es
Feedback

¡No caigas en manos de tramposos! Telemetrio encuentra y marca estos canales 👉 Si quieres ver la etiqueta, suscríbete

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)

Ir al canal en Telegram

قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.

Mostrar más
El país no está especificadoLa categoría no está especificada
899
Suscriptores
-124 horas
-177 días
+3530 días
Archivo de publicaciones
👉በደዕዋው ላይ ያላችሁ ጀግኖቻችን አብሽሩ «ማዕበሉን ቅዘፈው» ---------------------- አንተ ለአምላክህ ለእምነትህ ስራ፡ በተቻለህ መጠን ያወቅካትን አቅራ፡ ይሙህ ይቅጠፉብህ ስም አጥፊን አትፍራ፡ መረጃ ሲጠየቅ እየፈረጠጡ፡ ለብቻ ፎክረው ስሜት እየጠጡ፡ እንወያይ ሲባል ፈጥነው እየሮጡ፡ በሐቅ ለመቅጠፍ ምስጥ ሆነው ሲመጡ፡ ሒዝብይ ባህሪው ይህ ነው የሐቅ ሰዎች ሆይ እንዳትደነግጡ፡ ስትከረችምበት የጥመት በራፉን፡ የቢዲዓው መንጋ ቢከፍትብን አፉን፡ ፈፅሞ አትገረም አታስተውል ፅንፉን፡ #ሱንይ_ከተውሒድ ነው የሚያገኘው ትርፉን፡ ተራ ወሬኛውን እየናቅክ እለፈው፡ ለሽርክ ሩቃ ሁን በሁጃ አስለፍልፈው፡ በመረጃ ጠንክር ሱናውን አግዝፈው፡ ዋና ተለማመድ ማዕበሉን ቅዘፈው፡ .....አብሽር... ....ኑር.... t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

