uk
Feedback
FM መረጃ

FM መረጃ

Відкрити в Telegram

እንኳን ወደ FM መረጃ በደህና መጡ በቻናላችን 🌐 ፈጣን ሀገራዊ መረጃዎች 📺 🌐 ዓለም ዓቀፍ መረጃዎች 📢 🌐 ወቅታዊ ጉዳዮች ሁሉንም በአንድ ታገኛላችሁ 📣

Показати більше
8 537
Підписники
+9524 години
+1587 днів
-2530 днів

Триває завантаження даних...

Хмара тегів
Немає даних
Виникли проблеми? Будь ласка, оновіть сторінку або зверніться до нашого support-менеджера.
Вхідні та вихідні згадування
---
---
---
---
---
---
Залучення підписників
жовт '26
жовтень '26
+214
в 1 каналах
вересень '26
+23
в 2 каналах
Get PRO
серпень '26
+357
в 4 каналах
Get PRO
липень '26
+525
в 0 каналах
Get PRO
червень '26
+274
в 0 каналах
Get PRO
травень '26
+234
в 0 каналах
Get PRO
квітень '26
+344
в 0 каналах
Get PRO
березень '26
+544
в 1 каналах
Get PRO
лютий '26
+595
в 0 каналах
Get PRO
січень '26
+288
в 1 каналах
Get PRO
грудень '25
+10
в 0 каналах
Get PRO
листопад '25
+13
в 1 каналах
Get PRO
жовтень '25
+31
в 1 каналах
Get PRO
вересень '25
+501
в 7 каналах
Get PRO
серпень '25
+917
в 4 каналах
Get PRO
липень '25
+1 583
в 2 каналах
Get PRO
червень '25
+1 709
в 1 каналах
Get PRO
травень '25
+356
в 5 каналах
Get PRO
квітень '25
+308
в 3 каналах
Get PRO
березень '25
+266
в 0 каналах
Get PRO
лютий '25
+295
в 0 каналах
Get PRO
січень '25
+106
в 0 каналах
Get PRO
грудень '24
+24
в 1 каналах
Get PRO
листопад '24
+21
в 2 каналах
Get PRO
жовтень '24
+16
в 2 каналах
Get PRO
вересень '24
+1 773
в 138 каналах
Get PRO
серпень '24
+1 249
в 216 каналах
Get PRO
липень '24
+1 963
в 0 каналах
Get PRO
червень '24
+1 293
в 66 каналах
Get PRO
травень '24
+1 615
в 49 каналах
Get PRO
квітень '24
+1 041
в 7 каналах
Get PRO
березень '24
+710
в 21 каналах
Get PRO
лютий '24
+743
в 32 каналах
Дата
Залучення підписників
Згадування
Канали
03 жовтня+4
02 жовтня+95
01 жовтня+115
Дописи каналу
መከላከያ ሰራዊት እና የትግራይ ሰላም ሀይል ወደ ትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ ገብተዋል።

2
📸 ትራምፕ እና ዢ ጂንፒንግ፣ ዢ አሜሪካ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት በኦቫል ቢሮ ውስጥ።
📸 ትራምፕ እና ዢ ጂንፒንግ፣ ዢ አሜሪካ ባደረጉት ጉብኝት ወቅት በኦቫል ቢሮ ውስጥ።
165
3
🚨 በአላማጣ ከተማና አካባቢው የተጣለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅና ጥብቅ እገዳዎች በአላማጣ ከተማ እና አካባቢው አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን፣ ኮማንድ ፖስቱ ከዛሬ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ
🚨 በአላማጣ ከተማና አካባቢው የተጣለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅና ጥብቅ እገዳዎች በአላማጣ ከተማ እና አካባቢው አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን፣ ኮማንድ ፖስቱ ከዛሬ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ የሚተገበሩ የሰዓት ገደቦችን፣ የእጅ መስጠት ጥሪን እና ጥብቅ እገዳዎችን ጥሏል። በእገዳው መሠረት ማንኛውም ተሽከርካሪ መንቀሳቀስ የሚችለው እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ብቻ ሲሆን፣ ሆቴሎች፣ መጠጥ ቤቶችና የመዝናኛ ቦታዎች አገልግሎት መስጠት የሚችሉት እስከ ምሽቱ 2:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው። በተጨማሪም ማንኛውም ሰው ከምሽቱ 3:00 ሰዓት በኋላ መንቀሳቀስ ሙሉ በሙሉ የተከለከለ ሲሆን፣ ከፌዴራል ፀጥታ ኃይሎች ውጪ በከተማው ውስጥ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ ተከልክሏል። ኮማንድ ፖስቱ አክሎም፣ በገጠርም ሆነ በከተማ የሚገኙ የግል የጦር መሳሪያ ያላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች በአቅራቢያቸው በሚገኝ የፖሊስ ጣቢያ በአስቸኳይ እንዲያስመዘግቡ አዟል። በሌላ በኩል፣ የግለሰብ፣ የሕዝብና የመንግሥት ንብረት ከመዝረፍ ሁሉም አካል እንዲቆጠብ ያስጠነቀቀው ኮማንድ ፖስቱ፣ ይህንን ድርጊት ሲፈጽም በተገኘ ማንኛውም አካል ላይ የማያወላዳ ጥብቅ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ አስታውቋል። በመጨረሻም፣ የጽምዶ ፀረ-ሰላም ኃይሎች (የህወሓት ሰራዊት እና የፋኖ ታጣቂ አባላት) በአምስት (5) ቀናት ውስጥ ከተደበቁበት እየወጡ ለፌዴራል ፖሊስ እጃቸውን እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቧል። ይህ የተጣለው ገደብና የቀረበው ጥሪ በአካባቢው የተከሰተውን የፀጥታ መበላሸት ለማስተካከልና ሰላምን ለማስፈን የታለመ መሆኑ ተገልጿል።
309
4
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ከግብፅ፣ ኤርትራ እና ሱዳን መሪዎች ጋር በካይሮ ሊመክሩ ነው የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ከግብፅ፣ ከኤርትራ እና ከሱዳን መሪዎች ጋር በአካል ለመገናኘት ዛሬ ወደ ካ+1
የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ከግብፅ፣ ኤርትራ እና ሱዳን መሪዎች ጋር በካይሮ ሊመክሩ ነው የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ከግብፅ፣ ከኤርትራ እና ከሱዳን መሪዎች ጋር በአካል ለመገናኘት ዛሬ ወደ ካይሮ ያመራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ቶሮንቶ የሚገኘው «ሂራን ኦንላይን»ን ጨምሮ ልዩ ልዩ የሶማሊያ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ። 📌  ምንም እንኳን የተያዘው አጀንዳ ይፋ ባይደረግም፣ ጉብኝቱ በአፍሪካ ቀንድ ውጥረት በነገሰበት ወቅት የሚካሄድ ሲሆን፤ ዛሬ ዓርብ መስከረም 22 እና ነገ ቅዳሜ መስከረም 23 ቀን 2017 ዓ.ም በግብፅ የባሕር ዳርቻ አላሜይን ከተማ በሚካሄደው የአፍሪካ ሕብረት የሦስት ቀናት ጉባኤ ጎን ለጎን እንደሚሆን ተገልጿል። 📌 ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ በያዝነው ሳምንት ማክሰኞ እና ረቡዕ በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ይፋዊ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወቃል። 📌 ሞሃሙድ አዲስ አበባን ከጎበኙ በኋላ፣ ኢትዮጵያ በሶማሊያ የሚገኙትን የሰላም አስከባሪ ኃይሎቿን ለማስወጣት ማቀዷን ብሉምበርግን ዋቢ በማድረግ ዘገባዎች የወጡ ቢሆንም፣ የሶማሊያ መንግሥት ባለሥልጣናት ግን ዘገባውን አስተብለዋል። ከኢትዮጵያ በኩል ጦሯን በማስወጣት ዙሪያ የደረሳቸው ምንም ዓይነት ይፋዊ መረጃ እንደሌለም አስታውቀዋል ሲል ዶቼቨለ ዘግቧል።
308
5
መቀሌ -ኩሓ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከመቀሌ ከተማ በ11 ኪሎ ሜትር (የ21 ደቂቃ ያህል የመኪና መንገድ) ርቀት ላይ የሚገኙትን ኩሓ ከተማን እና የአሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርትን በቁጥጥር
