ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ ​አላህ በትልቁ የቂያማ ቀን እንዲህ ይላል፡- በእኔ ታላቅነት ምክንያት የተዋደዱት ሰዎች የት አሉ? ዛሬ ከእኔ ጥላ ውጭ ምንም ጥላ በሌለበት ቀን በ ጥላዬ ስር አጥላቸዋለሁ። ሙስሊም ዘግበውታል ስለዚህ አንዲትን ልጅ ብንወድ እሷን ወደ ሀራም አስፈላጊ ነገር ከመጥራት የተሻለው በሀላሉ መንገድ ተጉዞ ነገ በቂያም ቀን በአላህ ጥላ ውስጥ እንድትሆን እና ሸሪዐዊ ውዴታን መለገስ ነው። ​ንፁህ ፍቅር፡ በአላህ ወሰን ውስጥ ያለ ወደ ጋብቻ የሚያመራ ልብን የሚያረጋጋ እና አላህን የበለጠ እንድትወድ የሚያደርግ ነው። ​ሀራም ፍቅር፡ በአላህ ትዕዛዝ ላይ ያመጸ በምስጢር እና በኃጢአት የተሞላ ልብን በጭንቀት እና በቅናት የሚያቃጥል እንዲሁም መጨረሻው ጸጸት የሆነ ነው። ​ቀልብን ለአላህ ፍቅር አስቀድሞ መስጠት  አላህ ደግሞ ህይወትን የሚያበራ እና ልብህ የሚያረጥብ ሃላል አጋር በጊዜው ይሰጣል። كتبه الفقير إلى عفو ربه ابو عبدالله

የኪታብ ደርስ ማስታወቂያ አሰላሙዓለይኩም ወረህመቱሏህ ወበረካቱህ !! በአላህ ፈቃድ በ2019 ኢ.አ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ የሚቀሩ ኪታቦች ዝርዝር በሚከተለው መልኩ ይሆናል፦ ١)
የኪታብ ደርስ ማስታወቂያ አሰላሙዓለይኩም ወረህመቱሏህ ወበረካቱህ !! በአላህ ፈቃድ በ2019 ኢ.አ በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ የሚቀሩ ኪታቦች ዝርዝር በሚከተለው መልኩ ይሆናል፦
١) الوجيز في عقيدة السلف الصالح «أهل السنة والجماعة»
የደርሱ አቅራቢ ኡስታዝ ሙሀመድ ሷሊህ
٢) منهج السالكين وتوضح الفقه في الدين
የደርሱ አቅራቢ ኡስታዝ ሙሀመድ ሷሊህ
٣) نواقض الإسلام
የደርሱ አቅራቢ ሀቢብ መህሙድ (ይሄኛው በወንድማችን ሀቢብ የሚሰጠው ደርስ  አድስ የተጠሩ ፍሬሽ ተማሪዎች ወደ ግቢ እስከሚገቡ አጠር ያለ ለጀማሪ የሚሆን ኪታብ ነው!! ፍሬሽ ተማሪዎች እንደገቡ አድስ ደርስ የሚጀመር ይሆናል ኢንሻአላህ ።) ኪታብ መግዛት የምትፈልጉ እና ያልተመዘገባችሁ ወንድሞች በአንድ ላይ አስመጥተን በቅርቡ ቂርአታችንን እንድንጀምር ስም እና የምትፈልጉትን ኪታብ  በ @Wdumstud ላኩልን ። እህቶች በእህቶች በኩል ምዝገባ እየተካሄደ ስለሆነ መመዝገብ ትችላላችሁ !! እውቀትን መፈለግ በሁሉም ሙስሊም ላይ ግደታ ነው!! ሁሉም ቂርአት የሚሰጠው ከፈጅር ሶላት በኋላ ይሆናል ኢንሻአላህ !!

