cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

የቅዱሳን ታሪክ

በዚህ ቻናል ውስጥ፦ በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ብቻ የሚገኙ ስዕላትን የቤተክርስቲያን ትውፊት የጠበቁ ስዕላት የአድባራት እና የገዳማት ፎቶዎችን ያገኛሉ የተለያዩ ስዕለ አድዕኖ ለመላክ @kidanemiherat_bot

Більше
Рекламні дописи
9 241
Підписники
+424 години
+137 днів
+3830 днів
Час активного постингу

Триває завантаження даних...

Find out who reads your channel

This graph will show you who besides your subscribers reads your channel and learn about other sources of traffic.
Views Sources
Аналітика публікацій
ДописиПерегляди
Поширення
Динаміка переглядів
01
...« ቅድስት ዮስቴና ሆይ ከሕጋዊ ባልሽ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ እርሱም ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም ፣ ሰው ሁሉ የሚማፀነው ፣ ገድሉ ትሩፋቱ በዓለም የሚነገርለት ፣ በነፍስም በሥጋም የሚያማልድ ፣ እንደ መልአክትም ክንፈ ጸጋ የሚሰጠው በምድር ሆኖ መንበረ ጸባኦትን የሚያይ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ » ተብሎ ትንቢት የተነገረላቸው የአባታችን የጻድቁ #የአቡነ_ሀብተ_ማርያም ልደት ግንቦት 26 ቀን በታላቅ ድምቀት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታከብራለች ። « በጸሎትህ አምኖ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ ስምህን የጠራውን ዝክርህን የዘከረውን ሁሉ የሀብተ ማርያም አምላክ ሆይ ከጠላት እጅ አድነኝ ያለኝን በኅሊና ያሰበውን በልቡናው የወሰነውን እፈጽምለታለሁ ። » ብሎ ቃልኪዳን የተገባልህ እኛን ደካማ ልጆችህን በምልጃህ በቃል ኪዳንህ አስበን!!
1834Loading...
02
በ ዓ ተ ፡ ግ ብ ጽ #ግንቦት_24 ቀን እመቤታችን ከተወዳጅ ልጅዋ ጋር በስደት ግብጽ የገባችበት ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው አበው የአበባን በዓል በአበባ ዘመን ብለው ማኅሌቱንም በዓሉን በወርኃ ጽጌ በጥቅምት ቢወስዱትም ጥንተ መሠረቱ ግንቦት 24 ቀን ነው ። እመቤታችን ቀጥኖ ከሚያመነምን ክፉ ዘመን ትሰውረን እፎይ ከምንልበት ዘመን በምልጃዋ ታድርሰን!!
4352Loading...
03
....ከዓመታት በፊት በታኅሣሥ ሃያ አራት የጻድቁ አባታችንን በዓል ለማክበር በግብጽ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተሰባስበው ቁስቋም ወዳለው የጻድቁ ቤተ መቅደስ በሌሊት ይደርሳሉ ። በስፍራው እንደደረሱም ከበሮ ይዘው #የኤቲሳ_አንበሳ_ተክልዬ_ተነሣ እያሉ እየዘመሩ በዛፎች እስከተከበበው እጅግ ሰፊው የገዳሙ ግቢ የውስጠኛ ክፍል ድረስ የጻድቁ አባታቸውን ስም እየጠሩ ገሠገሡ ። ይህንን የተመለከቱ የገዳሙ አባቶች በደስታ ተውጠው ሲመለከቱ አንድ አባት ግን እየተንሰቀሰቁ ያለቅሱ ጀመር ። እኚህ አባት የተክለ ሃይማኖት መቅደስ ያለበትን ቤተ ክርስቲያን ቁልፍ የሚይዙ መነኩሴ ናቸው ። የሚዘምሩትን ወጣቶች እያዩ በመደሰት ፈንታ ዕንባቸውን ለመግታት አልቻሉም ። ሁኔታው ግራ ያጋባቸው ኢትዮጵያውያኑ ወጣቶች ዝማሬአቸውን ገታ አድርገው እኚህን አባት ቀርበው የለቅሶአቸውን ምክንያት ለመጠየቅ ተገደዱ ። መነኩሴውም እንዲህ ሲሉ ከዕንባ ጋር ነገሩአቸው ። ትናንት ማታ ከሰርክ ጸሎት በኋላ እንደተለመደው ቤተ ክርስቲያኑን ልቆልፍ ስል ከተክለ ሃይማኖት መቅደስ ውስጥ ጢስ ሲወጣ ተመለከትሁ ። ምናልባት የሚነድ ነገር ይኖር ይሆናል ብዬ ወደ ውስጥ ስገባ መቅደሱ በዕጣን ጢስ ተሞልቷል ። ምንም የሚነድ ነገር ግን የለም ። በነገሩ ተገርሜ ቤተ ክርስቲያኑን ቆልፌ ሔድኩ ። ለካስ አባታችሁ እናንተ ዛሬ እንደምትመጡ አውቀው መቅደሱን አጥነው እየጠበቁአችሁ ነበር !! አሏቸው ። #የኢትዮጵያ_ቤተ_ክርስቲያን_ከመላእክት_ጋር_የዘመረ_ቅዱስ_ያሬድን #ከካህናተ_ሰማይ_ጋር_ያጠነ_ተክለ_ሃይማኖትን_ያፈራች_ቤተ_ክርስቲያን #ናት ። #ከግዮን_ወንዝ_መጽሐፍ_የተወሰደ
5004Loading...
04
https://t.me/mekanehyawan2016
5320Loading...
05
Media files
4991Loading...
06
Media files
7161Loading...
07
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ግንቦት ፳፩ ቀን ፳፱፲ወ፮ ዓ/ም ባደረገው የጠዋቱ የግንቦት ርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ሰባት አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በመወያያ አጀንዳ አርቃቂነት ሰየመ። በዚሁም መሰረት በመወያያ አጀንዳ አርቃቂነት የተሰየሙት ሰባት አበው ሊቃነ ጳጳሳት ሕገ ቤተ ክርስቲያን በሚያዘው መሰረት ከቋሚ ሲኖዶስ ለምልአተ ጉባኤ እንዲቀርቡ የተመሩ እና ተጨማሪ የሚባሉ አጀንዳዎችን በመቅረጽ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የማስጸደቅ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴነት የተመረጡት አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚከተሉት ናቸው። 1.ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ 2.ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ 3.ብፁዕ አቡነ ማርቆስ 4. ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ 5. ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል 6. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ 7. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ምንጭ ኢኦቴቤ ሕዝብ ግንኙነት
7631Loading...
08
Media files
4310Loading...
09
በመጨረሻም ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት በእግዚአብሔር ፈቃድ የተጀመረ መሆኑን በመንፈስ ቅዱስ ስም እናበስራለን ፡፡ መልካም ጉባኤ ያደርግልን! እግዚአብሔር አምላካችን ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!! ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!! አሜን፡፡ አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ግንቦት ፳፩ ቀን !፻0፮ ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
5890Loading...
