🌹قَـــنَـــاةُ بِـــنـــتْ مُـــحَـــمَّـــد 🌹
Yopiq kanal
Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
546
Obunachilar
-224 soatlar
+177 kunlar
+5730 kunlar
Postlar arxiv
🌹በስደት ለሚገኙ፣ የናፍቆትና የብቸኝነት ስሜት ለሚፈታተናቸው ጀግና እህቶቻችን የኢድ መልዕክቴ🌹
👑 የኔ ጀግና... የፅናትና የፍቅር ተምሳሌት የሆንሽው ስደተኛዋ ሰለፊዮ እህቴ! 👑
ኢድ ሲመጣ የሀገር ሽታ፣ የእናት ምርቃት፣ የአባት እቅፍና የወንድም እህት ሳቅ ይበልጥ እንደሚናፍቅና ልብን እንደሚከብድ አውቃለሁ። አዎ... በሰው ሀገር ላይ በዓል እንደ በዓል ላይሰማሽ ይችላል። ሌሎች ቤተሰቦቻቸውን አቅፈው ሲደሰቱ፣ አንቺ በብቸኝነትና በናፍቆት ማዕበል መሀል ሆነሽ በስልክ ስክሪን ላይ በሚታይ ምስል ትዝታሽን ልታክሚ ትሞክሪ ይሆናል።
ግን ውድ እህቴ ሆይ... ለአፍታ ቆም ብለሽ እራስሽን ተመልከቺ!
አንቺ እኮ ተራ ስደተኛ አይደለሽም፤ አንቺ ለአገርሽ ኩራት፣ ለቤተሰብሽ የጀርባ አጥንት፣ ለቤተሰቦችሽ የደስታቸው ምንጭ ነሽ ለታናናሾችሽ የተስፋ ጮራ ነሽ። ዛሬ በሰው ሀገር የምታፈስሺው እያንዳንዱ የላብ ጠብታና በብቸኝነት የምታፈሽው እያንዳንዱ የናፍቆት እንባ አላህ ዘንድ ትልቅ
ዋጋ አለው። በዓላትን ከቤተሰብሽ ርቀሽ የምታሳልፊው እራስ ወዳድ ስለሆንሽ ሳይሆን፣ እነሱን ለማስደሰትና የነገ ሕይወታቸውን ብሩህ ለማድረግ ደስታቸው የተሟላ እንዲሆን ምንም እንዳይጎድልባች ራስሽን መስዋዕት ስላደረግሽ ነው።
የኔ ጀግና እህት ! ዛሬ ልብሽ በናፍቆት ቢደማም፣ ከዚህ በስተጀርባ ግን የሚያምርና ብሩህ የሆነ የአላህ ራህመት እንዳለ በፍጹም አትዘንጊ። ዛሬ አንቺ በሩቅ ሆነሽ የምትልኪው ስጦታ በቤተሰቦችሽ ውስጥ ትልቅ ደስታን እንደሚፈጥር ሁሉ፣ አላህም በስደት ሀገር ባለሽበት ቦታ ላይ ሰላሙንና በረካውን ያውርድልሽ።
ጀግናዬ ይሄም ቀን ያልፋል! ነገ በሀገርሽ፣ በገዛ ቤትሽ፣ ከወላጆችሽ ምርቃትና ከምትወጃቸው ሰዎች እቅፍ ጋር በደስታና በሳቅ የምታከብሪበት ጊዜ በእርግጥ ይመጣል። ያኔ የዛሬው ትግልሽ ለጣፋጭ ትዝታ ይበቃል። የዛሬው ድካምሽ ነገ
በሀገርሽ ላይ በኩራት እንድትቆሚ ያደርግሻል።
ጀግናዬ ዛሬ የደስታ ቀን ነው! የጌታሽ ስጦታ ነውና ራስሽን አታሳዝኚ። ፈገግ በይ፣ የኢድን ልብስሽን ልበሺ፣ ልብሽን በምስጋና ሙሊው። ከቻልሽ ከውድ ሰለፊይ እህቶችሽ ጋር ተገናኝተሽ ከነሱ ጋር አላህን በማያስቆጣ መልኩ ኢድን ደስተኛ ሁነሽ አሳልፊ አብሽሪ አላህ ደስተኛ ያድርግሽ ።አንቺ ኮ ለኛም ሆነ ለቤተሰቦችሽ እውነተኛ ልዕልትና የቁም ጀግና ነሽ!
