uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

Werabe City Government Communication Affairs Office

Werabe City Government Communication Affairs Office

Відкрити в Telegram
3 029
Підписники
-224 години
-97 днів
+2830 днів
Архів дописів
ከወራቤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የተላለፈ የሁለተኛ ዙር ማስጠንቀቂያ መልዕክት! የወራቤ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ባወጣዉ የሊዝ ጨረታ አሸናፊ ሆነዉ መሬት የተረከቡ መሆኑ የታወቃል፡፡ ነገር ግን አመታ
+2
ከወራቤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የተላለፈ የሁለተኛ ዙር ማስጠንቀቂያ መልዕክት! የወራቤ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ባወጣዉ የሊዝ ጨረታ አሸናፊ ሆነዉ መሬት የተረከቡ መሆኑ የታወቃል፡፡ ነገር ግን አመታዊ ክፍያ ከ4 እስከ 6 አመት ያልከፈሉ 39 (ሰላሳ ዘጠኝ) ከተራ ቁጥር 1 እስከ 39 ያሉ ባለይዞታዎች ዉዝፍ የሊዝ እዳ ያለባችሁ ስለሆነ በ17 (አስራ ሰባት) ቀናት ውስጥ ማለትም ከቀን 25/02/2019 እስከ 17/03/2019 ድረስ የለቦትን የሊዝ ዉዝፍ ዕዳችሁን አጠናቃችሁ የማትከፍሉ ከሆነ በከተማ መሬት የሊዝ አዋጅ 721/2004 አዋጁን ለማስፈፀም ተሻሽሎ በወጣዉ መመሪያ ቁጥር 8/2007 አንቀጽ 86 የሊዝ ዕዳ መሰብሰብ በተመለከተ ከንዑስ አንቀጽ 1 እስከ 12 በተቀመጠዉ መሰረት የሊዝ መሬቱን በማገድ ለማዘጋጃ ቤቱ የሊዝ ዉዝፍ ዕዳዉን ለመሰብሰብ /የመንግስት ዕዳ የምናስመልስ መሆኑን በጥብቅ እናሳዉቃለን፡፡ የወራቤ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ጥቅምት 26 ቀን 2019

#ሀበይ_ተስ_ባለሙ! #እንኳን_ደስ_አላችሁ! የወራቤ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት 1ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ! የስልጤ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መምሪያ ዛሬ ባካሄደው የ
+2
#ሀበይ_ተስ_ባለሙ! #እንኳን_ደስ_አላችሁ! የወራቤ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት 1ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ! የስልጤ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መምሪያ ዛሬ ባካሄደው የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጻም ጉባዔው በበጀት ዓመቱ የላቀ ለፈጸሙ መዋቅሮች እውቅና ሰጥቷል። በዚህም የወራቤ ከተማ አስተዳደር ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት በዞኑ ካሉ መዋቅሮች የላቀ ውጤት በማስመዝገብ 1ኛ ደረጃ በመያዝ ዋንጫ እና የዕውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶለታል። በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!! ጥቅምት 26፣ 2019 [ወራቤ ከተማ ኮሙኒኬሽን]

#ሀበይ_ተስ_ባለሙ_ባለነ!! የወራቤ ከተመ መትንዳደሬ ኣደዋ ቱሪዝም ክ/ጋር 2ኘ መቃም በውጦት የዋንጨ ተሼላሚ ሆናን! የስልጤ ዞን አዳዋ ቱሪዝም መምረ አውጄ ባትዋሳደይ ቡልሻን ቦ2018 በጀት ዘማን
#ሀበይ_ተስ_ባለሙ_ባለነ!! የወራቤ ከተመ መትንዳደሬ ኣደዋ ቱሪዝም ክ/ጋር 2ኘ መቃም በውጦት የዋንጨ ተሼላሚ ሆናን! የስልጤ ዞን አዳዋ ቱሪዝም መምረ አውጄ ባትዋሳደይ ቡልሻን ቦ2018 በጀት ዘማን የጠቀለ ውጣትዋ ቆማሪ ብል ለናረይሙ መዋቅርቸዋ ጅጋኛኞ ያንሻሽጦት ሹልመ ዋባን፡፡ መምራይ ባትዋሰደይ ቡልሻን የወራቤ ከተመ መትንዳደሬ ኣደዋ ቱሪዝም ክትበት ጋር ባለፈይ ዘማን የጠቀለ ውጣት ባምጦት በዞኒ ታሉይ ጅጋኛኞ 2ኘ መቃም ቢንዞት የዋንጨ ሹልም የሻይድነት ወረቀት ታበያን። በድባየ ሀበይ ተስ ባለሙ፤ ባለነ!! 26-02-2018 ቶ.እ

የወራቤ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የማኅበረሰቡን ሁለንተናዊ የጤና ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማረጋገጥ እና የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ያለመ የ2019 በጀት ዓመት የ1ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የቀጣይ የ100 ቀናት ዕቅድ ግምገማ መድረክ አካሂዷል! https://www.facebook.com/100070047665762/posts/1416251137386462/?app=fbl

#ሀበይ_ተስ_ባለሙ! #እንኳን_ደስ_አላችሁ! የወራቤ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ተቋም 1ኛ ደረጃ በመያዝ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ! ‎የስልጤ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ የ2018 በጀት ዓ
+1
#ሀበይ_ተስ_ባለሙ! #እንኳን_ደስ_አላችሁ! የወራቤ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ተቋም 1ኛ ደረጃ በመያዝ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ! ‎የስልጤ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2019 ዓ.ም የህብረተሰብ ተሳትፎ የመንገድ ንቅናቄ ሴክቶሪያል ጉባኤውን አካሂዷል። ‎ በዚህም ‎​የወራቤ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት በዞኑ ካሉ የከተማ መዋቅሮች መካከል የተሟላ የመናኻሪያ ሪፎርም በመተግበር ተቋሙን በክልል ደረጃ "የተሞክሮ ማዕከል" ማድረግ በመቻሉ፣ የሄልሜት አጠቃቀምን የከተማዋ ባህል በማድረጉ እና የትራንስፖርት ህግና ስርዓትን በማስከበሩ የ1ኛ ደረጃ ተሸላሚ በመሆን ዋንጫ እና የዕውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶለታል። በሌላበኩል ደግሞ በዞኑ ካሉ የግል የአሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋማት መካከል ወራቤ-ሰላም አሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ተቋም 1ኛ በመያዝ የዋንጫ ተሸለሚ ሆኗል። በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ! ጥቅምት 25፣ 2019 [ወራቤ ከተማ ኮሙኒኬሽን]

#ሀበይ_ተስ_ባለሙ! #እንኳን_ደስ_አላችሁ! የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት 2ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ! የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ ዛሬ ባካሄደው የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ
#ሀበይ_ተስ_ባለሙ! #እንኳን_ደስ_አላችሁ! የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት 2ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ! የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ ዛሬ ባካሄደው የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጻም ጉባዔው በበጀት ዓመቱ የላቀ ለፈጸሙ መዋቅሮች እውቅና ሰጥቷል። በዚህም የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ጽ/ቤት በዞኑ ካሉ መዋቅሮች የላቀ ውጤት በማስመዝገብ 2ኛ ደረጃ በመያዝ ዋንጫ እና የዕውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶለታል። በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!! ጥቅምት 25፣ 2019 [ወራቤ ከተማ ኮሙኒኬሽን]

