የአኺራ ተጓዦች☁️
Відкрити в Telegram
ኢንሻአላህ በዚህ ቻናል ላይ ሱናን የሚደግፉ የሚያነቃቁ እና አሪፍ አሪፍ የሆኑ ስንቆችን እንለቃለን inshallah የሱና ቻናሎች መገኛ @bahruteka @shakirsultan @alateriqilhaq @abdulham
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
978
Підписники
+724 години
+367 днів
+15630 днів
Архів дописів
978
ስብራት
ስብራት
ስብራት
ስብራት ያማል ወላህ🙌ግን ሁሉም ህመም ለመጥፋት አይመጣም።አንዳንድ ስብራቶች አላህን እንድናውቅ በእርሱ ላይ እንድንመካ እና ወደርሱ እንድንመለስ ይመጣሉ።ሰዎች ሲተዉን፣በሮችን ሲዘጉብን፤ ተስፋ ስንቆርጥ እንኳን አላህ መቼም አይተወንም።ደሞ የተሰበረ ልብ ለአላህ ቅርብ ነው።ከተሰበረው ልብ የሚወጣው ዱዐ ደግሞ ከልብ ነው።ስለዚህ በስብራታችን ተስፋ አንቁረጥ
ምክንያቱም አላህ ከእያንዳንዱ ስብራታችን ቡሀላ ይክሰናልና🙌
@nesihetulinisa
978
Repost from Abu Umer Ibnu Sadik
~ከባድ ነው ብለን የምናስበው ነገር ለአላህ ቀላል ነው፤ ትልቅ ነው ብለን የምሰጋው ለአላህ ትንሽ ነው፤ እሩቅ ነው ብለን የምንፈራው ለአላህ ቅርብ ነው፤ ዉስብስብ ነው ብለን የምንሸሸው ለአላህ ገር ነው፤
ኦ! ይሔማ አይታሰብም ብለን የተውነው ለአላህ ምንም ነው፤ወላሂ ምንም ነው፡፡ብቻ ጉዳይህን ለርሱ ስጥ…ለአላህ የሠጡት ነገር ሁሉ መላ አለው፡፡
الحمد لله!
978
በቅርቡ coming soon በገበያ ላይ ይጠብቁን
🌸اداب النساء🌸
👇
🌸የሴት ልጅ ስረአቶች🌸
بقلم الشيخ مُحَمَّد حیاة الولوي
ዝግጅት:- በሸይኻችን🫴🏻 አቡ መንሱር ሸይኽ ሙሀመድ ሀያት አል-ወሎዊይ
ይህች ወሳኝ ኪታብ ታትማ ለህዝቡ ለማቅረብ ዝግጅት ላይ ነን ان شاء اللہ
https://t.me/AbuImranAselefy/12224
978
Repost from የወራቤ ሰለፊዮች መገናኛ
የማስጠንቀቂያ መልዕክት
በአሁን ሰአት ከማስረጃ የተራቆተ የጭፍን ጥላቻ ፍርዶች በየቦታው ተበራክቷዋል። በአላህ ባሮች ላይ አላህን መፍራት ግድ የሆነ የሸሪዓችን መርሆ ከመሆኑ ጋር አንዳንድ ሰዎች ይህን ከባድ የሆነ ሸሪዓዊ መርሆ ጥሰው ስሜት ወለድ ጥላቻዊ ፍርድን በመጠቀም በሰለፊይ ወንድሞችና እህቶች ክብር ላይ እየተረማመዱ ስለሆነ ከወዲሁ እነዚህን ሰዎች ያለማስረጃ በጭፍን ከመከተል በመቆጠብ ለሚፈርጁት ፍረጃ ማስረጃ አምጡ በማለት ሸራቸውን መግታት አስፈላጊ ነው። ያለ ተጨባጭ ማስረጃ በማንም ላይ አቋም ከመያዝ ከአንበሳ እንደምትሸሸው ሽሽ።