🌹 ኢድ ሙባረክ! ውዷና ብርቱዋ ስደተኛዋ እህቴ!🌹
አላህ ዕድሜሽን በበረካ፣ በጤናና በደስታ ያርዝመው። የሚመጣው ዓመት በሀገርሽ፣ በናፈቅሽው ቅጥር ጊቢ ውስጥ ከቤተሰቦችሽ ጋር የምታከብሪው ያድርግሽ።
ከወንድማችሁ አቡ ሒበቲላህ ሁሰይን
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
اَلسَّلَامُ عَلَيْكُمْ وَرَحْمَةُ اللّٰـهِ وَبَرَكاتُهُ
عيدكم مبارك واخواتي واخواني
ኢድ ሙባረክ በሀገር ላላችሁ፡
እድሁም በስደት ኢድ ሙባረክ ፡
አልኩኝ ባሴትና ናፍቆት የርሱ ፡
ፍቃድ ሁኖ የአላህ ችሎታ የኢድ
አል አድሃ በዓል መጣልን የአላህ
ስጦታ ይሄው ለዚህ አበቃን ፈቅዶ
የኛ ጌታ አልሀምዱሊላህ ኢድ ሙባረክ
በሀገር ያላችሁ በዚህ ታላቅ ወራት
ላልተለያያችሁ ኢድ ሙባረክ አልኩኝ
በስደት ላላችሁ በሀሳብ እና ናፍቆት
በሰው ቤት ላላችሁ ኢድ ሙባረክ
አልኩኝ በስደት ጎዳና አሁን በዚህ
ሰዓት መንገድ ከብዶባችሁ ሽቅበት
ቁልቁለቱ ለሚያባዝናችሁ እህት ወንድሞቸ
ኢድ ሙባረክ ሁሉም ነገር ያልፋል አብሺሩ
አይዟችሁ ሀሳባችሁ ይስመር እድል ይዉጣ
ላችሁ ቀጣዩን ዓመት በዓል በፍቅር በደስታ
ለሀገር ያብቃችሁ ፡፡
عيدكم مبارك علينا وعليكم تقبيل الله ومنا ومنكم صالح الأعمال جميع مسلم يامسلمت
እህታችሁ ኡሙ ሓቲም ስደተኛዋ
ኢላሒ...! ጭንቀቴ ለአንተ ቀላል ነው!
"የኔ አላህዬ... ለእኔ እንደ ተራራ የከበደኝና እንቅልፍ የነሳኝ ትልቁ ጭንቀቴ... በአንተ ዘንድ እጅግ በጣም ቀላልና በአንድ
ቃል 'ሁን' (ኩን) ሲባል የሚፈታ ነው። በልቤ የታመቀውን ምኞቴን ሁሉ አንተ ታውቀዋለህና፤ ካሰብኩት በላይ አድርገህ
ስጠኝ።
ወዳጆቼ...! አንዳንዴ ሕይወት ትከብደናለች። በትከሻችን ላይ ዓለምን የተሸከምን ያህል ይሰማናል። በሐሳብ ማዕበል እንዋጣለን፣ ሌሊቱ ይረዝምብናል፣ እንቅልፍ ከዓይናችን ይሸሻል። ያ የያዝነው ጭንቀት መውጫ የሌለው ተራራ ሆኖ ይታየናል። ነገር ግን...
አንድ ትልቅ እውነት እናስታውስ!
ያ ለእኛ እንደ ተራራ የከበደን ጉዳይ፣ ሰማያትና ምድርን ያለ አንዳች ድካም ለፈጠረው ጌታ እጅግ በጣም "ቀላል" ነው። እኛ በሰበቦችና በምክንያቶች ዓለም ውስጥ ስንባክን፣ እርሱ ግን በምክንያቶች ላይ የበላይ ነው።
አላህ (ሱበሀነሁ ወተዓላ) በቁርአኑ እንዲህ ይላል፦ "ነገሩን (ሊሆን) በሻ ጊዜ ትእዛዙ ለእርሱ 'ሁን' ማለት ብቻ ነው፤ ወዲያውም
ይሆናል።" (ያሲን 82)
አዎን! ያ አንተን ያስለቀሰህ፣ ያ አንቺን ተስፋ ያስቆረጠሽ ጉዳይ በአላህ ዘንድ በአንድ ቃል የሚፈታ "ቀላል" ነገር ነው።
ጌታችን ሰጪነቱ እንደ እኛ ስስት የለበትም። እኛ "ይህ ቢሆንልኝ" ብለን በጠበበ አእምሯችን ስንመኝ፣ እርሱ ግን
ካሰብነውና ከገመትነው በላይ አትረፍርፎ የመስጠት ችሎታና ቸርነት አለው።
በልብህ የታመቀውን ሚስጥር ያውቀዋል!
