uk
Feedback

Не попадись на ботовода! Telemetrio знаходить і позначає такі канали мітками 👉 Хочеш бачити мітку, оформляй підписку

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

ደዕዋ ሰለፍያ በመካነ-ሰላም እና አካባቢዋ

Відкрити в Telegram

ይህ ቻናል በአላህ ፈቃድ በማህበረሰባችን ውስጥ በሰፊው ስለተሰራጨው ታላቁ ሙንከር ስለ(ሽርክ) እና የተፈጠርንበት አላማ ስለሆነው ስለ (ተውሒድ) እንድሁም ስለሱና እና ቢድዓ እና ሌሎችም ኸይር ነገሮች የሚለቀቅበት ቻናል ነው።

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
319
Підписники
-124 години
-27 днів
+5430 днів
Архів дописів
የሰኞ ፆም እና መውሊድ ~ የመውሊድ አክባሪዎች ለዚህ ቢድዐቸው ከሚያጧቅሷቸው “ማስረጃዎች” ውስጥ አንዱ ነብዩ ﷺ ሰኞን ከሚፆሙባቸው ምክንያቶች አንዱ የተወለዱበት ቀን መሆኑን መግለፃቸው ነው። ይህንን መነሻ በማድረግ “እንዲያውም መውሊድ መከበር የተጀመረው በራሳቸው በነቢዩ ﷺ ነው” ይላሉ። ይሄ ግን ፈፅሞ ማስረጃ ሊሆናቸው አይችልም። ምክንያቱም፦ 1. ፆምና ጭፈራን ምን አገናኘው?! እናንተ'ኮ በጭፈራ እንጂ በፆም አይደለም የምታከብሩት። ተግባራችሁ ባልተመሳሰለበት በምን ስሌት ነው የሰኞን ፆም ለጭፈራ ማስረጃ የምታደርጉት? የልደት ቀናቸውን በጭፈራና በድግስ ማሳለፍ ከሳቸውም፣ ከሶሐቦችም፣ ከታቢዒዮችም፣ ከአትባዑ ታቢዒንም፣ ከአራቱ ኢማሞችም፣ በዐቂዳ እንከተላቸዋለን ከምትሏቸው እነ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪም፣ አቡ መንሱር አልማቱሪዲም ፈፅሞ አልተገኘም። እስቲ ከቻላችሁ አንዲት ስንጥር ማስረጃ ጥቀሱ! ደግሞም ነብዩ ﷺ ሰኞን የሚፆሙበትን ምክንያት ሲናገሩ “ስራዎች ሰኞና ሐሙስ ቀን (ወደ አላህ) ይቀርባሉ። እናም ፆመኞ ሆኜ ስራዬ እንዲቀርብልኝ እወዳለሁ” ነው ያሉት። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 2959] የናንተ ተግባር ግን “ጨፋሪ ሆኜ ስራዬ እንዲቀርብልኝ እወዳለሁ” የሚል ነው የሚሰጠው። 2. እናንተ'ኮ ሰኞ ቀን አይደለም የምታከብሩት! ረቢዑል አወል 12 ሁሌ ሰኞ ጋር አይገጥምም። ኧረ እንዲያውም እዚሁ ሃገራችን ውስጥ ሆነ ብለው በያመቱ እሁድ ቀን ብቻ የሚያከብሩ አሉ። ሌሎች ደግሞ ህዳር ላይ፣ ሌሎች ጥቅምት ላይ፣ ሌሎች ደግሞ ረጀብ ወር ላይ የሚያከብሩ አሉ። እንኳን ቀኑና ወሩም አይገናኝም። አመት ጠብቆ የልደት ቀናቸውን ማክበር ከሳቸውም፣ ከሶሐቦችም፣ ከታቢዒዮችም፣ ከአትባዑ ታቢዒንም፣ ከአራቱ ኢማሞችም፣ በዐቂዳ እንከተላቸዋለን ከምትሏቸው እነ አቡል ሐሰን አልአሽዐሪም፣ አቡ መንሱር አልማቱሪዲም ፈፅሞ አልተገኘም። እስቲ ከቻላችሁ አንዲት ስንጥር ማስረጃ ጥቀሱ! ስለዚህ እየተፈፀመ ያለው ነገር ሲወርድ ሲዋረድ የመጣን ባህል ማስቀጠል ብቻ ነው። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ ለሱና የተጨነቃችሁ ይመስል ከናንተ ፀያፍ ተግባር ጋር የማይዛመደውን የነብዩን ﷺ ሳምንታዊ የሰኞ ፆም ማጣቀስ ማጭበርበር አይደለም ወይ? 3. ሰኞን ብትጠብቁም ከጥፋትነት አይወጣም! ሌላው ቀርቶ በየሳምንቱ እየጠበቃችሁ ሰኞን ብታከብሩ እንኳ የናንተ ተግባር በሺርክ የታጨቀ፣ በቢድዐ የተወረረ እና ከስነ ምግባር ያፈነገጠ ነው። አሁንማ ጭራሽ የብልግና መፈፀሚያም ሆኗል። ደግሞስ ነብዩ ﷺ ሰኞን በፆም እንጂ በጭፈራ አላከበሩ? ጭፈራ በምን ስሌት ነው ዒባዳ የሚሆነው? በዚህ ላይ ሺርክ ሲጨመርበት ከድጡ ወደ ማጡ ይሆናል። 