የቅዱሳን ታሪክ
Відкрити в Telegram
በዚህ ቻናል ውስጥ፦ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብቻ የሚገኙ ስዕላትን የቤተክርስቲያን ትውፊት የጠበቁ ስዕላት የአድባራት እና የገዳማት ፎቶዎችን ያገኛሉ የተለያዩ ስዕለ አድዕኖ ለመላክ @kidanemiherat_bot
Показати більше8 530
Підписники
+224 години
+117 днів
-1230 днів
Архів дописів
8 530
Repost from አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
"በመከራ ውስጥ ለሚጸኑ ሰማዕታት መጠጊያቸው በደሙ ለዋጃት ቤተ ክርስቲያን ክብሯ... እርሱ መድኃኔ ዓለም ነው!"
#ጥቅምት_፳፯ ቀን የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ነው። ታድያ በዚህች በተቀደሰች ዕለት ማኅሌታውያኑ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በቅዱስ ያሬድ ዜማ "እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን፤ መድኃኒቶሙ ለጻድቃን፤ አሠርገዋ ለምድር በጽጌ ሮማን፤ ስብሐተ ዋሕድ ዘምስለ ምሕረት፤ በመስቀሉ ወበቃሉ፤ አዕበዮሙ ለአበዊነ" እያሉ በምሥጢር ሲዘምሩና ሲያመሰግኑ ያድራሉ።
ሊቃውንቱ ሌሊቱን በዜማ ሲቆሙት ያደሩት ይኽ ምስጋና ድንቅ ምሥጢር ያለዉ እና ቤተ ክርስቲያን ለአማንያን ልጆቿ የምታስተላልፋቸዉ ብዙ መልእክቶችን የያዘ ሆኖ እናገኘዋለን። እስኪ ጥቂቶቹን በስሱ እንዳስሳቸዉ፡
፩, ታሪካዊ አመጣጥና የአፄ ዘርዐ ያዕቆብ ሥርዓት
ይህ በጥቅምት ፳፯ ቀን የሚከበረው የመድኃኔ ዓለም በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ትልቅ ሥፍራ አለው። በ15ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተነሡት ታላቁ ሊቅና ንጉሥ አፄ ዘርዐ ያዕቆብ መጽሐፈ ሥርዓትንና መጽሐፈ ሚላድን በመድረስ የቤተክርስቲያንን ሥርዓተ አምልኮና ዶግማ አጽንተዋል። ንጉሡ ጌታችን ለዓለም የከፈለውን መሥዋዕትነትና የሰማዕታትን ክብር በማስበብ እንዲሁም ጥንተ ዕለቱ መጋቢት ፳፯ ቀን በጾመ ዐቢይ ይውላልና እንደሚታወቀዉ የዐቢይ ጾም ወቅት ደግሞ የኀዘን እና የልቅሶ እንጂ የደስታ ዘመን ባለመሆኑ በዓል ማክበርንም ስለማይፈቀድ ይህ ዕለት በጥቅምት ወር በታላቅ መንፈሳዊ ድምቀትና ሥርዓት እንዲከበር የደነገጉበት በመሆኑ በዓሉ ታሪካዊ መሠረቱን ከሊቃውንት አባቶቻችን ትዕዛዛትና ቀኖና ጋር በጥብቅ ያገናኛል።
፪, "ስብሐተ ዋሕድ ዘምስለ ምሕረት" ምስጢረ ሥላሴና መለኮታዊ ቸርነት
ሊቃውንቱ "የአንድ ልጅ ክብር ከምሕረት ጋር" ሲሉ የአብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስን አንድነትና ሦስትነት (ምስጢረ ሥላሴን) እና የሰውን ልጅ የማዳን መለኮታዊ ፈቃድ ይገልጣሉ። ዓለምን ለማዳን አንድያ ልጁን የላከው የአብ ቸርነት፣ በፈቃዱ ሰው ሆኖ ደሙን ያፈሰሰው የወልድ ፍቅር፣ እና ያንን መሥዋዕትነት ለሰው ልጅ የሚያጸናው የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በአንድነት ተገልጠዋል።
ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በቅዳሴው ላይ "አብ መረጠ፣ ወልድ ሥጋ ሆነ፣ መንፈስ ቅዱስም መጣ (አደረ)" እንዳለ፣ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በመስቀል ላይ የፈጸመው የማዳን ሥራ የሥላሴን ዘላለማዊ የምሕረት ቃልኪዳን ለፍጥረት ሁሉ ያበሠረበት ነው። ይህ ቸርነት በሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልእክት ላይ፡- "ነገር ግን የመድኃኒታችን የእግዚአብሔር ቸርነትና ሰውን መውደዱ በተገለጠ ጊዜ... እንደ ምሕረቱ መጠን አዳነን" ቲቶ፡ ፫፥፬-፭ ተብሎ እንደተጻፈው ያለ እኛ ጽድቅ በነፃ የተሰጠን መለኮታዊ ስጦታ ነው።
፫, የሮማን አበባ ምስጢርና ከዘመነ ጽጌ ጋር ያለው ትስስር
በአሁኑ ወቅት ቤተ ክርስቲያናችን የምትገኘው በዘመነ ጽጌ (የአበባ ወራት) ውስጥ በመሆኑ የሊቃውንቱ "ምድርን በሮማን አበባ አስጌጣት" የሚለው ምስክርነት ጥልቅ ትርጉም ይኖረዋል። ሮማን ውጫዊ ቅርፊቱ ሻካራና እሾሃማ (የመከራና የስደት ምሳሌ) ቢሆንም ውስጡ ግን በብዙ ቀይና ጣፋጭ ፍሬዎች የተሞላ ነው።
ይህ በዘመነ ጽጌ ስደቷንና መከራዋን የምናስባት የድንግል ማርያም (የጽጌ ማርያም) እና የልጇ የመድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ምሳሌ ነው። ጌታችን በመስቀል ላይ የተቀበለው መከራና የፈሰሰው ደሙ ውጫዊ እይታው አሰቃቂ ቢሆንም ውስጣዊ ምስጢሩ ግን ለዓለም ሕይወትንና ድኅነትን ያስገኘ መለኮታዊ ፍቅር ነው።
ቅዱስ ጳውሎስ "በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ..." ሐዋ፡ ፳፥፳፰ በማለት እንደገለጠው ክርስቲያኖች የተከፈለላቸውን ይህንን ታላቅ የደም ዋጋ ሊረዱና ሕይወታቸውን በቅድስና ሊጠብቁ ይገባል። የዳንበትን ዋጋ ማቃለል ሳይሆን በመስቀሉ የተሰጠንን ነፃነት በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ መታተም መገንዘብ ክርስትናችንን መጠበቅ ማለት ነው።
፬, ስለ ሃይማኖታቸው መከራ ለሚቀበሉት የታላቅ ቃልኪዳን በዓል
ይህ በዓል ዛሬ ላይ ሆነን ስንመለከተው ለስሙ አጠራርና ለቀናች ሃይማኖታቸው ሲሉ መከራ ለሚቀበሉ፣ ከቀያቸው ለሚሰደዱና በሰማዕትነት ለሚታረዱ ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ትልቅ መጽናኛና ትርጉም አለው። ሊቃውንቱ "እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን፤ መድኃኒቶሙ ለጻድቃን" ይላሉ። ቅዱሳንና ሰማዕታት በመከራ ውስጥ ሆነው ለሃይማኖታቸው የጸኑት መድኃኔዓለም ክብራቸውና አዳኛቸው ስለሆነ ነው።
ጌታችን በወንጌል፡- "ስለ ስሜ በሰው ሁሉ የተጠላችሁ ትሆናላችሁ፤ እስከ መጨረሻ የሚጸና ግን እርሱ ይድናል" ማቴ፡ ፲፥፳፪ እንዳለ ዛሬም ስለ ሃይማኖታቸው ዋጋ ለሚከፍሉ ቅዱሳን ሁሉ መድኃኔ ዓለም መጠጊያቸውና የሰማዕትነት አክሊላቸው ነው። ይህ ዕለት የእነርሱን መከራና ስደት የሚወክል በመጨረሻም በመስቀሉ ድል አድራጊነት የሚያሻግር ታላቅ የተስፋ በዓል ነው።
፭, "በመስቀሉ ወበቃሉ..."
