የቀጠናው ተመልካች
Відкрити в Telegram
በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።
Показати більшеКраїна не вказанаКатегорія не вказана
4 316
Підписники
-824 години
-117 днів
-8230 днів
Архів дописів
4 316
🇷🇺🇺🇦⚡️ሩሲያ አፍሪካ ለምን መጣች? ምን ፈልጋለች? ኦፊሴላዊ የጉብኝቱን ምክኒያት እርሱት። እሱ ሽፋኑ ነው። ቅጥረኛ ተዋጊዎችን ፈልጋለች? ይህንን እንደ ምክኒያት ማንም ባያነሳውም፣ ምናልባት ቅጥረኞችን ፈልገዋል።
ቅጥረኛ በመቅጠር ዩክሬን ከሩሲያ በላይ ሄዳለች። በተለይ ከላቲን አሜሪካ፣ ከኮሎምቢያ፣ ብራዚል እና ቬኔዝዌላ በሺዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎች ከዩክሬን ጎን በገንዘብ ተቀጥረው ይዋጋሉ። የራሳቸው ብርጌድ፣ የራሳቸው ክፍለ ጦር እና መዋቅር ሁሉ አላቸው። ከአውሮፓ ሀገራትም፣ በተለይ ከምሥራቁ ክፍል፣ ብዙ ቅጥረኞች አሏት።
በነገራችን ላይ፣ ዩክሬን የራሷን ተዋጊ ዕድሜ ያላቸውን ወንዶች ጨርሳ ነው፣ በስፋት ወደ ቀጠራው የሄደችው። ገሚሱ ተሰዷል።
ሩሲያም በበኩሏ፣ ቅጥረኞችን አሰልፋ ትገኛለች፣ እንደ ዩክሬን የበዙ ባይሆንም፣ አሏት። በተለይ ከምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች የተመለመሉ በዩክሬን ጦር ሜዳዎች በመዋጋት ላይ ናቸው።
ጦርነቱ ከ25-35 ሺ ወታደሮችን በወር ከመጨረሱ ጋር፣ ምናልባት የዚህ የጉብኝቱ ውስጠ ወይራዊ ዓላማ፣ ተዋጊዎችን ፍለጋ ይሆናል።
አሁን ላይ፣ ሩሲያ ኢትዮጵያን በዚህ ጉዳይ የምትጠይቃት ከሆነ፣ በስልጣን ያለው መንግሥት ሐሳቡን በደስታ ሊቀበል አያቅማማም። ለምን ቢባል፣ መንግሥታት እንዲህ ያሉ ጦርነቶችን ያስቸገራቸውን ሕዝብ ለመጨረስ ይጠቀሙበታል (አርጀቲና Afro አርጀንቲናዊያንን ወይም ጥቁር አርጀንቲናዊያንን ያጠፋችበትን መንገድ ታሪክ፣ መለስ ብላችሁ አንብቡት። እንደ ፈረንጆች 2022 በWashington Post የወጣውን ጽሑፍ ብታነቡት እመክራለሁ።)
በተለይ የሰሜኑ ወጣት ተጠንቀቅ! የሩሲያና የዩክሬን ጦርነት መልኩን ለውጧል። የሚያልቅ አይመስልም። አሁን ላይ meat grinder ሲሉ ይጠሩታል ጦርነቱን። የሥጋ ወፍጮ ማለታቸው ነው። ሩሲያ ብላችሁ እንዳትቀልጡ!
