ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ
Kanalga Telegram’da o‘tish
ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
318
Obunachilar
-424 soatlar
-77 kun
+5430 kun
Postlar arxiv
Repost from []ትዳር የአማኞች ምሽግ[]
..
أَلَّا تَحْزَنِي
«አትዘኚ...»
ጌታሽ "አትዘኚ" ካለሽ፣ ከጭንቀትሽ በላይ የሆነ ትልቅ ሽልማት #ስላዘጋጀልሽ ብቻ ነው! ♡♡♡
🍂 ከ ቁርአን አያህ...
የፈተና መብዛት!
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿إِنَّ أُمَّتَكُمْ هذه جُعِلَتْ عافِيَتُها في أولِها وإِنَّ آخِرَهُمْ يُصِيبُهُمْ بَلاَءٌ وأُمُورٌ تُنْكِرُونَها ثُمَّ تَجِيءُ فِتَنٌ يُرَقِّقُ بَعْضُها بَعْضًا فيقولُ المؤمنُ هذه مُهْلِكَتِي ثُمَّ تَنْكَشِفُ ثُمَّ تَجِيءُ فِتْنَةٌ فيقولُ المؤمنُ هذه مُهْلِكَتِي ثُمَّ تَنْكَشِفُ
“ከዚህ ህዝበ ሙስሊም (ከተለያዩ ፈተናዎችና መከራዎች) አፊያ (ነፃ) የተደረገው በመጀመሪያው ዘመን ያለው ትውልድ ነው። የመጨረሻ ዘመን ላይ የሚመጡት መከራና የሚፀየፉትና (የማይወዱት) የሆነ ነገር ይገጥማቸዋል፤ ፈተናዎች ይከሰታሉ አንዷ ፈተና በሌላኛው ፈተና ላይ እየተደራረቡ ይመጣሉ፤ የዚህን ግዜ አማኝ የሆነ ሰው እንዲህ ይላል፦ ‘ይህቺ ፈተና መጥፊያዬ ናት’ ከዛም ፈተናው ይነሳል (ያልፋል) ሌላም ፈተና ይመጣል የዚህን ግዜ አማኝ የሆነ ሰው እንዲህ ይላል፦ ‘ይህቺ ፈተና መጥፊያዬ ናት’ ከዛም ፈተናው ይነሳል (ያልፋል)።”
📚 ኢብኑ ማጃህ ሶሂህ ብለውታል፡ 3210
Repost from نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے
ፉዩሽ ለሚማሩ ኢቲዩጵያውያን የተሰጠች አጭር ምክር። በዚሁ አጋጣሚ ወንድም ኢዲሪስ ጀዛከላህ
الشيخ الفقيه المربي أبي عمار محمد بن عبدالله باموسى حفظه الله
t.me/abdu_rheman_aman
t.me/abdu_rheman_aman
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
🎈ሁሉም ነገር ያልፋል…⁉️
"ሁሉም ነገር ያልፋል ይባላል... አዎን! በምድር ላይ የማይነጥፍ የለምና ማለፉስ እውነት ነው።
ግን ለመሆኑ «ያልፋል’»በሚለው ቀሊል ቃል ውስጥ ስንት የተሰበሩ ልቦችና የፈረሱ ተስፋዎች ተደብቀው እንዳሉ ማን ያውቃል ይሆን⁉️
...በየማለፉ ሂደት ውስጥ በየቀኑ የምንሞታቸው ፣ ማንም የማያይልን ትናንሽ ሞቶች አሉ መቸስ!።
ሰውም በቁም እየተራመደ ፣ በቁም እየሳቀ... በውስጡ ግን ስንት ስፍራ ላይ ተቆራርጦ ወድቋል⁉️ ያ በየቀኑ የሚመረቀዘው ፣ ማንም የማያውቅለት የውስጥ ቁስልስ እንዴት ሆኖ ነው የሚደርቀው⁉️
ህይወት እንዲህ ናት ዛሬ ከሳቅ ወደ ነገ ለቅሶ ፣ ከትናንት ደስታ ወደ ዛሬ ከባድ ሀዘን በቅጽበት ታሻግረናለች።
ከመኖር ወደ አለመኖር የምናደርገው ጉዞስ ቢሆን እንዲህ በቀላል ቃል የሚቀነበብ ነውን⁉️ በፍፁም! ይሄ የሚያልፍበት መንገድ … ይሄ የምንረግጠው ፍም የመሰለ ጎዳና ግን ምንኛ የጨከነ …ምንኛስ የከበደ ነውና‼️
እኛ ሰዎች ግን ክፉዎች ነን ።
የአንዱን ሰው የውስጥ መረር ያለ ስቃይ ሳናውቅለት ፣ ነፍሱ በህመም ስትወራጭ በዓይናችን ሳናይለት ፣ ገና በሩቅ ቆመን 'አይዞህ ያልፋል' እንላለን።
...በምን ያህል አቅማችን … በምንስ የልብ ስፋታችን ህመሙን ተካፍለነው ነው 'ያልፋል' ብለን በቃል የምንቀጥፈው ⁉️ ቃሉ ከንፈር ላይ ሲወጣ ይቀላል የደረሰበት ሰው ልብ ውስጥ ግን እንደ እሳት ይፋጃል ።
.. ማለፉስ አይቀርም... ግን እኮ አልፎ ሲሄድ ባዶነቱን… ትዝታውንና የማይሻረውን ጠባሳውን ጥሎብን ነው የሚሄደው ።
ታዲያ ይሄ ጉዞ እንዴት አይማረር ?
