قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
Відкрити в Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
899
Підписники
-224 години
-167 днів
+2730 днів
Архів дописів
Repost from Woldia University Muslim Students
💧~ከኡለማወች ንግግር
ዋናው ነገር ከሱናው ባቡር ላይ ተሳፈር!
قال الإمام الأوزاعي رحمه الله : « عليك بآثار من سلف وإن رفضك الناس ، وإيّاك وآراء الرجال وإن زخرفوها لك بالقول ؛ فإن الأمر ينجلي - حين ينجلي - وأنت على طريق ..
【الشريعة للآجري (1/138)
“አደራህን!የቀደምቶችን ፋና አጥብቀህ ያዝ!
ሰዎች ጀርባቸውን ቢሰጡህም! ከሰዎች አስተያየት ተጠንቀቅ!በቃላት ቢያሸበርቁልህም እንኳ፣ አንተ ቀጥ ያለው መንገድ ላይ ከሆንክ ነገሩ በሒደት ይገለጣል።” [ኢማሙ አል አውዛዒይ፡ “አሸሪዓ ሊል አጁሪይ “(1/138)]
አጋር ጠፋ ብለህ ወንድሜ አትከፋ፤
መንገዱ ላይ ከሆንክ ሐቅ ይወጣል ይፋ፤
✍የተወሰደ
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
በድጋሚ ለማስታወስ
~
ተቋርጦ የነበረው ሳምንታዊ የደርስ ፕሮግራም ዛሬ እሁድ ይጀመራል፣ ኢንሻአላህ።
* ቦታ፦ ሑዘይፋ መስጂድ
* ጊዜ፦ ከረፋዱ 4፡00 ጀምሮ
ኪታቦች
1. منھج السالكين
2. كن سلفيا على الجادة
Repost from ዳዕዋ ሰለፍያ በአልብኮ ወረዳ ሶባ እና ጀብል ቀበሌ(አሸዋዉ) ✈
⭕️👉ለውዱ ኡስታዛችን ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር አሏህ አፊያ ያድርገውና አድርሱልኝ።✅
➣🔻አንተን ክፉ አይንካህ🤲
*_ክፍል➝➊ ►𝓸𝓷𝓮
የነብያት ወራሽ ዳዒ ነህ ታታሪ፤
የኢስላም ወታደር ባጢል አባራሪ።
የሱና ሳተና የቢዲዓ ጠላት፤
በሁጃ ተውበህ ሀቅን ያፀናሀት፤
ባጢልን አባረህ አጭደህ የወቃሀት።
በእኔ ጭልፍ ሆሄ በአጭር አማረኛ፤
ሊደርስህ ባይችልም ተራ ፈረሰኛ፤
ላንጎራጉር ብየ እንደመንገዳኛ፤
ሲሰማኝ ቋጠርኳት ከውስጤ ማደኛ።
የኔ ጀግና ብየ ባወሳህ አልጠግብም፤
አንበሰና ነህ ብልህ አንጀቴ አይገግብም።
የሀበሻው ኮኮብ ስጦታው ይደንቃል፤
በማራኪ አንደበት ዒልምን ያስታጥቃል ።
አህባሽ ግሳንግሱ ብቅ ሲል ሀበሻ፤
በሎጅክ ለማጥመቅ ሲያሳጣ መድረሻ፤
ወገቡን ሰበረው በሁጃ መዶሻ።
ተዕዊል እና ተእጢል አንግቦ በውስጡ፤
ሹቡሀ እየነዙ ምድር ሲቀውጡ፤
የሱናን ሰው ጠልተው ከሀገር ሲያስወጡ፤
ሲያስገርፉ አሳስረው ዋሽተው ሲያናውጡ።
የነብዩን መንገድ ገርሳሹ ሲበዛ፤
ውሸትን ተዋጋው ቆልቶት እየነዛ፤
ቁርአን ሀድስን ከሰለፎች መቅጃ፤
ኢጅማዕን አስፍሮ አጣቅሶ ማስረጃ፤
አበረከተልን ሹብሀን ማስወገጃ፤
ጀግናው የኔ ዑስታዝ ድንቅ ኢብኑ ሙነወር፤
ኢላማው አይስትም ሁጃው ሲወረወር።
ሱፍያን፣አህባሽን ድባቅ ያስገባቸው፤
ከአርሹ በላይ ነው ብሎ ፃፈባቸው።
