የቀጠናው ተመልካች
Відкрити в Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
4 303
Підписники
+824 години
-47 днів
-7130 днів
Архів дописів
4 304
🇺🇸 ፕሬዚዳንት ትራምፕ፣ ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ጎን ለጎን ከሳዑዲ ዓረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ፣ ኳታር፣ ባሕሬን፣ ኩዌት እና ኦማን መሪዎች ጋር በማክሰኞ እንደሚገናኙ AXIOS ዘግቧል።
ትራምፕ፣ "የት እንዳሉና እንዴት እንደሆኑ ማወቅ እፈልጋለሁ። ደህና ናቸው ወይ? እኛ ለእነሱ ከፍተኛ ጥበቃ እያደረግን ነው" ብሏል።
ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ወይም በኋላ፣ በጦርነቱ ዙሪያ ውሳኔ ይወስን እንደሆን ለተጠየቀው፣ ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆነም።
አንዳንድ የአሜሪካ ባለሥልጣናት፣ የአሁኑን "ጦርነትም፣ ሰላምም ያልሆነውን" ሁኔታ አደገኛና አሜሪካን የሚጎዳ ፖሊሲ አድርገው ይመለከቱታል፣ እናም ስምምነት ካልተደረሰ መጠነ ሠፊ ሌላ ዙር ጦርነት እንደገና ሊጀመር ይችላሉ ብለው ይፈራሉ ።
4 304
አጀብ! ስንት ሀገር ለእርዳታ ተለመነ! የስንቱ ደጅ በልመና ተጠና … በጎረቤት ሀገር ያሉን ሽምቀኞች ለመዋጋት… ኧረ ተወኝ!
ይታያችሁ እስቲ፣ ሳዑዲ እድሜ ዘመኗን የኖረችው የአሜሪካን መሳሪያ ስትገዛ ነው። (ትናንት ትናንት፣ በዕለተ- እሮብ፣ $24 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጣ መሳሪያ ከአሜሪካ አዝዛለች፣ አሜሪካኖች ግዢውን ገና አላጠደቁትም እንጂ።) ስታግበሰብስ እና ስትሰበስብ፣ ስታከማች እና ስትከዝን ነው የኖረችው።
ከማንም ሀገር በላይ፣ 'ያድኑኛል' ያለቻቸውን መሳሪያዎች ከሮማዊያን (ከፈረንጆች) ላይ በመግዛት፣ ሳዑዲ ዓረቢያን የሚደርስባትም ሆነ የሚወዳደራት ሌላ ሀገር በዓለም የለም። ታዲያሳ… የት ነው ያ ሁሉ ብረት አሁን ላይ? ምን ውጦት ነው ያ ሁሉ የሰበሰበችው የሮማዊያን ቴክኖሎጂ? ራሷን እንዲህ መጠበቅ እስኪያቅጣት ተአማጢያኖች?
ከመጀመሪያው እኮ የቀጠናው ተመልካቾች ተይይ…አይሆንም ብለናታል። ተማጥነናታል በተቻለን … ይቅርብሽ ብለን ተናግረናል! አሁን ምን ይደረጋል? አንዴ ገብተውበታል፣ የሚወጡበትን መንገድ ቁጭ ብለን እናያለን!
እንደ እኔ፣ ሳዑዲ የመንን ሙሉ በሙሉ እርግፍ አድርጋ መተው አለባት። ከየመን ሙሉ በሙሉ መውጣት አለባት። ከዚያ ነገሮች ይስተካከላሉ፣ ባሕሩም ይከፈትላታል።
ሳዑዲ የመን ውስጥ ምንድነው የምትሠራው? በዚያ ያለችው ለምን ዓላማ ነው? በየመን፣ በሰው ሀገር፣ የሙጥኝ ማለት፣ ምን ፈልጋ ነው? ምን ድነው ጎሏ? የሷ በየመን መገኘት እኮ ምንም ጥቅም የለውም፣ አንገብጋቢ የሆነ የሚያገባት ጉዳይም የለም። አላስፈላጊ እኮ ነው።
ነው ወይስ ሳዑዲ በቅጥረኝነት የጽዮናዊያንን ጦርነት ነው በዚያ እየተዋጋች ያለችው?
