uz
Feedback
የቀጠናው ተመልካች

የቀጠናው ተመልካች

Kanalga Telegram’da o‘tish

በአለማችን ቀጠናዎች የሚከሰቱ ክስተቶችን ይዘግባል፣ ሳይቀዘቅዝ በትኩሱ። ለጥያቄና ለአስተያየቶች በኢሜል asuleyma246@Gmail.com ብላችሁ ፃፉልኝ።

Ko'proq ko'rsatish
Mamlakat belgilanmaganToif belgilanmagan
4 318
Obunachilar
-824 soatlar
-117 kun
-8230 kun
Postlar arxiv
🇮🇷🇺🇸⚡️IRGC: አታላይዋ አሜሪካ፣ በድጋሚ የገባችውን ቃል በመጣስ፣ በኢራን ደቡባዊ የባህር ዳርቻ አውራጃዎች በሚገኙ በርካታ ቦታዎች ላይ ጥቃት ሰንዝራለች። 🔺 በሌላ ፀረ-ሲቪል ድርጊቷም፣
🇮🇷🇺🇸⚡️IRGC: አታላይዋ አሜሪካ፣ በድጋሚ የገባችውን ቃል በመጣስ፣ በኢራን ደቡባዊ የባህር ዳርቻ አውራጃዎች በሚገኙ በርካታ ቦታዎች ላይ ጥቃት ሰንዝራለች። 🔺 በሌላ ፀረ-ሲቪል ድርጊቷም፣ በሀገሪቱ ምስራቃዊ አውራጃዎች ወደ ቅድስት ከተማ ማሽሃድ የሚወስዱ ሁለት ድልድዮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የሰነዘረች ሲሆን ይህም የሰማዕቱን መሪ የስንብት ሥነ ሥርዓት ለመሸፈን የተሞከረ ነበር። 🔺 እንደነዚህ ያሉት ወንጀሎች በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎችን የበለጠ እንደሚያነቃቁ እና "ከታላቁ ሰይጣን" ጋር በሚደረገው ትግል ውስጥ የበለጠ ሚና ለመጫወት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንደሚያጠናክር ሊገነዘቡ አልቻሉም። 🔺 የእስላማዊ ሪፐብሊክ ኢራን ተዋጊዎች፣ ሕጻናትን ለሚገድል የአሜሪካን ጦር ጥቃት፣ ምላሽ ሳይሰጥ አይተዉም!

🇮🇷🇺🇸⚡️አታላይዋ አሜሪካ፣ በድጋሚ የገባችውን ቃል በመጣስ፣ በኢራን ደቡባዊ የባህር ዳርቻ አውራጃዎች በሚገኙ በርካታ ቦታዎች ላይ ጥቃት ሰንዝራለች። 🔺 በሌላ ፀረ-ሲቪል ድርጊቷም፣ በሀገሪቱ
🇮🇷🇺🇸⚡️አታላይዋ አሜሪካ፣ በድጋሚ የገባችውን ቃል በመጣስ፣ በኢራን ደቡባዊ የባህር ዳርቻ አውራጃዎች በሚገኙ በርካታ ቦታዎች ላይ ጥቃት ሰንዝራለች። 🔺 በሌላ ፀረ-ሲቪል ድርጊቷም፣ በሀገሪቱ ምስራቃዊ አውራጃዎች ወደ ቅድስት ከተማ ማሽሃድ የሚወስዱ ሁለት ድልድዮች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የሰነዘረች ሲሆን ይህም የሰማዕቱን መሪ የስንብት ሥነ ሥርዓት ለመሸፈን የተሞከረ ነበር። 🔺 እንደነዚህ ያሉት ወንጀሎች በዓለም ዙሪያ ያሉ ሰዎችን የበለጠ እንደሚያነቃቁ እና "ከታላቁ ሰይጣን" ጋር በሚደረገው ትግል ውስጥ የበለጠ ሚና ለመጫወት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንደሚያጠናክር ሊገነዘቡ አልቻሉም። 🔺 የእስላማዊ ሪፐብሊክ ኢራን ተዋጊዎች፣ ሕጻናትን ለሚገድል የአሜሪካን ጦር ጥቃት፣ ምላሽ ሳይሰጥ አይተዉም!

