uz
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Kanalga Telegram’da o‘tish

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
4 327
Obunachilar
+2824 soatlar
+307 kun
-4230 kun
Postlar arxiv
🇮🇷🛸🚫🇺🇸 'የአሜሪካ ስስ ብልት'፣ (The Achilles' heel of the USA) ጣሊያናዊ ዲዛይነር እንደገለፀው። የኢራን "ሸሂድ" ድሮን ከአሜሪካ ጋር በሆርሙዝ ወሽመጥ ያለውን ጦርነ
+1
🇮🇷🛸🚫🇺🇸 'የአሜሪካ ስስ ብልት'፣ (The Achilles' heel of the USA) ጣሊያናዊ ዲዛይነር እንደገለፀው። የኢራን "ሸሂድ" ድሮን ከአሜሪካ ጋር በሆርሙዝ ወሽመጥ ያለውን ጦርነት እንዴት በሆነ ስልታዊ መንገድ 'በአቻ' እንዲቋጭ እንዳደረገ፣ እንደ ጣልያናዊው ሰዓሊ።

🇺🇸 🇮🇶 ኩርዶች አሜሪካንን በኢራን ጦርነት ለመርዳት ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው፣ የትራምፕ አስተዳደርን ክፉኛ አስቆጥት እንደነበር ይታወሳል። እንደሚታወሰውም፣ ከሳምንት በፊት ትራምፕ አሜሪካ
🇺🇸 🇮🇶 ኩርዶች አሜሪካንን በኢራን ጦርነት ለመርዳት ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው፣ የትራምፕ አስተዳደርን ክፉኛ አስቆጥት እንደነበር ይታወሳል። እንደሚታወሰውም፣ ከሳምንት በፊት ትራምፕ
አሜሪካ ለኩርዶች በመሬት ኢራንን እንዲወሩ 'ጥሩ ጥሩ መሳሪያዎች' ሰጥተናቸው ነበር፣ እናም ጊዜው ደርሶ በሉ ጀምሩ ስንላቸው፣ መሳሪያውን ይዘው ተሰወሩ፣ ለዚህ ክህደታቸው ደግሞ ይከፍሏታል
ብሎ ነበር። በዛሬው ዕለት የአሜሪካ ፍትህ ሚንስትር፣ Beverly Hills ካሊፎኒያ የሚገኘውን የኩርድ ፕሬዝዳንት መስዑድ ባርዛኒን መኖሪያ ቤት እና 'ቤተመንግሥቱ' እንዲወረሱ ትዕዛዝ ያስተላለፈ ሲሆን፣ በገንዘብ ዝርፊያም ባርዛኒን ከነ ልጁ ከሷል።

🇮🇱 እስራኤል በ AI ምላሾች ላይ ተጽእኖ ለማሳደር የቀድሞ የትራምፕ አማካሪን ቀጥራለች፣ ሲል Axios ዘግቧል። እስራኤል የ AI ሲስተሞች (ChatGPT፣ Claude፣ Gemini) ሀገሪቱን እን
🇮🇱 እስራኤል በ AI ምላሾች ላይ ተጽእኖ ለማሳደር የቀድሞ የትራምፕ አማካሪን ቀጥራለች፣ ሲል Axios ዘግቧል። እስራኤል የ AI ሲስተሞች (ChatGPT፣ Claude፣ Gemini) ሀገሪቱን እንዴት እንደሚገልጹ ለመቅረጽ ዘመቻ ጀምራለች፣ ይህንን ለማድረግም የትራምፕ የቅርብ ሰው የሆነውን፣ ብራድ ፓርስኬል፣ ቀጥራለች። ፕሮጀክቱ ድረ-ገጾችን እና የማህበራዊ ሚዲያ ርዕሶችን፣ ውይይቶችን እና መድረኮችን ወደ AI ሲስተሞች ሊመገቡ እና በምላሾቻቸው ውስጥ ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉ ይዘቶችን መፍጠርን ያካትታል።