بارك الله فيكم
https://t.me/ibnbaz1212
978
መለያየት ሁልግዜ ጥላቻ ማለት አይደለም።አንዳንድ ጊዜ አላህ የማይጠቅምሽን ነገር ከህይወትሽ ለማራቅ የሚመርጠው እዝነት ነው። የተለየሽበትን ነገር አትዘኝበት ምንአልባት አላህ ከእሱ የተሻለ ነገር እያዘጋጀልሽ ይሆናል👐🫰🏻
ስለዚህ አብሽሪ የምን መቿኮል ነው hhh🤌🏻
@nesihetulinisa
978
Repost from የልቦች ፍቅር ツ
እህትዋ ሁሉን ነገር ለአላህ መተው ልመጂ።ችግር ይመጣል ይሄዳል። ሶብርሽ ላይ አደራ የነገሮች መክበድ ወይም መጠንከር የሚመጣውኮ ከአላህ ነው ምንአልባት እየተፈተንሽ ቢሆንስ ??? ፈተናውን በአግባቡ ለማለፍ ደሞ ከምንም በላይ صبر አስፈላጊ ነው።
እናማ ሶብሪ እህትዋ🫰🏽
@yeselefochteketay
978
ብቻሽን አይደለሽም ነገሮች ቢከብዱሽ፣ልብሽ ቢደክም አላህ አለ።አላህኮ የልብሽን ሚስጥር ያውቃል የእንባሽን ምክኒያት ያውቃል።
ደሞ በጨለማ ጊዜሽ አላህ ይመራሻል እናማ አብሽሪ እህቴ🫰🏼
@nesihetulinisa
978
Repost from Abu abdirahman«አብዱልቃዲር ኢብኑ ሐሰን»
"
ሁሉም ጸጥተኛ ደካማ አይደለም አንዳንዴ ዝምታ ክብር ነው አንዳንዴ ደግሞ ችላ ማለት እረፍት ነው ።
978
Repost from N/a
👌 አንድ ቀን!
— " አንተን አፈር ውስጥ የቀብር ጨለማ ውስጥ መጣል አንተን ማክበር የሚሆን ግዜ ይመጣል። "
#የመገናኛው_ግሩፕ
t.me/Multeqa_Ahlissuneh
978
Repost from 👑 የተስፋ ብእሮች ♕ ✍🏻
"ከማይጠግቡ የሰው ዓይኖች ዋጋሽን አትለምኚ''ራሷን አክብራ በሐያእ የሸፈነች ሴት ከነፍስዋ ይልቅ ለአላህ ትእዛዝ እጅ የሰጠች ናት። የፊት ውበት ከእድሜ ጋር ይረግፋል.. በሐያእ፣በሒጃብና በጥብቅነት የተገነባ ግርማ ሞገስ ግን በታሪክና በልብ ውስጥ ታትሞ ይቆያል—አይጠፋም https://t.me/+vwLl6dpEQrAzMmRk
978
Repost from የመልካም መንገድ መሰባሰቢያ ቻናል 🇸🇦مجموعة طريق الإحسان🇸🇦
ውድ እህቴ በዲንሽ ጉዳይ ከአንቺ የተሻሉትን እያየሽ
መበርታት እንጂ ከአንቺ የባሱትን እያየሽ መሳነፍ የለብሽም ።
አላህ ለሁላችንም ያግራልን🌺
https://t.me/Al_elhsan_Zz
978
Repost from 👑 የተስፋ ብእሮች ♕ ✍🏻
+1
እናንተ'ኮ አሏህ ዘንድ ቲኒሹን ነገር ነው
የጠየቃችሁት...እርሱ ግን ሞልቶ ይሰጣል።
ብቻ በየቂንበኢኽላስ ጠይቁት!
እርሱ በመስጠት ላይ የሚሰስት ጌታ አይደም።
978
ማነው ተሳዳቢው!