↪⭕የስም ሰለፍያ ሳይሆን የተግባር ሰለፍያ ሁኝ እህቴ ሰለፍያ ብለሽ እራስሽን ሰይመሽ የሰለፍ ተግባር ከለለሽ ምኑ ላይ ነው ሰለፍያነቱ ኡውነተኛ የነዛ ጀግና አርአያ ተከታይ ለኡማው ለልጆቻ ጠቃሚ ሀያእ የለበሰች ጀግና ሴት ሁኝ በምትሰርያቸው በምተገብርያቸው በምትፅፍያቸው ሁሉ ጠቀቅ በይ እህቴ ይህ ስልክ ኸይር እዳለው ሸርም አለው አጠቃቀምሽን በደምብ ተቆጣጠሪ እውነት ሀያእ የተላበሰች ሴት በየ ቦታው በየ ሚድያው እራሳን አታረክስም ‼ እህቴ ሀያእ ማለት ምድነው‼ ⭕እህቴ እውነት ሀያእ የተላበሰች ሴት በየ ሚድያ ስትኮምት እዚህ ግባ እማይባል ወሬ ሴትም ትሁን ወድጋ ስትለፈልፍ ትውላለች‼ ↪እውነት ሀያእ የተላበሰች ሴት ሀጅነቢጋ ስትመላለስ ትውላለች⁉ ↪እውነት ሀያእ የተላበሰች ሴት እዚህ ግባ እማይባል ትፖስታለች⁉ ↪እውነት ሀያእ የተላበሰች ሴት ዕይባን በየ ቦታው ታወጣለች⁉ ↪እውነት ሀያእ የተላበሰች ሴት በየ ሄደችበት ጅል ሳቅ ታበዛለች⁉ ↪እውነት ሀያእ የተላበሰች ሴት መገኘት የለለባታ ቦታላይ ትገኛለች⁉ ↪እውነት ሀያእ የለበሰች ሴት ፈስቡክ ገብታ ረድ ትሰጣጣለች⁉ 🔥ምኑ ላይ ነው ሀያእሽ እህቴ ወዴትስ እያመራሽ ነው⁉ ⭕የማንን ተግባር ነው እየተከተልሽ ያለሽው⁉ 👑💎ሀያእ ቀስ በቀስ  ነው እሚረግፈው  ልብ በይ ሀያእሽን እምታከብሪውም እምጥይውም አችው እራስሽ ነሽ!!🍁 🍃ሚድያን ኸይርን ሼር ለማረግ ካልሆነ በስተቀር ለሌላ አትጠቀሚበት🍃 ⭕አችው ስለ ሀያእ ትፅፍያለሽ ትፖስቻለሽ መልሰሽ ተወር ብለሽ ሀጅነቢጋ ትካምቻለሽ ትስቂያለሽ⁉ ⭕መች ባገባሁ ላጤነት ጠላሁት ያጀግናው ህልሜ መች ይሆን መምጫው የተውሂዱ ጀግና እያልሽ በየ ሚድያ እምፅፊው ምን ይሉታል ይህንስ ለማን ነበር ማማከር ያለብሽ?? ያረብ ብለሽ ሁሌም በድአሽ ሳሊሁን እዲወፍቅሽ ዱአ ማረግ ሲገባሽ ሚድያላይ ወተሽ ወንድሞችሽን ግራ ታጋቢያለሽ‼ ➡ሁኖም ቡዙ ወንድሞችም አሉ ይህን ክፉ ተግባር የተላበሱ ይህ ነው ሱኒ መሆን ይህ ነው የጀግኖች ተግባር እሳ ትኮምታለች እሱም ስር ገብቶ ይኮምታል የታለ ሰለፍነቱ መልሰው ሀያእ የተላበሰች ሴት ለትዳር ይፈልጋሉ እሱ ራሱ ሀያአን እያስገፈፈ ይህ ነው የነዛ የጀግኖች ተግባር⁉ 💦ሲጋቡ በሚድያ!! ሲጣሉ በሚድያ!! ለሀላሉ ፍቅሩን እሚገልፅላት በሚድያ!! በቃ ነውርን በቤት መሸፈን የለም ሀላ የሰው አይን ሆነብን ብለው ኡኡ ይላሉ ማነው ስተተኛው ማነው ጥፋተኛው⁉ ሰለፍነት በስም! በግጥም!  በወሬ! አይደለም‼ 🎀ሰለፍነት በተግባር ሰለፍነት ሰለፎችን በመከተል ነው።።🎀 🍃የተግባር ሰዎች እንሁን ባረከላሁ ፊኩም🍃

👉 ዛሬ ላይ የደረስነው እኛ ጠንካራ ስለሆንን ሳይሆን፣ አላህ በጥላው ስር ስለጠበቀን ነው እቅዳችን ሳይሆን የእሱ እዝነት ነው ያሻገረን!