መቀሌ -ኩሓ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከመቀሌ ከተማ በ11 ኪሎ ሜትር (የ21 ደቂቃ ያህል የመኪና መንገድ) ርቀት ላይ የሚገኙትን ኩሓ ከተማን እና የአሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርትን በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተሰምቷል። በጎግል ማፑ እንደሚታየው ኩሓ ከተማ እና የአሉላ አባ ነጋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ጎን ለጎንና በጣም ቅርብ ለቅርብ የሚገኙ ሲሆን፤ የመከላከያ ሰራዊቱ የአሉላ አባ ነጋ ኤርፖርትን ጨምሮ አጠቃላይ አካባቢውን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ነው የተሰማው።
280
6
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ወደ ቀደመው መደበኛ ሁኔታ ሲመለስ፣ የኢትዮጵያ መንግስት በአሁኑ ወቅት እያደረገ ያለውን አጠቃላይ የነዳጅ ድጎማ እንዲያነሳ መከረ። በምትኩ መንግስት የነዳጅ ድጎማውን ሀብታም ደሃ ሳይል ለሁሉም ከማዳረስ ይልቅ፣ ድጋፍ ለሚገባቸው ዝቅተኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ እንዲያደርግ ተቋሙ አሳስቧል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር የዘንድሮውን የነዳጅ ድጎማ ጣሪያ በ20 ቢሊዮን ብር የገደበ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ያለበትን ከፍተኛ እዳ ለማቃለል እና የፋይናንስ አቅሙን ለማሳደግ የ286 ቢሊዮን ብር የካፒታል ማሳደጊያ በጀት አጽድቋል። ከዓለም ባንክ (World Bank) - የተመደበው መጠን - 170 ቢሊዮን ብር ከፌደራል መንግስት በጀት - የተመደበው መጠን - 116 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ ድምር = 286 ቢሊዮን ብር ከገንዘብ ሚኒስቴር የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ መንግስት የነዳጅ ዋጋን በገበያ እንዲወሰን በማድረግ፣ ድጎማውን ለህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች እና ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ በዲጂታል የክፍያ ስርዓት ለማድረግ አቅዷል። የዚህ ሽግግር አካል የሆነው የሴፍቲኔት (PSNP) ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ቁጥር በገጠር ከ8 ሚሊዮን ወደ 9.5 ሚሊዮን ከፍ የሚል ሲሆን፣ ለድንገተኛ አደጋ ምላሽ የሚሆን ተጨማሪ 4 ቢሊዮን ብርም ተመድቧል። በአንጻሩ የአውሮፕላን (Jet-fuel) ነዳጅ ድጎማ ሙሉ በሙሉ ተነስቷል። ይህ አጠቃላይ ድጎማን የማንሳት እቅድ በመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት ምክንያት የነዳጅ ዋጋ በማሻቀቡ ለጊዜው ዘግይቶ የነበረ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ኃላፊዎች አስረድተዋል። የኢንቨስትመንት ባለሙያ እና የፕራግማ ካፒታል (መስራች የሆኑት መርዕድ ፍቅረዮሐንስ፣ አሁን ያለው አጠቃላይ የነዳጅ ድጎማ መንግስት በግምጃ ቤት ሰነድ ሚወስደው ብድር እየተሸፈነ መሆኑን በመግለጽ፣ መንግስት የነዳጅ ዋጋን ርካሽ ለማድረግ ብድር ውስጥ መዘፈቁ በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል ብለዋል። ባለሙያው አክለውም መንግስት ለድጎማ የሚያወጣውን ወደ 150 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ገንዘብ ዝቅተኛ ተከፋይ ለሆኑ 2.2 ሚሊዮን የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ ማሻሻያ (ከ15,000 እስከ 20,000 ብር ለማድረስ) እና ተጨማሪ ከ5,000 እስከ 6,000 ሜጋ ዋት የኃይል ማመንጫዎችን ለመገንባት ቢያውለው የተሻለ የኢኮኖሚ አቅም እንደሚፈጥር መክረዋል። "መንግስት ኃይል ማመንጫ ግድብ ሊገነባበት የሚችልበትን ገንዘብ ነው ለነዳጅ ድጎማ እያወጣ ያለው" ያሉት ባለሙያው፣ የህብረተሰቡን የመግዛት አቅም ማሳደግ እንጂ ሁሉንም ሸማች በእኩል መደጎም ተገቢ አለመሆኑን ሞግተዋል። @FM_mereja @FM_mereja
273
7
Немає тексту...