*-
4 316
🇷🇺🇺🇦⚡️ቅጥረኛ ተዋጊዎችን ፈልገው ይሆን ተጨማሪ ከአፍሪካ ሀገራት? ይህንን እንደ ምክኒያት ማንም ባያነሳውም፣ ምናልባት ቅጥረኞችን ፈልገዋል።
ቅጥረኛ በመቅጠር ዩክሬን ከሩሲያ በላይ ሄዳለች። በተለይ ከላቲን አሜሪካ፣ ከኮሎምቢያና ብራዚል በሺዎች የሚቆጠሩ ተዋጊዎች ከዩክሬን ጎን በገንዘብ ተቀጥረው ይዋጋሉ። የራሳቸው ብርጌድ፣ ክለ ጦር እና መዋቅር ሁሉ አላቸው።
ሩሲያም በበኩሏ፣ ቅጥረኞችን አሰልፋ ትገኛለች፣ እንደ ዩክሬን የበዙ ባይሆንም አሉ። በተለይ ከምዕራብ አፍሪካ ሀገሮች የተመለመሉ በዩክሬን ጦር ሜዳዎች በመዋጋት ላይ ናቸው።
ጦርነቱ ከ25-35 ሺ ወታደሮችን በቀን ከመጨረሱ ጋር፣ ምናልባት ተዋጊዎችን ፈልጋ እንዳይሆን።
አሁን ላይ፣ ሩሲያ ኢትዮጵያን በዚህ ጉዳይ የምትጠይቃት ከሆነ፣ በስልጣን ያለው መንግሥት ሐሳቡን በደስታ ሊቀበል አያቅማማም። ለምን ቢባል፣ መንግሥታት እንዲህ ያሉ ጦርነቶችን ያስቸገራቸውን ሕዝብ ለመጨረስ ይጠቀሙበታል (አርጀቲና Afro አርጀንቲናዊያንን ወይም ጥቁር አርጀንቲናዊያንን ያጠፋችበትን መንገድ ታሪክ፣ መለስ ብላችሁ አንብቡት። እንደ ፈረንጆች 2022 በWashington Post የወጣውን ጽሑፍ ብታነቡት እመክራለሁ።)
በተለይ የሰሜኑ ወጣት፣ ዐማራው፣ ተጠንቀቅ! ጦርነቱ መልኩን ለውጧል። አሁን ላይ meat grinder ሲሉ ይጠሩታል ጦርነቱን። የሥጋ ወፍጮ ማለታቸው ነው። ሩሲያ ብላችሁ እንዳትቀልጡ!
4 316
🇷🇺 ሩሲያ ከአሁን በኋላ ምዕራባውያን ለመደራደር ፍላጎት አላቸው ብላ አታምንም። - ሰርጌ ላቭሮቭ።
የሩስያ ዲፕሎማሲ ኃላፊ፣ በአሁኑ ጊዜ፣ በአፍሪካ ሀገራት የሥራ ጉብኝት አካል በሆነችው ሞዛምቢክ፣ ጉብኝት ላይ ናቸው።
*-*-*-
4 316
⚡️🇮🇷🇺🇸 Axios: የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ ባለፉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ በኢራን ላይ የተደረገ ምንም ዓይነት ድብደባ የለም ብለዋል።
4 316
⚡️🇮🇱🇺🇸🇹🇷 የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ እና የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዛሬ አመሻሽ ላይ የስልክ ጥሪ ያደረጉ ሲሆን፣ በእስራኤል እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል በበርካታ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ የጠበቀ ቅንጅታቸውን ለመቀጠል ተስማምተዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ በቅርቡ አሜሪካ በባሕረ ሰላጤው ስላደረገችው እንቅስቃሴዎችም ለኔታንያሁ ገለጻ ሰጥቷል።
በውይይቱ ወቅት፣ የኔታንያሁ ጽህፈት ቤት፣ የቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋንን በእስራኤል ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የጥላቻ ንግግሮችና ትቢቱን በማንሳት፣ ደውሎ እንዲቆጣው ለፕሬዝዳንት ጥሪ አቅርቧል።
4 316
🇬🇷🇹🇷🇺🇸 የግሪክ ጠቅላይ ሚኒስቴር፡ ኪሪያኮስ ሚቶስታኪስ፡