⚠️ "አንተ ለእኔ አባቴም፣ ወንድሜም ነህ ማለት ይቻላልን!"⁉️ ብዙ ጊዜ ሚስቶች ለባሎቻቸው ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር፣ ክብርና መተማመን ለመግለጽ "አንተ ለእኔ ባለቤቴ ብቻ አይደለህም፤ አባቴም፣ ወንድሜም፣ በዱንያ ያለኝ ነገር ሁሉ ነህ" ይላሉ። ታዲያ ይህ ንግግር በሸሪዓው እንዴት ይታያል? ትዳርን ያፈርሳልን? ⚠️ ሸይኽ ዑሰይሚን እንዲህ ተጠየቁ፦⁉️ ጥያቄ፦ "ሚስቴ ሁሌም 'አንተ ባለቤቴ፣ ወንድሜ፣ አባቴና በዱንያ ላይ ያለኝ ነገር ሁሉ ነህ' ትለኛለች። ይህ ንግግሯ እሷን በእኔ ላይ ሐራም ያደርጋታልን (ትዳራችን ይፈርሳልን)?"❓ ሸይኹ እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ > "ይህ ንግግሯ እሷን በአንተ ላይ ሐራም አያደርጋትም። ምክንያቱም 'አንተ አባቴና ወንድሜ ነህ' ስትል ትርጉሙ፦ አንተ ለእኔ ያለህ ክብር፣ የምትሰጠኝ እንክብካቤና ጥበቃ ልክ እንደ አባቴና እንደ ወንድሜ ደረጃ ነው ለማለት እንጂ፤ በአንተ ላይ ሐራም ለመሆን ፈልጋ አይደለም!" 🔍 ሸይኹ አክለውም እንዲህ አሉ፦ "አንዲት ሴት ሆን ብላ አንተን እንደ አባቷ ወይም ወንድሟ አድርጋ ሐራም ለማድረግ ብታስብ እንኳ፤ በሸሪዓው 'ዚሃር' (ሚስትን እንደ እናት ማመሳሰል) የሚፈጸመው በወንዶች ላይ እንጂ በሴቶች ላይ አይደለም።" አንዲት ሴት ለባሏ "አንተ በእኔ ላይ እንደ አባቴ ወይም እንደ ወንድሜ ጀርባ ነህ" ብትል እንኳ ብይኑ እንደ መሐላ (የሚን) ነው የሚታየው። ይህም ማለት፦ 1. ወደ ትዳር ግንኙነት ከመመለሷ በፊት የመሐላ ማስረዣ (ከፋራ) መክፈል ይኖርባታል። 2. የመሐላ ማስረዣውም፦ 10 ምስኪኖችን ማብላት፣ ወይም ማልበስ፣ ወይም አንድ ባሪያ ነፃ ማውጣት ነው። ይህንን ካልቻለች ደግሞ 3 ቀን መጾም ይኖርባታል። 🍲👕🌙 ስለዚህ ውድ ወንድሞች! ሚስቶቻችሁ ፍቅራቸውንና ክብራቸውን ለመግለጽ የሚጠቀሙባቸው እነዚህ ቃላት ትዳራችሁን አያፈርሱም። ይልቁንም የእናንተን መልካም አያያዝ የሚመሰክሩ ጣፋጭ ቃላት ናቸው። አላህ ትዳራችሁን በበረካና በጥበብ ያስውብላችሁ! *(ምንጭ፦ ፈታዋ አል-መርአህ አል-ሙስሊማህ፣ 2/803)* t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

   ''እውነቱን ተናግረህ የምታጣው ነገር ቢኖር በአጠገብህ ያሉትን ውሸታም ሰዎችን ብቻ ነው።!" የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/Abulabas1444 t.me/Abulabas1444