237
8
አምነስቲ አዲስ ግጭት እየተስፋፋ በመሆኑ የአፍሪካ ኅብረት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ጠየቀ ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ አርብ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም.
አምነስቲ አዲስ ግጭት እየተስፋፋ በመሆኑ የአፍሪካ ኅብረት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ጠየቀ ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ዛሬ አርብ መስከረም 22 ቀን 2019 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፤ በኢትዮጵያ ያገረሸው ግጭት እየተስፋፋ በመሆኑ የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ እንዲጠራ ጥሪ አቀረበ። የድርጅቱ የምስራቅ እና ደቡባዊ አፍሪካ ዳይሬክተር ቲገረ ቻጉታህ ኅብረቱ የጅምላ ጭፍጨፋ እስኪከሰት መጠበቅ እንደሌለበት አሳስበው፣ የፕሪቶሪያው ስምምነት በተግባር መፍረሱን ገልጸዋል። አምነስቲ በትግራይ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች በሚካሄደው ውጊያ በከባድ መሣሪያና በአየር ጥቃቶች የሰላማዊ ሰዎች ንብረት መውደሙን፣ እንዲሁም የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን የሚጠቁሙ ተአማኒ ሪፖርቶች እንደደረሱት አስታውቋል።
271
9
የታጠቁ ሰዎች ጄኔራል ታደሰን እና ሌሎች ታሳሪዎችን ወደ ኤርትራ ለመውሰድ በማሰብ ኤችዜድ ሆቴልን ከቦታል ተብሏል። ታሳሪዎቹ “አንሄድም” በማለት ለመሄድ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ተሰምቷል። 📍 ኤችዜድ ሆ
የታጠቁ ሰዎች ጄኔራል ታደሰን እና ሌሎች ታሳሪዎችን ወደ ኤርትራ ለመውሰድ በማሰብ ኤችዜድ ሆቴልን ከቦታል ተብሏል። ታሳሪዎቹ “አንሄድም” በማለት ለመሄድ ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ተሰምቷል። 📍 ኤችዜድ ሆቴል — ዳዊት ከበደ
308
10
የትራምፕ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ትኩረት እንዲሰጥ ተጠየቀ በኢትዮጵያ ዳግም እያገረሸ ባለው የጸጥታ ስጋት ዙሪያ ያሳሰባቸው ስድስት የአሜሪካ ሴናተሮች፣ የትራምፕ አስተዳደር እና የውጭ ጉዳ
የትራምፕ አስተዳደር  ለኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ትኩረት እንዲሰጥ ተጠየቀ በኢትዮጵያ ዳግም እያገረሸ ባለው የጸጥታ ስጋት ዙሪያ ያሳሰባቸው ስድስት የአሜሪካ ሴናተሮች፣ የትራምፕ አስተዳደር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ በጉዳዩ ላይ ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎ በአስቸኳይ እንዲያጠናክሩ ጠየቁ። ጄን ሻሂን፣ ኮሪ ቡከር፣ ክሪስ ኩንስ፣ ጄፍ መርክሌይ፣ ክሪስ ቫን ሆለን እና ቲም ኬይን የተባሉት የዴሞክራትና ሪፐብሊካን የሁለቱ ፓርቲዎች ሴናተሮች በጋራ ባወጡት መግለጫ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ፣ በትግራይ፣ በአማራ፣ በኦሮሚያና በሌሎች አካባቢዎች ያለው አለመረጋጋት ወደ ሰፊ የእርስ በእርስ ጦርነት እንዳያመራ ስጋታቸውን ገልጸዋል። ሴናተሮቹ የኢትዮጵያ መንግሥት፣ የትግራይ አመራሮችና ሌሎች የታጠቁ ኃይሎች በውይይትና በዲፕሎማሲ የንጹሐን ዜጎችን ደኅንነት እንዲጠብቁና ታሪካዊቷን የላሊበላ ሥፍራ እንዲታደጉ ጥሪ አቅርበዋል።
329
11