10
#መልእክተ_ቅዱስ_ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! - ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የሰሜን ጎጃምና የባሕር ዳር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ - ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት! እግዚአብሔር አምላካችን በቤተ ክርስቲያን ላይ በየጊዜው የሚደርሰውን ፈተና በማስቻል ለዚህ ሲኖዶሳዊ ምልአተ ጉባኤ እንኳን በሰላም አደረሰን! ‹‹አስተብቊዓክሙ አኃዊነ በስሙ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ትበሉ ኵልክሙ አሐደ ቃለ ወአሐደ ነገረ ወትኩኑ ፍጹማነ ወኢትትፋለጡ ወሀልዉ በአሐዱ ምክር ወበአሐዱ ልብ፤ ወንድሞች ሆይ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ፣ በአንድ ልብና በአንድ ሐሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ›› (፩ቆሮ ፩፥፲)፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን መልእክት ለቆሮንቶስ ሰዎች ለመጻፍ ሲያስብ አንድ ዓቢይ ምክንያት እንዳለው ከመልእክቱ ይዘት መረዳት ይቻላል፤ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖች አንድነትንና ሰላምን ፍቅርንና መተባበርን ከምትሰብከው ወንጌለ መንግሥተ እግዚአብሔር ወጥተው ብዙ ርቀት ሂደዋል፤ አንድነቱ፣ ኅብረቱ መረዳዳቱ መተጋገዙና መተባበሩ ከመካከላቸው ጠፍቶአል፤ ሌላው ቀርቶ ቅዱስ ቊርባንን ለመቀበል በሚሰበሰቡበት ጊዜ እንኳ የሀብታምና የድሀ የሚል ክፍፍል ተፈጥሮ ቤተ ክርስቲያኗን አደጋ ላይ ጥሎአል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን እና ይህንን የመሳሰለ ፈተና በቆሮንቶስ ቤተ ክርስቲያን ሥር እየሰደደ መምጣቱን በእጅጉ አሳስቦታል፤ ይህ የሰላምና የአንድነት ጠንቅ የሆነው የመለያየት አዝማሚያ በጣም ሰፍቶ ቤተ ክርስቲያንን ከማፍረሱ በፊት በትምህርት በምክርና በተግሣጽ ማረም እንዳለበት ቅዱስ ጳውሎስ ተገንዝቦአል፤ እሱ ራሱም በአካል በመካከላቸው ተገኝቶ ሊያስተካክላቸው ፈቃደኛ ነበረ፤ ነገር ግን እሱ በዚህ ጊዜ በሮም ውስጥ እስር ቤት ላይ ስለነበረ አልቻለም፤ የነበረው አማራጭ በጽሑፍ ማስተማርና መምከር ነውና፤ ይህንን መልእክት ጽፎላቸዋል፡፡ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት! ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዘላቂው የቤተ ክርስቲያን ፈተና ሲነግረን ‹‹ወበዓለምሰ ሀለወክሙ ትርከቡ ሕማመ፤ በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ›› እንዳለው ቤተ ክርስቲያን ከፈተና ተለይታ አታውቅም፤ ፈተናውም ከተወሰነ አቅጣጫ ብቻ የሚመጣ ሳይሆን ከብዙ አቅጣጫ ይከባታል፤ የቤተ ክርስቲያን መከራ ከውጭ ብቻም አይደለም ከውስጥም እንጂ፤ ከባዕድ ብቻም አይደለም ከወዳጅም እንጂ፣ የወዳጅ ፈታኝ እንደሚብስም ታውቆ ያደረ ነገር ነው፤ ባዕዳውያን አይሁድ ጌታን ይዘው የገደሉ የውስጥ ሰው የሆነው ይሁዳ በሰጣቸው ምልክት ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች፤ እንደተነገረው የውጭው ፈተና ባይቀርላትም ከሱ በላይ ግን በውስጧ የሚነሡ ፈተናዎች ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት ሆነውባታል፤ ከጥንት ጀምሮ የነበረ፣ በእግዚአብሔር ቃል የተቃኘ፣ የጸሊአ ሢመትና የጸሊአ ንዋይ መንፈሳዊ ባህሏ ተዘንግቶአል፤ በምትኩም ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤ መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋል፣ ሃይማኖታችንንና ባህላችንን የማይወክሉ ኃይለ ቃላት፣ ኃላፊነት በጐደለው አገላለጽ እየተሰነዘሩ በጎቻችንን አስበርግገዋል፤ ድርጊቶቹ በበጎቻችን ዘንድ የነበረንን ተሰሚነትና ተደማጭነት ሊቀንሱብን እየተንደረደሩ ነው፡፡ እነዚህና እነዚህ የመሳሰሉ ክሥተቶች በውስጣችን ሥር በሰደዱ ቁጥር ጉዳትን እያስከተሉ ነው፤ ሰዎች ከኦርቶዶክሳዊ ቀኖና እና ሥርዓት ባፈነገጠ መልኩ ራስን በራስ የመሾም አባዜ እየተለማመዱ ነው፤ እሽቅድምድሙም በዚህ ዙሪያ አይሎአል፤ በአጠቃላይ የቆሮንቶስ ክርስቲያኖችን የፈተነ መለያየት በቤተ ክርስቲያናችንም ብቅ ጥልቅ እያለ እየፈተነን ነው፤ የፈተናው መንሥኤ ውጫዊ ሳንካ ባይጠፋበትም የውስጣችን ሰዎች ለሱ ምቹ ሆነው መገኘታቸው አልቀረም፤ በመሆኑም ቤተ ክርስቲያናችን በዚህ ፈተና የማይናቅ ጉዳት እየደረሰባት ነው፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ ሰላምዋና አንድነቷ ጥያቄ ላይ ወድቆአል፡፡ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት! በሀብተ መንፈስ ቅዱስ ወልደን፣ በሀብተ ክህነት ሹመን፣ በመዐርገ ምንኩስና አልቀን በቤተ ክርስቲያን ኃላፊነት ያስቀመጥናቸው ሰዎች በውኑ ‹‹እርስ በርስዋ የምትለያይ ቤት… የሚለውን አምላካዊ አስተምህሮ እንዴት ዘነጉት? ወይስ ድሮውንም ሳያውቁት ነው ኃላፊነቱ የተሰጣቸው? ወይስ ደግሞ ሆን ብለው ቃሉን ቸል ብለውታል? ሁሉም ውሉደ ክህነት ለዚህ መልስ መስጠት ይጠበቅበታል፤ በመልካም አስተዳደርና በቂም በቀል እያሳበቡ ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም ብሎም ለማፍረስ መሮጥ በማናቸውም መመዘኛ ሚዛን አይደፋም፤ ውሃም አያነሣም፡፡ ችግር ሲኖር በመወያየት በጥበብና በሕግ ማረም እንጂ የጋራ ችግርን ለተወሰነ አካል በመለጠፍና እሱን ብቻ ተጠያቂ በማድረግ ንጹህ መሆን አይቻልም፤ ሁሉም ጓዳው ቢፈተሽ ከዚህ የተለየ ነገር አይገኝም፤ አንድነትንና ሰላምን ግቡ ያደረገ ግምገማን መገምገም፣ መወያየትና መመካከር፣ ሕግንና ሥርዓትን ማእከል አድርጎ መሥራት ተመራጭ መፍትሔ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ባለፉት ዓመታት አስከፊ በደል ተፈጽሞአል አሁንም አልቆመም፤ ይሁን እንጂ በደል ዛሬ ብቻ የተጀመረ አድርገን አናስብ፤ ይብዛም ይነስ በደል ፊትም ነበረ፤ ዛሬም አለ፤ ነገም የተለየ ነገር ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በደልን በካሣና በዕርቅ በይቅርታና በምሕረት መዝጋት፣ ተመሳሳይ በደል እንዳይፈጸም አስተማማኝ የሆነ ተቅዋማዊ ሥርዓትን ማበጀት መልካም ፈሊጥ ይሆናል፤ በደልንና ጥፋትን ምክንያት አድርገን እስከ ዘለቄታው መለያየትን መምረጥ ግን ራስን በራስ መጉዳት ይሆናል፤ ስለዚህ ይህ ቅዱስ ጉባኤ በዚህ ዙሪያ በስፋትና በጥልቀት በመወያየት ሁሉንም ሊያስማማ በሚችል መልኩ ወደ ሰላምና ዕርቅ ሊያደርስ የሚችል ስራ መስራት ይኖርበታል፡፡ ብፀዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖስ አባላት! የማኅበረ ሰባችን ችግር በቤተ ክርስቲያን ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ በሀገር ደረጃ እየቀጠለ ያለው አለመግባባትም ለጠቅላላ ማኅበረ ሰባችን ፈተና ከሆነ ውሎ አድሮአል፤ የቤተ ክርስቲያናችን ፈተና ምንጭ ከሆኑትም አንዱና ዕድል ሰጩ ይህ ሀገራዊ አለመግባባት ነው፤ በዚህ አለመግባባት ምክንያት ገዳማውያን መነኮሳት፤ መምህራን ካህናት ምእመናን አብያተ ክርስቲያናት ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ በሰላም ወጥቶ መግባትም አጠራጣሪ ሆኖአል፤ ይህንን ችግር ለመፍታት የሚደረግ ጥረትም ጎልቶ አይታይም፡፡ በመሆኑም ይህ ክሥተት እውን ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ችግር በራሳችን መፍታት የማንችል ሰዎች ነን ወይ? ለኛስ ከኛ የበለጠ ማን ይመጣልናል? የሚለውን ጥያቄ ልናነሣ ግድ ነው፤ ስለዚህ ለሀገር ህልውናና ድኅነት የሚበጅ ነገር እንዲመጣ ቤተ ክርስቲያን ባላት ሃይማኖታዊና ሰብአዊ ኃላፊነት ጠንክራ መስራት ይጠበቅባታል፤ ከዚህ በተረፈ ይህ ዓቢይ ጉባኤ ወሳኝና ወቅታዊ እንዲሁም ሐዋርያዊና ቀኖናዊ በሆኑ የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ለቤተ ክርስቲያንና ለሀገር የሚበጁ ነገሮችን በማየት ጠቃሚ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፍ በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡
5080Loading...