እኛም እንደ እስራኤል አሜሪካ ለቱርክ F35 አይሮፕላኖችን እንዳትሸጥ የበኩላችንን ጥረት እናደርጋለን። ማንም ምንም አያመጣም።
4 316
🇮🇷🇺🇸⚡️ኢራን 10 ባለስቲክ ሚሳዬል ወደ ጆርዳን መተኮሷ አስደንጋጭ መባባስ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ሚሳዬሎቹ የተሸከሙት ተቀጣጣይ ፈንጅ ክብደት፣ ከዚህ በፊት ያላሳዩት ነው CNN
4 316
—❗️🇮🇷/🇮🇶 ኢራን፣ በሺ የሚቆጠሩ ልዩ ኃይሎቿን፣ በኢራን ኢራቅ/ኩርድ ድንበር ላይ ማሰለፏ ታውቋል።
የIRGC ኮማንደር እንደገለጸው፣ ኩርዶች በማንኛውም መንገድ ከአሜሪካና እስራኤል ጋር ተባብረው ትንኮሳ ቢያደርጉ፣ ግዛታቸው ድረስ በመግባት "የፀጥታ ዞን" እንደሚመሰርቱ ተናግሯል።
4 316
🇮🇷⚡️🇺🇸 በባግዳድ እና በጆርዳን አሜሪካ ጦር ሰፈሮች አቅራቢያ፣ የአደጋ ጊዜ ደውሎች ዋይ ዋይ እያሉ ናቸው።
በቁጥር ብዙ የኢራን ሚሳዬሎች ወደነዚህ ሥፍራዎች ተተኩሰዋል።
በጆርዳን የሚገኝ የአሜሪካ ፔትሪዮት አየር መቃወሚያ ሲስተም በቀጥታ ምት መውደሙን የሚያሳዩ ዘገባዎች እየወጡ ናቸው።
የኢራን ጦር ኃይሎች "ከፍተኛ የጦርነት ንቃተ-ሕሊና ውስጥ" እንዲሆኑ እና እንዲዘጋጁም ትዕዛዝ ወርዷል።
4 316
🇮🇷🇺🇸⚡️ይህ፣ ትናንት ኢራን መርከቦች ላይ ለፈፀመችው ጥቃት የተወሰደ አፀፋዊ እርምጃ ነው። የሚደገም ከሆነ፣ እርምጃችን የባሰ ይሆናል።
4 316
🇪🇹🇷🇺🇲🇱🇧🇯🇳🇪 የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ ሰርጌ ላቭሮቭ፣ ትናንትና ወደ ምዕራብ አፍሪካ እየተጓዘ ሳለ መንገድ ላይ ሽንቱ መጥቶበት አዲስ አበባ ወርዶ እንደነበር ሰምተናል።
እንደወረደም በቀጥታ፣ "ሽንት ቤቱን አሳዩኝ፣ የቱ ጋ ነው" ሲል እንደነበር ምንጮቼ ነግረውኛል።
ምሽት ላይ ስለነበር ያረፈው፣ እዚሁ እደር፣ ቡና ጠጣ፣ ራትም ብላና ነገ ትሄዳለህ ብለውት፣ በመነጋታው ተነስቶ ወደ ጉዳዩ እንደሄደ ነው የማውቀው።
ሰርጌ ላቭሮቭ፣ ከቡርኪና ፋሶ፣ ከኒጀር፣ ከማሊ እና ከሌሎች ሀገር መሪዎች ጋር መገናኘቱን እና ጉብኝቱ አሁንም ድረስ እንደቀጠለ መሆኑ ታውቋል።
*-*-*-
4 316
🇮🇷🇺🇸⚡️IRGC:
አታላይዋ አሜሪካ፣ በድጋሚ የገባችውን ቃል በመጣስ፣ በኢራን ደቡባዊ የባህር ዳርቻ አውራጃዎች በሚገኙ በርካታ ቦታዎች ላይ ጥቃት ሰንዝራለች።
🔺 በሌላ ፀረ-ሲቪል ድርጊቷም፣ በሀገሪቱ ምስራቃዊ አውራጃዎች ወደ ቅድስት ከተማ ማሽሃድ የሚወስዱ ሁለት ድልድዮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የሰነዘረች ሲሆን ይህም የሰማዕቱን መሪ የስንብት ሥነ ሥርዓት ለመሸፈን የተሞከረ ነበር።
🔺 እንደነዚህ ያሉት ወንጀሎች በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎችን የበለጠ እንደሚያነቃቁ እና "ከታላቁ ሰይጣን" ጋር በሚደረገው ትግል ውስጥ የበለጠ ሚና ለመጫወት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንደሚያጠናክር ሊገነዘቡ አልቻሉም።
🔺 የእስላማዊ ሪፐብሊክ ኢራን ተዋጊዎች፣ ሕጻናትን ለሚገድል የአሜሪካን ጦር ጥቃት፣ ምላሽ ሳይሰጥ አይተዉም!