የቅዱሳን አባቶቻችን ታላቅነትና ክብር የተመሠረተው በሁለት ምሰሶዎች ላይ ነው፤ እነርሱም፡- የእግዚአብሔር ሕይወት ሰጪ የሆነዉ "ቃል" እና መሥዋዕትነት የተከፈለበት "መስቀል" ናቸው። ሊቁ ቅዱስ አትናቴዎስ፡- "እግዚአብሔር ሰው የሆነው እኛን አምላክ ያደርገን (የጸጋ አማልክት ያደርገን) ዘንድ ነው" እንዳለው አባቶቻችን በቃሉና በመስቀሉ ከፍ ከፍ ያሉበትን ይህንን አሰር እኛም ልንከተለው ይገባል።
ክርስቲያን መሆን ማለት መከራን አለመፍራት፣ የተከፈለልንን ዋጋ ማወቅና በቅድስና መኖር ማለት ነው። መድኃኔ ዓለም አምላካችን ስለ ስሙ መከራ ለሚቀበሉ ወገኖቻችን ጽናቱንና መጽናናቱን ይስጥልን፤ ሀገራችንን በደሙ ዋጋ ይጠብቅልን።
የመድኃኔ ዓለም ቸርነት፣ የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳኑ ሁሉ ጸሎትና በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን!🤲
ክቡራን እንኳን ለታላቁ የመዳናችን ቀን በሰላም አደረሳችሁ መልካም በዓል ይሁንልን🙏
8 530
Repost from አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
መ ድ ኃ ኔ ዓ ለ ም#ጥቅምት_27 ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የመድኃኔ ዓለምን በዓል በደማቁ ታከብራለች ይህም የለውጥ በዓል ነው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደሙን ያፈሰሰው ሥጋውን የቆረሰው መጋቢት 27 ነው። ነገር ግን እንደዛሬዉ በግለሰቦች ፈቃድ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ሳይጣስ በፊት ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያናችን አባቶች መጋቢት 27 ቀን ዐቢይ ጾም ላይ ስለሚውል በዐቢይ ጾም ደግሞ ኀዘን እንጂ ደስታ ስለሌለ በዓል ማክበርም ስለማይፈቀድ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ ደስ ብሎን ከድሆች ጋር እንድናከብረው በቤተ ክርስቲያን ሥርዓትን ሠርተውልን ነበር። በሞቱ ሞታችንን ያስወገደ፣ በኀዘኑ ኀዘናችንን ያራቀ በለቅሶው ዕንባችንን ያበሰ፣ ከወደቅንበት ያነሳን፣ ጠላታችንን ከመንገዳችን በመስቀሉ ጠርቆ ያስወገደ፣ በደሙ የቀደሰን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በአይሁድ ተንኮልና ክፋት በሐሰት ተወንጅሎ 6666 ጊዜ ተገርፎ 41 ጊዜ በብረት ዘንግ አናቱን ተመቷል። በምራቁ ዕውር የሚያበራ ምራቅ ተተፋበት ሥጋው አልቆ ደሙ ፈሶ አጥንቱ ይቆጠር ነበር ስለ ሁላችንም እርሱ ታመመ ስለሁላችን እርሱ ሞተ መስቀል ተሸክሞ በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ወድቆ ተነሳ። አይሁድ በወንጀለኛው በርባን ፋንታ ክርስቶስ ይሰቀል በርባን ይፈታ በማለት መድኃኒታቸውን ሰቀሉት ይሆን ዘንድ ግድ ነውና በቀራኒዮ አደባባይ በማዕከለ ምድር የዓለም መድኃኒት ተሰቀለ። አይሁድ በውስጣቸው ባደረ ጠላት ዲያቢሎስ ምክንያት ክፋት ጭካኔያቸው የበዛ ሆነ አዳኝ መድኃኒት ህይወት ፍቅር ተስፋ የሆነውን ክርስቶስ በክፋት ተነሳስተው ቢሰቅሉትም ለእኛ ግን መዳን ሆነልን ሥጋውን በልተን ደሙን ጠጥተን የምንድን ሆንን። በክርስቶስ ሞት ሞታችን ተወግዶ ህይወት አገኘን በነፃነት እንኖር ዘንድ ነፃ አወጣን ተስፋችን መታመኛችን ኃይላችን እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እግዚአብሔር የሆነ በመስቀል ሞት ነፃነታችንን አውጆ የዲያቢሎስ ክፋትና ተንኮል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አስወግዶ #ተፈፀመ በማለት ነፍሱን ሰጠ ዛሬ በቀደመው ክብሩ በዙፋኑ አለ ለማማለድ ሳይሆን ለመፍረድ አማላጅነት የአገልጋዮቹ የቅዱሳን ተግባር ነውና። ጌታ : ሆይ : ወሰን : ስለሌለው : ፍቅርህ : እናመሰግንሃለን። እንኳን አደረሳችሁ ክቡራን🙏
8 530
Repost from አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
የዚህ ዘመን ቅዱስ እስጢፋኖሶች!!
