قَنَاةُ أَبِي الْعَبَّاسِ الْأَثَرِيِّ الْوَلَوِيِّ (Abul Abas Nur)
Відкрити в Telegram
قَالَ عَبْدُ اللَّهِ بْنُ مَسْعُودٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: الْجَمَاعَةُ مَا وَافَقَ الْحَقَّ وَإِنْ كُنْتَ وَحْدَكَ، فَإِنَّكَ أَنْتَ الْجَمَاعَةُ حِينَئِذٍ.
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
906
Підписники
-124 години
-127 днів
+4430 днів
Архів дописів
ይልቅ ፅና! ጠላቶችህ የፀናህ ሆነህ ማየት ነው የሚያስፈራቸው።
Repost from كُنَّاشَةُ أَبِي عِمْرَان (Abu imran)
ሰሞኑን ተቋርጦ የነበረው፦
~ «አህሉ-ተውሒድ» መስጂድ የሚሰጠው፣ የ«አልቀዋዒዱል ሙሥላ» ደርስ፣
~ «መድረሰቱ ዒልሚል ዓረቢያ» የሚሰጠው፣
የ«ላምየቱል አፍዓል» ደርስ እና
~ «አህሉል አሠር» የሚቀርበው፣
የ«ኪታቡ ተውሒድ» ደርስ
ነገ (ሐሙስ) ነሃሴ 21/2018 ዓ.ል ይቀጥላል ኢንሻአላህ።
أَمُرُّ عَلى الدِيارِ دِيارِ لَيلى
أُقَبِّلُ ذَا الجِدارَا وَذَا الجِدارَا
وَمَا حُبُّ الدِّيارِ شغَفْنَ قَلْبِي
وَلَكِنْ حُبُّ مَنْ سَكَنَ الدِّيَارَا
كما قال قيس
በለይላ መንደር (ሰፈር) አቋርጬ
ሳልፍ፣
ይህኛውንም ግድግዳ እስማለሁ፤ ያኛውንም ግድግዳ እስማለሁ።
ልቤን በፍቅር ያነደደው (የማረከው) የመንደሩ ፍቅር ሆኖ አይደለም፣
ነገር ግን እዚያ መንደር ውስጥ የሰፈረችው (የምትኖረዋ) ሰው ፍቅር እንጂ!
ቀይስ እንዳለው
►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►►
🌟 ቢሻራህ ኦንላይን የሴቶች መድረሳ በሴት ኡስታዛ 🌟
ያለ ምንም ፍርሀት እና ጭንቀት በጥሩ ተጅዊድ ቁርአንን መማር ለሚፈልጉ እህቶች በሙሉ ጥሩ እድል ተዘጋጅቶሎታል !!
● የምንሰጣቸው ትምህርቶች ፦
➪ ቃኢዳ በተጅዊድ
➪ ቁርአን ነዘር
➪ ሂፍዝ ከሙራጀአ ጋር
➪ መሰረታዊ የዲን ትምህርቶች
📍ለሴቶች በሙሉ ምቾት፣ ነፃነትና ግላዊነት
ያለው የትምህርት እድል !!
⏰ ሰአታችን ለእርስዎ ከሚመች ፕሮግራም ጋር የሚጣጣም !
⚠️ ያለን ቦታ ውስን ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ !
ለመመዝገብ ፦🔻
@bisharat_al_quran ያናግሩን !
«اقْرَؤُوا الْقُرْآنَ فَإِنَّهُ يَأْتِي يَوْمَ الْقِيَامَةِ شَفِيعًا لِأَصْحَابِهِ»
“ቁርአንን አንብቡ፤ እርሱ በቂያማ እለት ለባለቤቶቹ አማላጅ ሆኖ ይመጣል።” (ሶሂህ ሙስሊም)
Repost from هَذِهِ عَقيدَتُنَا
ፎቶሽን እንዳትልኪ!
~
ምንም ያህል ብታፈቅሪው፣ ምንም ያህል «እንደ ራሴ አምነዋለሁ» ብትይ እንኳ በሀራም ግንኙነት ውስጥ እያለሽ ፎቶሽን በፍጹም እንዳትልኪለት!
