ግጥም
Відкрити в Telegram
በዚህ ቻናል በጣም ምርጥ እና መንፈስን የሚያድሱ ግጥሞች ፣ ተከታታይ ታሪኮች ፣ የኦንላይን ቢዝነስ ቲፖች ይቀርቡበታል መርጣችሁ አብራችሁን ስላላችሁ እናመሰግናለን Buy Ads https://telega.io/c/gitm_post ADMIN 👉 @Big_jor
Показати більше5 554
Підписники
+524 години
+457 днів
+18130 днів
Триває завантаження даних...
Схожі канали
Хмара тегів
Немає даних
Виникли проблеми? Будь ласка, оновіть сторінку або зверніться до нашого support-менеджера.
Вхідні та вихідні згадування
---
---
---
---
---
---
Залучення підписників
жовтень '26жовт '26
жовтень '26
+53
в 0 каналах
вересень '26
+263
в 3 каналах
Get PRO
серпень '26
+289
в 4 каналах
Get PRO
липень '26
+335
в 4 каналах
Get PRO
червень '26
+275
в 3 каналах
Get PRO
травень '26
+315
в 4 каналах
Get PRO
квітень '26
+178
в 1 каналах
Get PRO
березень '26
+199
в 5 каналах
Get PRO
лютий '26
+87
в 3 каналах
Get PRO
січень '26
+107
в 1 каналах
Get PRO
грудень '25
+129
в 1 каналах
Get PRO
листопад '25
+133
в 1 каналах
Get PRO
жовтень '25
+150
в 1 каналах
Get PRO
вересень '25
+126
в 1 каналах
Get PRO
серпень '25
+112
в 2 каналах
Get PRO
липень '25
+137
в 2 каналах
Get PRO
червень '25
+160
в 1 каналах
Get PRO
травень '25
+199
в 3 каналах
Get PRO
квітень '25
+169
в 3 каналах
Get PRO
березень '25
+170
в 3 каналах
Get PRO
лютий '25
+186
в 3 каналах
Get PRO
січень '25
+353
в 3 каналах
Get PRO
грудень '24
+394
в 5 каналах
Get PRO
листопад '24
+431
в 6 каналах
Get PRO
жовтень '24
+373
в 5 каналах
Get PRO
вересень '24
+271
в 6 каналах
Get PRO
серпень '24
+404
в 12 каналах
Get PRO
липень '24
+173
в 15 каналах
Get PRO
червень '24
+108
в 1 каналах
Get PRO
травень '24
+172
в 15 каналах
Get PRO
квітень '24
+388
в 28 каналах
Get PRO
березень '24
+376
в 26 каналах
Get PRO
лютий '24
+139
в 15 каналах
Get PRO
січень '24
+205
в 22 каналах
Get PRO
грудень '23
+601
в 41 каналах
| Дата | Залучення підписників | Згадування | Канали | |
| 07 жовтня | +4 | |||
| 06 жовтня | +10 | |||
| 05 жовтня | +9 | |||
| 04 жовтня | +12 | |||
| 03 жовтня | +10 | |||
| 02 жовтня | +4 | |||
| 01 жовтня | +4 |
Дописи каналу
በተሳልኹት (ሥ)ስለት
ምነው ዛሬ?
"ምኑ ማሬ?"
ሳቅሕ በዛ...
"ልትሄጅ አይደል እንደዋዛ?"
እና ያስቃል?
"እሱንማ ልብሽ ያውቃል"
ይሄ ማሳቁን?
"ከልቤ ሥር ያለው ሩቁን"
እንደምትወድደኝ ነበር 'ሚገባኝ
"ምኑ ሆነና እኔስ 'ሚያስነባኝ?"
ታዲያ እኮ ጥርስሕ.....
"ኦ! ልክ ነሽ አንቺ ፡ ለካ ይሄ ሳቅ ነው..
አታወሳስበው ኸረ ምንድነው?
"እኔም ያወቅኹት ፡ካንቺው እኩል ነው ።
እ?.."እናስይዝ ሰክረሃል!"
"ብዙ ገጽ ተቀድዷል ከሕይወቴ መሃል!"
ተው አትንካው ቁስሌን "
"አያመኝ ይመስል የኔ አልሽው ሥጋሽን?