🇮🇷🇺🇸 USS Rafael Peralta፣ የተባለ የአሜሪካ የባሕር ኃይል መርከብ፣ የኢራንን ነዳጅ ጫኝ መርከብ፣ ከኢንዶኒዢያ ነዳጅ አራግፎ ሲመለስ በሕንድ ውቂያኖስ ላይ መጥለፉና በቁጥጥር ሥር
🇮🇷🇺🇸 USS Rafael Peralta፣ የተባለ   የአሜሪካ የባሕር ኃይል መርከብ፣ የኢራንን ነዳጅ ጫኝ መርከብ፣ ከኢንዶኒዢያ ነዳጅ አራግፎ ሲመለስ በሕንድ ውቂያኖስ ላይ መጥለፉና በቁጥጥር ሥር ማድረጉ ታወቀ።

🇺🇸🇵🇰🇮🇷⚡️ - ፓኪስታን በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል በሽምግልና ውስጥ ቁልፍ ተዋናይ ሆና ብቅ ብላለች። ዶናልድ ትራምፕን በቀጥታ 'ይግባኝ' ካለች በኋላ የተኩስ አቁም ጊዜውን
+1
🇺🇸🇵🇰🇮🇷⚡️ - ፓኪስታን በዩናይትድ ስቴትስ እና በኢራን መካከል በሽምግልና ውስጥ ቁልፍ ተዋናይ ሆና ብቅ ብላለች። ዶናልድ ትራምፕን በቀጥታ 'ይግባኝ' ካለች በኋላ የተኩስ አቁም ጊዜውን ማራዘም ችላለች ሲል The Hill ዘግቧል። ➡️ የፓኪስታን ጦር አዛዥ አሲም ሙኒር ሁለቱን ወገኖች ለማገናኘት በመሞከር ከትራምፕ ጋር ያለውን ግንኙነት በማጠናከር የኢራንን የፖለቲካ አመራር እና IRGC ን ወደ ጠረጴዛ ለማምጣት ከፍተኛ ሚና ተጫውቷልም ብሏል። ➡️ አክሎም፣ ትራምፕ በተለይ በፓኪስታን ወታደራዊ መሪ የተደነቁ ሲሆን፣ በወታደራዊ መለዮአቸው እና በማዕረግ ዲዛይናቸው በተለይም በፊልድ ማርሻል አሲም ሙኒር እንደተደነቀ ተናግሯል። ባለሥልጣናቱ ትራምፕ ስለ ፓኪስታን ያላቸው አጠቃላይ ግንዛቤ በጣም አዎንታዊ ነው ሲሉም ተናግረዋል - ትራምፕ አሸናፊዎችን ይወዳል፣ እና ተደንቋል። እንዲያውም፣ '
እነዚህ ፓኪስታናውያን እነማን ናቸው? ትንሽ ሀገር ነች... ሕንዳውያንን ግን ደበደቡ'
ማለቱ ተዘግቧል።

🇺🇸🇮🇷🇸🇦 NBC News: ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ሰፈሮች ላይ ይፋ ከተደረገው የበለጠ ጉዳት አድርሳለች። እንደዘገባው፣ የአሜሪካ ባለስልጣናት እና የኮንግረስ
🇺🇸🇮🇷🇸🇦 NBC News: ኢራን በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ሰፈሮች ላይ ይፋ ከተደረገው የበለጠ ጉዳት አድርሳለች። እንደዘገባው፣ የአሜሪካ ባለስልጣናት እና የኮንግረስ አባላት ስለ ጉዳቱ መጠን ትክክለኛ መረጃ አልተነገራቸውም። ➡️  የአሜሪካ የአየር መከላከያ ቢኖርም፣ በገልፍ አገራት የሚገኙ የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች ያለማቋረጥ ጥቃት ደርሶባቸዋል፣ የኢራን F-5 ተዋጊ ጀት ጥቃትን ጨምሮ። ➡️  የጉዳቱ መጠን ከፍተኛ ነው፣ የጥገና ወጪዎች በ 10 ቢሊዮኖች የሚቆጠር ሊሆን ይችላሉ.

