cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Ethio-Universities Salafi Community(EUSaCo)

የዚህ Community ዓላማ በመላው ሀገሪቱ የሚገኝ ሰለፊይ የዩንቨርስቲ፣ኮሌጅ እና ሌሎች የትምህርት ተቋማት ኮሚኒቲን በአንድ አስተሳስሮ ትክክለኛውን እስላማዊ አስተምህሮ ለዑማው ማድረስ ነው። ኑ ሀቅን ከባለቤቶቹ እንማር! ገንቢ አስተያየትና ጥቆማዎትን @EUSaCofeedbackBot ያድርሱን። #ኢዩሰኮ #EUSaCo

Більше
Рекламні дописи
1 331
Підписники
-124 години
-97 днів
-630 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

🔷   የዘንድሮ ዓሹራእ   የዘንድሮ የዓሹራእ ፆም ነገ ማክሰኞ ሀምሌ 9/2016 ነው ። በመሆኑም በዚህ ፆም የሚገኘውን ምንዳ ለወንድምና እህቶች እንዲሁም አባትና እናቶች በማስታወስ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን ። https://t.me/bahruteka
Показати все...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👉 የቻናል እና የግሩፕ በልተቤቶች ሼር በማድረግ ተባበራቸው. የእህታችን ጉዳይ እጅግ አሳሰቢ ነው ከእናቷጋ ለሁለቱ ብቻ ነው የሚኖሩት እህታችን ለብዙ አመታት በከባድ ህመም እያተሰቀዬች ትገኛለች መሬት ንብረት ሚባል ነገር ዬለቸውም እህታችን የቋረጠችውን ቂርዓቷን እንድትቀጥል የበኩላችንን እናድርግ ✍️አቡ ያሲር ኢብን ሙዘይን ለእህታችን ገቢ ማሰበሰቢያ ተብሎ የተከፈተው ግሩፕ ይህ ነው👇👇 https://t.me/ye_selefiyoch_eht
Показати все...
እህታችንን ካለችበት ህመም እንታደጋት

