የቀጠናው ተመልካች
Відкрити в Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
4 301
Підписники
Немає даних24 години
-137 днів
-8030 днів
Архів дописів
4 302
⚡️🇮🇷🇮🇶🇵🇰 ሮይተርስ፡ ኢራቅ እና ፓኪስታን ከኢራን ጋር የነዳጅ ዘይት እና የተፈጥሮ ጋዝ በባሕረ ሰላጤው በኩል ለመጫን ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ይህም፣ ቴህራን በሆርሙዝ ባሕር በኩል ባለው የኃይል ፍሰት ላይ፣ ሚናዋ እና ጡንቻዋ እየፈረጠመ መምጣቱን አጉልቶ ያሳያል።
4 302
🇺🇸🏴⚔️🇮🇷 ትራምፕ "ጥሩ ስምምነት ካልሆነ በስተቀር ከኢራን ጋር ስምምነት አንፈጽምም" ብሏል።
"ኢራንን በተመለከተ የቻይና ፕሬዝዳንት እርዳታ ያስፈልገናል ብዬ አስባለሁ" ያለው ትራምፕ፣ "የኔቶ ህብረት አሳዝኖኛል እና ከእነሱ እርዳታ አያስፈልገንም" ሲል ተናግሯል።
ኢራንን በተመለከተ "አሁን ላይ ይሄ ነው የሚባል ዕርዳታ አያስፈልገንም፣ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ፣ በሰላማዊም ሆነ በሌላ መንገድ፣ እናሸንፋለን" ሲል አክሎዋል።
4 302
⭕️ CNN የሳተላይት ምስሎችን በመጥቀስ፣ ከኢራን ካርግ ደሴት ከ12 እስከ 20 ካሬ ኪሎ ሜትር ሥፋት ያለው እና ወደ ሳውዲ አረቢያ ውሃ እየተንሳፈፈ ያለ የፈሰሰ የነዳጅ ብክለት መኖሩን ዘግቧል።
4 302
🇸🇦⚡️🇮🇷 ትኩስ ዜና | ሮይተርስ ሳዑዲ ዓረቢያ በጦርነቱ ወቅት በኢራን ላይ በድብቅ ጥቃት ሰንዝራ እንደነበር በምርመራ ደርሼበታለሁ አለ።
የሮይተርስ ምርመራ እንዳመለከተው፣ ሳውዲ ዓረቢያ በመጋቢት ወር መጨረሻ ላይ፣ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ባደረጉት ጦርነት፣ በድብቅ የአየር ድብደባ እንደፈፀመች እና ይህም በኢራን ግዛት ላይ የመጀመሪያው የሳዑዲ ወታደራዊ ጥቃት እንደሆነ ዘግቧል።
የኢራንና የምዕራባዊያንን ምንጮች ጠቅሶ ሮይተርስ እንደዘገበው፣ ጥቃቶቹ ከፍተኛ እንደነበሩና፣ ያንን ተከትሎ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች እና የሳዑዲ ዛቻዎች ተፋፍመው እንደነበር ዘግቧል።
በመጨረሻም በሚያዝያ ወር፣ ጦርነቱ ቀጠናዊ እንዳይሆን በመስጋት፣ የአሜሪካ-ኢራን የተኩስ አቁም ከመታወጁ በፊት፣ በቴህራን እና በሪያድ መካከል መደበኛ ባልሆነ መንገድ ዲፕሎማሲያዊ መግባባት እንዲፈጠር ሆኗል።
ሮይተርስ እንደዘገበው ሪያድም ከቴህራን ጋር የለየለት ጦርነት ውስጥ ላለመግባት ስትል ዲፕሎማሲያዊ ቻናሎችን እንደዘረጋች ዘግቧል።
4 302
🇺🇸🇺🇦የፔንታጎን ኃላፊ ፒት ሄግሴት: በዩክሬን የሚገኘው የአሜሪካ ጦር በድሮን ውጊያ ልምድ እያገኘ መሆኑን ተናግረዋል።