እህ...
"ተይው.. ቦታዬ እንደጠፋኝ ፡ አታውቂም ዋጋሽን!"
እና ..ወዴት ትሔድ ?፡
"እዚሕ ጋር ይቆረጥ ይሄ ከንቱ ገመድ?"
ፍቅር ነበር ከንቱ?
"ከነዘር ማንዘሩ ከነምን ጅላቱ!!"
" ካልሕ እንግዲሕ......
ቻው! ቢያስደነግጥም!!"
"አንቺ ካደረግሽው ፡ በፍጹም አበልጥም!"
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
ብጽዓት ስዩም
| 2 | #የእኛ_ድንቁርና
አሁን በዚህ ዘመን አሁን በዚህ ግዜ፣
ዘር የመቁጠር ልክፍት የማበድ አባዜ፣
የዓለም ስልጣኔ ከሰማይ ላይ ደርሷል፣
የእኛ ድንቁርና እንደ አዲስ ታድሷል!
ሰው መሆን ተንቆ፣
ትልቅ ክብር ወድቆ፣
በዘር ብረት ምጣድ ሀገሩ ሲታመስ፣
የተማረው ሁሉ እያደር ሲረክስ፣
ምሁር ለምርምር ቆሞ ካላደረ፣
ግዜውን ካጠፋ ዘር እየቆጠረ፣
የትኛው ትውልድ ነው ሀገር የሚሰራ፣
ሁሉም ሰው ደንዝዟል በጅል ዘር ቆጠራ፣
ከዓለም ተነጥለን ወደ ሗላ ቀርተን፣
እስከመቼ ድረስ በዘር ተከፋፍለን?
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ | 862 |
| 3 | #ደኀና_ነው_ማለት_ነው
የፊቱን ውሃ ልክ ፂሙን አፈራርሶት፣
ጠይም ወዙ ነጥፎ፣ መልኩን ዳዋ ውጦት፣
ፀጉሩን አጎፍሮ፣ ከንፈሩን አጥቁሮ፣
ስስ ጭስ ተከልሎ፣ ብርጭቆ ስር አድሮ፣
የማይነቅዝ እህህ ለቀለቡ ሰፍሮ፣
ቤቱን ይቆልፋል::
ሰንብቶ ይወጣል
እግሩ ጥሎት ሲሄድ እየተከተለ፣
አካላቱን አዝሎ ዝግ፣ ቀስ እያለ፣
ይራመዳል አሉ በአበቦች መሐል
አብረን በተከልነው
ደኀና ነው ማለት ነው::
ትዝታ እየሳመ፣ ትላንትናን አቅፎ፣
ጨለማ ደርቦ፣ ደጃፉን ቆልፎ፣
ናፍቆት እየኳለ፣ ነፍሱን በሹል ሲነቅስ፣
ዘመን ሲሻገረው ሳይስቅ ሳያለቅስ፣
ይሉኛል አየነው
ደህና ነው ማለት ነው::
ማለዳ፣ ማለዳ ለአፉ ቡና አያስቀር፤
አከለበት እንጂ ለልቡ አዲስ ምሳር
አሁንም ያን ግጥም በቃሉ ይወጣል፣
አስር ሰዓት ሲሆን እደጅ ይቀመጣል፣
"በሚስጥር ቅበሪኝ" ቴፑን ያጫዉታል፣
ህልሙን ብቻ ትቷል!
