fa
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

رفتن به کانال در Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 303
مشترکین
+824 ساعت
-47 روز
-7130 روز
آرشیو پست ها
🇦🇪ፈርተን ያስፈራራናችሁ ባልተረጋገጠ ወሬ ነበር፣ ወደ ኖርማል እንቅስቃሴያችሁ መመለስ ትችላላችሁ፣ ብሏል የ UAE ማስታወቂያ ሚንስኒቴር።
🇦🇪ፈርተን ያስፈራራናችሁ ባልተረጋገጠ ወሬ ነበር፣ ወደ ኖርማል እንቅስቃሴያችሁ መመለስ ትችላላችሁ፣ ብሏል የ UAE ማስታወቂያ ሚንስኒቴር።

🇦🇪❗️አስቸኳይ፡ UAE ባሁኑ ሰዓት ከኢራን የሚሳዬል ጥቃት ሊሰነዘርብኝ ነው በሚል አስቸኳይ መግለጫ አውጥታለች። ሕዝቡም ራሱን ከጥቃት መሸሸጊያ ቦታ አሁኑኑ እንዲያስገባ አሳስባለች።
🇦🇪❗️አስቸኳይ፡ UAE ባሁኑ ሰዓት ከኢራን የሚሳዬል ጥቃት ሊሰነዘርብኝ ነው በሚል አስቸኳይ መግለጫ አውጥታለች። ሕዝቡም ራሱን ከጥቃት መሸሸጊያ ቦታ አሁኑኑ እንዲያስገባ አሳስባለች።

🇮🇷 ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ "አዲስ የአሠራር መንገድ" ያለችውን መመሪያ ከተያያዥ የአካባቢው ካርታ ጋር ይፋ አድርጋለች። በዚህ ሁሉንም የኤሜሬት ወደቦች በአዲሱ ካርታ ማጠቃለሏ አነጋጋሪ ሆኗል።
🇮🇷 ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ "አዲስ የአሠራር መንገድ" ያለችውን መመሪያ ከተያያዥ የአካባቢው ካርታ ጋር ይፋ አድርጋለች። በዚህ ሁሉንም የኤሜሬት ወደቦች በአዲሱ ካርታ ማጠቃለሏ አነጋጋሪ ሆኗል። "የ UAE ወደቦች በኢራን ቁጥጥር ሥር ይሆናሉ፣ በአሁኑ ሰዓትም ከሥራ ውጭ ናቸው፣ ታሽገዋል" ብላለች።

🇮🇷❌🇦🇪 - የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋዊ መግለጫ፡ "ሚኒስቴሩ፣ በሆርሙዝ ባሕር ወሽመጥ ለማለፍ በሞከሩ ሁለት የADNOC መርከቦች ላይ (ባለቤትነታቸው የኤሜሬት መንግ
🇮🇷❌🇦🇪 - የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይፋዊ መግለጫ፡ "ሚኒስቴሩ፣ በሆርሙዝ ባሕር ወሽመጥ ለማለፍ በሞከሩ ሁለት የADNOC መርከቦች ላይ (ባለቤትነታቸው የኤሜሬት መንግሥት የሆኑ) በኢራን ድሮኖች ጥቃት እንደተሰነዘረባቸው አረጋግጧል" ብሏል። ክስተቱን "የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ 2817 ን በግልፅ መጣስ" እና "ለዓለም አቀፍ የኢነርጂ ደህንነት ቀጥተኛ ስጋት" በማለት ፈርጆታል። መግለጫው ይህ ተግባር "የኢራን ሽብርተኝነት" ነው ብሎታል። ኤሜሬት የኢራንን የመርከቦች እገዳ ጥሶ ለማለፍ ከቀን ወደ ቀን የምታደርገው ጥረት ጨምሯል። ብዙዎች ይህን የኤሜሬት እንቅስቃሴ "ተስፋ የመቁረጥ" ያሉት ሲሆን፣ "ገንዘብ ተዘዋውሮ መሥራት ካለመቻል እና ገቢ ከማጣት" የመጣ እርምጃ ብለውታል።

🚨🔊 🇮🇱አሜሪካ የእስራኤልን ጦርነቶች ካልተቀላቀለች በስተቀር 'ሌላ 9/11' ሊገጥማት ይችላል - ቤኔት የቀድሞው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር። ናፍታሊ ቤኔት አሜሪካውያን የመካከለኛው ምስራቅን እና የእስራኤልን ጥያቄ ችላ ማለት ጥፋት እንደሚጋብዝ አስጠንቅቀዋል። "9/11 ሲከሰት ማንሃተን ነበርኩ። እነዚያ ሕንፃዎች በእሳት ሲቃጠሉ አይቻለሁ... መካከለኛው ምስራቅ 'የእኛ ችግር አይደለም' ስትሉ የሚሆነው ያ ነው" ብሏል። ☢️ "አሜሪካን ከእስሬኤል ጎን እስካልሆነች ድረስ አሸባሪዎች በኑክሌር ጭምር ሊመቷት ይችላሉ" ብሏል ቀጣይ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው የኔታንያሁ ተቀናቃኙ ናፍታሊ ቤኔት።  መልዕክቱ ግልጽ ነው፣ Blackmail ነው። አሜሪካን ጦርነታችንን ትዋጋ ወይም ውጤቱን ትጋፈጥ ነው። 

