uk
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Відкрити в Telegram

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Показати більше
Країна не вказанаКатегорія не вказана
4 303
Підписники
+824 години
-47 днів
-7130 днів
Архів дописів
🇸🇩🇦🇪🇪🇹⚡️ - የሱዳን መንግስት የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና ኢትዮጵያ ዛሬ በካርቱም አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በደረሰው የድሮን ጥቃት ተሳትፈዋል ሲል ከሷል። የሱዳን ባለስልጣናት ለጥቃቱ በወሰኑት ጊዜና ቦታ ምላሽ የመስጠት መብት እንዳላቸው ተናግረዋል።

🇸🇦🇦🇪❌🇮🇷 - የሳውዲ ልዑል መሀመድ ቢን ሳልማን ከተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት መሀመድ ቢን ዛይድ ጋር በስልክ ተነጋግረዋል። ሳዑዲ አረቢያ በኢራን ጥቃት ላይ "ጠንካራ ውግዘት" እ
🇸🇦🇦🇪❌🇮🇷 - የሳውዲ ልዑል መሀመድ ቢን ሳልማን ከተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ፕሬዝዳንት መሀመድ ቢን ዛይድ ጋር በስልክ ተነጋግረዋል። ሳዑዲ አረቢያ በኢራን ጥቃት ላይ "ጠንካራ ውግዘት" እንዳደረገች ተገልጿል። ➡️ ሪያድ ጥቃቱን ተገቢ ያልሆነ ነው በማለት ያወገዘች ሲሆን፣ ለተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ "ደህንነቷን እና መረጋጋቷን ለመጠበቅ" የምታደርገውን ድጋፍ በድጋሚ አረጋግጣለች።

🇺🇸 ከ 27 በላይ የአሜሪካ አየር ኃይል (USAF) አይሮፕላኖች በዚህ ምሽት በቀጠናው እየበረሩ ይታያሉ። እንደ FOX NEWS ዘገባ፣ አሜሪካ ወደ ውጊያ የመመለስ እድሏ ባለፉት 24 ሰዓታት በከፍ
🇺🇸 ከ 27 በላይ የአሜሪካ አየር ኃይል (USAF) አይሮፕላኖች በዚህ ምሽት በቀጠናው እየበረሩ ይታያሉ። እንደ FOX NEWS ዘገባ፣ አሜሪካ ወደ ውጊያ የመመለስ እድሏ ባለፉት 24 ሰዓታት በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።

🇺🇸🇮🇱❌🇮🇷 - አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ላይ ላደረሰችው ጥቃት ምላሽ፣ የኢራን ሚሳኤል ማስወንጨፊያዎችን እና የኢነርጂ ተቋማትን ለመምታት እያሰቡ ነው ሲሉ ምን
🇺🇸🇮🇱❌🇮🇷 - አሜሪካ እና እስራኤል ኢራን በተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ላይ ላደረሰችው ጥቃት ምላሽ፣ የኢራን ሚሳኤል ማስወንጨፊያዎችን እና የኢነርጂ ተቋማትን ለመምታት እያሰቡ ነው ሲሉ ምንጮች ለእስራኤል ሃዮም ተናግረዋል።

🇮🇷🇦🇪 ከኢራን ጥቃት በኋላ የፉጃይራን ቃጠሎ የሚያሳይ የምሽት አዲስ ምስል። ኢራን የሆርሙዝ ባሕርን ስትዘጋ፣ ዓለም የነዳጅ ማስተላለፊያውን የቀየረበት ተርሚናል ይህ ነበር። ሆርሙዝ መተላለፊያ ከተዘጋ በኋላ እና ከዚያ የዓለም ክፍል፣ በዚህ በኩል ነበር ወደ ሌላው ሀገር ነዳጅ የሚጫነው። ተለዋጭ መንገድ ነበር። የማለፊያ መስመር፣ የመጠባበቂያ እቅድ። ኢራን ያጠቃችው ይህን ነው።

🇮🇷⚡️🇦🇪🇮🇱 በ UAE የእስራኤል አየር መቃወሚያ በዛሬው ዕለት ጥቅም ላይ ውሏል CNN
🇮🇷⚡️🇦🇪🇮🇱 በ UAE የእስራኤል አየር መቃወሚያ በዛሬው ዕለት ጥቅም ላይ ውሏል CNN

🇮🇷⚡️🇦🇪🇮🇱🇺🇸 "ኢራን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያበቃልሻል፣ ትረሻለሽ ከዚያ በኋላ!" የ UAE ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪዎችና ግለሰቦች ኢራንን "እንጨርስሻለን" ማስፈራሪያቸው እንደቀጠለ ነ
+1
🇮🇷⚡️🇦🇪🇮🇱🇺🇸 "ኢራን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ያበቃልሻል፣ ትረሻለሽ ከዚያ በኋላ!" የ UAE ከፍተኛ ተጽእኖ ፈጣሪዎችና ግለሰቦች ኢራንን "እንጨርስሻለን" ማስፈራሪያቸው እንደቀጠለ ነው። ዛቻቸው፣ ዘለፋቸው በስፋት አለ። "ሙሉ በሙሉ እናጠፋሻለን" ነው የሚሉት ኢራንን።