ዛሬም ቡኒ ሹራብ ከጥቁር ሱሪ ጋር፤
ምን ገላው እንደኔ ቢከዳው ባያምር
ይለብሳል ይሉኛል ያኔ እንደምወደው
ደኀና ነው ማለት ነው::
ለራስ ለዘመዱ ያላነሰው ጉልበት
ልቡን በቀን በሌት ለማድቀቅ፣ ለማንከት
አጥቶት ለግዑዙ አውርዶ ለመስበር
ግድግዳው መሐል ላይ ከቆመ ምስሌ ጋር
ፊትለፊት አንጋጦ ይቆማል ውሎ አዳር
ናፈቀችኝ ይላል፣
ደኀና ነው ማለት ነው፤
ቃላት ይበቁታል::
ሴት ህፃን ልጅ አይቶ
ቶሎ አይሻገርም ሲወጣ ሲገባ
አይኑን ይጋርዳል
ህልሙን ገድሎ ሲቀብር ያልወጣለት እንባ
ሲነጋ ትኩስ ቁስል ለራሱ እየተካ፣
አቅሙን እዬፈጬ፣ ቅስሙን እየከካ፣
ነፍሱን እያረደ፤ ግን አለ እንደ ሰው፣
ሞት ልውስ ክህደት ፈትፍቼም ባጎርሰው፤
ደኀና ነው ማለት ነው::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ማህደር ወሰኑ | 1 236 |
| 4 | #ባይጨንቀው_አይደለም
ካብ ጸንቶ የቆመው በመደጋገፍ ነው
አንዱ ደንጋይ አንዱን ስለወደደው ነው
አንዱ ከተነካ ሁሉም ስለሚፈርስ
ከስር ያለው ድንጋይ ችሎ በመታገስ
ሌላውን ከላዩ ያነገሰው አዝሎ
መሰረት የሆነው ከስር ተንከባሎ
ከላይ የተጫነው ባለብዙ መንጋ
እሱ ከተነካ ቢያውቅ እንደሚንጋጋ
ችሎ ማደር መርጦ ለሌሎች እርጋታ
ሸክሙ እየከበደው ቢመርጥም ዝምታ
ባይጨንቀው አይደለም ከስር ተቀምጦ
በጋራ መኖርን ቢያስቀድም ነው መርጦ
አንተ ከላይ ሆነህ የስሩን ብትረግጥም
ያለመሰረትህ አንድ ቀን አታድርም!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ | 1 434 |
| 5 | #ተይ_ይግባሽ_ተመለሽ
ነፍሴ እስከሚወጣ ~ እኔ እየወደድኩሽ ፤
በቃኝ ህይወት ብሎ ~ ካመረረ ልብሽ ፤
ለመሄድ ወስኖ ~ ከቆረጠ አንጀትሽ ፤
የኔ ልብ ቆስሎ ~ ሆዴ ካዘነብሽ ፤
እመኝኝ የኔ ዉድ ~ አይቀናም መንገድሽ ።
የተዳፈነ እሳት ~ ፍቅር እኮ ህመም ነው ፤
ቆስቋሹን ሳይፈልግ ~ ድንገት ነው ሚነደዉ፤
ለተፈቃሪ እንጂ ~ ላፍቃሪ ከባድ ነው ።
ያሳለፍነው ጊዜ ~ ያሁሉ ትዝታ ፤
ላያልቅ ተነግሮ ~ በቀለም ጠብታ ፤
ሊያለያየን ከቶ ~ እንደምን በረታ ።
አስታወስሽ የኔ አለም !
ያኔ ስንገናኝ ~ እድሜያችን ነዉ ለጋ ፤
የወደፊቱን ህልም ~ህይወት ስናወጋ ፤
በፍፁም ሳንተኛ ~ እነዴት እንደነጋ ።
ይቅር ታዉቂ እንደሆን ~ ልማፀንሽ በእንባ ፤
አሉባልታ ወሬ ~ ላይጠቅመን ላይረባ ፤
ክፉንና ደጉን ~ ችለን እንግባባ ።
የማይዘልቅ ፍቅር ~ አጉል አስለምደሽ ፤
ይኸው አቅሌን ጥየ ~ ተንከራተትኩልሽ ፤
ልቤንም ወስደሽዉ ~ ሌላ እንዳላይ አርገሽ፤
እንደዘጋሽዉ ነው ~ እንኪ ግቢ ከፍተሽ ።
የዚህ ሁሉ ሮሮ ~ ምክንያቴ አንቺ ነሽ ፤
እንዲህ ስለምንሽ ~ ተይ ይግባሽ ተመለሽ ።
እኔም ሳልጀማምር ~ አንቺም ሳትጀምሪ ፤
ሳይርቅ እንታረቅ ~ እንሁን አስተማሪ ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍️ ሐና | 1 708 |
| 6 | #አባ_ጨጓሬ_ነው
በእኔና አንቺ ፍቅር በእኔና አንች አብሮነት
ተፈጥሮም ያዜማል እንኳንስ አንደበት
አበቦች ፈንድቀው ንቦች ማር ቢሰሩ
ዜመኜች በዋሽንት ምን ቢያንጎራጉሩ
በእኔና አንቺ ፍቅር ሀሳብ መነሻ ነው
የደራሲው ብዕር ቅኔን የሚቀኘው
ፀሀይ ከጨረቃ የሚፈራረቁ
በተራ በተራ ዘወትር የሚደምቁ
ሳጋንን አይደለም እመኝኝ ለኛ ነው
ህይወት ያለ ፍቅር ከቶ ጣዕምም የለው
ሁሉም የተሰራው እጅግ ውብ የሆነው
ፍቅርን ለማጀብ ለእኛ ደስታ ነው!!!