4. ከሰኞ ፆም ጋር በቂያስም አይገናኝም! የሰኞን ፆምና የመውሊድን ጭፈራ በቂያስ ማገናኘትም ጭራሽ የሚያዋጣ አይደለም። የሐሙስን የሱና ፆም በጭፈራና በውዝዋዜ ማሳለፍ ይቻላልን? በደስታ እንድናሳልፍ የታዘዝናቸውን ሁለቱን ዒዶች በፆም ማሳለፍ ይቻላል? የምስጋና ሱጁድን በሩኩዕ መቀየር ይቻላል? ዒባዳኮ በታዘዘው መሰረት እንጂ በመሰለኝና በደሳለኝ አይፈፀምም። እውነት ከመውሊድ የሚፈልጉት አላማ ለአላህ ምስጋና መግለፅ ከሆነ ሊከተሉ የሚገባው ነብዩ ﷺ የተከተሉትን እርምጃ ብቻ ነበር። “ከመመሪያ ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነውና።” [ሙስሊም፡ 2042] እሳቸው ደግሞ የተወለዱበት ሰኞን በፆም እንጂ በጭፈራና በውዝዋዜ ምስጋናቸውን አልገለፁም። እየተፈፀመ ያለው እሳቸው ከሰሩት ተቃራኒ ነው። ታዲያ ለምን ነብዩን ﷺ የበቃቸው አይበቃንም?! ለምንስ ከሳቸው ፊት እንሽቀዳደማለን? አላህ እንዲህ አላለምን? {يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ لَا تُقَدِّمُواْ بَيۡنَ يَدَيِ ٱللَّهِ وَرَسُولِهِۦۖ وَٱتَّقُواْ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ سَمِيعٌ عَلِيمٞ} {እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአላህና በመልእክተኛው ፊት (ነፍሶቻችሁን) አታስቀድሙ። አላህንም ፍሩ። አላህ ሰሚ አዋቂ ነው።} [አልሑጁራት፡ 1] ነብዩስ ﷺ “በኔ ላይ መልካም ምሳሌ አይኖርህምን? በአላህ ይሁንብኝ! እኔ ከናንተ ይበልጥ አላህን ፈሪያችሁ ከማናችሁም በበለጠ ድንበሮቹን ጠባቂ ነኝ” አላሉምን? [አሶሒሐህ፡ 1782] 5. ነብዩ ﷺ ስለ ሰኞ ፆም እንጂ ስለ ረቢዑል አወል 12 አልተናገሩም! ነብዩ ﷺ ሰኞ ቀን እንደተወለዱ በግልፅ የተናገሩ ሲሆን ረቢዑል አወል 12 መወለዳቸውን በተመለከተ ግን አስተማማኝና ሶሒሕ ማስረጃ የለም። ጠንካራ ማስረጃ አለመምጣቱ በራሱ ቀኑ ያን ያክል አንገብጋቢ እንዳልሆነ ነው የሚያሳየው። መውሊድ ዛሬ የሚሰጠውን ያክል ክብደት ቢሰጠው ኖሮ ከሳምንቱ ቀናት ውስጥ ሰኞ መወለዳቸውን እንደነገሩን ሁሉ ከአመቱ ወራት ውስጥ በየትኛው ቀን እንደተወለዱ በግልፅ በነገሩንና እንድናከብረውም ባስተማሩን ነበር። 6. የሰኞ ፆም እንጂ የረቢዑል አወል 12 መውሊድ በሐዲሥ ድርሳናት ውስጥ አይገኝም በሱና ድርሳናት ላይ የሰኞ ፆም ትኩረት ተችሮት የተወሳ ሲሆን ረቢዑል አወል 12ን የሚመለከት ግን አንድም መረጃ የለም። ምክንያቱም ሊቀርብ የሚችል መረጃ የለምና። ቡኻሪ፣ ሙስሊም፣ አራቱ ሱነኖች፣ … ብንፈትሽ ረቢዑል አወል 12ን በደስታ፣ በጭፈራ፣ በተለየ ዒባዳ፣ በሶደቃ እንድናሳልፍ የሚጠቁም አንድም መረጃ አይገኝም። ይህም የሰኞ ፆም ለመውሊድ መረጃ እንደማይሆን ጠቋሚ ነው። ቢሆን ኖሮ ከመውሊድ አጋፋሪዎች በፊት እነ ቡኻሪ ይረዱት ነበርና። 7. ነብዩ ﷺ የተወለዱበት ቀን ዒድ አይደለም! በኢስላም ዒድ እንዳማይፆም የታወቀ ነው። ሰኞ ቀን መፆም ግን የተወደደ ነው። ከመሆኑም ጋር ይህ መፆሙ የሚወደደው ሰኞ ቀን ከዒድ ቀን ጋር ከገጠመ መፆም አይፈቀድም። ይህም የተወለዱበት ቀን ዒድ እንዳልሆነ በተጨባጭ የሚያሳይ ነው። ነብዩም ﷺ ሰኞን መፆም የሚወደድ እንደሆነ አስተማሩ እንጂ “ቀኑ ዒድ ነው” አላሉም። እለቱ ዒድ ቢሆን ኖሮ በፆም አያሳልፉትም ነበር። የመውሊድ አክባሪዎች ግን ቀኑን ዒድ አድርገውታል። በሚደንቅ ሁኔታ “ቀኑ ዒድ ስለሆነ መፆም አይቻልም” እስከማለት የደረሱ አሉ። "መዋሂቡል ጀሊል ሸርሕ ሙኽተሶሪል ኸሊል" የተሰኘውን ከታብ ገፅ 2/406 ላይ ማየት ትችላላችሁ፡፡ ሙሐመድ ብኑ አሕመድ በኒስ፣ ኢብኑ ዐባድና ሌሎችም እንዲሁ እለቱን ዒድ ነው ይላሉ። የሚያሳፍር! ታዲያ እንደዚያ የሚሉ ከሆነ ለምን ነብዩ ﷺ በፆም ያሳለፉትን ሰኞን ለዚህ ድርጊታቸው መረጃ ያደርጋሉ? ዒድ ይፆማል እንዴ? ቀንደኛ የመውሊድ አቀንቃኝ የሆነው ኢብኑል ዐለዊ ግን መውሊድን መሀይም እንጂ በዒድ አይገልፀውም ይላል። መውሊድ ዒድ (በአል) ነው የምትሉ የዋሀን ሆይ! መሃይማን ባትሆኑ ኖሮ መውሊድን ‘ዒድ ብላችሁ አትገልፁም ነበር’ እየተባላችሁ ነው!! በርግጥ እሱ በዚህ በኩል የሚነሳውን ትችት ለመሸሽ ያክል ነው ይህን የሚለው። እንጂ ዞር ብሎ “ቀኑ ከዒድም በላይ ነው” ይላል። [አልኢዕላም፡ 8] የዞረበት ጉድ! የቢድዐ ፍቅር ሰዎቹን የት እንደሚያደርሳቸው ተመልከቱ። ለዚህ ሙግቱ ከከንቱ ትንተና ባለፈ ከቁርኣንም ከሐዲሥም ከሰለፎች ንግግርም አንድም ሊያቀርበው የሚችለው ነገር የለም። ሲጠቃለል የነብዩ ﷺ የሰኞ ፆም እና አመታዊ የሱፍያ ጭፈራ በየትም አቅጣጭ አይገናኝም። አራምባና ቆቦ ነው። (ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 20/2014) የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor

የማለዳ መልእክት (42) ~ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- مَنْ أحبَّ أن يَصِلَ أباهُ في قبرِهِ، فلْيَصِلْ إخوانَ أبيهِ مِن بَعدِه "በመቃብሩ ውስጥ ላለ (ለሞተ) አባቱ መልካም መዋል የሚወድ ሰው፣ ከእርሱ በኋላ ለአባቱ ወንድሞች (ወዳጆች) መልካም ይዋል።" [ሶሒሑል ጃሚዕ ፣ አልአልባኒይ ፡ 5960] የወላጆች ሐቅ በመሞታቸው አይቋረጥም። የአላህ መልእክተኛ ﷺ በዚህ ሐዲሥ ውስጥ አባት ከሞተ በኋላም ቢሆን ለእርሱ መልካም ነገርንና ምንዳን ማብዛት የሚቻልበትን ተግባራዊ መንገድ ያሳዩናል። እርሱም የአባትን ወዳጆችና የቅርብ ዘመዶች መዛመድ/መንከባከብ፣ መጠየቅ ነው። ለአባት መልካም ማድረግ በእርሱ ህልፈት የሚያበቃ ሳይሆን፣ በሕይወት እያለ ይወዳቸውና ይዛመዳቸው የነበሩትን ሰዎች ሁሉ የሚያጠቃልል ነው። ከዚህም ባሻገር ለወላጆች በማሰብ ሶደቃ ማውጣት፣ ዱዓእ ማድረግ፣ ዑምራ ማድረግ፣ ... ከሞቱም በኋላ አጅራቸው እንዲቀጥሉ ከሚያደርጉ ተግባራት ውስጥ ናቸው። = (ኢብኑ ሙነወር፣ ሶፈር 20 /1448) = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

«ሐጅ እና ዑመራ» ~ የሐጅ መሰረትና ግዴታዎች ~ የዑምራ መሰረትና ግዴታዎች ~ የኢሕራም አፈፃፀም አይነቶች ~ የኢሕራም ማድረጊያ ቦታዎች ~ የሐጅ እና የዑምራ ክልክላዎች ~ የሐጅ እና የዑምራ ተግባራት ቅደም ተከተል የተዳሰሰባት ቲንሽየ ማስታወሻ። አዘጋጅ : አቡ ዒምራን = የቴሌግራም ቻናል t.me/Abu_lmran_Alaseriy t.me/Abu_lmran_Alaseriy

"የሰው ልጅ ሆይ ስማ!" ዛሬ በምድር ላይ እንደፈለግክና ያሻህን እየሰራህ ልትኖር ትችላለህ ነገር ግን ነገ ሞተህ ከምድር ስር እስረኛ ትሆናለህ!
🫀 ልብ በል !
✍ ምድር ላይ እየኖረ ዕድሜውን በጥሩ ነገር ያሳለፈ ሰው ሞቶ ምድር ውስጥ ሲገባ በሰላምና በደስታ ይኖራል ቀብሩም ይሰፋለታል የጀነት በርም ተከፈቶለት ፀጋዎቿን እያየ -ያረብ ቂያማን ቶሎ አቁማት-!እያለ በተስፋ ይኖራል ✍ ምድር ላይ እየኖረ በወንጀልና በግዴለሽነት ህይወቱን ያሳለፈ ሰው ሞቶ ምድር ውስጥ ሲገባ የሆድ እቃው ካፍንጫው እስኪወጣ ድረስ ምድር ታጣብቀዋለች ከላይዋ  ላይ እየኖረ አላህን በማስቀየሙ ትጠላው የነበረውን ያክል ከስሯ ሲገባ ዋጋውን ትሰጠዋለች! ✍ ይህም ቀን መች እንደሆነ ማንም በትክክል አያውቅም አሁን ከቅፅበት በኋላም ሊሆን ይችላል! ©

+1
ክፍል : 06  📚ኪታብ : አልቀዋዒዱል ሙስላ 🎙በኡስታዝ አቡ ኢምራን 📔የኪታቡን PDF ለማግኘት https://t.me/sefinetunuh/9009 ደረሱ የሚሰጠዉ 📣በአህሉ-ተውሂድ መስጂድ 😂 ደርሱን በላይቭ ለመከታተል ➡️ ➡️ https://t.me/sefinetunuh

🏷ጀግናዬ...‼️ ለሁሉም እሽ ማለት ሲበዛ ደግነት ሳይሆን ከሞኝነትና ከጂልነት ስለሚቆጠር እምቢ ማለትን ተማር...!! ጀግናዬ የተነገረ ሁሉ እውነት እንዳልሆነ ሁሉ ያልተነገረ ሁሉ ደግሞ ስህተት አይደለም። ..ወዳጅና ጠላትህን ለይ...ልንገርህ ወዳጅና ጠላት ማለት አብረው የሚፈጠሩ እና ጎን ለጎን የሚያድጉ እንክርዳድና ስንደዎች ናቸው። ..🏷ዝምታህን ስበር.. ዝም ያለ ሁሉ አጥፊ የለፈለፈ ሁሉ ተበዳይ የሚመስላቸው አሉ እና አስፈላጊውን ጊዜና ቦታው ስታገኝ ዝምታህን አበረው። ለላከህ ሁሉ አትላክ ክፉ ክፉ ነው ወዳጅ መስሎ ወደ ገደል ይገፋሀል ተጠንቀቅ‼️ ..ስማ‼️ አብዝተህ ተቀናቃኝ..ተባዝተህ ደግ ሁን «ቀናወችና ደጎች ዋጋቸው የሚታወቀው ከስሜት ወጥተህ ተረጋግተህ ስታስብ ቦታቸው ላይ ስታገኛቸው ነው። ....ኑር...✍️ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦ (( بل نشهد الله على ما يعلمه من قلوبنا بأن من عمل بالتوحيد وتبرأ من الشرك وأهله فهو المسلم في أي زمان وأي مكان، وإنما نكفر من أشرك بالله في إلهيته بعدما نبين له الحجة على بطلان الشرك )) "ይልቁንም አላህን በልቦናችን ባለው ነገር ላይ ምስክር እናደርጋለን፤ በተውሒድ የሠራ፣ ከሺሪክና ከባለቤቶቹም ያገለለ ሰው እርሱ በማንኛውም ጊዜና በማንኛውም ቦታ ያለ ሙስሊም ነው። ከእስልምና ወጥቷል የምንለው በአላህ አምላክነት ላይ ሺርክ የፈጸመን ሰው ሲሆን፤ ይህንንም የምናደርገው በሺርኩ ውድቅነት ላይ ማስረጃ ካብራራንለት በኋላ ነው።" ምንጭ፦ መጅሙዑ ሙአለፋቲ አሽ-ሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ዐብዲልወሃብ ፡ 3/34] ተመሳሳይ ንግግሮቻቸው ብዙ ናቸው። የሚነሱ ብዥታዎችንና መልሶቻቸውን በተመለከተ ሌላ ጊዜ እመለሳለሁ ኢንሻአላህ። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor

ከሳሽና ተከሳሽ እውነቱን ያውቁታል። እየተፈተነ ያለው #ዳኛው ነው።

....ለሁላችንም ይድረስ አንብቧትማ...‼️ …እንድህ ነን ሁላችን… ------------------------ ሁሉም የራሱን አይብ አርቆ ይቀብራል፡ የሌሎችን ነውር ደፍሮ ይናገራል፡ ወንዱ ወንድነቱን አራግፎ ጨርሷል፡ ወኔው ላሽቆ ወድቆ ብዙ ነገር ፈርሷል፡ ሴቱ በሴትነት መከበር አልቻለም፡ ሁሉም ተቃራኒ ሆኗል በዚህች አለም፡ ሁሉም አስመሳይ ነው አያውቅም ሀቂቃ፡ ከሊቅ እስከ ደቂቅ እንደዚህ ነን በቃ!! ሁሌ በመሰለኝ ሰው የምንወነጂል፡ የራሳችን ሳያልቅ የሌላ እምንከጂል፡ ስም የምናወጣ ለአዛኝ ብለን ጨካኝ፡ አዋቂ እምንንቅ ባለ ራዕይ አምካኝ፡ ......እንደዚህ ነን እኛ.... ስንቱን የጥበብ ሰው ደጋግመን በደልነው፡ ስንቱን በሌለበት ቀጥቅጠን ገደልነው፡ ሁሉም አውቃለሁ ባይ ሁሉም ተናጋሪ፡ ከፈረሱ በፊት የሚቀድም ጋሪ፡ ሁላችንም ዘፋኝ ሁላችን ዘማሪ፡ ሁላችንም ሌባ ሁላችን አዝማሪ፡ ሁላችንም አጫሽ ሁላችን ሰካሪ፡ ሁላችን ዘረኛ በውሸት መስካሪ፡ ቃላችን ተግባር ጋር በቃ አልተጣጣመም፡ ዛሬም እንደ ትናንት ግፋችን አልቆመም፡ አክባሪ ተንቆ ጋጠ-ወጥ ደምቆ፡ አንባ-ገነን ጎልቶ ፍትህ ተሸምቆ፡ መመስገን ሲናፍቅ ግፈኛው በሙሉ፡ ታጋይ መባል ሲመርጥ አጭበርባሪው ሁሉ፡ ከሚመኝ ኗሪ ጋር፤ በሔድናቸው መንገድ ባለፍናቸው ቀናት፡ ለካ ሁላችንም፤ ልባችን ቀጣፊ ነፍስም ዱርዬ ናት፡ .....አዎ....‼️ ሁላችንም አዳኝ ሁላችን ታማሚ ሁላችንም ዶክተር መዳኒት ቀማሚ፡ ሁላችንም ደጋሽ ሁላችን ታዳሚ፡ ሁላችንም ችግር ሁላችን አውዳሚ፡ ሁላችን ባላገር ሁላችን እንግዳ፡ ሁላችንም ዘመድ ሁላችንም ባዳ፡ ሁላችን እንቅልፋም ሁላችንም ንቁ፡ ሁላችንም ድንጋይ ሁላችንም እንቁ፡ ሁላችንም ሳቂ ሁላችን አኩራፊ፡ ሁላችንም ሌባ ሁላችን ዘራፊ፡ ሁላችን ዝመኞች ሁላችን ለፍላፊ፡ ሁላችንም ክፉ ሁላችን ጠላፊ፡ ሁላችንም ተራ ሁላችን ዝነኛ፡ ሁላችንም ደጎች ሁላችን ምቀኛ፡ አስተውሎ ላየን እንደዚህ ነን እኛ፡ ሁላችን ፀበኛ ሁላችን ገላጋይ፡ ሁላችን ሴረኛ ሁላችንም ሸምጋይ፡ ሁላችን የበታች ሁላችን የበላይ፡ አንድነት ያቃተን ተናበን አንድ ላይ፡ ሁላችንም ተጓዥ ሁላችንም መጪ፡ ሁላችንም ቀሚ ሁላችንም ሰጪ፡ ሁላችን ከሳሽ ሁላችንም ቀጪ፡ ሁላችንም ጠላት ሆነን ለሁላችን፡ የጠላት መሳቂያ ሆኗል መኖራችን፡ መጨቆን መሰደድ በሀይማኖታችን፡ ሰበር ዜና ሆኗል ሁሌም መሞታችን፡ አሁን ያለንበት እንድህ ነው ሁላችን፡ 🔸...ኑረዲን አል-ዓረብ..✍️ t.me/nuredinal_arebi t.me/nuredinal_arebi