ብዙ ጊዜ አስቤ ስንኜን ልቋጥር ፣
ስለ ታላቁ ሸይኽ በኢትዬ ምድር ፣
ወቀሳ ማይፈራ ቆራጥ ጀግና ደፋር፣
ዱኒያን ቺላ ያለ የሚኖር ከገጠር፣
መብራት ውሀ የለ መቀማጠል ነገር፣
ቆርቆሮ ቤት ሳይል በሳርቤት የሚሮር፣
ገጠር ቁጭ ብለው ያዳረሱ ሀገር፣
ለዳእዋ ለኮርስ ሁሌ ማይበገር ፣
ልበ ሰፊ አሊም ሲያወራ ሲናገር ፣
ውጭ ውስጡ አንድ የሆነ ነገር የማይቋጥር፣
ኡስታዞች ያወጣ የበዙ እንደጠጠር፣
እድሜውንም ለጋሽ ዲኑ እንዳይደፈር፣
የደቡቡ አለኝታ ተንቀሰቃሽ ሞተር ፣
ሸይኽ አብዱል ሀሚድ ነው ወደሌላ አትዙር።
የሂፍዝን ችሎታ አላህ የገጠመው፣
ቁርአን ሀፍዞ ሀድስ የጬመረው፣
ፊቅህን ተምሮ ነህው ሶርፍ ያልቀረው፣
በላጋ መዓኒን ሀፍዞ ያስገባው፣
ኡሱሉን አዳቡን ሁሉን የሸመተው፣
ሀድስ ተፍሲርንም አላምጦ የዋጠው፣
በልጅነት እድሜ ወጣት እያለ ነው።
በጥመት አካሎች ቢሆኑም ጠንካራ፣
ለሱና ሰው ናቼው ሆዳቼው የራራ፣
ሌሊት እሚቆሙ ቀን ውሎ ሲያስቀራ፣
ኪታብ ወዳድ ምሁር ተውሂድ የሚዘራ፣
ከሳቼው የቆዬ ስለ ሸይኩ ያውራ።
እናም አንድ ነገር ሰሞኑን ተለቆ፣
በስድብ በዝልፊያ እጂጉን ታጪቆ፣
ሸይኹን ዝቅሊያደርግ ምላሱን አዝልቆ፣
የፈተና ሞተር ያልተማረ ታጥቆ፣
ብዙውን ቀርሺቷል በተክፊር ተዘፍቆ።
እጂግ የሚገርመው የአይኑ መታወር፣
መረጃ ሲያቅተው ወደ ስድብ መዞር፣
የራስን ሸሽጎ የሰዎችን መቁጥር፣
ሁሌ በባጢል ላይ ሲደነፉ መኖር፣
የተለመዴ ነው ከጦሳዎች መንደር።
አንተ ደፋር
ስድቡን ተወውና እስኪ መረጃ አምጣ፣
አላህንም ፈርተህ ከውሼትህ ውጣ።
ማነው ተሳዳቢው ቆይ ማነው ዘረኛ፣
እናውቃቼዋለን ወሎ ሆነን እኛ ፣
ወላሂ አታቃቼው አይደሉም ዘረኛ፣
አንተ ግን ሆንክና የኢኽዋን ዘበኛ፣
ውጥርጥር ብለህ የተክፊሮች ፊኛ፣
አሊም አሊም መሳይ የኢሞ ጉረኛ፣
ፈግሞ ካንተ በላይ ጉድ አናውቅም እኛ።
ጉራጌ ስልጤ እያልክ ያድስ አባዎቹን፣
በዘር ስትከፋፍል ጀማልና አብራንን፣
ወሎዎች ላይ ብቻ ስታረግ ውዳሴን፣
እየሞገታችሁ ባንድ መንሀጅ ላይ ነን፣
ውስጣችሁ ውጭ ወቶ ይሄው ስንቱን አየን።
እጂግ ታዋቂ ነህ በተሳዳቢነት፣
እስኪ ትንሽ ላንሳ ትሁን ለአብነት፣
ለራስህ ጉዋደኛ ስንኝ የቋጠርካት፣