ስነግርሽ እመኝኝ ውዴ አለጥርጥር
አባ ጨጓሬ ነው ዓለም ያለፍቅር።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ | 1 741 |
| 7 | #ዛሬ_ወዴት_አለ?
ቅኝ አገር መሻማት ዛሬ ወዴት አለ?
የመርከብ ወንበዶች ጊዜዓቸው የታለ?
እንደዱሮ አይሆንም
ታሪኩ ቢወራ ሃተታው ቢለቀም
እንደጥንቱ አይሆንም።
መሰሉም ቢመጣ ጥቂት ተለውጦ
«ታሪክ ተደገመ!»
ይባላል ሲጠፋ ጊዜ እየታመመ።
በራሱ ከረጢት ገብቶ ተጠቅልሎ
ለብቻው ሲደበቅ ሸሽቶ ተገልሎ
ሁሉም ይለወጣል ጊዜ እየቆጠረ
አንዳንዴም ይረሳል እየተሰወረ።
ጨረቃ እንደክብሪት ፀሃይ እንደሻማ
በርተው ይጠፋሉ
ተቃጥለው ያልቃሉ።
ሰማይ ተቀዳዶ እንዳሮጌ ሸማ
ከዋክብት አንድ ባንድ ወድቀው ተንጠባጥበው
የባህርይ ፍጥረቶች እንዳልነበር ሆነው
ሲመጣ ጊዜያቸው
ያልፋሉ ጨልመው።
የማይቀር ምን አለ?
የማይቀር ምን አለ?
ሞትም ሙት ይሆናል የሚሞት ሲጠፋ
ጊዜም እየገፋ
የሚገፋው ሲያጣ ይሆናል የጠፋ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ገብረ ክርስቶስ ደስታ። | 1 985 |
| 8 | #ቀልባቸው_ተወስዶ
ሞልተሽ በጎዳናው መልተሽ በመንገዱ
ሌሎች ትኩረት ሰጥተው እንዴት ይራመዱ
ቀልባቸው ተወስዶ በውበትሽ ፈዘው
ሁሉም አድናቂሽ ነው ያንቺ ነው ጎዳናው
ስንቱ ተላተመ ስንቱ ሰው ሰመጠ
አረማመድሽ ላይ ትኩረት እየሰጠ
አፍዝ አደንግዝ ነው መልክሽ አስገራሚ
ኬሬ ዳሽ ነው ጆሮሽ ማንንም አትሰሚ
ተመላለሽበት ጎዳናው የግልሽ
ግድ አይሰጥሽ ከቶ ማንም ቢከተልሽ
ጥላሽን ዘርግተሽ ከቤትሽ ውጪና
ሁሉም እግሩ ይጋጭ ልማዱ ነውና።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ | 2 232 |
| 9 | #ሰው_ነው_የረቀቀ
ሰው ነው የረቀቀ
ከሜርኩሪ ቬነስ፥ ከጨረቃ ከማርስ
ከፕሉቶ ኔፕቱን፥ ኡራኑስ የላቀ
ከጁፒተር ሳተርን፥ ከጣይ የደመቀ
ባካባቢው ሁሉ እያሸበረቀ፥
ሰው አደገ አወቀ፥
መሬት እንቁላሉን ሰበረ መጠቀ፤
ሰው ዓለምን አዬ....