🇮🇷🇺🇸⚡️የኢራን የፖርላማ ቃል አቀባይ እና ዋና ተደራዳሪ፣ መሐመድ ባጋር ቃሊባፍ፡ አሜሪካ አሁንም ጉልበተኝነት እና ክህደት በነጻ እንደማይመጣ አልተገነዘበችም። ግልጽ ላድርግ፣ የዘራሃውን ታጭ
🇮🇷🇺🇸⚡️የኢራን የፖርላማ ቃል አቀባይ እና ዋና ተደራዳሪ፣ መሐመድ ባጋር ቃሊባፍ፡
አሜሪካ አሁንም ጉልበተኝነት እና ክህደት በነጻ እንደማይመጣ አልተገነዘበችም። ግልጽ ላድርግ፣ የዘራሃውን ታጭዳለህ። ጊዜያችሁን አታባክኑ፣ አለበለዚያ የበለጠ ጠልቃችሁ ትሰምጣላችሁ። የሆርሙዝ ወሽመጥ የሚከፈተው በአሜሪካ ዛቻ ሳይሆን በኢራን መስማማት ብቻ ነው።

የኢራን የፖርላማ ቃል አቀባይ እና ዋና ተደራዳሪ፣ መሐመድ ባጋር ቃሊባፍ፡ አሜሪካ አሁንም ጉልበተኝነት እና ክህደት በነጻ እንደማይመጣ አልተገነዘበችም። ግልጽ ላድርግ፣ የዘራሃውን ታጭዳለህ። ጊዜያችሁ
የኢራን የፖርላማ ቃል አቀባይ እና ዋና ተደራዳሪ፣ መሐመድ ባጋር ቃሊባፍ፡
አሜሪካ አሁንም ጉልበተኝነት እና ክህደት በነጻ እንደማይመጣ አልተገነዘበችም። ግልጽ ላድርግ፣ የዘራሃውን ታጭዳለህ። ጊዜያችሁን አታባክኑ፣ አለበለዚያ የበለጠ ጠልቃችሁ ትሰምጣላችሁ። የሆርሙዝ ወሽመጥ የሚከፈተው በአሜሪካ ዛቻ ሳይሆን በኢራን መስማማት ብቻ ነው።

+1
🇺🇸🇧🇭⚡️🇮🇷 በባሕሬን የአሜሪካ 5ኛ የባሕር ኃይል ጦር ሰፈር፣ በቀጥታ በወረደ የኢራን ሚሳዬሎች ምሽቱን ተመትቷል። ጭስ ከጦሩ ሰፈሩ ሲወጣ እየታየ ነው። ኢራን ከዚህም በተጨማሪ፣ በጆርዳን እና በኩዌት በሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች ላይ ጥቃት እየሰነዘረች ነው።

Repost from Press TV
🔴 Powerful explosions rock US Fifth Fleet headquarters in Bahrain @PressTV
🔴 Powerful explosions rock US Fifth Fleet headquarters in Bahrain @PressTV

🇺🇸❌🇮🇷 - ዩናይትድ ስቴትስ በኢራን ላይ የምታደርገው ወታደራዊ ጥቃት እንደቀጠለ ሲሆን፣ ይህ የተኩስ አቁሙ ከታወጀ በኋላ የአሜሪካ ጦር በኢራን ላይ የፈፀመው ትልቁ እና ኃይለኛው ጥቃት ነው።