አልተቀየርንም፤ ለሰዎች የሚገባቸዉን ቦታ መስጠት አወቀንበት እንጂ።

አህባሽ ማን ነው? አህባሽ የሚባለው አንጃ ከውጪ ሲታይ የሚከተሉት ገጽታዎች አለት፡፡ 1. “አህባሽ” የኢትዮጵያ ተወላጅ በነበሩት ሼኽ አብደላሂ ሙሀመድ ዩሱፍ (ወይም ሼኽ አብደላህ አል-ሀረሪ አል-ሀበሺ) ጠንሳሽነት በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ውስጥ በ1983 አ.ል. የተመሰረተ ፖለቲካና ሀይማኖትን አንድ ላይ አጣምሮ የሚራመድ አንጃ (ጀመአ) ነው፡፡ 2. አንጃው በአረብኛ አጠራር “ጀምኢየቱል መሻሪኢል ኸይሪየቱል ኢስላሚያ” ይባላል ፡፡ የእንግሊዝኛ ስሙ “Association of Islamic  Charitable Projects” የሚል ነው፡፡ 3. “አህባሽ” የአንጃው ተከታዮች በጋራ የሚጠሩበት የቡድን ስማቸው ነው፡፡ እያንዳንዱ የጀመአው አባል “ሀበሺይ” ይባላል (ሴት ከሆነች “ሀበሺያ”  ትባላለች )፡፡ በሀገራችን ውስጥ ያሉት የአንጃው ተከታዮች ግን “አህባሽ”  ከሚለው ስም ይልቅ “የሼኽ ጀመዐ ነኝ” ማለትን ይመርጣሉ ፡፡ 4. “አህባሽ” የሚውለው ቃል ምንጩ “ሐበሻ” ከሚውለው የሀገራችን የአረብኛ  ስም ነው፡፡ ይህም የአንጃው መስራች የተወለደበትን ሀገር (ኢትዮጵያን)  ያመለክታል፡፡ የጀመኣው አባላት ይህንን ስም ይወዱታል እንጂ አይቃወሙትም፡፡ ስለዚህ እኛ የአህባሽ ተቃዋሚዎች ያወጣንላቸው ስም አድርጋችሁ እንዳታዩት ያስፈልጋል ፡፡ (እውነቱን ለማወቅ አህባሾችን ራሳቸውን ጠይቋቸው፡፡ ዌብሳይቶቻቸውንና የፋስቡክ ቡዴኖቻቸውን የሚጠሩበትንም ስም ተመልከቱ )፡፡ 5. አንጃው በሄደበት ሀገር ሁለ “መንግስታዊ ያልሆነ ማህበር” ተብሎ ነው የተመዘገበው፡፡ በመሆኑም ማህበራዊ አገልግልት የሚሰጡ አንዳንድ  ተቋማትን (እንደ መድረሳና የጤና ክሊኒክ የመሳሰሉትን ) ከፍቷል ፡፡ በሀገራችን ውስጥ ግን እንድህ አይነት ፕሮጀክቶችን የሰራ አይመስለኝም፡፡ 6. አህባሽን የመሰረቱት “ሼይኽ አብደላህ አል-ሀረሪ” ከአስራ ሰባት አመታት በፉት ቢሞቱም እስካሁን ድረስ የአንጃው ከፍተኛ መንፈሳዊ መሪ ተደርገው ይታያሉ ፡፡ በመሆኑም የጀመአው አባላት “ሼይኹና” ወይም “ሰይዱና” ይሏቸዋል ፡፡ በቤታቸው ግድግዳና በሌሎችም ቦታዎች (በሞባይል ስልካቸውም ጭምር) የመሪያቸውን ፎቶ ያስቀምጣሉ ፡፡ 7. የአንጃው ዋና ማዕከል (Head Quarter) ነሆው በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ውስጥ ነው፡፡ በተጨማሪም በሶሪያ፣ ዮርዲኖስ፣ ግብጽ