● አንደኛ፦ ያለ ኒካህ የሚደረግ ግንኙነት ራሱ ሀራም ሆኖ ሳለ፣ ፎቶ በመላክ አውራሽን መግለጥ ድርብ ወንጀል ነው።
● ሁለተኛ፦ የሰው ልጅ ልብ ተለዋዋጭ ነው። ዛሬ ያመንሽው ሰው ነገ ሲቀያየር ነውርሽን በሚዲያ ላለማውጣቱና ህይወትሽን ላለማበላሸቱ ዋስትና የለሽም።
● ሦስተኛ፦ ነገ በአላህ ፈቃድ ሌላ ንጹህ ትዳር በምትመሰርቺበት ጊዜ፣ ያ ትናንት በስሜት የላክሽው ፎቶ የትዳርሽን ጣሪያ እንዳያፈርሰውና እንዳያዋርድሽ ተጠንቀቂ።
የሚያፈቅርሽ ወንድ በአላህ መንገድ በኒካህ ወደ ቤትሽ ይመጣል እንጂ በስልክ ፎቶሽን እየለመነ ለፈተና አይዳርግሽም። የኔ እህት ዕንቁ ነሽ፤ ክብርሽን በአላህ ፍራቻ ጠብቂ!✅👈
ከነጭራሹም ወደትዳር በፍጥነት ለማይገባ ወንድ ገና አገባሻለሁ እያለ ለሚያታልል በጭራሽ ቤትሽን አትክፈች ትዳርኳን ከመጣልሽ ከሳምንት በላይ አታውሪው በሳምንት ውስጥ ማንነቱንና ድኑን አጥኚ ከሆነ ቶሎ ወደሀላል ካልተዋጠልሽ በብሎክ አሰናብች በስልክሽ ውስጥ block የሚል የተቀመጠው ለእንደዚህ አይነት ቀማኞች ማሰናበቻ ነው ቆራጥ ሁኚ ውዷ👑
https://t.me/qdemiy_letwuhide
💎 መተኪያ የሌለው "ንጹህ ጓደኛ ወዳጅ" እንዳለህ የሚያሳዩ 5 ምልክቶች💎
በሕይወትህ ውስጥ ብዙ ሰዎች ሊመጡና ሊሄዱ ይችላሉ። ነገር ግን አንዳንዶቹ መኖራቸው በራሱ ስጦታ ነው፤ ቢሄዱ እንኳ ማንም የማይተካቸው። እንዲህ ዓይነት ጓደኛ ካለህ እነዚህ 5 ምልክቶች ይታዩበታል፦
⚠️1. የምትግባቡበት ሚስጥራዊ ቋንቋ አላችሁ፦ በተመሳሳይ ነገር ትስቃላችሁ፤ እንዲያውም በመካከላችሁ ሌሎች ሰዎች የማይረዱት የራሳችሁ የሆነ "ሚስጥራዊ ቋንቋ" ያለ ይመስላል። በዓይን ጥቅሻ ወይም በአንዲት ቃል ብቻ ብዙ ነገር ትግባባላችሁ።
🎁 2. ሁልጊዜም በአእምሮው ትመላለሳለህ፦ ጠቃሚ ወይም ደስ የሚል ነገር ባገኘ ቁጥር ወዲያውኑ ለአንተ ይልካል። ወደ አእምሮው የሚመጣው የመጀመሪያው ሐሳብ፦ *"ይህ ነገር ለጓደኛዬ በእርግጥ ይመቸዋል/ይጠቅመዋል!"* የሚል ነው።
❤️ 3. "እንዴት ነህ?" የሚለው ጥያቄው ጥልቅ ነው፦"እንዴት ነህ?" ብሎ ሲጠይቅህ፣ ልክ እንደማንኛውም ሰው የጨዋነት ወይም የይስሙላ መልስ ፈልጎ አይደለም። ይልቁንም በእርግጥም በውስጥህ ምን እየተሰማህ እንደሆነና እውነተኛ ማንነትህን ለማወቅ ፈልጎ ነው።
🎉 4. በስኬትህ አይቀናም፤ አብሮህ ይደሰታል፦ያንተ ስኬት በምንም መልኩ ስጋት አይፈጥርበትም። ይልቁንም ያንተ ስኬት የራሱ ስኬት እንደሆነ አድርጎ አብሮህ ይደሰታል፣ ያከብርሃልም። ምቀኝነት በእውነተኛ ጓደኝነት ውስጥ ቦታ የለውም።
🌿 5. ራስህን ሆነህ ትቀርባለህ፦
ከእሱ ጋር ስትሆን ቃላቶችህን አትመርጥም፣ "ይህን ብናገር ምን ይለኛል?" ወይም "ተሳስቶ ይረዳኝ ይሆን?" ብለህ አትሰጋም። ፍጹም ነፃነት ይሰማሃል፤ ማንነትህን ሳትደብቅ ራስህን ሆነህ ትቆያለህ።
💡አንዳንድ ጓደኞች ቢጠፉ በማንም አይተኩም፤ ምክንያቱም የእነሱ መኖር በራሱ እጅግ ብርቅዬ የሆነ ስጦታ ነውና።
እንዲህ ዓይነት ጓደኛ ካለህ/ሽ "Tag" በማድረግ ወይም ይሄን መልእክት በመላክ ምን ያህል ቦታ እንዳላቸው ግለጽላቸው።
የቴሌግራም ቻናል፦
t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy• ራስህሽን ለሰዎች ማስረዳት ስታቆሚ የሚጠቅምሽን ነገር ብቻ ስታደርጊ ሕይወት በጣም ቀላል ትሆናለች።
*የኔ ሴት በአላማሽ ላይ ብቻ ፅኒ🫶🌹💥
Repost from 🎀ማስታወሻ ለስዴተኛዋ እህቴ📚
የአእምሮህ ሰላም ይቅደም አላስፈላጊውን ነገር እርሳው!