#ጥቅምት_17_ቀን የስሙ ትርጓሜ ‹አክሊል› የሆነው በሕገ ወንጌል የመጀመሪያ ሊቀ ዲያቆናትና ቀዳማዊ ሰማዕት የተባለ ቅዱስ እስጢፋኖስ ዲያቆን ሆኖ የተሾመበት ቀን ነው።
እንኳን አደረሰን አደርሳችሁ🙏
በአሁኑ ጊዜ ልክ እንደቀደመው ዘመን ክርስትናንና ኦርቶዶክሳውያንን ለማጥፋት ጠላት በሰዎች ላይ እያደረ ክርስቲያኖችን ያስ*ድ*ል ያስጨ*ጭፋል እንዲሁም ያሳድዳል፡፡
ወቅትና ጊዜን እየጠበቀ በየጊዜው በተለያዩ ክፍለ ሀገራት በጅምላ የሚጨ*ጨ*ት ሕፃናት አረጋዊያን እንዲሁም ወጣቶች እልፍ ናቸው።
ምንም በማያውቁት ምክንያት በሃይማኖታቸው በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በመናገራቸው ሳቢያ ቤተ ክርስቲያን ሄደው በዓላትን በማክበራቸውና ባህላቸውንና ሃይማኖታቸውን ለማስጠበቅ በመፈለጋው ብቻ ይሳደዳሉ፡፡
እነዚህ እርኩስ መንፈስ ያደረባቸው ሰዎች የጠላት ተገዢ ከመሆናቸው ባሻገር ለራሳቸውና ለሌሎች ጥፋት መንሥኤ በመሆናቸው እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ሐሰተኞችን በመቃወም ለእውነት መመስከር ይገባናል፡፡
ለዚህም በሃይማኖት ጸንቶ መኖር ይጠበቃልና እንጽና!
የቅዱስ እስጢፋኖስ አማላጅነትና ተረዳኢነት አይለየን🤲
8 530
Repost from አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
“ ም ሬ ል ሻ ለ ሁ” አ ላ ት ፡፡
ከክርስቲያን ወገን የሆነ ሀብት አግኝቶ ያጣ አንድ ሰው ነበር “ከብሬ በኖርሁበት ሀገር ተዋርጄ አልኖርም” ብሎ ጓዙን ጠቅልሎ ሄደ ።
ሰይጣን ያዘነ መስሎ ደንጊያውን በምትሐት ወርቅ አስመስሎ “አብን ወልድን መንፈስ ቅዱስን፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታትን፣ መላእክትን ካድልኝና ይህን እሰጥሃለሁ” አለው፡፡
ካደለትና ተቀብሎ ዞር ሲል “ምእመናን የሚመኩባት ድንግል ማርያም
የአምላክ እናት አይደለችም ብለህ ካድልኝ” አለው፡፡ “እሷንስ አልክድም” አለው ፡፡ በደንጊያ ቀጥቅጦ ገደለው፡፡
መላእክተ ጽልመት ነፍሱን እጅ አደረጉ፤ መላእክተ ብርሃንም አብረው ቀረቡ እመቤታችንም ቀርባ፤ “ልጄ ይህችን ነፍስ ማርልኝ” አለችው፡፡
“ እናቴ ውሻ ይማራልን” አላት፡፡ “ስምሽን የጠራውን መታሰቢያሽን ያደረገውን እምርልሻለሁ ያልኸው ቃል ይታበላልን” አለችው “ምሬልሻለሁ” አላት፡፡
ሁል ጊዜ ድንግል የምትሆኚ አምላክን የወለድነሽ የክርስቶስ እናት ሆይ ኀጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ወደ ልጅሽ ወደ ወዳጅሽ ወደ ላይ ጸሎታችንን አሰርጊ እያልን እንማፀናታለን።8 530
Repost from አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
"ተይው አታንሺው አምላክነቱን ይግለጥ"
እመቤታችን በዚህ በወርኃ ጽጌ ወቅት ወደ ግብጽ በተሰደደች ጊዜ ከደረሱባት ጸዋትወ መከራ መካከል ኮቲባ የምትባል ገረድ ጌታን ከእመቤታችን ነጥቃ ከደንጊያ ላይ መጣሏ አንዱ ነው
እመቤታችን በስደቷ ወቅት ኅብስተ ሕይወትና ማየ ሕይወት የሆነ ጌታ በጀርባዋ አዝላ ምድራዊ እንጀራና ውኃ ለመለመን መንደር ለመንደር ስትንከራተት ትዕማን ከምትባል አንዲት ሴት ቤት ደረሰች
ስመ እግዚአብሔር ጠርታ ብትለምን የቤቱ እመቤት ከሰገነት ላይ ሆና አይታት «አንቺ ሴት ከወዴት የመጣሽ ነሽ?» አለቻት እመቤታችንም «ከይሁዳ ምድር የተሰደድኩ ስደተኛ ሴት ነኝ አለቻት»