ጠቃሚ ምክሮች❗️ ✅ ወደ አላህ ተጠጋ፤ እሱ ለባሪያው ቅርብ ነውና! ✅ ለሁሉም ነገር አትቸኩል፤ ችኮላ የሸይጧን ነውና! ✅ የትም ብትሆን ፈጣሪህን ፍራ፤ እርሱ ካንተ ጋር ነውና! ✅ የበደለህን ይቅር
ጠቃሚ ምክሮች❗️ ✅ ወደ አላህ ተጠጋ፤ እሱ ለባሪያው ቅርብ ነውና! ✅ ለሁሉም ነገር አትቸኩል፤ ችኮላ የሸይጧን ነውና! ✅ የትም ብትሆን ፈጣሪህን ፍራ፤ እርሱ ካንተ ጋር ነውና! ✅ የበደለህን ይቅር በል፤ አላህ ይቅር ባዮችን ይወዳልና! ✅ በሁሉም ነገር ላይ ታገስ፤ አላህ ከታጋሾች ጋር ነውና! ✅ ድሆችን እርዳ፤ ሰደቃ/ ምጽዋት ወንጀልን ታብሳለችና! ✅ ባጣኸው ነገር አትበሳጭ፤ የተሻለውን ረበና ይሰጥኋልና! ✅ አትበሳጭ! ብስጭት የሰይጣንን በር ትከፍታለችና! ✅ በእጅህ የያዝከውን አትልቀቅ፤ ካጣኸው በኃላ ይቆጭኋልና! ✅ የትም ብትሆን ፈጣሪህን አስታውስ፤ ያስታውስኋልና! ✅ ባለህ ነገር አመስግን፤ አላህ ይጨምርልኋልና! ✅ ሰዎች ላይ አትመቀኝ፤ ምቀኝነት መልካም ስራን ትበላለችና! ✅ ተስፋህ በፈጣሪ ብቻ ይሁን፤ ሁሉን ማድረግ የሚችል ፈጣሪ ነውና! ✅ በወንድምህ ውድቀት አትደሰት፤ በሌላ ቀን ባንተም ላይ ሊደርስ ይችላልና! ✅ ያንተ ያልሆነን ነገር ያንተ ለማድረግ ብዙ አትድከም፤ ውሳኔው የፈጣሪ ነውና! ✅ ስትደሰት ብቻ ሳይሆን ስትከፋም ፈጣሪህን አመስግን፤ እርሱ አመስጋኞችን ይወዳልና! http://t.me/UmuAbais

አዎን ገንዘብ ወሣኝ ነው፡፡ ዲናችንም ቢሆን ድህነትንና ደካማነትን አይመክርም፡፡ ዛሬ ላይ በተለይ ኢማን ተዳክሞ ቁሳዊ ነገሮች ትልልቅ ዋጋ ባገኙበት ሰዓት ይዞ መገኘት መልካም ነገር ነው፡፡ ኢማን በሌላቸው ሰዎች ዘንድ፤ ያለዉና የሌለው ሰው በእኩል ዐይን እየታየ አይደለም፡፡ ቁሳዊነት በነገሰባት ዓለም፤ ገንዘብ ያላቸው ሰዎች ከፍተኛ ቦታ አላቸው፡፡ ገንዘብ ከሌለህ በድሮ ጓደኞችህ ጭምር ትገፋለህ፡፡ - ስልክህ ቶሎ አይነሳም፤ ንግግርህ ለጆሮ አይስብም፣ ወሬህ ዉሃ አይነሳም፣ ቀጠሮህ አይከበርም፣ ሽምግልናህ አይደመጥም ~ውዱ ነቢያችን የኸድጃ ገንዘብ እንደጠቀመኝ የማንም አልጠቀመኝም ይላሉ፡፡ የሚስታቸው። እነ ኸሊፋ ዑሥማን ኢብኑ ዐፋን በገንዘባቸው የሙስሊሙን ጦር ታድገዋል፡፡ ታላቁ የዒልም እና የሐዲሥ ሰው ዐብዱላህ ኢብኑ አል-ሙባረክ ሀብታም ነጋዴ ነበሩ፡፡ ዒልም ፈላጊዎች ዐይናቸው ወደ ዓለማዊ ጉዳይ እንዳያማትርና ሥራቸው ዒልም ብቻ እንዲሆን ብለው በከፍተኛ ሁኔታ ይደጉሟቸው ነበር፡፡ ትልቅ ስፖንሰር ሺፕነት ይሏል ይህ ነው፡፡ ለዲን የሚሠራን ሰው ከጀርባ ሆኖ ማሠራት፡፡ አንዳንዴ ራስህን ለማስከበርና  ለእልህም ስትል ገንዘብ ያስፈልግሃል!! t.me/AbuSufiyan_Albenan t.me/AbuSufiyan_Albenan