የአህባሾች መሪ "ሀሰን ታጁ" ሲዋሽ፤
ከኢኽዋኖች መጥቶ በመውሊድን ሲቀረሽ፤
እርምት አረገበት የታሪኩን ግድፈት፤
በማስረጃ አድርጎ ውሸትን ቀበራት።
በሱና ስም ሰርገው ፊልም ለሚሰሩ፤
ተገቢ ያልሆነን ተግባር ላሰመሩ፤
አደብ አስያዛቸው በውብ መነፀሩ።
ሀጃዊራ ዘልቃ ያለ አግባብ ስትቀረሽ፤
የሁጃ ጦር ስሎ በደሊሉ ጥንቅሽ።
አልበያንን ከትቦ እያሰጣ ቀንጣሽ፤
ከታላላቆቹ ማስረጃን አጣቃሽ፤
አንተኮ ነህ ጀግና እውነትን አስታዋሽ ።
አካሄዱ በሳል ንግግሩ ቁጥብ፤
ምክሩ አንጀት አርስ ነው ልብን የሚያረጥብ፤
በምን ፊደል ላውሳው በምን ቃላት ነጥብ፤
ብቻ ማር ያዘንባል ጀግና ነው እንደ ንብ።
ለፊትና አይቸኩልም ይፈራል አደጋ፤
ሱናን ይጠብቃል ነቅቶ ሳይዘነጋ፤
ወዳሴም አይሻ የማንንም ታርጋ፤
አፉን የለጎመው የለተሞን መንጋ፤
ያላግባብ ሲወራጭ ተሳክሮ ሲንጋጋ፤
ድምፅ ባለው ፅሁፍ ቅጥፈት የተዋጋ፤
የሙነወር ልጅ ነው የባጢል አለንጋ ፤፦
የተክፊርን ቅሪት ወገቡን የቀጨው፤
በአንድ ንግግሩ መንጋውን ያጋጨው፤
አንድ ኳስ ወርውሮ "ሽ" ያነጫነጨው ።
ለሀቅ ዘብ ቆሞ ለፍትህ የሚኖር፤
ለሱና ኻድም ነው የኢስላም መምህር።
ልክ እንደ ፔንዱለም ፊትና ሲያናውጠን፤
ድንገት ተከስቶ አካቦ ሲውጠን፤
ፈጥነህ በመመከት እረፍት የምሰጠን።
አሏህ ይጠብቅህ ከመከራ ከጭንቅ፤
ከሴረኞች ተንኮል ከአይሁድ ከሙናፊቅ።
ሻፊ ነው ጌታችን በቶሎ ያሽርህ፤
ወንጀልክን አብሶ በኸይር ያበሽርህ።
የአተን ሀላፊነት የለም የሚተካህ፤
የሀበሻው ኮኮብ አንተን ክፉ አይንካህ።
➘➘ይቀጥላል ኢንሻ አሏህ.........
✍بقلم أبي شورى أحمد
https://t.me/Sobabilalmesjid
https://t.me/Sobabilalmesjid
Repost from ዳዕዋ ሰለፍያ በአልብኮ ወረዳ ሶባ እና ጀብል ቀበሌ(አሸዋዉ) ✈
በእህቶች ብር ነው የተጣላነው የሚለውን የጊንባውን ድምፅ በዚህ ወንድሞች ነሽረውት ሰምቸው ገረመኝ እኒህን ገፋፊወች አላህ ዘንድሮ የውስጥ ጉዳቸውን ዘርግፎ አሳየን ..
🔻👌..ሙስጦፋ ሙሀመድ መሸሻ ማለት በብዙ ነገር አካሄዱ የተበላሸ አቋመ ቢስ ነው።
🔻ከየት አመጣው ሴቶችን ሁልጊዜ በሶሀባ ሴት ስም በማወደስ ልምድ አርጎ መያዝ ።
🔻..እነዶክተር ጀይላኒን ያሸይኹነል ፋድል ያሉበትን እያሉ ያወደሱበት እስካሁን ተገርመን ሳናበቃ አሁን ደሞ በብር ተጣላን ብለው በራሳቸው ላይ መሰከሩ።
كما قال جل وعلى..وشهد شاهد من أهلها. شرحتم أنفسكم ولله الحمد.....وكفى الله المؤمنين القتال وكان الله قويا عزيزا.
https://t.me/Sobabilalmesjid
https://t.me/Sobabilalmesjid
የደሴው አልባኒ "በምን ሁኔታ ነህ?
▫️▫️▫️▫️▫️▫️▫️▫️
ደረሰህ ወይ መልክት የጦሳወቹ ሸይኽ፣
ተስማማህ ኢላጁ ወይስ አስቀረሸህ?!፣
እንደምንስ አደርክ ፤እንደትስ አነጋህ!?፣
ምግብህን ብላና ዋጠው መዳኒቱን፣
አይንህን ግለጠው እስኪ ስማ እውነቱን፣
የ'ኢርጃዕ መሰአላ ኡዙር ቢል
ጀህል ጋ ምን አገናኛቸው?!