ይሄ መንገድስ እንዴት ሰውን አያብሰልስል? "
ሁሉም ነገር ያልፍ ይሁን!?…እእእ አይመስለኝም!"
....Nur..✍️
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
🎈ናፍቆት ሽው ብሎብኝ ፃፍኳት...
«እንደዚህ ነው ወሎ»
------------------------
እስኪ እንተዋወቅ ፍቅር እንቋደስ፡
እኔ ከወሎ ነኝ ከሙሀባው መቅደስ፡
ወሎ ውብ አርማ ነው ጥልን ለመገንደስ፡
ወሎ በፍቅር እንጅ በዘር አይለካም፡
ያለውን ይሰጣል የሰው ሐቅ አይነካም፡
ገራገሩ ህዝቤ ይህ ነው የኔ መልካም፡
ሐሴትን ከፈለክ ሒድ ወረሒመኖ፡
ጠጥተህ ተመለስ ሙሀባን ከመስኖ፡
እውነተኛ ፍቅር አለ ተወስኖ፡
ከፈለክም ተጓዝ ዝመት ወረባቦ፡
ወይ ደግሞ ተሳፈር በራያ-ዓዘቦ፡
የደግነት ፀጋ እንደ ዝናብ ዘንቦ፡
ከወሎየዎች ጋር አምሮና ተውቦ፡
በቻልከው ተመገብ ተዘጋጅቷል ቀርቦ፡
ከፈለክም ውረድ በወለዲ ቃሉ፡
ተንኮል ያልበረዘው ውብ ፍቅር ያውቃሉ፡
ካልደከመህ አዝግም ግባ በአልቡኮ፡
ደግነት በልብስህ በጂስምህ ላይ ሾልኮ፡
ከንፁህ ልብ ጋር ያደርሳል ተልዕኮ፡
ወሎየነት ማለት እንደዚህ ነውኮ‼️
በከለላ ብትል ጠቅላላው ቦረና፡
አለ ገራሚ ህዝብ ቆራጥና ጀግና፡
ታሪክ የዘገበው በአቋሙ የፀና፡
ስንቱን ልዘርዝረው በምን ቃል ወድሬ፡
ሙሀባ ነፍ ነው ወሎ ተሁለደሬ፡
ለጎ-ጎራ ብትዘልቅ ብቴድ ለገ-ሒዳ፡
ወሎን ሙሉ ብትቃኝ ቀበሌ ወረዳ፡
ሰፈሩን መንደሩን ብታስስ ለጋንቦ፡
ሁሉን ብታስተውል በራያ በቆቦ፡
በንፁህ አዕምሮ ግባ ወረባቦ፡
አለ ንፁህ ፍቅር እንደ ምግብ ቀርቦ፡
የዘር ጂኒ-ጃንካ አይደርስም ከደጁ፡
ሁሉንም አክባሪ እንደዚህ ነው የጁ፡
እኔም ወደዛው ነኝ #ወሎዬ ነኝ ልጁ፡
.....ስማ....‼️
ከሰፊው ሜዳ ላይ ተጫውቶ ገራዶ፡
ከወሎ ከተማ ደሴ ላይ ተወልዶ፡
ከእንቅልፉ ሲነቃ ጦሳን ያዬ ማልዶ፡
ፍቅር ነው መለዮው ይኖራል ቀልዶ፡
ፈገግ ይላል ፊቱ በሙሀባ ነ'ዶ፡
ጠላት አንበርካኪ እየሰራ ሀትሪክ፡
ፅናት ነው መዝገቡ የወሎ ልጅ ታሪክ፡
በእምነቱ የፀና የማይደራደር ፡
ወሎ ነው ክልሌ የሙሀባው መንደር፡
ጨፋና ጨቆርሶ አጣዬ ከሚሴ፡
ሀርቡ ብሎ ባቲ ኮንቦልቻና ደሴ፡
በትዝታ ብቻ ይግላል መንፈሴ፡
ናፍቆት ይወረኛል ከእግር እስከ ራሴ፡
ሐይቅና ቢስቲማ ድፍን ወረባቦ፡
ፍቅር ደግነት ጋር ይላወሳል ቀርቦ፡
ህዝቤ ደግነትን አያውቅም ተርቦ፡
የሸጋ ልጅ ሀገር የቆንጆ ፋብሪካ፡
በፍቅር በውበት መዲና የአፍሪካ፡
ሁሉንም አብሽሩ ባይ ክብር የማይነካ፡
ተራራ ነው ህዝቤ መጠለያ ዋርካ፡
.....ወሎ....!!
