fa
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

رفتن به کانال در Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

نمایش بیشتر
کشور مشخص نشده استدسته بندی مشخص نشده است
4 294
مشترکین
اطلاعاتی وجود ندارد24 ساعت
-137 روز
-8030 روز
آرشیو پست ها
- 🇮🇷 /🇻🇦ትኩስ ዜና፡ የሮማው ፖፕ ሊዮ አሥራ አራተኛ፣ በቫቲካን ለኢራን አምባሳደር አያቶላ ሆሴን ሞክታሪ፣ የቫቲካንን ከፍተኛ የዲፕሎማሲያዊ ክብር ሜዳሊያን 'Order of Pius' አበርክ
+2
- 🇮🇷 /🇻🇦ትኩስ ዜና፡ የሮማው ፖፕ ሊዮ አሥራ አራተኛ፣ በቫቲካን ለኢራን አምባሳደር አያቶላ ሆሴን ሞክታሪ፣ የቫቲካንን ከፍተኛ የዲፕሎማሲያዊ ክብር ሜዳሊያን 'Order of Pius' አበርክተዋል። ሜዳሊያው የተሸለመው ኢራን በክርስቲያኖች እና በሙስሊሞች መካከል ለሠላም እና ለእምነት ትብብር ላበረከተችው ልዩ አስተዋፅዖ ነው፣ ተብሏል።

- 🇮🇷 / 🇴🇲 ትኩስ ዜና፡ የኢራን እና የኦማን ባለስልጣናት ስለ ሆርሙዝ ባሕር የወደፊት ዕጣ ፈንታ ዛሬ የጋራ ስብሰባ አካሂደዋል። የኦማን አቋም ካለፈው ጊዜ ጀምሮ የተቀየረ ይመስላል። ኦማን፣ በባሕሩ የሁለቱ ሀገሮች የጋራ ቁጥጥር መኖር፣ ሉዓላዊነትን ማስከበር እንደሆነ አምናለች። ኢራንም ግንኙነቱ የመልካም ጎረቤት ግንኙነት እና የእስልምና ወዳጅነት አካል ነው ብላ የምታስብ በመሆኗ በሁለቱም ወገኖች መካከል የገቢ ክፍፍል እንደሚኖር ለኦማን ወገን ቃል ገብታለች።

🇮🇷🇮🇱- ኢራን ዩሬኒየም የማበልፀግ አቅሟ ወድሟል ብለው ነበር። ዛሬ ደግሞ በፍጥነት ልታበለፅግ አቅሙ አላት እና ፈጥነን እንምታት እያሉ ነው፣ እንደ አዲስ።
🇮🇷🇮🇱- ኢራን ዩሬኒየም የማበልፀግ አቅሟ ወድሟል ብለው ነበር። ዛሬ ደግሞ በፍጥነት ልታበለፅግ አቅሙ አላት እና ፈጥነን እንምታት እያሉ ነው፣ እንደ አዲስ።

🇦🇪 አቡ ዳቢ እራሷን ለመጠበቅ በቢሊዮን የሚቆጠር ፔትሮዶላሮችን በመከላከያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ አቅዳለች። አቡ ዳቢ በመከላከያ ላይ ያተኮረ የኢንቨስትመንት ፈንድ ለማቋቋም እያሰበ
🇦🇪 አቡ ዳቢ እራሷን ለመጠበቅ በቢሊዮን የሚቆጠር ፔትሮዶላሮችን በመከላከያ ኢንዱስትሪ ውስጥ ኢንቨስት ለማድረግ አቅዳለች። አቡ ዳቢ በመከላከያ ላይ ያተኮረ የኢንቨስትመንት ፈንድ ለማቋቋም እያሰበች ነው ተብሏል። በ 2 ትሪሊዮን ዶላር ንብረት የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በሰው አልባ አውሮፕላኖች፣ በሳይበር ደህንነት እና በራስ ገዝ ሥርዓቶች ላይ ያተኮሩ የውጭ ኩባንያዎች ላይ ማነጣጠር ትፈልጋለች።

🇺🇸🇮🇷| US Secretary of War: - አስፈላጊ ከሆነ በኢራን ያለውን ሁኔታ ለማባባስ ዕቅድ አለን። ትራምፕ እየተወጣ ባለው ተልዕኮ አደጋ ምክንያት፣ በኢራን ላይ የሚቀጥለውን እርምጃ አንገልጽም።