በጨለማው ቦታ ዶቃ አንፀባራቂ
ውብ ሰማያዊ ኩዋስ፥ ሮዝ አብረቅራቂ።
በተጣራው አየር በነጣው ደመና
ባረንጉዋዴው ባህር ውሃ ተሸፍና ፥
ውብ ሉል ኮከብ ዓለም፥ የጠፈር ላይ ጤዛ፥ የሰው ልጆች እናት፥ የሰው ልጆች ቤዛ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ | 2 786 |
| 10 | #ማነው_ስልጡን_ታዲያ?
ቀሚስ ገዛሽ አሉ በውድ ሸምተሽ፣
ለምን አለበስሽም? እንደናትሽ ፈትለሽ?
ጭኗ እዝርት አያውቀው ይልሻል ሀገሩ፣
ስለምን አቃተሽ? ከእናት ስር መማሩ?
አለላ ቢሰጡሽ ሰበዝ ገዝተው ዛሬ፣
መስፋቱ ተስኖሽ ትሪ ሞላ ሀገሬ።
አገልግል መሶቡ የእናትሽ ፈጠራ፣
ተዘነጋሽ እንዴ? እንቅጩን እናውራ?
ስንደዶ ተገዝቶ ቢሏት ስፊ ሰፌድ፣
ተጠቀመችበት እሳቱን ለማንደድ።
አንች የከተሜ ልጅ ልውሰድሽ ወይ ገጠር፣
እራስ ፈትሎ መልበስ ከናፈቀሽ ማማር!
ሗላ ቀር ይሏታል ባለሀገሯን ጉብል፣
ከፊት ግን ቀድማለች ተውባ በባህል፣
አንች ገዝተሽ ልበሽ ሰልጥኝ በመግዛት፣
የገጠሯ እህቴን በሙያ ላትቀድሚያት፣
ፈትላ ትለብሳለች ሰፍታ ትበላለች፣
ከተሜዋ እፈሪ ቀድማሽ ሰልጥናለች።
ውብ ኢትዮጵያዊት በኩታ ደምቃለች፣
የእናቷን ጥበብ ውርስ ጠብቃ ዘልቃለች!!!
ያንች ማወቅ ከንቱ ሸምቶ መልበስ ነው፣
እስኪ እንጠያየቅ ማነው የሰለጠነው?!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ | 2 662 |
| 11 | #መጭውን_ጠበቅሁት
ከማዶ እሚመጣው፥ ዘመድ ነው እንግዳ
ከላይ የተለጋው፥ ኳስ ነው ወይስ ናዳ
ብየ መች ጠየቅሁኝ
መጭውን ጠበቅሁት
ድንጋይ ላይ ቁጭ ብየ፤ ጸሀይ እየሞቅሁኝ፥
መከራም አላጣም፥ ተድላም አልጎደለኝ
ደንታ ነው የሌለኝ፥
ባካል በስሜትም፥ ታሞ ላገገመ
ወድቆ ለተነሳ ፥ እየደጋገመ
ከገዛ ጉድጓዱ ፥አጽሙን ለሚለቅም
ሞትም ብርቅ አይደለም፥ ትንሳኤም አይደንቅም ::
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም | 2 596 |
| 12 | #ሰው_ማጣት_ነው_ክፉ!!
የኔን ሆድ ለመሙላት አትሽቀዳደሙ
ይልቅ ፍላጎቴን ጭንቅላቴን ስሙ
እርሱ የሚላችሁን ህመሙን አክሙ
ሰው ነው የጎደለው ሰው በመሆን ቁሙ
ስጋ ጉርስ አያጣም አሽቃብጦም ይበላል
ሰው ምግብ አይነፍግም አሽሟጦ ይሰጣል
ጭንቅላት ነው እንጅ ሰው አምጡ የሚለው
ሆድስ ስልቻ ነው በህል ነው የሚቆመው
ከርስማ ይሞላል ለምኖም ይጠግባል
ከባሰበት ደግሞ ሀገርን ይዘርፋል!