በሰሜኑ ደግሞ ከራያ ጀምሮ፡
ጀግንነት እዝነት ጋር ውበት ተጨምሮ፡
ሁሉም ተሰብስቦ ወሎዬ ላይ አምሮ፡
የአሏህ ተዓምር ይገርማል ተፈጥሮ፡
ውጫሌ ወርጌሳ ሀርቡና ጊራና፡
ነፍስና ስጋህን ብትሰጠው አማና፡
አሏህ አለን አብሽር ብሎ ያኮራሀል፡
የኔ ይቅር ብሎ ላንተ ያጎርስሀል፡
ከወሎዎች ውጭ ይህን የት አይተሀል⁉️
ዶሮ ግብር ሀራ ሐሮና ሲሪንቃ፡
ደግነት ቸርነት ርካሽ ነው በቃ፡
መርሳና ወልዲያ ሰዶማና አረሪት፡
አንበሳ ነው እንጅ የለም እንቁራሪት፡
በእምነቱም በሀገሩ የማይደራደር፡
ዱሌ-ሮቃ ልግባ ከጀግኖቹ መንደር፡
ጎብዬና ሐራ አለ-ውሀ ወርቄ፡
አለ ግሩም ጀግና ተናዳፊ ቃንቄ፡
ከጎፈሬው በላይ ጥምጣሙን ጠምጥሞ፡
አሳ-በረንዳውን ሽርጥ አገልድሞ፡
አሞት አለውና አይፈራም ፈፅሞ፡
ቀጭን ነው መለሎ አይገመት ልኩ፡
ድል አድራጊነት ነው ዘወትር ታሪኩ፡
ጃማና ደጎሎ ካቤ ወረኢሉ፡
እጂግ አደገኛ ብዙ ጀግኖች አሉ፡
ለማየት አሳስተው አበባ እሚመስሉ፡
....ብቻ በአጠቃላይ...
የሚመዘዝባት ሸጋና መለሎ፡
በደስታ እሚቀበል ሁሉን አርሒብ ብሎ፡
የተወለድኩበት እንደዚህ ነው ወሎ፡
....ኑረዲን አል-አረብ...✍️
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
ምርጥ ኑስኻ ነው ተጠቀሙት
Repost from ዳእዋ ብቻ الدعوة فقط
ስለ ሐጃዊራ (ሀዳድያ ) (ተክፊሪ) ሙስጠፋ አብደላ
የተደረጉ በውድ እና በሱና ኡስታዞች ሙሓደራወች ስብሰብ በቀላሉ ለማገኘት👇👇👇👇👇👇
የተለያዩ መሳጭ ዳእዋወች ርዕሶቹ ከዚህ በታች ናቸው ርዕሱን አንዲ ብቻ በመካት ማዳመጥ ይችላሉ 42 አከባቢ ሙሓደራወችሐጁሪያ እና ሰለፍያ ልዩነቱ ሙስጠፋ እና እውቀት ይለያያሉ ጀምዕያ እና ሐጃዊራ የሐጃዊራ አስቀያሚነት የሙስጠፋ ችግር የህያ አል ሀጁሪ የሙስጠፋ አላዋቂነት የየህያ ሁጁሪ ስህተት የሀጃዊራወች ውርደት ሀዳድያ እና ሙስጠፋ ሀዳድያ ዝቅጠት የሀገራችን ሀዳድያወች ረድ በሙስጠፋ ላይ ረድ በሀጃዊራወች ላይ ሙስጠፋ አብደላ ቡዙ ሰው እየፈተነ ሙስጠፋ ሙብተድእ አይደለም ለምትሉ ጦሀም እኳ ጥምጣም ይለብሳል ጀምዕያ እና ተያያዥ ነጥቦች የሀጁሪ መንጋ በመረጃ ሙስጠፋ በራሱ ጀምዕያ ይቻላል ያለበት ሀጁሪ ፊርቃ ከየመን የወረሱት አለባበስ ብቻ ነው የጀምዕያ ጉዳይ ሀጁሪይ ሰለፎችን ይቃረናል ሙስጠፋ በመረጃ ሲጋለጥ የሐጃዊራ ድበር ማለፍ ሐጃዊራ እስበሳቸው ሲረጋገሙ በአጭሩ ሀጁሪያወች ይድረስ ለሀጁሪያወች ረድ በሙስጠፋ የሀጃዊራ ቂልነት የተጋለጠበት ከለላ ከተማ ላይ በአቡ ሂዛም ❶ የሀጁሪ አላዋቂነት የተጋለጠበት በከለላ ከተማ ላይ በአቡ ሂዛም ➋ ጀምዕያ እና ተብድዕ ይድረስ ለሙስጠፋ ተገላባጩ ሙስጤ ጀምዕያ እና ሙስጠፋ በአንድ ራስ ሁለት ምላስ ረድ በሙስጠፋ ላይ ኡዙር ቢል ጀሀል ላይ በኡስታዝ ኸድር አህመድ ❶ ረድ በሙስጠፋ ላይ ኡዙር ቢል ጀሀል ላይ በኡስታዝ ኸድር አህመድ ➋ ረድ በሙስጠፋ ላይ ኡዙር ቢል ጀሀል ላይ በኡስታዝ ኸድር አህመድ ➌ ረድ በሙስጠፋ ላይ ኡዙር ቢል ጀሀል ላይ በኡስታዝ ኸድር አህመድ ❹ ረድ በሙስጠፋ ላይ ኡዙር ቢል ጀሀል ላይ በኡስታዝ ኸድር አህመድ ❺
Repost from 𝐀𝐛𝐮 𝐒𝐮𝐟𝐲𝐚𝐧~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥
በነገራችን ላይ...ዛሬ ላይ መመካከርና ማስታወስ እጅግ ፈታኝ በሆነበት ዘመን ላይ እንገኛለን።