ሰበር መረጃ❗️ የዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የትላንቱ መግለጫ የተሰጠው ከአስመራ መሆኑ ተረጋገጠ! ትላንት የተላለፈውና ብዙዎችን ያነጋገረው የዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል መግለጫ የተሰጠው ከኤርትራ
ሰበር መረጃ❗️ የዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል የትላንቱ መግለጫ የተሰጠው ከአስመራ መሆኑ ተረጋገጠ! ትላንት የተላለፈውና ብዙዎችን ያነጋገረው የዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል መግለጫ የተሰጠው ከኤርትራዋ መዲና አስመራ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል። ዶ/ር ደብረፅዮን በመግለጫቸው የትግራይን ህዝብ ፖለቲካዊ ፈተናዎች፣ የህልውና ትግል፣ እውነተኛ ሰላም እና የፍትህ ጥያቄዎች በማንሳት ህዝቡ ለደህንነቱ ደጀን ሆኖ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል። ይሁን እንጂ የትግራይን ደህንነት እና የትግል ፅናት በተመለከተ አበክረው የገለፁበት ይህ ያልተጠበቀ ንግግር የተላለፈው በቀጥታ ከአስመራ መሆኑ የፖለቲካውን ድባብ እጅግ አነጋጋሪ እና አስገራሚ አድርጎታል። @FM_mereja @FM_mereja
372
12
የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት የሕወሓት ትልቁን ወታደራዊ ስልጠና እና ሎጅስቲክስ ማዕከል የሆነውን አግቤን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አውሏል። በትግራይ ክልል ወጣ ገባ እና ምሽግ በሆነው ተምቤን
የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት የሕወሓት ትልቁን ወታደራዊ ስልጠና እና ሎጅስቲክስ ማዕከል የሆነውን አግቤን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ስር አውሏል። በትግራይ ክልል ወጣ ገባ እና ምሽግ በሆነው ተምቤን ውስጥ የሚገኘው አግቤ ከአቢ አዲ ጥቂት ማይሎች በስተደቡብ ይገኛል።
389
13
የትግራይ ፕሬዚዳንት ዶክተር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ዛሬ ማታ በሰጡት መግለጫ እንዲህ ብለዋል፦ “እስካሁን ስናካሂደው የቆየነው ጦርነት የመከላከል ነው። ከአጋሮቻችን ጋር በመሆን ውጊያውን በጋራ እየተወጣነው እንገኛለን። ሁኔታዎች እየዳበሩ ሲሄዱ ወደ ተቃራኒ ማጥቃት እና ቀጥተኛ ማጥቃት ይለወጣል።”
431
14
"አለማጣ እየዋጋን ነው" ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከረጅም ጊዜ መጥፋት በኋላ የምርጫ ቦርድ እውቅና የሌለው ህውሃት መሪ ዶ/ር ደብረጽዮን የፌደራልና የአጋር ኃይሎች «ይገባሉ እንጅ አይወጡም "
"አለማጣ እየዋጋን ነው" ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከረጅም ጊዜ መጥፋት በኋላ የምርጫ ቦርድ እውቅና የሌለው ህውሃት መሪ  ዶ/ር ደብረጽዮን የፌደራልና የአጋር ኃይሎች «ይገባሉ እንጅ አይወጡም " ሲሉ  ተናግረዋል። "ተንቀሳቃሽ የውጊያ ስልትን እየተከተልን ነው" ሲሉም ተደምጠዋል። "አለማጣ እየዋጋን ነው" ካሉ በኋላ አክለውም ፍልሚያው ከሌሎች አጋር ኃይሎች ጋር በመቀናጀት በራያ፣ አላማጣ፣ ጨርጨር፣ ወጀራትና አበርገለ ግንባሮች እየተካሄደ እንደሚገኝና የሎጂስቲክስ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጸዋል። እሳቸው ይህንን ይበሉ እንጅ መከላከያ የጠቀሳቸው አካባቢዎች ጨርሶ ማይጨውን አልፏል።የራያ አላማጣው ከተጠናቀቀ ሳምንት ሆኖታል።ከአፋር ያለው ከመቀሌ 43 ኪግ ርቀት ላይ ይገኛል።ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ከመንግስት ጋር አደራድሩኝ ማለታቸው ትናንት ተዘግቧል።
421
15
Немає тексту...