ሆዴ መች ጎደለ ሳይሰራም ይጎርሳል
ቁራሽ ዳቦን በልቶ መኖርን ለምዶታል
እኔን የሚርበኝ የሚያንገበግበኝ
አላስተኛ ብሎ እንቅልፍ የሚነሳኝ
ሰው መሆን ጠፍቶብኝ ግራ ቢገባኝ ነው
ሰው ሁኑኝ እያልኩኝ ሰው የምፈልገው
ሆዴን የሚሞላ ወዳጅ መቸ አጣሁኝ
ምግብን የሚሰጥ ሰው እኔ አልጠየኩኝ
እውነት የሚያስተምር አጥቼ አለቅሳለሁ
ለመኖር በመቅመስ ገዜ እጠብቃለሁ!!!
በድቅድቅ ጨለማ ፀሀይ እሞቃለሁ
ውሃንም በወንፊት ስቀዳ እኖራለሁ
ሰው በሌላት ሀገር ሰው እየናፈኩኝ
ከተከመረ ጭድ መድፌ እየፈለኩኝ
በቀን ፋኖስ ይዠ መብራት አበራለሁ
ደግሞ በጨረቃ ፀሐይ እሞቃለሁ!!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ | 2 875 |
| 13 | 🌼እንኳን ለ 2019 አዲስ ዓመት በሰላም፣ በጤና እና በፍቅር አደረሰን!🌼
አዲሱ ዓመት፡ የጤና፣ የሰላም እና የፍቅር፤
የታሰቡት መልካም ምኞቶች ሁሉ የሚሳኩበት፤
የስኬት እና የበረከት ዓመት ይሁንላችሁ!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
🌼🌼🌼መልካም አዲስ አመት!🌼🌼🌼 | 2 668 |
| 14 | #እኔ_ወድሻለሁ
እኔ ወድሻለሁ
ታስሮ እንደ መፈታት
እንደ ጣኦስ ውበት
እንደ ዝሆን ብርታት
ዳዊትን ከጎልያድ
ደርቦ እንደመምታት፤
እኔ ወድሻለሁ
ጦም ውሎ እንደመጉረስ
ወልዶ እንደመታረስ
ቶምቦላ እንደመድረስ
ካላሙዲ ንብረት
ግማሽ እንደመውረስ፤
እኔ ወድሻለሁ
እንደ መቅደስ እጣን
እንዳፍለኛ ስልጣን
ያንች ልዝብ ሰይጣን።
እኔ ያንች ቡዳ
ያንች ልዝብ ሰይጣን።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ገብረ ክርስቶስ ደስታ | 2 875 |
| 15 | #እኔ_ሞኙ_ልጅሽ
አንችን ገላጭ ቅኔ አንች ገላጭ ዜማ
የውበትሽን ጥግ የክብርሽን ግርማ
ብሞክር ባስሞክር በስንኝ ቋጠሮ
ቤት ባልመታ ግጥም በቃል እጉርጉሮ
በሀገር መስዬ ላወድስሽ ብጥር
አልገልጽልህ አለኝ እኔስ ያንችን ፍቅር
አናት ከማለት ውጭ ሌላው ቀለለብኝ
ብጽፈው ባጽፈው ሚዛኑ አነሰብኝ!
የፍቅርሽን ልኬት የደግነት ጥልቀት
የትኛው ቃል ይሆን ገላጭ እናትነት
ቃል አዋቂ ፈለኩ የተማረ አብዝቶ
ከውስጡ የሚፈስ ዜማ ቅኔ ሞልቶ
ግን አላረካኝም ውበቱ አነሰብኝ
ለደግነትሽን ክብር በቂ ቃል አጣሁኝ
ያወቁ የበቁ ሽህ አመት ቢመክሩ
ቋንቋ ላይ ተራቀው አብዝተው ቢማሩ
እናት ነው ውብ ቃሉ ረቂቅ ቀመሩ
ሌላ ስም የላትም አትመራመሩ!
አልኳቸው እናቴ እኔ ሞኙ ልጅሽ
ቢሳነኝ በቅኔ በዜማ ልገልጽሽ
ሌላ ቃል ፈልጌ አስፈልጌ ባጣ
ከደጋ እስከቆላ ወርጄ ስወጣ
ከፊደላት ድምር እናት የሚል መጣ
እየደጋገመ እርሱው ከአፌ ይውጣ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ | 2 797 |
| 16 | አንዳንዴ...