በአንድ ሚዲያ ላይ የሚፃፍ ጠቅላላ ምክር በወጣ ቁጥር፦ «እኔን ፈልጎ ነው... በእኔ ላይ ረድ አስቦ ነው፣...» እያለ ነገሩን የግል ጥቃት የሚያደርገውና በጥርጣሬ የሚመለከተው ሰው ቁጥር በርክቷል።
ሐቢቢ አንድ የተፃፈ መልዕክት ከሕይወትህ
እውነታ ጋር ከተገጣጠመ፦
◈ አላህ እንድትማርበትና ራስህን እንድትፈትሽበት የላከልህ የሂዳያ ሰበብ ሊሆን ይችላልና አትበሳጭ፤
◈ ራስህን ለመከላከልና ለዛ ምክር የራስህን ምላሽ ለመስጠት ብዙ ሜትሮችን አትሩጥ፤
◈ በሺዎች የሚታደሙበት መድረክ ላይ ለአንድ ግለሰብ ተብሎ የሚፖሰት ማንም የለም።
ከሁሉ በላይ ደግሞ፤ የሚያስታውስና የሚመክር ሰው ከአንተ የተሻለ፣ ከስህተት የጠራ ንጹሕ ሆኖ አይደለምና ዕልክ ውስጥ አትግባ።
መካሪውም ቢሆን ያቺን ቃል በመጀመሪያ ለደካማዋ ነፍሱ ነው የፃፈው። ሁላችንም በአላህ ምሕረት ሥር የምንዳክሩ፣
አንዱ በሌላው ማስታወስ የሚድን ድሆች ነን።ስለዚህ ምክርን በ በጎ አስተሳሰብ እንቀበል፤ ልባችንን ለነሲሐ ክፍት እናድርግ። ምክንያቱም ትልቁ ጥንካሬ ራስን መከላከል ሳይሆን በሐቅ ፊት ራስን ዝቅ ማድረግ ነውና።
t.me/AbuSufiyan_Albenan
t.me/AbuSufiyan_Albenan
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
የህይወት ❷ መንገዶች
የመጀመሪያው፦
🎈«አስታውሱኝ አስታውሳችኋለሁ የሚል ቃሉ ሲሆን....
ቀጣዩ ደግሞ፦
🎈አሏህን ረሱትና #ተዋቸው የሚለው ነው።
«በየትኛው መንገድ እንደምትገቡ #የሚጣፍጣችሁን እናንተ ታውቃላችሁ።»
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
Repost from Abu muhammed (አቡ ሙሀመድ
~ሌባ ቢለብሰው ኒቃብ ምን አጠፋ!
ሙናፊቅ ቢሰግደው ሶላት ምኑ ከፋ!
አጭበርባሪ ቢያሳድገው ፂም ምን አጎደለ!
አታላይ ቢያሳጥረው ሱሪ ምን በደለ!
ዐረቄ ቢጨመቅበት ገብስ አይወቀስም፣
ጃሂል ቢያሸብርበት ኢስላም አይኮሰስም።
=
https://t.me/UstazAbuMuhammed
Repost from إذاعة العلم الشرعي || ሸሪዐዊ እውቀት ማሰራጫ
3️⃣0️⃣ ቀዳሜ ነሐሴ 3️⃣0️⃣
🟩🟩🟩🟩🟩🟩
➡️ መርከዝ አቡ ሙሳ አል አሽዐሪ የቁርአን ሂፍዝና የተርቢያ ማእከል በበጋና በክረምት በአዳሪ መርሀግብር ሲያስተምራቸው የቆዩ ወንድና ሴት ተማሪዎችን የፊታችን ቅዳሜ ነሐሴ 30 አጠና ተራ እፎይታ የገቢያ ማእከል በሚገኘው ትልቁ አዳራሽ በደማቅ ሁኔታ ያስመርቃል ። ኢንሻአላህ
➡️ በፕሮግራሙ ከተመራቂ ተማሪዎች የተለያዩ ማራኪ ዝግጅቶች ይጠብቋቹሀላ ።
➡️ በፕሮግራሙም ላይ የተለያዩ መሻይኾችና ኡስታዞች አጫጭር ሙሐደራዎች ይኖሯቸዋል ።
ተጋባዥ እንግዶች ⤵️
➡️ሸይኽ ሙሐመድ ሀሰን ፈድሉ
➡️ሸይኽ ሙሐመድ አወል ባህርዳር
➡️ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
➡️ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ
➡️ኡሰታዝ ሳዳት ከማል
➡️ኡስታዝ አቡ ሙስሊም
ማሳሰቢያ:
➡️ ፕሮግራሙ የሚጀመረው ከጠዋቱ 2:30 ስለሆነ ፈጥነው እንዲደርሱ ለማሳሰብ እንወዳለን ።
➡️ ለሴቶችም በቂ ቦታ ያለ ሲሆን ፕሮግራሙንም በላይቭ ቀጥታ ስርጭት የሚከታተሉ ይሆናል ።
ነሐሴ 3⃣0⃣
★★★
Telegram : -
https://t.me/merkezabumussa1
https://t.me/merkezabumussa1
لا أحد يأمن على نفسه من الانتكاس، لذا سلوا الله الثبات.