🇮🇷 እንዳለፉት ሁለት ወራት፣ የኢራን አየር ክልል ዛሬም ነፃ ነው።
🇮🇷 እንዳለፉት ሁለት ወራት፣ የኢራን አየር ክልል ዛሬም ነፃ ነው።

🇮🇷🇦🇪🇮🇱 የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ የመከላከያ ኮሚቴ ለእስራኤል አቻዎቻቸው አቡ ዳቢ ለኢራን ጥቃቶች ምላሽ እንደምትሰጥ እና "ዝም እንደማይሉ" ተናግሯል።

🇧🇭⚡️ባሕሬን ሀገር አቀፍ የአደጋ ጊዜ አዋጅ አወጀች።

🇦🇪🇺🇸🇮🇱🇮🇷⚡️በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች ውስጥ አንድ ኦፊሴላዊ ምንጭ ለ CNN እንደተናገሩት፣
ኤሚሬትስ በሚቀጥሉት 24 ሰዓታት ውስጥ አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ ጥቃት ሊያደርሱ እንደሚችሉ ትገምታለች።

🇦🇪 የኤሜሬት ተጽእኖ ፈጣሪዎች ኢራን ላይ እየዛቱ ናቸው፡ "ዛሬ ማታ አንቺን አያርገን" ለዚህ ሥራሽ "ትጸጸቺያለሽ" እያሉ ናቸው።
+1
🇦🇪 የኤሜሬት ተጽእኖ ፈጣሪዎች ኢራን ላይ እየዛቱ ናቸው፡ "ዛሬ ማታ አንቺን አያርገን" ለዚህ ሥራሽ "ትጸጸቺያለሽ" እያሉ ናቸው።

❗️🇮🇷 🇦🇪በዚህ አጋጣሚ፣ የኢራንን ስትራቴጂካዊ ብልጠት አለማድነቅ ንፉግነት ይሆናል። በድርድር ስም አሜሪካ እና እስራኤልን ከሜዳው ውጭ ካደረገቻቸው በኋላ፣ የምትፈልጋቸውን One on One በግላጭ አገኘቻቸው። ከ 50 ሀገሮች ጋር በአንዴ ከመዋጋት ይልቅ በስትራቴጂ አላያንሳቸውን በታትነህ፣ አንድ በአንድ ለብቻቸው ታጫውታቸዋለህ። በእርግጥ በሚቀጥሉት ሰዓታት ነገሮች ይለዋወጡ፣ እነ አሜሪካም ሊገቡበት ይችላሉ።

🇮🇷⚡️IRGC ጄኔራል ለኤሜሬት፡ ከእሳት ጋር አትጫወቱ ብለን አስጠንቅቀናል!

ኢራን ትናንት ያስጠነቀቀችውን ዛሬ ተግባራዊ ማድረግ ጀምራለች!

🇮🇷🇦🇪⚡በUAE ወደብ ሁለት መርከቦች በኢራን ተመትተው እየነደዱ ናቸው።
🇮🇷🇦🇪⚡በUAE ወደብ ሁለት መርከቦች በኢራን ተመትተው እየነደዱ ናቸው።

🇦🇪 🇮🇷 በዱባይ የፋጁራ ወደብና የነዳጅ መሠረተ ልማቶች በክሩዝ ሚሳዬልና በድሮኖች ተመትተዋል። በቦታዎቹ እሳት እየነደደ ነው። ኢራን አዲስ ያለችውን የሆርሙዝ አስተዳደራዊ መዋቀርና አሠራር በኤሜሬት ወደቦች ላይ ተግባራዊ እያደረገች ነው።

🇮🇷❗️🇦🇪 በኤሜሬት የፋጁራ ነዳጅ ኢንዱስትሪ በእሳት ተያይዟል፣ የፋጁራ ማውጫና ማጣሪያ እየነደደ ነው። UAE በድሮኖችና በሚሳዬሎች ተመታሁ ብላለች።
🇮🇷❗️🇦🇪 በኤሜሬት የፋጁራ ነዳጅ ኢንዱስትሪ በእሳት ተያይዟል፣ የፋጁራ ማውጫና ማጣሪያ እየነደደ ነው። UAE በድሮኖችና በሚሳዬሎች ተመታሁ ብላለች።

ትናንት ኢራን የ UAE የጦር ጀቶች በጦርነቱ ወቅት ኢራንን በመደብደብ በቀጥታ እንደተሳተፉ የሚያሳይ መረጃ በእጄ ገብቷል፣ በመጪው ቀናት አፀፋውን እመልሳለሁ ብላ ነበር።

🇦🇪 🇮🇷 ሰበር፡ ኢራን ሚሳዬሎች ወደ UAE ተኩሳለች። በኤሜሬት ፋጁራ ወደብ እሳት ተነስቷል። ከሰዓታት በፊት ኤሜሬት ምንም አደጋ የለም ብላ ነበር።