የቀጠናው ተመልካች
前往频道在 Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
显示更多未指定国家未指定类别
4 321
订阅者
+824 小时
-47 天
-7130 天
帖子存档
4 330
🇺🇸🇮🇷🇵🇰⚡️ - ፕሬዝዳንት ትራምፕ ለAxios -
አሁን ባለው ሁኔታ [በድርድሩ] ዊትኮፍ እና ኩሽነርን 18 ሰዓታት በሚፈጅ በረራ ወደ ፖኪስታን የመላኩ ፋይዳ ምንም አይታየኝም። በጣም ረጅም ነው። በስልክ ልናደርገው እንችላለን። ኢራን ከፈለች ትደውል። ሁሉም መጫዎቻ ካርዶች አሉን። እዚያ ተቀምጠን ስለ ምንም ነገር ለመነጋገር አንሄድም።
4 330
+2
❗️በጋዛ ሰርጥ በ21 ዓመታት ውስጥ ለመጀመሪያው ጊዜ፣ የቀበሌ ምርጫዎች ተካሂደዋል። ለምርጫ የተመዘገቡ ፍልስጤማውያንም ድምጽ ሲሰጡ መዋላቸው ታውቋል።
4 330
🇬🇷🇫🇷⚡️ - የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪሪያኮስ ሚትሶታኪስ፡
ኢማኑኤል ማክሮንን በድጋሚ ማመስገን እፈልጋለሁ፣ ምክንያቱም ግሪክ የፈረንሳይን ድጋፍ ከፈለገች ፈረንሳይ እዚያ እንደምትገኝ በግልፅ በመናገሩ።
4 330
+1
—🇫🇷/🇬🇷/ 🇹🇷 ትኩስ፡ የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በአቴንስ ባደረጉት ይፋዊ ጉብኝት፣ ግሪክ ሉዓላዊነቷ በቱርክ በምንም ዓይነት መንገድ አደጋ ላይ የሚገባ ከሆነ፣ ፈረንሳይ ከግሪክ ጎን እንደምትቆም ቃል ገብተዋል።
➡️ ማክሮን "ቱርክ ግሪክን የምታስፈራራ ከሆነ፣ እዚህ እንገኛለን" ብሏል።
4 330
🇮🇷🇵🇰⚡️ - የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ፣ ከፓኪስታን ጠቅላይ ሚኒስትር ሻባዝ ሸሪፍ ጋር፣ በኢስላማባድ ተገናኝተዋል።
4 330
🇮🇱🇱🇧የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስቴር፣ ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምንታት ወደ ዋሽንግተን በማቅናት ከሊባኖስ ፕሬዝዳንት፣ ዮሴፍ አውን፣ ጋር ውይይት ያደርጋል። .
4 330
🇮🇷⚡️ - የኢራን ፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን
- ጠላቶቻችን መሠረተ ልማቶቻችንን ያፈርሳሉ፣ አሁን ያለውን የሕዝባችንን የድል አድራጊነት ጠንካራ መንፈስ ሊሰብሩ ይፈልጋሉ። ይሄን ለማሳካት ከበባቸውን እያጠነከሩ እና ሸምቀቆውን እያጠበቡ ይሞክራሉ። ለአሁኑ ሕዝባችን መስዋዕትነት እንዲከፍል አንፈልግም፣ ነገር ግን አባካኝነትን ማስቀረት ይገባል። ለምሳሌ፣ በቤት ውስጥ አሥር አምፖል የሚበራ ከሆነ፣ ሁለት ማብራት። ችግሩ ምንድነው?
4 330
🇮🇱 🇺🇸 ከአሜሪካ ጋር እጅ እና ጓንት ሆነን፣ በአንድነት ነው እየተንቀሳቀስን ያለነው በኢራን ላይ።
በሊባኖስም ላይ እንደዚያው።
ትናንትም ደብድበናል፣ ዛሬም ደብድበናል …… የመካከለኛውን ምሥራቅ ገፅታ እስከምንለውጠው ድረስ!" — ኔታንያሁ Netanyahu
🚩
4 330
Repost from ሞዐ ሚዲያ- Moaa Media…✍
200 ወጣት ኢትዮጵያውያን በሳውዲ ሊረሸኑ ነው‼️
የትግራይ ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ በጅምላ የሞት ፍርድ ተላልፎባቸዋል ያላቸውን ከ200 በላይ ኢትዮጵያዊያን ሕይወት ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እንዲታደግ በደብዳቤ ጠይቋል። ቢሮው፣ "መንጠጋ አሲሪ" በተባለ አካባቢ "ከሚስ ምሽት" በሚባል እስር ቤት ውስጥ ከትግራይ፣ ኦሮሚያ እና አማራ የሄዱ ከ200 በላይ ፍልሠተኞች በጅምላ የሞት ቅጣታቸውን እየተጠባበቁ እንደሚገኙ መረጃ ደርሶኛል ብሏል። ሥራ ፍለጋ የተሠደዱ ፍልሠተኞች የሕግ ጥብቅና አገልግሎት ባላገኙበት ሁኔታ የተላለፈባቸው የጅምላ የሞት ፍርድ፣ "ኢሰብዓዊ" እና የሁለቱን አገራት "መልካም ግንኙነት የሚያኮላሽ" ሆኖ ሳለ የፌደራል መንግስቱ በጉዳዩ ላይ ግድ እንዳልሰጠው ቢሮው ገልጧል። ውሳኔው በሕዝቡ ላይ "የስነ ልቦና ጠባሳ" የሚፈጥር እና "ብሄራዊ የሀገር ክብራችን የሚያዋርድ" ነው ያለው ቢሮው፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቢሮ በኢትዮጵያ ከሚገኘው የሳዑዲ ዓረቢያ ኢምባሲ ጋር በመተባበር ጉዳዩ "በዲፕሎማሲያዊ መንገድ" እልባት እንዲያገኝና የፍልሠተኞችን ሕይወት እንዲታደግ ጠይቋል።