كان من دعاء النبيﷺ
"اللهم يا مقلب القلوب ثبت قلبي على دينك"
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ሸይኽ ዐብዱረዛቅ አልበድር - አላህ ከክፉ ይጠበቃቸውና - እንዲህ ብለዋል፦
*إنّ فاقد التوحيد ميّت ولو كان يمشي على الأرض ومحقّق التوحيد هو الذي يحيا الحياة الحقيقية
*يقول الله -جلّ وعلا-: {أَوَ مَن كَانَ مَيْتاً فَأَحْيَيْنَاهُ} [الأنعام:١٢٢]. أي أحييناه بالإيمان والتوحيد"*
“ተውሒድ የሌለው ሰው፣ ምድር ላይ የሚንቀሳቀስ ቢሆን እንኳ፣ የሞተ ነው። እውነተኛውን ህይወት የሚኖረው ተውሒድን ያረጋገጠ ነው። የላቀውና ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ብሏል፡-
“ሙት የነበረና ሕያው ያደረግነው ሰው…” [አል-አንዓም፡ 122]
ይህም ማለት፡- “በኢማንና በተውሒድ ሕያው አደረግነው” ማለት ነው።
🎙️[“የተውሒድ ደረጃ በሙስሊም ህይወት ውስጥ” ከሚል ኹጥባ የተወሰደ።]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ነውረኛ ጥፋት እንደሆነ አውቆ በግልፅ ለማውገዝ አይሸማቀቅም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። አለቀ።
(ኢብኑ ሙነወር፣ ረቢዑልአወል 18/1448)
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
"በእንቁላሌ በቀጣሽኝ!"
~
"ከነቢ ሙሐመድ በኋላ ሌላ ነብይ አይመጣም። ይገባሀል አይደል? እንዲህ ተቸገርን። ወልይ ካልኩትስ ምን ትላለህ?"
ይሄ እንግዲህ ሰሞኑን በመጅሊሱ መሪ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀረበ መወድስ ነው። ይህንን ንግግር እንደ ሙስሊም የምንቃወመው የመንግስት ተቃዋሚ ፖለቲከኞች ወይም ያኮረፉ አሕባሾች በሚያዩት መነፅር እየተመለከትን አይደለም። ይልቁንም ከኢስላማዊ መርህ አንጻር ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙስሊም አለመሆን የሚታወቅ ነው። ሙስሊም ያልሆነን አካል በዚህ መልኩ መግለፅ ደግሞ ከባድ ጥፋት ነው። እንኳን ሙስሊም ያልሆነን ሰው፣ ሙስሊም የሆነን ደግ መሪ እንኳ በዚህ መልኩ መግለፅ ድንበር ማለፍ ነው። በኢስላም በደጋጎች ላይ ድንበር ማለፍን የሚያስጠነቅቁ የሸሪዐ ማስረጃዎችና የዑለማእ ማሳሰቢያዎች ብዙ ናቸው። ዛሬ ዛሬ ግን ሙስሊም ባልሆኑ አካላት ላይ ድንበር ስለማለፍ እንድንነጋገር እየተፈረደብን ነው። አላሁል ሙስተዓን!
ልብ በሉ! እንዲህ ዓይነት ጥፋት ሲገጥመን የመጀመሪያችን አይደለም። ምን ማለት ፈልጌ ነው? እንዲህ አይነት ጥፋቶችን ማውገዝ ያለብን የጠቅላዩ ሁኔታ ሲደብረንና ስናኮርፍ እየጠበቅን አይደለም። እንዲህ አይነቱ አካሄድ የፖለቲከኛ እንጂ የዲን አካሄድ አይደለም። የአሁኑ የሐጂ ኢብራሂም ጥፋት ጫጫታ የበዛበት ጥፋቱ ከባድ ስለሆነ ብቻ አይደለም። ይልቁንም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ያኮረፈው ህዝብ ስለበዛ ነው። እንጂ ከዚህ ጥፋት ጋር ተመሳሳይ ወይም የሚቀርቡ ብዙ ጥፋቶች ከዚህ በፊት ተፈጽመዋልኮ። ያኔ ግን ልክ እንዳሁኑ የሐጂ ኢብራሂም ሁኔታ አብዛኛው ህዝብ ምርቃና ላይ ነበር። በዚያን ሰሞን ስለ ጠቅላዩ የተባሉትን ላስታውሳችሁ:-
* አደም ካሚል፡ "ሙሳም ቢመጡ፣ ዒሳም ቢመጡ ፣ ነብያችን ሙሐመድም ቢመጡ..." እያለ ዘግናኝ ንፅፅር ሲሰራ አይተናል። ያኔ ይህንን ንግግር ስንተች አሁን ከሚንጫጫው ውስጥ ቀላል የማይባለው ሲሰድበን ነበር። ሌላው ደግሞ ጥፋቱን እንዳላየ እንዳልሰማ ፀጥ ብሎ ነበር። የአደም ካሚል ንግግር ከአሁኑ የመጅሊሱ መሪ ንግግር ያነሰ ነው ወይ?