የሙንተቂሉ ሸይኽ እስኪ ና
ብቅ በል መልስ ስጥባቸው!።
በሙሪዶችህ ላይ ስትጎራባቸው፣
ሰጠህ አጥጋቢ መልስ የሓቲም አባት፣
ተቀበል እውነትን ቢመር እንደ ሬት።
አጀብ ነው:-
ኡለማኡል ኪባር ከነሱ ጋር አብረን
ተጓዦች ነን ይላል፣
ደግሞም ዞር ይልና እነዚያን ቀደምቶች
በኢርጃዕ ይወርፋል ።
ያንተን ሙግት አይነት ፊር
አውን ሞግቷል፣
ስለ ሞገተ ግን እውነትን አግኝቷል?! !ከላ"
የአንተን አፈ ታሪክ ሁልጊዜ፣
ማዳመጥ ለማይሰለቻቸው፣
በውሸትህ መረብ ለተበተብካቸው፣
ጀግናው ኡስታዛችን በሚገባ መልኩ
ይሄው መዳኒቱን አዘጋጀላቸው፣
ቀመስ ሲያረጉት ሲለሚከብዳቸው፣
ትንሽ ትንሽ አርገህ በጥብጠህ ስጣቸው።
እምን በሽታህን አፍኖ እዳይገልህ፣
በጊዜ ታከሙ እስከ ግልገሎችህ።
እኔ የገረመኝ አንድ እኳን
መረጃ የማታጣቅሰው፣
በአፈ ታሪክህ ሰውን የምትላጨው፣
የማይሆንን ነገር የምታገጫጨው፣
ስኳር ያው ስኳር ነው በጭራሽ አይሆን ጨው።
ረድ ሲደረግ እኔን ፈርተውኝ ነው
ብለህ እንዳታስብ፣
ለማትረፍ ነው እንጂ አላዋቂውን ህዝብ፣
በአንበሶች መንደር ዋጋ የላትም ዝንብ።
ይሄ መሰአላ ሲያሻህ ኢጅቲሀድን
የሚያስተናግድ ነው ፣ሲያሻህ ደግሞ የለም፣
እንዳተ ሙሪዶች ቂላ ቂል ሰው የለም፣
በሬ ወለደ እኳን ብለህ ብትላቸው፣
ሁሉም በአንድ ድምፅ የሚያፀድቁ ናቸው።
ከሙቀሊዲነት ጀሊሉ ያውጣቸው።
የወሎዮች መርጂዕ የደሴው አልባኒ
የትሪ ውሃ ጋሸ አቡ ኒብራስ "በደንብ መዳኒቱን ዋጥ።
የረያን እናት🖊🖊
https://t.me/Umu_Reyan_channel_No1
ሙሓደራ ቁጥር :-🟤3️⃣7️⃣
ክፍል :-1️⃣
ርዕስ= ረድ በ ሙስጠፋ አብደላህ ላይ
"መስዓለቱ ዑዝር ቢል ጀሕል''
▫️▫️▫️▫️▫️▫️▫️
🎙 በ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ከሚሴ (አቡ ሓቲም)
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
https://t.me/UstazKedirAhmed
ሙስሊም ወንድማማቾች (ኢኽዋኑል ሙስሊሚን) እነማን ናቸው?
ታላቁ፣ ታዋቂውና የሐዲስ ምሁር ሼክ አህመድ ቢን ያህያ አል-ናጅሚ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፡-
👌የከሰሩት ወንድማማቾች ቡድን (ጀማዓቱል ኢኽዋኒል ሙፍሊሲን)
እነሱ የጥመት ፈጣሪና ጠማማው ሐሰን አል-በና ተከታዮች ናቸው። አካሄዳቸው (መንሐጃቸው) ላይ የሚታዩ ዋና ዋና ጉድለቶች የሚከተሉት ናቸው፡-
❶ የአምልኮ ተውሂድን (ተውሂድ አል-ኢባዳህን) ማቃለል፤ ይህ በኢስላም ውስጥ ትልቁና ዋናው ነገር ሲሆን፣ ያለ እሱ የአንድ ባሪያ ኢስላም ትክክል አይሆንም።
❷ ሰዎችን በትልቁ ሽርክ ላይ ዝም ማለታቸውና ማፅደቃቸው፤ ከአላህ ውጭ ካሉ አካላት እገዛን መለመን (ዱዓ ማድረግ)፣ በቀብሮች ዙሪያ መዞር (ጠዋፍ ማድረግ)፣ ለቀብር ባለቤቶች መሳል (ነዝር ማድረግ)፣ በስማቸው ማረድ እና የመሳሰሉትን።