11
Media files
4180Loading...
12
#ግንቦት_21 #ደብረ_ምጥማቅ ግንቦት ሃያ አንድ በዚች ዕለት አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ ፊቷ በግልጥ ስለመታየቱ የክርስቲያን ወገኖች ሁሉም ታላቅ በዓልን ያደርጋሉ። እርሷም በልጅዋ የመለኮት ብርሃን የተጐናጸፈች ናት በዙሪያዋም የመላእክት ሠራዊት የመላእክት አለቆችም በየማዕረጋቸው ክንፋቸውን ዘርግተው ይቆሙ ነበር ይጋርዷታልም። ሱራፌልም ማዕጠንታቸውን ይዘው ለንግሥዋ ገናናነት ይሰግዳሉ በየስግደታቸውም እንዲህ እያሉ ያመሰግኗታል። አብ በሰማይ ሁኖ ተመለከተ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም አንድ ልጁንም ልኮ ከአንቺ ሰው ሆነ። ሁለተኛ ሰማዕታትም በየማዕርጋቸው ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው እየመጡ መጀመሪያ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአምባላይ ፈረሱ ወርዶ ይሰግድላታል እንዲሁም ባልንጀሮቹ ሰማዕታት መጥተው ይሰግዱላታል ። ከእርሱ በኋላ የሚመጣው በዱሪ ፈረስ የሚቀመጥ ይህ መርቆሬዎስ ነው። ከዚህም በኋላ ሰማዕታት ሁሉ በመከታተል መጥተው ይሰግዱላታል ምስጋናም ያቀርቡላታል። ሁለተኛም ደግሞ የጻድቃን አንድነታቸው መጥተው በፊቷ ሰግደው ይመላለሳሉ። ሄሮድስ የገደላቸው ሕፃናትም መጥተው ይሰግዱላታል በፊቷም እየዘለሉ አንዱ በአንዱ ላይ እየዘለለ በመተቃቀፍም ይጫወታሉ የተሰበሰቡትም በአዩ ጊዜ ደስታ ይመላባቸዋል በሰማይም ያሉ ይመስላቸው ነበር። እናትና አባቱም የሞቱበት ቢኖር ወይም ከዘመዶቹ ወይም ባልንጀራዉ ቅድስት ድንግል እመቤቴ ሆይ ዕገሌን አሳዪኝ ብሎ በሚለምናት ጊዜ ቀድሞ በነበረበት መልኩ ያን ጊዜ ታመጣዋለች። ደግሞ መሀረባቸውን ወደላይ ይወረውሩላታል የወደደችውንም በእጇ ተቀብላ መልሳ ትጥልላቸዋለች ለበረከትም በየጥቂቱ ይካፈሉታል። እንዲህም አምስት ቀን ሁሉ ክርስቲያንም እስላሞችም አረማውያንም ያይዋታል። ወደ ቤታቸውም ለመሔድ ሲሹ በፊቷ ሰግደው ይሰናበቷታል እርሷም ትባርካቸውና ይመለሳሉ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ለአባት እናቶቻችን የተገለጠች እመቤታችን ለእኛም በረድኤት ትገለጥልን ጣዕመ ስሟ በአንደበታችን ጣዕመ ፍቅሯ በልባችን ይደርብን! #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
4321Loading...
13
#ደብረ_ምጥማቅ ፦ ከሠላሳ ሶስት የእመቤታችን በዓላት አንዱ ነው #ግንቦት_21 ቀን የሚከበረው ይህ የእመቤታችን በዓል ደብረ ምጥማቅ በምትባል ቦታ የወርቅ ወንበር ላይ ተቀምጣ ለአምስት ቀን የታየችበት ሲሆን በዚህ ቀን በግብጽ ደብረ ምጥማቅ በተባለ ቦታ በተሰራች ቤተክርስቲያን እመቤታችን ጻድቃንን መልአክትን አስከትላ ተገለጽላቸው ነበር ። እመቤታችን በስደት ሳለች ጌታ በዚህ ቦታ በስምሽ ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል ስሙንም ደብረ ምጥማቅ ይሉታል ብሎ ነግሯት ነበር ይኸውም አልቀረም በዚሁ ቦታ በእመቤታችን ስም ቤተ ክርስቲያን ታንጾ ስሙ ደብረ ምጥማቅ ተብሏል ። በዚህ ዕለት እመቤታችን ከፀሐይ ሰባት እጅ አብርታ ከጉልላቱ ላይ በመንበር ብርሃን ተቀምጣ መላእክት ሊቃነ መላእክት ከበው ሲያመሰግኗት ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት እጅ ሲነሣት ታይታለች እስከ አምስት ቀንም ምእመናኑን አረማውያኑን አንድ ወገን አድርጋ ስትባርክ ሰንብታለች ከዚህም በኋላ ምእመናንም አረማውያንም በየዓመቱ እነዚህን ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 25 ለአምስት ዕለታት በደብረ ምጥማቅ ተሰብስበው የሚያከብሩ ሆነዋል ። . #ለኛም_ለልጆቿ_በሕይወታችን_ሁሉ . #እየተገለጠች_በረድኤት_በበረከት_ትባርከን !!!
57414Loading...
14
እግዚአብሔር ሲቀጣን "አንድ ሐኪም አእምሯቸውን የሳቱ ሰዎች ቢሰድቡት፥ ስድባቸውን ከቁም ነገር አይቆጥረውም፡፡ እንዲህ አእምሯቸውን እንዲስቱ ያደረጋቸውን ምክንያት ያስወግድላቸው ዘንድ ይተጋል እንጂ፡፡ 'ሰድበውኛል' ብሎ የራሱን ጥቅም አያይም፤ የሕሙማኑን እንጂ፡፡ በጥቂቱም ቢኾን ሻል ካላቸውና ራሳቸውን መግዛት የሚችሉ ከኾነም እጅግ ደስ ይሰኝባቸዋል፡፡ ውስጡ በፍጹም ሐሴት ይሞላል፡፡ መድኃኒት መስጠቱን በፊት ከሚያደርግላቸው ይልቅ ተግቶ ይሰጣቸዋል፡፡ 'ከዚህ በፊት ሰድበውኛልና ልበቀላቸው' ብሎ በፍጹም አያስብም፡፡ ይበልጥ እንዲጠቀሙና ወደ ቀድሞ ጤናቸው ይመለሱ ዘንድ ተግቶ ይሠራል እንጂ፡፡ "እግዚአብሔርም እንደዚህ ነው፡፡ ምንም እንኳን እጅግ ጥልቅ በኾነ ኃጢአት ውስጥ ብንወድቅም፥ ኹሉንም ነገር የሚያደርገው እኛን ከመቅጣት አንጻር አይደለም፤ የሚቀጣን ስለ ሠራነው የኃጢአት ዓይነት አይደለም፡፡ ከዚህ ሕመማችን እንድንፈወስ ብሎ ነው እንጂ፤ በዚሁ መንገድ ሊመለሱ ይችላሉ ብሎ በማሰብ ነው እንጂ፡፡" (ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ፥ ወደ ቴዎድሮስ፥ ገጽ 36) ተወዳጆች ሆይ! እግዚአብሔርን ከማሳዘን ውጪ ምንም ይኹን ምን [አንፍራ፡፡] ሠለስቱ ደቂቅ የሚንበለበል እሳት በፊታቸው ቢያዩም ናቁት፤ ኃጢአትንም ብቻ ፈሩ፡፡ በእሳቱ ቢቃጠሉ ምንም የሚያስፈራቸው ነገር እንደሌለ፣ ፈሪሐ እግዚአብሔር ባይገኝባቸው ግን እጅግ የከፋ ጉስቁልና እንደሚያገኛቸው ያውቃሉና፡፡ ምንም ሳንቀጣ ብንቀርም እንኳን እጅግ ትልቁ ቅጣት ግን ኃጢአት መሥራት ነው፤ በሌላ መልኩ ደግሞ ምንም ያህል ቅጣት ቢያገኘንም እጅግ ትልቁ ክብርና ጸጥታ ግን በተጋድሎና በምግባር