የቀጠናው ተመልካች
Відкрити в Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
4 303
Підписники
+824 години
-47 днів
-7130 днів
Архів дописів
4 321
🇺🇸 ትራምፕ፣ ምሽቱን በዋይት ኃውስ በደገሰው የ UFC ድብድብ ትርዒት፣ ከነ ሙሉ ግርማው ሲንጎማለል ታይቷል።
*-*-*-
ችግሩ አሁን በዚህ ሰዓት ኃይለኛ ዝናብ እየጣለ ነው የእድር ቤቱ ድንኳን ብዙ ቦታ የተጣጣፈነው። እንደው ያ ወጥ፣ ስንት የተለፋበት እንዴት ሆኖ ይሆን?
4 321
🇺🇸🇮🇷 ከእኔ በፊት ብዙ ፕሬዝዳንቶች ከኢራን ጋር ለመግባባት ሞክረዋል፣ አንዳቸውም ግን አልተሳካላቸው። ከእኔ በቀር። የሆርሙዝ ባሕር መንሸራሸሪያዎች ዓርብ ክፍት ይሆናሉ፣ ነዳጆች በሁለቱም በኩል ይፈሳሉ፣ ለቀጠናው እና ለዓለም -- Trump
4 321
🇮🇷🤝🇺🇸 ትራምፕ፡ እንኳን ደስ ያላችሁ፣ እንኳን ደስ ያላችሁ፣ እንኳን ደስ ያላችሁ። የሆርሙዝ ወሽመጥ ተከፍቷል፣ እገዳውን አንስቻለሁ። የዓለም መርከቦች ይንሸራሸሩ፣ ነዳጁ በቦዩ ይፍሰስ።
4 321
ሰበር ዜና፡ በስተመጨረሻም ሁሉ ነገር ተሳካ።
የድርድሩ አለቃ፣ የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ ሻባዝ ሸሪፍ፣ ተ ፈ ራ ረ ሙ፣ ሲል አወጇል። ኦፊሴላዊ የፍርሚያው ቀን እንደ ፈረንጆች June 19,2026 እንደሚሆን ተናግሯል።
አለቃ ሻባዝ ሸሪፍ አክሎም፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ኢራን ላደረጉት ጥረት ሁሉ፣ ምሥጋና ይገባቸዋል፣ ብሏል።
ከዚህ በኋላ፣ በሚመጡት ጥቂት ቀናት፣ የተደረሰበትን ስምምነት ለማሳለጥ ይረዳ ዘንድ፣ በሁለቱ ቡድኖች መካከል በርካታ ስብሰባዎችና መገናኘቶች እንደሚኖሩ፣ ሁሉምም በጥሩ ይሄዳል የሚል ተስፋ እንዳለው ተናግሯል።
4 321
🇺🇸🇮🇷⚡️ትራምፕ፡
የኢራንን የኒውክሊየር አቧራ ቀስ ብለን የምንሰበስበው ይሆናል፣ ከአንድ ከሁለት ወር በኋላ፣ የሚያጣድፈን ምንም ነገር። አያሰጋንም።
4 321
🇮🇷⚡️🇮🇱 ሰበር ዜና፡ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከኢራን ጋር ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተናገረ። እስካሁን ግን፣ ከኢራን የተሰጠ ማረጋገጫ የለም።
4 321
🇮🇷⚡️🇺🇸 እንደ እስራኤሉ ጋዜጣ፣ Ynet ዘገባ፡ ኢራን በእስራኤል ላይ ያሰበችውን ጥቃት፣ ለድርድሩ እስትንፋስ ለመስጠት ስትል፣ ለማራዘም እንደወሰነች ጽፏል።
የኳታር ልዑካን ዛሬ ጠዋት ጀምሮ፣ በቴህራን ተገኝተው፣ መስገድ እስኪቀራቸው ድረስ፣ የኢራን ባለስልጣናትን "ያሰቡትን ጥቃት፣ ለጊዜው እንዲተው" ከፍተኛ ጥረት አድርገው ውለዋል፣ ይህም ፍሬ ሳያፈራላቸው እንዳልቀረ ተነግሯል።
4 321
🇮🇷⚡️🇺🇸 በእስራኤል ላይ በማንኛውም ሰዓት ጥቃት ሊሰነዘር ይችላል፣ ብዬ እየጠበቅኩኝ ነው።
ኢራን፣ የሀገሯን ምዕራባዊ ክፍል አየር፣ ለምንም ዓይነት በረራ ዝግ አድርጋለች።
4 321