ታለበለዚያ ግን፣ አልወጣም ብላ በየመን የውስጥ ጉዳይ መፈትፈቷን የምትቀጥል ከሆነ፣ ሳዑዲን የሚሰባብሩት የመኖች ይሆናሉ።
አዎ! ሳዑዲን የሚሰባብሩት የአቢሲኒያዊያን (የሰሜኖች) ደም ያላቸው የኛው ዘመዶች ይሆናሉ።
4 304
🇸🇦/🇮🇷/🇾🇪/🇨🇳 ሳዑዲ ዓረቢያ ከቻይና እርዳታ መጠየቋ ተሰማ።
የባብ አል መንደብ ወሽመጥ እና የቀይ ባሕር ዳርቻዎች በሁቲዎች ቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ተከትሎ፣ ሳዑዲ ዓረቢያ፣ ቻይና ሁቲዎችን በመቆጣጠር ላይ ኢራንን እንድትለምንላት ተማጽናለች፣ ሦስት የኢራን እና የቻይና ምንጮች እንደተናገሩት።
ቻይና መልእክቱን ለኢራን አስተላልፋለች፣ ነገር ግን ምንም አይነት ማስፈራሪያ አልሰጠችም ወይም ደግሞ በቴህራን ላይ የኢኮኖሚ ኃይሏን ተጠቅማ ጫና ስለማሳደር አላነሳችም፣ ብለዋል።
ኢራን በበኩሏ፣ በጉዳዩ ምንም አይነት ዋስትና ከመስጠቷ በፊት፣ አሜሪካ እና እስራኤል የጁመሩትን ሕገ-ወጥ ጦርነት ሊያቆሙ ይገባል ብላለች።
"የቀጠናው መረጋጋት የተመሠረተው የአሜሪካ እና የእስራኤል ጦርነት በማስቆም ላይ ነው በማለት ምላሽ ሰጥታለች። - ሮይተርስ
4 304
🇸🇦⚡️🇾🇪 ሰበር ዜና፡ ሳውዲ ዓረቢያ ከሁቲ ጋር ለመደራደር ፍላጎቷ እንደሆነ ገለጸች። ኦማንን ሽማግሌ አድርጋ ልካለች።
በኦማን በኩል ከአንሷረላህ (ሁቲዎች) ጋር ለሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ጠይቃለች።
ኦማን፣ ሳዑዲ ዓረቢያ ጥያቄውን ያቀረበችው ትናንት ምሽት መሆኑን ተናግራለች።
4 304
AXIOS:
🇺🇸🇸🇦🇦🇪🇶🇦 🇵🇸🇴🇲🇯🇴 ትራምፕ ከጦርነቱ በኋላ ከኢራን ጋር ስለሚኖረው ግንኙነት ስትራቴጂ ሀሳቦችን ለባሕረ ሰላጤው ሀገራት ያብራራሉ።
*-*-*-
ቁጭ ብለህ ተማር ከፕሮፌሰር ትራምፕ። ሳዑዲ፣ ክላስ እንዳትቀሪ።
4 304
🇺🇸🇮🇱⚡️ጄዲ ቫንስ፡
የመካከለኛው ምሥራቅ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲያችን ለእስራኤል መንግሥት አጎብዳጅ እንዲሆን ልንፈቅድ አንችልም … ከኔቶም ጋር እንዲሁ፣ ለማንም ብለን አናጎበድድም።
ከሰዎች ጋር ስንሠራ አብረን እንሠራለን። ባልተስማማንበት ጊዜ ደግሞ፣ አንስማማም!
4 304
🇸🇦⚡️ሳዑዲ ዓረቢያ ከየመን ሁቲዎች (አንሷሩላህ) ጋር ያለው ግጭት እየቀጠለ በመምጣቱ፣ የአየር መቃወሚያ ሚሳዬሎቿ እንደተሟጠጡባት ገልፃ፣ ተጨማሪ የአየር መከላከያ ድጋፍ ከቀጠናው እና ከምዕራባውያን አጋሮች እንድትፈልግ አስገድዷታል፣ ሲል AP ዘግቧል።
ሳዑዲ ዓረቢያ ፈረንሳይን፣ ብሪታንያን፣ ፓኪስታንና ግብጽን፣ መንግሥቷን ለመጠበቅ የአየር መከላከያ ድጋፍ እንዲያደርጉላት ጠይቃለች።
እስካሁን ሊረዳት የፈቀደ አልተገኘም።