⚡️🇮🇷🇺🇸🇧🇭 አል አረቢያ: ባሕሬን በዛሬ ምሽቱ የኢራን ድብደባ ላይ፣ ከአሜሪካ ጋር በአንድነት ተሳትፋለች።

🇮🇱🇺🇸🇹🇷⚡️ - የእስራኤል የገንዘብ ሚኒስትር ቤዛሌል ስሞትሪች -
ኤርዶጋን በጣም አደገኛ ሰው ነው። ቱርክ ዛሬ ባለችው ሁኔታ ለእስራኤል መንግስት ትልቅ ስጋት ነች። ከፕሬዚዳንት ትራምፕ እና ከአስተዳደሩ ጋር በጣም የተጠናከረ ውይይቶችን እያደረግን ነው፣ እና F-35ን ለቱርክ እንዳይሸጥ ለመከላከል በአደባባይም ሆነ ከትዕይንቱ በስተጀርባ ጠንክረን እየሰራን ነው። ኤርዶጋንም ሆነች ቱርክ፣ ጨዋታን የሚቀይሩ መሳሪያዎችን ማግኘት የለባቸውም።

🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር ዜና፡ የኃይል ማመንጫዎችን ጨምሮ፣ ቡሸር የኒውክሊየር ማብላሊያ ጣቢያ በአሜሪካ ጥቃት እንደደረሰባቸው መረጃዎች እየወጡ ነው። የኃይል መቆራረጥ በተለያዩ ቦታዎች መከሰታቸው ተነግሯል።  እንደሚባለው እውነት ከሆነ፣ ይሄ መባባስ እጅግ ከፍተኛና አደገኛ ነው።

🇮🇷⚡️🇺🇸 ሰበር ዜና፡ የኃይል ማመንጫዎችን ጨምሮ፣ ቡሸር የኒውክሊየር ማብላሊያ ጣቢያ በአሜሪካ ጥቃት እንደደረሰባቸው መረጃዎች እየወጡ ነው። የኃይል መቆራረጥ በተለያዩ ቦታዎች መከሰታቸው ተነግሯል። እንደሚባለው እውነት ከሆነ፣ ይሄ መባባስ እጅግ ከፍተኛና አደገኛ ነው።

🇮🇱🇺🇸❌🇮🇷 - የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ - ትራምፕ ኢራናውያን እያጭበረበሩ እና ይህን ሂደት እየጎተቱ እንደሆነ ያውቃሉ። ይህንንም ይናገራል። ለማንኛውም ሁኔታ ዝግጁ
🇮🇱🇺🇸❌🇮🇷 - የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ -
ትራምፕ ኢራናውያን እያጭበረበሩ እና ይህን ሂደት እየጎተቱ እንደሆነ ያውቃሉ። ይህንንም ይናገራል። ለማንኛውም ሁኔታ ዝግጁ ነን።
ይቅርታ የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስቴር፣ አርፈው ይቀመጡ! የእርሶ ተሳትፎ እዚህ ውስጥ አያስፈልግም። የእስራኤል መግባት፣ ከማባባስ ውጭ መፍትሄ አያመጣም።

🇺🇸🇮🇷| አሜሪካ፣ ኢራን የሆርሞዝ ወሽመጥን ከመቆጣጠር አቅም ጋር የተያያዙ ወታደራዊ ኢላማዎቿን እያጠቃው ነው ብላለች።
🇺🇸🇮🇷| አሜሪካ፣ ኢራን የሆርሞዝ ወሽመጥን ከመቆጣጠር አቅም ጋር የተያያዙ ወታደራዊ ኢላማዎቿን እያጠቃው ነው ብላለች።

🇮🇷⚡️🇺🇸 በኢራን ላይ የተጠበቀው የአሜሪካ ወታደራዊ ጥቃት፣ አሁን ተጀምሯል። ደቡብ ኢራን ያሉ ወታደራዊ ዒላማዎች እና ሲሪክ፣ ካሽም እንዲሁም ባንዳር አባስ ደሴቶች በአሁኑ ሰዓት በአሜሪካ ወታደራዊ ጥቃት ሥር ናቸው። ምናልባት አሜሪካ ኢራን ቀብር ላይ ስላለች፣ አጸፋዋ እምብዛም ነው ብላ አስባ ይሆናል። በሌላ መልኩ፣ ኢራን በቀጠናው ያሉ አረብ ሀገሮችን፣ በምንም መልኩ ለአሜሪካ ጦር ማስወንጨፊያነት የምታገለግሉ ከሆነ፣ አጸፋዋን በእነሱ ላይ እንደምታደርግ አስጠንቅቃለች። እስራኤል በበኩሏ፣ አጋጣሚውን ተጠቅማ ለመግባት ብትቋምጥም፣ ለአሁን ዳር ናት።