"ብዙ ትላልቅ ባለስልጣናት እዚያ (በዩክሬን) ነበሩ እና ከፍተኛ መጠን ያለው መረጃ ደርሶናል።
እንዲያውም ከእነዚህ የድሮን ፍልሚያዎች፣ ከመከላከልም ሆነ ከማጥቃት ዘርፍ እንዲማሩ በግሌ፣ ተጨማሪ ሠራተኞችን ዩክሬን እንዲሄዱ አጽድቄያለሁ" ሲል ተናግሯል።
4 302
+9
— 🇮🇷 — : የኢራን IRGC አካል የሆነው፣ 'ሙሐመድ ረሱሉላህ' የተባለው አንዱ ክፍለ-ጦር፣ ዛሬ፣ የአሜሪካንን ወረራ በመከላከል ላይ ሲሰለጥን የሚያሳዩ ምስሎች ተለቀዋል።
4 302
+2
- 🇮🇷 /🇻🇦ትኩስ ዜና፡ የሮማው ፖፕ ሊዮ አሥራ አራተኛ፣ በቫቲካን ለኢራን አምባሳደር አያቶላ ሆሴን ሞክታሪ፣ የቫቲካንን ከፍተኛ የዲፕሎማሲያዊ ክብር ሜዳሊያን 'Order of Pius' አበርክተዋል።
ሜዳሊያው የተሸለመው ኢራን በክርስቲያኖች እና በሙስሊሞች መካከል ለሠላም እና ለእምነት ትብብር ላበረከተችው ልዩ አስተዋፅዖ ነው፣ ተብሏል።
4 302
- 🇮🇷 / 🇴🇲 ትኩስ ዜና፡ የኢራን እና የኦማን ባለስልጣናት ስለ ሆርሙዝ ባሕር የወደፊት ዕጣ ፈንታ ዛሬ የጋራ ስብሰባ አካሂደዋል።
የኦማን አቋም ካለፈው ጊዜ ጀምሮ የተቀየረ ይመስላል። ኦማን፣ በባሕሩ የሁለቱ ሀገሮች የጋራ ቁጥጥር መኖር፣ ሉዓላዊነትን ማስከበር እንደሆነ አምናለች።
ኢራንም ግንኙነቱ የመልካም ጎረቤት ግንኙነት እና የእስልምና ወዳጅነት አካል ነው ብላ የምታስብ በመሆኗ በሁለቱም ወገኖች መካከል የገቢ ክፍፍል እንደሚኖር ለኦማን ወገን ቃል ገብታለች።
4 302
🇮🇷🇮🇱- ኢራን ዩሬኒየም የማበልፀግ አቅሟ ወድሟል ብለው ነበር። ዛሬ ደግሞ በፍጥነት ልታበለፅግ አቅሙ አላት እና ፈጥነን እንምታት እያሉ ነው፣ እንደ አዲስ።
4 302
🇦🇪 አቡ ዳቢ እራሷን ለመጠበቅ በቢሊዮን የሚቆጠር ፔትሮዶላሮችን በመከላከያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ አቅዳለች።
አቡ ዳቢ በመከላከያ ላይ ያተኮረ የኢንቨስትመንት ፈንድ ለማቋቋም እያሰበች ነው ተብሏል። በ 2 ትሪሊዮን ዶላር ንብረት የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በሰው አልባ አውሮፕላኖች፣ በሳይበር ደህንነት እና በራስ ገዝ ሥርዓቶች ላይ ያተኮሩ የውጭ ኩባንያዎች ላይ ማነጣጠር ትፈልጋለች።
4 302
🇺🇸🇮🇷| US Secretary of War: - አስፈላጊ ከሆነ በኢራን ያለውን ሁኔታ ለማባባስ ዕቅድ አለን። ትራምፕ እየተወጣ ባለው ተልዕኮ አደጋ ምክንያት፣ በኢራን ላይ የሚቀጥለውን እርምጃ አንገልጽም።
4 302
+1
🇮🇱❗️እስራኤል የፍልስጤም እስረኞችን እንዲደፍሩ ውሾችን ታሰለጥናለች፣ ሲል የኒውዮርክ ታይምስ ዘጋቢ ጽፏል።