ባልተገራ ፈረስ
በፈጣን ድንጉላ
ኑሮን ባቦ ሰጠኝ
ህይወትን በመላ
በዚህ በኩል ሲሉህ
ንጎድ ወደ ሌላ፤
እስከመቼ ድረስ
ዳር ዳሩን መራመድ ፤ በጭምት ሰው ስሌት
በክብር ካልመጣ፤ ሞክረው በቅሌት
ሰው ቅፅር አይደለም፤ በእሾህ የታጠረ
እንድትጥሰው ነው፤ ህግ የተፈጠረ::
አይሰለቺህም ወይ
መኖር በተጠንቀቅ
አንዳንዴ
አየር ላይ ደንሰህ ፤ በግንባርህ ውደቅ
አንዳንዴ
ኮርቻህን እርሳት
ርካህብህንም ሳት
ፋይዳ አይጠፋምና፤ ወድቆ ከመነሳት !
በትቢያ ላይ ወድቀው
የተነሱ አሉና፤ በሉል ባልማዝ ደምቀው !
አንዳንዴ
ልጉዋሙን ልቀቀው!
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ በእውቀቱ ስዩም | 2 781 |
| 17 | #ማሪኝ_እንዳትለኝ
ውዴ ትዝ ይልሀል ያኔ እንደጀመርን
እኔና አንተ ሁነን ፍቅርን ስንወጥን
ወሬህ ማይጠገብ ንግግርህ ጣፋጭ
የጨዋታህ ለዛ ቃላቶችን መራጭ
በስሜንኳ አጠራኝ ቁልምጫህ የብቻ
አስተዋይነትክ የትም የለህ አቻ
ቀልቤን ማንነቴን እኔነቴን ወሰድክ
ልቤንም ሰጠሁህ ሁሉን ተቆጣጠርክ
ባሌ ብቶን ብዬም አብዝቼ ተመኘሁ
ያንተ ሆኜ ልኖር ህይወቴንም ሰጠሁ
አንተ ግን °°°
መሸነፌን አይተህ ባንተ መረታቴን
መውደዴን አቅለህ አሳንሰህ ፍቅሬን
ሌላ ሰው ሆንክብኝ የማላቀው ትናንት
ፍፁም ተቃራኒ ካለፉት ግዚያት
ያሳየኸኝ ነገር ያ ሁሉ ቀነሰ
ፍቅሩም ቁልምጫውም እያደር አነሰ
መምረጡም ቀረና ቃላቱን ማሳመር
በእሾክ ንግግርህ ታሳምመኝ ጀመር
ልቤን ስለፈተሽክ የመውደዴን መጠን
የትም አቴድ ብለህ ጀመርክ መጨከን
ምን አጠፋሁ ውዴ?
ታምኜልህ በኖርኩ ሁሉን ነገር ትቼ
ጥፋት ስተትህን በይቅርታ አጥፍቼ
ሁሉን ረስቼ
ቁም ነገር ባሰብኩኝ ለነጋችን በሚል
አብረን እንድንኖር ጎጆ እንድንደለድል
ምነው የምወድህ ታድያ ምን አደረኩ
ነውር ሰራሁ እንዴ አንተን ስላፈቀርኩ
ያ ሁሉ ሳያንሰኝ
ላንተ ስል ደክሜ ላንተ ስል ታምሜ
ከሳቅ ተጣልቼ ጠፍቶ ያ ሰላሜ
በእንባ ስገፋ ዕልፍ የሆኑ ቀናት
ሀዘን ያጀባቸው ምሽትና ንጋት
አንተ ግን ጉዳቴን ሰምተህ ህመሜንም
እንዴት ሆነች እንኳ ብለህ አልጠየክም
አንደምን አስቻለህ...?
እንዴትስ አራራህ ...?
እንዲህ ነበር እንዴ ለኔ የሚገባው ?
ለፍቅርህ ለሆንኩት ምላሹና ዋጋው?