⚠️"ሚስት ለባልዋ የዓይን ማረፊያ (ቁረተ ዐይን) የምትሆነው መቼ ነው?" በትዳር ውስጥ ትልቁ ስኬትና ደስታ የትዳር አጋርህ ለዓይንህ ማረፊያ፣ ለልብህ ደግሞ የሰላም ምንጭ ሲሆን ነው። ይህ "ቁረተ አይን" የሚባለው ታላቅ ጸጋ መቼና እንዴት እንደሚገኝ ታላቁ ዓሊም ሼክ ኢብኑ ዑሰይሚን (ረሒመሁላህ) እንዲህ ሲሉ ይነግሩናል፦ ⁉️ጥያቄ፦ "ሚስት ለባልዋ የዓይን ማረፊያ (ቁረተ አይን) የምትሆነው መቼ ነው?" ሼኩ እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ "ሚስት ለባልዋ፣ ባልም ለሚስቱ የዓይን ማረፊያና የልብ ሰላም የሚሆኑት፤ ሁለቱም በአላህ ሃይማኖት (ዲን) ውስጥ በእነርሱ ላይ ግዴታ የሆኑባቸውን መብቶችና ግዴታዎች በትክክል ሲወጡ ብቻ ነው።" 🌟 በትዳር ውስጥ ትልቁ ደስታ የአላህን ድንበር ማክበር ነው ⚠️ትዳር የተባረከ ይሆን ዘንድ መሠረቱ አላህን መፍራት ነው። ባል አላህን ፈርቶ የሚስቱን መብት ሲያከብር፣ ሚስትም አላህን ፈርታ ለባሏ ያላትን ግዴታ ስትወጣ፤ አላህ በመካከላቸው ልዩ የሆነ ፍቅርንና እዝነትን ያሰፍናል። የትዳር ጣዕም የሚመነጨው ከአላህ ትዕዛዝ ስር ነውና። ⚠️ባልሽ ወይም ሚስትህ ለዓይንሽ ማረፊያ እንዲሆኑ ከፈለግሽ/ህ፣ መጀመሪያ ከአላህ ጋር ያላችሁን ግንኙነት አሳምሩ። አላህን ስታስደስቱ፣ እርሱ ደግሞ በመካከላችሁ ያለውን ግንኙነት ያሳምርላችኋል። ዲኑን የጠበቀ ትዳር የዱንያ ጀነት ነው! ⚠️ እውነተኛ የትዳር እርካታ የሚገኘው በቁሳቁስ ብዛት ሳይሆን፣ አላህ በሰጣችሁ ኃላፊነት ላይ ታማኝ ስትሆኑ ነው። አላህ ትዳራችሁን የሰላም፣ የፍቅርና የአይን ማረፊያ ምንጭ ያድርግላችሁ። (ምንጭ፦ አል-ሊቃእ አል-ሸህሪ፣ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሂመሁሏ - 40) t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy

﴿رَبِّ إِنَّهُنَّ أَضلَلنَ كَثيرًا مِنَ النّاسِ﴾ - محمد أيوب

قال ابن القيم -عن يوم الجمعة-: «وهو في الأيام كشهر رمضان في الشهور، وساعة الإجابة فيه كليلة القدر في رمضان. ولهذا من صحَّ له يومُ جمعته وسلِمَ؛ سلِمَتْ له سائرُ جمعته. ومن صحَّ له رمضانُ وسَلِم؛ صحَّت له سائرُ سَنته. ومن صحَّت له حجَّته وسلِمَتْ؛ صحَّ له سائر عُمره. فيومُ الجمعة ميزان الأسبوع، ورمضانُ ميزان العام، والحجُّ ميزان العمر». «زاد المعاد» ٤٩٢/١

አላህ ሆይ! እሰው ፊት ከመቆም፣የሰው እጅ ከማየት፣ጤናን ከማጣት አንተው ጠብቀን።

✍          [  سنن يوم الجمعة ] قال فضيلة الشيخ العلامة محمد بن صالح العثيمين -  رحمه الله تعالى - : ➊ قراءة سورة الكهف . ➋ الإغتسال . ➌ السواك . ➍ الطيب . ➎ التبكير إليها، أن يبكر حين تطلع الشمس . ➏ أن يلبس الإنسان أحسن ثيابه التي عنده سواء كان جديداً أم غسيلاً . ➐ يتحرى الدعاء لأن في الجمعة ساعة لا يوافقها عبد مسلم يسأل الله شيئاً وهو قائم يصلي إلا أعطاه إياه . ➑ أن يكثر من الصلاة على النبي ﷺ . ( لقاء الباب المفتوح، 105). = የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/Abulabas1444 t.me/Abulabas1444

የሙሐደራ ማስታወቂያ ተጋባዥ እንግዶች፦ 1. ኡስታዝ ኢብኑ መነወር ርዕስ፦ { العذر بالجهل } 2. ዶ/ር ሰዒድ ሙሳ ርዕስ፦ { التسرع في التبديع } 3. ዶ/ር ሑሰይን ዓሊ ርዕስ፦ { خطر التعصب } ፕሮግራሙ በአቡ ሂበቲላህ እና በአቡ ሐኒፋ የሚመራ ይሆናል። የፊታችን ጁሙዓ ከምሽቱ 3:00pm በኢትዮ አድራሻ፦ ዳሩ ተውሒድ https://s.imoim.net/A6NRGx?from=copy_link

