ዘ ተ ሐ ር ያ ን 🧘🏻♂️
Відкрити в Telegram
እኔ ምናቤ ውስጥ የተፈጠረብኝን አልያም አንብቤ የወደድኩትን አሰፍራለሁ። . . . ለማንኛውም ሀሳብ ወይም አስተያየት inbox:- @Beck1me
Показати більше1 114
Підписники
Немає даних24 години
+17 днів
+2030 днів
Архів дописів
1 114
እቺን ቃል ንገሯት
ተፈርዶብኝ እንጂ
መለየት ተስኖኝ ጥሬውን ከብስል
ሀገሬው ምድር ላይ
እሷ ብቻ ቆንጆ የቀረች ይመስል
ዞር ባለች ቁጥር
አትራቂኝ እያልኩኝ የምለማመጣት
ልቻለው ብዬ እንጂ
:
ምሳሌ ከምሆን አፍቅሮ ከማጣት።
ገደል ግቢ በሏት
ይሄው ደግሞ ዛሬ
ገላዋን በሙሉ አወደችው ሎሽን
ፀጉሯን አጎፈረች ደመቀች በሽንሽን
ከንፈሯን ምን ይሆን ደግሞ የቀባችው
የእጇን አይበሉባ በቄንጥ
አኮናትራ ሰአቷን አየችው
ገናነው መሰለኝ ጊዜን ታዘበችው
መንቀር አለችና መስታወት ፊት ቆመች
ደግሞ ፈገግ አለች ጥርሷ ይርገፍና።
:
ማርያምን ታምራለች
ዘከርኳት በወዳጅ መከርኳት በዘመድ
ቀለበት አይጠቅማት አሰርኳት በገመድ
ገደል ግቢ በሏት
ልቤን ከጋረደው ወዳጅ
እንደ እደማ/በት
ከከለላት ስውር አይነጥላ እንዲ እዳማረባት
ገደል ግቢ በሏት
:
ልቤን ከጋረደው ወዳጅ
ከከለላት ስውር አይነጥላ
መሄድ ከጀመረች አፍቃሪ ሰውጥላ
ልክ እደገላዋ ይለስልስ መንገዱ
ፍፁም አይጎርብጣት
አየሩ በሙሉ ፍክት ይበልላት
እንደ ጥርሷ ንጣት
እያልኩኝ ፎክሬ
እንደ ገጣሚ ቃል ልቤ አልጀነጅን
የት አባቷን እና በፀበል ካልወጣች ትረሳለች በጅን።
:
ገደል ግቢ በሏት
የት አባቷን እና እንዲህ የሚያምርባት
የት እናቷን እና እንዲህ የሚደምቅባት
ገደል ግቢ በሏት
እስከ መቼ ድረስ ስቀባ
እኖራለው ጉድፍ ልቧን ስኩል
ገደል ግቢ በሏት
እኔ ገደል ስር ነኝ
ድንገት ከወደቀች እንድቀበላት።
✍️ አስታወሰኝ ረጋሳ
1 114
Repost from ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚
ግዜ የማይፈታው ችግር የለም የሚባለው እውነት አይደለም። አንዳንድ ነገሮችን ውሳኔ እንጂ ግዜ አይፈታቸውም ለመወሰን የፈራችሁት ነገር ምናልባት ትክክለኛው ውሳኔ ሊሆን ይችላል።😇
1 114
Repost from ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚
ሮማን ከፊቱ ፤ የፊያሚታ ጊላይ መቃብር ከኋላው ፤ በመካከላቸው ቆሞ ቀረ ። በመጨረሻ ሰው ብቻውን ነው ፤ብቸኛ ነው ። ብቸኛነት ተሰማው ። ልቡ የኃዘን አንጉርጉሮ አንጎራጎረ ። ልቡ የኃዘን አንጉርጉሮ የማያንጎራጉር ሰው አለ ይሆን? ግን ልናዳምጠው አንፈልግም ። ለምን ? ደስተኞች መሆን እንፈልጋለን ። ተስፋ ከመቁረጥ ተስፋ ማድረግ ይሻላልና ባናገኘውም ቅሉ ዘላለም እንሻዋለን ። ዘላላማዊ ተስፋ ፤ የኃዘንና የእንጉርጉሮ። ሰው ያለትስፋ ምንድነው? ተስፋ በልባችን ማሳደር አለብን ፤ ተስፋ በሌለበት ቦታም ቢሆን ።
ኦሮማይ፦ ገጽ 371
1 114
በርግጥ ምን እንደምፈልግ ታውቂያለሽ? ሰላም ነው የምፈልገው፣ ሰላም ስጡኝ፣ ማንም እንዳይረብሸኝ ስል መላዋን ዓለም ላንድ ሳንቲም ብሽጣት ቅር አይለኝም፡፡ ሻይ መጠጣቴን በመተው የሰውን ዘር ሁሉ ከኩነኔ ማዳን ቢቻለኝ እንኳን ሻይዬን አግኝቼ ፍጡር ገሃነም ሲገባ ማየት እንደምመርጥ ታውቂያለሽ???