እረፍትህን የሚነሱና ስሜትህን የሚረብሹ ገጠመኞችንም ሆነ የበደሉህን ሰዎች ለመርሳት ወይም እንዳልነበሩ አድርገህ አልፈህ ለመተው ጣር፤ መርሳት ትልቅ ፀጋ ነውና።
ጤናህና የልብህ ሰላም ከምንም ነገር በላይ ቀዳሚና ትልቅ ዋጋ ያላቸው ናቸው።
አላህ በቂህና ያጣኸውን ነገር እንደሚሰጥህ፣ እንደሚበቃህና በተሻለ ነገር እንደሚተካህ ሁልጊዜም በሙሉ እምነት ላይ ሁን።
t.me/ibrahim_furii
Repost from አል ኢርሻድ የሠለፍዮች ስቱድዮ
🎙ሸይኽ ሙሐመድ አሚን እና ሸይኽ ጀማሉ አዝ-ዘሀቢ
📚 ጥያቄ እና መልስ
📡 በአልብኮ ወረዳ ሶባ ቢላል መስጅድ
https://t.me/yedaewachannel
Repost from شـبـاب السـلــفـــيـــيــن
«ታላላቅ ታቢዕዮች»
-----------------
❶♦️ሰዒድ ኢብኑ ሙሰዬብ
❷♦️ሐሰኑል በስሪ
❸♦️ዑወይስ አል-ቀረኒ
❹♦️ሙሀመድ ኢብኑ ሲሪን
❺♦️ዑመር ኢብኑ አብደል አዚዝ
⛔️ማስታወሻ‼️
ታቢዕይ ማለት፦
«በነብዩ አምኖ ሶሀቦችን የተገናኘ ብሎም በእስልምና ላይ እንደፀና የሞተ ሲሆን....እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ደግሞ...እውቀትን ለቀጣዩ ትውልዳቸው ያሰራጩ ባለ ውለታዎች ናቸው።
.....ኑር...✍️
t.me/nuredinal_arebi
t.me/nuredinal_arebi
Repost from Yusuf App™
「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」
╭┄┈┈
┆የቁርአን ተፍሲር
╎⚊⚊
╎» በሸይኽ አወል አሕመድ አል ኬሚሴ
╰─────────────────╯
🏷በ6 አፕሊኬሽን ተዘጋጅቶ የቀረበ
╭𑁍─────────── ╎➺ቁጥር 1 ከሱራ አል ፋቲሃ - ኣሊ ኢምራን 🖇https://play.google.com/store/apps/details?id=com.YusufApp.Tafsir.Quran ╎𑁍──────────
╎➺ቁጥር 2 ከሱራ አን ኒሳዕ - አል አንፋል 🖇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.YusufApp.Tafsir.Quran2 ╎𑁍──────────
╎➺ቁጥር 3 ከሱራ አት ተውባህ - አል ከህፍ 🖇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.YusufApp.Tafsir.Quran3 ╎𑁍──────────
╎➺ቁጥር 4 ከሱራ መርየም - አር ሩም 🖇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.YusufApp.Tafsir.Quran4 ╎𑁍──────────
╎➺ቁጥር 5 ከሱራ አል ሉቅማን - ሙሀመድ 🖇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.YusufApp.Tafsir.Quran5 ╎𑁍──────────