ውሾቹ በምርመራ ወቅት ተጠርተው፣ ራቁታቸውን ሆነው በኃይል እንዲጎነበሱ የተደረጉ እስረኞችን እንደሚደፍሩ፣ ጠባቂዎችና ወታደሮችም ይህን በቪዲዮና በፎቶ እንደሚያስቀሩ ተጠቂዎች ለጋዜጣው ተናግረዋል።
4 302
🇺🇸🇮🇷 - ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት በመቀጠሉ ብስጭቱ እንደጨመረና ካለፉት ሳምንታት በበለጠ በኢራን ላይ የሚደረገውን የውጊያ ዘመቻ ለመቀጠል እያሰበ እንደሚገኝ ተገልጿ።
ፕሬዚዳንቱ ወደ ቻይና ከመጓዙ በፊት በኢራን ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ይወስናል ተብሎ ባይጠበቀም፣ ከኢራን ጋር ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ በተመለከተ ትዕግስቱ በአብዛኛው እንዳለቀ ይገመታል - CNN |
4 302
🇺🇸🇮🇱🇮🇷 - ኢራን በሳተላይት ፕሮጄክቶች ላይ የሰራውን የ29 አመቱ የኢራን ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የኤሮስፔስ ምህንድስና ተመራቂ ተማሪ ኤርፋን ሻኩርዛዴህን በሞት ፍርድ ገድላለች።
የኢራን ባለስልጣናት ከአሜሪካ የስለላ ድርጅት CIA እና ከእስራኤል የስለላ ድርጅት MOSSAD ጋር በመስራት የሳተላይት መረጃን እና የሰራተኞች መረጃ ጨምሮ ሚስጥራዊ ቁሳቁሶችን አስተላልፏል እና በLinkedIn፣ WhatsApp እና Google ጥሪዎች ከተገናኘ በኋላ የክሪፕቶፕ ክፍያዎችን ተቀብሏል፣ ብለዋል።
4 302
- 🇮🇷 / 🇦🇪 ሰበር ዜና፡ ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በኢራን ላይ ጥቃት ስትፈጽም መቆየቷን በመረጃ ምንጮች ላይ በመመስረት አረጋግጧል።
በሚያዝያ ወር ከተደረጉት ጥቃቶች አንዱ በላቫን ደሴት የሚገኘውን የላቫን ነዳጅ ማጣሪያ ኩባንያ (LORC) ላይ ያነጣጠረ ነበር።
የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ጥቃቱን ፈጽማለች ተብሎ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ተጠርጥሮ የነበረ ቢሆንም እስካሁን አልተረጋገጠም። በወቅቱ ኢራን የኢሚሬትስ ማጣሪያ ፋብሪካ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በመፈጸም ምላሽ ሰጥታለች።
በዚህ መጠንና ልክ ኤሜሬት ኢራንን ያጠቃች እንደነበር መረጋገጡ ከኢራን ከፍተኛ የብቀላ ጥቃት እንዳያስነሳ ተፈርቷል።
4 302
🇮🇱🇮🇶🇮🇷 - የኢራቅ ጦር ኃይሎች- "ኃይሎቻችን በመጋቢት ወር በካርባላ በረሃ ውስጥ በአውሮፕላኖች ከሚደገፉ ማንነታቸው ያልታወቁ እና ያልተፈቀዱ ክፍሎች ጋር ተጋጭተዋል።
በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ግዛት ላይ ያልተፈቀዱ ሃይሎች ወይም ጦር ሰፈሮች አለመኖራቸውን እናረጋግጣለን።