📖 :~ The notes from under ground
1 114
አንዳንዴ . . . ያለ ነው!
አንዳንድ ጊዜ ማመንታት ያለ ነው - በፍጹም ግን ወደ ኋላ አንመለስም!
አንዳንድ ጊዜ መፍራት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንንበረከክም!
አንዳንድ ጊዜ ተስፋ መቁረጥ ያለ ነው - በፍጹም ግን አናቆምም!
አንዳንድ ጊዜ መሸነፍ ያለ ነው - በፍጹም ግን ሕይወት ከሚያቀብለን የየእለት ጦርነት አንሸሽም!
አንዳንድ ጊዜ መድከም ያለ ነው - በፍጹም ግን ዝለን አንወድቅም!
አንዳንድ ጊዜ ግራ መጋባት ያለ ነው - በፍጹም ግን አንቅበዘበዝም!
አንዳንድ ጊዜ በሰው መገፋት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከዚያ ሰው ውጪ መኖር አያቅተንም!
አንዳንድ ጊዜ ድብርት ያለ ነው - በፍጹም ግን ደንዝዘን አንቀርም!
አንዳንድ ጊዜ ለጥያቄ መልስ ያለማግኘት ያለ ነው - በፍጹም ግን ከመጠየቅ አናርፍም!
አንዳንድ ጊዜ ክፋት ያሸነፈ መምሰሉ ያለ ነው - በፍጹም ግን መልካምነትን አንጥልም!!!
1 114
Repost from ኖህቶኤል ከመጻሕፍት ገፅ📚
እንዳንድ ምሽቶች ስለ እግዜር መኖር መጠየቅ አቆምና ከናካቴው የነገሮች መኖር በራሱ ምን ማለት እንደሆነ ማሰብ እጀምራለሁ፤ ለዚች አጭር ሕይወት ለምን እንደተፈጠርኩ፤ ለምን እንዳውቅ እንደተፈረደብኝ...
ምንአልባት ዩኒቨርስ መልስ የለው ይሆናል።
ምናልባት ከዝምታው ጀርባ ምንም ድምጽ የለም፣
ምንም የሚገኝ ትርጉም የለም።
እና ግን አሁንም አለሁ።
እንደነቃሁ ነኝ።
እየተነፈስኩ ነው።
ጨለማው ላይ አፍጥጫለሁ።
ምንአልባት ህልውና ይሄው ይሆናል...