╎➺ቁጥር 6 ከሱራ አል ፈትህ - አን ናስ 🖇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.YusufApp.Tafsir.Quran6 ╰𑁍──────────── ⎙ አሁኑኑ ዳውንሎድ በማድረግ ይጠቀሙ! ↻ ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ! ⎘ ለመሰል ስራዎች ይቀላቀሉን 𑁍 http://t.me/Yusuf_App1
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
በ 12 ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ሁሉ እንኳን ደስ ያላችሁ። የዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁን ያማረ፣ የምትጠቅሙበትና የምትጠቀሙበት ያድርግላችሁ። በዩኒቨርስቲ ቆይታችሁም አላህ ከፈተና ይጠብቃችሁ።
ማለፊያ ውጤት ያላመጣችሁ ደግሞ በመጀመሪያ አልሐምዱ ሊላህ በሉ። ሙእሚን ማለት የሚያስደስተው ነገር ሲገጥመው ብቻ ሳይሆን በየትኛውም ሁኔታ ላይ ጌታውን የሚያመሰግን ነው። በዚያ ላይ ለናንተ የሚሻለው ማለፋችሁ ይሁን አለማለፋችሁ ይሁን የሚያውቀው አላህ ነው። ባይሆን በጊዜ አማራጮችን በመፈለግ ላይ ተፍ ተፍ ማለት ያስፈልጋል። ተቀምጦ መቆዘም በሽታ ነው። ስንፍና ስንፍናን ይስባል። ስንፍና ወደ ተስፋ መቁረጥ ይወስዳል።
በተረፈ ቤተሰብ ልጆችን በውጤታቸው ሰበብ ሊያሸማቅቅ አይገባም። ይልቁንም ሌሎች አማራጮችን በመፈለግ ላይ መመካከርና በሀሳብ ማገዝ ነው የሚያስፈልገው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
እኛም እንድናለን እነሱም ይድናሉ!
~
እኛ አጅር አግኝተን እነሱ ወንጀል ከሚሰሩ እኛም ድነን እነሱም መዳናቸው ይሻላል!
ምርጥ ታሪክ ከሰለፎች፦
ታላቁ ሊቅ ኢብራሂም አን-ነኸዒ (ረሒመሁላህ) አንድ ዓይናቸው የማይሰራ ነበሩ ተማሪያቸው ሱለይማን ኢብኑ ሚህራን (አል-ዕመሽ) ደግሞ ዓይናቸው (ደካማ) ነበሩ።
በዕለቱ ሁለቱ ሊቃውንት #በኩፋ ጎዳናዎች በኩል ወደ መስጊድ ሊሄዱ አብረው እየተጓዙ ነበር። በመንገድ ላይ እያሉም ኢማም አን-ነኸዒ ተማሪየቸውን እንዲህ አሏቸው፦
"ሱለይማን ሆይ! አንተ አንዱን መንገድ ይዘህ እኔ ሌላኛውን መንገድ ብይዝ ምን ይመስለሃል? ምክንያቱም አብረን ሆነን ስንሄድ የሰፈሩ ሞኞች (ሰዎች)፦ 'አንድ ዓይን ያለው ሰው ዕውር ሰው እየመራ ነው!' እያሉ እንዳያሾፉብን እፈራለሁ። በዚህም ምክንያት ሐሜት ውስጥ ወድቀው ኃጢአት ይሸከማሉና።"
ሱለይማን እንዲህ ብለው መለሱላቸው፦ "አይ አባ ዐምራን! እኛ (በትዕግስታችን) ምንዳ አግኝተን እነሱ ኃጢአት ቢሰሩ ምን ችግር አለው?"
ኢብራሂም አን-ነኸዒም (ረሒመሁላህ) ልብ የሚያረካ ይህንን ታላቅ ወርቃማ መልስ ሰጡ፦
"ሱብሐናልላህ! ይልቅ እኛም (ከኃጢአት) እንድናለን እነሱም (ከኃጢአት) ይድናሉ እኛ አጅር አግኝተን እነሱ ወንጀል ከሚሰሩ እኛም ድነን እነሱም መዳነቸው ይሻላል !"
