uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Bureau of Labor and Skills-Dire Dawa

Відкрити в Telegram

Показати більше
1 318
Підписники
+324 години
+207 днів
+15030 днів
Архів дописів
ፕሮጀክት ጽ/ቤቱ በበጀት ዓመቱ የሰጠውን ስልጠናና ምዘና የተመለከተ ሪፖርት ለባለድርሻ አካላት በማቅረብ በ2019 በጀት ዓመት ለሚሰጠው ስልጠና ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ በከተማና መሠረተ-ልማት ሚኒስቴር የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጀክት ጽ/ቤት በከተማ ፕላን፣ መሬት እና በከተማ ፋይናንስ ዘርፍ ስራዎች የባለሙያዎችን አቅም ለመገንባት እና በሙያቸው ብቁ በማድረግ ለነዋሪዎቻቸው የተሻለና ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል በ2018 በጀት ዓመት ለ8ኛ ዙር በአምስት ዩኒቨርሲቲዎች (አምቦ፣ አዳማ፣ ባህርዳር፣ ድሬዳዋ እና ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲዎች) የሰጠውን የስልጠናና ምዘና የመዝጊያ መርሃ-ግብር አካሄደ፡፡ መድረኩን የከፈቱት የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ተወካይ አቶ አበበ ፈለቀ እንደተናገሩት ስልጠናውና ምዘናው የከተማ አስተዳደር ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ፤ የማዘጋጃ ቤት አካላትን የማስፈጸም አቅም ለማሳደግ እና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ዕውን በማድረግ የህዝብን እርካታ ለማረጋገጥ ነው ብለዋል፡፡ በተከናወኑ ዘርፈ-ብዙ የሰው ኃይል ልማት ስራዎችም ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል፡፡ በንግግራቸው ማጠቃለያም የስራ ኃላፊዎች የሙያ ስልጠና ወስደው ምዘናውን ያለፉ ባለሙያዎችን በሰለጠኑበት የሙያ ዘርፍና በሚመጥናቸው ቦታ በመመደብ ዕውቀታቸውን ለህዝብ አገልግሎት እንዲያውሉ ጠንካራ የአሠራር ስርዓት በመዘርጋት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በመድረኩ በ2018 በጀት ዓመት የተካሄደውን ስልጠናና ምዘና በማስመልከት የተዘጋጀውን ሪፖርት አቶ መቅሱድ ኸይሩ፣ የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ የአቅም ግንባታና ኮሙዩኒኬሽን አሀድ አስተባባሪ አቅርበዋል። ከደረጃ ሁለት እስከ ደረጃ አምስት ባሉ የሙያ ደረጃዎች በአምስት ቁልፍ ስትሪሞች ማለትም (Cadastral Surveying, Cadastral Registry, Urban Planning, Real Property Valuation እና Urban Finance)ን የተመለከቱ ርዕሰ-ጉዳዮች የስልጠናው አካል እንደነበሩ ገልጸው የተፈጠረው የዕውቀት ሽግግር የሰው ኃይል ልማቱን ዕውን ለማድረግና የሚጠበቀውን ውጤት ለማምጣት ያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመድረኩ ላይ የፌዴራልና የክልል የስራ ኃላፊዎችና የዩኒቨርሲቲዎች የስራ አመራሮች እንዲሁም የስልጠናና ምዘና ተሳታፊዎች ተገኝተዋል። በቀረበው ሪፖርት መነሻነት በ2019 በጀት ዓመት ለሚሰጠው ስልጠና ትኩረት ሊያገኙ ይገባቸዋል በተባሉ ጉዳዮች ላይ የጋራ ውይይት ተደርጓል ቀጣይ አቅጣጫዎችም ፡፡ የስልጠናና ምዘና ስራው ውጤታማ እንዲሆን ላደረጉ ተቋማትም የምስጋና እና የዕውቅና የምስክር ወረቀት ተበርክቷል፡፡ አዳማ፤ መስከረም 7/2019 ዓ.ም፤ (ከመልሚ)