ታላቁ ዛሂድና ዓሊም ፉደይል ብን ዒያድ 🤎ስለ እውነተኛ የዲን አዋቂ (ፈቂህ) ባህሪያትና ስነ-ምግባር ሲናገሩ እንዲህ አሉ፦
«እውነተኛ ፈቂህ የዲን አዋቂ ማለት፡-»
➣የአላህ ፍርሃት እንዲናገር ያደረገው! ➣​ፍርሃትም ዝም እንዲል ያደረገው ነው! ➣​ከተናገረ በቁርኣንና በሱና ይናገራል፣​ዝም ካለም በቁርኣንና በሱና (መመሪያ) ዝም ይላል! ➣​አንድ ነገር ከአልተረዳውና  ከተሸፈነበት ዘንድ ይቆማል አይቸኩልም! ➣​ወደ አሊም ወደሆነ አካልም ይመልሰዋል።
♥️طبقات الحنابلة [١٥٠/٢]
t.me/Ibnu_siraj_Alkemissie

ኢላሂ.......... እኔ ነኝ ያንተ ባሪያ ሆድ የባሰኝ እኔ ነኝ ደካማዋ ሀዘን የወረሰኝ እኔ ነኝ አላህዬ እንባ አይኔ ያራሰኝ እኔ እኮ ነኝ የኔ ጌታ አንተ የምታውቃኝ መሄጃ የለኝም አንተው ካልታረቅከኝ።

Repost from Dr. Seid Musa
🕌 የደሴ መስጂደ አስ-ሱና የእርዳታ ጥሪ! ዛሬ የምናበረክተው የነገውን የዕውቀት ብርሃን ለማስፋት  ነው! በአላህ ፈቃድ የሚተላለፍ የዒልም ብርሃን፤ ከዱንያ ሕይወታችን በኋላም የሚቀጥል ሰደቀተል ጃሪያ ነው! 📢 ለዓለም ዙሪያ ለምትገኙ ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በሙሉ የተላለፈ የኸይር ጥሪ! በደሴ ከተማ የሰለፊዮች ዐይን ፣ የሱና ብርሃን መፍለቂያ እና የቁርአንና የሸሪዓ ዕውቀት መማሪያ የሆነችው መስጂደ አስ-ሱና ዛሬ በእናንተ እገዛ የሚታሰብ ታሪክ ለመሥራት በር ከፍታለች! በቅርብ ጊዜ ይህ መስጂድ በትንሽ ቦታ፣ ቆርቆሮ በቆርቆሮ በትንሽ ቦታ ላይ ፣ በትንሽ አቅምና በታላቅ ተስፋ ተጀመረች። በሸይኽ መሐመድ መኪን መሪነት የተለያዩ ቂርኣቶች፣ የዳዕዋ ፕሮግራሞች፣ የዒልም ደርሶችና የኮርስ ትምህርቶች ሲሰጡባት ቆይተዋል። በዚያ ትንሽ ቦታ ውስጥ የአላህ ቃል ተነብቧል፤ የነቢዩ ﷺ ሱና ተምሯል፤ የዒልም ተማሪዎች ተቀምጠዋል፤ የብዙ ሕፃናትም ልብ በቁርአን ብርሃን እንዲበራ ጥረት ተደርጓል። ነገር ግን፣ አልሐምዱ ሊላህ! ዛሬ በዚህች መስጂድ የሚቀሩ ሕፃናት ቁጥር እጅግ ጨምሯል። ይህ የሚያስደስት የኸይር ዜና ቢሆንም፣ የሚማሩበት ቦታ መድረሳ ጠባብ በመሆኑ ትልቅ ፈተና ሆኗብናል። ዛሬ በዚያ ጠባብ መድረሳ ውስጥ የሚቀመጡት ሕፃናት የነገው የኡማችን ተስፋዎች ናቸው። ከእነርሱ መካከል የቁርአን ሐፊዞች፣ የሐዲስ ዕውቀት ተሸካሚዎች፣ የሱና ጥሪ አስተላላፊዎችና ለእስልምና የሚጠቅሙ የዒልም ሰዎች ሊወጡ ይችላሉ። እነዚህ ሕፃናት የአላህን መጽሐፍ በሰፊ ቦታ፣ በተመቻቸ አካባቢና በተሻለ የመማሪያ ሁኔታ እንዲማሩ ማድረግ የእኛ የዛሬ ኃላፊነት ነው። ⚠️ ወዳጆቻችን ሆይ! የዚህ ታላቅ ኸይር ተባባሪዎች እንሁን! የመስጂደ አስ-ሱናን የመማሪያ ቦታ ለማስፋፋት፣ ሕፃናቱ የሚቀሩበትን መድረሳ ለማሻሻልና የቁርአንና የሱና ትምህርት የበለጠ እንዲስፋፋ ለማድረግ የእናንተን ድጋፍ እንሻለን። አንዳንዶቻችን ብዙ ልናዋጣ እንችላለን፤ ሌሎቻችን ደግሞ ትንሽ ልናዋጣ እንችላለን። ነገር ግን በአላህ ዘንድ የሚቀበለው በቁጥር ብቻ የሚለካ ሳይሆን በኢኽላስና በመልካም