ለሰው መናገር የከበደህን፣ በቃላት መግለጽ ያቃተህን የልብህን ትርታና ምኞት እርሱ ያውቀዋል። ገና ሳይወጣ የታፈነውን እንባህን ያያል። ስለዚህ ለሰዎች ከማማረር ይልቅ፣ ጉዳዩን ወደ ባለቤቱ አቅርብ።
"ያ አላህ! አቅሜ ደክሟል፣ አንተ ግን ጠንካራ ነህ። እኔ መውጫውን አላውቅም፣ አንተ ግን መላሽ ነህ። ጭንቀቴን በአንተ ራህመት አቅልልልኝ፤ የልቤን መሻት ካሰብኩት በላይ አሳካልኝ" ብለህ ተማጸነው።
ያኔ ተራራው ሜዳ ሲሆን፣ እንቅልፍ የነሳህ ጭንቀት የሰላም እንቅልፍ ሲሆን ታየዋለህ።
አላህ ሆይ! የሁላችንንም የልብ መሻት በቸርነትህ ካሰብነው በላይ አድርገህ ስጠን!
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
ፈጥኖ ማን ይመልስ ! ✈️✈️
ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው ብዙ ጠቃሚ የሱና ቻናሎችን add የሚለውን በመጫን ያገኛል ።
1ኛ ጥያቄ፦ የዒድ ሶላት እንደ ጁሙዓ ሶላት ሁሉ መጀመሪያ ኹጥባ (ምክር) ይደረግና ከዚያ በኋላ ነው 2 ረከዓ ሶላት የሚሰገደው።
اللهم إني استودعتك حياتي كلها خيرها وشرها، يارب اجعل أيامي القادمة رضا وسعادة وتوفيق منك، يا رب أخرجني من حولي إلى حولك، ومن عزمي إلى عزمك، ومن ضعفي إلى قوّتك، يارب اجعلني اسعد خلقك، وتولني فيمن توليت، ربي اشرح لي صدري ويسر لي أمري واحلل عقدة من لساني يفقهوا قولي
أوصيكم ونفسي بهذه الدعوات كل يـوم 💌
♡ اللهــم آتنا في الدنـــــيــا حـــسنـة وفي
الآخــــرة حــــسنـة وقـــنا عــذاب النــــار
♡ اللهــم اغفــــــر لي ذنبــــــي كله دِقّـهُ
وجِلّهُ وأولـــه وآخـــــره وعلانيتــــه وسـره
♡ اللهــــــم إنـــي أســــألك الهـــــــدى
و التـــــــقى و العفـــــــاف و الغنـــــــى
♡ اللهم إني أعوذ بك من جَهْد البلاء ودَرَك
الـشقاء وســوء القضـاء وشماتــة الأعــداء
Repost from Abdur-Razzaq|Al-Habeshi
🎯በዒድ ቀን መታረም ያለባቸው ተግባሮች❗️
1. የሜካፕ ማዕበል እና የ"Face ID" ፈተና (ተበሩጅ)
በዒድ ጠዋት አንዳንድ እህቶቻችን ፊታቸው ላይ የሚቀቡት የሜካፕ ብዛት የራሳቸው ስልክ እንኳን በ"Face ID" ሊያውቃቸው እስኪቸገር ድረስ ነው። ከንፈር ደም መስሎ፣ ቅንድብ እንደ ቀስተ ደመና ተስሎ ወደ መስገጃው ሜዳ ሲወጣ፣ የዒድ ሶላት ቦታ የሜክአፕ ውድድር ይመስላል።
ማስረጃው ምን ይላል? እስልምና ሴት ልጅ ለባሏ እና እቤቷ ውስጥ እንድታምር ያበረታታል፤ ነገር ግን ውበቷን አደባባይ ላይ ለባዳ ወንዶች ማሳየት (ተበሩጅ) በጥብቅ ይከለክላል። አላህ በሱረቱል አህዛብ (33:33) ላይ እንዲህ ይላል፡- "በቤቶቻችሁም ውስጥ እርጉ፤ እንደ ፊተኛው (የአለማወቅ) ዘመን ጌጣችሁንም አትግለጡ..."