ሕይወት መኖር ነው፡፡ እግዚአብሔር ራሱ፡- “በደላችሁ በእናንተና በእኔ መካከል አልለየችምን?” ብሎ እንደ ተናገረ ኃጢአት ከእግዚአብሔር ይለየናል (ኢሳ.59፡2)፡፡ ቅጣት ግን “እግዚኦ አምላክነ ሰላመ ሀበነ እስመ ኵሎ ወሀብከነ - አቤቱ አምላካችን ኹሉን ሰጥተኸናልና ሰላምን ስጠን” እንደ ተባለ ዳግመኛ ወደ እግዚአብሔር እንድንመለስ ያደርገናል (ኢሳ.26፡12)፡፡ እንበልና አንድ ሰው ቁስል ወጣበት፡፡ የሚያስፈራው የትኛው ነው - የሚሰፋው ቁስል ወይስ የቀዶ ጥገና ሐኪሙ ቢላ? ብረቱ ወይስ እጅግ እየባሰበት ያለው ቁስል? ኃጢአት የሚሰፋ ቁስል (Gangrene) ነው፤ ቅጣት ደግሞ የቀዶ ጥገናው ሐኪም ቢላ ነው፡፡ ያልፈረጠ የሚሰፋ ቁስል ያለው ሰው ሕመሙ እንዳለበትና ለወደፊቱም የማያፈርጠው ከኾነ ሥቃዩ እየባሰበት እንደሚኼድ ኹሉ፥ ቅጣት ያላገኘው ኃጢአተኛ ሰውም ከሰዎች ኹሉ ይልቅ ጎስቋላው ሰው እርሱ ነው፤ ለወደፊቱ ጭራሽ ቅጣትና መከራ የማያገኘው ከኾነ ደግሞ ከአሁኑ ይልቅ እጅግ ጎስቋላው ሰው እርሱ ነው፡፡ የጣፊያ ወይም የሆድ በሽታ ያለባቸው ሰዎች ብዙ መብል ቢበሉ፣ ቀዝቃዛ መጠጦችን ቢጠጡ፣ የተለያዩ ዓይነት ጣፋጭና ቅመማ ቅመም የበዛባቸው መብሎችንም ቢወስዱ ይህ ድሎት ሕመማቸው እንደሚጨምረውና እንደ ሕክምናው ሕግ ራሳቸውን ከመብሉም ከመጠጡም በመጠኑ ቢወስዱ ግን የመዳን ተስፋ ሊኖራቸው እንደሚችል ኹሉ፥ በክፋት ዓዘቅት የሚኖሩ ሰዎችም ቅጣት ካገኛቸው በጎ ተስፋ ሊኖራቸው ይችላል፤ ከክፋታቸው ጋር አብረው ዝንጋዔንና ድሎትን የሚጨምሩበት ከኾነ ግን ሆዳቸውን ከሚያማቸው ሰዎች በላይ እጅግ ጐስቋሎች ሰዎች ናቸው - ደዌ ዘነፍስ ከደዌ ዘሥጋ ይልቅ የከፋ ነውና፡፡ ተመሳሳይ ኃጢአት እያላቸው አንዳንዶቹ በማጣትና በብዙ ሕመም ሲሠቃዩ፣ ሌሎቹ ግን እስኪበቃቸው ድረስ እየጠጡና እየተስገበገቡ የሚበሉ እየተመቻቸውም በደስታ የሚኖሩ ሰዎችን ብትመለከት እነዚያ መከራ የሚቀበሉት የተሻሉ እንደ ኾኑ አስተውል፡፡ በእነዚህ መከራዎች የተወገደላቸው የፈንጠዝያ ሕይወት እሳት ብቻ ሳይኾን ሊመጣ ወዳለው ፍርድና አስፈሪ ዙፋን ሲኼዱም ከቀላል ዕረፍት ጋር አይደለምና፤ ስለኾነም እዚያ ሲኼዱ ከኃጢአታቸው የሚበዛውን በዚህ ዓለም ባገኛቸው ሥቃይ አስወግደው ነው፡፡ #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
7343Loading...
15
#የጌታ_እቅፍ "#ወደ_ጌታ_እቅፍ_ዘንበል_ያለው_ሐዋርያ" ወደ ጌታ እቅፍ ዘንበል ያለው ሐዋርያ ዮሐንስ መሆኑን በመጽሐፉ የገለጸው አውሳብዮስ የተባለው የታሪክ ጸሐፊ ነው። ወደ ጌታ እቅፍ ዘንበል ማለት ግን እንዴት ይሆን? የጌታ እቅፍ ሙቀቱ እንደ ምን ይሆን? ይህን ሊመልስ የሚችለው እቅፉን የሚያውቀው ሐዋርያውና እመቤታችን ይመስሉኛል። ገነት፣ መንግሥተ ሰማያትን በአብርሃም እቅፍ እንመስላታለን - በሞተ ሥጋ የተለየንን "ነፍሱን በአብርሃም እቅፍ ያሳርፍልን" እንድንል። ዮሐንስ ግን ወደ ጌታ እቅፍ ዘንበል አለ። የአብርሃም እቅፍ ገነትን ከመሰለ፣ ዮሐንስ ያረፈበት የጌታ እቅፍ እንዴት ያለ ይሆን? ሲከፋንና የሚጎረብጥ ስሜት ውስጥ ስንሆን እቅፋቸውን የምንመኘው ሰዎች አሉ። ሽጉጥ ብለንባቸው ብንደበቅ የምንመርጣቸው። በእቅፋቸው ውስጥ ሆነን ብናነባ የምንፈልጋቸው። ከፍቅራችን ጽናት የተነሣ ከእቅፋቸው መለየት የማንፈልግ ሰዎች ይኖሩናል። ዮሐንስ ግን መጽናናትን ፈልጎ ይሆን? ወይስ ከፍቶት? የጌታው እቅፍ ውስጥ የሸጎጠው ምን ይሆን? በርግጥ ቁጹረ ገጽ ነውና ይህ ቢያስኬድም፣ ያኔ የጌታ መከራ ገና በመሆኑ: ወደ ጌታው እቅፍ ዘንበል ያደረገው ፍቁረ እግዚእነቱ ነው እንላለን። የፍቅሩ ጽናት ከእቅፉ ከተተው። ያ የጌታችን እቅፍ ግን ምን ያህል ያጽናና!? ምን ያህል ያስደስት!? ሕፃን ልጅን እናትና አባቱ "ትወደኛለህ?" ቢሉት "አዎ" ይላቸዋል። "እንዴት አድርገህ?" ቢሉት የመውደዱን መጠን የሚገልጸው በቻለው ኃይሉ ሁሉ ዕቅፍ በማድረግ ነው። ያለ የሌለ ኃይሉን ተጠቅሞ በዕቅፉ ለማስጨነቅ ይሞክራል። እመቤታችን ጌታን በልጅነቱ ስታጫውተው መውደዱን እንዴት ገልጾላት ይሆን? እንዴትስ አቅፏት ይሆን? አምላክ እናቱን ሲያቅፍስ እንዴት ይሆን? እርሷስ ዕለት ዕለት አቅፋ ስታሳድገው አምላክን በእናትነት ማቀፍ እንደ ምን ይሆን? ስምዖን አረጋዊ ጌታን ለቅጽበት ቢያቅፈው ከዚያ በኋላ መሞትን ተመኘ። ጌታን ማቀፍ ማዳኑን እንደ መቅመስ መሆኑን ነገረን። ከእናቱ እቅፍ ተቀብሎ አቀፈውና "...እግዚአብሔርንም እየባረከ እንዲህ አለ፦ 'ጌታ ሆይ፥ አሁን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ፤ ዓይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋልና"። (ሉቃስ 2:28-31)። (ልጅን ከእናቱ እቅፍ ሲያወጡት እንዲያለቅስ፣ ስምዖን ከእናቱ እቅፍ ሲወስደው ሕፃኑ ጌታ አይኑን ወደ እናቱ እያንከራተተ አልቅሶ ይሆን?) ስምዖን አንድ ጊዜ አቅፎትና አይቶት ከዚህ ምድር መለየትን ከለመነ፣ ዕለት ዕለት አቅፋ ዓይን ዓይኑን የምታየው እመቤታችን ገናናነቷ ምን ይረቅ!? ምን ይደንቅ!? ኧረ በጌታ የታቀፈ የዚህ ሐዋርያ እቅፍ፣ ጌታ ሲያቅፋት ያደገች፣ እርሷም ስታቅፍ ያሳደገችው የድንግል እቅፍ ምን ይመስል ይሆን!? ቅዱስ ያሬድን አብልጠው የሚወዱት አንድ ሊቅ "እኔ ስሞት እንዲያው ቢፈቅድልኝ በአብርሃም እቅፍ ሳይሆን በቅዱስ ያሬድ እቅፍ ብሆን" ብለው ተመኙ። አንባቢ ሆይ! ማድላት እንዳይመስልህ፤ ዘይቤ ነው። እኔ ደግሞ ዛሬ ይህን ሳሰላስል የዮሐንስንና የድንግልን እቅፍ ተመኘሁ። እንኳን ለውዱ ሐዋርያ በዓል አደረሰን! በዲያቆን ሕሊና በለጠ #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
1 1202Loading...
