የቀጠናው ተመልካች
Kanalga Telegram’da o‘tish
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Ko'proq ko'rsatishMamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
4 327
Obunachilar
+2824 soatlar
+307 kun
-4230 kun
Postlar arxiv
4 330
🇺🇸 ትኩስ፡ "የ CBS News የሕዝብ አስተያየት እንደሚያሳየው ከሆነ፣ ከ70% በላይ የሚሆኑ አሜሪካውያን እንደ ምግብ፣ መኖሪያ ቤት እና የጤና ኢንሹራንስ ያሉ አስፈላጊ ነገሮችን ለመግዛት እየተቸገሩ እንደሆነ ይናገራሉ።"
ጦርነቶች መዘዝ አላቸው!
4 330
🇺🇸⚔️🇨🇳 The Washington Post: የትራምፕ አስተዳደር በቻይና በሚገኘው ዋና የነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ እና የኢራንን ዘይት በማጓጓዝ ላይ በተሳተፉ ወደ 40 የሚጠጉ የመርከብ ኩባንያዎች እና ታንከሮች ላይ፣ የኢኮኖሚ ማዕቀብ መጣሉን አስታወቀ። እርምጃው፣ ትራምፕ ከኢራን ጋር የንግድ ሥራ በሚሠሩ ኩባንያዎች እና አገሮች ላይ ሁለተኛ ማዕቀብ ለመጣል ያደረገውን ዛቻ ተግባራዊ አድርጎታል። እንዲሁም የሪፐብሊካን አስተዳደሩ፣ የኢራንን ቁልፍ የገቢ ምንጭ - የነዳጅ ኤክስፖርት- ለመቁረጥ የሚያደርገው አጠቃላይ የተጠናከረ ዘመቻ አካል ነው። ኩባንያዎቹን ከአሜሪካ የፋይናንሺያል ስርዓት የሚቆርጠው እና ከእነሱ ጋር የንግድ ሥራ የሚፈጽም ማንኛውንም አካል የሚቀጣው ማዕቀቡ፣ ትራምፕ እና ዢ ጂንፒንግ በቻይና ከመገናኘታቸው ጥቂት ሳምንታት ቀደም ብሎ የተከሰተ ሆኗል።
4 330
🇮🇷❌🇺🇸🛥 - ኢራን IRGC ሌላ መርከብ መያዙ ተሰማ። አዲስ የተያዘውን መርከብ አስመልክቶ ከ IRGC የተሰጠ ሙሉ መግለጫ እንዲህ ይላል፡
- ከአሜሪካ ጦር ጋር በመተባበር የተጠረጠረ መርከብ፣ ማስጠንቀቂያዎችን ችላ በማለቱ እና ጥሰቶችን በመፈፀሙ በቁጥጥር ሥር ሊውል ችሏል።
4 330
- 🇺🇸 /🇵🇰/ 🇮🇷 🇺🇸 ቴህራን ወደ ፓኪስታን ከበረሩት ዊትኮፍ እና ኩሽነር ጋር ለመደራደር አላሰበችም - Tasnim.
እንደ Tasnim ገለጻ፣ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ኢራን ከፓኪስታን ጋር ያለውን ጦርነት ለማቆም ያላትን አቋም ለመወያየት ወደ ኢስላማባድ እየተጓዙ እንጂ፣ ከአሜሪካ ልዑካን ለመገናኘት አይደለም።
4 330
- 🇺🇸 /🇵🇰/ 🇮🇷 ኢራናዊው ጋዜጠኛ ከኢስላማባድ - ኩሽነር እና ዊትኮፍ ለምን ወደ ኢስላማባድ እንደሚላኩ አናውቅም፣ ከእነሱ ጋር የሚደረግ ምንም ዓይነት ስብሰባ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ አጀንዳ ውስጥ የለም። በተጨማሪም፣ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ እነሱ እዚህ እስኪደርሱ ፓኪስታንን ለቆ ሊሄድ ይችላል።
4 330