photo content
+5

photo content
+6

photo content
+6

በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ኮሌጁ የሚጠበቅበትን ውጤት እንዲያመጣ የኢንዱስትሪዎችና የባለድርሻ አካላት የጋራ ስራ ያስፈልጋል ተባለ፡፡ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የEASTRIP ፕሮጀክት ያለፈውን አመት የእቅድ አፈጻጸም እንዲሁም የ2019 በጀት አመት እቅድ ለኢንዱስትሪ ቴክንካል አማካሪ ቦርድ በዛሬው እለት አቀረበ፡፡ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ላይ ከተማችን ብሎም ሃገራችን የምትፈልገውን ለውጥ ለማስመዝገብ በዚህ ረገድ ኮሌጁ የሚጠበቅበትን ውጤት ለማምጣት ኮሌጁ ከሚሰራው ስራ ባልተናነሰ መልኩ ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በጋራ ሊሰሩ ይገባል ያሉት በመርሃ ግብሩ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ሰለሃዲን አብዱልሃሚድ ሲሆኑ ከኢንዱስትሪዎችና ከተለያዩ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጋር እየተሰሩ ያሉ ዘርፈ ብዙ ስራዎች በዘንድሮው በጀት አመትም ተጠናክረው የሚሰሩ ሲሆን የታቀዱ እቅዶችም ተግባራዊ ተደርገው ሁለንተናዊ ለውጥ እንዲመጣ ኮሌጁ ቁርጠኛ ነው ብለዋል፡፡ የኮሌጁ ዲን አያይዘውም ኮሌጁን በICT የበለጸገ ለማድረግ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ ነው በዚህም መሰረት ኮሌጁ ዘመናዊ ከማድረግ በዘለለ ከተማችን ብሎም ሃገራችን በዘርፉ የታቀደውን እቅድ ከግብ ለማድረስ በትጋት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ የተሳተፉ የኢንዱስትሪ ቴክንካል አማካሪ ቦርድ አባላት ኮሌጁ በደረሰበት ለውጥ እጅግ እንደረኩና በከተማ አስተዳደሩ እምነት የሚጣልበት ትልቅ ተቋም እንደመሆኑ መጠን ለኢንዱስትሪዎች እየሰጠ ያለው አገልግሎት በተለይ ተተኪ መለዋወጫ ከማምረትና ኢንዱስትሪውን የሚያንቀሳቅሱ ባለሙያዎችን ከማፍራት አንጻር እየሰራ ያለው ስራ እጅግ የሚበረታታና ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ነው ብለዋል፡፡ለዚህ ውጤት ደግሞ በኮሌጁ እየተተገበረ የሚገኘው የEASTRIP ፕሮጀክት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል ብለዋል፡፡ በመርሃ ግብሩ ላይ የድሬደዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ ኮሌጁ ፕሮጀክቶች የ12 ወር አፈጻጸም የተገመገመ ሲሆን የ2019 በጀት አመት እቅድም ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል በመጨረሻም በEASTRIP ፕሮጀክት አማካኝነት እየተገነባ የሚገኘውን የልህቀት ማዕከል እንዲሁም የICT ማእከል ህንፃ ግንባታ ጉብኝት ተደርጓል። ከተለያዩ ኢንዱስትሪዎችና ባለድርሻ አካላቶች የተውጣጣው አማካሪ ቦርድ በየሩብ አመቱ እየተገናኘ በቴክኒካል ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር ለኮሌጁ ገንቢ ሀሳቦች እንደሚያፈልቅ ይታወቃል፡፡ የኮሌጁ ኮምኒኬሽን መስከረም 8/2019 ድሬዳዋ ለኮሌጁ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት College website፡ https://ddptc.edu.et/ College telegram: https://t.me/diredawapolytechniccollege You tube: Dire Dawa Polytechnic College(DDPTC) Facebook: https://web.facebook.com/Dire Dawa Polytechnic College Regional Flagship TVET Institute TikTok: tiktok.com/@diredawapolytechnicollege