🇺🇸🇮🇷🇵🇰⚡️ - ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለAxios - አሁን ባለው ሁኔታ [በድርድሩ] ዊትኮፍ እና ኩሽነርን 18 ሰዓታት በሚፈጅ በረራ ወደ ፖኪስታን የመላኩ ፋይዳ ምንም አይታየኝም። በጣም ረጅ
🇺🇸🇮🇷🇵🇰⚡️ - ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለAxios -
አሁን ባለው ሁኔታ [በድርድሩ] ዊትኮፍ እና ኩሽነርን 18 ሰዓታት በሚፈጅ በረራ ወደ ፖኪስታን የመላኩ ፋይዳ ምንም አይታየኝም። በጣም ረጅም ነው። በስልክ ልናደርገው እንችላለን። ኢራን ከፈለች ትደውል። ሁሉም መጫዎቻ ካርዶች አሉን። እዚያ ተቀምጠን ስለ ምንም ነገር ለመነጋገር አንሄድም።

❗️በጋዛ ሰርጥ በ21 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያው ጊዜ፣ የቀበሌ ምርጫዎች ተካሂደዋል። ለምርጫ የተመዘገቡ ፍልስጤማውያንም ድምጽ ሲሰጡ መዋላቸው ታውቋል።
+2
❗️በጋዛ ሰርጥ በ21 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያው ጊዜ፣ የቀበሌ ምርጫዎች ተካሂደዋል። ለምርጫ የተመዘገቡ ፍልስጤማውያንም ድምጽ ሲሰጡ መዋላቸው ታውቋል።

🇬🇷🇫🇷⚡️ - የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪሪያኮስ ሚትሶታኪስ፡
ኢማኑኤል ማክሮንን በድጋሚ ማመስገን እፈልጋለሁ፣ ምክንያቱም ግሪክ የፈረንሳይን ድጋፍ ከፈለገች ፈረንሳይ እዚያ እንደምትገኝ በግልፅ በመናገሩ።

—🇫🇷/🇬🇷/ 🇹🇷 ትኩስ፡ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በአቴንስ ባደረጉት ይፋዊ ጉብኝት፣ ግሪክ ሉዓላዊነቷ በቱርክ በምንም ዓይነት መንገድ አደጋ ላይ የሚገባ ከሆነ፣ ፈረንሳይ ከግ
+1
—🇫🇷/🇬🇷/ 🇹🇷 ትኩስ፡ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በአቴንስ ባደረጉት ይፋዊ ጉብኝት፣ ግሪክ ሉዓላዊነቷ በቱርክ በምንም ዓይነት መንገድ አደጋ ላይ የሚገባ ከሆነ፣ ፈረንሳይ ከግሪክ ጎን እንደምትቆም ቃል ገብተዋል። ➡️ ማክሮን "ቱርክ ግሪክን የምታስፈራራ ከሆነ፣ እዚህ እንገኛለን" ብሏል።

🇮🇷🇵🇰⚡️ - የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ፣ ከፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሻባዝ ሸሪፍ ጋር፣ በኢስላማባድ ተገናኝተዋል።

🇮🇱🇱🇧የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስቴር፣ ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ወደ ዋሽንግተን በማቅናት ከሊባኖስ ፕሬዝዳንት፣ ዮሴፍ አውን፣ ጋር ውይይት ያደርጋል።  .

🇮🇷⚡️ - የኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን - ጠላቶቻችን መሠረተ ልማቶቻችንን ያፈርሳሉ፣ አሁን ያለውን የሕዝባችንን የድል አድራጊነት ጠንካራ መንፈስ ሊሰብሩ ይፈልጋሉ። ይሄን ለማሳካት ከበባቸውን እያጠነከሩ እና ሸምቀቆውን እያጠበቡ ይሞክራሉ። ለአሁኑ ሕዝባችን መስዋዕትነት እንዲከፍል አንፈልግም፣ ነገር ግን አባካኝነትን ማስቀረት ይገባል። ለምሳሌ፣ በቤት ውስጥ አሥር አምፖል የሚበራ ከሆነ፣ ሁለት ማብራት። ችግሩ ምንድነው? 