16
Media files
8230Loading...
17
ሰገደ ላቲ በመጋቤ ምሥጢር ሰሎሞን https://youtube.com/watch?v=npQ9IXNTn-E&feature=shared
9050Loading...
18
Media files
7281Loading...
19
#አቡነ_አረጋዊ እንኳን ለጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ የመታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን !!! ታላቅ የክርስትና አባት ሲሆኑ የተወለዱት በሮም ከተማ ከአባታቸው ንጉሥ ይስሐቅ እና ከእናታቸው ቅድስት እድና ነው። ስማቸውም ዘሚካኤል አሏቸው። ቤተሰቦቻቸው እግዚአብሔርን የሚፈሩና በቅድስና የሚኖሩ ነበሩ። ለአቅመ አዳም ሲደርሱ ሚስት ቢታጭላቸውም ለክርስቶስ ከነበራቸው ፍቅር የተነሳ ትዳር መመስረትን ትተው ወደ ገዳም ገቡ። የምድር መንግሥት ጠፊ ነው፣ የማትጠፋዋን ዘለዓለማዊት መንግሥት መውረስ እፈልጋለሁ በማለት በ14 ዓመታቸው በአባ ጳኩሚስ እጅ የምንኩስናን ልብስ ለበሱ። የመመንኮሳቸው ዜና ሲሰማ በድርጊታቸው የተማረኩ 7 ቅዱሳን ከቂሳርያ እርሳቸው ወዳሉበት ገዳም በመምጣት የምንኩስናን ትምህርት ተማሩ። እናታቸውም የልጃቸውን መመንኮስ በሰሙ ጊዜ መንኩሰው ወደ ሴቶች ገዳም ገቡ። መነኮሳትም መሪ አደረጓቸው፤ ብስለታቸውንም በማየት ስማቸውን አቡነ አረጋዊ አሏቸው፤ ትርጉሙም "ብልህ አዋቂ" ማለት ነው በኋላም ከሁለት ደቀ መዛሙርታቸው ጋር ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ከተመለከቱ በኋላ ወደ ሮም ተመለሱ። ስምንት ቅዱሳንንም ይዘው (ከሮምና ከመካከለኛው ምስራቅ ወደ ኢትዮጵያ ከፈለሱት ዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ አቡነ አረጋዊ ናቸው) ተመልሰው በመምጣት መኖር ጀመሩ። ቅዱሳኑ ወንጌልን ለማስፋት በማሰብ በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ሲመዳደቡ አቡነ አረጋዊ ወደ ትግራይ ሄዱ። እነዚህ ዘጠኙ ቅዱሳን ወንጌልን በመላ ሀገሪቷ አሰራጩ። አቡነ አረጋዊም በደብረ ዳሞ በዓታቸውን አደረጉ። ወደ ደብረ ዳሞ በወጡ ጊዜ በእግዚአብሔር የታዘዘ ዘንዶ ወገባቸውን ይዞ አደረሳቸው። በዚያም ሲጋደሉ ከቆዩ በኋላ በተራራው ላይ ቤተክርስቲያን በመስራት ለአገልግሎት እንዲስፋፋ አደረጉ። ጻድቁ አባታችን በዚያው በበዓታቸው ሳሉ ደቀ መዛሙርቱን "ከዛሬ ጀምሮ በሥጋ አታዩኝም" በማለት ተሰናበቷቸው። ጥቅምት 14 ቀን በ99 ዓመታቸው ተሰወሩ፤ በበዓታቸውም ከመቋሚያና መስቀል በስተቀር ምንም አልተገኘም። የጻድቁ አባታችን በረከትና ምልጃ አይለየን። እግዚአብሔር የቃልኪዳናቸው ተካፋይ ያድርገን በረከታቸውም አይለየን ! #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
9958Loading...
20
#አነ #ውእቱ #ሩፋኤል #አሐዱ #እምሰብዓቱ #ሊቃነ_መላእክት ከሰባቱ የመላእክት አለቆች አንዱ እኔ ሩፋኤል ነኝ ( መጽ ቀሌምንጦስ) ጌታ በደብረዘይት ደቀመዛሙርቱን ሰብስቦ ጉባኤ ዘርግቶ እያሰተማረ ባለበት መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል መጣ ጌታም ስምህን ለደቀመዛሙርቴ ንገራቸው አለው የመጽሐፈ ቀሌምንጦስ ጸሐፊ ያንጊዜ ነው ስሙን እስከትርጓሜው የነገራቸው ይላል በረከቱ ይደርብን የቁስጥንጥንያው ሊቀጳጳስ ካሳነጻቸው ሰባት አቢያተ ክርስቲያናት አንዱ የቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ነው ቤተክርስቲያኑ የታነጸው ደሴት በሚመስለው በአሳ አንበሪው ጀርባ ላይ ስለነበር በቅዱሱ አባት አባ ቴዎፍሎስ ተባርኮ አገልግሎት ሲጀመር አጋጣሚው ተጠቅሞ አሳ አንበሪውን ሰይጣን እንዲናወጥ በማድረግ ሊያጠፋቸው ሲል ያዳናቸው መልአኩ እንደሆነ ድርሳኑ ይናገራል ቤተክርስቲያንዋን እና በውስጥዋ የነበሩትን አገልጋዮች ምዕመናን ከመሰጠም ታድጓቸዋል ዛሬም በውስጥም በውጭም ሁነው እንደ አሳ አንበሪው ቤተክርስቲያንን ከሚያናውጧት አገልጋይ ከሚመስሉ ቁማርተኞች አጋንንት ቤተክርስቲያንን ይታደግልን ቅዱስ ሩፋኤል ሰባት ዓመት ሙሉ እንደተራ ሰው ያገለገለው ከዓይነ ስውርነት የፈወሰው የእግዚአብሔር ሰው ቅዱስ ጦቢያ ስለቅዱስ ሩፋኤል ምልጃና ተራዳኢነት በሰፊው ጽፏል ጦቢያን የፈወሰ የቅዱሳን ባለሟል ቅዱስ ሩፋኤል ሁላችንም በአማላጅነቱ ይጠብቀን ከሚያናውጠን ከእርስ በእርስ የጦርነት ማዕበል ይታደገን! #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
9515Loading...
21
Media files
8492Loading...