ለኢኽዋን ወንድምህ ያው የሞጫጨርካት፣
ይሄንን ይመስላል እስኪ ጉዱን ስሙት፣
የግጥሙ እርእስ ጀናዛው ሰው ሆኖ
ይላል አቶ ሙስጤ እስኪ ስሙት አቦ
ነስር ስጂዳችን የድናችን ጮራ፣
በሱንዮች ደምቃ በሂዝብዮች ታፍራ፣
ትኖር የነበረች በሁሉም ተከብራ፣
አለቀሰች አሉ ባጉል ሰው ተደፍራ።
በደካማ ጃሂል ያውም በደንባራ፣
ህፃን በማይባል ወይም አባውራ፣
ተንኮል የቀጠነው ያለቀ እንደጪራ፣
ሰው ይቅር ሪጅለይኒ ወገቡ ጎብራራ፣
እግሩ ቅጪጭ ያለች ሀሳቡ ሸውራራ፣
ከዶሮ ከፍ ያለ ያውም ካበሻ አውራ፣
የፈረንጂንማ ምንም ቢንጠራራ፣
እሱን አያክልም ከጃኬቱ ጋራ፣
እንደ አዎ ይመስላል ጀናዛ
ይመስላል ጀናዛ ቆሞ የሚያወራ
ከቀብር የወጣ በቀን በጠራራ፣
ስጋው እልቅ ያለ አቤት ሲያስፈራራ፣
አይተከው አስተንትን ጉድ ነው ያላህ ስራ።
ይገርማል
ሰዎች እንዳይኖሩ ጀናዛው አቅራራ፣
ብሎ ተናገረ ሂዱ ከኔ ስፍራ፣
ልቀቁልኝ ቤቴን ሁሉን እንድሰራ።
እንደልቤ እንድጮህ ተንኮል እንዳወራ
አለ ይህ ጀናዛ ሰው መሳይ ቀብራራ፣
ተላላኪ ምስኪን በሌላ እሚመራ
ድሮም ጀናዛ ሰው ስጋ የለው ሞራ፣
በምኑ ያስባል ተሰብሮ እንደንስራ።
ይነዳዋል ጀለፍ ይነዳዋል ፋራ፣
አድርጎት አረፈ የሂስድ ሀራራ፣
የተንኮል ኪራይ ቤት የሼር ጎተራ።
ይላል አቶ ሙስጤ የተክፊሮች አውራ፣
ይህን ሁሉ ስድብ በግጥም ሲያወራ፣
ስሜቱን ያልገታ ነቄ መስሎ ፋራ፣
ሸይኽን ተሳዳቢ ብሎ ይህ ቢያወራ፣
ለጤነኛ ሁሉ አላህን ለፈራ፣
ግልፅ ነው ወላሂ ተው አላህን ፍራ።
ደግሞ የሚገርመው ወደ ቋንቋ ሄዴ
ሸይኹንም ሳላቸው ልክ እንደ ወንበዴ፣
አብዷል ማለት ባንተ ምች ተጀመረና፣
ነብዩስ ከስድብ መቼ ተረፉና፣
አብድ ነው ደጋሚ ሳሂርና ጨምርና፣
በማሉ መች ሲገርም በነብዩ ሱና፣
ብዙም አይገርመንም ፋሽኑ አልፏልና።
ደግሞ በመናደድ አቡዘርን ተቼህ
ሁሌ መንጠራራት ብቻ ሆኖ ስራህ
ልክ እንደ ዝንጆሮ መላጣ አይታይህ፣
ያንተ ብው ማለት ብሎ መናደድህ፣
በወራዳ ድርጊት በእኩይ ደረሶችህ፣
ብው ብያለሁ እኔ ብለህ እያወራህ፣
እራስህን ረስተህ ሸይኹን ትተቻለህ።
ሸይክ አቡዘር ማነው ብለህ ለጠየቅከኝ፣
ስለርሱ ልንገርህ ሀያ ተከተለኝ።
በርታ