ብቻ እንዲ ስትገፋኝ ደርሰህ ስታርቀኝ
ደስታ እንደናፈቀኝ
ባንተ ተስፋ ስቆርጥ ሁሉም ነገር አልፎ
ልቤም ከጉዳቱ ከስብራቱ አርፎ
መከፋቴም ቀርቶ እምባዬም ሲደርቅ
ውስጤም ያንተን ፍቅር ከልቡ ላይ ሲፍቅ
ማሪኝ እንዳትለኝ ከረፈደ ገብቶህ
አዲስ ቀን ሲጀምር ልቤ አንተን ረስቶህ
ሂዎትን ሲቀጥል አንተን ላንተ ትቶህ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ | 2 928 |
| 18 | #እኔ_ልማልብሽ
አብሬሽ እያለሁ በፍቅር ሰክሬ
ልሙትልሽ ያልኩሽ ውዴ ቀባጥሬ
ዛሬ ፀፅቶኛል እውነቱን ልገርሽ
አንቺም እንዳታዝኝ በቃ ልኑርልሽ
ማይብኝ በስሜ ብየ የነገርኩሽ
ዛሬ ግን ሳስበው እኔ ልማልብሽ
አፅምሽ እንዳያዝን በብቸኝነቴ
በሀዘን ተጎድቶ ሳስቶ ሰውነቴ
ይረሳኛል ብለሽ አታስቢ ፍቅሬ
ከጓደኛሽ ጋራ ብኖር ነው አብሬ
ከዚያ ውጭ በፍጹም ከአንቺ ሌላ ማሬ
ድንገት እርሷም ብትሞት ከጓደኛዋ ጋር ብጀምር ነው ፍቅሬ።
እመኝኝ¡¡¡¡¡ ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ | 2 721 |
| 19 | የማይወዳደር እኩያ የሚያጣ
ከልቤ ግርጌ ስር አንዳች ስሜት ወጣ
ተሰማኝ ወደድኩህ ያንተን ጣዕም ለየሁኝ
ቆዳዬ ቀመሰህ ምላሴን ከዳሁኝ
ከየትኛው አካሌ ፍቅርህ የወደቀው
የሚያርበተብተኝ ጥፍሬን የሚነዝረው
አካልስ አለ ወይ የሚታይ ሚቀመስ
ሴትነት ገላዬን ነክቶ ሚያጎለምስ
ንገረኝ አንተዬ ከደጅ እንዳያድር ዳስም ልጣልለት
እንዲህ ያለ ፍቅር አያድርም ከኔ ቤት
በአዳፋዬ ባያድፍ ንፁህ ጥሩ ፍቅርህ
ከቆሸሸ ገላ ከዚህ በድን ይሽሽ
እንዲህ ያለ ልመና ሚዛን አያነሳም
የፍቅር ባህሪ ዙፋንን አይሻም
የት ጋር ነው የሚሰማኝ ምኔን ነው የያዝከው
የት ጋር ነው ያገኘኸኝ ምኔን ነው ያጣኸው
ብቻ ከልቤ ስር ስሜቴ ይፈልቃል
የደረስክበትን ያልደረስክበትን
ረቂቁ ፍቅርህ እሱ ብቻ ያውቃል።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ረድኤት ተረፈ | 2 846 |
| 20 | #የእድሜ_ሌባ!!!
ከህይወት ሰሌዳ ከእድሜ ያልተማረ
በሽበቱ ደምቆ በአንቱ ያልከበረ
ኮረዳ ፍለጋ ዘቅጦ የዛከረ
የእድሜ " ፐ " ላይ ደርሶ ግን የደነቆረ
በቅሌት ጎዳና የሚመላለሰው
የትዳሩን ዋጋ አንሶ ያሳነሰው
ንሯል አትበሉኝ በከንቱ እድሜ ቁጥር
ሳይኖር የሞተ ነው ያልታደለ ፍቅር
ከልጆቹ እኩያ አስረሽ ምችው ዜማ
የሚርመሰመሰው በሀብት ከተማ
እድሜውን ዘንግቶ ቁልቁል የወረደ
ጤነኛ ምትሉት ግን እርሱ ያበደ
የምትሰግዱለት ሲወጣ ሲገባ
መሆኑን እወቁ እርሱ የእድሜ ሌባ።
@gitm_post
♡ ㅤ ❍ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢʰᵃʳᵉ
✍ ስንታየሁ ሀብታሙ | 2 902 |