🇮🇱❗️እስራኤል የፍልስጤም እስረኞችን እንዲደፍሩ ውሾችን ታሰለጥናለች፣ ሲል የኒውዮርክ ታይምስ ዘጋቢ ጽፏል። ውሾቹ በምርመራ ወቅት ተጠርተው፣ ራቁታቸውን ሆነው በኃይል እንዲጎነበሱ የተደረጉ እስረ
+1
🇮🇱❗️እስራኤል የፍልስጤም እስረኞችን እንዲደፍሩ ውሾችን ታሰለጥናለች፣ ሲል የኒውዮርክ ታይምስ ዘጋቢ ጽፏል። ውሾቹ በምርመራ ወቅት ተጠርተው፣ ራቁታቸውን ሆነው በኃይል እንዲጎነበሱ የተደረጉ እስረኞችን እንደሚደፍሩ፣ ጠባቂዎችና ወታደሮችም ይህን በቪዲዮና በፎቶ እንደሚያስቀሩ ተጠቂዎች ለጋዜጣው ተናግረዋል።

ትራምፕ አሜሪካ ይዋል ይደር እንጂ የኢራንን የበለፀገ የዩራኒየም ክምችት እንደምትይዝ ተናግሯል።
ትራምፕ አሜሪካ ይዋል ይደር እንጂ የኢራንን የበለፀገ የዩራኒየም ክምችት እንደምትይዝ ተናግሯል።

🇺🇸🇮🇷 - ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት በመቀጠሉ ብስጭቱ እንደጨመረና ካለፉት ሳምንታት በበለጠ በኢራን ላይ የሚደረገውን የውጊያ ዘመቻ ለመቀጠል እያሰበ እንደሚገኝ ተገልጿ። ፕሬዚዳንቱ ወደ ቻይና ከመጓዙ በፊት በኢራን ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ይወስናል ተብሎ ባይጠበቀም፣ ከኢራን ጋር ያለውን አጠቃላይ ሁኔታ በተመለከተ ትዕግስቱ በአብዛኛው እንዳለቀ ይገመታል - CNN |

🇺🇸🇮🇱🇮🇷 - ኢራን በሳተላይት ፕሮጄክቶች ላይ የሰራውን የ29 አመቱ የኢራን ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የኤሮስፔስ ምህንድስና ተመራቂ ተማሪ ኤርፋን ሻኩርዛዴህን በሞት ፍርድ ገድላለች።
🇺🇸🇮🇱🇮🇷 - ኢራን በሳተላይት ፕሮጄክቶች ላይ የሰራውን የ29 አመቱ የኢራን ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የኤሮስፔስ ምህንድስና ተመራቂ ተማሪ ኤርፋን ሻኩርዛዴህን በሞት ፍርድ ገድላለች። የኢራን ባለስልጣናት ከአሜሪካ የስለላ ድርጅት CIA እና ከእስራኤል የስለላ ድርጅት MOSSAD ጋር በመስራት የሳተላይት መረጃን እና የሰራተኞች መረጃ ጨምሮ ሚስጥራዊ ቁሳቁሶችን አስተላልፏል እና በLinkedIn፣ WhatsApp እና Google ጥሪዎች ከተገናኘ በኋላ የክሪፕቶፕ ክፍያዎችን ተቀብሏል፣ ብለዋል።

- 🇮🇷 / 🇦🇪 ሰበር ዜና፡ ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በኢራን ላይ ጥቃት ስትፈጽም መቆየቷን በመረጃ ምንጮች ላይ በመመስረት አረጋግጧል። በሚያዝያ ወር ከተደረጉት ጥቃቶ
- 🇮🇷 / 🇦🇪 ሰበር ዜና፡ ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በኢራን ላይ ጥቃት ስትፈጽም መቆየቷን በመረጃ ምንጮች ላይ በመመስረት አረጋግጧል። በሚያዝያ ወር ከተደረጉት ጥቃቶች አንዱ በላቫን ደሴት የሚገኘውን የላቫን ነዳጅ ማጣሪያ ኩባንያ (LORC) ላይ ያነጣጠረ ነበር። የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ጥቃቱን ፈጽማለች ተብሎ ከረዥም ጊዜ ጀምሮ ተጠርጥሮ የነበረ ቢሆንም እስካሁን አልተረጋገጠም። በወቅቱ ኢራን የኢሚሬትስ ማጣሪያ ፋብሪካ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በመፈጸም ምላሽ ሰጥታለች። በዚህ መጠንና ልክ ኤሜሬት ኢራንን ያጠቃች እንደነበር መረጋገጡ ከኢራን ከፍተኛ የብቀላ ጥቃት እንዳያስነሳ ተፈርቷል።