#ሀበይ_ተስ_ባለሙ!! #እንኳን_ደስ_አላችሁ!! የወራቤ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት 1ኛ ደረጃ በመያዝ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ! የስልጤ ዞን ትምህርት መምሪያ ባካሄደው 26ኛው የትምህርት አስተዳደ
+1
#ሀበይ_ተስ_ባለሙ!! #እንኳን_ደስ_አላችሁ!! የወራቤ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት 1ኛ ደረጃ በመያዝ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ! የስልጤ ዞን ትምህርት መምሪያ ባካሄደው 26ኛው የትምህርት አስተዳደር ጉባኤ በ2018 በተከናወኑ የትምህርት ልማት ስራዎች የተሻለ ለፈጸሙ መዋቅሮች እውቅናና ሽልማት አበርክቷል። በዚህም የወራቤ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ በዞኑ ካሉ የከተማ አስተዳደር መዋቅሮች 1ኛ ደረጃ በመያዝ ዋንጫ እና የዕውቅና ሽልማት ተሰጥቶታል። በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!! ጥቅምት 24፣ 2019 [ወራቤ ከተማ ኮሙኒኬሽን]

የኑሮ መሻሻልና የኢኮኖሚ እድገት መሰረት ትምህርት በመሆኑ ለዘርፉ አትኩሮት መስጠት እንደሚያስፈልግ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ዘይኔ ቢልካ ገለፁ ጥቅምት 24፣ 2019 [ወራቤ ከተማ ኮሙ
+9
የኑሮ መሻሻልና የኢኮኖሚ እድገት መሰረት ትምህርት በመሆኑ ለዘርፉ አትኩሮት መስጠት እንደሚያስፈልግ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ዘይኔ ቢልካ ገለፁ ጥቅምት 24፣ 2019 [ወራቤ ከተማ ኮሙኒኬሽን] የኑሮ መሻሻልና የኢኮኖሚ እድገት ትምህርት በመሆኑ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ መሆኑን በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ አሳሰቡ። "ዘላቂ የትምህርት ጥራት ለላቀ የመማር ውጤትና ብልጽግና!" በሚል ቃል 26ኛው የስልጤ ዞን ትምህርት አስተዳደር ጉባኤ በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ነው። አለም በቴክኖሎጂው ዘርፍ ርቃ የሄደችው የሰለጠኑ ሀገራት ለትምህርቱ ዘርፍ ትኩረት ሰጥተው ስለሚሰሩ መሆኑን አስገንዝበዋል።(ስልጤ ሬድዮና ቴሌቪዥን)

#ሀበይ_ተስ_ባለሙ! #እንኳን_ደስ_አላችሁ! የወራቤ ከተማ አስተዳደር ንግድ ተቋም 1ኛ ደረጃ በመያዝ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ! የስልጤ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ በዛሬው ዕለት ባካሄደው የ2018
#ሀበይ_ተስ_ባለሙ! #እንኳን_ደስ_አላችሁ! የወራቤ ከተማ አስተዳደር ንግድ ተቋም 1ኛ ደረጃ በመያዝ የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ! የስልጤ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ በዛሬው ዕለት ባካሄደው የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጻም የማትጊያ ጉባዔው ላይ በበጀት ዓመቱ የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ ከ1-3 ለወጡ የወረዳና ከተማ አስተዳደር ተቋማት እውቅና ሰጥቷል፡፡ በዚህም በዞኑ ካሉ የከተማ ንግድ ተቋማት መካከል የወራቤ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት የላቀ ውጤት በማስመዝገብ 1ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫ ሽልማት እና የዕውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶለታል።           በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!! ጥቅምት 24፣ 2019 [ወራቤ ከተማ ኮሙኒኬሽን]

#ሀበይ_ተስ_ባለሙ!! #እንኳን_ደስ_አላችሁ!! የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ ተቋም የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል! የስልጤ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ዛሬ ባካሄደው የ20
#ሀበይ_ተስ_ባለሙ!! #እንኳን_ደስ_አላችሁ!! የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ ተቋም የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል! የስልጤ ዞን ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሀብት ልማት መምሪያ ዛሬ ባካሄደው የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጻም የማትጊያ ጉባዔው ላይ የላቀ ለፈጸሙ መዋቅሮች የእውቅና ሽልማት አበርክቷል። በዚሁ የማትጊያ መርሃ-ግብር ላይ በባለፈው በጀት ዓመት የወራቤ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ልዩ ተሸላሚ በመሆን ዋንጫና ሰርተፊኬት ተሰጥቶታል። በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!! ጥቅምት 23፣ 2019 [ወራቤ ከተማ ኮሙኒኬሽን]