...አላፊ እንደሆንክ እያወቅክ መኖር...🌘
1 114
ባሻዬ! ሆስፒታል ሄጄ ዶክተሩ ሁለት መድኃኒቶችን አዘዘልኝ። ሁለተኛውን መድሃኒት ወዲያውኑ አገኘሁት። መጀመሪያ ላይ የተጻፈውን አንደኛውን መድኃኒት ግን 13 ፋርማሲዎች ዞሬ አጣሁት።
ድራጊስቶቹ ያሉኝን ልንገርህ፣
አንዱ "መድኃኒቱ ዛሬ የለም። ነገ ላምጣልህ" አለኝ፣
ሌላው "ይህንን መድኃኒት የሚያመርተው ካምፓኒ ተዘግቷል። ሌላ ካምፓኒ ያመረተውን ተመሳሳዩን ልስጥህ?" አለኝ፣
ሌላው ደግሞ "ይሄንን መድኃኒት ብዙ ሰው ይፈልገዋል። አሁን ከተማ ውስጥ አይገኝም። በብላክ ላምጣልህ?" ብሎ አስደነገጠኝ።
አንዱ ግን "ይሄ መድኃኒት ለካንሠር ህሙማን የሚሰጥ መድኃኒት ነው። ካንሠር የያዘው ቤተሰብ አለህ?" ሲለኝ በጀርባዬ ልወድቅ ስል ግድግዳውን ተደግፌ ተረፍኩ።
በመጨረሻም ያዘዘልኝ ዶክተር ጋ ሄጄ "መጀመሪያ ላይ የጻፍከውን መድኃኒት ፈልጌ አጣሁት" ስለው፣ ወረቀቱን ተቀበለኝና እንዲህ አለኝ "አቶ ተሰፋዬ! ይሄ እኮ የመድኃኒት ስም አይደለም። እስክሪብቶዬ አዲስ ስለሆነ እንዲጽፍልኝ የሞከርኩበት ነው" ብሎ ወረቀቱን ቀዶ ጣለው።
ባሻዬ! . . ባልተጻፈ ህግ ሰው በሚሞትበት አገር በተጻፈ ወረቀት ብሞትብህ እንዳይደንቅህ።
ፋርማሲስቶቻችን ለዘላለም ይኑሩ!!!🤍🙌
1 114
“ሰዎች የተሻለ ነገር ይዘው ወደ አለም ካልመጡ መጋባት የለባቸውም አልኳት። ካንቺ የበለጠ ቆንጆ ልጅ፣ ካንቺ በላይ ሀብታም፣ በሁሉም ነገር ካንቺ የተሻለ ልጅ ለመውለድ ብቻ ታገቢያለሽ። ነገር ግን ደስታን ለማምጣት መከራን ማግባት ምን ዋጋ አለው?። ከአቧራ የባሰ ጭቃን ከመሸከም ውጭ። በእንዲህ ያለህ ችግር መጋባት ከመከራ በቀር ለዓለም ምንም አዲስ ነገር አያመጣም!!!።”
:~አህመድ ካሊድ ታውፊቅ
1 114
✍️አትረባም ስትባል አመስግናለሁ እያልክ፣አታውቅም ሲሉህ እስኪ አስተምሩኝ እያልክ፣የለህም ሲሉህ ያለኝ ይበቃኛል እያልክ፣ዝም በል ሲሉህ በደስታ ዝም እያልክ ፣ተቀደምክ ሲሉህ እለፉ እያልክ፣እርግጠኛ የሆንክበትን ነገር ሲያስረዱህ እህ፣አሃ፣እም.. እያልክ ሰምተህ በማለፍ ሰላምህን አስጠብቅ!! 🤍🤝
ኦሾ1 114
Someone said💭
.
.
እሩቅ ያለው ያከብርሀል
ቅርብህ ያለው ይንቅሀል. . .
እኛም ጨረቃን የምንወዳት እሩቅ በመሆኗ ነው!!!
sometimes ራቅ ብሎ መኖር is much better 🙌🖤
1 114
የ self development እንደ
1.Atomic Habits
2.The power of now
3.Limitless
4.The subtitle of art not giving a fuck
5. rich dad poor dad
6.time management
ያሉ መፅሀፍ ይፈልጋሉ እንግዲያውስ ይቀላቀሉ
https://t.me/Amharic_Books_storee
1 114
እና ይኸውልሽ :
ምን ብንበረከክም ደጁ ተደፍቼ
ወደርሱ ብጠጋ ሁሉን ነገር ትቼ
አንቺን እንዲያስረሳኝ ብውል ከደብሩ
አውቆ እንዳላወቀ ዝም አለኝ እግዜሩ!