በትንሽ ስንኞች አንድ እውነት ልናገር፣
የወሎው እንቁ ፈርጥ ከኮንቦልቻ ሀገር
ሙብተድዑን ሁሉ ድምፁ ሚያንዘረዝር
ሙመይዐን ኢኽዋን ያጎረሳት አፈር፣
አንበሳ ታታሪ በሰለፍያ ስም የማይደራደር፣
ሀቅን ማውራት እንጂ ለውሸት የማይኖር፣
ለተቺዎች ትችት ወደ ሇላ ማይዞር፣
በሰፊ መረጃ አጭቆ እሚናገር፣
ሱናን ያራመደ ከ ወንድሞቹ ጋር፣
አለ ወሎ ምድር ሸይኻችን አቡዘር፣
እኔም አልኩት ያ ሸይኸና
ጠንክር በርታ በአቋምህ
ብዙ አለ ሚጠብቅህ
በሀቅ ላይ የወደደህ
ለሱና ቁም ሁሌ እስካለህ፣
በጀሊሉ ተመክተህ
ጀግን በርታ ተውሂድ ይዘህ
ሰው ቢጠላህ በአቋምህ
ቢሰድቡህም ጠላቶችህ
እለፋቼው እንዳይገርምህ
አባት ሆነህ ዱኣ አድርገህ።
መልሳቼው በመረጃህ
ባስገራሚ አንደበትህ፣
ሱንይ ሁሉ ያው ሲወድህ
ኡለማዎች ሲያወድሱህ፣
በሱና ላይ ስላወቁህ
ጠንክር በርታ ተመክተህ
ሀቅ ላይ ኑር በስንፋስህ።
እራስ ምታት ለተክፊሮች ፣
ጣፋጭ ማር ነህ ለሱንዮች
አስደማሚ ኪታቦችህ
ቢያማቼውም ጠላቶችህ
ሱናን ጠቅሟል እሪከርድህ
ተፍሲር ሙሉ እንዲያ አብራርተህ፣
ኪታቦችን አስተምረህ፣
በያይነቱ እረድ አርገህ፣
ሱናን ጠቅሟል ፅኑ አቋምህ።(2)
ለሱና ሁሌ ቁም ሸይኻችን አቡዘር፣
ሙብተዲዑ ሁሉ ወደ ሀቅ እንዲዞር።
እንደ ረፋድ ፀሀይ ግልፅ ነው አቋምህ፣
በሀጅር ጉዳይ ላይ በሰፊ መፃፍህ፣
በየፊቅሁ ዘርፍ ሰፋፊው ጥናትህ፣
እጂግ ይማርካል ደርስ አቀራረብህ፣
ምቀኛህ ይመራ ዛሬ የሚሰድብህ፣
ቃላትም የለኝም በምንስ ልግለፅህ፣
ለአላህ ብዬ ነው ወላሂ ስወድህ፣
ባለህበት ምድር አላህ ይጠብቅህ።
አወ ያንሳቼዋል ሸይኻችን አቡዘር
እረዱ ብርቱ ነው ያስግጥሀል አፈር፣
ጀምሯል አዳምጠው ገብተህ ቻናሉ ስር።
ሙስጦፋ ያቼፍችፍ ይሳደብ ልምዱ ነው፣
ጃሂል ስድብ እንጂ እውቀት መች ሲገራው።
እናማ አንተ ጀግና ለተሞ ያለኸው፣
እናማ አንተ ጀግና ኮቻ ላይ ያለኸው፣
ሀቅ ወዳድ ሆነህ ነው ምቀኛህ የበዛው።
እንዴ ውሻ ይጩህ በመረጃ አስተፋው፣
ይህን ያክል ካልኩኝ ብእሬ እዚ ትቁም
በርቱ የኛ ጀግኖች ወሰላሙአለይኩም።
✍ኢብኑ ኢድሪስ አል–ወሎዊ
ibnu_idris_public_chanal
@Nikabistuwanigist
@nesihetulinisa