የሳዑዲ ዓረቢያ ዋነኛ ወታደራዊ አቅራቢ የሆነችው አሜሪካም፣ ከኢራን ጋር ለስድስት ወራት በነበረው ጦርነት ምክንያት፣ የኢንተርሴፕተር ሚሳዬሎች ክምችቷ እንዳሽቆለቆለና ለመስጠት የምትችልበት ዕድል እንደሌለ ታውቋል፣ እንደ ሕትመቱ ዘገባ።
4 304
🇺🇦⚡️🇷🇺 ኪይቭ፣ በአሁኑ ሰዓት በከባድ የሩሲያ ሚሳዬል ጥቃት ሥር ናት።
ተመትቶ የወደቀ ሚሳዬል እስካሁን የለም፣ በ10 ደቂቃ ከ15 በላይ ከፍተኛ ፍንዳታዎች በከተማው ተሰምተዋል፣ እንደ ምንጮች መረጃ።
4 304
🇸🇦⚡️🇾🇪🇮🇶 ይህንን ምስል በኢራቅ መገናኛ ብዙሀን ማምሻውን አገኘሁት እና የሪያድ መንግስት ተቃዋሚዎችን ቅዱስ ካዕባን ለማጥፋት አሲረዋል ብሎ መክሰስ የሳውዲ ንጉሣዊ ቤተሰብ የረዥም ጊዜ ባህል እንደሆነ ተረዳሁ።
ምስሉ፣ ሳዳምን ከአብርሃ ጋር ያመሳስለዋል እና እ.ኤ.አ. በ1991፣ በDesert Storm ዘመቻ ወቅት፣ ኢራቅ በሳውዲ አረቢያ ላይ ያደረሰችውን ጥቃት፣ ካዕባን ለማጥፋት ያደረገው ሙከራ አድርጎ ይተረጉመዋል።
ዛሬም፣ ሳዑዲ የመኖችን ካዕባን ሊያጠፉ እየሞከሩ ነው በማለት መክሰስ ይዛለች።
የሐሰት ፕሮፓጋንዳ፣ የሐሰት ክስ!
የእስላሙ ዓለም፣ እንደ ሳዑዲ ገዢዎች የሚጠየፈው አገዛዝ ሌላ የለም፣ ሥራቸው አፍራሽ ሆኖ ኖሯልና! ስለዚህም፣ ሕዝበ ሙስሊሙን 'ካዕባን ሊያፈርሱት ነው' በሚል ስሜታዊ አድርጎ ከኋላ ማግተልተል፣ የሚቻል አይሆንም!
በካዕባ ጀርባ መደበቅ አይቻልም!
ሳዑዲን ላለፉት 80+ ዓመታት ሲገዛ የኖረው ቤተሰብ፣ ከጅምሩም አገሬ አይደለም። በእንግሊዝ ወደ ስልጣን እንዲወጡ የተደረጉ መጤ ማሕበረሰቦች መሆናቸው የሚታወቅ ነው። ሆኖ ሳለ፣ 'ውጫዊ ሕዝብ ቤተ-መቅደሳችንን ሊያፈርስ ነው' የሚል ትርክት አይሰራም።
4 304
🇺🇦🇪🇺 ዩክሬን ከአውሮፓ ሕብረት ደህንነት ጥበቃ ፈንድ፣ እስከ $30 ቢሊየን ዩሮ ልታገኝ መሆኑ ተነገረ።
ኡርሱላ ቫን ደር ሌየን፣ የአውሮፓ አገራት ለሕብረቱ የጦር መሳሪያ ማዘመን ፕሮግራም ከመደቡትን (150 ቢሊዮን ዩሮ) ውስጥ፣ የገንዘቡን የተወሰነ ክፍል አልተጠቀሙበትም። ስለዚህ ይህን ገንዘብ፣ ለዩክሬን ወታደራዊ ድጋፍ እና የአገር ውስጥ ወታደራዊ-ኢንዱስትሪ ልማት ላይ እንድታውለው ይሰጣታል፣ ብላለች ።
4 304
🇺🇦⚡️🇷🇺 ዘለንስኪ፡
ሩሲያውያን ይሸነፋሉ ብለን እናስባለን። በዚህ ዓመት 300,000 ወታደሮቻቸው ይገደላሉ ብዬ አስባለው❗️ ሁሉንም የሩስያ ወታደራዊ ተቋማትን በተቻለ መጠን እናወድማቸዋለን።
4 304
🇮🇱⚡️ — የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ፡ የ IDF ወታደሮችን ስም የሚያጠፉትን እና የጦር ሰራዊቶቻችንን ሞራል የሚያጎድፉትን ከእንግዲህ አንታገስም! ዜግነታቸውን እንቀማቸዋለን፣ በገንዘብም እንቀጣቸዋለን። ይህን የምናደርግበት ጊዜ ነው።
*-*-*-