22
#ግንቦት_12 #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ባሕረ ምስጢራት የሆነ የሰውን ፊት አይቶ የማያደላ "መምህር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ" (በርሱ ዘንድ ንጉሥ፣ ሐብታም፣ ደሃ፣ ነዳይ እኩል ነውና)፣ አፈ በረከት፣ አፈ መዐር (ማር)፣ አፈ ሶከር (ስኳር)፣ አፈ አፈው (ሽቱ)፣ ልሳነ ወርቅ፣ የዓለም ሁሉ መምሕር፣ ርዕሰ ሊቃውንት፣ ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)፣ የሐዲስ ኪዳን ዳንኤል፣ ሊቀ ጳጳሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)፣ ጥዑመ ቃል... እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እረፍቱ ነው። #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ሲናገር በአንድ ወቅት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ አለ፡ከዕለታት አንድ ቀን በሀገረ ስብከቴ ሥር በነበሩ በሜዲትራኒያን ባሕር በሚገኙ ደሴቶች ውስጥ የሚኖሩ ምእመናንን  ለመጎብኘት አሰብሁ፡፡ ከእኔ ጋር ቀሳውስትንና ዲያቆናትን አስከትዬ በጀልባ ተሳፍሬ ወደ ቆጵሮስ ደሴት ተጓዝሁ፡፡ በደሴቱ ውስጥ ስንዘዋወር የሰው ዱካ ብንመለከትም  ምንም ሰው ማየት አልቻልንም ነበር፡፡ በአሸዋው ላይ ታትሞ የነበረውን የሰው ዱካ ተከትለን ስንጓዝ ካልተፈለፈሉ ዐለቶች የተሠራ ቤተ ክርስቲያን የሚመስል ዋሻ ላይ ደረስን፡፡ ዋሻው በርም ሆነ መስኮት የለውም፡፡ ወደ ውስጥ ስንገባ ልክ እንደ ሰባቱ ደማቅ ከዋክብት እጅግ በጣም አንጸባራቂ ብርሃን ቆመው ከሚጸልዩ ሰባት አባቶች ዘንድ ሲወጣ ተመለከትን፡፡ እኛም ከእነርሱ ጋር ለመጸለይ ባለንበት ቆምን። አባቶች ጸሎታቸውን ከጨረሱ በኋላ ወደ እኛ ዞሩና በፊቴ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ሰገዱ። በመቀጠልም ሰላምታ ሰጡን፡፡ እኔ ዮሐንስም ‘እኔ አባታችሁና ፓትርያርካችሁ ዮሐንስ ነኝ’ አልኳቸው፡፡ ቅዱሳኑ እንደገና ራሳቸውን ዝቅ አድርገው በፊቴ ሰገዱ እና እኔን ደካማውን እንዲህ አሉኝ፡- “የምንወደው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንድትባርከንና እኛም አንተን በማየት እንድንበረታ ወደዚህ አመጣህ” አሉ። እኔም “እባካችሁ ታሪካችሁን ንገሩኝ” አልኋቸው፡፡ ሰባቱ አባቶችም “ከብዙ ዓመታት በፊት ሰባታችንም ከቍስጥንጥንያ ወጥተን በአንድነት ተሰባስበን ሕይወታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምና በአምልኮ ብቻ ለማሳለፍ ወደዚህ ደሴት መጣን፡፡ ከዚህ ደሴት በደረስንበት ዕለት ከባሕሩ ከሚመጣው አስቸጋሪ ነፋስ ራሳችንን ለመከላከል ዋሻዎችን ለመገንባት ዐለቶችን ሰበሰብን፤ በሁለተኛው ቀን ደግሞ ይህን ቤተ ክርስቲያን መሥራት ጀመርን፡፡  በዐለቶች መካከል ከሚበቅለው ሣር እንበላለን፤ ውኃም ከባሕሩ እንጠጣለን፡፡ ቤተ ክርስቲያኑን የከበቡትን እነዚህን የአሸዋ ክምሮች ለማስወገድ ፈልገን ነበር፤ ግን አእምሯችንና አሳባችን ሁሉ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፍቅር ስለተያዘ ጊዜ አጣን” በማለት ታሪካቸውን ነገሩኝ። እኔም “መንፈሳዊ አባታችሁ የት ነው?” ብዬ ጠየቅኋቸው፡፡ ይህን ጥያቄ ከመጠየቄ ወዲያውኑ አንድ ሽማግሌ በትሩን ተደግፎ ወደ እኔ ቀረብ አለና “እኔ የአንተ አገልጋይ ነኝ” አለኝ፡፡ አረጋዊው ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ ራቁቱን ነበረና “ሰውነትህን የምትሸፍንበት ትንሽ ልብስ ትፈልጋለህ?” ስለው እሱም “ጌታ ከክረምቱ ቅዝቃዜ፣ ከበጋው ሙቀት ይከላከልልናል፤ ይጠብቀናልም” በማለት መለሰልኝ፡፡ “ምግብ ያስፈልጋችኋል?” ብዬ ስጠይቀው እርሱም “የሚበቃንን ያህል ከእነዚህ ዕፅዋት እንመገባለን ከዓለም የሆነ ምንም ነገር አያስፈልገንም” በማለት መለሰልኝ፡፡ እኔም “አባቶቼ እባካችሁ ለእኔ እና ስለቤተ ክርስቲያን ደኅንነት ጸልዩ” አልሁት። የእነዚያን ቅዱሳን ባሕታውያን አባቶች በረከት ከተቀበልን በኋላ ዛሬም ዘወትርም ለዘለዓለም ምሥጋና የሚገባውን የምንወደውን ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እያመሰገንን ወደ መጣንበት ተመለስን” ይለናል ቅዱሱ አባታችን ዮሐንስ አፈ ወርቅ። #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
8976Loading...
23
#ግንቦት_12 #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ባሕረ ምስጢራት የሆነ የሰውን ፊት አይቶ የማያደላ "መምህር ወመገስጽ ዘኢያደሉ ለገጽ" (በርሱ ዘንድ ንጉሥ፣ ሐብታም፣ ደሃ፣ ነዳይ እኩል ነውና)፣ አፈ በረከት፣ አፈ መዐር (ማር)፣ አፈ ሶከር (ስኳር)፣ አፈ አፈው (ሽቱ)፣ ልሳነ ወርቅ፣ የዓለም ሁሉ መምሕር፣ ርዕሰ ሊቃውንት፣ ዓምደ ብርሃን (የብርሃን ምሰሶ)፣ የሐዲስ ኪዳን ዳንኤል፣ ሊቀ ጳጳሳት ዘበርትዕ (እውነተኛው)፣ ጥዑመ ቃል... እየተባለ የሚጠራው ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እረፍቱ ነው። ምልጃውና የከበረች ጸሎቱ ከእኛ ጋር ትሁን!
9023Loading...
24
Media files
6741Loading...
25
#ቅዱስ_ሚካኤል #እስራኤል_ዘሥጋን • የመራቸውና የጠበቃቸው • ባህር የከፈለላቸው • ጠላት ፈርዖንን ከነሠራዊቱ ያጠፋላቸው • በአምላኩ ፈቃድ መና ከሰማይ ያወረደላቸው • በለዓም እንዳይረግማቸው ሰይፉን መዞ መርገማቸውን የመለሰላቸው • ለመራገም የሄደው እንዲመርቃቸው ያደረገው ....በዚህም መጋቤ ብሉይ ተብሎ የተጠራው • የባህራንን የሞት ደብዳቤ ወደ ሕይወት የቀየረው • የቅድስት አፎምያን ፈታኝ በሥልጣን የረገጠው ... መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው!!! ቅዱስ ያሬድ "አስተምሕር ለነ ሰአልናከ በዐሠርቱ ወአርባዕቱ ትንብልናከ " ብሎ እንደለመነው.... እኛም እስራኤል ዘነፍስ በቅዱስ ያሬድ ቃል ♥ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ሆይ!♥ ተማጽነንሃል! በአሥራ አራቱ ምልጃዎችህ ማልድልን" እንደ አምላክህ በሆነው ርኅሩህነትህ ከፈጣሪያችን ጋር አስታርቀን ክፉዎን ሁሉ በምልጃህ ተቋቋምልን በጠላቶቻችን የተጻፈብንን የሞት ደብዳቤ ወደ ሕይወት ቀይርልን በልዩ ልዩ ፈተና የሚፈትኑንን አጋንንትን ከአምላክህ በተሰጠህ ሥልጣን እርገጥልን .. እያልን እንለምነዋለን! የቅዱስ ሚካኤል ምልጃ ሁላችንንም በያለንበት ይጠብቀን! #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
7602Loading...