❌ ድንግል ያልሆነች ሴት አታግባ”❌                ግን ለምን ⁉️ ​በአሁኑ ወቅት በየሚዲያውና በየሶሻል ሚዲያው ሰልጥነናል በሚሉ፣ ነገር ግን የዕውቀትና የሃይማኖት ጠብታ በሌላቸው “ጃሂሎች” የሚነገሩ ቃላትንና የሚሰነዘሩ አስተያየቶችን እንታዘባለን። ከእነዚህም መካከል ትልቁ ማስተዋያ አልባነታቸውን የሚያሳየው “ድንግል ያልሆነች ሴት አታግባ” እያሉ በሴቶች ክብር ላይ የሚቀልዱትና የማይገባቸውን ስም የሚለጥፉት አጉል ሰለጠንኩ ባዮች ናቸው። ​እነዚህ አካላት ሊያውቁት የሚገባው ትልቅ እውነት አለ፦ ሴት ልጅ ማለት ከምንም በላይ በእስልምና ውስጥ ታላቅ ክብርና ቦታ የተሰጣት ውድ ፍጡር ናት! 💢 ​በቅድሚያ የነቢያችን (ﷺ) ህይወት እና የእስልምና ሚዛን ምን ይመስል ነበር የሚለውን እናያለን ​እነዚህ አጉል ሰለጠንኩ ባዮች የንፅህና ሚዛናቸውን ከራሳቸው ጠባብ አስተሳሰብ ሲቀዱ፣ እስልምና ግን ንፅህናንና ክብርን የሚያየው ከልብ፣ ከአኽላቅ (መልካም ስነ-ምግባር) እና ከእምነት ጥንካሬ ነው። ​ለመሆኑ እነዚህ ሰዎች የዓለማቱ እዝነት የሆኑትን የነብያችንን (ﷺ) የትዳር ህይወት አያውቁትም? ​የነቢያችን (ﷺ) የመጀመሪያ፣ ተወዳጅና የልባቸው ማረፊያ የነበሩት እናታችን ኸዲጃ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ድንግል አልነበሩም። ነገር ግን በታሪክ “ጧሂራህ” (ንፅህቷ) በሚል ስም የምትታወቅ፣ ነቢያችንን በገንዘቧ፣ በጉልበቷና በሃሳቧ የደገፈች ታላቅ ሴት ናት። ​ከእናታችን ዓኢሻ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ውጭ የነቢያችን (ﷺ) ሚስቶች በሙሉ (የሙዕሚኖች እናቶች) ቀደም ሲል ትዳር የነበራቸው፣ የፈቱ ወይም ባሎቻቸው የሞቱባቸው ነበሩ። ⁉️ ​ታዲያ እነዚህ አጉል ሰለጠንኩ ባዮች ከነብዩ (ﷺ) በላይ ሊያስተምሩን ነውን? ድንግልናን ብቻ የሴት ልጅ ብቸኛ የክብር መለኪያ አድርጎ ማስቀመጥ የጃሂሊያ (የድንቁርና) ዘመን አስተሳሰብ እንጂ የስልጣኔ ምልክት አይደለም። 