2. "ሲኪኒ" አባያ እና የሒጃብ ትርጉም "ሒጃብ ለብሻለሁ" ለማለት ብቻ ፀጉርን ሸፍኖ፣ ነገር ግን ቀሪውን የሰውነት አካል "እኔን እዩኝ" በሚል ጠባብ ልብስ ማጣበቅ የተለመደ ሆኗል። አባያው ከጠባቡ የተነሳ ለመራመድም ሆነ ሱጁድ ለማድረግ ጂምናስቲክ መስራት ይጠይቃል። ሌላው ደግሞ ቀሚሱ ረጅም ሆኖ ከስር በኩል ግን እስከ ጉልበት ተቀዶ የውስጥ ሱሪን የሚያሳይ የ"ዘመናዊ" አባያ ስታይል ነው። ማስረጃው ምን ይላል? ትክክለኛ ሂጃብ ማለት ፀጉርን መሸፈን ብቻ ሳይሆን፡ ሰፊ የሆነ (አካልን የማይገልፅ)፣ የማያሳጭ፣ ጌጠኛ ያልሆነና የካፊሮችን ልብስ የማይመስል መሆን አለበት። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ስለ መጨረሻው ዘመን ሲናገሩ፡- "ለብሰው ያለበሱ (ልብሱ ጠባብ ወይም አሳጭ ከመሆኑ የተነሳ ገላቸውን የሚያሳይ)፣ የሚያማልሉና የተዘነበሉ ሴቶች... ጀነት አይገቡም፣ ጠረኗንም አያገኙም" ብለዋል (ሙስሊም ዘግበውታል)። 3. የሽቶ "GPS" እና የተንቀሳቃሽ እጣን ሱቅ አንዳንድ እህታችን ተቀብታው የምትወጣው ሽቶ፣ መንገዱን በሙሉ አውዳው፣ እሷ አልፋ ከሄደች ከግማሽ ሰዓት በኋላ እንኳን "እከሊት በዚህ አልፋለች" ብሎ ለመናገር ያስችላል። መዓዛው አፍንጫን ሰንጥቆ የሰዎችን ትኩረት በግድ ይስባል። ማስረጃው ምን ይላል? ከላይ እንደተጠቀሰው ይህ ድርጊት በሸሪዓው እጅግ ከባድ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶበታል። "ማንኛዋም ሴት ሽቶ ተቀብታ (መዓዛዋን እንዲያሸቱት አስባ) በወንዶች ስብስብ አጠገብ ካለፈች እርሷ አመንዝራ (ዝሙተኛ) ናት።" (አቡ ዳውድ፣ ቲርሚዚ)
4. እንደ ጤፍ መቀላቀል (ኢኽቲላጥ) እና የፎቶ ግርግር ሶላት እንዳለቀ ዒድ ዒድ የሚሸተው ፆታን ሳይለዩ እንደ ሰርዲን ታሽጎ ፎቶ በመነሳት ይመስል፣ ወንዱና ሴቱ ትከሻ ለትከሻ ይላፋል። "የአጎቴ ልጅ ነው፣ የሰፈሬ ልጅ ነው፣ አብሮ አደጌ ነው" በሚል ሰበብ ከባዳ (አጅነቢ) ወንዶች ጋር መተቃቀፍና መተራመስ የዘመኑ የዒድ "ፋሽን" ሆኗል። ማስረጃው ምን ይላል? አጅነቢ (ሊያገቧቸው የሚፈቀዱ) ወንዶችን መጨበጥም ሆነ መነካካት ክልክል ነው። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡- "ከእናንተ አንዳችሁ (የማትፈቀድለትን) ሴት ከሚነካ፣ ጭንቅላቱ ላይ በብረት መርፌ ቢወጋ ይሻለዋል።" (ጦበራኒ ዘግበውታል)።
