ግጥም
Відкрити в Telegram
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
Показати більше4 823
Підписники
+324 години
+557 днів
+23030 день
Архів дописів
4 827
#ግዜ
ጌዜ ዳኛ ሆኖ በሁሉም ይፈርዳል
የሄደው ይመጣል የመጣው ይሄዳል
ያበደው ይድናል ጤነኛውም ያብዳል
ግዜ እንደፔንዱለም በሁሉም ይዞራል
አንድ የሚቀር የለም ሁሉም ይቀየራል
ቀባሪም በተራው ሞቶ ይቀበራል
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 827
#ናፍቀሽኛል_ብዬ
ናፍቀሽኛል ብዬ ለመጮህ አልወጣ
ሰውም ቢያፌዝ እንጅ አንችን ይዞ አይመጣ
ናፍቀሽኛል ብዬ እኔም ግጥም አልፅፍ
ምን ቤቱን ቢመታ ህመም አያሳልፍ
ናፍቀሽኛል ብዬ ከአንቺ ዘንድ አልደርስም
ከፊትሽ የመቆም ድፍረቱም የለኝም
ናፍቀሽኛል ብዬ እምባም አይወርደኝም
ያንችን ሲያስነባ አይቷል ዓይኔም እሽ አይለኝም
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 827
#እንዲህ_ብለሽ_ጻፊ
በፍቅሬ ተይዞ ስሜን እየጠራ
በየጎዳናው ላይ ብቻውን ሲያወራ
ወፍፎ እየሳቀ አጥቶኝ ሲንከራተት
ለእኔ ፍርቅር ታምኖ ሲሸለመው እብደት
እኔ እስቅ ነበረ በድል ኩራት ጥርሴ
ለእርሱ ጥልቅ ፍቅር ማዘን ትታ ነፍሴ
በሞቀው ከተማ በትርምስ ቀለም
ወድቆ በእኔ ውበት ሲስቅበት ዓለም
አብሬ ስቂያለሁ መውደቁ አስደስቶኝ
ስሜን እየጠራ ሁሌም ሲከተለኝ!!!
ግና ግፌ በዝቶ ሞልቶ ፈሰሳና
እጣውን ቀመስኩኝ በእኔ ደረሰና
እኔም በተራዬ በሌላ ሰው ፍቅር
ወፍፌ እዞራለሁ በወሰድኩት ብድር
እርሱ ዛሬ የለም ለእውነት ኖሮ ሞቷል
ህመም ስቃዩን ግን ለራሴ ውርስ ሆኗል
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 827
ተከታይ ትረካ በ Facebook page ተጀምሯል Follow እያደረጋችሁ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61557221074498
4 827
አንገቴ ጎንበስ በል ይለፍ ይኼ ግዜ
ለሁሉም መልስ አለው ለዛሬው ትካዜ
ነገ ሌላ ቀን ነው ዛሬን አይወክልም
ሀዘን መከራውም በዚህ አይቀጥልም
ቅዝምዝሙ ይለፍ ጎንበስ ልበልና
ጨለማው ሲገፈፍ ብርሃን ነውና
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 827
#ናፈቅሽኝ
ከፍቶሻል መሰለኝ እኔን ሀዘን ዋጠኝ
አልቅሰሻል መሰል ዓይኔን ቆጠቆጠኝ
ሆድ ባሰሽ መሰለኝ ሆዴ ተላወሰ
ትዝ አልኩሽ መሰለኝ ትዝታሽ ፈሰሰ
ካልጠፋው አካሌ ልቤጋ ከበደኝ
ዓይን፣ጥርስ አካልሽ ጨዋታሽ ናፈቀኝ
አቦ ናፍቀሽኛል ብዙ አታስለፍልፊኝ
መምጣት ባትችይ እንኳን ባሳብሽ እቀፊኝ
ያንችን ልክ የያዘው....
የልቤ ላይ ጥጉ ብርድ አንዘፍዝፎታል
አለሁልህ በይው ያ ድምፅሽ ናፍቆታል
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 827
#ማዘንስ_ለከዳ!