ነገ እኛ ሀገር መከላከያን አዳሜ ትናገሪና ወይም በተንሸዋረረ ዓይን አያለው ትይና፣ ዋ! ነጣነትሽን እና ኢትዮጵያዊነትሽን ትነጠቂያለሽ።
ዲሞክራሲ የሚባል ነገር ወይም የሚፈልጉትን ሓሳብ የማንጠባረቅ ነጣነት እስራኤል ውስጥ አልሰራም።
4 304
🇮🇱⚡️ — የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ፡ የ IDF ወታደሮችን ስም የሚያጠፉትን እና የጦር ሰራዊቶቻችንን ሞራል የሚያጎድፉትን ከእንግዲህ አንታገስም! ዜግነታቸውን እንቀማቸዋለን፣ በገንዘብም እንቀጣቸዋለን። ይህን የምናደርግበት ጊዜ ነው።
*-*-*-
ነገ እኛ ሀገር መከላከያን አዳሜ ትናገሪና ወይም በተንሸዋረረ ዓይን አያለው ትይና፣ ዋ! ነጣነትሽን እና ኢትዮጵያዊነትሽን ትነጠቂያለሽ።
ዲሞክራሲ የሚባል ነገር ወይም የሚፈልጉትን ሓሳብ የማንጠባረቅ ነጣነት እስራኤል ውስጥ አልሰራም።
4 304
+2
🇸🇦⚡️🇾🇪 የማይታመን፣ እጅግ አሳፋሪ፣ አደናባሪም ጉዳይ! ሳዑዲ ዓረቢያን የሚያህል ሀገር፣ በዚህ መጠን አቅም አጥታ፣ በሽርጣሞች ተገልባ ስትገረፍ፣ ይሄ ታሪክ ነው!
4 304
🇸🇦⚡️🇾🇪 የሳዑዲ ጀት በየመን ተመትቶ እንደወደቀ ሲወራ የነበረው ከሰዓታት በፊት ጀምሮ ነበር። ነገር ግን፣ የሳዑዲ መንግሥታዊ ምንጮች እና በአሜሪካ የሚገኙ ወታደራዊ ተንታኞች፣ F15 ተመትቶ መውደቁን "የሁቲዎች ቅዠት" በማለት አጣጥለውት ነበር።
አሁን ሁቲዎች በለቀቁት የማረጋገጫ ምስልና ተንቀሳቃሽ ቪዲዮ፣ ሁሉም የሳዑዲ መንግሥታዊ ምንጮች ደንግጠው ጭጭ ይገኛሉ።
4 304
🇸🇦⚡️🇾🇪 ሰበር ዜና፣ ሰበር ዜና፣ ሰበር ዜና፡- ሁቲዎች (አንሷሩላህ) በአየር መከላከያ መሳሪያቸው፣ የሳዑዲ ዓረቢያን F15 ተዋጊ አይሮፕላን መትተው መጣላቸውን ይፋ በማድረግ አረጋገጡ።
4 304
🇺🇸🇾🇪🇸🇦 የአሜሪካ ባለስልጣናት በሳምንቱ መጨረሻ በኦማን ከአንሷረላህ (ሁቲ) ልዑካን ጋር ተገናኝተው ነበር። በስብሰባው ወቅት ዩናይትድ ስቴትስ ለሳውዲ ወይም በሳዑዲ ለሚደገፉ ኃይሎች የአየር ድጋፍ እንደማታደርግ ወይም በሁቲ ቁጥጥር ሥር ባሉ ግዛቶች ላይ ጥቃት እንደማትሰነዝር ቃል ገብታለች።
በምላሹ፣ ሁቲዎች ባብ አል-ማንዳብን (ቀይ ባሕር) ለዓለም አቀፍ መርከብ ክፍት ሆኖ እንዲቆይ እንዲያደርጉ ጠይቃለች።
ሁቲዎች በበኩላቸው፣ ወሽመጡ ለዓለም አቀፍ መርከቦች ክፍት እንደሆነ ተናግረው፣ ለሳዑዲ ጭነቶች ክልክል እንደሆነ አስምረውበታል -- ሮይተርስ
4 304
🇷🇺🇯🇵⚡️ — ቶኪዮ በሩሲያ ፌዴሬሽን ላይ ቀጥተኛ ስጋት የሚፈጥሩ ተግባራትን ከቀጠለች፣ ሩሲያ አስፈላጊ እርምጃዎችን እንደምትወስድ አስጠንቅቃለች፣ ሲል የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ።
4 304
🇷🇺 ሩሲያ፣ የፅንስ ማስወረድ መጠን እያሽቆለቆለ ከሚገኝባቸው ሀገራት ቀዳሚ ሆናለች።
ባለፉት 15 ዓመታት፣ የፅንስ ማቋረጥ በ74 በመቶ ቀንሷል።