«አንቺ ሴት ደረቅ ነሽ መሰለኝ በድርቅናሽ ቤትሽን ትተሸ ባልሽን ፈትተሽ ትንከራተቻለሽ እንጂ እንዳንቺ ያለ ቆንጆ ሴት ካዳራሽ ወደ ዕልፍኝ ከሰገነት ወደ ሰገነት ከመጋረጃ ወደ መጋረጃ ይላል እንጂ ሀገሩን ትቶ ሀገር ለሀገር አይንከራተትም አለቻት»
ቅዱስ ዮሴፍም «ቢኖር ይስጡታል ባይኖር ደግሞ ካለበት ያድርስህ ይባላል እንጂ እንዲህ እንደ ዕንጨት የሚያደርቅ ነገር ምን ያናግራል» አላት
ኮቲባ የምትባል አሽከር ደርቡን እያነዋወጠች ወርዳ «ይህ ጀውጃዋ ሸማግሌ ደፍሮ እመቤቴን እንዴት እንዲህ ይመልስላታል» ብላ እሱን በጥፊ ቃጥታ ጌታን ከእመቤታችን ነጥቃ ሎቱ ስብሐት ከደንጊያ ላይ ፈጠፈጠችው
ሕፃኑም እሪ ብሎ አለቀሰ እመቤታችንም የሞተ መስሏት ብክንክን ብላ አለቀሰች አነሣለሁ ስትል ዮሴፍ "ተይው አታንሺው አምላክነቱን ይግለጥ" አላት።
እመቤቲቱን ከነባሪያዋ መሬት ተከፍታ ዋጠቻት ነገር ለማዳነቅ ግርግር ለመፍጠር የተሰበሰቡ ቤተሰቡ ሁሉ ጦጣ ዝንጀሮ እየሆኑ የገዛ ውሾቻቸው እያባረሩዋቸው ወደ ዱር ተሳደዱ።
እመቤታችን ተወዳጅ ልጇን ይዛ ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር በዚህ ቤት በተድላ በደስታ መንፈቅ ያህል ተቀምጠዋል፡፡
8 530
Repost from አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
የ መ ድ ኃ ኔ ዓ ለ ም : እ ጆ ች
ጌታ በጥብርያዶስ ባሕር ላይ ሌሊት በእግሩ ሲመጣ ቅዱስ ጴጥሮስ ቢመለከተው ወደ አንተ እመጣ ዘንድ እዘዘኝ በማለት ካስፈቀደ በኋላ ወደ ጌታ ለመምጣት መንገድ ጀምረ ።
በመሐል ግን ቅዱስ ጴጥሮስ ጥርጣሬ ገባውና መስጠም ሲጀምር ጌታችን «ያመንክ እንጂ ያላመንክ አትሁን» ብሎ ገስፆ ከመስጠም አድኖታል። (ማቴ 14፥22-33)
ከመስጠም : የሚታደግ : መድኃኔዓለም : እኛንም : ይታደገን
8 530
Repost from አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
ብ ዙ ኃ ን : ማ ር ያ ም
በቤተ ክርስቲያናችን ከሚዘከሩ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓላት መካከል መስከረም 21 ቀን የሚውለው በዓል ‹‹ብዙኃን ማርያም›› በመባል ይታወቃል፡፡
በዓሉ በሁለት ዐበይት ምክንያቶች ይከበራል የመጀመሪያው ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊ ውሳኔ ለማዘጋጀት ከሩቅም ከቅርብም የተሰባበሰቡት ቀን ሲሆን ።
ሁለተኛው ደግሞ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል በግሸን ደብረ ከርቤ የተቀመጠበት ዕለት ነው፡፡
የጌታችን የመድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ፣ የእመቤታችን አማላጅነት፣ የክርስቶስ የመስቀሉ ኃይል፣ የአባቶቻችን ሊቃውንትና ነገሥታት በረከት አይለየን፡፡
8 530
Repost from አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
#ቅዱስ_ሚካኤል_ሆይ ቅዱስ መስቀሉ በተገኘበት ዘመን ክርስቲያኖች ደስታቸውን ይገልጡ የምሥራች ዜና ይናገሩ የነበረው እሳትን በማንደድ ችቦ አብርተው እየዘመሩ ሌሊትም በመጓዝ በማመስገን ጭምር ነበር ።