ይሄ የኾነው፣ CENTCOM በሆርሙዝ ወሽመጥ የማለፍ ነፃነትን ለማረጋገጥ "Project Freedom" ያለውን ዘመቻ መጪው ሰኞ እንደሚጀምር ካወጀ ከሰዓታት በኋላ ነው።

🇮🇷🇦🇪⚡️- ሰበር፡ IRGC ከፋጁራ UAE በስተሰሜን ሲንቀሳቀስ የነበረን መርከብ በሚሳዬል መምታቱን ገለጸ።
🇮🇷🇦🇪⚡️- ሰበር፡ IRGC ከፋጁራ UAE በስተሰሜን ሲንቀሳቀስ የነበረን መርከብ በሚሳዬል መምታቱን ገለጸ።

🇷🇺 ማምሻውን በሞስኮ ከተማ ሰማይ ላይ የዩክሬን ድሮኖች ዝቅ ብለው ሲበሩ ማምሸታቸው ተነግሯል። የተመቱ ህንፃዎችም ስለመኖራቸው መረጃዎች እየወጡ ናቸው። የኢራን ሸሂድ በዱባይ ሰማይ ይመስላል።

🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር፡ ትራምፕ፣ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የአሜሪካ ጦር በሆርሙዝ ባሕር ወሽመጥ ውስጥ መርከቦችን ማጀብ እንደሚጀምር ተናገረ። ሥራው በወሽመጡ ለወራት የቆሙትን አጅቦ በማሻገር የሚጀመር ይ
🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር፡ ትራምፕ፣ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የአሜሪካ ጦር በሆርሙዝ ባሕር ወሽመጥ ውስጥ መርከቦችን ማጀብ እንደሚጀምር ተናገረ። ሥራው በወሽመጡ ለወራት የቆሙትን አጅቦ በማሻገር የሚጀመር ይሆናል ብሏል። ትራምፕ፣ ኢራን ይህን ጉዳይ በማንኛውም መንገድ ለማስተጓጎል ብትሞክር፣ በኃይል እናስቆማታለን ሲልም አስጠንቅቋል።

+1
🇮🇷🇦🇪🇮🇱🇺🇸🇮🇷⚡️ የእስራኤል የፀጥታ ካቢኔ በኢራን ጉዳይ ከኔታንያሁ ጋር እስካሁን ለ 3 ሰዓት በቀጠለ ዝግ ስብሰባ ተቀምጠዋል። የኢራን ጦር፣ IRGC፣ በሚና ሳክር እና ራስ አል ካይማህ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ወደቦች ላይ የቆሙ መርከቦች፣ አሁኑኑ ወደ ዱባይ እንዲሄዱ፣ ያለበለዚያ መዘዝ እንደሚከተላቸው አስጠንቅቋል። ይህን ያለው፣ በጦርነቱ ጊዜ ኢራንን በመደብደብ ላይ የኤሜሬት የጦር ጀቶች በቀጥታ መሳተፋቸውን በማያዳግም ማስረጃ አረጋግጫለሁ ካለ በኋላ ነው። ዛሬ በቀጠናው የአየር ክልል፣ ብዛት ያላቸው የአሜሪካ ወታደራዊ አይሮፕላኖች ከፍተኛ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ውለዋል፣ በአካባቢው የጦር መሳሪያ ሲያራግፉ ነው የዋሉት። እንደ ሊባኖስ ቴሌቪዥን ጋዜጠኛ፣ በትናንትናው ዕለት ብቻ የአሜሪካ አይሮፕላኖች 6500 ቶን የጦር መሳሪያ በእስራኤል አራግፈዋል። በዚህ ሰዓት የኢራን ጦርም በተጠንቀቅ ላይ ይገኛል ተብሏል። ትራምፕ አዲሱን የኢራንን ፕሮፖዛል ውድቅ ማድረጉን ካስታወቀ በኋላ፣ በአካባቢው የነበረው ውጥረት ወደ ከፋ ሁኔታ ተሸጋግሯል። ምናልባት መጪዎቹ ጥቂት ሰዓታት ቀጠናው ትልቅ ክስተት ሊያስተናግድ ይችላል፣ ተብሎ ተፈርቷል።

🇺🇸 ትራምፕ፡ የኢራንን ፕሮፖዛል አይቼዋለሁ። ልቀበለው ይከብደኛል፣ አልቀበለውም!