💢​ ሌላው ደግሞ ሴት ልጅ በእስልምና ያላት የክብር ከፍታ ምን ይመሳላል⁉️ ​እስልምና ለሴት ልጅ የሰጣት ክብር ፍፁም ወደር የለውም። ሴት ልጅ በየደረጃው የጀነት መክፈቻ ቁልፍ ናት፦ ● ​ልጅ ስትሆን፦ በጥሩ ሁኔታ ላሳደጋትና ላስተማራት አባት ለጀነት መግቢያ ሰበብ ናት። ● ​ሚስት ስትሆን፦ የባሏን ዲን (እምነት) ግማሽ የምታሟላ፣ የቤቱ ንግስት ናት። ● ​እናት ስትሆን ደግሞ፦ “ጀነት ከእናቶች እግር በታች ናት” ተብሎ የተነገረላት፣ የሰው ልጅ ሁሉ ሊያከብራትና ሊንከባከባት የሚገባ ታላቅ መድረክ ናት። ​ሴት ልጅ በተለያዩ የህይወት አጋጣሚዎች (በትዳር መፍረስ፣ በሞት ወይም በተለያዩ ፈተናዎች) ድንግልናዋን ልታጣ ትችላለች። ይህ ማለት ግን ክብሯ ቀነሰ፣ ትዳር አይገባትም ማለት በፍጹም አይደለም! 👁‍🗨 ይልቁኑ በእስልምና መስፈርት ትልቁ ሚዛን ዲን (እምነት) እና መልካም ስነ-ምግባር ነው። ነቢያችን (ﷺ) በትዳር ጊዜ እንድንመርጥ ያዘዙን ባለዲኗን ሴት እንጂ ሌላ አይደለም። ​ወንድሞቼ ሆይ! በሚዲያ ላይ በሚለቀቁ የድንቁርና መርዞች አትታለሉ። አንዲት ሴት መልካም ስነ-ምግባር ካላት፣ አላህን የምትፈራ ከሆነች፣ ለትዳሯ ታማኝና አፍቃሪ ከሆነች እሷ የአይን ማረፊያና የዱንያ ትልቁ ጸጋ ናት። ​እህቶቻችን፣ እናቶቻችንና ሚስቶቻችን ሊከበሩ፣ ሊጠበቁና ሊወደዱ ይገባቸዋል። በምላሳችን የምንወረውረው ቃል ልባቸውን እንዳይሰብረው እንጠንቀቅ። እውነተኛ ስልጣኔ የአላህን ዲን ማወቅ፣ የነብዩን (ﷺ) ሱና መከተልና ለሴቶች የሚገባውን ክብር መስጠት ብቻ ነው።
​"ከናንተ መካከል ምርጡ ማለት ለሚስቱ (ለቤተሰቡ) መልካምና ገር የሆነው ነው!" — ነብዩ ሙሐመድ (ﷺ)
​አላህ እውነተኛውን እውቀት ይስጠን፤ እህቶቻችንንም በኢስላም ጥላ ስር ክብራቸውን ጠብቆ ያኑርልን። አሚን። 👉✍𝓪𝓫𝓾 𝓶𝓪𝓱𝓲 𝓲𝓫𝓷𝓾 𝓲𝓭𝓻𝓲𝓼 ሼር እያደረጋችሁ ተቀላቀሉ፣ትጠቀሙበታላችሁ https://t.me/BerhanFelega https://t.me/BerhanFelega