ሰለፊይ እህትህ ስትሰቃይ አይተህ/ሽ ጨክነህ/ሽ አትለፍ/ፊ

👍 1
ካሚል ሸምሱ፣ ኢልያስ አህመድ እና ሳዳት ከማል ============> ↪️ ❝ ተመዩዕ ዳር የሌለው ባህር ነው ! ❞ ↩️ ❞ التمييع بحر لا ساحل له! ❝ ♻️ የተመይዕ ቢድዓ ልክ ዳር እንደሌለው ባህር ነው ከገባህበት በኋላ ለመውጣት ብትሞክር አትችልም ምክንያቱም ባህሩ ዳርቻ የለውምና። ወደ ተመዩዕ Ideology የተነከሩ ሰዎች በቆዩ ቁጥር ባህሩን ያንቦጫርቃሉንጂ አይሻሻሉም። ➲ ከታች በቅደም ተከተል የምንጠቅሳቸው ሰዎች በተለዬ እርከን የሚገኙና የተለያዩ ስህተቶችን የሚፈፅሙ ናቸው። እንመልከት፦ ❶ኛ 🎙 ካሚል ሸምሱ፦ ➲ ❝ሱፊይ ሰለፍይ የሚለው በእስልምና አስተምህሮት ጥንት ያልነበረ አሁን የመጣ ቢሆንም ሱፍይ ነን ከሚለው ቡድንም በፊደራልም በአድስ አበባም በተለያዩ ክልል መጅሊሶችም የተካተቱበት የተወከሉበትም ተጨባጭ ነው ያለው።❞ ➘➴➘ ማዳመጥ ይችላሉ https://t.me/AbuImranAselefy/7523 ✅ መልስ፦ እጅግ በጣም ሰቅጣጭ ሀሳብ ነው። እንደት ሰው «...ሰለፍይ የሚለው በእስልምና አስተምህሮት ጥንት ያልነበረ አሁን የመጣ ቢሆንም...» ብሎ በድፍረት ይናገራል!? በእርግጥ ኢኽዋንዮች ምንም ለማለት የማይጨንቃቸው በተለያዩ አጋጣሚዎች የሻቸውን የሚናገሩ ሸይኽ እንዳሻዎች መሆናቸውን በደንብ እናውቃለን። ቢሆንም ግን እንዲህ አይነት ግልፅ ጥፋት እንግዳ ሊሆን ይችላል። ካሚል ሸምሱ ሰለፍይ ስለሚለው ፅንፀ-ሀሳብ ምንም አይነት ግንዛቤ እንደሌለው መገንዘብ ይቻላል። ለመሆኑ ሰለፍይ ማለት የሰለፎች (የደጋግ ቀደምቶች) ተከታይ አይደለምን!? ሰሃቦችን እና እነሱን በመልካም የተከተሉትን መከተል አይደለምን!? ነውንጂ ወሏህ وَالسَّابِقُونَ الْأَوَّلُونَ مِنَ الْمُهَاجِرِينَ وَالْأَنصَارِ وَالَّذِينَ اتَّبَعُوهُم بِإِحْسَانٍ رَّضِيَ اللَّهُ عَنْهُمْ وَرَضُوا عَنْهُ وَأَعَدَّ لَهُمْ جَنَّاتٍ تَجْرِي تَحْتَهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا أَبَدًا ۚ ذَٰلِكَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከእነሱ ወዷል ከእርሱም ወደዋል፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በውስጣቸው ዘለዓለም ነዋሪዎች ሲኾኑ ለእነርሱ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ ይህ ታላቅ ዕድል ነው፡፡   [ሱረቱ አል-ተውባህ - 100] ♻️ ሰለፍያን መጤ ማለት ከባድ አደጋ እንደሆነ ብንገነዘብ ኖሮ ምን ያክል በጨነቀን ነበር። ለማንኛውም ይህ ለሱና ሰዎች ግልፅ ስለሆነ መደጋገም አልፈልግም። ካሚል ቀጥሎ እንዲህ ይላል፦ ➲ ❝አሁን ያለው መጅሊስ መውሊድን ኮሚቴ አዋቅሮለት በጀት በጅቶለት መውሊድ እንዲከበር እያደረገ ያለ መጅሊስ ነው።❞ ✅ መልስ፦ አዎ እንዲህ ሰዎች ማንነቱን እንዲገነዘቡ በዚህ መልኩ መናገሩ ጥሩ ነው። ለመውሊድ ይሄን ያክል ቦታ ከሰጡ የታለ ቢድዓን መቃወም እ? መጅሊሱን አስተካክለናል የሚሉት ሰወችስ ምን እየሰሩ ነው!? ❷ኛ 🎙 ኢልያስ አህመድ፦ ➲ ❝ይህ (መጅሊስ) የተለያዩ አመለካከት ያሏቸው ከተለያዩ background የመጡ ስብስቦች በአንድ ... የሚመሰርቱት ህብረት ነው❞ ✅ ማዝገንዘቢያ፦ ኢልያስ እንዳለው መጅሊስ የተለያዩ ሰዎች ስብስብ ነው። በህብረቱ ድብን ያሉ ከባባድ ልዩነቶች ያሏቸው አካላት የተጠራቀሙበት ነው። በዚህ መጅሊስ የተለያዩ የቢድዓ ባለቤቶች ተከማችተዋል። ከንግግሩ እንደምንገነዘበው እነዚህ የቢድዓ ሰዎች በጋራ እየሰሩ ነው። ታዲያ የሱና ሰው ነኝ የሚል አካል እንደት ከነዚህ አጥፊዎች ጋር በጋር ለአመታት ይቀጥላል!? የባሰው ደግሞ ከነዚህ የጥፋት አካላት ጋር በመሆን የሀቅ ሰዎችን መዋጋት ነው። 