ወዳጅ ሸርተት ሲል ጊዜ ሲያዳልጠው
ሰው ከመሆን ወርዶ ገንዘብ ሲለውጠው
አትከፋ ከቶ ወቀሳ አታብዛበት
ጉዳቱ ለእርሱ ነው ከጠላ ሰውነት
በገንዘብ መዝኖ ውብን ጓደኝነት
ሲያረክሰው በንዋይ ያንተን ታማኝነት
ማዘን ለከዳ ነው ለተከዳ አይደለም
ለቃል ያልታመነ ሰላም አያገኝም
ወርቅን አበድረህ መዳብ ቢመልሱ
ይብሳል ፀፀቱ አይተኙም እነርሱ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 827
#በላቡ_ጠብታ
የከበረ ካለ በላብ በጥረቱ
በተሰጠው ጸጋ እዲሁም በእውቀቱ
የእግዚአብሔርን ገንዘብ ደፍሮ ያላነሳ
ከድሃ ጉሮሮ ነጥቆ ያላገሳ
በላብ በጉልበቱ ለፍቶ የከበረ
ለእውነተኛ ድካም ለቃሉ ያደረ
እስኪ ሰው ፈልጉ ጀግና ባለጸጋ
በቅጡ የሚሰጥ የእግዚአብሔርን ዋጋ
ከእናቶች መቀነት ነጥቆ የማይበላ
በተሰጠው ወንበር ከቶ ማያዳላ
በህጻናት ጉልበት በአባቶች ሳይነግድ
በእውነተኛ ድካም ሀብቱን የሚያሳድግ
በላብ በጉልበቱ በጥረቱ ደክሞ
ሀገሩን ሳይቀማ ለማደጓ ቆሞ
በላቡ ጠብታ ለክብር የበቃ
ለስራ ለትጋት ገስግሶ የነቃ
እርሱ ነው ሰው ማለት ትልቅ ባለዋጋ
ሲጠሩት ደስ የሚል የእውነት ባለጸጋ
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 827
#ምን_አለበት?
ኮንትራት ለሆነ ለዚች ዓለም ኑሮ
ዘመን ላይሻገር ዕድሜ ተበድሮ
ሁልጊዜ እንደሮጠ በሕይወት ጎዳና
በከንቱ ሲባዝን ብሎ ጎንበስ ቀና
ጭቅጭቅ ቅራኔ ሰንቆ ጥላቻ
መዋደድን ጠልቶ ሲኖር ለየብቻ
ላያስከፍል ዋጋ ቅንነት ደግነት
ሰው በክፋት መንገድ ባይሄድ ምን አለበት?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 827
#ይልቅስ_ልብን_ላክ ❤
ልባችን ሳይማር የፍቅር አቡጊዳ
እንዲሁ እንደ ዘቀጥን ሰው ሳይሰናዳ
አትምጣ ጌታ ሆይ በጎችን ፍለጋ
ትከፍላለህና ዛሬም ሌላ ዋጋ።
ይልቅስ ልብን ላክ ለልብ አልባው ትውልድ
ከመምጣትህ በፊት እርስ በእርስ ይዋደድ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
4 827
የድሀ ፍቅር
ክፍል15
የመጨረሻው ክፍል
አሪፍ ውጤት ስለነበረ ያመጣሁት ከዮኒቨርሲቲያችን ውስጥ እኔና ሌላ ሁለት ልጆች ለትምህርት እድል ወደ ውጪ ለመሄድ ተመረጥን ነገር ግን ሜላት ደስተኛ እንደማትሆን ሳስብ ግራ ገባኝ ከተመረቅሁ በኃላ እኔና ሜላት እንደድሮው አይደለንም በቃ አብዛኛን ጊዜ እኛ ቤት ስለምትውል በቃ ፀባይዋ ተቀያይሯል የት ወጣህ የት ገባህ ማለትም ጀምራለች እኔ በፍፁም ሜላቴን ማስከፋት አልፈልግም