「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」 ╭┄┈┈⟢ ┊❏ ሒስኑል ሙስሊም ╰──────────╯ ╭🎙የደርሱ አቅራቢ:- ╎────⟢ ╎🎧 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ╰────────── ┍🖇 የዳውንሎድ ሊንክ: │h
「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」 ╭┄┈┈⟢ ┊❏ ሒስኑል ሙስሊም ╰──────────╯     ╭🎙የደርሱ አቅራቢ:- ╎────⟢ ╎🎧 ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ╰────────── ┍🖇 የዳውንሎድ ሊንክ: │https://play.google.com/store/apps/details?id=com.YusufAppNew.Hisnul.Muslim │ ├⎙  አሁኑኑ ዳውንሎድ በማድረግ ይጠቀሙ! └──────── ╭╼─────⟢ ┆📮 መሰል ጠቃሚ 📲አፖችን ማሰራት ┆የምትፈልጉ በ @Yusufapp_developer  ┆የቴሌግራም አድራሻችን ይነግሩን! ╰┈┈ ╭  ለመሰል ስራዎች ይቀላቀላሉን ┆ ┆http://t.me/Yusuf_App1 ╰╼─────────╯

🔘አጭር እና ቆንጆ የጁሙዓ ኹጥባ ​👤 ኹጥባውን ያደረጉት፡ ሸይኽ አህመድ (ከሳዑዲ ኤምባሲ) 📍 ቦታ፡ አዲስ አበባ — ቦሌ ጀዕፈር መስጂድ   🗣 ቋንቋ፡ በአረብኛ ቋንቋ የተደረገ ​📖 በኹጥባው ላይ የተዳሰሱ ዋና ዋና ነጥቦች ​① ተውሂዱል ኡሉሂያ (የአላህን ብቸኛ  ተመላኪነት)    🔘 ​የኢባዳ ዓይነቶች በሙሉ ለአላህ ብቻ እንደሚገቡ በሰፊው ተዳሷል። ​② የተውሂድ አሳሳቢነትና ታላቅነት   🔘​የሰው ልጅ የተፈጠረበት ዋና ዓላማና የእስልምና መሠረት መሆኑ በሰፊው ተብራርቷል። ​③ የሽርክ  አስከፊነት   🔘​አላህ ዘንድ የማይማር ትልቅ ወንጀልና የሥራዎችን ዋጋ የሚያሳጣ መሆኑ በሰፊው ተብራርቷል። ​④ ስለ ቢድዓ ምንነት   🔘​ቢድዓ በዲን ላይ የሚያስከትለው አደጋና ትክክለኛው መንገድ ምን እንደሆነ በሰፊው ተወስቷል። ​⑤ ኢኽላስ እና ሙታባዓ በዒባዳ ላይ ያላቸው አስፈላጊነት   🔘​ማንኛውም መልካም ሥራ በአላህ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ለአላህ ተብሎ ጥራት ተደርጎ የተሰራ(ኢኽላስ) እና የነቢዩን ሱና መከተል (ኢትባዕ) ግዴታ መሆናቸው ተብራርቷል። ​⑥ ስለ ተቅዋ (አላህን መፍራት)    🔘​የአላህን ትእዛዝ ማክበር፣ ክልከላዎቹን መራቅና የልብ መረጋጋትን ስለሚያስገኘው ተቅዋ ምክር ተለግሷል። ​   አላህ የሰማነውን ሰምተው ከሚተገብሩትና የተውሂድ ባለቤቶች ከሆኑት ባሮቹ ያድርገን!
ሼር ይደረግ
🔗🔗🔗https://t.me/ansuar_muhammed_0088

خطبة الجمعة  عنوانه ( تعظيم شأن الجمعة والتذكير ببعض أحكامها)             في مسجد  الصفا بمدينة هرا                                                                 🕌  ሃራ መስጂደ ሶፋ                                           صفر. 17     لِعَامِ. ١٤٤٨ه‍                                   🎤    በወንድም           አቡ ፈውዛን                       https://t.me/abufwzan31

Repost from TewhideAcadamy
👆ትምህርቱን ካዳመጡ በኋላ የሚከተለውን ማስፍጠሪያ በመጫን ጥያቄ በመስራት ምን ያህል እንደተረዱ እራሶን ይገምግሙ፡፡ https://forms.gle/V1aHARagVCWBtGoYA