- 🇮🇱 /🇱🇧/ 🇮🇷 አዲስ፡ በደቡባዊ ሊባኖስ፣ ቢንት ጅቤይል በተባለች ከተማ መሃል፣ ላለፉት ሁለት ሳምንታት በአንድ ህንፃ ውስጥ የተከበቡ ስድስት የሂዝቦላህ ተዋጊዎች፣ የእስራኤል ጦር በቅርብ ርቀት ውጊያ ደጋግሞ ሊያጠፋቸው ባለመቻሉ፣ በአየር ድብደባ ገድሏቸዋል።
4 330
CNN: ትራምፕ፣ ልዑኮቹን ዊትኮፍ እና ኩሽነርን፣ ወደ ኢስላምአባድ የኢራንን የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር እንዲገናኙ ልኳቸዋል።
ከሰዓታት በፊት አልጀዚራ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴሩ ከአሜሪካ ልዑካን ጋር በምንም መልክ መገናኘት ዕቅዱ እንዳልሆነ ዘግቦ ነበር።
4 330
🇮🇷🚫🇺🇸 የኢራን የመንግስት ቴሌቪዥን ጦርነቱ ዳግም ከተነሳ ኢላማ ይደረጋል ያለውን የኢነርጂ ተቋማት ዝርዝር አውጥቷል።
• 🇶🇦 በኳታር ውስጥ Ras Gas እና Ras Laffan LNG መገልገያዎች
• 🇦🇪 በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ውስጥ Das እና Zirku ደሴቶች (ዋና የባሕር ዳርቻ የነዳጅ እና ጋዝ ማዕከሎች)
• 🇸🇦 በሳውዲ አረቢያ ውስጥ Ab Qayk, Safaniya እና Kurais የነዳጅ እና ጋዝ መሠረተ-ልማቶች እና መገልገያዎች
• 🇰🇼 በኩዌት ውስጥ የ Burgan የነዳጅ ዘይት መሬቶች።
🔴 እነዚህን IRGC እንደሚያጠቃ አሳስቧል።
4 330
🇮🇷🇵🇰🇴🇲🇷🇺⚡️ - የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራክቺ፣ ኢስላማባድን በሚጎበኙበት ወቅት ከአሜሪካ ጋር ምንም ዓይነት ውይይት ወይም ግንኙነት አያደርጉም። ይልቁንም፣ በሁለትዮሽ - በኢራን እና በፖኪስታን- ግንኙነት ላይ ያተኮሩ መሆናቸውን አልጀዚራ አንድ ከፍተኛ የኢራን ምንጭን ጠቅሶ ዘግቧል።
➡️ ሞስኮ፣ ዲፕሎማሲያዊ አለመግባባቱን ለመፍታት የሚረዱ ሀሳቦች ሊኖሯት ይችላልም ተብሏል። ኦማን ከቴህራን ጋር ያላት የጠበቀ ግንኙነትም እንዲሁ፣ ኢራን ወደ ድርድር እንድትመለስ በማመቻቸት ረገድ ሚና ሊጫወት ይችላል።
ኢራን 'ከአሜሪካ ጋር አልደራደርም' በሚለው አቋሟ እስካሁን እንደፀናች ነው።
4 330
+2
🇷🇺 🌎ሩሲያ አዳዲስ የምድር ምስሎችን ለቅቃለች።
የሩሲያ ስፔስ ተቋም፣ Elektro-L. በተባለች ሳተላይቱ የተነሱ አዳዲስ የምድር ምስሎችን አጋርቷል።
4 330
- 🇮🇷 / አዲስ፡ የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራክቺ ከኢራቅ ኩርዲስታን ፕሬዝዳንት ጋር ተገናኝቶ፣ ድንበር ተሻጋሪ ሽብርተኝነትን ማስቆም አስፈላጊ መሆኑን አሳውቋል። አራክቺ በተጨማሪም፣ ኢራን ኩርዶች ከጠላት አሜሪካ ጋር እየተባበሩ ነው ብላ ባሰበችበት ጊዜ ሁሉ፣ በቦምብ ለመምታት እና በኤርቢል የአሸባሪ መሪዎችን ለማጥፋት ወደ ኋላ እንደማትል ተናግሯል።
4 330
🇺🇸🇮🇷Pets Hegseth በኢራን ወደቦች ላይ ስላለው እገዳ -