ዓላማ የሚመዘን ነው። በትንሽ አቅማችሁ ትልቅ ለውጥ ማምጣት ትችላላችሁ! አንድ ሕፃን በእናንተ ድጋፍ ቁርአንን በትክክል ቢያነብ፣ አንድ ተማሪ ትክክለኛ የዲኑን ዕውቀት ቢያገኝ፣ አንድ ልጅ የተማረውን ዕውቀት ለሌሎች ቢያስተላልፍ፣ የእናንተ እገዛ በዚህ መልካም ሥራ ውስጥ ድርሻ እንዲኖረው አላህ ሊያደርግ ይችላል። የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «إِذَا مَاتَ الْإِنْسَانُ انْقَطَعَ عَنْهُ عَمَلُهُ إِلَّا مِنْ ثَلَاثَةٍ: إِلَّا مِنْ صَدَقَةٍ جَارِيَةٍ، أَوْ عِلْمٍ يُنْتَفَعُ بِهِ، أَوْ وَلَدٍ صَالِحٍ يَدْعُو لَهُ». “የሰው ልጅ በሞተ ጊዜ ሥራው ይቋረጣል፤ ከሦስት ነገሮች በስተቀር፦ የሚቀጥል ሰደቃ፣ ከእርሱ የሚጠቀምበት ዕውቀት፣ ለእርሱ ዱዓ የሚያደርግ መልካም ልጅ።” 📚 ሰሒሕ ሙስሊም፣ 1631 ወንድሞችና እህቶች ሆይ! ዛሬ በመስጂድ ማስፋፊያ ላይ የምናዋጣው ገንዘብ የዛሬ ድጋፍ ብቻ አይደለም። በዚያ ቦታ ቁርአን ሲነበብ፣ የአላህ ዲን ሲማር፣ ልጆች ሲያድጉና የሚጠቅም ዕውቀት ሲተላለፍ፣ አላህ ከምሕረቱ ድርሻ እንዲያደርግልን የምንሻበት ታላቅ እድል ነው። እኛ እዚህ ምድር ላይ ለዘላለም አንኖርም። ነገር ግን በኢኽላስ የተሠራ መልካም ሥራ አላህ ከተቀበለው፣ ከሞታችን በኋላም የምንጠብቀው የኸይር ምክንያት ሊሆን ይችላል። ስለዚህ ዛሬ የምንችለውን እናድርግ፤ የምንችለውን እናዋጣ፤ ሌሎችም እንዲሳተፉ እንጋብዝ። ምናልባት በእኛ የተነሳ የአላህ ዲን የሚማሩ ልጆች ቁጥር ይጨምር ይሆናል። ⚠️ዛሬ የእናንተ ድጋፍ የእነዚህ ሕፃናት ተስፋ ነው! 🌍 በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በዓለም ዙሪያ ለምትኖሩ ሙስሊም ወንድሞቻችንና እህቶቻችን፦ በዚህ የኸይር ሥራ ላይ የቻላችሁትን ያህል ድጋፍ እንድታደርጉልን በአላህ ስም ጥሪያችንን እናቀርባለን። የምትሰጡት ትንሽ ቢመስልም አትናቁት። የምታደርጉት ድጋፍ በአላህ ፈቃድ ለብዙ ሕፃናት የዒልም መንገድ ሊያመቻች ይችላል። ካልቻላችሁ ደግሞ ይህን ጥሪ ለሌሎች በማድረስ ተባበሩን። የኸይርን መንገድ የሚያመለክትም ከሠሪው ምንዳ ያገኛል። ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 🏦 የመስጂደ አስ-ሱና የባንክ ሂሳቦች 💳 1. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) 1000469830277 💳 2. ዘምዘም ባንክ 0005649620101 💳 3. ሂጅራ ባንክ 1000030300001 📌 ከላይ የተጠቀሱት የባንክ ሂሳቦች በመስጂደ አስ-ሱና ስም የተመዘገቡ ናቸው። ስለ መስጅዱ ሙሉ መረጃ ለማገኘትና ለመጠየቅ ስልክ፦+251914718693 ━━━━━━━━━━━━━━━━━━ 📣 ይህን መልእክት ሼር በማድረግ ለመስጂደ አስ-ሱና ማስፋፊያ የሚያግዙ ወንድሞችና እህቶች እንዲደርሱ እንርዳ! 🕌 በመስጂደ አስ-ሱና — ላይ የማናደርገው የዛሬው ድጋፋችን፣ የነገው የዒልም ብርሃን ያሰፋል!