❸ የዚህ አካሄድ (መንሐጅ) መስራች ሱፊ መሆኑ እና ከሱፊያ ጋር ግንኙነት ያለው መሆኑ፤ ከዐብዱልወሀብ አል-ሐሷፊ በሐሷፊያ ሻዚሊያ መንገድ (ጦሪቃ) ላይ ቃልኪዳን (በይዓ) መውሰዱ
❹ በእነሱ ዘንድ ቢድዓዎች (በዲን ላይ አዳዲስ ፈጠራዎች) መኖራቸውና በእነሱም አላህን መገዛታቸው፤ ይልቁንም የመንሐጁ መስራች ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በዚክር መጅሊሳቸው ላይ እንደሚገኙና ያለፈውን ወንጀላቸውን ይቅር እንደሚሏቸው በእነዚህ ስንኞች አፅድቋል፡-
አላህ ብርሃን በሆነው ላይ የአላህ እዝነት ይውረድ፣
ለዓለማት በግልፅ በወጣው፣ ፀሐይና ጨረቃን በበለጠው።
ይህ ውዱ ነቢይ ከወዳጆቹ ጋር ተገኝቷል፣
ላላለፈውና ለተፈጠረው ነገር ሁሉንም ይቅር ብሏል።
❺ ወደ ኸሊፋነት (የእስልምና መንግስት) መጣራት፤ ይህ ቢድዓ ነው፤ ምክንያቱም መልእክተኞችና ተከታዮቻቸው ወደ ተውሂድ እንዲጣሩ እንጂ አልታዘዙም፤ አላህ እንዲህ ብሏል፡-
«በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ “አላህን ተገዙ፤ ጣዖትንም ራቁ” በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል» [አል-ነሕል፡ 36]።
➏ በእነሱ ዘንድ "አል-ወላእ ወል-በራእ" (ለአላህ ብሎ መውደድና ለአላህ ብሎ መጥላት) አለመኖሩ ወይም መዳከሙ፤ ይህም በሱና እና በሺዓ መካከል ለማቀራረብ ከሚያደርጉት ጥሪ እና የመስራቻቸው ንግግር ላይ ግልፅ ይሆናል፡-
"በተስማማንበት ነገር ላይ እንሰባሰብ፣ በተለየንበት ነገር ላይ ደግሞ አንዳችን ለሌላውን ኡዝር ይስጥ)"
➐ ተውሂድን የሚወዱትን (አህሉ ተውሂድን) እና የሰለፊያን መንገድ ተከታዮች መጥላቸውና መቃወማቸው፤ ይህ በተውሂድ ላይ ከተመሰረተችውና በየቀኑ በሕዝብ ትምህርት ቤቶች፣ በተቋማትና በዩኒቨርሲቲዎች ተውሂድን ከምታስተምረው የሳውዲ መንግስት ላይ ከሚናገሩት ንግግር ግልፅ ይሆናል።
እንዲሁም ተውሂድን የሚያስተምርባቸው ትምህርት ቤቶች የነበሩትን ጀሚል አል-ረሕማን አል-አፍጋኒን ወደ ተውሂድ ስለተጣራ ብቻ ከመግደላቸው ማየት ይቻላል።
❽ የገዢዎችን (የመሪዎችን) ስህተት መፈለግና ጉድለቶቻቸውን መቆፈር፤ እውነትም ይሁን ውሸት፣ ወጣቱ ትውልድ መሪዎቹን እንዲጠላና ልባቸው በክፋትና በጭካኔ እንዲሞላ ያንን ማሰራጨት።
❾ አምርረው የሚይዟት የተወገዘችው ቡድነኝነት (ሐዝቢያ)፤ ለዚህ ቡድን ሲሉ ይወዳጃሉ፣ ለእሱም ሲሉ ይጣላሉ።
❿ የመንሐጁ መስራች በጠቀሳቸው አስር መስፈርቶች መሰረት ለኢኽዋን መንገድ ለመስራት ቃልኪዳን (በይዓ) መውሰድ፤ ከዚህ ውጪ ሌሎችም ምልከታዎች አሉ፣ ወደፊት ልንጠቅሳቸው እንችላለን።
ምንጭ፡- ይህ ፈትዋ "አል-ፈታዋ አል-ጀሊያ ዐን አስኢለቲል መናሂጅ" ከተሰኘው መጽሐፍ የተወሰደ ነው።
👌ታዲያ በምን እንወቃቸው???