በIOM ዋና ዳይሬክተር የተመራው ልዑክ በድሬዳዋ የልማትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራትን ጎበኘ የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ዋና ዳይሬክተር ሉካስ ጌሄርክ የተመራው ልዑክ ቡድን በድሬዳዋ አስተዳደር የተከናወኑ የልማት፣ የሪፎርም፣ የዜግነትና ኢሚግሬሽን አገልግሎት እንዲሁም የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራትን ተዘዋውሮ ጎበኘ። ልዑኩ ወደ ድሬዳዋ አለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርስ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ከድር አሊ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው፣ የተባበሩት መንግሥታት ቢሮ አመራሮች እና የአስተዳደሩ የዘርፉ ኃላፊዎች በጋራ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። በጉብኝቱ ወቅት ልዑኩ የድሬ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል እንዲሁም በወረዳ 02 በሥራ ዕድል ፈጠራ የተከናወኑ ተግባራትን ተዘዋውሮ በመመልከት የተቋማትን ተግባራዊ ሥራ ተመልክቷል። በዚህ አጋጣሚ የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው ቢሮው በተመላሽ ዜጎች ዙሪያ እያከናወነ ያለውን ተግባር ለልዑኩ አብራርተዋል። የቢሮ ኃላፊው እንደገለጹት፣ በቅርብ ዓመታት መንግሥት ከውጭ ሀገራት ለሚመለሱ ዜጎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ከሚመለሱበት ሀገር ጀምሮ የተቀናጀ የድጋፍና የዳግም ማቋቋሚያ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል። ቢሮው ለተመላሽ ዜጎች ከሚያቀርባቸው ድጋፎች መካከል፦ ምዝገባ፣ የክህሎት ሥልጠና፣ በንግድና በፈጠራ ሥራዎች ዙሪያ ሥልጠና፣ የንግድ ዕቅድ ዝግጅት ድጋፍ፣ የብድርና የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲሁም ቀጣይነት ያለው ድጋፍና ክትትል ይገኙበታል። በተጨማሪም የተመላሽ ስደተኞችን ዳግም ማቋቋም ለማጠናከር ከIOM እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሥራት አስፈላጊ መሆኑ ተጠቁሟል። በተለይም ደህንነቱ የተጠበቀና ተደራሽ የውጭ ሀገር የሥራ ዕድል ለማስፋት የተሻሻሉ የትብብር ማዕቀፎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተገልጿል። የIOM ልዑክ ጉብኝት የድሬዳዋ አስተዳደር በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በተመላሽ ዜጎች ዳግም ማቋቋም፣ በክህሎት ልማትና በተቋማት ትብብር ዙሪያ እያከናወነ ያለውን ተግባር በተግባር ለማየትና ቀጣይ የትብብር አቅጣጫዎችን ለማጠናከር ያስቻለ መድረክ ሆኗል። መስከረም 8/2019 ዓ.ም | ድሬዳዋ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት

photo content
+9

የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ሴት ሠራተኞች ለአዲስ አመት ያሰባሰቡትን ጥሬ ገንዘብ እና የተለያዩ አልባሳት ለአሰገደች የአረጋውያን መጦሪያ ማዕከል በአካል በመገኘት ድጋፍ አደረጉ፤ ለዚህም ድጋፍ በማዕከሉ የተገኙት ሠራተኞች የማዕከሉን ሁኔታ የጎበኙ ሲሆን ማዕከሉ እየሰጠ የሚገኘውን አገልግሎት አድንቀው ከተደረገው ድጋፍ በተጨማሪ ቀጣይነት ባለው መልኩ የተለያዩ የገንዘብና የአይነት ድጋፎችን እንደሚያደርጉ የቢሮው ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ቃል ገብተዋል፡፡ አሰገደች የአረጋውያን መጦሪያ በድሬዳዋ  ከተማ በ1980 ዎቹ የተቋቋመ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው። ድርጅቱ የተጠነሰሰው በወ/ሮ አሰገደች መኖሪያ ቤት ሲሆን ይህ ጅማሮ የመንግስት እና የበጎ አድራጊ ግለሰቦች ጥረት ታክሎበት አሁን ያለበትን የአገልግሎት ማዕከል መመስረት ችሏል፤ በአሁኑ ወቅት ማዕከሉ ውስጥ ለሚገኙ አዛውንቶች የምግብ፣ የመጠልያ፣ የጤና፣ እና የንፅህና ግልጋሎቶች ይሰጣል። ከዚህ በተጨማሪም ከመጠለያ ውጪ ላሉ በርካታ አዛውንቶች የገንዘብ ድጋፍ ያደረጋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት መስከረም 8/2019 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+2

የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የ2019 በጀት አመት የእቅድ ፊርማ ስነ-ስርዓት አካሄደ:: #EIPC መስከረም 7. 2019 ዓ.ም ድሬዳዋ በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የሚገኙ የዋና ስራ ሂደት ዳይሬክቶሬቶች የ2019 ዓ.ም መሪ ዕቅዶቻቸውን ለኮሌጁ ማኔጅመንት አቅርበው ከኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ ጋር የፊርማ ስነ-ስርዓት አከናውነዋል:: ከፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ በተጨማሪ የዋና ስራ ሂደት ዳይሬክቶሬቶች በበጀት አመቱ ያቀዷቸውን ዕቅዶች በሚፈለገው ደረጃ እንዲፈፅሙ የሚያስችልና ቅንጅታዊ አሰራርን በመፍጠር ዙሪያ የኮሌጁ ማኔጅመንት አባላቱ በተገኙበት ውይይቶች ተድርገው የቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ ተችሏል። ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡- በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001 በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1 በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/

ከተረጂነት ወደ አምራችነት—የሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም እንዲመራ የቅድመ ዝግጅት ሥራ አፈጻጸም ተገመገመ በድሬዳዋ አስተዳደር “ከተረጂነት ወደ አምራችነት” ኢኒሼቲቭ የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለማከናወን እየተካሄደ የሚገኘው የቅድመ ዝግጅት ሥራ ከሥራ ዕድል ፈጠራ አንጻር አፈጻጸሙን በመገምገም ቀጣይ የስራ አቅጣጫ በቴክኒካል ኮሚቴ ደረጃ ተካሄደ። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የሥራ ዕድል ፈጠራና የአንድ ማዕከል ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ያዘጋጀው ይህ የግምገማ መድረክ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች በተቀናጀ አሠራር ለመደገፍ የተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በመገምገም፣ ቀጣይ የሥራ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ ነው። በመድረኩ የተገለጸው እንደሆነ፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራ በመንግሥት ተቋማት ብቻ የሚከናወን ሳይሆን የአምራች ኢንዱስትሪዎችን፣ የንግዱ ማኅበረሰብን፣ ባለሀብቶችን፣ የመንግሥት ሠራተኞችንና የነዋሪውን አቅምና ሀብት በማስተባበር በራስ አቅም ሊመራ ይገባል። ይህም ድጋፍ የሚሹ ዜጎችን በዘላቂነት ለመደገፍና በተቻለ መጠን ከተረጂነት ወደ አምራችነት ለማሸጋገር የሁሉንም ተሳትፎ የሚጠይቅ ነው። የመድረኩ ተሳታፊዎችም በቅድመ ዝግጅት ሥራው የታዩ ጠንካራ ጎኖችንና ያሉ ክፍተቶችን በመለየት፣ ቀጣይ ተግባራት በጊዜ፣ በጥራትና በተጠያቂነት እንዲፈጸሙ በትብብር ለመሥራት አቅጣጫ ተቀምጧል። በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ሰኢድ አሊ የተላለፈው መልዕክትም የሰብዓዊ ድጋፍ ሥራው ትኩረት የሚሻ መሆኑን አመራሩ በግልጽ በመረዳት በቁርጠኝነት ሊረባረብበት እንደሚገባ አመልክቷል። በተጨማሪም ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት መከናወን የሚገባቸውን ተግባራት በጋራ በመለየትና በተናበበ አሠራር በመፈጸም የተጠቃሚዎችን የሕይወት አቅም ማሳደግ እንደሚገባ አቅጣጫ ተሰጥቷል። “ድጋፍ ለዛሬ፤ አቅም ለነገ፤ ምርታማነት ለዘላቂ ሕይወት!” መስከረም 07/2019 ዓ.ም | ድሬዳዋ የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት

photo content
+4

በድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ከአስተዳደሩ የልማት ዘርፍ ተቋማት ጋር የ2019 በጀት ዓመት የዘርፉን ዕቅድ በተቀናጀና በተጠያቂነት ለመፈጸም የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል። የጋራ ስምምነቱ ዋና ዓላማ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንን ማጠናከር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማፋጠን፣ የካይዘን ትግበራን ማሻሻል፣ አገር በቀል ዕውቀትና ክህሎትን ማልማት እንዲሁም ከተለያዩ የልማት ዘርፎች በመነሳት የዕሴት ሰንሰለት ሰነዶችን በጋራ ማዘጋጀት ነው። በተጨማሪም የቴክኖሎጂ፣ የክህሎት እና የተግባራዊ ጥናትና ምርምር ውድድሮችን በማዘጋጀት ፈጠራን፣ የተግባር ክህሎትንና ችግር ፈቺ የምርምር አቅምን ለማጎልበት ትኩረት ተሰጥቷል። ይህም የሥልጠና ተቋማትን ከኢንተርፕራይዞች፣ ከምርምርና ከቴክኖሎጂ ተቋማት ጋር በማስተሳሰር የሚፈጠረውን የእውቀት፣ የክህሎትና የቴክኖሎጂ ትስስር ለማጠናከር ያግዛል። በስምምነቱ የተሳተፉት የግልና የመንግሥት ኮሌጆች፣ የኢንተርፕራይዝ ልማት ዳይሬክቶሬት፣ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች ልማት ኤጀንሲ፣ የድሬዳዋ ሙያ ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ፣ የድሬ ብድርና ቁጠባ ተቋም፣ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ፣ የድሬዳዋ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኤጀንሲ፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ እንዲሁም የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እንደተናገሩት የስምምነት ሰነዱ በ2019 በጀት ዓመት የዘርፉ ዕቅዶች በአንድ ተቋም ጥረት ብቻ ሳይሆን በተቋማት የተቀናጀ አሠራር፣ በጋራ ተጠያቂነትና በውጤት ተኮር ትብብር እንዲፈጸሙ የሚያደርግ መሠረት ይፈጥራል ብለዋል። ከእውቀት ወደ ቴክኖሎጂ፣ ከክህሎት ወደ ምርታማነት፣ ከትብብር ወደ ውጤት! የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት | መስከረም 7/2019 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+9

ለውጥን በውጤት ለማስመዝገብ፦ የሥራና ክህሎት ቢሮ የ2019 በጀት ዓመት ዝግጅት ምዕራፍ አፈጻጸም ሂደትን ገመገመ የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት በዝግጅት ምዕራፍ እየተከናወኑ ያሉ ዋና ዋና ሥራዎችን፣ የሪፎርም ሥራዎችን አፈጻጸም እና ለቀጣይ የሥራ ዘመን የተያዙ አቅጣጫዎችን ገመገመ። የግምገማው መድረክ በዝግጅት ምዕራፉ የተከናወኑ ተግባራትን በውጤት፣ በአፈጻጸምና በተጠያቂነት ለመመዘን ያለመ ሲሆን፣ የተገኙ ስኬቶችን ማጠናከር፣ የታዩ ክፍተቶችን መለየት እና ለቀጣይ ምዕራፍ የማሻሻያ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ ላይ ትኩረት አድርጓል። በተለይም የሪፎርም ሥራዎች አፈጻጸም በመገምገም፣ ተቋማዊ አሠራርን ማሻሻል፣ የሥራ ቅልጥፍናን ማሳደግ፣ የአገልግሎት ጥራትን ማሻሻልና የተገልጋይ እርካታን ማጠናከር የሚያስችሉ ቀጣይ እርምጃዎች ተለይተዋል። በቢሮው የእቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር አቶ ይታገስ ካሳሁን በግምገማው ላይ እንደገለጹት፣ ግምገማ የሪፖርት ማቅረቢያ ሂደት ብቻ ሳይሆን የተማሩበትን በመውሰድ ቀጣዩን ውጤት የሚያሻሽሉበት የሥራ መሣሪያ መሆን አለበት። እያንዳንዱ ክፍልና ተቋም በተሰጠው ኃላፊነት ላይ ግልጽ ውጤት ማስመዝገብና ለተገልጋዩ የሚታይ ለውጥ ማምጣት እንዳለበት አስገንዝበዋል። በመጨረሻም በግምገማው የተለዩ ጉዳዮችን ወደ ተግባር በመቀየር፣ የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዶችን በተቀናጀ አሠራር ለማስፈጸም፣ የሪፎርም ሥራዎችን በውጤት ለማስደገፍ እና ተቋሙ የሚሰጠውን የሥራና ክህሎት አገልግሎት በጥራትና በቅልጥፍና ለማጠናከር የሚያስችሉ የሥራ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል። የሥራና ክህሎት ቢሮ ህዝብ ግንኙነት | መስከረም 6/2019 ዓ.ም ድሬዳዋ

photo content
+3

የደብረ ማርቆስ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮችን ያቀፈ ልዑካን ቡድን በኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ የስራ ልምድ ልውውጥ ጉብኝት አካሄደ፡፡ #EIPC መስከረም 5.2019 ዓ.ም ድሬዳዋ የደብረ ማርቆስ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ አመራሮችን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ሀላፊዎችን የያዘ የልዑካን ቡድን በኮሌጃችን ያለውን የስራ እንቅስቃሴ ለመመልከት እንዲሁም በEASE ፕሮጀክት ትግበራ ያለውን ተሞክሮ ለመውሰድ የሚያስችላቸውን የስራ ልምድ ልውውጥ በኮልጁ አካሂደዋል:: ልዑካን ቡድኑ በኮሌጃችን በነበረው የልምድ ልውውጥ መርሃ-ግብር ወቅትም የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ የEASE ፕሮጀክት ትግበራን ጨምሮ ጠቅላላ በተቋም የተመዘገቡ የአፈፃፀም ውጤቶችን በዝርዝር የተመለከቱ ሲሆን በተጨማሪም ኮሌጁ ከምስረታው አንስቶ አሁን እስከደረሰበት ደረጃ የነበረውን ሂደት እና ያከናወናቸውን ዘርፈ ብዙ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን በኮሌጁ ዲን አቶ ታደለ አሰፋ እንዲሁ በEASE ፕሮጀክት አስተባባሪ ኢንጂነር ፋሲል ማዘንጊያ አማካኝነት ሰፋ ያለ ገለፃና ማብራሪያም ተደርጎላቸዋል:: ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ በተደረገላቸው አቀባበልና በተመለከቱት የኮሌጁ እንቅስቃሴ መነሻ በማድረግ የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊቴክኒክ ኮሌጁ እያከናወናቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የስራ እንቅስቃሴዎች አስደናቂ መሆናቸውን ጠቅሰው በዚህም በቀጣይ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ከኮሌጁ ጋር አብሮ የመስራት ፍላጎት እንዳሳደረባቸውም ገልፀዋል:: በተጨማሪም ልኡካን ቡድኑ በኮሌጁ የሚገኙ የተለያዩ የስልጠና ዎርክ ሾፖችን ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን በነበራቸው የልምምድ ልውውጥ መርሃ-ግብርም የተሳካ ቆይታን በኮሌጃችን ማድረጋቸውን በመግለፅ ለተደረገላቸው አቀባበልና የላቀ ትብብር የምስጋና ሰርተፊኬት ለኮሌጁ አበርክተዋል:: ተጨማሪ መረጃዎችን በሚከተሉት አማራጮች ያግኙ፡- በፌስቡክ -https://www.facebook.com/share/19wDiZAD7x/?mibextid=wwXIfr በቴሌግራም -https://t.me/EIPC2001 በቲክቶክ -https://www.tiktok.com/@ethioitaly2001?_t=ZM-90MxIrBN8qe&_r=1 በዌብሳይት - https://ethioitalypolytechniccollege.com/