ምክንያቱም ሜላት ሁሉ ነገሬ ናት ፍቅር ሀ ብዬ የጀመርኩባት ብቻ ሳትሆን ዛሬ ላይ ለመድረስ ትልቅ አስተዋፆ ያበረከተችም ጨምር ናት በቃ የምትለኝን ከማድረግ ውጪ ምንም ነገር አላገርግም በፍፁም ከፍቷት ማየት አልፈልግም ሜላት አንዳንዴ በነገር ወጋ ታደርገኛለች እዚህ አድርሼህ ትለኛለች ግን እኔ ምንም መናገር አልፈልግም ብትልም እውነቷን ነው በሷ ሀይል ነው እዚህ የደረስኩት ግን አንዳንዴ ይሄንን ሳስብ የትምህርት እድሉን መጠቀም እንዳለብኝ ይሰማኛል ምክንያቱም ነገ አብረን መኖር ስንጀምር ነገሮች ሊበላሹ ይችላሉ የኔ የሆነ ነገር ሳይኖረኝ አብረን መኖር እንደማንችል ይሰማኛል ሜላት አብረን እንድንኖር ትፈልጋለች በተለይ ታላቅ እህቷ በሚያምር ሰርግ ካገባች በኋላ የማግባት ትዳር የመመስረት ፍላጎቷ ጨምሯል እኔ ደግሞ ይሄንን የማድረግ አቅሙ የለኝም ሜላቴ ሁሌም በስልክም ሆነ በአካል ወሬዋ ትዳር አብሮ መኖር ከዛም ባለፈ ስለ ገንዘብ ሆኗል የእሷ ገንዘብ እንደሚያኖረን ትነግረኛለች ግን ይሄ ለእኔ አላስደሰተኝም እስካሁን ያደረገችልኝ ይበቃል ከዚህ በኋላ እኔ የምትፈልገውን ላደርግላት ነው የምፈልገው ስለዚህ የሷ ሀሳብ አልተስማማኝም ሁሌም በህይወቴ የሚፈጠሩትን ነገሮች ውሳኔ ከመወሰኔ በፊት ለእናቴ አሳውቃታለው በቃ እሷ አድርግ ያለችኝን አደርጋለው እሷ አይሆንም ካለች እተወዋለሁ በቃ አሁንም እናቴን ማማከርና ውሳኔዋን ማወቅ እፈልጋለው እሷ ያለችው ይሆናል ማታ ላይ በረንዳ ቁጭ ብለን እያወራን እያለ ለእናቴ የተፈጠረውን ሁሉ ነገርኳት ምንም አላስቀረሁም ውሳኔሽን እፍልጋለው ምን ልወስን ግራ ገባኝ አልኳት እናቴ በጣም ስለምታስብልኝ ትክክለኛውን ውሳኔ ነው
የምትነግረኝ ልጄ እዚህ ደረጃ ለመድረስህ የሜላት አስተዋፆ በጣም ትልቅ ነው እሷን በፍፁም እንዳታስከፋት የትምህርት እድልህንም እንዳታጣ ይሄ ላንተ በጣም ጥሩ እድል ነው ለወደፊት ህይወትህ ይጠቅምሀል እኔ የምልህ ከሜላት ጋ ተነጋግራችሁ ውሳኔ ወስኑ ነው አስፋላጊ ከሆነ ነገ ማታ ጥራትና እንመካከር ይሄ ይሻላል ነው የምልህ አለችኝ እሽ እማ አልኳት እናቴ ያለችኝ ነገር ትንሽ ቀለል እንዲለኝ አደረገኝ በማግስቱ ጠዋት ተነስቼ ሜላቴ ጋ ደውዬ ማታ ላገኛት እንደምፈልግና እቤት እንድትመጣ ነገርኳት እሽ አለችኝ ሜላት ጥሩ ስሜት የላትም ብቻ ግን እሽ ስላለች ደስ ብሎኛል ሜላቴ መጥታ ምን እንደምንባባል እያሰብኩ ዋልኩ መምሸቱ አይቀር ሜላትም መጣች እኔም እናቴም ሜላቴም ቁጭ ብለን መነጋገር ጀመርን እናቴ ለሜላት ሁሉንም ነገር ነገረቻት በቃ በመነጋገር የድሮ ፍቅራችሁን አድሱ እኔ እንደድሮው እንድትሆኑ ነው የምፈልገው አለችኝ ተነጋግረን አንድ ውሳኔ ላይ ደረስን እኔም የትምህርት እድሌን እንዳያመልጠኝ መሄድና መማር እንዳለብኝ እኔና ሜላትም ቀለበት ማድረግ እንዳለብን ተወሰነ በሀገር ባህላችን እኔና እናቴ ለሜላት ቤተሰቦች ሽማግሌ ላክን ቤተስቦቿ ትንሽ ቢግደረደሩም እሽ እሉ እኔና ሜላት ቀለበት አሰርን እኔም ወደ አወስትራሊያ ለትምህርት ሄድኩ ፍቅራችን እንደድሮው ሆነ እኔ ያለ ሜላት ሜላት ያለ እኔ ማንንም አንፈልግም ፍቅራችን ችግር ቢበዛውም ችግሩን ተቋቁመን አለፍን::
ተፈፀመ
ውድ አንባቢያን አስተያየትዎን ይስጡን 🙏
@gitm_post
4 827
✍Not Coin ምንድን ነው?✍
👉Not Coin በፈረንጆቹ January 2024 የተጀመረ ሲሆን፤ ሌላኛው የወደፊቱ Crypto currency ሆኖ እንደሚያገለግል ተስፋ ተጥሎበታል።
👉የመጀመሪያው Crypto Currency Bitcoin ሲሆን Jan 3, 2009 ነበር የተጀመረው። አሁን ላይ የአንድ bitcoin ዋጋ 68,825 የአሜሪካ ዶላር ነው። በኢትዮጲያ ብር ደግሞ ከ4ሚሊየን ብር በላይ ይሆናል።
👉Not coin ከተለቀቀ ገና 3ኛ ወር የያዘ ሲሆን ፤ April 1, 2024 ላይ ይጠናቀቃል ተብሏል። ከዛሬ ጋር 5ቀን እንደማለት ነው።
Not coin እና Crpto Currency በአገራችን ተቀባይነት ባይኖረውም፤ በሰለጠኑ ሀገራት ግን የተለመዱ ናቸው ይባላል።
👉bitcoin እስኪታወቅ ድረስ በነፃ ተለቆ ነበር ይላሉ ሰዎች፤ ጥቂቶች ብቻ በእጅ ቢያስገቡትም በዋላ በብዙ ገንዘብ እንኳ ሊገኝ የማይችል የአለማችን ትልቁ ገንዘብ ሆኗል እየተባለ ነው። ማን ያውቃል Not coin በተመሳሳይ ከፍተኛ ዋጋ የሚያወጣ ገንዘብ ቢሆንስ?
👉ለማንኛውም ከታች ሊንኩ ተቀምጦላችዋል።
https://t.me/notcoin_bot?start=r_581063_14978408
4 827
የድሀ ፍቅር
ክፍል 14
ሜላት ደወለችልኝ በጣም ደስተኛ ነበረች ደስተኛ ስለሆነች በጣም ደስ አለኝ ግን ምን እንዳስደሰታት አላውቅም የኔ ፍቅር ምን ተገኘ ዛሬ ደስተኛ ሆነሽልኛል አልኳት የኔ ውድ ዛሬ አዲስ አበባ ብትሆን አለህበት ድረስ እመጣ ነበር አለችኝ በደንብ አሳቀችኝ የኔ ፍቅር እውነት ደስታሽ እኔንም አስደሰተኝ የኔ ፍቅር አለችኝ ሜላት በሚያምር ድምጿ ወዬ የኔ ውድ አልኳት በምን ደስ እንዳለኝ ታውቃለህ ንገሪኛ ካልነገርሽኝ በምን አውቃለው አልኳት ሊያገባኝ የሚፈልገው ልጅ መጣ አለችኝ ቆሌዬ ግፍፍ አለ ተርበተበትኩ ሜላቴን ይሄንን ያክል ያስደስታል ብዬ አስቤ አላውቅም ግን ደስታዋ አስደነገጠኝ ምን ማለት ነው የእሱ መምጣት ነው እንደዚህ ያስደሰተሽ? አልኳት ከትትትትትትት😄 ብላ ሳቀችብኝ ይበልጥ ተናደድኩ እሽ ጠዋት እደውልልሻለው አልኳት ቆይ ቆይ እንዳትዘጋው አለችኝ የሜላት በልጁ መምጣት እንደዚህ መደሰት በጣም አበሳጭቶኛል ለዛም ነበር ደህና እደሪ ብዬ ስልኩን ልዘጋባት የነበረው መናደዴ ስለገባት ልንገርህ ምን መሰለህ ልጁ ስለመጣ አይደለም የተደሰትኩት እሱ እኔን ሳይሆን ታላቅ እህቴን ማግባት እንደሚፈልግ ስለተናገረ ነው አለችኝ ቆሌዬ ግፍፍ አለ ምን አልኳት አዎ እህቴን እንዳያት እሷን ነው ያጫችሁልኝ ብሎ ሲጠይቅ አባቴም አዎ አለ ከዛ እኔ ከጨዋታው ውጪ ሆንኩልህ ማለት ነው አለችኝ እየተፍለቀለቀች ኦ አምላኬ ብዬ ደስ አለኝ ሜላቴ እኔ ማመን አልችልም አልኳት እመን በቃ ከዚህ በኋላ ማንም በመሀከላችን አይገባም አለችኝ አብረን ደስ አለን ፈተናዬን ጨረሼ እስከማገኛት ድረስ ጓጉቻለው ፈተና ለመፈተን ለ3 ቀን ያክል ሲቀረኝ ሙሉ በሙሉ ትኩረቴ ጥናቴ ላይ ሆኖል ሜላትን በቀን አንድ ጊዜ ነው የማገኛት የሳምንት ፈተናዬን እንደምንም ተወጣሁ በጣም ይከብድ ነበር ግን በቃ ሰራሁት ውጤት እስከሚመጣ ድረስ ቤተሰብ ጋ ሂድኩኝ ሜላቴ መኪናዋን ይዛ መጥታ ወሰደችኝ ፍፁም ሰላም ተሰማኝ እናቴ ያላትን ብር አሰባስባ ለእኔ የምርቃት ዝግጅት ለማዘጋጅት ደፋ ቀና ማለት ጀመረች እኔ ግን ምንም ድግስ አልፈልግም ብላት ልትሰማኝ ፈቃደኛ አይደለችም ጊዜው ደርሶ የምርቃት ቀን ደርሶ እኔም ሜላቴም እናቴም ታናሽ ወንድሜን ይዘን ወደ ዮኒቨርሲቲ ሄድን የሚገርመው ከዮኒቨርሲቲ ተማሪዎች የበለጠውን ውጤት ያመጣሁት እኔ ነበርኩ የማዕረግ ተመራቂ ሆኜ ተመረቅሁኝ እናቴን አሰደስትኩ ሜላቴን አስደሰትኩ በቃ እኔም የልፋቴን ውጤት ሳይ ደስ አለኝ ሁሉንም አስደስቼ ድህነቴ ሳያግደኝ የምፈልግበት ደረጃ ላይ ደረስኩኝ በዮኒቨርሲቲያችን ከተማሩና ከፍተኛ ውጤት ካመጠት ተማሪዎች ውስጥ ተመርጠን የውጪ የትምህርት እድል እንደመጣልን ተነገረኝ ለሜላት ይሄ ዜና ባያስደስታትም ለኔ ግን ጥሩ እድል ነበር እኔና ሜላት ፍቅራችን በጣም ደስ የሚል ነው ለደቂቃ እንኳን ተጣልተን አናውቅም ይህ የትምህርት እድል ከተፈጠረ ጊዜ ጀምሮ ግን በወጣሁ በገባሁ ቁጥር ስልክ ባወራን ቁጥር መጨቃጨቅ ጀምረናል ነገሩ በጣም እያሳሰበኝ ነው.....
የመጨረሻው ክፍል ነገ ከ 30 React በኋላ ይቀርባል
@gitm_post
Вже доступно! Дослідження Telegram за 2025 — головні інсайти року 