🇺🇸🇨🇺 የኩባ ፕሬዝዳንት ዲያዝ-ካኔል ትራምፕ አገሪቱን ለመውረር ስለሚያደርጉት ዛቻ - "
ማንም አጥቂ፣ የቱንም ያህል ኃያል ቢሆን፣ በኩባ ውስጥ እጅ የሚሰጥ ሰው አያገኝም። በእያንዳንዱ ኢንች ብሔራዊ ግዛታቸው ላይ ሉዓላዊነታቸውን እና ነፃነታቸውን ለመጠበቅ የቆረጠ ህዝብ ይገጥማቸዋል።"

🇮🇷 አሜሪካ ለኢራን አዲሱ ፕሮፖዛል መልስ ሰጥታለች፣ ኢራን መልሱን እያጠናችው ነው -- ኢራን ውጭ ጉዳይ

⚡️🇦🇪 🇵🇰 ሰብዓዊ መብቶች፡ የተባበሩት አረብ ኢሚሬት በሀገሪቱ ውስጥ የሚኖሩ የፓኪስታን ሺአዎችን ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ ጀምራለች። እነዚህ ሺዓዎች በህጋዊ ፈቃድ የሚሠሩና የሚኖሩ ሲሆኑ፣ ሺዓዎች በመሆናቸው ብቻ ቁጠባቸው እና ደሞዛቸው ተይዞ ያለምንም ካሳ በግዳጅ ተጎትተው ከሀገር እየተባረሩ ነው።

🇱🇧 ዛሬ፣ በሰሜን ሊባኖስ ቀውራ በተባለች መንደር በምትገኘው የማርያም ቤተ ክርስቲያን፣ ለቀስተኞች ለተገደለ የሂዝቦላ ተዋጊ፣ ኢብራሒም ጃዕፈር ሳሊም፣ የአሸኛኘት ፕሮግራም ሲያደርጉለት ታይተዋል።

🇮🇷⚡️🇺🇸 — IRGC ደህንነት ባለሥልጣን: የአሜሪካ የውሳኔ 'መስኮት' በጣም ጠቧል፣ አጣብቂኝ ውስጥ ነው። እናም ትራምፕ፣ ወይ አዳጋች ጦርነት ኢራን ላይ መክፈት አለበት ወይ ለሀገሩ ጥሩ ያልሆነ ስምምነት መፈራረም አለበት።

🚨⚠️ ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ 4pm በምሥራቅ አሜሪካ ሰዓት አቆጣጠር ላይ፣ ወይም ከምሽቱ 5: 30 በቴህራን ሰዓት፣ አስቸኳይ መግለጫ ያወጣል! አንድ አስፈላጊ ነገር ካልተከሰተ በስተቀር ብዙውን ጊዜ ቅዳሜና እሁድ አይናገርም።

ትራምፕ ስለ አዲሱ የኢራን ፕሮፖዛል፡ በጥንቃቄ የማጤነው ይሆናል … ነገር ግን ኢራን በሰው ልጅ ላይ ባለፉት 47 ዓመታት ላደረሰችው መዓት የሚገባትን ዋጋ አለማግኘቷ ለማሰብ ራሱ ይከብዳል።
ትራምፕ ስለ አዲሱ የኢራን ፕሮፖዛል፡
በጥንቃቄ የማጤነው ይሆናል … ነገር ግን ኢራን በሰው ልጅ ላይ ባለፉት 47 ዓመታት ላደረሰችው መዓት የሚገባትን ዋጋ አለማግኘቷ ለማሰብ ራሱ ይከብዳል።

🇮🇷⚡️🇺🇸🇮🇱 ኢራን ለአሜሪካ ያቀረበችው አዲስ ፕሮፖዛል ዝርዝር: - ዳግመኛ ላንጠቃ ዋስትና ይሰጠን። - የአሜሪካ ወታደሮች ከ'ኢራን አካባቢ' ለቀው ይውጡ። - የተወረሱ ንብረቶች ይለቀቁ፣ ማካካሻ ይከፈል። - ማዕቀቦች ይነሱ - ሊባኖስን ጨምሮ በሁሉም ቦታ ሰላም ይስፈን - አዲስ የሆርሙዝ የሀሠራር ሥርዓት ይዘርጋ - የባህር ኃይል እገዳ ካሁን በኋላ ይቁም። ቴህራን አሁን የዋሽንግተንን መልስ እየጠበቀች ነው። 

🇮🇷 ሰበር፡ ኢራን ጦርነቱ ሙሉ በሙሉ በዘላቂነት እስካልቆመ ድረስ፣ በኒውክሊየር ፕሮግራሜ ጉዳይ በምንም ሁኔታ አልወያይም አለች -- The New York Times