🇮🇱 🇺🇸 ከአሜሪካ ጋር እጅ እና ጓንት ሆነን፣ በአንድነት ነው እየተንቀሳቀስን ያለነው በኢራን ላይ። በሊባኖስም ላይ እንደዚያው። ትናንትም ደብድበናል፣ ዛሬም ደብድበናል …… የመካከለኛውን ምሥራቅ ገፅታ እስከምንለውጠው ድረስ!" — ኔታንያሁ Netanyahu 🚩

200 ወጣት ኢትዮጵያውያን በሳውዲ ሊረሸኑ ነው‼️ የትግራይ ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ በጅምላ የሞት ፍርድ ተላልፎባቸዋል ያላቸውን ከ200 በላይ ኢትዮጵያዊያን ሕይወት ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እንዲታደግ በደብዳቤ ጠይቋል። ቢሮው፣ "መንጠጋ አሲሪ" በተባለ አካባቢ "ከሚስ ምሽት" በሚባል እስር ቤት ውስጥ ከትግራይ፣ ኦሮሚያ እና አማራ የሄዱ ከ200 በላይ ፍልሠተኞች በጅምላ የሞት ቅጣታቸውን እየተጠባበቁ እንደሚገኙ መረጃ ደርሶኛል ብሏል። ሥራ ፍለጋ የተሠደዱ ፍልሠተኞች የሕግ ጥብቅና አገልግሎት ባላገኙበት ሁኔታ የተላለፈባቸው የጅምላ የሞት ፍርድ፣ "ኢሰብዓዊ" እና የሁለቱን አገራት "መልካም ግንኙነት የሚያኮላሽ" ሆኖ ሳለ የፌደራል መንግስቱ በጉዳዩ ላይ ግድ እንዳልሰጠው ቢሮው ገልጧል። ውሳኔው በሕዝቡ ላይ "የስነ ልቦና ጠባሳ" የሚፈጥር እና "ብሄራዊ የሀገር ክብራችን የሚያዋርድ" ነው ያለው ቢሮው፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቢሮ በኢትዮጵያ ከሚገኘው የሳዑዲ ዓረቢያ ኢምባሲ ጋር በመተባበር ጉዳዩ "በዲፕሎማሲያዊ መንገድ" እልባት እንዲያገኝና የፍልሠተኞችን ሕይወት እንዲታደግ ጠይቋል።

⚡️ ፖፕ ሊዮ አሥራ አራተኛ፣ "በሊባኖስ የተገደለ ሙስሊም ልጅ ፎቶ በኪሴ ይዤ ነው የምዞረው … … ጦርነትን መደገፍ አልችልም።"

⚡️🇨🇳🇮🇷 ዛሬ በኢራን የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ፣ ሁሉም የቻይና ዜጎች ኢራንን ለቀው እንዲወጡ ሁለተኛ የአስቸኳይ ጊዜ ትዕዛዝ አውጥቷል። የመጀመሪያው ትዕዛዝ የወጣው፣ ጦርነቱ ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀደም ብሎ በፈረንጆች Feb 27 ነበር።

🇺🇸 ⚡️🇮🇷 ልክ ከኢራን ጋር ጦርነት ከመጀመሩ በፊት እንደነበረው፣ ዛሬም የእስራኤል ቤን-ጉሪዮን አውሮፕላን ማረፊያ በድጋሜ በአሜሪካ ነዳጅ የሚሞሉ አውሮፕላኖች KC-135 KC-46 ተጨናንቋል ተብሏል። ድርድሩ ምንም ውጤት ካላመጣ፣ አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃቱን ለመቀጠል በዝግጅት ላይ እንደሆነች ያሳያል፣ ተብሏል።

🇺🇸⚰ አሜሪካ በፌዴራል ደረጃ የሞት ፍርድን፣ በርሸና (በተኳሽ ቡድን)፣ በኤሌክትሪክ እና በጋዝ ማስፈጸም እንዲቻል የሚያደርግን ፍቃድ አጽድቃለች። ይህን ያለችው 'ለገዳይ ክትባት' መድኃኒቶችን ማ
🇺🇸⚰ አሜሪካ በፌዴራል ደረጃ የሞት ፍርድን፣ በርሸና (በተኳሽ ቡድን)፣ በኤሌክትሪክ እና በጋዝ ማስፈጸም እንዲቻል የሚያደርግን ፍቃድ አጽድቃለች። ይህን ያለችው 'ለገዳይ ክትባት' መድኃኒቶችን ማግኘቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ አስቸጋሪ ሆኗል በሚል ነው።