26
. #ተክለ_ሃይማኖት . #የሃይማኖት_ተክል_ተክለ_አብ_ተክለ_ወልድ_ተክለ_መንፈስ_ቅዱስ ༺◉❖═───◉●◉🌹🌹🌹◉●◉────═❖◉༻ #ሐዲስ_ሐዋርያ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት_ዘደብረ_ሊባኖስ እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ የመረጣቸው ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 11 97 ዓ.ም ተወለዱ ። ጸድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ❝ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ ❞ ማለትም ❝ አንዱ አብ ቅዱስ ነው አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው ❞ በማለት የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነዋል ። #አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ከልጅነታቸው ጀምሮ በወላጅ አባታቸው በካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ግብረ ዲቁናን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ሲያጠኑ ቆይተው በ 15 እና በ 22 ዓመታቸው ከእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ከአቡነ ቄርሎስ ( ጌርሎስ ) ዲቁናንና ቅስናን ተቀብለዋል ብፁዕ ወቅዱስ አባታችን ቅድስት ቤ.ክ በወጣትነት ዕድሜያቸው ያገለግሉ እንደነበር በዚህ ይታወቃል ። ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በዚህች ምድር በኖሩባት 99 ዓመት ውስጥ ለአገልግሎት የሚያበቃ ሃይማኖታዊ ትምህርታቸውን ከቀሰሙ በኋላ ወደ ተለያዩ ገዳማት በመዘዋወር ዕውቀታቸውን ያሰፉበትንና ለሐወርያዊ ተልዕኮዎች የተሰማሩባቸውን ጊዜያትና ቦታዎች እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስም የፈጸሙትን ተጋድሎ በአጭሩ የሚከተለውን ይመስላል ። #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ1219-1222 ዓ.ም በተከታታይ ለሦስት ዓመታት ወንጌልን አስተማሩ ቀጥለውም ዘጠኝ ወር በዊፋት አገልግሎታቸውን ፈጸሙ ። #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ12 23-12 34 ዓ.ም ዳሞት በተባለው ስፍራ ወይም በወላይታ ሀገር ለ12 ዓመታት ሕዝቡን በማስተማር ከአምልኮተ ጣዖት ወደአምልኮተ እግዚአብሔር ከገቢረ ኀጢአት ወደ ገቢረ ጽድቅ መልሰዋል ። ቤተ ክርስቲያንንም አንጸዋል። በዚም ሀገር ዲያብሎስ በዛፍ ላይ አድሮ አምላክ ነኝ እያለ ለረጅም ዘመናት ሕዝቡን በማሳት የሚጠቀምበትን ዛፍ በተአምራት ከሥሩ ነቅለው አፍልሰውታል ። #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ1234-1244 ዓ.ም ባለው ጊዜ ደግሞ በእግዚአብሔር ፈቃድና ትእዛዝ ወደ አማራ ሳይንት ወሎ በመሄድ ከአባ በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ገብተው ሥርዓተ ምንኲስናን እየተማሩ ለ 10 ዓመታት የተለያዩ ገቢረ ታምራትን በማድረግ በጉልበት ሥራም ሲያገለግሉኖሩ #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ1244-1254 ዓ.ም አባ ኢየሱስ ሞዐ ወደሚገኙበት ሐይቅ ቅዱስ እስጢፋኖስ ገዳም በቅዱስ ሚካኤል መሪነት ሐይቁን በእግራቸው እንደ ደረቅ መሬት በመርገጥ ወደ ደሴቱ በመግባት የአገልግሎትና የትሩፋት ሥራን በማብዛት የምንኲስናን ተግባራቸውን በመቀጠል ከፍጻሜ አድርሰዋል በአባ ኢየሱስ ሞዓ እጅም የንጽሕና ምልክት የሆነውን የምንኲስናን ቀሚስ ተቀብለዋል ። #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ1254-1266 ዓ.ም ወደ ትግራይ ሄደው ከአቡነ አረጋዊ ገዳም ደብረ ዳሞ ገብተው በጊዜው ከነበሩት አበምኔት ከአባ ዮሐኒ ቆብና አስኬማ ተቀብለው ለ12 ዓመታት በገዳሙ በገድል በትሩፋት መንፈሳዊ ተጋድሎአቸውን ቀጠሉ ። #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ1266-1267 ዓ.ም ለአንድ ዓመት ያህል የትግራይን ገዳማት በሙሉ በመጐብኘት ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ግብፅም በመሄድ በዚያ ያሉ ቅዱሳት መካናትን ጎብኝተው መጥተዋል ። ከዚህ በኋላ ዳዳ በተባለ ስፍራ ይመለክ የነበረውን 75 ክንድ የሚረዝመውን ዘንዶ በጸሎት ኃይል በመስቀል ምልክት አማትበውበት በተአምራት ገድለውታል ። በቦታው ላይ በአርባዕቱ እንስሳ ስም ቤተ ክርስቲያን አንጸው ታቦተ ሕግ አስገብተውላቸዋል ከሴቶችና ከልጆች ሌላ ሦስት ሺህ በጣዖት የሚያመልኩ ወንዶችን አስተምረው መልሰው አጥምቀው አቍርበዋቸዋል ። #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ1267-1289 ዓ.ም ባለው ጊዜ ደግሞ በደብረ ሊባኖስ ካለችው ገዳመ አስቦ ዋሻ በመግባት 8 ጦሮችን ሁለቱን በፊት ፣ ሁለቱን በኋላ ፣ ሁለቱን በቀኝ ሁለቱን ደግሞ በግራ አስተክለው እጆቻቸውን በትእምርተ መስቀል በመዘርጋት የክርስቶስን ሕማምና ሞት ፣ ነገረ መስቀልን በማሰብ በተመስጦ ሌትናቀን ያለማቋረጥ በጾምና በጸሎት በአርምሞ ተወስነው ሲጋደሉ ከቁመት ብዛት የተነሣ ጥር 4 ቀን 12 89 ዓ.ም. አንዲቱ የእግራቸው አገዳ ተሰብራለች ቅዱስ አባታችን በመዓልትና በሌሊት በትጋትና በቁመት በተጋድሎ ብዛት አንዲት የአገዳ እግራቸው ስትሰበር ዕድሜያቸው 92 ዓመት ሆኗቸው ነበር ። #ጻድቁ_አቡነ_ተክለ_ሃይማኖት ፦ ከ1289-1296 ዓ.ም ለሰባት ዓመታት በአንድ እግራቸው በመቆም ያለምግብና ያለውኃ በትኅርምት ሌትና ቀን እንቅልፍ በማጣት እንደ ምሰሶ ጸንተው በተመስጦ በትጋት ለሰው ዘር ሁሉ ድኀነትን ሲለምኑ ኖረዋል ። ከሰባቱ ዓመታት ውስጥ ጥቂት ውኃ የቀመሱት በአራተኛው ዓመት ብቻ ነበር በዚህ ጊዜ ውስጥ ጌታችን ተገልጦላቸው በሰው አእምሮ ሊታሰብና ሊለካ የማይችል ትልቅና ልዩ የመንግሥት አዳራሽ ከሰጣቸው በኋላ የመለኮትን ነገር የሚናገር የእሳት አንደበት ያላቸው የመንግሥት ልብስ አለበሳቸው በመስቀል ምልክት የተጌጡት ሰባት የሕይወት አክሊላትን አቀዳጅቷቸዋል ። #ይኸውም ፦ ስለ ቀናች ሃይማኖትህ፣ሃይማኖትን ለማስተማር መላዋን ኢትዮጵያን ስለመዞርህ ። ከአረማውያን ሕዝብ ጋር በሃይማኖት ስትታገል ደምህን ስለማፍሰስህ ። ወደ ኢየሩሳሌም ወርደህ ልዩ ልዩ የቅዱሳን ቦታዎች ስለመሳለምህ ። በሰባት ዓመታት ቍመት የአንዱ አገዳ እግርህ ስለመሰበሩ። ስለብዙ ጾም ጸሎት ስግደትህ ስለልብህ ንጽሕናና ቅድስና ። በማለት የሕይወት አክሊላትን ካቀዳጃቸው በኋላ ዝክራቸውን በማዘከር መታሰቢያቸውን የሚያደርጉ ሁሉ በዚህ ዓለምም ሆነ በወዲያኛው ዓለም ፍጹም ዋጋና ፍጹም ክብር እንደሚሰጣቸው ጌታችን ታላቅ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል ። ሥጋቸውም ወዴት ይቀበር ዘንድ ሲነግራቸው ❝ እስከ 57 ዓመት ሥጋህ ከዚህ ይቀበራል ከ 57 ዓመት በኋላ ግን ይህች ዋሻ ትናዳላች በዚህም ገዳም አደባባይ በስምህ ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ልጆችህ ሠርተው ሥጋህን አፍልሰው በውስጡ ያኖራሉ ❞ አላቸው ። በመጨረሻም አባታችን ለ10 ቀናት ያህል በተስቦ ሕመም ቆይተው ፈጣሪያቸው የገባላቸውን ቃል ኪዳን ለመነኰሳት መንፈሳውያን ልጆቻቸው ከነገሯቸው በኋላ ( ነሐሴ 24 )ቀን በታላቅ ክብር ዐርፈዋል ። #የቅዱስ_አባታችን_በዓላት_እነዚህ_ናቸው ✟ ኅዳር 24 ቀን ከ 24 ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር በሕይወተ ሥጋ እያሉ የሥላሴን መንበር ያጠኑበት ። ✟ ታኅሣሥ 24 ቀን 11 97 ዓ.ም ልደታቸው ። ✟ ጥር 4 ቀን 12 89 ዓ.ም ደግሞ በጸሎት ብዛት አንድ እግራቸው የተሰበረበት ቀን ነው ( ነገር ግን የዕረፍታቸውን ቀን ይዞ በዚሁ በጥር ወር በ 24 ይከበራ ) ✟ መጋቢት 24 ቀን 11 96 ዓ.ም ፅንሰታቸው ። ✟ በግንቦት 12 ቀን 13 53 ዓ.ም ፍልሰተ ዐፅማቸው ነው ✟ ነሐሴ 24 ቀን 12 96 ዓ.ም ዕረፍታቸው ። . #ጸሎታቸው_በረከታቸው_ረድኤታቸው_ምልጃቸው_በመላው_ሕዝበ_ክርስቲያን_አድሮ_ይኑር_ለዘለዓለም።
96415Loading...
27
Media files
8081Loading...
28
Media files
1 0332Loading...
29
Media files
6322Loading...