ሼክ አህመድ ቢን ያህያ አል-ናጅሚየኢኽዋን ቡድን መንገድ (መንሐጅ) ብልሽትን የሚያሳዩ 50 ነጥቦች እንደሚከተለው በሚገባ አብራርተውልናል።
👉በተውሂድ ጉዳይ ላይ መዘናጋትና ማቅለል
👉የ"ወላእ ወል-በራእ" መዳከም
👉በቢድዓ ላይ መውደቅ
👉የቡድነኝነት (የሐዝቢያ) ቢድዓ
👉መሪዎችንና ገዢዎችን ማማት (መተቸት)
👉የኢኽዋን አካሄድ በሚስጥራዊነት ላይ 👉የተመሰረተ መሆኑ ለኢኽዋን መሪዎች አክራሪ መሆን
👉ለኢኽዋን መጽሐፍት አክራሪ መሆን
👉ለኢኽዋን ትምህርቶች (ሙሐዶራዎች) አክራሪ መሆን
👉በኢኽዋኖች መካከል ለቡድኑ ጥቅም ብቻ መተባበር
👉ኢኽዋንን ከሚተቹ ሰዎች አጥብቆ ማስጠንቀቅ
👉ከኢኽዋን ቡድን ከሚያስጠነቅቁ መጽሐፍት ማስጠንቀቅ
👉የእስልምና እውቀትን (ሸሪዓዊ ዒልምን) በመፈለግ ላይ መዘናጋት
👉የተከለከሉ ካሴቶችን (ኦዲዮዎችን) ማሰራጨት
👉በመንደር ውስጥ መሪ (አሚር) መሾምን መፍቀድ
👉ጥመት ያለባቸውን መጽሐፍት ማሰራጨት
👉በ"ተቂያህ" (እውነታን በመደበቅ) እና በውሸት መማል መሸሸግ
👉መንሐጃቸውን ትቶ ወደ ሰለፊያ መንሐጅ የገባን ሰው ማስፈራራት
👉አንዳቸው ለሌላው ምናባዊ የሆኑ የደረጃ ስሞችን መስጠት
👉ሰውን በሚመልሱበት (በሚተቹበት) ጊዜ መልካም ጎኑንም መጥቀስ ግዴታ ነው
👉ሙዋዘናህ) የሚል አካሄድን መከተል
👉ሰላማዊ ሰልፎችንና አመፆችን ማደራጀት
👉ወጣቶችን በመፈንቅለ መንግስት (ኢንቅላብ) ላይ ማሳደግ
👉ወደ ኸሊፋነት (ብቻ) መጣራት
👉ከወጣት ወንዶች (ቆንጆ ልጆች) ጋር አብሮ መሆን
👉ባለስልጣናትን መቅረብና ከእነሱ ጋር ብዙ ጊዜ መቀመጥ
👉ቢድዓ ያለባቸውን ነሺዳዎች (አናሺዶችን እና ዘፈኖችን ) ማዳመጥ
👉ድራማና ትወናን (ተምሲልን) መፍቀድ
👉በሩቅ ቦታዎች የምሽት ጉዞዎችን (ሽርሽሮችን) ማብዛት
👉ከእያንዳንዱ የኢኽዋን አባል ለቡድኑ ጥቅም ሲባል የተወሰነ ገንዘብ ማስከፈል
👉ወጣቶችን በባዶና ባልሆነ መመሪያቸው ስር ለመሰብሰብ መጓጓት
👉የእነሱ ቡድን በምድር ላይ ካሉ ቡድኖች ሁሉ በላጭ እንደሆነ ማመን
👉በሰለፊዮችና በኢኽዋኖች መካከል ያለው ልዩነት የቅርንጫፍ (የልዩነት አይነት) ብቻ ነው ብሎ መሞገት
👉ዳዕዋ (ጥሪ) ሊሳካ የሚችለው ወደ እነሱ ቡድን በመቀላቀል ብቻ ነው ብሎ መናገር
👉መጽሔቶችንና ጋዜጣዎችን በማንበብ መጠመድ
👉የፖለቲካ ግድያዎችን (ሴራዎችን) ማቀድ
👉ከትናንሽ ልጆች ይልቅ ወጣቶችን ለመሳብ መጓጓት
👉አንዳንድ ይፋዊ (መንግስታዊ) እንቅስቃሴዎችን ለቡድኑ ጥቅም ማዋል
👉መሪዎቻቸውን ማግዘፍና በውዳሴ ላይ ወሰን ማለፍ
👉ከጠማማ ፓርቲዎችና ቡድኖች ጋር በጋራ መስራት
👉ለቡድኑ አገልግሎት ሲባል የመሪነት(ስልጣን ) ቦታዎችን ለማግኘት መጓጓት
👉ወጣቶችን ቀስ በቀስ ወደ ኢኽዋን ድርጅታዊ መዋቅር ማስገባት
👉በኢኽዋን መንሐጅ ላይ ቃልኪዳን (በይዓ) መውሰድ
👉ተውሂድን ከሚይዙ ሰለፊዮች ጋር ጠላትነት መፍጠር
👉ከዓቂዳ (ከእምነት) ውጪ ለትውፊትና ለበጎ ሥነ-ምግባራት (ፈዳኢል) ትኩረት መስጠት
👉የሐጅና የዑምራ ወቅቶችን ወጣቶችን በኢኽዋን አስተሳሰብ አእምሮአቸውን ለማጠብ መጠቀም
👉ወጣቶችን ለመሳብ የመዝናኛ ጉዞዎችን ማብዛት
