የቀጠናው ተመልካች
الذهاب إلى القناة على Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
إظهار المزيدلم يتم تحديد البلدالفئة غير محددة
4 307
المشتركون
-124 ساعات
-217 أيام
-8630 أيام
أرشيف المشاركات
4 307
🇮🇱⚡️🇹🇷 የቱርኩ ኤርዶጋን እና የእስራኤሉ ኔታንያሁ፣ ዛሬ፣ በለየለት የቃላት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል። ኤርዶጋን፡
ሞራለ-ቢሱ እና ሰው በላው ኔታንያሁ እና ፋሽስት ሀገሩ እስራኤል፣ በግዜ እንዲቆሙ ካልተደረገ፣ አንድ ሂትለር በለኮሰው ጦርነት 80 ሚሊዮን አውሮፓዊያን እንዳለቁት ሁሉ፣ እነዚህ እብዶችም ዓለምን በእሳት ያያይዙታል። በጋዛ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በኛም ቀጠና የምታደርገው ኢ ሰብዓዊ ድርጊት ሁሉም ተረባርቦ ካላስቆመ፣ ፍርድ ከራሴ፣ ኋላ ሁልሽም ታለቅሻለሽ። ይሄንን ጉዳይ፣ በቅርቡ በአንካራ በሚደረገው እና ትራምፕ በሚካፈልበት የኔቶ ስብሰባ ላይ ስለዚህ ጉዳይ አንስቼ፣ በሆዳችን አምቀን የያዝነውን እናፈነደዋለን'ለዚህም የኤርዶጋን ክስ እና ማስፈራራት፣ ኔታንያሁ ምላሽ ሰጥቷል፡
'አንተ ሞራል አለኝ ብለህ ስታወራ፣ ትንሽ አይሰቀጥጥህም? አፍህን ብትዘጋ ይሻላል፣ አንት ግጭት ጠማቂ! ቱርክ የምትባል ፀረ-ሴማዊ ሀገር እየመራህ፣ በኩርዶች ላይ ዘር ማጥፋት የምትፈጽም፣ አርሜኒያን የበላህ፣ በሶሪያ ላይ ላለፉት 13 ዓመታት ሕዝብና ሀገሩን ስታጨፋጭፍ የነበርክ አረመኔ፣ እስራኤልን እና ክቡር ሰራዊቷን፣ በምንም ዓይነት ሞራል ልትናገር አትችልም። አርፈህ ተቀመጥ!
4 307
🇮🇱⚡️🇹🇷 የቱርኩ ኤርዶጋን እና የእስራኤሉ ኔታንያሁ፣ ዛሬ፣ በለየለት የቃላት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል። ኤርዶጋን፡
ሞራለ-ቢሱ እና ሰው በላው ኔታንያሁ እና ፋሽስት ሀገሩ እስራኤል፣ በግዜ እንዲቆሙ ካልተደረገ፣ አንድ ሂትለር በለኮሰው ጦርነት 80 ሚሊዮን አውሮፓዊያን እንዳለቁት ሁሉ፣ እነዚህ እብዶችም ዓለምን በእሳት ያያይዙታል። በጋዛ፣ በመካከለኛው ምሥራቅ፣ በኛም ቀጠና የምታደርገው ኢ ሰብዓዊ ድርጊት ሁሉም ተረባርቦ ካላስቆመ፣ ፍርድ ከራሴ፣ ኋላ ሁልሽም ታለቅሻለሽ። ይሄንን ጉዳይ፣ በቅርቡ በአንካራ በሚደረገው እና ትራምፕ በሚካፈልበት የኔቶ ስብሰባ ላይ ስለዚህ ጉዳይ አንስቼ፣ በሆዳችን አምቀን የያዝነውን እናፈነሀዋለን'ለዚህም የኤርዶጋን ክስ እና ማስፈራራት፣ ኔታንያሁ ምላሽ ሰጥቷል፡
'አንተ ሞራል አለኝ ብለህ ስታወራ፣ ትንሽ አይሰቀጥጥህም? አፍህን ብትዘጋ ይሻላል፣ አንት ግጭት ጠማቂ! ቱርክ የምትባል ፀረ-ሴማዊ ሀገር እየመራህ፣ በኩርዶች ላይ ዘር ማጥፋት የምትፈጽም፣ አርሜኒያን የበላህ፣ በሶሪያ ላይ ላለፉት 13 ዓመታት ሕዝብና ሀገሩን ስታጨፋጭፍ የነበርክ አረመኔ፣ እስራኤልን እና ክቡር ሰራዊቷን፣ በምንም ዓይነት ሞራል ልትናገር አትችልም። አርፈህ ተቀመጥ!