4 330
⚡️🇨🇳🇮🇷 ዛሬ በኢራን የሚገኘው የቻይና ኤምባሲ፣ ሁሉም የቻይና ዜጎች ኢራንን ለቀው እንዲወጡ ሁለተኛ የአስቸኳይ ጊዜ ትዕዛዝ አውጥቷል። የመጀመሪያው ትዕዛዝ የወጣው፣ ጦርነቱ ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀደም ብሎ በፈረንጆች Feb 27 ነበር።
4 330
🇺🇸 ⚡️🇮🇷 ልክ ከኢራን ጋር ጦርነት ከመጀመሩ በፊት እንደነበረው፣ ዛሬም የእስራኤል ቤን-ጉሪዮን አውሮፕላን ማረፊያ በድጋሜ በአሜሪካ ነዳጅ የሚሞሉ አውሮፕላኖች KC-135 KC-46 ተጨናንቋል ተብሏል። ድርድሩ ምንም ውጤት ካላመጣ፣ አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃቱን ለመቀጠል በዝግጅት ላይ እንደሆነች ያሳያል፣ ተብሏል።
4 330
🇺🇸⚰ አሜሪካ በፌዴራል ደረጃ የሞት ፍርድን፣ በርሸና (በተኳሽ ቡድን)፣ በኤሌክትሪክ እና በጋዝ ማስፈጸም እንዲቻል የሚያደርግን ፍቃድ አጽድቃለች። ይህን ያለችው 'ለገዳይ ክትባት' መድኃኒቶችን ማግኘቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ አስቸጋሪ ሆኗል በሚል ነው።
4 330
🇺🇸 ትኩስ፡ "የ CBS News የሕዝብ አስተያየት እንደሚያሳየው ከሆነ፣ ከ70% በላይ የሚሆኑ አሜሪካውያን እንደ ምግብ፣ መኖሪያ ቤት እና የጤና ኢንሹራንስ ያሉ አስፈላጊ ነገሮችን ለመግዛት እየተቸገሩ እንደሆነ ይናገራሉ።"
ጦርነቶች መዘዝ አላቸው!
4 330
🇺🇸⚔️🇨🇳 The Washington Post: የትራምፕ አስተዳደር በቻይና በሚገኘው ዋና የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ እና የኢራንን ዘይት በማጓጓዝ ላይ በተሳተፉ ወደ 40 የሚጠጉ የመርከብ ኩባንያዎች እና ታንከሮች ላይ፣ የኢኮኖሚ ማዕቀብ መጣሉን አስታወቀ። እርምጃው፣ ትራምፕ ከኢራን ጋር የንግድ ሥራ በሚሠሩ ኩባንያዎች እና አገሮች ላይ ሁለተኛ ማዕቀብ ለመጣል ያደረገውን ዛቻ ተግባራዊ አድርጎታል። እንዲሁም የሪፐብሊካን አስተዳደሩ፣ የኢራንን ቁልፍ የገቢ ምንጭ - የነዳጅ ኤክስፖርት- ለመቁረጥ የሚያደርገው አጠቃላይ የተጠናከረ ዘመቻ አካል ነው። ኩባንያዎቹን ከአሜሪካ የፋይናንሺያል ስርዓት የሚቆርጠው እና ከእነሱ ጋር የንግድ ሥራ የሚፈጽም ማንኛውንም አካል የሚቀጣው ማዕቀቡ፣ ትራምፕ እና ዢ ጂንፒንግ በቻይና ከመገናኘታቸው ጥቂት ሳምንታት ቀደም ብሎ የተከሰተ ሆኗል።
4 330
🇮🇷❌🇺🇸🛥 - ኢራን IRGC ሌላ መርከብ መያዙ ተሰማ። አዲስ የተያዘውን መርከብ አስመልክቶ ከ IRGC የተሰጠ ሙሉ መግለጫ እንዲህ ይላል፡
- ከአሜሪካ ጦር ጋር በመተባበር የተጠረጠረ መርከብ፣ ማስጠንቀቂያዎችን ችላ በማለቱ እና ጥሰቶችን በመፈፀሙ በቁጥጥር ሥር ሊውል ችሏል።
4 330
- 🇺🇸 /🇵🇰/ 🇮🇷 🇺🇸 ቴህራን ወደ ፓኪስታን ከበረሩት ዊትኮፍ እና ኩሽነር ጋር ለመደራደር አላሰበችም - Tasnim.
እንደ Tasnim ገለጻ፣ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ኢራን ከፓኪስታን ጋር ያለውን ጦርነት ለማቆም ያላትን አቋም ለመወያየት ወደ ኢስላማባድ እየተጓዙ እንጂ፣ ከአሜሪካ ልዑካን ለመገናኘት አይደለም።
4 330
- 🇺🇸 /🇵🇰/ 🇮🇷 ኢራናዊው ጋዜጠኛ ከኢስላማባድ - ኩሽነር እና ዊትኮፍ ለምን ወደ ኢስላማባድ እንደሚላኩ አናውቅም፣ ከእነሱ ጋር የሚደረግ ምንም ዓይነት ስብሰባ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አጀንዳ ውስጥ የለም። በተጨማሪም፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ እነሱ እዚህ እስኪደርሱ ፓኪስታንን ለቆ ሊሄድ ይችላል።