🇮🇱🇮🇶🇮🇷 - የኢራቅ ጦር ኃይሎች- "ኃይሎቻችን በመጋቢት ወር በካርባላ በረሃ ውስጥ በአውሮፕላኖች ከሚደገፉ ማንነታቸው ያልታወቁ እና ያልተፈቀዱ ክፍሎች ጋር ተጋጭተዋል። በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ግዛት ላይ ያልተፈቀዱ ሃይሎች ወይም ጦር ሰፈሮች አለመኖራቸውን እናረጋግጣለን።

🇱🇻 በላቲቪያ ፖሊሶች አንዲትን ሴት 'የቦርሳሽ ቀለም ውቅር የሩሲያን ባንዲራ ያሳያል' በሚል አቁመው ሲጠይቋት በተንቀሳቃሽ ምስሉ ይታያል፣ ምንም እንኳ የቦርሳው ቀለም የ Tommy Hilfiger ብራንድ ቀለም ቢሆንም። በላትቪያ፣ እንደ ዩክሬን ሁሉ፣ የሩሲያን ባንዲራ በምንም ሁኔታ መያዝ አይቻልም። በልብስ፣ በጥልፍ፣ በዕቃ … ቀለሙን ማሳየት በገንዘብ ያስቀጣል። ላትቪያ ከሩሲያ ጋር ጦርነት ላይ አይደለችም፣ ግን ባንዲራውን በምንም ሁኔታ ማሳየት ወንጀል ነው። ባለፈው ዓመት በላትቪያ በነበረ የEuro Basktball ግጥሚያ፣ ፖሊስ ተመልካቾች ይዘውት የነበረን የሰርቢያ ባንዲራ፣ ቀለሙ ከሩሲያ ጋር ስለሚመሳሰል ብቻ መቀማታቸው ይታወሳል። ነገሩ፣ የባለፉትን የኢትዮጵያ ባንዲራ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ይዞ መገኘትን ይመስላል። Total Paranoia! 

⚡️🇮🇷🇺🇸 የኢራን ፓርላማ አፈጉባኤ የኢራን ጦር ኃይሎች ለማንኛውም ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን በመግለጽ የተሳሳቱ ስልቶች እና ውሳኔዎች ሁል ጊዜ ወደ ተሳሳተ ውጤት እንደሚመያሩ እ
⚡️🇮🇷🇺🇸 የኢራን ፓርላማ አፈጉባኤ የኢራን ጦር ኃይሎች ለማንኛውም ጥቃት ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን በመግለጽ የተሳሳቱ ስልቶች እና ውሳኔዎች ሁል ጊዜ ወደ ተሳሳተ ውጤት እንደሚመያሩ እና "መላው ዓለም ይህንን ተረድቷል" ሲሉ አስጠንቅቀዋል። አክለውም፣ "ለሁሉም አማራጮች ተዘጋጅተናል፣ እናስደነግጣቸዋለን" ብለዋል።

- 🇺🇸 /🇮🇱/ 🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ ድርድሩ መደናቀፉን ተከትሎ፣ በኢራን ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንደገና ለመጀመር እያሰበ ሲሆን፣ ዛሬ ከጄኔራሎቹ ጋር ይገናኛል። የሚቀርቡት አማራጮች በሆ
- 🇺🇸 /🇮🇱/ 🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ ድርድሩ መደናቀፉን ተከትሎ፣ በኢራን ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንደገና ለመጀመር እያሰበ ሲሆን፣ ዛሬ ከጄኔራሎቹ ጋር ይገናኛል። የሚቀርቡት አማራጮች በሆርሙዝ ወሽመጥ መርከቦችን አጅቦ የመሄዱን 'ፕሮጀክት ነፃነት' እንደገና ማስጀመርን ያካትታል ተብሏል። ሌላው አማራጭ፣ በኢራን ውስጥ እስካሁን ያልተመታ 25% ተለይተው የሚታወቁ ኢላማዎች ላይ ጥቃቱን እንደገና ማስጀመር ነው። በተጨማሪም፣ እስራኤል የኢራንን የበለፀገ ዩራኒየም በልዩ ኦፕራሽን ከኢራን ማውጣቱን በተመለከተ ትራምፕ እንዲፈቅድ ጫና እያደረገች ቢሆንም፣ ፕሬዚዳንቱ ኦፕሬሽኑ ሊያስከትል በሚችለው ከፍተኛ አደጋ ምክንያት እያመነታ ይገኛል።  