ደግሞም : ይኸውልሽ
..ያ ሰይጣንም እንኳን የክፉዎች አውራ
ምን ባጎበድድም ብዘይር ባጓራ
ከውስጤ ያስወጣሽ አንቺን ያስረሳኝ ለት
ሙዳይ ሙሉ ጨሌ ነበር ማስገባለት።
ግና ለኔ ፡ ግዜ
ግና ለኔ ግዜ ሰይጣን እንኳን ጸድቆ
ጠብቃት ይለኛል እንደማትመጪ አዉቆ
1 114
የባከነ ጊዜ!
“በአንድ በሚፈስ ወንዝ ውስጥ ከአንድ ጊዜ በላይ ማቋረጥ አትችልም” ይባላል፡፡ እውነት ነው!
ይህ አባባል ሲተነተን፣ አሁን በእግሮችህ ተራምደህ የገባህበት ወንዝ አልፏል፡፡ ስትገባበት የነበረው ውኃ ቀጥሎ ለሚፈስሰው ውኃ ስፍራውን ለቆ በመሄዱ ምክንያት ተመልሰህ ብታቋርጥ ሌላ ውኃ ነው የምታገኘው፡፡ ወንዙ አንድ ነው፣ ውኃው ግን የተለያ ነው፡፡ ፍሰቱ ተመሳሳይ ነው፣ ወንዙ ይዞት የሚመጣው ነገር ግን የተለያየ ነው፡፡ የአፈሳሰሱ ሂደት ያው ነው፣ የፈሰሰው የውኃው አካል ግን ሌላ ነው፡፡
የጊዜያችንም ጉዳይ እንደዚሁ ነው፡፡
⏱️ የሰዓታት፡- ነግቶ እስኪመሽ የሚመጡትና የሚሄዱት ሰዓታት በተመሳሳይ ስም ይጠራሉ፣ ይዘውት የሚመጡትና ይዘውት የሚሄዱት ምርጫ ግን የተለያየ ነው፡፡
⏱️ የቀናት፡- ከሰኞ እስከ እሁድ ያሉን ቀናት በስም ተመሳሳይ ናቸው፣ ይዘው መጥተው የሚያሳልፉት እድል ግን ልዩ ልዩ ነው፡፡
⏱️ የወራት፡- በየሰላሳ ቀናት የሚቀያየሩት ወራቶች መምጣትና መሄድ አንድ አይነት ነው፣ እነሱም ቢሆኑ ደግሞ የማይገኝ እድልን ይዘው መጥተው ጥርግ ብለው ይሄሉ፡፡
ጊዜ እንዲህ ነው! ሲመጣና ሲሄድ ያለው “አንድ አይነትነት” ያታልላል፡፡ የምንባንነው በወቅቱ ማድረግ የምንችለውን ነገር ማድረግ የማንችልበት ቀን ከመጣና ኋላ ከቀረን በኋላ ነው፡፡
ዶክተር እዮብ ማሞ
1 114
ከሁሉም ነገር ተመችቷቹ አትደርሱም
ትንፋሽ አጥሯቹ ጉልበት ክዷቹ
ደክሟቹ ተዝለፍልፋቹ ነው የምትደርሱት
እንዲሁ የምንደርስበት ነገር የለም
ልማር ቢሉት ያው ነው ላስተምር ቢሉት ያው ነው
ልመንን ቢሉት ያው ነው ቢያገቡም ያው ነው
ቢነግዱም ያው ነው
ምንድነው ተራራ ያልሆነ ነገር???
የሰው ህይወቱ በዚህች ምድር ላይ
ብርቱ ሰልፍ ነው፣. . . ሰልፍ ውጊያ ነው፣
ከአጋንንት እና ከዚህ አለም አኗኗር ጋር ይዋጋል የሰው ልጅ፣
ስለዚህ ያንን አውቀን የምንኖረው ነው
አባ ገ/ኪዳን