🇮🇷⚡️🇺🇸 ኢራን እስራኤልን እንዳታጠቃ፣ አሜሪካ $12 ቢሊዮን ዶላር በምላሹ ልትሰጣት ፈልጋ እንደነበር፣ ነገር ግን ኢራን "ሞራሌን እና ወዳጆቼን በገንዘብ አልለውጥም" በማለት ውድቅ እንዳደረገች፣ የእስራኤሉ ቻናል 12 ዘግቧል።
በዘገባው፣ ገንዘቡ ለኢራን ቀርቦ የነበር ሲሆን፣ ወዲያው ኢራን አልፈልግም ማለቷ ተገልጿል።
4 321
🇺🇸🇮🇱🇱🇧🇮🇷 ⚡️ — ፕሬዚዳንት ትራምፕ ለAxios:
ቢቢ ለምን አባቱ ኢራንን እንዳጠቃ አላውቅለትም። በጣም ነው የተናደድኩት። አሳውቄዋለሁ። የእሱ (የብልግና ቃል) ማገናዘቢያው ተዘግቷል።ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ይፈረማል የሚል ትልቅ ተስፋ አለኝ። ኢራን ሚሳዬል በአፀፋ እስራኤል ላይ እንዳትተኩስ እየተማፀንኳት ነው። አያስፈልገንም።
4 321
🇺🇸🇮🇷🇮🇱 ፕሬዚዳንት ትራምፕ፣ ዛሬ እስራኤል በሊባኖስ ላይ በሰነዘረችው ጥቃት እንዳዘነ እና መፈፀም የሌለበት እንደነበር ተናገረ። በዚህ ሁላችንም ስንጠብቀው በነበረው ትልቅ ቀን፣ የለፋንበት ሁሉ ጫፍ በደረሰበት፣ የእስራኤል ጥቃት መሆን ያልነበረበት ነው፣ ብሏል። አክሎም፣ ሁሉም አካላት በያሉበት እንዲረጋጉ እና ለቀጠናው ዘላቂ ሰላም ሊያመጣ ያለው ስምምነት እንዲፈረም አሳስቧል።
4 321
🇺🇸 ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ መልካም የ80 ዓመት የልደት በዓል ይሁንልዎ እላለሁ።
'መልካም ልደት' የሚለውን ሙዚቃ ስጋብዝዎ በደስታ ነው። ማርኮ ሩቢዮ ከዩትዩብ ላይ ሊያወርድልዎ ይችላል። ሊንኩን ልኬለታለሁ።
4 321
🇮🇷 የኢራን ደህንነት መስሪያ ቤት፣ 'የአሜሪካ እና የፅዮናዊያንን ዓላማ' ለማሳካት እና ሀገር ለማወክ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 126 የወሃቢ/ተክፊሪ አመራሮችን በክትትል መያዙን እና ህቡዕ አደረጃጀታቸውን ማፍረሱን ተናገረ።
4 321
🇮🇱⚡️🇮🇷 እስራኤል ጦሯ በተጠንቀቅ እንዲሆን አሳስባለች። ከኢራን ባለስቲክ ሚሳዬሎች ይተኮሳሉ ብላም እየጠበቀች ነው። ዮርዳኖስ በበኩሏ፣ ለእስራኤል በማገዝ የኢራንን ሚሳዬል እስራኤል ከመድረሱ በፊት በአየሯ ለመታት ጦሯ እንዲዘጋጅ ትእዛዝ አውርዳለች።
4 321
🇮🇱🇮🇷⚡️የእስራኤል HAARETZ ጋዜጣ፡
"እስራኤል በስሌቷ ተሳስታለች፣ ማድረግ የነበረባትን ነው ያደረገችው። አፀፋውን ከኢራን ትጠብቅ።
4 321
🇷🇺⚡️🇺🇦 — እጅግ ግዙፍ የተባለ የዩክሬን የድሮን ጥቃት፣ ሪብኒስክ ሩሲያ ውስጥ በሚገኝ የነዳጅ ማጣሪያ፣ የማዳበሪያ ፋብሪካ እና የኬሚካል ኢንዱስትሪ ላይ፣ ዛሬ ንጋት መፈፀሙ ታውቋል። የፍንዳታው ጭስ መላውን ከተማና አካባቢውን ሸፍኖታል።
*-*-*
ሩሲያ ዓይናችን እያየ እየተበለተች ነው፣ አላወቀችውም እንጂ። ፑቲን፣ ሀገሩ እና ጦሩ፣ ያለውን እምቅ አቅም ተጠቅሞ ጨዋታውን በአንድ ጊዜ የሚቀይር እርምጃ እንዳይወስድ፣ እጅና እግሩን አሳስሮታል። ሩሪያንም እያስበላ ነው። ምን አስቦ ነው ግን? ይህ የኔ ምልከታ አይደለም፣ የብዙ የሩሲያዊያን ምልከታ ነው። ሰውዬው ፈርቷል!