5. የቲክቶክ ሱስና የዒድ ተክቢራ ድሮ ዒድ ሲመጣ ተክቢራ በማድረግ አላህን በማላቅ ነበር ጊዜው የሚያልፈው። አሁን ግን ሶላቱ ቦታ ላይ እንኳን ሳይቀር በጀርባ ተክቢራ እየተባለ፣ ከፊት ለፊት ለቲክቶክ እና ለስናፕቻት ዳንስ እና የተንሻፈፈ የከንፈር ፖዝ ይሰጣል። ዒዱ ዒባዳ (አምልኮ) መሆኑ ቀርቶ የላይክ እና የቪው (View) ማግኛ ፕሮጀክት ሆኗል። ማስረጃው ምን ይላል? እስልምና "ሐያእ" (አይነ አፋርነት/ክብርን መጠበቅ) የኢማን (የእምነት) አንዱ አካል መሆኑን ያስተምራል። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) "እያንዳንዱ ሃይማኖት የራሱ የሆነ መለያ አለው፤ የእስልምና መለያ ደግሞ ሐያእ (አይነ-አፋርነት) ነው" ብለዋል (ኢብኑ ማጃህ)። ቪዲዮ እየቀረፁ ራስን ለባዳ ወንዶች ማጋለጥ የዚህን ሐያእ ተቃራኒ ነው። 6. የዓይን "ራዳር" (እይታን አለመሰብሰብ) በዒድ ቀን ሁሉም አምሮና አጊጦ ስለሚወጣ፣ ዓይን አላረፍ ይላል። "ያቺ ምን ለበሰች? የሱ ጫማ ያምራል" እያለ አይን እንደ አውሮፕላን ራዳር 360 ዲግሪ ይዞራል። በዚህ መሃል አይን ባልተፈቀዱ (አጅነቢይ) ሰዎች ላይ አፍጥጦ ይውላል። ማስረጃው ምን ይላል? አላህ በሱረቱ-ኑር ለአማኝ ወንዶችም ሆነ ሴቶች እይታቸውን ዝቅ እንዲያደርጉ (አይናቸውን ከሐራም እንዲሰብሩ) በጥብቅ አዟል (24:30-31)። እይታ የሰይጣን መርዛማ ቀስት ነች። ➖➖➖➖➖➖➖ 7. የሒል ጫማ ፈተና (High Heel) በዒድ ጠዋት፣ በተለይ የዒድ መስገጃው ሜዳ ወይም ጎድጓዳ ቦታ ሲሆን፣ አንዳንድ እህቶቻችን 15 ሳንቲ ሜትር የሚረዝም የሒል ጫማ አድርገው የሚገጥማቸው ፈተና ቀላል አይደለም። ጫማው መሬት ውስጥ ሲሰምጥ፣ ወይም እንደ አዲስ ጥጃ ሚዛን ለመጠበቅ ሲንገዳገዱ ማየት የተለመደ ነው። ከዚህም በላይ ደግሞ አስፋልት ላይ ሲራመዱ ጫማው የሚያወጣው ዜማ፣ የሰፈሩን ወንድ ሁሉ አንገት አስጠምዝዞ እንዲያይ ያደርጋል። ማስረጃው ምን ይላል? አላህ በቁርኣን ውስጥ ሴቶች እግራቸውን መሬት ላይ እያጋጩ ድምፅ በማሰማት ትኩረት እንዳይስቡ አዟል። በሱረቱ-ኑር (24:31) ላይ እንዲህ ይላል፡- "ከጌጣቸውም የሚደብቁት እንዲታወቅባቸው በእግሮቻቸው አይምቱ (አያጋጩ)..." ይህ የሚያሳየው ጌጥን (አምባርን) ለማሰማትም ሆነ ትኩረትን ለመሳብ ተብሎ በሚጮህ ጫማ መራመድ ከሸሪዓው ጋር እንደሚጋጭ ነው። በተጨማሪም ጤናን የሚጎዳና ለውድቀት የሚያጋልጥ (አደጋ ያለው) ጫማ ማድረግ እስልምና ከሚያበረታታው ራስን ከመጠበቅ መርህ ጋር ይላተማል። 