🎞 ቀጥሎም የሚከለክለውን መልዕክት ያዘለ ንግግር ያስተላልፋል፦ ➲ ❝ሌሎችን የምንገፋ ከሆነ ለሌሎች እውቅና የማንሰጥ ከሆነ....❞ ✅ ጉድኮ ነው! አሉ በኢልያስ ሙግት ከሆነ ሌሎች መገፋት የለባቸውም እውቅና መሰጠት አለበት ማለት ነው። አይይይ ሰው አውቆ ያላወቁትን ያህል ሲያጠፋ ይሰቀጥጣል። እርግጥ ነው ሰዎች ከንግግሩ የሚረዱት በዚህ መልኩ የተናገረው ለሆነ አላማ ሲባል ነው በማለት ነው። አላማውም መጅሊስ ገብቶ አንዳንድ ጥቅሞችን ማስገኘት ነው በማለት ይሞግታሉ! ⁉️ የኛ ጥያቄ የታለ ጥቅሙ? ⁉️ ለመውሊድ ከተበጀተ ሰለፍያ ልክ እንደሱፍያ መጤ ከተደረገ የታለ ጥቅሙ!? ⁉️ የሚገኘው ጥቅም በግልፅ የሚታየው መች ነው!? ⁉️ የአሁኑ መጅሊስ ከድሮው በምን ይለያል!? እንደውም እነ ኡመር ገነቴ ሰለፍይ ነኝ ያላለ ይከፍራል አሉንጅ ሰለፍያህ መጤ ነው አላሉም። ትክክለኛውን ሱና የፈለገ ይፁምንጅ እየበላ እየጠጣ መውሊድ ማክበር የለበትም ነው ያሉት! የነኢልያስ ካሚሎች ግን ለመውሊድ አብይ ኮሚቴና ከመጅሊሱ በጀት አውጥተው ይደግሱና በድፍረት ተግባራቸውን ይነግሩናል። የታለ የድሮውና የአሁኑ መጅሊስ ልዩነት!??? ❸ኛ 🎙 ሳዳት ከማል፦ ➲ ❝የመጅሊሱ ሰዎች ከእኛ በእድሜ የጠገቡ ናቸው❞ ✅ መልስ፦ ሳዳት ከማል ከተመዩዕ በሽታ በፊት የመጅሊስ ሰዎችን ጥፋቶች እየለቃቀመ ማስተካከያ ያደርግ ነበር። ያኔ ጥፋታቸውንጅ እድሚያቸው አልታየውም ነበር። በጥፋታቸው ሙስሊሙን የሚጎዱ እንጂ ጥቅማቸው አልተገለፀለትም ነበር። ምክንያቱም ያኔ በሹብሃ ሳይበከል በንፁህ አስተሳሰብ ላይ ነበር። ሰው ካጠፋ ትልቅ ነው ጠቃሚ ነው ወዘተ እየተባለ ጥፋቱ አይሸፍንም። መነገር ባለበት ልክ መነገር አለበት። ግን ሳዳት ዳርቻ ወደሌለው የተመዩዕ ባህር ከሰመጠ በኋላ ሀሳቡን ቀየረ። እንዲህም ይላል፦ ➲ ❝እንዳንተ ልጅ አይደሉም ጅል አይደሉም፤ ልጅና ጅል ቶሎ አይበስልም❞ ✅ መልስ፦ በዚህ ንግግሩ ምክንያት አንድ ድምፅ ትዝ አለኝ። ዶክተር ጀይላን በአንድ ወቅት ስለነሳዳትና መሰሎቹ እንዲህ ብሎ ነበር «ተዋቸው ልጅ ስለሆኑ ነው ይመለሳሉ ታገሱ» በማለት እስኪበስሉ ጠብቁ ብሎ ነበር እናም ዛሬ ሳዳት በስለናል እያለ መሆኑ ነው። አይ ጨዋታ ጉድ! ➲ ❝ስትሸብት መብት እያለህ እንደሌለህ ሆነህ መንግስት ቤት ሆነህ ትለምናለህ። ፈሪነት ግን አይደለም።❞ ✅ መልስ፦ ስንትና ስንት ሰዎች ሸብተው ሀይማኖታችንን ለመበረዝ ጥረት ያደርጋሉ። ተፈላጊው ነገር በትክክለኛው መንገድ መሆን እንጂ መሸበት አይደለም። ሳጠቃልል ♻️ እነዚህ ሰዎች ተሳስረው እየተጓዙ ነው። ከመንጫጫታችሁ በፊት ነገሮችን ለአላህ ብላችሁ ለማስተዋል ሞክሩ! እነ ኢልያስም ሆነ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ እነሳዳትም በኢክዋኖች ላይ ደራርበው ተኝተዋል። ይህ የሚካድ አይደለም። በዚህ አመት ብቻ የሀገራችን ኢኽዋኖች ስንቱን ቀባጠሩት ማነው ትንፍሽ ያለው!? የሳዳት ወዳጆች ረድ የምትመስል ነገር ካገኙ ይሄው ረድ አደረገ ይሄው ዝም አላለም በማለት ይንጫጫሉ። ይህ የሚያሳየው ረዱ ብርቅ ሆኖባቸዋል። በቃ እንደበፊቱ አይደለም። ወደድክም/ሽም ጠላህም/ሽም 📝 ➷➘➴ https://t.me/AbuImranAselefy
Показати все...
Abu Imran Muhammed Mekonn