Repost from Sputnik Africa
+3
Rosatom Begins Manufacturing Fourth Reactor Vessel for Egypt's El Dabaa Nuclear Plant ⚛️ The first metal blanks—weighing over 65 tonnes — have arrived for the fourth VVER-1200 reactor. These massive pieces will be machined to precise specifications and coated with anti-corrosion cladding to ensure decades of durability. 🇷🇺🤝🇪🇬 Rosatom has already delivered reactor vessels for Units 1 and 2. Production is now underway for: ⚡️Unit 3 reactor vessel; ⚡️12 steam generators for Units 2–4; ⚡️other key nuclear island equipment. ⚛️ The manufacturing involves Rosatom's plants across Russia — in St. Petersburg, Moscow, Rostov, and Karelia. Subscribe to @sputnik_africa 🔸 Sputnik Africa | X 🔸

🇷🇺🇺🇦 ፑቲን ከዘለንስኪ ጋር ከሞስኮ ውጭ ለመገናኘት የፈራው ለምንድነው? 'ሩሲያ መነጋገር ትፈልጋለች' ካለ፣ ለምን ገለልተኛ ሀገር ከዘለንስኪ ጋር አይገናኝም? ምን አስፈራው? ይሄ ግትርነት የዥል አይደለም ወይ? ሁሉን ትቶ በሙሉ ልብ ቆርጦለት አልተዋጋ፣ ወይ አልተነጋገረ፣ ምንድነው ዓላማው? እስከ አሁን በወር 35ሺ ወታደሩን እያስጨረሰ፣ የምድር ሲዖሉን፣ 'ጦርነት' ብሎ መጥራት የማይፈልግ ሰው ነው ፑቲን። ሩሲያ ውስጥ ሁኔታውን 'ጦርነት' ብለህ ከዘገብክ፣ ትታሰራለህ። SMO ነው የሚባለው፣ Special Military Operation. 'War' ማለት ጉላግ ያስልካል። እንደ ፀረ ሽብር አነስተኛ ዘመቻ፣ ልዩ የፖሊስ ዘመቻ እንጂ ወይም እኛ ሀገር 'ግጭት' እንደሚሉት፣ 'ጦርነት' 'War' አይባልም። እንግዲህ ይህን 'ጦርነት' ብሎ ለመጥራት ጉሮሮውን የሚያንቀው ሰው ነው፣ ሩሲያን በዚህ ጦርነት እየመራ ለዚህ ያደረሰው። ምክኒያቱ ምንም ይሁን ምንም፣ ይሄ አጉል ጉራ እና የዥል ግትርነት ሽንፈትን ያመጣል እንጂ የትም አያደርሰም። ለሰላም ድርድር ያድርግ አይደለም እያልኩኝ ያለሁት። ማድረግም አይጠበቅበትም። ጉዳዩን በጦርነት ብቻና ብቻ ነው የምፈታው፣ 'ከናዚና' ከሽብርተኛ ጋር ድርድር አይሆንም፣ ፖሊሲያችንም አይደለም፣ ካለ መብቱ ነው። በውጊያ በኪየቭ ያለውን መንግሥት አንበረክካለሁ፣ ማለት ይችላል። አቅሙም አለው። ነገር ግን፣ 'ሩሲያ ለሰላም ድርድር ዝግጁ ናት፣ ጦርነቱን በድርድር ማቆም እንፈልጋለን' ካለ፣ አለቀ! የትም ይሁን፣ ሁለቱ ሀገሮች በሚስማሙበት፣ ቻይናም ይሁን፣ መደራደር ነው፣ መነጋገር ነው። 'አይ፣ ሞስኮ ካልሆነ ሞቼ እገኛለሁ' ካለ ግን፣ ሌላ ነገር ነው። በዚህ መሃል፣ በእሱ ግራ በገባውና በማይታወቅ ምክኒያቱ፣ ሩሲያ ደማች። ተመልከቱ አሜሪካን፣ ስዊዘርላንድ ሄዳ ከኢራን ጋር ተደራደረች። በጉራ መነፋት እና በትዕቢት እምቢ ማለት ቢኖርባት፣ ያለባት አሜሪካ ነበረች። ባለፈው እንዳልኩት፣ የአውሮፓዊያን ጦርነቱን ለመጨረስ ያለመፈለግ ዝንባሌ እንዳለ ሆኖ፣ የፑቲንም ውሳኔ ለመወሰን ያለመቻል ተደምሮበት፣ ጦርነቱን ለሩሲያ ሲዖል እያመጣባት ነው።