* የ"ሙፍቲ" ዑመር ደጋፊዎች በአሁኑ የሐጂ ኢብራሂም ጥፋት ጮቤ ሲረግጡ እያየን ነው። "ሙፍቲው" ጠቅላይ ሚኒስትሩን "ከሰማይ የወረደ መለይካ ይመስላል" ያሉበትን የረሳን መስሏቸው ይሆን? ወይስ ይሄኛው ጥፋት ቀላል መስሏቸው ነው? "መለስ የጀነት ነው" ሲል የነበረው የነ ያቁተል ዐርሽ ጀማዐ ዝም ቢል ይሻለው ነበርኮ።
* "ያ በዲዐ ዘማን" የሚል ረጅም መወድስ በዐረብኛ የፃፈ ዳዒያም አለ። አሁን ላይ አዲስ አበባ ውስጥ ኢማም መሰለኝ። የአፄዎቹን ዜና መዋእል ሲፅፉ የነበሩትን ደብተራዎች የሚያስታውስ አካሄድኮ ነው የሄዱት።
* ጠቅላዩ ሙስሊም ነኝ ባላለበት "ከፊርዐውን ቤት የወጣ ሙሳ ነው"፣ "ከዑመር ብኑ ዐብዲል ዐዚዝ ወዲህ አምሳያው አልታየም"፣ "ከዐረብ መሪዎች ይሻላል"፣ "ከሸይኽ ረቢዕ ይሻላል" እየተባለ ሲፃፍ አይተናልኮ።
* አቡበክር አለሙ:-
(إِنَّ اللَّهَ اصْطَفَاهُ عَلَيْكُمْ وَزَادَهُ بَسْطَةً فِي الْعِلْمِ وَالْجِسْمٌِ)
በማለት ስለ ጧሉት በቁርኣን የተወሳውን ሙስሊም ላልሆነው ሰው ሲሸልም ነበር።
* የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር ልክ እንደ ደዕዋ መስጂድ ውስጥ ከፍተው በማይክ ሲያሰሙ የነበሩ አካላት አሉኮ። የሚገርም እብ^ ደትኮ ነው ያለፈው።
* "መኖር ከጀመርን ገና ሶስት ወራችን" እስከማለት የደረሱም ነበሩ። እንዲያውም ይሄ በንፅፅር ቀላሉ ነው።
ይሄ ሁሉ ሲሆን "ኧረ አላህን እንፍራ!" በማለት ባደባባይ ደፍሮ የተናገረ ምን ያህል ሰው ነበር?! በሃገራችን አንድ አባባል አለ። ልጅ ከጎረቤት እንቁላል እየሰረቀ ሲያመጣ እናት እየተቀበለች ስትበላና ስታበላ ቆይታ፣ ልጅ አመሉ ስር ሶዶ አ^ህያ ሰርቆ ይያዛል። አ^ህያው ላይ አስቀምጠው በህዝብ መሀል "እኔን ያየ ይቀጣ" እያስባሉ ሲያዞሩት እናት አይታ ስትሸማቀቅ ልጅ ምን አላት? "በእንቁላሌ በቀጣሽኝ!"
ብቻ የሐጂ ኢብራሂም ቱፋ ዘግናኝ ንግግር ጥፋትነቱ ለማንም የማይሰወር ነው። እንደምናየውም ብዙ ሰው እየጮኸበት ነው። ከመሆኑም ጋር ትኩረት የሚሹ ነገሮች አሉ።
1ኛ፦ የሐጂ ኢብራሂም ንግግር በሐዲሥ የተገለፀው "አላህ ሆይ! አንተ ባሪያዬ ነህ፤ እኔ ጌታህ ነኝ" በማለት በደስታ ብዛት እንደተሳሳተው ሰው አይነት ጥፋት ነው የሚል አይቻለሁ። ይሄ በጭራሽ ልክ አይደለም። በሐዲሡ ላይ የተገለፀው ሰውየኮ አስቦበት አይደለም ጥፋቱን የተናገረው። ሳያስበው ነው በስህተት ያመለጠው። ያሁኑ እንደዚያ እንዳልሆነ ግልፅ ነው፡፡ በምርቃና/ በነሻጣ መናገር እና ሳያስቡት የሆነ ቃል ማምለጥ የተለያዩ ናቸውኮ። ደግሞም ጥፋቱ ሲስሰማ መደንገጥና ማረም ሳይሆን በተክቢራ ማጀብ ነው የተሰማው።
ስለዚህ የጥፋቱን ክብደት ለማቃለል አላስፈላጊ ንፅፅር መጠቀም ተገቢ አይደለም። ተሰራ የተባለው ልማት በዚህ ደረጃ 0ቅልን የሚያስት አድርጎ ማቅረቡም ሌላ የሚገርም ነገር ነው።
2ኛውና ዋናው ማንሳት የምፈልገው በመንግስትም ሆነ በመጅሊስ ኃላፊነት ላይ በየተዋረዱ ላላችሁ መልእክት ማስተላለፍ ነው። እንዲህ አይነት የእምነትን መርሆዎች እየጨፈለጉ ሰዎችን ማወደስ የምታስቡትን ትርፍ ሊያስገኝላችሁ ቀርቶ ውርደትና መንናቅን ነው የሚያመጣባችሁ። አንደኛ ህዝብ ይተፋችኋል። ይሄ ትልቅ ኪሳራ ነው። ሁለተኛ በሹማምንቱም ዘንድ ያስንቃችኋል። ትልቁ አደጋ ደግሞ ከአላህ ጋር መጣላታችሁ ነው፡፡ በተሳሳተ መንገድ ጥቅምንና ክብርን መሻት ውርደትን ነው የሚያመጣው።
3ኛ፦ እንዲህ ዓይነት ጥፋት ሲከሰት በምንም መነሻና ማመሀኛ መከላከል አይገባም። ቢያንስ ዳግም እንዳይደገም ጥፋቱን ማመንና ጫን አድርጎ መነጋገር ነው የሚሻለው። (አንዳንዶች እንደሚሉት ማስተካከያ ይሰጣሉ ብዬ አልገምትም። ከሆነ ቀላል ነገር አይደለም።) ይልቅ እነዚህ የሚያሳቅቁ ጥፋቶች እንዲቆሙ ጫና መፍጠር ነው የሚሻለው። ከሁለት ዓመት በፊት እዚሁ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የተናገርኩትን ደግሜ ልናገር፦ "አንዳንድ በመጅሊስ አመራሮች ሚዲያ ላይ የሚቀርቡ ንግግሮች የሚያሳቅቁ ናቸው። አድማጭን የሚያሳቅቅ ወይም ከዲን ጋር የሚጋጭ ንግግር ከሚወጣ ወይ ቀድሞ መዘጋጀት አልያ ፅፎ ማንበብ ይሻላል።" ያሁኑ ይባስ!