#ሀበይ_ተስ_ባለሙ #እንኳን_ደስ_አላችሁ! የወራቤ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ልዩ ተሸላሚ በመሆን ዋንጫ ተበርክቶለታል! የስልጤ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ባካሄደው የ2018 በጀት
#ሀበይ_ተስ_ባለሙ #እንኳን_ደስ_አላችሁ! የወራቤ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ልዩ ተሸላሚ በመሆን ዋንጫ ተበርክቶለታል! የስልጤ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ባካሄደው የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸምና የ2019 ንቅናቄ ሴክቶሪያል ጉባኤው በ2018 በጀት ዓመት በአጠቃላይ የከተማ ልማት ስራዎች የተሻለ ለፈጸሙ መዋቅሮች እውቅና ሰጥቷል። በዚህም የወራቤ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በኮንስትራክሽን ዘርፍ የላቀ በመፈጸም፤ የልዩ ተሸላሚ ደረጃን በመያዝ ዋንጫ እና የዕውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶለታል። በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!! ጥቅምት 23፣ 2019 [ወራቤ ከተማ ኮሙኒኬሽን]

በወራቤ ከተማ አስተዳደር የተማሪዎችን ዉጤት ለማሻሻልና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ገለጸ! https://www.facebook.com/100070047665762/posts/1414114164266826/?app=fbl

ያልለማ መሬት ተነጥቆ መሬት ባንክ የገባ መሆኑን እናሳውቃለን - የወራቤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት! የወራቤ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት በከተማው ያልለማ መሬት ተነጥቆ ወደ መሬት ባንክ የገባ መሆኑን አስ
ያልለማ መሬት ተነጥቆ መሬት ባንክ የገባ መሆኑን እናሳውቃለን - የወራቤ ከተማ ማዘጋጃ ቤት! የወራቤ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት በከተማው ያልለማ መሬት ተነጥቆ ወደ መሬት ባንክ የገባ መሆኑን አስታውቋል። በወራቤ ከተማ አስተዳደር በኢንቨስትመንት እና ለተለያዩ አገልግሎቶች መሬት ወስደው ያላለሙ አካላትን ከቀን 23/02/2019 ዓ.ም ጀምሮ የከተማ መሬትን ስለመያዝ በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀጽ 22 እና አንቀጽ 23 አዋጁን ለማስፈጸም ተሻሽሎ በወጣው ደንብ ቁጥር 11/2016 አንቀጽ 34-36 እና ደንቡን ለማስፈጸም ተሻሽሎ በወጣው መመሪያ ቁጥር 05/2018 አንቀጽ 52፤ አንቀጽ 50-51 መሰረት መሬቱን ማዘጋጃ ነጥቆ ወደ መሬት ባንክ ገቢ አድርጓል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ጊዜያት ለኢንቨስትመንትና ለሌሎች ልማቶች መሬት የወሰዱ አካላት በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ግንባታቸውን እንዲያጠናቅቁና በተገቢ እንዲያለሙ ማዘጋጃ ቤቱ ጥብቅ መልዕክቱን አስተላልፏል። ታዲያ ይህ ሳይሆን ሲቀር የሚወሰደው ህጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳስቧል። የወራቤ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ጥቅምት 23፣ 2019 [ወራቤ ከተማ ኮሙኒኬሽን]

የወራቤ ከተማ አስተዳደር እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት የሁለተኛ ዓመት የአባላት ጠቅላላ ጉባኤውን በወራቤ ከተማ አካሂዷል! https://www.facebook.com/100070047665762/posts/1412542534423989/?app=fbl

በወራቤ ከተማ አስተዳደር ለተከታታይ ሁለት ወራቶች ሲካሄድ የቆየው የ2019 ዓ.ም የፕሮጀክት U-17 የእግር ኳስ ውድድር በአሊፍ አሸናፊነት ተጠናቋል! https://www.facebook.com/100070047665762/posts/1412469947764581/?app=fbl