📚 [አል-ሙንተዘም ፊ አት-ታሪክ - 7/15]
ሰለፎች
እንዲህ ነበሩ እውቀት የማይቋረጥ ታሪክ መልካም ባህሪ ለራስ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም መኖር!
የተወሰደRepost from Mohammed Siraj Al kemissie
صلاة المؤمومين خلف الإمم ~~~
إن صلوا جلوسًا فهو أفضل، وإن صلوا قيامًا
فلا حرج؛ لأن النبي ﷺ أقرهم في الصلاة الأخيرة أقرهم قيامًا خلف أبي بكر.
العلامة ابن باز رحمه الله 🦻🦻🦻
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
"ዒደል ፊጥርና ዒደል አድሓም ቁርኣን ውስጥ አልተጠቀሱም" ይላል አንዱ። ቁም ነገር መፃፉ ነው በሱ ቤት። በዚህ ደረጃ ናቸው ሰዎቹ። አምስቱ ሶላቶችም ከነ ረከዐቸው በቀጥታ ቁርኣን ውስጥ አልተጠቀሱም። ስለዚህ ምን ይሁን? ሐዲሥ ልክ እንደ ቁርኣን አስተማማኝ ማስረጃ መሆኑ ማንም ሙስሊም ዘንድ የታወቀ ነው። ሁለቱን ዒዶች የሚመለከቱ የሐዲሥ ማስረጃዎች ደግሞ እጅግ ብዙ ናቸው። በኢስላም ከነዚህ ሁለት በዓላት ውጭ ሌላ አመታዊ በዓል የለንም። ነብዩ ﷺ ወደ መዲና ሲገቡ ጊዜ የመዲና ሰዎች የሚጫወቱባቸው ሁለት በዓላት ነበሯቸው። “ምንድን ናቸው እነኚህ ቀናት?” ሲሉ ጠየቁ። እነሱም፡ “ከጃሂሊያህ ዘመን ጀምሮ የምንጫወትባቸው ቀናት ናቸው” አሉ። በዚህን ጊዜ እንዲህ አሉ መልእክተኛው ﷺ፦
قَدْ أَبْدَلَكُمُ اللهُ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا: يَوْمَ الْأَضْحَىٰ وَيَوْمَ الْفِطْرِ
“አላህ እነዚህን ቀናት ከነሱ በተሻሉ ተክቷችኋል፡- እነሱም የአድሐ ቀን እና የፊጥር ቀን ናቸው።” [አን-ነሳኢይ፡ 1556] [አስ-ሶሒሐህ፡ 2021]
ሲጀመር የዒደል ፊጥርና ዒደል አድሓ በቁርኣን አለመጠቀስ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሺዐዎች ለተጀመረው የመውሊድ ቢድዐ በምን አግባብ ማስረጃ ይሆናል? ምሳሌያችን ነብያችን ﷺ እንጂ ሺ0ዎች አይደሉም። ጌታችን እንዲህ ይላል፦
{ لَّقَدۡ كَانَ لَكُمۡ فِی رَسُولِ ٱللَّهِ أُسۡوَةٌ حَسَنَةࣱ لِّمَن كَانَ یَرۡجُوا۟ ٱللَّهَ وَٱلۡیَوۡمَ ٱلۡـَٔاخِرَ وَذَكَرَ ٱللَّهَ كَثِیرࣰا }
"ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አልላችሁ።" [አልአሕዛብ፡ 21]
~
ቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ቢድዐን ለማውገዝ፣ ወገንን ለማንቃት፣ ብዥታን ለመግፈፍ፣ ከሱና ለመከላከል ስንፍናም፣ መሰልቸትም፣ ይሉኝታም ሊይዘን አይገባም። ማን እንዳፈረ ነው የምናፍረው?! ማን እንደቆመ ነው የምንቆመው?! ወደፊት ብቻ! ሰው በምርቃና በሚዋጋበት ዘመን የቁርኣንና የሐዲሥ ማስረጃ ታጥቆ ለመዋጋት ማመንታት አይገባም።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Repost from ዳዕዋ ሰለፍያ በአልብኮ ወረዳ ሶባ እና ጀብል ቀበሌ(አሸዋዉ) ✈