8. የድምፅ ማለስለስ እና የሳቅ ማዕበል ዒድ በመጣ ቁጥር ከመንገድ ዳር፣ ከካፌዎች እና ከፓርኮች የሚሰማው የሴቶች ከፍተኛ ሳቅ እና ጫጫታ ሌላው ጉዳይ ነው። አንዳንዷ ደግሞ ሱቅ ውስጥም ሆነ መንገድ ላይ፣ ከማይገባት (አጅነቢ) ወንድ ጋር ስታወራ ድምጿን ቀይራ፣ ከወትሮው በተለየ አለስልሳና አስውባ ትናገራለች። በመንገድ ላይ የሚለቀቀው ከፍተኛ ሳቅስ ቢሆን የአካባቢውን ሰው ሁሉ ትኩረት ይስባል። ማስረጃው ምን ይላል? እስልምና የሴት ልጅ ድምፅ ሙሉ በሙሉ ሐራም ነው አይልም (ለአስፈላጊ ጉዳይ ማውራት ይቻላል)፤ ነገር ግን ድምፅን ከባዳ ወንዶች ጋር ሲያወሩ ማለስለስና ማሳመርን በጥብቅ ይከለክላል። አላህ በሱረቱል አህዛብ (33:32) ላይ ለነቢዩ ሚስቶች (እና በነሱ በኩል ለሙስሊም ሴቶች ሁሉ) እንዲህ ይላል፡- "በንግግርም አታለስልሱ፤ በልቡ ውስጥ በሽታ ያለበት ሰው ይመኛልና። መልካምንም (የተለመደና ቀጥተኛ) ንግግር ተናገሩ..." በየመንገዱ ከፍ ባለ ድምፅ መሳቅና መጮህም ከሙስሊም ሴት ውበት ከሆነው "ሐያእ" (አይነ አፋርነትና ክብር) ጋር አብሮ የሚሄድ አይደለም።
እነዚህን ሁሉ ስንል ዒድን በሀዘን እናሳልፍ፣ አንደሰት ማለታችን አይደለም። እስልምና የደስታ ሃይማኖት ነው! ነገር ግን የደስታችን ልክ እና ድንበር የጌታችንን ህግ በማይጥስ መልኩ መሆን አለበት። መልካም ልብስ (ነገር ግን ሒጃብ የሆነ)፣ ጥሩ ሽቶ (ነገር ግን እቤት ውስጥና ለሴቶች ብቻ የሚረጭ)፣ ፈገግታ እና ደስታ (ነገር ግን ሐያእን የጠበቀ) መሆን ሲችል ነው የዒድ ደስታችን በረካ የሚኖረው። ✨መልካም፣ ሸሪዓውን የጠበቀና በበረካ የተሞላ ዒድ ይሁንልን!
استغفرالله العظيم واتوب اليه عدد خلقه ورضا نفسه وزنه عرشه ومداد كلماته
‧ ₊ ˚ ♡ ليبلغ تكبيركم عنان السماء
كبروا فإن الله عظيم يستحق الثناء ‧ ₊ ˚ ♡
الله أكبر لا إله إلا الله
الله أكبر الله أكبر ولله الحمد
الله أكبر لا إله إلا الله
الله أكبر الله أكبر ولله الحمد
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته
باركل الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكما في خير
አልሀምዱሊላህ ይገባዉ ምስጋና
ለደስታወ ለኒካ እዚህ ደረስንና፡
ዉዱ ኡስታዝአችን እኮን ደስ አላህ፡
ከላጤነት ህይወት አላህ አወጣህ፡
በባከነ ህይወት ደርሰህ ነበር እዚህ ፡
ዉሀ አታጭህን ጌታችን ወፈቀህ፡
የዛሬ ሙሺራ አላህ አድርጎህ በል፡
አልሀምዱሊላህ ምንስ ቃል አለህ፡
ጋብቻ ሱና ነው የሙዕሚን ጎዳና፡
የፍቅር ቃል ኪዳን ማህደር ሰኪና፡
ትዳርህን ያርገው ያማረ ያበበ በነብዩ ፡