👉ከሌሎች ይልቅ ብልህና ንቁ የሆኑትን ብቻ መምረጥ
👉የካፊሮችን ምርቶች ማቋረጥ (ቦይኮት ማድረግ) ግዴታ ነው ማለት
👉ስሜታቸውን የሚገጥሙ ፈትዋዎችን ብቻ መውሰድ
👉በፎቶግራፍ (በምስል)ጉዳይ ላይ በጣም መላላት
"ጀሙ አሽ-ሸታት ፊማ ኩቲበ ዐኒል ኢኽዋን" በተሰኘውና በታላቁ ሼክ አህመድ ቢን ያህያ አል-ናጅሚ መቅድም ከተፃፈለት መጽሐፍ።
Repost from ዳዕዋ ሰለፍያ በአልብኮ ወረዳ ሶባ እና ጀብል ቀበሌ(አሸዋዉ) ✈
👉በደዕዋው ላይ ያላችሁ ጀግኖቻችን አብሽሩ
«ማዕበሉን ቅዘፈው»
----------------------
አንተ ለአምላክህ ለእምነትህ ስራ፡
በተቻለህ መጠን ያወቅካትን አቅራ፡
ይሙህ ይቅጠፉብህ ስም አጥፊን አትፍራ፡
መረጃ ሲጠየቅ እየፈረጠጡ፡
ለብቻ ፎክረው ስሜት እየጠጡ፡
እንወያይ ሲባል ፈጥነው እየሮጡ፡
በሐቅ ለመቅጠፍ ምስጥ ሆነው ሲመጡ፡
ሒዝብይ ባህሪው ይህ ነው
የሐቅ ሰዎች ሆይ እንዳትደነግጡ፡
ስትከረችምበት የጥመት በራፉን፡
የቢዲዓው መንጋ ቢከፍትብን አፉን፡
ፈፅሞ አትገረም አታስተውል ፅንፉን፡
#ሱንይ_ከተውሒድ ነው የሚያገኘው ትርፉን፡
ተራ ወሬኛውን እየናቅክ እለፈው፡
ለሽርክ ሩቃ ሁን በሁጃ አስለፍልፈው፡
በመረጃ ጠንክር ሱናውን አግዝፈው፡
ዋና ተለማመድ ማዕበሉን ቅዘፈው፡
.....አብሽር...
....ኑር....
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
↪⭕የስም ሰለፍያ ሳይሆን የተግባር ሰለፍያ ሁኝ እህቴ ሰለፍያ ብለሽ እራስሽን ሰይመሽ የሰለፍ ተግባር ከለለሽ ምኑ ላይ ነው ሰለፍያነቱ ኡውነተኛ የነዛ ጀግና አርአያ ተከታይ
ለኡማው ለልጆቻ ጠቃሚ ሀያእ የለበሰች
ጀግና ሴት ሁኝ በምትሰርያቸው በምተገብርያቸው በምትፅፍያቸው ሁሉ ጠቀቅ በይ እህቴ ይህ ስልክ ኸይር እዳለው ሸርም አለው አጠቃቀምሽን በደምብ ተቆጣጠሪ
እውነት ሀያእ የተላበሰች ሴት በየ ቦታው በየ ሚድያው እራሳን አታረክስም ‼
እህቴ ሀያእ ማለት ምድነው‼
⭕እህቴ እውነት ሀያእ የተላበሰች ሴት በየ ሚድያ ስትኮምት እዚህ ግባ እማይባል ወሬ ሴትም ትሁን ወድጋ ስትለፈልፍ ትውላለች‼
↪እውነት ሀያእ የተላበሰች ሴት ሀጅነቢጋ ስትመላለስ ትውላለች⁉
↪እውነት ሀያእ የተላበሰች ሴት እዚህ ግባ እማይባል ትፖስታለች⁉
↪እውነት ሀያእ የተላበሰች ሴት ዕይባን በየ ቦታው ታወጣለች⁉
↪እውነት ሀያእ የተላበሰች ሴት በየ ሄደችበት ጅል ሳቅ ታበዛለች⁉
↪እውነት ሀያእ የተላበሰች ሴት መገኘት የለለባታ ቦታላይ ትገኛለች⁉
↪እውነት ሀያእ የለበሰች ሴት ፈስቡክ ገብታ ረድ ትሰጣጣለች⁉
🔥ምኑ ላይ ነው ሀያእሽ እህቴ ወዴትስ እያመራሽ ነው⁉
⭕የማንን ተግባር ነው እየተከተልሽ ያለሽው⁉
👑💎ሀያእ ቀስ በቀስ ነው እሚረግፈው ልብ በይ ሀያእሽን እምታከብሪውም እምጥይውም አችው እራስሽ ነሽ!!🍁
🍃ሚድያን ኸይርን ሼር ለማረግ ካልሆነ በስተቀር ለሌላ አትጠቀሚበት🍃
⭕አችው ስለ ሀያእ ትፅፍያለሽ ትፖስቻለሽ መልሰሽ ተወር ብለሽ ሀጅነቢጋ ትካምቻለሽ ትስቂያለሽ⁉