እናም የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሆይ ንጉሥ ሕርቃል በፋርስ ዘመቻ የጌታን መስቀል ከምርኮ አስመልሶ በድል ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ በዚያ ያሉ ክርስቲያን ምእመናን በእልልታ በደስታ አበባ ይዘው ችቦ አብርተው በደስታ እንደተቀበሉት ሁሉ በቃል ኪዳንህ ለምንታመን ለኛ ከምሕረት አልባው ከዲያብሎስ ደባ ከአጋንንት ድብደባ ከዚህ ዓለም ፈተና ብርሃናዊ በሆነው መስቀልህ ታደገን የመስቀሉን ብርሃንም አብራልን አሜን ።
8 530
Repost from አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
« አ ሁ ን ፡ አ ረ ፈ ች ፡ እ ህ ት ሽ ፡ ኤ ል ሳ ቤ ጥ »
#መስከረም_ሰባት_ቀን_ቅድስት_ኤልሳቤጥ_ዐረፈች ቅድስት ኤልሳቤጥ የቅዱስ ዮሐንስ እናት የጽድቅ እመቤት ከመሆኗም በላይ የቅድስት ድንግል ማርያም የቅርብ ዘመድ በትሕትናዋ የምትወደድ ደገኛ ሴት ናት ።
ሰውነቷ ከኀጢአት ንግግሯ ከትዕቢትና ከስሕተት የታረመ በመንፈስ ቅዱስ የተቀመመ ከቅዱስ ገብርኤል ቀጥላ ስለወላዲተ አምላክ ስለ ድንግል ማርያም ማንነት የመሰከረች በዘመኑ ለነበሩ ማኅበረሰብ ወንጌልን የሰበከች የመጀመሪያዋ የሴት ሐዋርያ የሆነች ክብርት ሴት ናት ቅድስት ኤልሳቤጥ ።
በዝምድና አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የእናቷ እኅት ልጅ ናት ይችንም ቅድስት ኤልሳቤጥ ካህኑ ዘካርያስ አገባት የከበረ ወንጌልም ኹለቱም ያለ ነውር ያለ ነቀፋ በእግዚአብሔር ሕግ ጸንተው የሚኖሩ እውነተኞችና ጻድቃን ሆነው እንደኖሩ መስክሮላቸዋል ።
ኤልሳቤጥ መካን ስለሆነች ወደ እግዚአብሔር የሚለምኑና የሚማልዱ ሆኑ አርጅተውም የመውለጃቸው ዘመን ባለፈ ጊዜ እግዚአብሔር መልአኩን ገብርኤልን ወደ ዘካርያስ ልኮ ልመናቸው እንደ ተሰማና ዮሐንስን እንደሚወልዱ አበሠረው ።
ከዚህም በኋላ ቅድስት ኤልሳቤጥ መጥምቁን ዮሐንስን ፀንሳ ወለደች ከሰዎችም የሚደርስባት ሽሙጥ ተወግዶ እጅግ ደስ አላት ሕፃኑም በማሕፀኗ እያለ እመቤታችን ድንግል ማርያም ሰላምታ በሰጠቻት ጊዜ እንዲህ ብላ ጮኸች ፦
« አንቺ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሸ የተባረክሽ ነሽ የማኅፀንሽም ፍሬ ቡሩክ ነው የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እኔ ምንድን ነኝ እነሆ እንዴት ነሽ ስትይኝ የሰላምታሽን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ልጁ በማኅፀኔ ውስጥ በደስታ ዘለለ»ብላ የእመቤታችንን ወላዲተ አምላክነትን መሰከረች ።
ከዚህም በኋላ ጌታችንን አየችው በአምላክነቱም አመነች የሚያምኑበት በመዳናቸው ደስ አላት ስትል መስክራለች ኤልሳቤጥ ልጅዋን ዮሐንስን ከሄሮድስ ሰይፍ ለማሸሽ በስደት በሐቅለ ዮሳፍጥ እንዳለች ከዚህ ዓለም #መስከረም_ሰባት_ቀን_ዐርፋለች።
እመቤታችን ተወዳጅ ልጇን አዝላ አረጋዊ ዮሴፍና ሰሎሜን አስከትላ ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ኖራ ከኢትዮጵያ ተነሥታ በመስከረም ወር ግብፅ ገባች ፤ በሐቅለ ዮሳፍጥ አቋርጠው ሲሄዱ ሕፃኑ ኢየሱስ ክርስቶስ #አሁን_አረፈች_እህትሽ_ኤልሳቤጥ እያለ በሕፃን አንደበቱ እየደጋገመ ቅድስት ኤልሳቤጥ ወዳረፈችበት ቦታ በጣቱ እየጠቆመ ያሳያቸው ጀመር ።