ሱና ደምቆ የተዋበ ጋብቻ ጥሩ ነው ፡
ብዙ ጥቅም አለው አዉቆ ለገባበት ፡
አላህ ለወፈቀው ከሀራም መሸሻ አይን፡
አይን መስበሪያ ነው፡በነብዩ ሱና ፡
ይድመቅ ትድርህ የሚስትህን ሀቅ
ጠባቂ ጌታችን ያድርግህ፡ዘላቂ ያድርገዉ
ሞቅ ይበል ጎጆህ ፡
አተውድ ኡስታዜ የዛሬው አበባ፡
የነገ ፍሬ ነህ ሆድህ እንዳይባባ፡
በሱና ካገባህ ይሄንን ከታደልክ፡
የነብዩን መንገድ ሀላሉን ከመረጥክ፡
እኔም መብሩክ አልኩኝ እንኳንም ደስ አለህ፡
ትዳር ሰኪናነው በደንብ ከገባህ ፡
ተግባብተህ በሀሳብ ስትኖር ተቻችለህ፡
ታዳ ከዝህ ሌላ ምንስ ውበት አለህ፡
በሀቅ ላይበርታ አይዞህ ስትልህ፡
ልጆችን በተውሂድ ስታሳድግልህ፡
ከዝህ የበለጠ ምንስ ስጦታ አለህ፡
ቤትህ ፍክት ብሎ መብራቱ ደምቆልህ፡
የሱናዋን ጀግና አላህ ወፍቆህ
ብልህ አስተዋይ ሁን ያዝ ጠበቅ አድርገህ
ዛሬ ጀምራችሁ ከዚሁ ሠአት ፡
በሃላል በኒካ በአሏህ በረከት፡
ሂወታችሁ ይመር በአላህ ራህመት፡
ሙሽራው ሙሽሪት ሰርጋቸው ነው እና
በሉ ባረከሏህ በነብዩ ሱና
አምሮ ይድመቅለት በሃላል ጎዳና
ይስመር ትዳራቸው ፍቅራቸው ይቃና
ውዷ ሙሽራችን እንዲያምርላት ቤቷ
ጎጆውም እንድሞቅ እንድሰምር ሃያቷ
መርቀን እንሸኛት ይህ ነው ፍላጎቷ
ባረከላህ እንበል ይስመር ፍላጎቷ
ልክ እንደታዘዝከው ቀጥ በል በሱና
መዳን የሚገኘው በተውሂድ ነውና
ዘላቂ ያድርገው እስከ ዳሩል ጀና
የነብዩን ሡና ያዉ ተከተላችሁ
በዛሬዋ ምሽት እኛም አጀብናችሁ
ከብቸኛዉ አለም ወጣ ሂወታችሁ
አልሀምዱሊላሂ እንኳን ደሥ አላችሁ
ለድኑ ጠቃሚ መልካም ልጅ ይሥጣችሁ
እኛ ደሥ ብሎናል እንኳን ደሥ አላችሁ
መብሩክ ሙሽራችን እንኳንም ደስ አለሽ
ከሀራም አርቆ ለሃላሉ አበቃሽ
ከቢድዓ ኮተት የሌለው ግርግር
ተመኘሁላችሁ የሰመረ ትዳር
ሷሊሆች ውለዱ ድኑን አስከባሪ፡
የማይሾፍራቸ የሂዝብያ ጋሪ፡
በጢልን በሁጃ በጣጥሰው መንጣሪ፡
በሱና ያጌጡ የተውሂድ ተጣሪ፡
ድምቀት ለምድሪቱ አንበሳ ኮከቦች፡
ሽርክን የሚያወግዙ ተወርዋሪ ጀቶች፡
የሙብተዲዕ ጠላት ተናዴዳፊ ንቦች፡
ኩፋርን አሰደንጋጭ ለድን ተሟጋቾች፡
አሏህ ይችራችሁ ውብ ወንድና ሴቶች፡
ግርማ ሞገስ ለብሰው ጥላት አሸባሪ፡
በየደረሱበት የኢስላም ተጣሪ፡
ወሀቡ ይስጣችሁ የሴት አናብስቶች፡
በኒቃብ ያጌጡ የእውቀት እንስቶች፡
አሏህ ይችራችሁ ሪዝቅን በስፋት:
በደስታ ላይ የኑሩ አይንካችሁ ልፋት:
አልሀምዱሊላሂ ምስጋና ይድረሰው
ሀራምን ከልክሎኒካህ ለፈቀደው
ለአለማቱ ጌታ ከአርሽ በላይ ላለው
ባረከሏህብየ በጣም ልባርክልሽ
እጅግደስ ብሎኛል ኒካህ በማሠርሽ
ትዳርም መሰረትሽ ኢማንሽም ሞላ
ምን ያስደስትሻል ታዳ ከዚህ ሊላ
የኛማ ሙሽራ በጣም ተውባለች