- 🇺🇸 / 🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ 'የኢራን መሪዎች ክብር የጎደላቸው ሰዎች ናቸው። ለማዘጋጀት 10 ደቂቃ ሊወስድ የሚገባውን የወረቀት ምላሻቸውን፣ 4 ቀን ፈጅቶባቸው ነው የላኩት። በዚያ ላይ ቆሻሻ ነበር።'

- 🇺🇸 / 🇮🇷 ኢራን ኳታርን፣ ባህሬንን፣ ኩዌትን ሳዑዲ አረቢያን አጠቃች - በሁሉም ቦታ ጥቃት ሰንዝረዋል። ማንም ሰው እነዚህን ሀገሮች ያጠቋቸዋል ብሎ አልጠበቀም፣ ያንን ማድረግ አልነበረባቸውም። ነገር ግን አደረጉት፣ ሚሳዬሎቻቸውን አባከኑ። ብክነት ነበር። እነዚያን ሁሉ ሚሳኤሎችና ማስወንጨፊያዎቻቸውን በሚያማምሩ ፔትሪዮት ሚሳዬሎቻችን አንኮታኮትንባቸው።

- 🇺🇸 / 🇮🇷 ፕሬዝዳንት ትራምፕ 'የኢራን መሪዎች አብደዋል፣ አብደዋል - ሁል ጊዜ ከእነሱ ጋር እገናኛለሁ፣ እብዶች ናቸው'

⚡️🇱🇧 የደቡብ ሊባኖሷ ቢንት ጅቤይል ከተማ ሙሉ በሙሉ በIDF ቁጥጥር ሥር ወድቃለች። ከተማዋ በሙሉ አሁን 'ባዶ' ተብሎ ተቆጥሯል፣ ከህንጻዋ ወይም ከሲቪሎች ምንም የቀረ ነገር የለም። በከተማው ወሰን ውስጥ ያለው የትጥቅ ተቃውሞ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም ተብሎ ይታሰባል፣ ከሰሜናዊ አቅጣጫ ከሂዝቦላህ ወደ IDF ከሚደረጉ ጥቃቶች በስተቀር።

🇷🇺🇸🇦 - ሩሲያ እና ሳዑዲ አረቢያ፣ አንዱ በሌላኛው ሀገር ፣ያለ ቪዛ በነፃ መግባትን አስጀመሩ።

🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር ዜና፡ የአሜሪካ አየር ሐይል F- 35A Lightning II Stealth ጀት ዛሬ፣ በዚህች ሰዓት፣ በሆርሙዝ ባሕር አቅራቢያ በኦማን ባሕረ ሰላጤ ላይ የአደጋ ጊዜ ኮድ እያጮኸ
🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር ዜና፡ የአሜሪካ አየር ሐይል F- 35A Lightning II Stealth ጀት ዛሬ፣ በዚህች ሰዓት፣ በሆርሙዝ ባሕር አቅራቢያ በኦማን ባሕረ ሰላጤ ላይ የአደጋ ጊዜ ኮድ እያጮኸ እንደነበር፣ ከዚያም በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የአየር ክልል ላይ መጥፋቱ ታውቋል። አውሮፕላኑ (13-5067 የተመዘገበ) ከኦማን ባሕረ ሰላጤ ከተሻገረ በኋላ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ላይ ሲበር የዓለም አቀፍ የአደጋ ጊዜ ጭንቀት ምልክትን አስተላልፏል። ከዚያም የጀት ትራንስፖንደሩ ጠፍቷል። የኢራን የመንግስት ሚዲያዎች F-35 በኢራን ጦር ተመቷል ይላሉ። ይህ፣ በተናጥል አልተረጋገጠም። አሜሪካ እስከ አሁን ድረስ ምንም አይነት መግለጫ አልሰጠችም።