378
16
አቶ አረጋ ከበደ በክልሉ እየተካሄደ ያለው ግጭት በአስቸኮይ እንዲቆም ለፋኖ ጥሪ አቀረቡ በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው “ግጭት እና ደም መፋሰስ” “በአስቸኳይ” እንዲቆም፤ በክልሉ ታጥቀው ለሚንቀሳቀ
አቶ አረጋ ከበደ በክልሉ እየተካሄደ ያለው ግጭት በአስቸኮይ እንዲቆም ለፋኖ ጥሪ አቀረቡ በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው “ግጭት እና ደም መፋሰስ” “በአስቸኳይ” እንዲቆም፤ በክልሉ ታጥቀው ለሚንቀሳቀሱ ኃይሎች አቶ አረጋ ከበደ ጥሪ አቀረቡ። በዛሬው ዕለት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው በድጋሚ የተመረጡት አቶ አረጋ “በጫካ የሚገኙ” ላሏቸው ታጣቂዎች ባስተላለፉት መልዕክት፤  የኢትዮጵያ እና የአማራ ክልል “ህዝብ ጠላት ከሆኑ ኃይላት ጋር መተባበር በታሪክ ፊት የሚያዋርድ [ነው]” ብለዋል። አቶ አረጋ ይህን የተናገሩት፤ ዛሬ ሐሙስ መስከረም 21፤ 2019 በባህር ዳር ከተማ በተካሄደው የክልሉ ምክር ቤት መስራች ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር ነው። ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ንግግራቸው፤ በክልሉ መሳሪያ ያነሱ ታጣቂዎች “ጥያቄዎች እና ቅሬታዎች” “ዘላቂ መፍትሔ የሚያገኘው በጠረጴዛ ዙሪያ በሚደረግ ውይይት” እንደሆነ አመልክተዋል። በክልሉ ውስጥ “ያሉ ልዩነቶችን በሰላማዊ እና ፖለቲካዊ ውይይት ለመፍታት” አስተዳደራቸው የሚከተለውን መንገድም አቶ አረጋ በንግግራቸው ጠቁመዋል።
364
17
ሩሲያ በካሊኒንግራድ ላይ እገዳ በሚጥሉ የኔቶ አገራት ላይ የኒውክሌር መሣሪያ እንደምትጠቀም አስጠነቀቀች የኔቶ አባል አገራት የሩሲያ ግዛት የሆነችውን ካሊኒንግራድን ከቀሪው የአገሪቱ ክፍል ለመነጠል
ሩሲያ በካሊኒንግራድ ላይ እገዳ በሚጥሉ የኔቶ አገራት ላይ የኒውክሌር መሣሪያ እንደምትጠቀም አስጠነቀቀች የኔቶ አባል አገራት የሩሲያ ግዛት የሆነችውን ካሊኒንግራድን ከቀሪው የአገሪቱ ክፍል ለመነጠል ወይም ከበባ ለማድረግ ቢሞክሩ፣ ሞስኮ የኒውክሌር መሣሪያዎችን ጨምሮ ሙሉ የጦር አቅሟን ለመጠቀም እንደማትራራ በጥብቅ አስጠነቀቀች። በአውሮፓ የሚገኙ የሩሲያ ኤምባሲዎች እንዳሉት፣ ኔቶ በግዛቷ ላይ የአየር እና የባሕር ከበባ ለማድረግ እየተዘጋጀ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ ደርሷቸዋል። የሩሲያ ባለሥልጣናት የአውሮፓ መሪዎች ሩሲያ አውሮፓን ልታጠቃ ነው" በማለት የሚያናፍሱትን ወሬ አደገኛ ጨዋታ ሲሉ አጣጥለውታል።
318
18
Немає тексту...
315
19
ኢትዮጵያ በግብፅ የተደናቀፉ የዓባይ ወንዝ ፕሮጀክቶችን የኪሳራ መጠን የሚያጠና ኮሚቴ አቋቋመች በግብፅ አሻጥር በዓባይ ወንዝ ላይ የታገዱ የውኃ ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ ላይ ያደረሱትን ምጣኔ ሀብታዊ ኪ
ኢትዮጵያ በግብፅ የተደናቀፉ የዓባይ ወንዝ ፕሮጀክቶችን የኪሳራ መጠን የሚያጠና ኮሚቴ አቋቋመች በግብፅ አሻጥር በዓባይ ወንዝ ላይ የታገዱ የውኃ ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ ላይ ያደረሱትን ምጣኔ ሀብታዊ ኪሳራ የሚያጠና ብሔራዊ ኮሚቴ መቋቋሙን የውኃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ሃብታሙ ኢተፋ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኮሚቴው የታላቁ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በግብፅ አማካኝነት የተስተጓጎሉ ከ22 በላይ የልማት ፕሮጀክቶችን ለይቷል። የቀድሞ ሚኒስትሮችንና የሕግ ባለሙያዎችን ያካተተው ይህ ስብስብ፣ የደረሰውን የኪሳራ መጠን በማስላት ኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊ የካሳ ጥያቄ የምታቀርብበትን የሕግ መሠረት እያዘጋጀ ይገኛል።
321
20
"ሌ/ጀ ታደሰ ወረደ ለኤርትራ ተላልፈው ሊሰጡ ነው" — ጃዋር መሐመድ በመቀሌ በቁም እስር ላይ የሚገኙት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ እና ሌሎች የትግራይ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ወደ ኤርትራ ድንበ
"ሌ/ጀ ታደሰ ወረደ ለኤርትራ ተላልፈው ሊሰጡ ነው" — ጃዋር መሐመድ በመቀሌ በቁም እስር ላይ የሚገኙት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ እና ሌሎች የትግራይ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ወደ ኤርትራ ድንበር ከተማ አሰናብ ሊተላለፉ መሆኑን ፖለቲከኛ ጃዋር መሐመድ ገለጹ። ዝውውሩ ከኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ጋር በተደረገ ስምምነት መሠረት የሚፈጸም ነው ተብሏል። በዚህ ዝውውር ውስጥ ከሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ፣ በተጨማሪ አቶ ኢሳይያስ ታደሰ፣ ኮሎኔል ተወልደ እምበብ እና ኮሎኔል ገብረእግዚአብሔር ዓለምሰገድ ይካተታሉ። አቶ ጃዋር አሰራሩ በሕይወታቸው ላይ ከባድ አደጋ የሚያስከትል በመሆኑ የተባበሩት መንግሥታት፣ የአፍሪካ ሕብረት እና ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት አስቸኳይ የሕይወት ዋስትና እና ከለላ እንዲሰጧቸው ጥሪ አቅርበዋል። ጄኔራል ታደሰ ወረደ ከወራት በፊት በደብረጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ህወሓት በኃይል ሥልጣን መያዙን በይፋ ተቃውመው ከተናገሩ በኋላ ከአስተዳደሩ ተገልለው በቁም እስር ላይ እንደሚገኙ ይታወቃል።
315