እነርሱም ወደ ጠቆማቸው ቦታ ቢሄዱ ቅድስት ኤልሳቤጥ አርፋ ልጇ ዮሐንስ ሙት የሆነውን የእናቱን ጡት ሲገጠግጥ አገኙት ፤ ዮሐንስ ሰው አይቶ ስለማያውቅ ምን መጣብኝ ብሎ ደንግጦ ከዱር ገባ ፤ እመቤታችን አረጋዊ ዮሴፍና ሰሎሜ አልቅሰው መቃብሩን የታዘዘ አንበሳ መጥቶ ቆፍሮላቸው በዚያ በዮሳፍጥ በረሃ አጥበው ገንዘው ቀብረዋት ሔደዋል ።
እመቤታችን አረጋዊ ዮሴፍን ዮሐንስን አባብለው ከተደበቀበት ዱር ጫካ እንዲያመጣው ልትልከው ስትል ሕፃኑ ክርስቶስ « ተውት እሺ አይላችሁም ጊዜው አልደረሰም ሠላሳ ዘመን ሲሞላው እርሱ ራሱ በክብር ይገለጣል ከፊቴ እየቀደመ የንስሐ ትምህርትን እያስተማረ መንገዴን የሚጠርገው እርሱ ነው » አላቸው ከዚያም ትተውት ሔደዋል ።
ዮሐንስም ሠላሳ ዘመን እስኪሞላው ድረስ በዚያው በተሰደደበት በረሃ አድጓል ኤልሳቤጥ የቅድስት ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክነትን በማብሠር የመጀመሪያ ሴት ሐዋርያዊት ስትሆን ልጇ ቅዱስ ዮሐንስ ደግሞ የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነትን በማብሠር የመጀመሪያ ሐዋርያ ሆኗል ።
በዚህም እናትና ልጅ በተመሳሳይ ሰዓት ተመሳሳይ ምስክርነትን በመስጠት ከመላእክት ቀጥሎ ከሰው ዘር አስቀድሞ የሥጋዌን ምሥጢር ገበታ በመቅመስ የመጀመሪያና ብቸኛ ናቸው ።
ቅዱስ ያሬድ የእናትና የልጅን ሕይወት እንዲሁም የሰጡትን ምስክርነት በድጓው እንዲህ ሲል ዘምሮላቸዋል « ኤልሳቤጥ ማርያምን ቃልሽን በሰማሁ ጊዜ በማኅፀኔ ያለው ልጅ በደስታ ዘለለ አንቺ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሸ የተባረክሽ ነሽ አለቻት መልአኩም ኤልሳቤጥን ተናገራት የዮሐንስን እናት እንዲህ አላት ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ የሚያሰክር ወይንና ጠጅን አይጠጣም መንፈስ ቅዱስ በላዩ ላይ ያድርበታል ( ይመላበታል ) የሙሽራው ወዳጅ ይባላል » በማለት ቅድስት ኤልሳቤጥ የወለደችው የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነ ጻድቅና ነቢይ መሆኑን በድጓው ዘምሯል ።
8 530
Repost from አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
ር እ ሰ : ዐ ው ደ : ዓ መ ት ና : ቅዱስ : ዮ ሐ ን ስ
የቅዱስ ዮሐንስ መታሰቢያ በዓል ከርእሰ ዐውደ ዓመት በዓል ጋር በአንድ ቀን እንዲከበር የተደረገበት ምክንያት የርእሰ ዐውደ ዓመት ወይም የዘመን መለወጫ በዓል ለአሮጌው ዓመት መጨረሻ፣ ለአዲሱ ዓመት መነሻ በመሆን ለጊዜ አቆጣጠር የሚያገለግል ስለሆነ ነው ።
ከዚህ መሠረታዊ ተግባር የተነሣ የቅዱስ ዮሐንስ ታሪክ ከዘመን መለወጫ ጋር በንጽጽራዊ ምሥጢር ብዙ የሚያመሳስለው ነገር ስላለ ነው ።
ቅዱስ ዮሐንስ የተፀነሰው መስከረም ወር ውስጥ መሆኑ ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ « በስድስተኛው ወር መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ድንግል ማርያም ተላከ» ብሎ ነግሮናል ( ሉቃ 1፥ 26 ) ።
ቅዱስ ገብርኤል መጋቢት 29 ቀን ድንግል ማርያም በድንግልና እንደምትፀንስ ባበሠራት ጊዜ እመቤታችን እንደምን ይሆንልኛል ባለችው ሰዓት ኤልሳቤጥ እንኳ ካረጆች ከሸመገለች በኋላ ከፀነሰች 6 ወር ሆኗታል›› በማለት ዮሐንስ በተፀነሰ በስድስት ወሩ እመቤታችንን እንዳበሠራት እንረዳለን ፡፡