⭕መች ባገባሁ ላጤነት ጠላሁት ያጀግናው ህልሜ መች ይሆን መምጫው የተውሂዱ ጀግና እያልሽ በየ ሚድያ እምፅፊው ምን ይሉታል ይህንስ ለማን ነበር ማማከር ያለብሽ?? ያረብ ብለሽ ሁሌም በድአሽ ሳሊሁን እዲወፍቅሽ ዱአ ማረግ ሲገባሽ ሚድያላይ ወተሽ ወንድሞችሽን ግራ ታጋቢያለሽ‼
➡ሁኖም ቡዙ ወንድሞችም አሉ ይህን ክፉ ተግባር የተላበሱ ይህ ነው ሱኒ መሆን ይህ ነው የጀግኖች ተግባር እሳ ትኮምታለች እሱም ስር ገብቶ ይኮምታል የታለ ሰለፍነቱ መልሰው ሀያእ የተላበሰች ሴት ለትዳር ይፈልጋሉ እሱ ራሱ ሀያአን እያስገፈፈ ይህ ነው የነዛ የጀግኖች ተግባር⁉
💦ሲጋቡ በሚድያ!! ሲጣሉ በሚድያ!! ለሀላሉ ፍቅሩን እሚገልፅላት በሚድያ!! በቃ ነውርን በቤት መሸፈን የለም ሀላ የሰው አይን ሆነብን ብለው ኡኡ ይላሉ ማነው ስተተኛው ማነው ጥፋተኛው⁉
ሰለፍነት በስም! በግጥም! በወሬ! አይደለም‼
🎀ሰለፍነት በተግባር ሰለፍነት ሰለፎችን በመከተል ነው።።🎀
🍃የተግባር ሰዎች እንሁን ባረከላሁ ፊኩም🍃
👉 ዛሬ ላይ የደረስነው እኛ ጠንካራ
ስለሆንን ሳይሆን፣ አላህ በጥላው
ስር ስለጠበቀን ነው እቅዳችን
ሳይሆን የእሱ እዝነት ነው ያሻገረን!
⚠️ "አንተ ለእኔ አባቴም፣ ወንድሜም ነህ ማለት ይቻላልን!"⁉️
ብዙ ጊዜ ሚስቶች ለባሎቻቸው ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር፣ ክብርና መተማመን ለመግለጽ "አንተ ለእኔ ባለቤቴ ብቻ አይደለህም፤ አባቴም፣ ወንድሜም፣ በዱንያ ያለኝ ነገር ሁሉ ነህ" ይላሉ። ታዲያ ይህ ንግግር በሸሪዓው እንዴት ይታያል? ትዳርን ያፈርሳልን?
⚠️ ሸይኽ ዑሰይሚን እንዲህ ተጠየቁ፦⁉️
ጥያቄ፦ "ሚስቴ ሁሌም 'አንተ ባለቤቴ፣ ወንድሜ፣ አባቴና በዱንያ ላይ ያለኝ ነገር ሁሉ ነህ' ትለኛለች። ይህ ንግግሯ እሷን በእኔ ላይ ሐራም ያደርጋታልን (ትዳራችን ይፈርሳልን)?"❓
ሸይኹ እንዲህ ሲሉ መለሱ፦
> "ይህ ንግግሯ እሷን በአንተ ላይ ሐራም አያደርጋትም። ምክንያቱም 'አንተ አባቴና ወንድሜ ነህ' ስትል ትርጉሙ፦ አንተ ለእኔ ያለህ ክብር፣ የምትሰጠኝ እንክብካቤና ጥበቃ ልክ እንደ አባቴና እንደ ወንድሜ ደረጃ ነው ለማለት እንጂ፤ በአንተ ላይ ሐራም ለመሆን ፈልጋ አይደለም!"
🔍 ሸይኹ አክለውም እንዲህ አሉ፦
"አንዲት ሴት ሆን ብላ አንተን እንደ አባቷ ወይም ወንድሟ አድርጋ ሐራም ለማድረግ ብታስብ እንኳ፤ በሸሪዓው 'ዚሃር' (ሚስትን እንደ እናት ማመሳሰል) የሚፈጸመው በወንዶች ላይ እንጂ በሴቶች ላይ አይደለም።"
አንዲት ሴት ለባሏ "አንተ በእኔ ላይ እንደ አባቴ ወይም እንደ ወንድሜ ጀርባ ነህ" ብትል እንኳ ብይኑ እንደ መሐላ (የሚን) ነው የሚታየው። ይህም ማለት፦
1. ወደ ትዳር ግንኙነት ከመመለሷ በፊት የመሐላ ማስረዣ (ከፋራ) መክፈል ይኖርባታል።
2. የመሐላ ማስረዣውም፦ 10 ምስኪኖችን ማብላት፣ ወይም ማልበስ፣ ወይም አንድ ባሪያ ነፃ ማውጣት ነው። ይህንን ካልቻለች ደግሞ 3 ቀን መጾም ይኖርባታል። 🍲👕🌙
ስለዚህ ውድ ወንድሞች! ሚስቶቻችሁ ፍቅራቸውንና ክብራቸውን ለመግለጽ የሚጠቀሙባቸው እነዚህ ቃላት ትዳራችሁን አያፈርሱም። ይልቁንም የእናንተን መልካም አያያዝ የሚመሰክሩ ጣፋጭ ቃላት ናቸው።
አላህ ትዳራችሁን በበረካና በጥበብ ያስውብላችሁ!