ካሚል ሸምሱ፣ ኢልያስ አህመድ እና ሳዳት ከማል ============> 🎙 ካሚል ሸምሱ፦ ➲ ❝ሱፊ ነን የሚሉት በፊደራልም በአድስ አበባም በተለያዩ ክልል መጅሊሶችም እንዲካተት አድርገናል።❞ ➲ ❝አሁን ያለው መጅሊስ መውሊድን ኮሚቴ አዋቅሮለት በጀት በጅቶለት መውሊድ እንዲከበር እያደረገ ያለ መጅሊስ ነው።❞ 🎙 ኢልያስ አህመድ፦ ➲ ❝ይህ (መጅሊስ) የተለያዩ አመለካከት ያሏቸው ከተለያዩ background የመጡ ስብስቦች በአንድ ... የሚመሰርቱት ህብረት ነው❞ ➲ ❝ሌሎችን የምንገፋ ከሆነ ለሌሎች እውቅና የማንሰጥ ከሆነ....❞ 🎙 ሳዳት ከማል፦ ➲ ❝የመጅሊሱ ሰዎች ከእኛ በእድሜ የጠገቡ ናቸው❞ ➲ ❝እንዳንተ ልጅ አይደሉም ጅል አይደሉም፤ ልጅና ጅል ቶሎ አይበስልም❞ ➲ ❝ስትሸብት መብት እያለህ እንደሌለህ ሆነህ መንግስት ቤት ሆነህ ትለምናለህ።❞ ጊዜ ሳገኝ በማብራሪያ እመለሳለሁ 📝 ➷➘➴ ጠብቁኝ!!!

https://t.me/AbuImranAselefy

👍 4 1💯 1
👉 የኒቃብ ጥላቻ በሽታ ሲሆን የታሪክ መዛግብቶች እንደ ሚያስነብቡት የአላህ መልእክተኛ ከመላካቸው በፊት አዩሁዶችና ነሳራዎች ( ክርስቲያኖች ) ዘንድ ኒቃብ የንፁህነትና የክብር ራስን የመጠበቂያ ምልክት እንደነበር ነው ። በዛን ዘመን አንድ ክብሯን የምትጠብቅና ከፀያፍ ተግባር ለመራቅ የፈለገች ሴት ሙሉ ልብስ ከነኒቃቡ ጋር ትለብስ እንደነብርና የዚህ አይነት ልብስ የምትለብስ ወጣት በማህበረሰቡ የተከበረች እንደነበረች መዛግብቶቹ ያስረዳሉ ። አላህ ነብዩ ሙሐመድን ሲልክ ሴትን ልጅ የክብር ማማ ላይ በማስቀመጥ የመጀመሪያ መለኮታዊ የህይወት መመሪያ በሆነው ሕያው ቃሉ ስለ ሒጃብ በሚቀጥለው ቃሉ አስቀምጧል ። « وَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا ۖ وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ ۖ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا لِبُعُولَتِهِنَّ أَوْ آبَائِهِنَّ أَوْ آبَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أَوْ أَبْنَائِهِنَّ أَوْ أَبْنَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أَوْ إِخْوَانِهِنَّ أَوْ بَنِي إِخْوَانِهِنَّ أَوْ بَنِي أَخَوَاتِهِنَّ أَوْ نِسَائِهِنَّ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُنَّ أَوِ التَّابِعِينَ غَيْرِ أُولِي الْإِرْبَةِ مِنَ الرِّجَالِ أَوِ الطِّفْلِ الَّذِينَ لَمْ يَظْهَرُوا عَلَىٰ عَوْرَاتِ النِّسَاءِ ۖ وَلَا يَضْرِبْنَ بِأَرْجُلِهِنَّ لِيُعْلَمَ مَا يُخْفِينَ مِن زِينَتِهِنَّ ۚ وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ » النور (31) " ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ ፡፡ (የውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንዶች ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለእህቶቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለሴቶቻቸው ወይም እጆቻቸው ለያዙት (ባሪያ) ወይም ከወንዶች ለሴት ጉዳይ የሌላቸው ለኾኑ ተከታዮች ወይም ለነዚያ በሴቶች ሐፍረተ ገላ ላይ ላላወቁ ሕፃኖች ካልኾነ በስተቀር አይግለጹ ፡፡ ከጌጣቸውም የሚሸፍኑት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው አይምቱ ፡፡ ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ ፡፡ በእነዚህ አንቀፆች ሴት ልጅ የውበቷ መገለጫዎች ለማን ግልፅ ማድረግ እንዳለባትና ከማን መሰተር እንዳለባት አስቀምጧል ። በመሆኑም ኒቃብ ኢስላም ሴት ልጅ ክብሯን መጠበቅ ስትፈልግ እንድትለብሰው ሳይሆን ለብሳው ክብሯን መጠበቅ እንዳለባት አዟል ። ኒቃብ በኢስላም ክብንና ንፅህናን የሚጠብቁበት ብቻ ሳይሆን ወደ አላህ የሚቃረቡበት የአምልኮ ክፍል ነው ። ምክንያቱም አምልኮ ( ዒባዳ) ማለት የአላህንና የመልእክተኛውን ትእዛዝ መፈፀም ስለሆ ነው ። በመሆኑም ኒቃብ በሁለቱም ሀገር እጅግ በርካታ ቱሩፋቶች ያሉት መሰተሪያ ሲሆን ከእነዚህ ቱሩፋቶቹ ውስጥ ጥቂት በቅርቢቱ ዓለም ካሉት ውስጥ እንመልከት : – አንደኛና ሁለተኛው – ተለይተው እንዲታወቁና ጎንታይ ባለጌዎች እንዳይጎነትሏቸው እንዳያስቸግሩዋቸውም ይረዳል ። ይህን አስመልክቶ አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ያላል : – « يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ الْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ اللَّهُ غَفُورًا رَّحِيمًا » الأحزاب ( 59 ) " አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም ፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው ፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው ፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው ፡፡" ሶስተኛው – ክብራቸውን ይጠብቁበታል ። አራተኛው – አላህን የመፍራታቸው ምልክት ነው ። አምስተኛው – ልባቸው በተቃራኒ ፆታ ፍላጎት የታመሙ ሰዎች በእነርሱ ምክንያት እንዳይሳሳቱ ያደርጋል ። ስድስተኛ – ዝሙት እንዳይስፋፋ ያደርጋል ። እነዚህ ከብዙ ጥቂት ቱሩፋቶቹ ናቸው ። በመሆኑም ኢስላም ሴትን ልጅ ከወርቅ በላይ ቦታ የሰጣት ስለሆነ አንድ ሴት ጌጥ የሆነው ወርቋን ደብቃ ከምትጠብቀው በላይ ራስዋን ደብቃ ለሚገባው አካል ብቻ እንድታስረክብ ያዛታል ። ይህን ስትፈፅም የክብሩ ማማ ላይ ትወጣለች ። በጣም የሚያሳዝነው ግን አብዛኛው ሙስሊም ማህበረሰብ ኒቃብ የኋላ ቀርነት ምልክት አድርጎ ያየዋል ። ከዚህም በላይ አንዳንዶች ልጃቸው ዝሙት ሰርታ በዝሙት አርግዛ ሲያዩ የማይደነግጡትና የማይበሳጩት አይነት ብስጭት ኒቃብ ለብሳ ሲያዩ ይበሳጫሉ ።‼️ ይህ በርግጥ ትልቅ በሽታ ነው ። ከዚህም በላይ ደግሞ ልጃችሁ ከፍራለች ቢባሉ በብስጭት የማይታመሙትን ያክል ታመው ሆስፒታል ይገባሉ ። ይህ ምናባዊ ሀሳብ ሳይሆን በገሀዱ ዐለም ያለ እውነታ ነው ። በቅርቡ ሶስት ኒቃብ የለበሱ እህቶቻችን ቤተሰቦች ላይ ከታየው አሳፋሪ ተግባር ውስጥ የአንደኛዋ እህት እናትና አባት በብስጭት ታመው አባትየው ሆስፒታል ይገኛሉ ። ‼️ በእነዚህ እህቶች ላይ ከተማም ገጠርም ያለ ዘመድ አዝማድ በሙሉ ኒቃቡን ለማስወለቅ የሚችለውን ያደረገ ሲሆን የሁለቱ እስካሁን አልተሳካም ። በተለይ ቤተሰቦቿ በዚህ ምክንያት የታመሙት ፀንታ ነው ያለችው ። ከሁለቱ እህቶቿ አንደኛዋ በጣም አሳፋሪና አሳዛኝ በሆነ መልኩ መብትሽ ነው እኔ ጋር ነይ ብሎ ከዘመዶቿ አንዱ ወደ ማታውቀው ከተማ እንድሄድ ካደረገ በኋላ መንገድ ላይ ጠብቆ ከመኪና ስትወርድ የምታወልቂ ከሆነ ልውሰድሽ ካልሆነ አዚሁ ጥዬሽ ነው ምሄደው ብሎ የቀን ጨለማ ውስጥ እንድትገባ አድርጎ አስሆልቋቷል ። ‼️ አላህ ይድረስልን እንጂ ኒቃብ ለበሽታ ሰበብ የሚሆንባቸው ሙስሊሞች ያሉበት ዘመን ላይ ነው ያለነው ። ለእህቶቻችን ፅናቱን ለቤተሰቦቻቸው አላህ ሂዳያ እንዲሰጣቸው ዱዓእ እናድርግ እላለሁ ። t.me/bahruteka
Показати все...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
عيد مبارك تقبل الله منا ومنكم ውድ የሱና እህት ወንድሞቻችን እንኳን ለዒድ አል-አድሃ በዓል አላህ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ‼️ በዓሉ አላህን በብዙ ምናወሳበት፣ ምንደሰትበትና በተለያዩ ምክንያቶች ለግዜው ሀዘን ላይ ያሉ ሙስሊም ወገኖቻችንን የምናስደስትበት ይሆን ዘንድ የዘወትር ዱዓችን ነው🤲 اللهم سلم أهلنا في #غزة ،اللهم لا تفجعنا فيهم وانصرهم على من عاداهم.🤲 አላህ በምድር ጫፍ ያሉ የሱና ተከታዮችን በሙሉ ይጠብቅ🤲🤲 الله أكبر الله أكبر الله أكبر #EUSaCo    #ኢዩሰኮ     #𝓔𝓲𝓭 𝓶𝓾𝓫𝓪𝓻𝓮𝓴 t.me/EUSaCochannel
Показати все...
👍 4🔥 1
Repost from N/a
አዲስ🕌🕌የምስራች 🕌 ➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️➡️ 🎤ታላቅ የደዕዋ ፕሮግራም🎤🎤 ✅ በወልቂጤ ሁንቨርሲቲ ሰለፍዮች የመስጂድ ቦታ ግዢ ገቢ ማሰባሰቢያ ግሩፕ ላይ በቀጥታ ስርጭት (online) ➡️ በአይነቱ ለየት ያለ የዳዕዋ እና የንያ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል ። 🪑 የእለቱ ተጋባዠ እንግዳችን ከሀገራችን ብርቅዬ መሻይኾች የሆኑት ታላቅ ሸይኽ ናቸው ስማቸው ሰርፕራይዝ ነው ፦     ➴➷➘ ርዕስ ፦ በሰአቱ ይገለፃል                🗓 ፕሮግራሙ ዛሬ ቅዳሜ በ 08/10/16 e c ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ በላይቭ (ቀጥታ ስርጭት) ይካሄዳል። ♻️ ፕሮግራሙን ለመከታተል ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉ ። ⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️ https://t.me/welkiteunver https://t.me/welkiteunver 🌐 ሼር እና አድ በማድረግ ሀላፊነታችንን እንወጣ !!
Показати все...
የወልቂጤ ዩንቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድ ማስገንቢያ የመሬት ግዢ ገቢ ማሰባሰቢያ ግሩፕ