⚠️ አትናገረው ወይም አተግብረው! ረሱል (📿) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿إِنَّ اللَّهَ تَجَاوَزَ لِأُمَّتِي عَمَّا وَسْوَسَتْ أَوْ حَدَّثَتْ بِهِ أَنْفُسَهَا، مَا لَمْ تَعْمَلْ بِهِ أَوْ تَكَلَّمْ﴾ “አላህ ለኡመቴ (ለሕዝቦቼ) በልባቸው ውስጥ የሚመላለሰውንና ነፍሳቸው የምታወራውን (መጥፎ ሃሳብ) ይቅር ብሏቸዋል። እስካልተገበሩት ወይም እስካልተናገሩት ድረስ።” 📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 6664 🟧🟧🟧🟧🟧🟧🟧

أبرز صفات السلف الصالح ومنهجهم السلف الصالح هم أهل القرون المفضلة الذين شهد لهم النبي ﷺ بالخيرية، وهم الصحابة والتابعون وأتباعهم بإحسان، الذين ساروا على كتاب الله وسنة رسوله ﷺ بفهمٍ صحيحٍ وعملٍ صادق. ومن أعظم صفاتهم: ١- التمسك بالكتاب والسنة فكانوا يجعلون القرآن والسنة أصلَ كلِّ اعتقادٍ وعبادةٍ ومعاملة، لا يقدمون قول أحدٍ على كلام الله ورسوله ﷺ. ٢- فهم الدين بفهم الصحابة رضي الله عنهم فلم يكونوا يخترعون طرقًا جديدة في الدين، بل كانوا يحرصون على اتباع الطريق الذي سار عليه النبي ﷺ وأصحابه. ٣- تحقيق التوحيد والإخلاص كانوا يخلصون العبادة لله وحده، ويحذرون من الشرك والرياء وكل ما يفسد عبودية القلب لله تعالى. ٤- اتباع السنة والحذر من البدع كانوا يعظمون سنة النبي ﷺ، ويحذرون من كل أمرٍ محدثٍ في الدين يخالف هديه ﷺ. ٥- العلم والعمل لم يكن علمهم مجرد معلومات، بل كان علمًا يقود إلى العمل والخشية والتواضع، قال الله تعالى: ﴿إِنَّمَا يَخْشَى اللَّهَ مِنْ عِبَادِهِ الْعُلَمَاءُ﴾ [فاطر: 28] ٦- الوسطية والاعتدال فهم بعيدون عن الغلو والتشدد، كما أنهم بعيدون عن التمييع والتفريط، يسيرون على الصراط المستقيم بلا إفراط ولا تفريط. ٧- تعظيم العلماء واحترام أهل العلم كانوا يعرفون لأهل العلم مكانتهم، ويرجعون إلى العلماء في النوازل والمسائل، مع بقاء الاتباع للدليل. ٨- التواضع وحسن الخلق فمع علمهم وفضلهم كانوا أشد الناس تواضعًا، ورحمةً بالخلق، وحسنًا في التعامل. ٩- الصبر والثبات على الحق كانوا يصبرون على الطاعة، وعن المعصية، وعلى ما يصيبهم في طريق الدعوة إلى الله. ١٠- سلامة القلوب كانوا يحرصون على طهارة قلوبهم من الحسد والكبر والبغضاء، ويحبون الخير للمسلمين. ١١- الأمر بالمعروف والنهي عن المنكر بالحكمة كانوا يدعون إلى الله بعلمٍ ورحمةٍ وحكمة، لا بالجهل ولا بالظلم. ١٢- الخوف من الله ومحاسبة النفس كانوا يخافون من التقصير، ويجتهدون في إصلاح أنفسهم قبل الانشغال بعيوب الآخرين. فهذه هي معالم طريق السلف الصالح: علمٌ صحيح، وعقيدةٌ سليمة، وعبادةٌ خالصة، واتباعٌ للسنة، وأخلاقٌ كريمة، واعتدالٌ في المنهج. https://t.me/A2mnt

አይ ሞት!! ​ቀን በቀን ሳናዉቀዉ ዕድሜያችን እየገፋ ወደ ሞት እየሄድን ነው፤ አንድ ቀን መድረሳችንም የማይቀር እውነት ነው። ዋናው የሚያሳስበን መቼ ነው የምንደርሰው ሳይሆን፣ «ከሞት በኋላ ምንድነው የሚጠብቀን?» የሚለው ጥያቄ ነው። الْمَوْتُ بَابٌ وَكُلُّ النَّاسِ دَاخِلُهُ فَلَيْتَ شِعْرِي بَعْدَ الْبَابِ مَا الدَّارُ؟ የቴሌግራም ቻናል፦ t.me/Abulabas1444 t.me/Abulabas1444