🇺🇸🇺🇦🇷🇺 - ዘሌንስኪ እና ትራምፕ ዛሬ በአንካራ ተገናኝተዋል፣ ከፕረሱ ጋር ከተደረገው ንግግር ትንሹ ክሊፕ ይኸውና። ትራምፕ፡
ፑቲንን ካነጋገርኩት ነገሮች አንዱ፣ 'የት መገናኘት ትፈልጋለህ?' የሚል ነበር። እናም 'በሐሳብ ደረጃ በሞስኮ' አለኝ። 'በሞስኮ አትገናኝም፣ እሱ የማይቻል ነገር ነው' አልኩት። … ወደ ሞስኮ ትሄዳለህ ዘለንስኪ?
ዘለንስኪ፡
ከባድ ነው። እዚያ ብዙ የዩክሬን ድሮኖች አሉ።

🇮🇷⚡️🇺🇸 ኢራናዊያን፣ 'መንግሥታችን ምን እያደረገ ነው? ለተሰነዘረብን ጥቃት አፀፋው ለምን አነሰ? ሚሳዬሎቻችን እና ድሮኖቻችን የት አሉ? አሜሪካ በግልፁ ዛሬ፣ ነገ፣ ምሽቱን … እደበድባችኋለሁ እያለች በምታውጅበት፣ የእኛ መቀመጥ ከምን የመጣ ነው? የጦሩ ምላሽ የት ነው? እያሉ እየጠየቁ ናቸው። በኢራናዊያን ዘንድ ከፍተኛ ሕዝባዊ ብስጭት ይስተዋላል። አስታውሱ፡ አብዛኛው የኢራን ሕዝብ የተኩስ አቁም መግባቢያ ስምምነቱን በከፍተኛ ደረጃ የተቃወመ ነው። 'የተረገመ' ሲሉ ይጠሩታል መግባቢያ ሰነዱን። ተፈረመ በተባለ ምሽት እና ተከታታይ ቀናቶች፣ ሰልፎችና ከፀጥታ አካላት ጋር ግጭቶች ነበሩ። ተደራዳሪዎቹን፣ በተለይም ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ሰይድ አባስ አራጋቺን እና የፖርላማ ቃል አቀባዩን መሐመድ ባጋር ጋሊባፍን ከሃዲዎች፣ ሀገር ሻጮች፣ ይያዙ፣ ይሰቀሉ እስከማለት ተደርሶ ነበር።

🇮🇷⚡️🇺🇸 ትራምፕ፡ ኢራንን፣ ትናንት እንደመታናት፣ ዛሬ ማታም በደንብ እንመታታለን ብዬ እጠብቃለሁ። የተማሩት ነገር ያለ አይመስለኝም፣ አሁንም እዚያው የጥፋት ሥራቸው ላይ ናቸው። ለ47 ዓመታት የአካባቢው ጉልቤ ሆነው ቆይተዋል። ይቅርታ፣ ይሄ አይቀጥልም ከአሁን በኋላ።

🇺🇸⚡️ የጃፓን እስላማዊ ሪፐብሊክ በጦር መርከባችን ላይ ሚሳዬል ተኩሳለች (አጠፋው ይሰጣል) ።