✍ አሰላሙ አለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበራካቱሁ በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው ምስጋና በአጠቃላይ ለአላህ የተገባ ነው መልካም ፍፃሜ አላህን ለሚፈሩ ባሮቹ ነው ጠላትነትም የለም ለበዳዮች ቢሆን እንጂ!! የአላህ ውዳሴውና ሰላምታው የነብያትና የመልክተኞች ሁሉ መደምደሚያ በሆኑት ነብያችን ላይ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረቦቻቸው እንዲሁም የእነርሱን ፋና በመልካ በተከተሉት ላይ ይውረድ!

4👍 2
★彡 ጀነትና ፀጋዎቿ 彡★ ቆየት ካሉት የሸይኽ አብዱልሀሚድ ምክሮች በውስጡ ከተዳሰሱት ጭብጠ ሀሳቦች ✔️ የጀነትና የጀሀነም ጠቅላላ ትርጓሜ ✔️ የጀነት አይነቶችና የጀሀነም አይነቶ ✔️ የጀነት ፀጋዎችና የጀሀነም አስፈሪ ገፅታዎች ✔️ የተለያዩ አንጃዎች በጀነትና ጀሀነም ላይ ያላቸው አቋም ቅምሻ 💥 ጀሀነም ጥልቀቷ ከጀሀነም ጫፍ ላይ ሆኖ ድንጋይ ቢወረወር ለመመምዘግዘግ 70,000 አመት ይፈጅበታል በዚህም የጀሀነምን አስፈሪነት እንገነዘባለን 💥ጀነት የገቡ ሰዎች -አያረጁም -አይሞቱም -አይታመሙም - ሀሳብ ጭንቀት ትካዜ የለም - ሽንት ሰገራ ንፍጥ አክታ የለም -ራበኝ ጠማኝ ሆዴን ነፍኝ ቆረጠኝ ፈለጠኝ የለም -ደም ግፊት ኤች አይቪ ተቅማጥ ባክቴሪያ ኮሮና የሚባል ነገር የለም -እንደ ዱንያ ደበርሽኝ ደበርከኝ አረጀህ አረጀሽ ፈታሀኝ ፈታሁሽ የለም በፀጋዎች የተንበሸበሸችው ተናፋቂዋ ሀገር ጀነት 💥 የጀነት ሴቶች-ሁሌም ድንግል ናቸው እንደ ሰጎን እንቁላል የፀዱ-አይናቸውን በባላቸው የሰበሩ ሁሌም ባሌ ባሌ የሚሉ-አይናቸው ሰፋፊ የአይናቸው ነጫጩና ጥቁሩ ክፍል የደመቀ 💥 ጀነት ውስጥ ባል ፊቱን በሚስቱ ጉበት ያያል ሚስቱም በባሏ ጉበት ታያለች 💥 የጀነት ሴት አንድ ጊዜ ወደ ዱንያ እትፍ ብትል ዱንያን ከአጥናፍ እስከ አጥናፍ በመልካም መአዛ ታውደዋለች 👌 ሌሎችም በርካታ ርእሶች ተዳሰውበታል በጀነት አጓጊ ገፅታዎች እየተመሰጣችሁ በጀሀነም አስፈሪ ገፅታዎች እየተገሰፅን ከሸይኹ ፈገግ የሚያሰኝና ጥርስ የማያስከድን ማራኪ አቀራረብ ጋር ሊደመጥ የሚገባ ምርጥ ምክር ⁼⁼⁼⁼ ➘➘➘➘ https://t.me/Abdulham
Показати все...
voice.mp314.86 MB
👍 2 1
🎤  ለአረፋ ተጓዘዦች    የተከበራችሁ በየአመቱ ለዒደል አድሓ ቤተሰብ ዚያራ የምትጓዙ ሙስሊም ወንድምና እህቶች በመጀመሪያ ጉዟችን ከሓራም የራቀ ሊሆን ይገባል ። አጅ ነብይ ወንድና ሴት ተቀላቅሎ ከመሄድ ፣ ከሙዚቃ ፣ ከጫት ፣ ከሲጋራ ፣ ካላስፈላጊ ቀልድና ንግግሮች የተጠበቀ ከተቻለ ሐዲስ እየሰማን ወይም እርስ በርሳችን እየተዋወስን አላህ አድረሶን ለቤተሰብ ዝያራ ስላበቃን እያመሰገንን መሆን አለበት ።     ሌላው ዲናችን ወላጅን ማስደሰት በጣም ትልቅ ቦታ ሰጥቶ መለኮታዊ በሆነው የአላህ ቃል ከሱ ሐቅ ቀጥሎ አውስቶታል ። በመሆኑም ወላጅን ለማስደሰት የሚሰሩ ነገሮች መጀመሪያ አላህ የፈቀዳቸውና የሚወዳቸው ሊሆኑ ይገባል ። አላህ እርም ( ሐራም ) ባደረገው ነገር ወላጅን ማስደሰት በራሱ ሐራም ስለሆነ ።      ወላጆቻችን ዱንያ ላይ እንዳይቸገሩ ፣ እንዳይራቡ ፣ እንዳይጠሙ ፣ እንዳይታረዙ ልብስና የተለያዩ ቁሳቁሶችን ይዘን እነደምንሄደው ሁሉ አኼራ ላይ እንዳይቸገሩ ፣ እንዳይበዝኑ ፣ ከከሳሪዎች እንዳይሆኑ አኼራን የሚያጠፉ ነገሮችን በማሳወቅ እንደ ሽርክና ወደ ሽርክ የሚያዳርሱ ተግባሮችን በመንገር እንዲርቁና እንዲጠነቀቁ ፣ ከተለያዩ ወንጀሎች እንዲርቁ ማስታወስ ፣ ሐዲስ እንዲሰሙ መንገር ፣ የሽርክን አደገኝነት በጥሩ አገላለፅ በአስተማሪነት ስሜት ሳይሆን በጣም በተጨነቀ ልጅነት ስሜት ማስረዳት ያስፈልጋል ። በፍፁም የበላይነትና አውቃለሁ የሚል ስሜት ከኛ እንዳያዩ ማድረግ ።      ከጎረቤት ጋር ከአካባቢ ጋር ሊኖር የሚገባውን መልካም አኗኗር ማስታወስ ። የተቸገረ ሰው ከረዱ ያን ነገር እንዳያስታውሱት ፣ እንዳይመፃደቁ ፣ የተረዳው ሰው ለእነሱ እንዲተናነስላቸው እንዳይፈልጉ መርዳታቸውን እንዲረሱት መንገር ። ስለ ጎረቤት ሐቅ ፣ ስለ ዘመድ ሐቅ ፣ ስለባልና ሚስት ሐቅ ማስታወስ በጣም አስፈላጊ ነው ። በተቻለ መጠን እነዚህን ለመፈፀም ከጣርንና ከወንጀል ነገሮች ርቀን በዒባዳ ላይ ጠንክረን ለሰዎች በተግባር አሳይተን ዒዱን ካሳለፍን በአላህ ፈቃድ እጥፍ ድርብ ምንዳ ይዘን እንመለሳለን ።          አላህ ከተጠቃሚዎች ያድረገን ። በድጋሚ የተለቀቀ። http://t.me/bahruteka
Показати все...
ባህሩ ተካ - Bahiru Teka

