የቀጠናው ተመልካች
Відкрити в Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
4 321
Підписники
+824 години
-47 днів
-7130 днів
Архів дописів
4 331
🇮🇷🇦🇪🇮🇱 የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የመከላከያ ኮሚቴ ለእስራኤል አቻዎቻቸው አቡ ዳቢ ለኢራን ጥቃቶች ምላሽ እንደምትሰጥ እና "ዝም እንደማይሉ" ተናግሯል።
4 331
🇦🇪🇺🇸🇮🇱🇮🇷⚡️በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ውስጥ አንድ ኦፊሴላዊ ምንጭ ለ CNN እንደተናገሩት፣
ኤሚሬትስ በሚቀጥሉት 24 ሰዓታት ውስጥ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት ሊያደርሱ እንደሚችሉ ትገምታለች።
4 331
+1
🇦🇪 የኤሜሬት ተጽእኖ ፈጣሪዎች ኢራን ላይ እየዛቱ ናቸው፡ "ዛሬ ማታ አንቺን አያርገን" ለዚህ ሥራሽ "ትጸጸቺያለሽ" እያሉ ናቸው።
4 331
❗️🇮🇷 🇦🇪በዚህ አጋጣሚ፣ የኢራንን ስትራቴጂካዊ ብልጠት አለማድነቅ ንፉግነት ይሆናል። በድርድር ስም አሜሪካ እና እስራኤልን ከሜዳው ውጭ ካደረገቻቸው በኋላ፣ የምትፈልጋቸውን One on One በግላጭ አገኘቻቸው።
ከ 50 ሀገሮች ጋር በአንዴ ከመዋጋት ይልቅ በስትራቴጂ አላያንሳቸውን በታትነህ፣ አንድ በአንድ ለብቻቸው ታጫውታቸዋለህ።
በእርግጥ በሚቀጥሉት ሰዓታት ነገሮች ይለዋወጡ፣ እነ አሜሪካም ሊገቡበት ይችላሉ።
4 331
🇦🇪 🇮🇷 በዱባይ የፋጁራ ወደብና የነዳጅ መሠረተ ልማቶች በክሩዝ ሚሳዬልና በድሮኖች ተመትተዋል። በቦታዎቹ እሳት እየነደደ ነው።
ኢራን አዲስ ያለችውን የሆርሙዝ አስተዳደራዊ መዋቀርና አሠራር በኤሜሬት ወደቦች ላይ ተግባራዊ እያደረገች ነው።
4 331
🇮🇷❗️🇦🇪 በኤሜሬት የፋጁራ ነዳጅ ኢንዱስትሪ በእሳት ተያይዟል፣ የፋጁራ ማውጫና ማጣሪያ እየነደደ ነው። UAE በድሮኖችና በሚሳዬሎች ተመታሁ ብላለች።
4 331
ትናንት ኢራን የ UAE የጦር ጀቶች በጦርነቱ ወቅት ኢራንን በመደብደብ በቀጥታ እንደተሳተፉ የሚያሳይ መረጃ በእጄ ገብቷል፣ በመጪው ቀናት አፀፋውን እመልሳለሁ ብላ ነበር።
4 331
🇦🇪 🇮🇷 ሰበር፡ ኢራን ሚሳዬሎች ወደ UAE ተኩሳለች። በኤሜሬት ፋጁራ ወደብ እሳት ተነስቷል። ከሰዓታት በፊት ኤሜሬት ምንም አደጋ የለም ብላ ነበር።
4 331
🇦🇪ፈርተን ያስፈራራናችሁ ባልተረጋገጠ ወሬ ነበር፣ ወደ ኖርማል እንቅስቃሴያችሁ መመለስ ትችላላችሁ፣ ብሏል የ UAE ማስታወቂያ ሚንስኒቴር።
4 331
🇦🇪❗️አስቸኳይ፡ UAE ባሁኑ ሰዓት ከኢራን የሚሳዬል ጥቃት ሊሰነዘርብኝ ነው በሚል አስቸኳይ መግለጫ አውጥታለች። ሕዝቡም ራሱን ከጥቃት መሸሸጊያ ቦታ አሁኑኑ እንዲያስገባ አሳስባለች።