የሆነ ሆኖ ጩኸታችን መርህ ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይገባል። ውግንናችንም ሆነ ተቃውሟችን እንደ ሙዳችን የሚቀያየር መሆን የለበትም። የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ መንግስት ለሙስሊሞች ያለው ቀረቤታና አያያዝ ካለፉት ስርአቶች ይሻላል ወይስ ይብሳል በሚለው ላይ አተያያችን ልዩነት እንደሚኖረው የሚጠበቅ ነው። ችግሩ ግን ደጋፊውም ሆነ ተቃዋሚው በአመዛኙ "እኔ የያዝኩትን አቋም ካልያዛችሁ" የሚል ፅንፈኛ ነው። የፈለገ ቢሆን ግን ድጋፍም ይሁን ተቃውሞ ዐቅል ሊያሳጣን አይገባም።
በዚህ አጋጣሚ ሙስሊም ያልሆኑ አካላት የሐጂ ኢብራሂምን ንግግር በማስታከክ እንደለመዱት "ወሃ^ቢያ" እያሉ እያላዘኑ፣ "ሙፍቲ ዑመር አማራ ስለሆኑ ነው የተገለሉት" እያሉ ወደ ኋላ ተመልሰው ሙሾ እያወረዱ እያየን ነው። እነ አባይ ፀሐዬን እየቀሰቀሰ ህዝበ ሙስሊሙን ለማስመታት ሲሰራ እንደነበረ በራሱ አንደበት የመሰከረን አካል በመና ^ፈቅ የምንቆዝም እንዳይመስላችሁ። የዛሬ ጥፋት ትናንትን አያስናፍቀንም። የዛሬን ለማውገዝ ትናንት ውስጥ አንወሸቅም። በግራም በቀኝም ካለ የዘር ትብታብም ውስጥ አንገባም። ችግር ያለበት ባይጠፋም፣ አብዛኛው ሙስሊም የትናንቱም የዛሬውም ጥፋት ያለምንም ሽፋን
ምርጥ ንግግሮች ከውዱ ኡስታዝ
ኡስታዝ ኢብኑ_ሙነወር ሀፊዘሁሏህ
በተለያዩ አጋጣሚዎች በአስተውሎት
የተሞሉ በጣም ያማሩ ሰፊ ቁም ነገር
ያዘሉ አባባሎች ይናገራል።
በአሏህ ፍቃድ ጥቂቶቹን እንመልከት፦
⤵️⤵️⤵️
1ኛ.╭──••──═••═─•••───╮
⬇️ «እውቀት በትጋት እንጂ ⬇️
በምኞት አይገኝም»።
ኢብኑ ሙነወር حفظه الله
2ኛ.╭──•••──═••═─•••───╮
⬇️«ርካሽ ማለት የሰዎችን ውዴታ ⬇️
ለማግኘት ብሎ የሃይማኖቱን መሰረታዊ
መርሆዎች የሚጥስ ነው»።
ኢብኑ ሙነወር حفظه الله
3ኛ.╭───•••──═••═─•••────╮
⬇️«ከማንም ጋር በገባበት ልንገባ ⬇️
በወጣበት ልንወጣ የህይወት ዘመን ውል የለንም። መንሃጅ ያገናኘናል፤ መንሃጅ ይለያየናል። መንሃጅ ከለያየን ከትላንት ቀርቶ
ከዛሬ ወዳጅም ጋር እንለያያለን።መንሃጅ ካገናኘን ዛሬ ከምንርቃቸው አካላት ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን እንጓዛለን። መለኪያችን የሰለፊያ መንሃጅ ብቻ ነው። ትላንት አንድ የነበርን የተለየናቸው አሉ። ትላንት
ተወጋግዘን ዛሬ ከልብ የምንወዳቸው ብዙ ናቸው። አላህ በሰለፊያ ላይ ያፅናን»።
ኢብኑ ሙነወር حفظه الله
4ኛ.╭───•••──═••═─•••───╮
⬇️«የሪፍቅ አስፈላጊነት ለማንም ⬇️
አይሰወርም። ሪፍቅን ከቢድዐ አውራዎች መከላከያ ማድረግ ግን በሪፍቅ ላይ በደል
መፈፀም ነው። ሪፍቅ የራስን የከሸፈ አቋም መሸፈያ ጭንብል አይደለም። የሸሪዐ መርሆዎችን ለብልሹ አካሄድ መከላከያ ማድረግ በራስ ላይ ውርደትን መጋበዝ ነው»።
ኢብኑ ሙነወር حفظه الله
5ኛ.╭────•••──═•••═─•••────╮
⬇️«አንድነት አንድነት ብሎ በመዘመር⬇️
ብቻ አንድነት አይመጣም። ይልቁንስ የልዩነት አረሞችን ከመሰረቱ በመንቀል እንጂ»።
ኢብኑ ሙነወር حفظه الله
6ኛ.╭───•••──═•••═─•••───╮ ⬇️«ለጉራ ከሚውል እውቀት ይልቅ ⬇️