30
ስለ ቅዱስ ያሬድ ተናግሬ አልጠግብም አብዝቼ ወደዋለሁ............ #የኢትዮጵያ_ኦርቶዶክስ_ተዋሕዶ_ቤት_ክርስቲያን መንዝራ ዘርዝራ አመሥጥራ የማትጨርሰው ከየዘመኑ ጋር አብሮ የሚጓዝ የዘመን ቅርስ ሀብቷ ነው ቅዱስ ያሬድ ። #ቅዱስ_ያሬድን ድንቅና ልዩ ከሚያሰኙት ምክንያቶች አንዱ በዓለማችን የመጀመሪያው የዜማ ምልክቶች ደራሲ በመሆኑ ነው ። ዜማን ቅርጽ በማስያዝ ሳይጠፋ ከትውልድ ትውልድ እንዲተላለፍ ያደረገ ለሌሎች የዜማ ሊቃውንት ፈር የቀደደ ሊቅ ነው ። #ቅዱስ_ያሬድ ገና የ12 ዓመት ልጅ እያለ በተፈጥሮዋ ትንሽ ከምትባለው ትል የጽናትን ውጤት ተገንዝቦ የሰው ልጅ እየወደቀና እየተነሣ ለውጤት መትጋት እንዳለበት እንዲሁም የሕይወት ስኬት የብዙ ልፋቶች ውጤት እንደሆነ በማመን ተስፋ ባለመቁረጥ በትዕግሥትና በጽናት ፍሬ ለማፍራት መታገል እንደሚገባው ተምሮ ያስተማረ ሊቅ ነው ። #ቅዱስ_ያሬድ ለዜማ ጥበባት ማኀፀን የሆነውን መተኪያ የማይገኝለትን ያሬዳዊ ዜማ ሰማያዊ ድርሰትን ለኢትዮጵያ ውበቷ የኩራት መቀነቷ የሆነውን የዜማ ድርሰቶችን ያበረከተላት ታላቅ ሊቅ ነው ። ቅዱስ እግዚአብሔር ያሬድንም ከብሔረ ሕያዋን ደምሮ ሞትን ሳይቀምስ በግንቦት 11 ቀን ሰወረው መታሰቢያውም በዚህ ዕለት ኾነ የሊቁ ቅዱስ ያሬድ ማሕሌታይ በረከቱና ረድኤቱ በአገራችን ኢትዮጵያና በመላው ሕዝበ ክርስቲያን ላይ ለዘላለም አድሮ ይኑር ። #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
8056Loading...
31
ከሰው ፡ ዐይን ፡ ተሰወረ ፡ አኗኗሩም ፡ ከሰማይ ፡ መላእክት ፡ ጋር ፡ ሆነ #ቅዱስ_ያሬድ ደብረ ሐዊ ከተባለው በሰሜን ተራራና ጫካ ብዙ ዓመታትን በምናኔ ካሳለፈ በኋላ ግንቦት 11 ቀን ሞትን ሳይቀምስ ከዚህ ዓለም ተሠወረ ፣ በዚህ ዓለም የኖረበት ጠቅላላ ዕድሜው ሰባ ዐምስት ነበር ፡፡ በቅዱስ ያሬድ ታሪክ ውስጥ አከራካሪ ትረካዎች አሉ ይኸውም በዕረፍቱና በዕርገቱ መካከል የሚነገረው ትረካ ነው አንዳንድ ሊቃውንት ቅዱስ ያሬድ ከዚህ ዓለም በሞት እንደተለየ መቃብሩም እንደተሠወረ ሲናገሩ ሌሎች ሊቃውንት ደግሞ እንደ ሄኖክና እንደ ኤልያስ ሞትን ሳይቀምስ እንደተሠወረ ይናገራሉ ፡፡ ሞቷል የሚሉት ሊቃውንት በስንክሣሩ ላይ ‹‹ በዚች ዕለት የሱራፌል አምሳያቸው የኾነ ማሕሌታይ ያሬድ ዐረፈ ፤ ከዚህ በኋላ ወደ ሰሜን ገዳም ሔዶ በዚያ ተቀመጠ በሰላምም ተቀመጠ ›› የሚለውን ገጸ ንባብ ይዘው ሞቷል የሚሉ አሉ ነገር ግን ይሄ ገጸ ንባብ በሞት መለየቱን አያመለክትም ። ምክንያቱም ‹‹ ጌታችን ከሥራው ሁሉ ዐረፈ ›› እንደሚለው ፤ ቅዱስ ያሬድም በድጓው ‹‹ በጎዳና ካገኘኝ ድካም ሰውነቴ ዐረፈች ›› ብሎ በተናገረው መሠረት ሰው እንደሚያርፍ ቅዱስ ያሬድም ማስተማሩን ፤ ከሰው ጋር መለየቱን ፤ ከዓይነ ሞት መሠወሩንና ከተጋድሎው ማረፉን የሚያመለክት ነው እንጂ መሞቱን አያመለክትም ብለው የሚከራከሩ ሊቃውንት አሉ ። ስለዚህ ቅዱስ ያሬድ ሞቷል ብለው የሚከራከሩ ሊቃውንት ከሞተ መቃብሩ የት ነው ሲባሉ መቃብሩ ተሠውሯል ይላሉ ፤ የመቃብሩ መሠወር ለምን አስፈለገ ተብለው ሲጠየቁ ልክ እንደ ሙሴ መቃብር ተሠውሯል ይላሉ ነገር ግን የሙሴ መቃብር የተሠወረበት የራሱ የሆነ ዓላማና ምክንያት ነበረው ። እርሱም ምንድነው ቢሉ እስራኤላውያን ቅዱስ ሙሴን በብዙ ይወዱት ነበርና እንዳያመልኩት ምክንያት ለማሳጣት እግዚአብሔር ይህን እንዳደረገ ሊቃውንት ይናገራሉ ፤ የቅዱስ ያሬድ መቃብር መሠወሩ ግን ምሥጢሩ ምንድ ነው ? ለሚለው ጥያቄ በቂ መልስ ስለሌለ ሞትን ሳይቀምስ እንደነ ኤልያስ ተሠውሯል የሚለው አብላጫውን ድምፅ ይዞ በብዙ ቤተ ጉባኤዎች የሚነገረው መሠወሩ ነው ፡፡ ድርሳነ ዑራኤልም ‹‹ ከሰው ዐይን ተሰወረ ፤ አኗኗሩም ከሰማይ መላእክት ጋር ሆነ ›› በማለት እንደነ ኤልያስ ከነሥጋው ማረጉን አስረግጦ ይናገራል ፡፡( የሰኔ ድርሳነ ዑራኤል ምዕራፍ 2 ፥ 50 ) ስለዚህ ሊቁ ቅዱስ ያሬድን ከሃይማኖታዊ ሚዛን ወጥተን ስንመለከተው ሀገራዊ ፣ ባህላዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ ፣ ሥልጣኔያዊ ፋይዳና ፍልስፍናዊ ድርሻ ያለው እንደሆነ እንገነዘባለን ፡፡ ቅዱስ ያሬድ ሃይማኖታዊ እሴት ያበረከተ ዘማሪ ብቻ ሳይሆን እጅግ ብዙ መጠነ ሰፊ ጉዳዮች የጻፈ የቀመረ ያረቀቀ ሊቅ ነው ፤ ስለሆነም ብሔራዊ መኩሪያችን ነው ። #ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ! አምኀ ተዋሕዶ ዘክርስቶስ በYoutube Sador Sisay on Youtube Sador Sisay on Instagram Sador Sisay on Facebook Sador Sisay on Tiktok #You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
7509Loading...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
...« ቅድስት ዮስቴና ሆይ ከሕጋዊ ባልሽ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ እርሱም ለዓለም ሁሉ የሚጠቅም ፣ ሰው ሁሉ የሚማፀነው ፣ ገድሉ ትሩፋቱ በዓለም የሚነገርለት ፣ በነፍስም በሥጋም የሚያማልድ ፣ እንደ መልአክትም ክንፈ ጸጋ የሚሰጠው በምድር ሆኖ መንበረ ጸባኦትን የሚያይ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ » ተብሎ ትንቢት የተነገረላቸው የአባታችን የጻድቁ #የአቡነ_ሀብተ_ማርያም ልደት ግንቦት 26 ቀን በታላቅ ድምቀት ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታከብራለች ። « በጸሎትህ አምኖ በጎ ሥራ ለሚሠራ ሁሉ ስምህን የጠራውን ዝክርህን የዘከረውን ሁሉ የሀብተ ማርያም አምላክ ሆይ ከጠላት እጅ አድነኝ ያለኝን በኅሊና ያሰበውን በልቡናው የወሰነውን እፈጽምለታለሁ ። » ብሎ ቃልኪዳን የተገባልህ እኛን ደካማ ልጆችህን በምልጃህ በቃል ኪዳንህ አስበን!!
Показати все...