አቡ ሙዓዝ❌➛ወደ ሀዋሳ ከሸሼ ቡኃላ የሱና መሻይኾችን መዘለፍ መጀመሩ አስገርሞኛል‼️ ሙመይዓ ስትል ባለህበት መንደር ታመኝ ለመምሰል ያሰብክ ትመስላለህ ሀቂቃ‼️ እንደመናቅ እሚያም ነገር ባይኖርም ባ
አቡ ሙዓዝ❌➛ወደ ሀዋሳ ከሸሼ ቡኃላ የሱና መሻይኾችን መዘለፍ መጀመሩ አስገርሞኛል‼️ ሙመይዓ ስትል ባለህበት መንደር ታመኝ ለመምሰል ያሰብክ ትመስላለህ ሀቂቃ‼️ እንደመናቅ እሚያም ነገር ባይኖርም ባተላይ ህመሙ መዳኒት መጥፋቱ እንደተ ናክ ሲገባህ ክፉኛ አቃጠለህ ለስደትም ዳረገህ‼️ በመጨረሻ ላስታውስህ የማይነካ ባትነካ በጣም ይሻልሀል አጸፋውን መቋቋም አትችል‼️ ምናልባት ካለህ ግርጭ ርጭ ፀባይህ ግንፍለተኝነትህ ይነሳብህና በጥገኝነት ከምትኖርበት ቡድን ጋር ትጣላ ለህ‼️ 🍃👉https://t.me/abujemila25 🍃👉https://t.me/abujemila25 🍃👉https://t.me/abujemila25

ያ አባ ሙዓዝ በል በነካ እጅህ የሸይኽ ሙሐመድ ሐሚዲንን ደረሳ (ሸይኽ አቡ ዘርን)ም ኢኽዋን/ሙመይዕ በልልኝማ ጎሽ የኔ ጎበዝ። ወይንስ በደንብ እንድታምነኝ ቪድዎውን ልላክልህ? ለነገሩ ባለፈው ሸይኽ
ያ አባ ሙዓዝ በል በነካ እጅህ የሸይኽ ሙሐመድ ሐሚዲንን ደረሳ  (ሸይኽ አቡ ዘርን)ም ኢኽዋን/ሙመይዕ በልልኝማ ጎሽ የኔ ጎበዝ። ወይንስ በደንብ እንድታምነኝ ቪድዎውን ልላክልህ? ለነገሩ ባለፈው ሸይኽ ሰዒድ አሐመድ ሙስጦፋ ላይ የቀራበትን ልኬልህ የለ? ፈተዋህ ግን አልደረሰኝም እሳ‽ ይልቁንስ አንተ ምንም ነገር አያምርብህም ዝም ብለህ ብትቀመጥ ይሻልሃል የቋጠርኩትን ሁሉ እንዳታስፈታኝ። አቡ ዑበይዳ t.me/AbuOubeida

🪶የሁኔታዎች መቀየያየር በዱኒያ ህይወት የሚጠበቅ ነው! ስለ አኼራ ጉዳዮች ሲወራ ኢማንህ እንደሚጠነክረው ሁሉ ከዚህ በተቃራኒ ሲሆን ደግሞ ስሜቱ ሌላ ነው! ሁሌም ቢሆን ግን ኢማንህን በሚያጠነክሩ ነ
🪶የሁኔታዎች መቀየያየር በዱኒያ ህይወት የሚጠበቅ ነው! ስለ አኼራ ጉዳዮች ሲወራ ኢማንህ እንደሚጠነክረው ሁሉ ከዚህ በተቃራኒ ሲሆን ደግሞ ስሜቱ ሌላ ነው! ሁሌም ቢሆን ግን ኢማንህን በሚያጠነክሩ ነገሮች ላይ ታገል!! ከሐንዘላ አል-ኡሰይዲ (🤎) ተይዞ: እንዲህ ይላሉ፦ ﴿نَافَقَ حَنْظَلَةُ يَا رَسُولَ اللَّهِ. فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: "وَمَا ذَاكَ ؟" قُلْتُ: يَا رَسُولَ اللَّهِ، نَكُونُ عِنْدَكَ تُذَكِّرُنَا بِالنَّارِ وَالْجَنَّةِ، حَتَّى كَأَنَّا رَأْيُ عَيْنٍ، فَإِذَا خَرَجْنَا مِنْ عِنْدِكَ عَافَسْنَا الْأَزْوَاجَ وَالْأَوْلَادَ وَالضَّيْعَاتِ، نَسِينَا كَثِيرًا. فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: "وَالَّذِي نَفْسِي بِيَدِهِ، إِنْ لَوْ تَدُومُونَ عَلَى مَا تَكُونُونَ عِنْدِي، وَفِي الذِّكْرِ ؛ لَصَافَحَتْكُمُ الْمَلَائِكَةُ عَلَى فُرُشِكُمْ، وَفِي طُرُقِكُمْ، وَلَكِنْ يَا حَنْظَلَةُ، سَاعَةً وَسَاعَةً" ثَلَاثَ مَرَّاتٍ﴾ “ሐንዘላ መናፍቅ ሆነ እኮ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አልኩኝ። የአላህ መልእክተኛም (🤎)፦ ‘ምንድን ነው ነገሩ? (ምን አጋጠመህ?)’ አሉ። እኔም፦ ‘የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ከአንተ ዘንድ ስንሆን እሳትና ገነትን ታስታውሰናለህ፤ ልክ በአይናችን የምናያቸው ያህል እንሆናለን። ከእርስዎ ዘንድ ወጥተን ወደ ሚስቶቻችን፣ ልጆቻችን እና ንብረቶቻችን ስንቀላቀል ግን ብዙ እንረሳለን (የቀድሞው ልባዊ ስሜት ይቀንሳል)’ አልኩኝ። የአላህ መልእክተኛም (🤎) እንዲህ አሉ፦ ‘ነፍሴ በእጁ በሆነችው አምላክ እምላለሁ! ከእኔ ዘንድ ባለችሁበት ሁኔታ እና በዝክር (በአላህ ማስታወስ) ላይ ሁልጊዜ ቢቀጥል ኖሮ መላእክቶች በአልጋችሁ ላይ እና በመንገዳችሁ ላይ በጎበኟችሁ (በጨበጧችሁ) ነበር። ነገር ግን ሐንዘላ ሆይ! ሁኔታችን አንዴ ለዚህ (ለተለያዩ የዱኒያ ህይወት ግዴታዎች)፣ አንዴ ለዚያ (ለዒባዳ) ሊሆን ይገባል ይህንንም ሶስት ጊዜ ደገሙት።’” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 2750 ➖➖➖➖➖➖➖ ✅️ በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦ 📱 Telegeram 📱 Whatsup 📱 Facebook  📱 Instagram 📱 X 📱 Youtube 📱 Tik tok

አዲስ የተጀመረ ደርስ ክፍል 01 ሙንከራቱን ሻኢዐህ #አዘጋጁ_የተከበሩት_ሸይኽ_ሙሐመድ_ብኑ_ሒዛም_ሐፊዞሁሏህ ደርሱ የሚሰጥበት ቦታ ደሴ 🕌 ጅብሪል ጎራ መስጅድ የደርሱ አቅራቢ 🎙Abu Useymin Ibnu Shfi ሶፍት ኮፒውን ለማግኘት፦ t.me/Ezedin_Ibnu_Shafi/11108 የቴሌግራም ቻናል፦ ¤t.me/Ezedin_Ibnu_Shafi

አስር ምክሮች ለሙስሊም መምህራን ~~ ① ሃላፊነት ይሰማህ። የምትገነባው ትውልድ ነው። የምታስተላልፈው ነገር እጅግ ውድ ነው። "ሃላፊነት የሚሰማው ሰው እራሱን እንደ ህዝብ ንብረት አድርጎ ይቆጥራል።" ② የሚያዩህ፣ ምሳሌ የሚያደርጉህ አሉና ተጠንቀቅ። ክፉ ምሳሌ እንዳትሆን። ከባህሪህ፣ ከገፅታህ፣ ከአቀራረብህ ሰዎች ይማሩ ዘንድ መልካም ሁን። ③ ፍትሃዊ ሁን። አንዱ ባጠፋው በጅምላ አትቅጣ። በጥቂቶች ጥፋት ተማሪዎችን በትምህርት፣ በፈተና አትቅጣ። በበደለኛ አስተማሪዎች ሳቢያ ስንቶች ትምህርት አቋርጠዋል?! ስንቶች የተወሰኑ የትምህርት አይነቶችን ጠልተዋል። የስንቶች ውጤት ተበላሽቶ  ሞራላቸው ተነክቷል። "የትምህርት ተቋማት በሰፊው ስለ መብት የሚቀነቀንባቸው፣ ብዙ ጭቆና የሚፈፀምባቸው የግፍ አፀዶች ናቸው።" ④ ልዝብ ሁን አታስበርግግ። ቁጥብ ሁን አትባልግ። ትሁት ሁን አትጨፍግግ። የቸገረው ሊያዋይህ የማይፈራህ፣ የከበደው ሊጠይቅህ የማይሰጋህ፣ ያበጠበት የማይደፍርህ ሁን። ሚዛንህን ጠብቅ። ለሁሉም የሚገባው ቋንቋ ይኑርህ። ⑤ ክፋትን፣ ዘረኝነትን አትመግብ። ትውልድ አትመርዝ። በአሁኑ ሰዓት ዘረኝነት ከገበሬው ይልቅ ምሁሩ ጋር ጎልቶ የሚታይበት ምክንያቱ አርቀው ማየት የማይችሉ የተማሩ መሀይማን በመብዛታቸው ነው። ⑥ ብቁ ሁን። እራስህን በእውቀት ገንባ። ተዘጋጅተህ ወደ ክፍል ግባ። ካልሆነ ትናቃለህ። ካልሆነ ሃላፊነትህን በአግባቡ አትወጣም። ካልሆነ ልበ ሙሉነት /confidence/ ታጣለህ። የምትስሰለች ሳይሆን ልብ የምታንጠለጥል፣ የምትናቅ ሳይሆን የምትወደድ፣ የምትፍፈራ ሳይሆን የምትከበር ሁን። ⑦ ለችግር ደራሽ ሁን። የተማሪ ችግር ይግባህ። የጤና፣ የኢኮኖሚ ችግር ያለበት፣ ቤተሰባዊ ቀውስ ያጋጠመው፣ ስነ ልቦናው የተጎዳ፣ ልቡ በሀዘን፣ በጉዳት የተሰበረ ይገጥማልና በምትችለው አግዝ። "አይዞን"፣ "አብሺር" ማለት ለተጎዳ ሰው ዋጋው ትልቅ ነው። ⑧ ቂመኛ አትሁን። ያለፍክበትን ያላለፉ፣ ነገን አሻግረው የማያዩ ጨቅላዎች ጋር ቂም አትጋባ። ከተማሪ ጋር እልህ ውስጥ አትግባ። ተማሪህ የሚናገረውን፣ የሚጠይቀውን ሁሉ በክፉ አትተርጉም። ⑨ ጥንቃቄ ይኑርህ። በአነጋገርህ፣ በአቀራረብህ፣ በሁለ ነገርህ ጥንቃቄ አይለይህ። በምታስተምራቸው ተማሪዎች ቁጥር ልክ በየቤቱ አጀንዳ እንደሆንክ ልብ በል። በክፉ ወይም በበጎ በየቤቱ ትነሳለህ። ከረጅም አመታት በኋላ ዛሬም ድረስ በክፉ ወይም በበጎ የማንረሳቸው አስተማሪዎች አሉ። ለሰዎች ከልብ የማይጠፋ ክፉ ትዝታ አትሁን። (10) ለዲንህ ዋጋ ስጥ። ዲንህን ስታውቅ ለተማሪዎችህ መልካም ምሳሌ ትሆናለህ። ዲንህን ስታውቅ የተሳሳተ አስተምህሮ ለተማሪዎችህ አትመግብም። መጠናቸው ቢለያይም ሁሉም የትምህርት አይነቶች ውስጥ ከዲን ጋር የማይሄዱ ነገሮች ይገጥሙሀል። ንቁና ብቁ ከሆንክ እርምት እየሰጠህ ማለፍ ትችላለህ። = የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/IbnuMunewor

ኢብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁማ እንዲህ ይላሉ፦ التقوى أن لا ترى نفسك خيراً مـن أحد "ተቅዋ ማለት ራስህን ከማንም በላይ አድርገህ ላታይ ነው።" 📚 [ተፍሲሩል በገዊ ፡ 1/60] = የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor