uk
Feedback
Arada education office

Arada education office

Відкрити в Telegram

Показати більше
8 800
Підписники
-324 години
+1247 днів
+20830 день
Архів дописів
photo content
+2

ቀን 26/10/2018 ዓ.ም ዜና አራዳ ትምህርት በአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ2018 ዓ.ም የ90 ቀናት ዕቅድ መነሻነት በሳምንት የተከናወኑ ተግባራት አፈፃፀም እና የትምህርት ለትውልድ ያመጣው ፋይዳ በተሰራው ጥናት ዙሪያ ከር/መምህራን: የወረዳ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት ተደርጓል።

መልካም አስተዳደር ችግር 2019.docx0.21 KB

photo content

ቀን 26/10/2018 ዓ.ም ዜና አራዳ በአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ቡድን በ2018 ዓ.ም ለሚጀመረው የክረምት ትምህርት ከዲፕሎማ ወደ ዲግሪ መርሃ ግብር የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና ተሳታፊ የሚሆኑ መምህራን ከትምህርት ቤት በመስፈርት መሰረት ተለይተው የመጡትን በክፍለ ከተማ ደረጃ ከኮሚቴ አባላት ጋር በማወዳደር ልየታ እየተደረገ ነው።

የማስታወቅያ ለተፈጥሮ ሳይንስ የግል ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ ቀን  25/10/2018 ዓ.ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ስር  በሚገኘው በአጋዝያን ቁ /2 ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ኦን ላይን ፈተና  ለመፈተን  ኦረንቴሽን መውሰዳችሁ ይታወቃል። በመሆኑም ነገ ጥዋት 26/10/2018 ዓ.ም 1:30 አጋዝያን ቁ/2 ትምህርት ቤት አድሚሽን ካርድ እና መታወቅያ  በመያዝ እንድትገኙ እናሳስባለን።

ውድ የመንግስት እና የግል ት/ቤት ር/መምህራን እንደምን አደራችሁ የሙያ ፍቃድ መመዘን ሲገባቸው ማለትም ፒጂዲቲ ያላቸው፣በትምህርት የተመረቁ፣በአመራርነት የተመረቁ ሆነው እስከ አሁን ምዘና ያልወሰዱ መምህራን እና የትምህርት አመራሮች መረጃ በጾታ ቁጥር ብቻ ላኩልን!!

ቀን 25/10/2018 ዓ.ም የውይይት ጥሪን ይመለከታል። የ2019 ዓ.ም የ90 ቀናት ዕቅድ የጋራ ተደርጎ ወደ ስራ መገባቱ ይታወቃል። በዚህም መሰረት ዕቅዱን መነሻ በማድረግ የተከናወኑ ስራዎች መገምገም ይኖርበታል። ስለሆነም ነገ አርብ 8:00 ሰዓት 1ኛ የመንግስት ዋና ር/መምህራን 2ኛ የወረዳ ሲፒ ቡድን መሪዎች 3ኛ የወረዳ ስርዓተ ት/ት ቡድን መሪዎች 4ኛ የክላስተር ሱፐርቪዥን አስተባባሪዎች 5ኛ የወረዳ ት/ጽ/ቤት ሀላፊዎች ትገኛላችሁ። ስትመጡ የ2018 ዓ.ም የትምህርት ለትውልድ የተጠቃለለ ሪፖርት በሀርድ ኮፒ መያዝ እንዳይረሳ የአንድ ሳምንት የ90 ቀናት ሪፖርት ቦታ:- ትምህርት ጽ/ቤት 7ኛ ፎቅ ቀን 26/10/2018 ዓ.ም ሰዓት ይከበር

ማሳሰቢያ ለሁሉም የመንግስት ት/ቤቶች የ2018ዓ.ም ትምህርት በመጠናቀቁ በውሰት የሰጣችሁትን የተማሪው መፀሐፍ እየተረከባችሁ እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ፡- 1. አገልግሎት መስጠት የማይችሉ መፀሐፍ እና 2. ተማሪው የጣለው (የጠፋበት) መፀሐፍት በተመለከተ በመፀሐፉ ምትክ ገንዘብ መሰብሰብ ከመመሪያ አኳየ ፈፅሞ የተከለከለ በመሆኑ ተማሪው መፀሐፉን ገዝቶ እንዲተካ እንድታደርጉ እናሳስባለን፡፡ 3. የት/ቤት ዋና ር/መምህርና የት/ቤት መሻሻል ምክትል ርዕሰ መምህራን የተማሪው መፀሐሀፍ ርክክብን እንድትከታተሉና ሪፖርት እንድታደርጉ፡፡ 4. ለ2019ዓ.ም ትምህርት ዘመን የተማሪው መፀፍ የመንሰጠው የተማሪ ቁጥር መሠረት በማድረግ ስለሆነ በዕጥረት ለሚያጋጥም የተማሪው መጥሐፍ ኃለፊነቱ የምትወስዱ መሆኑን ከወዲሁ ይታወቅ

የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት ይፋ ይሆናል፡፡ (ሰኔ 22/2018 ዓ.ም) የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና
የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት ይፋ ይሆናል፡፡ (ሰኔ 22/2018 ዓ.ም) የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ዛሬ ከሰዓት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በማለፊያ ነጥቡ ላይ ውይይት ካደረጉ በሃላ ይፋ ይደረጋል። የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና በአጭር ጊዜ ታርሞ ይፋ መደረጉ ተማሪዎች ለቀጣዩ የትምህርት አመት ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የሚያስችል ሲሆን የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ሰኔ 11 እና 12 /2018 ዓ.ም በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 201 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለተከታታይ ሁለት ቀናት ለ 85,737 ተማሪዎች መሰጠቱ ይታወሳል።

photo content

ለመንግስት የመጀመሪያ ደረጃ የመምህራን ልማት ም/ር/መምህራን አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ በክረምት የትምህርት እድል አሰጣጥ ዙሪያ አጠር ያለ ውይይት ስለሚደረግ ሰኞ ሰኔ 22/10/2018 ዓ.ም በትምህርት ጽ/ቤት 2:30 ሰዓት እንድትገኙ እናሳስባለን!መቅረት ማርፈድ አይቻልም!!

ክ/ከተማው መጠቀሱ እንዳይዘነጋ
ክ/ከተማው መጠቀሱ እንዳይዘነጋ

ማሳሰቢያ 1ኛ/ በሌላ በኩል ከላይ ማሸጊያው ላይ የተፃፈው ዓይነት እና ውስጡ የሚለያይ ከሆነ ቁጥሩ እና እሽጉ ተለይቶ መቅረብ ከቻለ የሚቀየር ይሆናል 2ኛ/ አሁንም በድጋሚ እጥረት በሚል እኛ ከምናውቀው የተማሪ ቁጥር ውጪ የሚቀርበውን በተመለከተ የፅ/ቤታችሁ መረጃ ቡድን ከቢሮ የመረጃ ዳይሬክቶሬት ጋር አናቦ እና ተማምኖ ሲቀርብ ብቻ ምላሽ እንደሚያገኝ በማወቅ ተግባሩን ለመረጃ ቡድን በመስጠት በእናንተ በኩል ክትትል ቢደረግ ይህ ሊሆን የሚችለው ሚኒሊክ 2ኛ ደረጃ የ12ኛ ፈተና ጣቢያ ስለሚሆን እና ስለምንቸገር  እስከ ነገ 18/10/18 ዓ.ም 11:00 መሆን አለበት

በጣም አስቸኳይ ለአራደ ክፍለ ከተማ የመንግስት እና የግል  ት/ቤት በሙሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ትምህርት ቢሮ የትምህርት ግብዓት ፍላጎትና ስርጭት ዳሬክቶሬት የ2018ዓ.ም የተማሪዊች ሪፖርት ካርድ ለክፍለ ከተሞች በመስጠት የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ለሁሉም ት/ቤቶች ማሰራጨቱ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን አንዳንድ ት/ቤቶች በተማሪዎች የውጤት መግለጫ ካርድ ዕጥረት እንዳጋጠማቸው  ገልፀውልናል፡፡ በመሆኑም  የዕጥረታችሁን ሁኔታ በተመለከተ  የትምህርት ግብዓት ፍላጎት ስርጭትበ ዳሬክቶሬት ባስተላለፈው ቅፅ መሠረት Emis እና ፈጣን መረጃ የተማሪ ቁጥር በሞላችሁት በተላከው ቅፅ መሠረት በደብዳቤ በማረጋገጥ ዛሬ 18/10/2018ዓ.ም 10፡00 ድረስ በቴሌግራም እንዲላክ፡፡ በተጨማሪ የተሰጣች የተማሪዎች እሽግ ከፍታች በመቁጠር እና በማረጋገጥ እያንዳንዱ የጎደለውን በመደመር እንዲላክ፡፡ የ2018ዓ.ም የ12 ክፍል መልቀቂያ ፈተና ደግማዊ ሚኒሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ስለሚሰጥ የትህርት ቢሮ ስቶር በት/ቤቱ ስለሚገኝ  መግባት ስለማይቻል መረጃው በፍጥነት ይድረሰን፡፡

photo content
+4

ቀን 18/10/2018 ዓ.ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ስር ለሚገኙ በትምህርት ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ የአስተዳደር ሰራተኞች በመንግስት የአገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ። በስልጠናው ላይ አገልግሎት ሰጭነትን ስነምግባር የተረዳ አመራርና ባለሙያ በመፍጠር  ለሀገርና ለትውልድ እድገት አሻራ የሚጥል አገልግሎት ሰጪ ማፍራት እንደሚገባ ተጠቆመ። የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዱጋሳ ፍቃዱ ስልጠናውን ባስጀመሩበት ወቅት ሀገራችን ፈጣን አገልግሎት መስጠት የሚችል ሲቪል ሰርቪስ እንዲኖራት መንግስት የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው ወደ ርፎርም ትግበራው ከገቡ ጽ/ቤቶች አንዱ የሆነው ትምህርት ጽ/ቤት ማገልገል ክብር ነው በሚል በክህሎትና በአመለካከትና በሙያ ብቁ የሆነ በክፍል ውስጥ ያለውን መማር ማስተማር ሂደት እንዴት መምራት እንዳለበት የሚያውቅ ፤ የአገልግሎት ሰጭነትን ስነምግባር የተረዳ አመራርና ባለሙያ በመፍጠር  ከጽ/ቤት ባለፈ ለሀገርና ለትውልድ እድገት አሻራ የሚጥል አገልግሎት ሰጪ ለማፍራት የሚችል ሪፎርም እንደሆነ ታሳቢ በማድረግ ስልጠናው መዘጋጀቱን አብራርተዋል :: በስልጠናው ላይ ከ29 የመንግስት ት/ቤቶች 1180 ሰራተኞች የስልጠና ተሳታፊ ሁነዋል። ስልጠናውን ወ/ሮ ፍቅርተ አበራ በፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ የማስፈፀም ዘርፍ ሀላፊ የሰጡ ስሆን ዓላማውን አስፈላጊነቱን በተገቢው አብራርተዋል። ከቤቱ የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተው ማብራሪያ ተሰጥቶበት ውይይቱ በመግባባት ተጠናቋል።

ሰላም የመንግስት ር/መምህራን ዛሬ 8:00 ሰዓት የፋይናንስ ስብሰባ ላይ ተገኙ። ቦታ:-8ኛ ፎቅ ፋይናንስ ጽ/ቤት

ተመራቂዎች፦ በአሰላ እና በደብረ ብርሃን ኮሌጅ የተማሩት የቅድመ-1ኛ ደረጃ መምህራን ቅዳሜ ማለትም በ20/10/2018ዓ.ም ጠዋት በአደዋ 00 ግቢ ውስጥ የሚመረቁ መሆኑን እየገለፅን። ተመራቂዎች አርብ በ19/10/18 2:30 ሚኒሊክ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተገኝታችሁ ኦረንቴሽን እና መግቢያ ካርድ እንድትወስዱ ጥሪ እናስተላልፋለን። ማሳሰቢያ ካርድ ሳይዙ ወደ አዳራሽ መግባት አይቻልም

ማስታወሻ ለመንግስት ትምህርት ቤት ርእሰ መምህራን  ኢስኩል ሲስተም ላይ የ2ኛ ሴሚስተር ውጤት መምህራን ጨርሰው እንዲያስገቡ  አድርጉ ሮስተር የተሟላ መሆን አለበት promotion ሲሰራ ያልተሟላ ውጤት እንዳይኖር ክሪላንስ ከመስጠታችሁ በፊት መጨረሳቸውን አረጋግጡ።