Repost from Dr. Seid Musa
✏️ [ ምስጋናን ችላ ማለት ] ሳሊህ አድ'ዲማሽቂይ - አላህ ይዘንላቸውና - ልጃቸውን እንዲህ ሲሉ መከሩ፦ “ልጄ ሆይ! እምነትህ፣ ሰውነትህ፣ ሀብትህ እና ቤተሰብህ ደህና የሆኑበት ቀንና ሌሊት ካለፈ፣ ለጌታህ አላህ - ሱብሐነሁ ወተዓላ - ብዙ ምስጋናን አቅርብ። በዚያ ቀን ስንት እና ስንት ሰዎች እምነታቸውን አጥተዋል፣ ንብረታቸውን ተነጥቀዋል፣ ክብራቸው ተጎድሏል፣ ጀርባቸው ተሰብሮ፣ አንተ ግን በጥሩ ጤንነት ላይ ነህ። (ስለዚህ አላህን ተገቢ የሆነን ምስጋና አመስግነው)።” [ የደማስቆ ታሪክ ቅጽ : 23 ገጽ : 325 ] = የቴሌግራም ቻናል https://t.me/AbulbukhariSeid

👉⭕️ለላጤወች አድርሱልኝ 🛡ለምን አታገባም⁉️🛡 አልሀምዱሊላሂ ሊመሊከል ቁዱስ ሶመ ሶላቱሁ መዲነቲል አሩስ ጌታችን በእዝነቱ ሀላልን ፈቀደ አግብቶ መኖርን መውለድም ላቀደ ያ ማእሸረ ሸባብ አሉና ጀግናችን ለቻለ ሰው ብለው ጠርተው በስማችን ያግባ እና ይጠንክር ከሀራም ይጠበቅ ያልቻለ ሰው ይፁም በተቅዋ እንዲመጥቅ 💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎 በሌላም ዘገባ ኢማሙ ሷኢሚን መክረዋል ወጣቱን ሙሀመዱል አሚን ያገባ ሰውማ በሀላሉ መንገድ ሸርጥ ሳያበዛ ሳይሄድ ወደ ፈሳድ ከመለ ኒስፉሁ ተማሏ ኢማኑ ፉል ይሆንለታል በአላህ የማመኑ በግማሹ ደግሞ ከዚህ በተረፈ አላህን ይፍራበት አመፅ በቀረፈ አወ ኒካህ ማለት ሰበብ ነው ለሪዝቅህ አግባና ፈልገው አላህ ይጠብቅህ የነብያት ሱና ፈለግ ነው ጎዳና ፀጋ ነው መከበር ደስታ የሰኪና 💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎 ሷሊህ ለወፈቀው ፀባይዋ ገራገር በተውሂድ ተውባ አምራ ሳትበገር ሰፈሯ ያደገች ወንዝ ሳትሻገር ሽርክያት እርቃ ሳታልፍ ከድንበር በሱና ያጌጠች ጃዳ ሰለፍያ ፈና ፈኑን ያየች የቀራች ባልፍያ የቢድአን ኮተት አንቅራ የተፋች ቤቷ ቢሆንጂ በየ አደባባዩ ሽቶ ያልተቀባች ኹራፋት ባጢልን በሩቅ ያወገዘች ይዘወጅ በግዜ በወጣትነቱ መጠኑ ሳይገፋ ደርሶ ለአንቱነቱ 💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎 አንተ ወንድሜ ሆይ መንሀጅ ያገናኘን ጀሊል በራህመቱ ፀጋው ላይ ያናኘን ጥያቄ አለኝ ላንተ ያው እየተያየን በሳቅ በፈገግታ ጨዋታ እየቃኘን ለምን አታገባም ምንድነው ሚስጥሩ አግዶ የያዘህ የፍረሀት እጥሩ ለምን አይፈታም ጥብቅህ ቁጥሩ ምክንያት አታብዛ ጭራሽ አንግባባም ሙስሊሙ ወንድሜ ለምን አታገባም 💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎💎 ✍ ወንድም አቡ ሹራ Ahmed ቻናሏን ጠቅ አርጓት👇👇👇👇👇 https://t.me/Sobabilalmesjid/4612 https://t.me/Sobabilalmesjid/4612