በወራቤ ከተማ አስተዳደር በከንቲባነት ላገለገሉትና በቅርቡ የስልጤ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ ሆነው ለተሾሙት አቶ ያሲን ከሊል የሽኝት እንዲሁም የወራቤ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሆነው ለተሾሙት ለአቶ ሳዲቅ አህመዲን የአቀባበል መርሃ-ግብር ተካሂዷል! https://www.facebook.com/100070047665762/posts/1412419537769622/?app=fbl

#ሀበይ_ተስ_ባለሙ_ባለነ #እንኳን_ደስ_አላችሁ_አለን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ማህበራዊ ጽ/ቤት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ! ~~~ የስልጤ ዞን ሴቶችና ማህበራዊ ጉደይ መምሪያ ባካሄደው የ2018 በ
+2
#ሀበይ_ተስ_ባለሙ_ባለነ #እንኳን_ደስ_አላችሁ_አለን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ሴቶችና ማህበራዊ ጽ/ቤት የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ! ~~~ የስልጤ ዞን ሴቶችና ማህበራዊ ጉደይ መምሪያ ባካሄደው የ2018 በጀት ዓመት ሴክቶሪያል ጉባኤ የወራቤ ከተማ አስተደደር ሴቶችና ማህበራዊ ጽ/ቤት በዞን ካሉ መዋቅሮች 3ኛ ደረጃ እንዲሁም በማህበራዊ ዘርፍ 1ኛ ደረጃ በመያዝ የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል። ጥቅምት 21፣ 2019[ወራቤ ከተማ ኮሙኒኬሽን]

የምርት አቅርቦት ትስስርን በማጠናከር የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት እየተሠራ መሆኑን የወራቤ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ! ጥቅምት 20፣ 2019 [ወራቤ ከተማ ኮሙኒኬሽን] በወራቤ ከተማ
+6
የምርት አቅርቦት ትስስርን በማጠናከር የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት እየተሠራ መሆኑን የወራቤ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ! ጥቅምት 20፣ 2019 [ወራቤ ከተማ ኮሙኒኬሽን] በወራቤ ከተማና አካባቢዋ የሚታየውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋትና ሸማቹ ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ የሸቀጦችን አቅርቦት እንዲያገኝ የምርት አቅርቦት ትስስር የመፍጠር ሥራ ተጠናክሮ እየተከናወነ መሆኑን የወራቤ ከተማ አስተዳደር ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት አስታውቋል። በከተማ አስተዳደሩ ዙሪያ ከሚገኙ አጎራባች ወረዳዎች የተለያዩ የግብርና ምርቶች በብዛት እየተመረቱ በመሆናቸው ከአምራቾች ጋር ቀጥተኛ የገበያ ትስስር በመፍጠር ምርቶቹን ለወራቤ ከተማ የቅዳሜ ገበያ የማቅረብ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል። ይህንኑ ሥራ ለማጠናከር የከተማ አስተዳደሩ ማዘጋጃ ቤት ለአምራቾች የተሽከርካሪ ድጋፍ በማድረግ ምርቶች ከምርት ቦታቸው በቀጥታ ወደ ወራቤ ከተማ ቅዳሜ ገበያ እንዲጓጓዙ እያገዘ መሆኑ ተጠቅሷል። የምርት አቅርቦት ትስስሩ በተጠናከረባቸው የቅዳሜ ገበያ የምርት አቅርቦትን በማሳደግ የገበያ ዋጋ ንረትን ለማረጋጋትና ሸማቹ ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲሸምት አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑ ተጠቁሟል። የአምራቾችና የሸማቾችን ቀጥተኛ ትስስር በማጠናከር፤ የምርት አቅርቦትን ለማሳደግና የኑሮ ውድነትን ለማረጋጋት የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል የከተማ አስተዳደሩ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት በላከልን መረጃ ገልጿል።