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته قناة رسمية لمحاضرات ودروس الأستاذ بحرو تكا (أبو عبيدة) الدعوة السلفية በአላህ ፈቃድ በዚህ ቻናል የአማርኛ ትምህርቶችን እንዲሁም አጫጭር የአረብኛና የአማርኛ ፁሁፎችን እንለቃለን ከዚህ ቻናል ውጪ ከሌላ ቦታ ተወስደው ለሚለቀቁ ኦዲዮዎች እውቅና አልሰጥም

https://telegram.me/bahruteka

👍 10
Фото недоступнеДивитись в Telegram
➹➹➹اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎             አስደሳች ዜና 🎤🎤ታላቅ የደእዋ እና የWell Go ፕሮግራም🎤       🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰🟰 🌷🌷🌷የተከበራቹህ ወንድም እህቶቻችን እነሆ በአላህ ፍቃድ የፊታችን እሁድ በቀን 2/10/2016 ዓ/ል ከወትሮው ለየት ባለና ባማረ ሁኔታ  ታላቅ የደእዋ እና የምክክር ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃቹኋል ። 🎓 ፕሮግራሙ ተመራቂ ተማሪዎችን ታሳቢ ያደረገና መገኘት የሚችሉ ሁሉ የሚሳተፉበት በአይነቱ ልዩ እና አጓጊ የሆነ ፕሮግራም ስለሆነ እንዳያመልጥዎት  ከወዲሁ በማመቻቸት ከቤተሰብዎ፣ ከጓደኛዎ፣ ከስራ ባልደረባዎ ጋር ለመታደም ፕሮግራሞን በግዜ አጀስት አድርገው ይዘጋጁ !!!   ✅🪑 የእለቱ ውድ ተጋባዥ ዳዒዎች 🥇ኛ  ውዱ ሸኻችን ሸይኽ ዐ/ሐሚድ ብን ያሲን አል`ለተሚይ አላህ ይጠብቃቸው ከሌራ 🥈ኛ. ኡስታዝ  ዐ/ሹኩር ካሚል አለህ ይጠብቀው  ከፎንቆ 🥉እና የተለያዩ ግጥሞች እና ስነ-ፅሁፎች በወንድሞች ይኖሩናል ‼️ 🧭 ሰዓት፡- አለህ ካለ ከጠዋቱ 3፡00 በግዜ ይጀመራል ። 🕌  አድራሻ፦ ዋቸሞ ዩንቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ(ዳሩል ሂጅረተይን) መስጅድ!! ማሳሰቢያ : – ▬▬▬▬▬▬▬ 🌷ለGC ተማሪዎች መጨረሻ ላይ በሚያስቀሩት ኡስታዛችን ወሲያ ይኖረል‼️  👉 አይደለም መቅረት ማርፈድ ያስቆጫል !!! 👉 ጥሪን ማክበር ኢስላማዊ ስነ-ምግባር ነው !!! ✅ በአካል መገኘት ለማትችሉ Livestream ይኖራል በዚህ ሊንክ ግቡ👉👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 👇👇👇 https://t.me/WCUMSJ2015
Показати все...
👌 3👍 1
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ዘወትር ጁመዓና ቅዳሜ በ ኢዩሰኮ-EUSaCo ተዘጋጅቶ ወደ እናንተ እየቀረበ የሚገኘው ደርስ ዛሬ ማታ የማይኖር መሆኑን ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን። እስከ ቀጣይ ፕሮግራምም ያመለጧችሁን ደርሶች በማድመጥና ሙጣለዓ በማድረግ ላይ አደራ እንላለን!! አላህ በነዚህ በተከበሩ የዙል-ሂጃ ቀናት ላይ እርሱን ማምለክን ያግራልን🤲🤲 🏝 ••⇣⇣.  🏖   ••⇣⇣  ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞.   ╰𝐒𝐡𝐚𝐫𝐞 🖥️ በ 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦~𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️ https://t.me/EUSaCochannel https://t.me/EUSaCoGroup #Share    #ሼር   #EUSaCo #ኢዩሰኮ
Показати все...
Ethio-Universities Salafi Community(EUSaCo)

የዚህ Community ዓላማ በመላው ሀገሪቱ የሚገኝ ሰለፊይ የዩንቨርስቲ፣ኮሌጅ እና ሌሎች የትምህርት ተቋማት ኮሚኒቲን በአንድ አስተሳስሮ ትክክለኛውን እስላማዊ አስተምህሮ ለዑማው ማድረስ ነው። ኑ ሀቅን ከባለቤቶቹ እንማር! ገንቢ አስተያየትና ጥቆማዎትን @EUSaCofeedbackBot ያድርሱን። #ኢዩሰኮ #EUSaCo

Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.