4 307
🇺🇦⚡️🇷🇺 ዩክሬን፣ ከትናት ቀትር ጀምሮ፣ ከድንበሯ ወደ ሩሲያ እስከ ሺ ሰባት መቶ ኪ.ሜ ዘልቃ በመግባት፣ በድሮኖች እና በሚሳዬሎች ከፍተኛ የሆነ ውድመት በሩሲያ የኢነርጂ መሠረተ- ልማቶች ላይ አድርሳለች።
ዘለንስኪ፣ ጦራችን ሩሲያ ዘልቆ መግባት ቀልሎታል፣ ሩሲያ እና ሩሲያዊያን እስኪያማቸው እና እስኪሰማቸው ድረስ ጥቃታችን ይቀጥላላል ብሏል።
በበርካታ የሩሲያ አካባቢዎች፣ በጋዝ ማደያዎች ፊት ለፊት ረጃጅም ሰልፎችን ማየት እየተለመደ መጥቷል።
4 307
🇺🇸⚡️🇮🇷 ሰበር ዜና፡ ትራምፕ ኢራን ከባድ ዋጋ መክፈል ይኖርባታል፣ በማለት ተናገረ። ከኢራን ጋር ሲደረግ የቆየው ድርድር እንዳበቃ ፍንጭ ሰጥቷል። "ብዙ ጊዜ ሞከርናቸው፣ ብዙ ልናሳምናቸው ጣርን፣ ነገር ግን ምላስ ብቻ ናቸው ተግባር የለም። እስካሁንም የፈረሙት ወይም ቃል የገቡች አንዳች ነገር የለም፣ ብሏል።
ለFOX NEWS በሰጠው ሌላ ቃለ መጠይቁ፣ የኢራንን የኢነርጂ መሠረተ ልማቶችን እና ድልድዮችን ወደ ማውደም በእርቡ ሊመለስ እንደሚችል ተናግሯል።
እንደ አንዳንዶች፣ ስምምነቱ በዚህ ያለ የአለመተማመን ሁኔታ ውስጥ መቀጠል እንደማይችል እና ከንግግሩ ልትወጣ እንደሆነ ቀደም ብላ ኢራን ለአሜሪካ አሳውቃለች።
4 307
🇸🇦 ሳዑዲ፣ NOEM ፕሮጀክትን ለመሰረዝ $16 ቢሊዮን ዶላር ክፍያ አፍጥጦባታል።
ሳዑዲ፣ NOEM የተባለ ምናባዊ ከተማ ለመገንባት እቅድ ይዛ ነበር።
በሳዑዲ 'በገበታ ለሀገር' ፕሮግራም፣ ለዚሁ ለማይጨበጥ ከተማ፣ አላሙዲንን ጨምሮ፣ ባለ ሃብቶቿ ኪሳቸው ተገልብጦ ተበርብሯል። መክፈል የሚችሉት ከፍለዋል፣ ሳይችሉ የቀሩት እስከ አሁን ዘብጥያ አሉ።
ግንባታው፣ $1 ትሪሊየን ዶላር ይፈጃል ተብሎ የነበረ ሲሆን፣ ነገር ግን፣ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ፣ ሳዑዲ ባጋጠማት የበጀት እጥረት፣ የውጭ ኢንቨስትመንት መቀዛቀዝ፣ የነዳጅ ዋጋ መውደቅ እና ወቅታዊው የቀጠናው ትኩሳት መፈጠር፣ ካዝናዋን ሊያራቁትባት ችሏል። ለፕሮጀክቱ ማስኬጃ ገንዘብ በማጣቷ ምክኒያትም፣ ፕሮጀክቱን ለመሰረዝ ተገዳለች።
አሁን ደግሞ ሌላ ትኩሳት መጥቶባታል፣ ፕሮጀክቱን ልሰርዝ ብላ ስትነሳ፣ ከኮንትራክተሮች ጋር የተዋዋለችው ስምምነት በቢሊዮን የሚቆጠር የገንዘብ ቅጣት የሚያስከፍላት ሆና አግኝተዋለች።
ሳዑዲ፣ የገባችውን ውል ለመሰረዝ፣ $16 ቢሊዮን ዶላር ክፍያ ተጠይቃለች።
*-*-*
በማንቁርት ላይ ጆሮ ደግፍ
4 307
❌🇺🇸🇯🇴🇧🇭 - IRGC የዛሬውን ምሽት ተግባራት አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል -
በቀጠናው በሚገኙ የአሜሪካ አየር እና የባሕር ኃይል ሰፈሮች ላይ፣ 21 ኢላማዎችን በመምታት እና በጃም ካውንቲ ሰማይ ላይ የ MQ9 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በማውረድ የ IRGC ባሕር ኃይል የተሳካ ሥራን መሥራት ችሏል። የጠላትን ከሃዲያዊ እርምጃ አይቶ፣ ዘመቻውን ለማጠናቀቅ፣ የእስልምና ሃይሎች እና የ IRGC ደፋር የኤሮስፔስ ተዋጊዎች፣ በዮርዳኖስ በሚገኘው የአሜሪካ አየር ማረፊያ እና በውስጡ ያሉ መሳሪያዎች እና የ F4 ተዋጊ መጠለያዎችን ጨምሮ፣ 35 አስፈላጊ ኢላማዎችን ኢላማ አድርገው አውድመዋል። ጦራችን፣ ለማንኛውም አዲስ ጥቃት አስጨናቂ እና ቆራጥ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ናቸው! ማንኛውም አዲስ ጥቃት በጠላት አሜሪካ ላይ መዘዝ የሚያመጣ ይሆናል።
4 307
❌🇺🇸🇯🇴🇧🇭 - IRGC የዛሬውን ምሽት ተግባራት አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል -
በቀጠናው በሚገኙ የአሜሪካ አየር እና የባህር ኃይል ሰፈሮች ላይ፣ 21 ኢላማዎችን በመምታት እና በጃም ካውንቲ ሰማይ ላይ የ MQ9 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን በማውረድ የ IRGC ባሕር ኃይል የተሳካ ሥራን መሥራት ችሏል። የጠላትን ከሃዲያዊ እርምጃ አይቶ፣ ዘመቻውን ለማጠናቀቅ፣ የእስልምና ሃይሎች እና የ IRGC ደፋር የኤሮስፔስ ተዋጊዎች በዮርዳኖስ በሚገኘው የአሜሪካ አየር ማረፊያ እና በውስጡ ባሉ መሳሪያዎች እና የ F4 ተዋጊዎችን መጠለያዎችን ጨምሮ 35 አስፈላጊ ኢላማዎችን ኢላማ አድርገው አውድመዋል። ጦራችን ለማንኛውም አዲስ ጥቃት አስጨናቂ እና ቆራጥ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ናቸው! ማንኛውም አዲስ ጥቃት በጠላት አሜሪካ ላይ መዘዝ የሚያመጣ ይሆናል።
4 307
🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር ዜና፡ በኩዌት የአደጋ ጊዜ አዋጅ ታውጇል፣ ጦሩ የኢራንን ሚሳዬሎች በኩዌት ሰማይ ላይ እየተጋፈጠ ስለሆነ፣ ነዋሪዎች ባሉበት እንዲቆዩና ማንኛውንም ጥንቃቄ እንዲወስዱ ተብሏል።
4 307
🇮🇷❌ 🇺🇸 🇯🇴 - ከደቂቃዎች በፊት፣ በዮርዳኖስ የሚገኘው ሙወፈቅ ሶልቲ አየር ሐይል ጣቢያ በአራት የኢራን ሚሳዬሎች ጥቃት ደርሶበታል።.
4 307
🇮🇷⚡️🇺🇸 ሦስተኛ ዙር የአሜሪካ ጥቃት እየተካሄደ ይገኛል።
በርካታ የኢራን ግዛቶች በድብደባ ሥር ናቸው። ደቡብ፣ ደቡብ ምዕራብ፣ ምዕራብ እና ሰሜኑ በከፊል፣ መጠነ ሰፊ ጥቃት ውስጥ ናቸው።
4 307
🇮🇷⚡️🇺🇸 አሜሪካ ወደ መሃል የኢራን ክፍል ድብደባውን ለማስፋት ያቀደች ይመስላል። አሁን ላይ በኢራን ግዛት ዳርቻዎች እና ድንበሮች ላይ ያሉ ራዳሮች እና አየር መቃወሚያዎች ላይ ትኩረቷን አድርጋ በመደብደብ ላይ ናት።
4 307
🇮🇷⚡️🇺🇸ጃስክ፣ ካሽም፣ ባንደር አባስ ኢራን በጥቃቱ እየተመቱ ያሉ የኢራን ደቡባዊ ክፍሎች ናቸው። እንደሚሳው ከሆነ (መረጋገጥ ይኖርበታል)፣ የካሸም ጥቃት የተፈጸመው በባሕሬን ጀት ነው።
4 307
🇸🇦⚡️ሳዑዲ ዓረቢያ ካሁን በኋላ ተመታው ብላ ብታለቅስ፣ ሰው ይስቅባታል።
የአሜሪካ የጦር አይሮፕላኖች በሳዑዲ ነዳጅ እየቀዱ ሲነሱ ታይተዋል።
ሳዑዲ፣ ለአሜሪካ ነዳጅ ማደያ ናት።