መልእክት~
በሀገራችን በሀበሻ ረቢኡል አወል /12/ ቀን የነብዩ መውሊድ እያሉ ቤተሰቦቻችን በየቦታው ወደ ሽርክያት መንደር እንደሚጓዙ የሚታወቅ የሆነ ነገር ነው።
በተለይ ገጠር አከባቢ ያለው ማህበሠሳባችን፣እናቶቻችን፣አባቶቻችን፤ ወደተለያየ ከአላህ ውጭ ወደሚመለክበት ቦታ ይጓዛሉ።
ለምሳሌ ያክል
👇👇👇👇
❌ወደ ጀማንጉስ
❌ወደ ማይባር
❌ወደ አርባ ጫማ
❌ ወደ ገታ
❌ወደ አና
❌ወደ ዳና
❌ወደ አብሬት
❌ወደ ቃጥባሬ
❌ወደ አብሬት
❌ወደ ቦረና ጌታው ሸህየ
❌ወደ መጂት
❌ወደ ሰይድ መሳል
❌ወደ አማን አንብይ
❌ወደ ጫሌ
❌ወደ ኑር ሁሴን
ስንቱ ተቆጥሮ ይዘለቃል ዛሬ ጀምረው ይጓዛሉ
❌ጫት ይያዛል
❌ ቡና ይያዛል
❌ስለትም በየ አይነቱ ይጎተታል
ሙክት
በግ
ዶሮ
❌የመሳሰሉት ይጎርፋል ማህበረሰባችን
አጋፋሪወች አሉ ሆን ተብሎ ኮሚቴ ተዋቅሮ ማህበረሰባችንን በእስቲጋሳ ፣በተበሩክ ስም ሽርክ ያሰሩታል ሶላትማ አይታወቅም❌ ኩፍር ብቻ ይታወጃል ፤አላህ የሚጠላቸው ስንት ስራ ይሰራል❌
ከአላህ ውጭ ይጠራል
ለጅን ይገበራል
ሴትና ወንድ ይቀላቀላል
ይጨፈራል
እርጉም የሆነው ጫት ይቃማል
ስንቱ ጉድ በሚሰራበት በዚህ እርጉም የፈጠራ በአል(መውሊድ) ቁጥር አንድ ተጠቃሚም ተዳናባሪም ቃልቻ ተብየ እውቀት ቀመስ መሆኑ ፍንትው ያለ እውነታ ነው።
በዋናነት የሚያሳዝነውና የሚሸወደው ደግሞ ተራው ማህበረሰባችን ነው።
እናም ወገኖቸ ሆይ ቤተሰቦቻችሁን ሀገርም ሁናችሁ ውጭም ሁናችሁ በአካልጨሁናችሁ ማስተማርና ማስጠንቀቅ ባትችሉ በስልክ እየደወላችሁ እንዲታስተምሩና ከዚህ አይነት ቦታ እንዳይሄዱ እንድታስጠነቅቁ ስል ትንሹ ወንድማችሁ በሀያሉ ጌታ ስም ጥሪየን አስተላልፍላችኋለሁ።
በድምፅ ለመቀዳት አልተመቸኝ ሆኖ ነው
መልእክቱን ሸር አድርገን እናዳርሰው ቤተሰቦቻችን ወደ ጓዝ ሳይሸክፋ
✍ወንድማችሁ አቡ ሹራ አህመድ ከወሎ
https://t.me/Sobabilalmesjid/4247
https://t.me/Sobabilalmesjid/4247
Repost from 🔹قَناةُ أبي جُلَيبيب الأثري
👈ياطالب العلم ، أيها السني ( ذكرا كنت أو أنثى ) اعلم أنه ليس أعظم شأنا ولا أعلى مكانا في الدنيا مع مايرجى لك من عظيم الثواب في الآخرة والرفعة عند الله تعالى - إن أخلصت لله - من أن تكون حارسا لثغر التوحيد ، وحارسا لثغر السنة ، وحارسا للدليل تحققه وتقدمه ، وحارسا للعلم النافع تتعلمه وتنشره ، وعاملا بالصالحات ، وحافظا للحقوق ، ومحسنا التعامل مع الناس ، ومتواصيا بالحق ، ومتواصيا بالصبر
فتمسك بهذا الشرف الرفيع ، وعض عليه بالنواجذ ، ولا تتزحزح عنه أبدا ، ولاتمدن عينيك إلى غيره وإن زخرفه المزخرفون .
--------------------------------------
ما أحسن كلام العلامة سليمان الرحيلي
ياسلام ، ياسلام ، ما أجمله ، وما أعظمه،
يارب احفظ هذا الشيخ المبجل .
=
https://t.me/Abu_juleibib