ይህ ከሆነ ከመጋቢት 29 ቀን ጀምረን ወደ ኋላ ብንቆጥር 6ኛው ወር መስከረም ስለሆነ ዮሐንስ የተፀነሰው በመስከረም ወር እንደሆነ እንገነዘባለን ።
ከዚህ በመነሣት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከመስከረም 1 ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 8 ቀን የቅዱስ ዮሐንስ መታሰቢያ በዓል ብላ ታከብራለች ።
የዮሐንስ መፀነስ በወርኃ መስከረም መሆኑን ለማስገንዘብ መስከረም 8 ቀን የወላጆቹን የካህኑ ዘካርያስና የቅድስት ኤልሳቤጥን በዓል ከፅንሰተ ዮሐንስ ጋር በማስተባበር ታከብራለች ፡፡
ስለዚህ መስከረም አንድ ቀን ለአሮጌው ዘመን መጨረሻ ለአዲሱ ዓመት ደግሞ መጀመሪያ ከመሆኑ አንጻር በሕዝብ የሚያሳድረውን ደስታ በማነጻጸር ‹‹ በልደቱ ብዙዎች ደስ ይላቸዋል ›› በተባለለት በቅዱስ ዮሐንስ እለቱን ሰይማ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታከብረዋለች ።
እንዲሁም ቅዱስ ዮሐንስ የብሉይ ኪዳን ሥርዓት ማክተሙንና የሐዲስ ኪዳን ሥርዓት መተካቱን በስብከቱ ማወጅ የጀመረበት ወርኃ መስከረም ነው ።
መስከረም አንድ ቀን ደግሞ የአሮጌው ዓመት ማብቂያ የአዲሱ ዓመት ደግሞ መጀመሪያ እንደሆነ ሁሉ የብሉይ ኪዳን ሥርዓት እንዳከተመና በምትኩ የሐዲስ ኪዳን ሥርዓት እንደተተካ የሚያበሥረው የቅዱስ ዮሐንስ ስብከት በመሆኑ በይዘቱና በምሥጢሩ ከርእሰ ዐውደ ዓመት ጋር እንዲከበር ሆኖአል ።
በእግዚአብሔር : ፊት : የምትሔድ : ዮሐንስ : ሆይ : አንተ : ንዑድ : ክቡር ነህ : ስለእኛ : ጸልይ : መታስቢያህ : በርእሰ : ዐውደ : ዓመት : ተጻፈ (ታሰበ) በረከትህን : እንቀበል : ዘንድ : ባርከን ።
8 530
Repost from አምኀ ተዋኅዶ ዘክርስቶስ
ቅ ዱ ስ : ራ ጉ ኤ ል ን
#መስከረም_አንድ_ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ራጉኤል ከዘጠኙ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን በክብርና በጸጋ ልቆ የመላእክት አለቃ ሆኖ የተሾመበት በዓለ ሲመቱ ሲሆን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዘንድ በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
ይህ ቅዱስ መልአክ የፀሐይን ሥነ ፍጥረት ለነቢዩ ለሄኖክ እንደተረጎመለት በመጽሐፈ ሄኖክ ምእራፍ 6 ላይ በግልጽ ተመልክቶ እናገኛለን።
ቅዱስ ራጉኤል በብርሃናት አሠራርና ዑደት ላይ ሥልጣን የተሰጠው መጋቤ ብርሃናት ከመሆኑም በላይ የዚህን ዓለም የጨለማው ገዢ ዲያብሎስን ለመበቀልና ለመቅጣት ፍፁም ሥልጣን የተሰጠው ታላቅ መላእክ ነው ።
ቅዱስ ራጉኤል ታላቅ ሥልጣን ያለው፣ ከክብሩ፣ ከብርሃነ-ረድኤቱና ከጸጋው ምልዓት የተነሳ ምድርን ሁሉ ለማብራት ማለትም ለማዳን የሚችል መሆኑን እንረዳለን ፡፡
ከታላቅ ሥልጣኑና ከብርሃነ ክብሩ ተካፋይ ለመሆን በተሰጠው ቃል ኪዳን ከሰው ልጆች ጠላት ከዲያብሎስ ስውር ወጥመድ ለመዳን በክንፈ ረድኤቱ ጠብቆ በንስሐ ወደ እግዚአብሔር የምሕረት ዙፋን እንድንቀርብ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤልን ፍጹም ተራዳኢነት አይለየን።