የአሜሪካ ጦር ተወዳዳሪ የለውም - ኃይልን ማቀድ፣ ለተቃዋሚዎች መተላለፍን መከልከል እና በመረጥነው ጊዜ እና ቦታ ፍላጎታችንን መጠበቅ እንችልበታለን። ከዩናይትድ ስቴትስ የባሕር ኃይል ፈቃድ ውጭ፣ ማንም ከሆርሙዝ የባሕር መስመር ወደ የትኛውም የዓለም ክፍል የሚጓዝ የለም።
4 330
🇺🇸❌🇮🇷- የአሜሪካ ጦር ሚንስቴር Pete Hegseth አሁን: የኢራን ጦር ወደ የባሕር ወንበዴዎች ቡድን ተቀይሯል፣ እነሱም አሸባሪዎች ናቸው።
4 330
🇺🇸⚔️🇮🇷 US Central Command (ማዕከላዊ እዝ)፡ ከብዙ አሥርተ ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት አውሮፕላኖች አጓጓዦች ደምሳሽ መርከቦች በመካከለኛው ምስራቅ በአንድ ጊዜ እየሠሩ ነው። የ US አውሮፕላን አጓጓዥ መርከቦች፣ አብርሃም ሊንከን (ሲቪኤን 72)፣ ጄራልድ ፎርድ (ሲቪኤን 78) እና ጆርጅ ኤችደብሊው ቡሽ (ሲቪኤን 77)፣ ከ200 በላይ አውሮፕላኖችን እና 15,000 መርከበኞችን እና የባሕር ኃይል ወታደሮችን አቅፈው በቀጠናው እየተንቀሳቀሱ ናቸው።
4 330
🇺🇸❌🇮🇷🛢 - ኢራን የድፍድፍ ዘይት የማከማቻ አቅሟ እያለቀ በመምጣቱ፣ የድሮውን የነዳጅ መርከብ Nasha ን ከጡረታ አውጥታ ወደ ሥራ መልሳለች።
የ30 ዓመቱ ታንከር ለብዙ ዓመታት ባዶ ሆኖ በመልህቁ ታስሮ ቆይቶ የነበረ ሲሆን፣ አሁን እንደ የባሕር ዳርቻ ማከማቻነት እንዲያገለግል ሆኖ ወደ ሥራ ገብቷል።
የአሜሪካ እገዳ እየጠነከረ ነው፣ ኢራንም በአብዛኛው ዘይት ወደ ውጭ መላክ አልቻለችም። በመሆኑም ኢራን የማከማቻ አቅሟን አሟጣ ከተጠቀመች በኋላ፣ የነዳጅ ጉድጓዶቿን መዝጋት ሊኖርባት ይችላል። ይህ ደግሞ በጣም ከባድ እና ውስብስብ ሥራ ሲሆን፣ መልሶ ለመክፈት ወራቶችን ይወስዳል።
4 330
🇺🇸🇮🇷 "አሜሪካ ከኢራን ጋር የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት ለመቅደድ በዝግጅት ላይ ትገኛለች፣ የጥቃት ዒላማዎችንም እያዘጋጀች ነው CNN
ከዒላማዎቹ መካከል በሆርሙዝ ወሽመጥ የኢራን የባሕር ኃይል ይገኝበታል።"
4 330
🇸🇦 🤝 🇺🇸 ዛሬ በሳዑዲ ዓረቢያ የአሜሪካ ግዙፍ ወታደራዊ ነዳጅ ጫኝ አውሮፕላኖች፣ እጅግ በብዛት ሲንቀሳቀሱ ታይተዋል። በአሁኑ ጊዜ፣ በአየር ላይ ቢያንስ ስድስት "የሚበሩ ታንከሮች" እንዳሉ ይታያል። ይህም በተዘዋዋሪ፣ በኢራን ላይ ሌላ ዙር ድብደባ ሊጀመር ቋፍ ላይ እንደተደረሰ እና ዛሬም እነ ሳዑዲ ለአሜሪካ ጦር ሽፋን እየሰጡ እንደሆነ አመላካች ነው።
4 330
🇵🇸 🇱🇧
ከእስራኤል በፊት ያልነበረችው እና በኋላ የተፈበረከችው ዮርዳኖስ እና ሁሉም ከፍልስጤም የመጡ እና ቃል በቃል ወንድሞቻችን ብለን የምንጠራቸው ዮርዳኖሳውያን፣ እንደ ሊባኖስ ሕዝብ ከእኛ (ፍልስጤማዊያን) ጋር አልቆሙም።
አዎ! ሊባኖሶች ጎረቤታችን ናቸው፣ ግን ዮርዳኖሳዊያን ለእኛ በጣም ይቀርቡን ነበር። ወደ 70% የሚሆኑት ከፍልስጤም የመጡ ናቸው። ድርጊታቸውን ላየ ግን፣ በጭራሽ እንደዚያ አይመስሉም። ሊባኖስን ሁሌም እናመሰግናለን።" Palestinian Observer