4 316
🇮🇷🇺🇸⚡️አታላይዋ አሜሪካ፣ በድጋሚ የገባችውን ቃል በመጣስ፣ በኢራን ደቡባዊ የባህር ዳርቻ አውራጃዎች በሚገኙ በርካታ ቦታዎች ላይ ጥቃት ሰንዝራለች።
🔺 በሌላ ፀረ-ሲቪል ድርጊቷም፣ በሀገሪቱ ምስራቃዊ አውራጃዎች ወደ ቅድስት ከተማ ማሽሃድ የሚወስዱ ሁለት ድልድዮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የሰነዘረች ሲሆን ይህም የሰማዕቱን መሪ የስንብት ሥነ ሥርዓት ለመሸፈን የተሞከረ ነበር።
🔺 እንደነዚህ ያሉት ወንጀሎች በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎችን የበለጠ እንደሚያነቃቁ እና "ከታላቁ ሰይጣን" ጋር በሚደረገው ትግል ውስጥ የበለጠ ሚና ለመጫወት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንደሚያጠናክር ሊገነዘቡ አልቻሉም።
🔺 የእስላማዊ ሪፐብሊክ ኢራን ተዋጊዎች፣ ሕጻናትን ለሚገድል የአሜሪካን ጦር ጥቃት፣ ምላሽ ሳይሰጥ አይተዉም!
4 316
🇮🇷🇺🇸⚡️የኢራን የፖርላማ ቃል አቀባይ እና ዋና ተደራዳሪ፣ መሐመድ ባጋር ቃሊባፍ፡
አሜሪካ አሁንም ጉልበተኝነት እና ክህደት በነጻ እንደማይመጣ አልተገነዘበችም። ግልጽ ላድርግ፣ የዘራሃውን ታጭዳለህ። ጊዜያችሁን አታባክኑ፣ አለበለዚያ የበለጠ ጠልቃችሁ ትሰምጣላችሁ። የሆርሙዝ ወሽመጥ የሚከፈተው በአሜሪካ ዛቻ ሳይሆን በኢራን መስማማት ብቻ ነው።
4 316
የኢራን የፖርላማ ቃል አቀባይ እና ዋና ተደራዳሪ፣ መሐመድ ባጋር ቃሊባፍ፡
አሜሪካ አሁንም ጉልበተኝነት እና ክህደት በነጻ እንደማይመጣ አልተገነዘበችም። ግልጽ ላድርግ፣ የዘራሃውን ታጭዳለህ። ጊዜያችሁን አታባክኑ፣ አለበለዚያ የበለጠ ጠልቃችሁ ትሰምጣላችሁ። የሆርሙዝ ወሽመጥ የሚከፈተው በአሜሪካ ዛቻ ሳይሆን በኢራን መስማማት ብቻ ነው።
4 316
🇺🇸🇧🇭⚡️🇮🇷 በባሕሬን የአሜሪካ 5ኛ የባሕር ኃይል ጦር ሰፈር፣ በቀጥታ በወረደ የኢራን ሚሳዬሎች ምሽቱን ተመትቷል። ጭስ ከጦሩ ሰፈሩ ሲወጣ እየታየ ነው።
ኢራን ከዚህም በተጨማሪ፣ በጆርዳን እና በኩዌት በሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት እየሰነዘረች ነው።
4 316
🇺🇸❌🇮🇷 - ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ የምታደርገው ወታደራዊ ጥቃት እንደቀጠለ ሲሆን፣ ይህ የተኩስ አቁሙ ከታወጀ በኋላ የአሜሪካ ጦር በኢራን ላይ የፈፀመው ትልቁ እና ኃይለኛው ጥቃት ነው።