4 331
🇮🇷 ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ "አዲስ የአሠራር መንገድ" ያለችውን መመሪያ ከተያያዥ የአካባቢው ካርታ ጋር ይፋ አድርጋለች። በዚህ ሁሉንም የኤሜሬት ወደቦች በአዲሱ ካርታ ማጠቃለሏ አነጋጋሪ ሆኗል።
"የ UAE ወደቦች በኢራን ቁጥጥር ሥር ይሆናሉ፣ በአሁኑ ሰዓትም ከሥራ ውጭ ናቸው፣ ታሽገዋል" ብላለች።
4 331
🇮🇷❌🇦🇪 - የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋዊ መግለጫ፡
"ሚኒስቴሩ፣ በሆርሙዝ ባሕር ወሽመጥ ለማለፍ በሞከሩ ሁለት የADNOC መርከቦች ላይ (ባለቤትነታቸው የኤሜሬት መንግሥት የሆኑ) በኢራን ድሮኖች ጥቃት እንደተሰነዘረባቸው አረጋግጧል" ብሏል። ክስተቱን "የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ 2817 ን በግልፅ መጣስ" እና "ለዓለም አቀፍ የኢነርጂ ደህንነት ቀጥተኛ ስጋት" በማለት ፈርጆታል። መግለጫው ይህ ተግባር "የኢራን ሽብርተኝነት" ነው ብሎታል።
ኤሜሬት የኢራንን የመርከቦች እገዳ ጥሶ ለማለፍ ከቀን ወደ ቀን የምታደርገው ጥረት ጨምሯል። ብዙዎች ይህን የኤሜሬት እንቅስቃሴ "ተስፋ የመቁረጥ" ያሉት ሲሆን፣ "ገንዘብ ተዘዋውሮ መሥራት ካለመቻል እና ገቢ ከማጣት" የመጣ እርምጃ ብለውታል።
4 331
🚨🔊 🇮🇱አሜሪካ የእስራኤልን ጦርነቶች ካልተቀላቀለች በስተቀር 'ሌላ 9/11' ሊገጥማት ይችላል - ቤኔት የቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር።
ናፍታሊ ቤኔት አሜሪካውያን የመካከለኛው ምስራቅን እና የእስራኤልን ጥያቄ ችላ ማለት ጥፋት እንደሚጋብዝ አስጠንቅቀዋል።
"9/11 ሲከሰት ማንሃተን ነበርኩ። እነዚያ ሕንፃዎች በእሳት ሲቃጠሉ አይቻለሁ... መካከለኛው ምስራቅ 'የእኛ ችግር አይደለም' ስትሉ የሚሆነው ያ ነው" ብሏል።
☢️ "አሜሪካን ከእስሬኤል ጎን እስካልሆነች ድረስ አሸባሪዎች በኑክሌር ጭምር ሊመቷት ይችላሉ" ብሏል ቀጣይ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የኔታንያሁ ተቀናቃኙ ናፍታሊ ቤኔት።
መልዕክቱ ግልጽ ነው፣ Blackmail ነው። አሜሪካን ጦርነታችንን ትዋጋ ወይም ውጤቱን ትጋፈጥ ነው።
4 331
ይሄ የኾነው፣ CENTCOM በሆርሙዝ ወሽመጥ የማለፍ ነፃነትን ለማረጋገጥ "Project Freedom" ያለውን ዘመቻ መጪው ሰኞ እንደሚጀምር ካወጀ ከሰዓታት በኋላ ነው።
4 331
🇷🇺 ማምሻውን በሞስኮ ከተማ ሰማይ ላይ የዩክሬን ድሮኖች ዝቅ ብለው ሲበሩ ማምሸታቸው ተነግሯል። የተመቱ ህንፃዎችም ስለመኖራቸው መረጃዎች እየወጡ ናቸው።
የኢራን ሸሂድ በዱባይ ሰማይ ይመስላል።