ከጅልባቧ በላይ ኒቃብ ደርባለች
የነብዩን ሡና ሀይ አድርጋዋለች
የድነል ኢስላምን መስፈርት አሟልታለች
እናማ እህቴ አደራ ብየ እምነግርሽ
ሀቁን ጠብቂለት ለውዱ ባልሽ
ከሷሊሆች ሁኝ ለትዳርሽ ብቁ
አላህን በመፍራት ሀቁን ከሚጠብቁ
ለባል ታዛዥ መሆን ኢባዳ ነውና
ፍቅርሽን መገቢው በንፁህ ልቦና
ትልቅ ደረጃ አለው ትዳር በስልምና
ወሚን አያቲሂ ብሏል ረበና
በሚያዝሽም ሰአት መረሀባ ብለሽ
በችጉሩ ሁሉ መፍተሄ ሁነሽ
በደስታውም ግዜ አብረሽ ተደስተሽ
ሙሽራው ልንገርህ አድምጥ በጥሞና
ውዷ ባለቤትህ ስጦታህ ናትና
ተከባክበህ ያዛት ዛሬም ትላትና
የረሡል አደራ አማናህ ናትና
ከምነግርህ በላይ በስፋትብታውቅም
ሀቋን ጥብቅላት በምትችለው አቅም
እሷም ባቅምህ እጅ በብዙ አጠይቅም
ሚስትኮ ላተ ሁለ ነገርህ ናት
የፍቅርህ ምርኮኛ የተለየች ከናት
ተዛዝናችሁ ኑሩ ሁለየም ተዋዳችሁ
በኢማን አጊጡ ሞቅ ይበል ቤታችሁ
መቻቻል ነውና የትዳር ሚስጥሩ
ባድነት ፀታችሁ በፍቅራችሁ አብሩ
የደስታ የአለም ይሁን ጋብቻችሁ
ሁለይም ተዋደዱ አላህ ያዋዳችሁ
ማን አለ እደኔ ኡስታዝን የሚወድ፡
ከጅህልና አዉጥቶ ያሳየን ቅን መንገድ
እኔማ ኡስታዜን በጣም ነዉ የምወደዉ
ትናት የነበረው ሂይወቴን ቀየረዉ ፡
በጭፍን ስንጎዝ ገደል ልንገባ
ብረሀን አሳየን መራን ቅን ጎዳና
አድበተ ጣፋጭ ምክሩ ተናፊቂ
ቢድዓን አባሮ ተዉሂድ አሳዋቂ
ምርጡ ኡስታዝአችን ኑርልን ዘላለም
እደ አንተ አስተማሪ ለኛ ማንም የለም
እኔ እዚህ ላይ ላቁም አላብዛ ዛዛታ
ተዘርዝሮ አያልቅም የኡስታዝ ዉለታ
ኡስታዜ
የሱናው ተዋናይ የተውሂዱ ጀግና
ፍርሃት የማያዉቅ ለአቂዳ ቆንቋና
ከቁርአን ከሀዲስ መረጃ ሰፋሪ
የጠላትን ሴራ አድቅቆ ሰባሪ
የተውሂዱ ጀግና የሱናው አንበሳ
ያለውን የሚሰጥ ለምንም ሳይሳሳ
ዉድ ነው ጀግናዬ የሽርክ መርዘኛ
የሱናው ነበልባል የተውሂድ ዘበኛ
መና የሚያስቀረው የባጢልን ነዶ
መረጃዉን ፈርቶ ወደ ኋላ ቯዶ
የጠላትን ሴራ ያስቀራል በባዶ
بَارَكَ اللهُ لَكُمَا، وَبَارَكَ عَلَيْكُمَا، وَجَمَعَ بَيْنَكُمَا فِي خَيْرٍ. اللَّهُمَّ اجْعَلْ بَيْنَهُمَا مَوَدَّةً وَرَحْمَةً، وَارْزُقْهُمَا ذُرِّيَّةً صَالِحَةً، وَبَارِكْ لَهُمَا فِي رِزْقِهِمَا، وَاجْعَلْ حَيَاتَهُمَا سَعَادَةً وَطَاعَةً."
"أدعو الله أن يجعل حياتكما مليئة بالحب والسعادة والخير."
መብሩክ ኡስታዙና
ከተማሪህ ኡሙ ሓቲም መኪያ
https://t.me/Multeka_Selefiyin