መሀይምነት ሺህ ጊዜ ይሻላል። ተውሂድ ቀራህ፣ ፊቂህ ቀራህ፣ ኡሱል ቀራህ፣ ነህውና ሶርፍ ቀራህ፣ ቁርኣን በተጅዊድ ሀፈዝክ፣ አካዳሚ ተማርክ፣ መማርህ ትህትናን ካላለበሰህ፣ አላህን መፍራትን ካላወረሰህ፣
አንተ የሰው ትንሽ ነህ፤ ከንቱ ፍጡር»።
ኢብኑ ሙነወር حفظه الله
7ኛ.╭───•••──═•••═─•••────╮
⬇️«አንድነት በሐቅ ላይ መሰባሰቢያ ⬇️
ገመድህን እንጂ የስሜት ተከታዮች
ማድፈጫ ጫካ አይደለም»።
ኢብኑ ሙነወር حفظه الله
https://t.me/Abulabas1444
https://t.me/Abulabas1444
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
ባል ሆይ ሚስት መሆን የፈለገችውን ሁሉ ከፈቀድክላት አንድ ቀን ውርደትን ታከናንብሃለች። ቆፍጠን ማለት ባለብህ ቦታ ቆፍጣና ሁን። አንተ የጌታህን ትዕዛዝ አክብር፣ አስከብር እንጅ ሚስትህም ትሁን ማንኛውም አካል በፈለገው ቢተረጉመው ግድ ሊሰጥህ አይገባም። የሰዎች መነፀር ይለያያልና ነፃነትን ጭቆና አድርገው የሚስሉ አካሎች ሸውደውህ ሚስትህን ሽፍን፣ ስትር ከማድረግ እንዳትለሳለስ አደራ። ሴትን ልጅ አላህ ያልፈቀደውን ወይም ከአቅሟ በላይ የሆነን ስራ አትዘዛት እንጅ፣ "ስስ ብጣሽ ጨርቅ ፊትሽ ላይ አድርጊና የጌታሽን ትዕዛዝ በማክበር ተከበሪ" ማለት በምንም አይነት መልኩ ጭቆና ሊሆን አይችልም። አዎ! ኒቃብ የነፃነት እንጅ የጭቆና አርማ አይደለም።
{ ٱلرِّجَالُ قَوَّ ٰمُونَ عَلَى ٱلنِّسَاۤءِ }
በነገራቹህ ላይ በንፅፅር ዘርፍ የሚንቀሳቀሰውና (Husu) በመባል የሚታወቀው ወንድማችን በሚያደርገው ወደ ኢስላም ጥሪና ከካፊሮች ጋር ባለው ትግል ምክኒያት በጣም ከማከብራቸው ወንድሞች ውስጥ ነው። ጥቂት የማይባሉ ጥፋቶች እንዳሉበት ባውቅም ያሉበትን ከፊል ክፍተቶች እንዲያስተካክል መምከርና የሚያስተካክለበትን የኢማን ጥንካሬ አላህ እንዲሰጠው ዱዓ ማድረግ እንጅ እርሱን በሚዲያ በማብጠልጠል የካፊርና የአሕባሽ መጠቀሚያ መሆን አስፈላጊ ነው ብየ አላምንም።
እንደጥቅል ግን በማንኛውም የትምህርት ዘርፍ በሚዲያ ኢስላምን ለማገልገል የምንሞክር ወንድሞች ማህበረሰቡ የዲን አስተማሪን የሚስልበት ስዕልና የሚሰጠው የሞዴልነት ቅርፅ የላቀ መሆኑን በመገንዘብ በምናደርገው ማንኛውም እንቅስቃሴ ጥንቁቅ መሆን ይኖርብናል። በተላይ የትዳር አጋሮችን መረጣ፣ የጋብቻ ስርዓትና ከሴቶች ጋር የተነካካ ጉዳይ ላይ በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ምክኒያቱም እናንተ ቀለል አድርጋቹህ የምታስቡት ጉዳይ ካላወቃቹህት አቅጣጫ ኢስላምን ሊጎዳ ይችላልና።
የፌስቡክ አርበኞች ደግሞ እባካቹህ አዲስ አጀንዳ በመጣ ቁጥር ጥቅምና ጉዳትን ሳታመዛዝኑ የመጣላቹህን አትለቅልቁ። አንዳንዴ ዝም ማለት ይልመድባቹህ። ሲጀመር አንድ ሰው ስላጠፋ ብቻ ሳይሆን ጥፋቱ ተረማማጅና ቢድዓ አዘል ሲሆን እንጅ ማጋለጥ ያለብን። በራሱ ላይ ብቻ የሚያጥር አመፅ ከሆነ ጥፋቱን መሸፈንና ከቻልን መምከር ነው የሚገባው። አላህ ሁላችንንም በዲኑ ላይ ያፅናን።
=
የቴሌግራም ቻናል
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
t.me/Abu_lmran_Alaseriy