*(ምንጭ፦ ፈታዋ አል-መርአህ አል-ሙስሊማህ፣ 2/803)*
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
''እውነቱን ተናግረህ የምታጣው ነገር ቢኖር በአጠገብህ ያሉትን ውሸታም ሰዎችን ብቻ ነው።!"
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/Abulabas1444
t.me/Abulabas1444
⚠️"ሚስት ለባልዋ የዓይን ማረፊያ (ቁረተ ዐይን) የምትሆነው መቼ ነው?"
በትዳር ውስጥ ትልቁ ስኬትና ደስታ የትዳር አጋርህ ለዓይንህ ማረፊያ፣ ለልብህ ደግሞ የሰላም ምንጭ ሲሆን ነው። ይህ "ቁረተ አይን" የሚባለው ታላቅ ጸጋ መቼና እንዴት እንደሚገኝ ታላቁ ዓሊም ሼክ ኢብኑ ዑሰይሚን (ረሒመሁላህ) እንዲህ ሲሉ ይነግሩናል፦
⁉️ጥያቄ፦ "ሚስት ለባልዋ የዓይን ማረፊያ (ቁረተ አይን) የምትሆነው መቼ ነው?"
ሼኩ እንዲህ ሲሉ መለሱ፦
"ሚስት ለባልዋ፣ ባልም ለሚስቱ የዓይን ማረፊያና የልብ ሰላም የሚሆኑት፤ ሁለቱም በአላህ ሃይማኖት (ዲን) ውስጥ በእነርሱ ላይ ግዴታ የሆኑባቸውን መብቶችና ግዴታዎች በትክክል ሲወጡ ብቻ ነው።"
🌟 በትዳር ውስጥ ትልቁ ደስታ የአላህን ድንበር ማክበር ነው
⚠️ትዳር የተባረከ ይሆን ዘንድ መሠረቱ አላህን መፍራት ነው። ባል አላህን ፈርቶ የሚስቱን መብት ሲያከብር፣ ሚስትም አላህን ፈርታ ለባሏ ያላትን ግዴታ ስትወጣ፤ አላህ በመካከላቸው ልዩ የሆነ ፍቅርንና እዝነትን ያሰፍናል። የትዳር ጣዕም የሚመነጨው ከአላህ ትዕዛዝ ስር ነውና።
⚠️ባልሽ ወይም ሚስትህ ለዓይንሽ ማረፊያ እንዲሆኑ ከፈለግሽ/ህ፣ መጀመሪያ ከአላህ ጋር ያላችሁን ግንኙነት አሳምሩ። አላህን
ስታስደስቱ፣ እርሱ ደግሞ በመካከላችሁ ያለውን ግንኙነት ያሳምርላችኋል። ዲኑን የጠበቀ ትዳር የዱንያ ጀነት ነው!
⚠️ እውነተኛ የትዳር እርካታ የሚገኘው በቁሳቁስ ብዛት ሳይሆን፣ አላህ በሰጣችሁ ኃላፊነት ላይ ታማኝ ስትሆኑ ነው።
አላህ ትዳራችሁን የሰላም፣ የፍቅርና የአይን ማረፊያ ምንጭ ያድርግላችሁ።
(ምንጭ፦ አል-ሊቃእ አል-ሸህሪ፣ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሂመሁሏ - 40)
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
قال ابن القيم -عن يوم الجمعة-: «وهو في الأيام كشهر رمضان في الشهور، وساعة الإجابة فيه كليلة القدر في رمضان.
ولهذا من صحَّ له يومُ جمعته وسلِمَ؛ سلِمَتْ له سائرُ جمعته.
ومن صحَّ له رمضانُ وسَلِم؛ صحَّت له سائرُ سَنته.
ومن صحَّت له حجَّته وسلِمَتْ؛ صحَّ له سائر عُمره.
فيومُ الجمعة ميزان الأسبوع،
ورمضانُ ميزان العام،
والحجُّ ميزان العمر».
«زاد المعاد» ٤٩٢/١
አላህ ሆይ!
እሰው ፊት ከመቆም፣የሰው እጅ ከማየት፣ጤናን ከማጣት አንተው ጠብቀን።
